ወታደራዊ ድሮኖች እና እያደገ የመጣው ግልጋሎታቸው
===================
ባለንበት ዘመን በድሮኖች አማካኝነት ስለሚከወን ጥቃት መስማት የተለመደ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ሆኖም የዛሬ 20 ዓመት ገደማ በወርሀ መስከረም የኒው ዮርክ መንትያ ህንፃዎች ላይ ከደረሰው ጥቃት ከአንድ ወር በኋላ ነበር አንድ የአሜሪካን አየር ኃይል አብራሪ ዘመናዊ ድሮንን ተጠቅሞ የግድያ ጥቃትን በመሰንዘር የመጀመሪያው ሰው የሆነው፡፡ ከዚህ በኋላ ግን በርካታ ርቀው ባሉ አብራሪዎች የሚንቀሳቀሱ አውሮፕላኖች (RPA) ተመራጭ የውጊያ መሳርያ ወደመሆን ተሸጋግረዋል፡፡ አሜሪካን እንኳን እንደምሳሌ ወስደን ብናይ ከአውሮፓውያኑ 2015 በኋላ በአፍጋኒስታን ውስጥ ብቻ ከ14 ሺህ በላይ የድሮን ጥቃቶችን አድርሳለች፡፡
ይህ መንግስታት በወታደራዊ ድሮኖች ላይ እያሳዩት የመጡት ከፍተኛ ፍላጎት ታድያ ሦስት አባይት ውጤቶችን አስከትሏል፡፡ የመጀመሪያው በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የወታደራዊ ድሮኖች ስርጭት መጨመሩ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ብዙዎቹ የዓለማችን ታላላቅ ብሎም በየአካባቢያቸው ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑት ሀገራት ድሮኖችን ለስለላና የአየር ላይ ምልከታ (ISR) አልያም ጥቃትን ለመሰንዘር እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ፡፡ ሁለተኛው ውጤት የመጀመሪያውን ተከትሎ የሚመጣ ነው፤ የድሮኖች መብዛትን ተከትሎ እነርሱን ማብረር እንዲችል ተደርጎ የሰለጠነ ወታደር የማፍራት ጉዳይ፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ድሮኖቹ በይበልጥ መሳርያን እየታጠቁ መምጣታቸው ነው፡፡
ምንም እንኳን ዘመናዊ ድሮኖችን ተጠቅሞ ጥቃት መሰንዘር ከተጀመረ ገና 20 ዓመታት ባያልፉትም ወታደራዊ ድሮኖች ግን የዘመኑ አዲስ ግኝቶች አይደሉም፡፡ እንዲያውም አውሮፕላን ከተፈጠረ ብዙም ሳይቆዩ ነው ድሮኖችም ገና በጠዋቱ በ1920 እና 30ዎቹ (እ.አ.አ) ከርቀት ሆኖ ጥቃትን ለመሰንዘር በማሰብ ወደ መድረኩ ብቅ ያሉት፡፡ ለምሳሌ ሚሳኤሎችም በሰው እየተመሩ ወደ ተልዕኮዋቸው የሚያመሩ ሲሆኑ ነገር ግን ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም የሚሰጡና ምንም አይነት ስለላን የማከናወን ብቃት የሌላቸው ናቸው፡፡ ሆኖም ዘመናዊ ወታደራዊ ድሮኖችን ለየት ከሚያደርጓቸው ውስጥ በመጀመሪያ አብራሪዎቻቸው ከደህንነት ከጥቃት የተጠበቁ መሆናቸው ነው፡፡ ሌላው እነዚህ ዘመናዊ ድሮኖች ኢላማቸውን ጠብቀው ጥቃት መሰንዘር የሚችሉ ስለሆኑ እንደ ሚሳኤል ካሉት አንፃር ጥቃት በሚፈፀምበት ቦታ ላይ አላስፈላጊ ተያያዥ ጉዳቶችን በተሻለ ያስቀራሉ፡፡ በተጨማሪም ለወታደሮቹ እና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎቹ ያለማቋረጥ መረጃን ይሰጣሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ድሮኖችን አስመልክቶ ከፍተኛ የሆነ የተሳሳተ ግንዛቤ ይታያል፤ በተለይም ድሮኖቹ እንዴት ይንቀሳቀሳሉ በሚለውና በአብራሪዎቹ ላይ፡፡ ድሮኖች የሚበሩት እነርሱን ለማብረር በማሰብ ተመልምለው በሰለጠኑ ወታደሮች አማካኝነት ነው፡፡ ታድያ እነዚህ አብራሪዎች እንደ ማንኛውም የአውሮፕላን አብራሪ ሁሉ ለሚከውኗቸው ተግባራት ኃላፊነትና ተጠያቂነት ቢኖርባቸውም በማህበረሰብም ሆነ በሌሎች ወታደሮች ዘንድ ግን በመልካም አይታዩም፡፡ ለምሳሌ ድሮኖችን ማብረር የቪዲዮ ጌሞችን ከመጫወት ጋር በማያያዝ የሚቀለድ ሲሆን አብራሪዎቹም ቢሆን ከሌሎች የአውሮፕላን አብራሪዎች አንፃር የስራ እድልን ሲከለከሉ ይታያል፡፡ ይህም የድሮን አብራሪዎች እጥረትን አስከትሏል፡፡ በሌላ መልኩ የድሮን አብራሪዎች ከአንድ አደጋ በኋላ የሚከሰት የጭንቀት በሽታ (Post traumatic stress disorder) ምልክት ቢታይባቸውም በወታደራዊ ተቋማቱ ጭምር የምር ተወስዶላቸው ህክምና ሲያገኙ አይስተዋልም፡፡
በሌላ መልኩ ጥቃት በሚፈፅሙበት ጊዜ ተያይዘው የተከሰቱ የንፁሀን ሞት በማህበረሰብ ዘንድ በመጥፎ እንዳይታዩ አድርጓቸዋል፡፡
ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-09-legacy-drone-warfare-view-military.html

Tech Xplore
9/11's legacy of drone warfare has changed how we view the military
In October 2001, nearly one month after the September 11 attacks on the World Trade Center, a US Air Force pilot made history as the first person to conduct a lethal strike with a modern drone—the Predator.
የወደፊቱን የመጓጓዣ ዘርፍ ይቀይራል የተባለለት ሀይፐርሉፕ
*******************************
ሀይፐርሉፕ የወደፊቱን የሰዎችና የእቃ ማጓጓዣ ስርዓት በእጅጉ ይለውጠዋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ በሰዓት 1200 ኪሎሜትሮችን መምዘግዘግ ይችላል የተባለለት ይህ ቴክኖሎጂ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ የዘርፉ ምሁራን በያዝነው የፈረንጆቹ መስከረም 14- 16 ምክክር ይደረግበታል ተብሏል፡፡
ሀይፐርሉፕ የተሰኘው የመጓጓዣ ቴክኖሎጂ ሰዎችና የተለያዩ ቁሶች ዙሪያውን ዝግ በሆነ እንደ ሳጥን ባለ ነገር (capsule) ውስጥ ሆነው በከፍኛ ፍጥነት በቶቦ ውስጥ ከቦታ ቦታ እንዲጓዙ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ከመደበኛ ባቡሮች በተቃራኒ ፉርጎዎችን የማይጠቀም ሲሆን በወና ውስጥ በመግነጢሳዊ ሀይል በመታገዝ የሚንቀሳቀስ ነው፡፡ ይህ ባቡር መሰል መጓጓዣ ለመንቀሳቀስም ሆነ ለመቆም መግነጢሳዊ ሀይልን ይጠቀማል፡፡ መግነጢሳዊ ሀይሉ የፍትጊያ ሀይልን በመቀነስ ሀይፐርሉፑ በከፍተና ፍጥነት እንዲጓዝ ያስችለዋል፡፡
የመጀመሪያው ቨርጂን ሀይፐርሉፕ የተሰኘው መጓጓዣ በላስቬጋስ በረሃማ ስፍራ መንገደኞችን በማሳፈር የተሳካ ሙከራ ማካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ይህ ከሳይንስ ፊክሽን እንኳን ላቅ ያለ ቴክኖሎጂ በቅርብ እውን የመሆን እድል እንዳለው እየተነገረ ነው፡፡ ሀይፐርሉፕ በጣም ዝቅተኛ የሆነ የካርቦን ተጽዕኖ ያለው መሆኑ እውን የመሆኑን ተስፋ ከፍ አድርጎታል፡፡
ይህ ዘመናዊ መጓጓዣ በሰፊው ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት ተመራማሪዎች አንዳንድ መመለስ ያለባቸው ጥያቄዎች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አዲሱን ቴክኖሎጂ አሁን ላይ ጥቅም እየሰጡ ካሉት የመጓጓዣ ቴክኖሎጂዎች ጋር እንዴት ማቀናጀት ይቻላል፣ አለማቀፍ የሆነ መሰረተ ልማት እንዴት መስራት ይቻላል እና የቴክኖሎጂውን ማህበራዊ ጥቅም እንዴት ማሳደግ ይቻላል የሚሉ መሰረታዊ ጥያቄዎች ይገኙበታል፡፡
ይህንን የተመለከተው ውይይት የፊታችን መስከረም 16 በፍራንክፈርት የሚካሄድ ሲሆን በኮንፈረንሱም አለማቀፍ የሆኑና በጉዳዩ ዙሪያ የሚሰሩ የትራንስፖርት ድርጅቶች፣ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች እና ሌሎች አምራቾች ይሳተፋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ ሁለት አጀንዳዎች የተቀረጹ ሲሆን እነዚህም ቴክኖሎጂው መንገደኞችን ለማጓጓዝ የሚገጥመውን ተግዳሮትና ከእቃ ማጓጓዝ ጋር ሊኖር የሚችለውን ችግር የተመለከቱ ናቸው፡፡
ከተሳታፊ ድርጅቶች መካከል ዋና ዋና የሚባሉት የቱቦ አምራቾች፣ የቫኪዩም ቴክኖሎጂ አምራቾች እና ከሀይፐርሎፕ ቴክኖሎጂ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ተቋማት ቴክኖሎጂውን በማበልጸግ ረገድ የደረሱበትን ደረጃ ያቀርባሉም ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
ባለፈው አመት ህዳር ወር ላይ በዲጂታል አማካኝነት ውይይት የተካሄደ ሲሆን የዘንድሮው ሁሉንም ባለድርሻዎች ፊት ለፊት የሚያገናኝ ይሆናል፡፡
ምንጭ Cities today
ለተጨማሪ ንባብ https://cities-today.com/.../hyperloop-tube-mail-traffic/...

Cities Today
Hyperloop: When tube mail becomes traffic - Cities Today
Promising speeds of 1,200 kilometres an hour and more efficient services with fewer...
ኤልሳልቫዶር ቢትኮይንን ህጋዊ መገበያያ ማድረጓ መነጋገሪያ ሆኗል
=======================
አለም የቢትኮይን ጥቅምና ጉዳት ላይ ገና ክርክሩን ጨርሶ ባላጠናቀቀበት ሁኔታ ኤልሳልቫዶር ቢትኮይንን ህጋዊ መገበያያ አድርጋ መወሰኗ አስገራሚ ሆኗል፡፡ ከትናትና ዕለት አንስቶ የንግድ ልውውጦችና ክፍያዎች በዲጂታል ገንዘብ እንዲሆን እያስገደደ ያለው የሃገሪቱ መንግስት ዜጎች የቢትኮይን ዲጂታል ዋሌት መተግበሪያ እንዲያወርዱና በምትኩ 30 ዶላር ዋጋ እንዲከፍሉ የሚያዝ መመሪያ አስቀምጧል፡፡
በሰኔ ወር መጀመሪያ ቢትኮይንን ህጋዊ መገበያያ ለማድረግ የሚያስችል አወዛጋቢ የህግ ረቂቅ ያሳለፈችው ሃገሪቱ ከመስከረም 7 ጀምሮ ደግሞ ህጉ የሚፀናበት ቀን እንደሚሆን አስቀምጣ ነበር፡፡ በዚህ መሰረት ከትላንት ጀምሮ ስራ ላይ የሚውለው ይህ መመሪያ 4 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ያላትን ኤልሳልቫዶር ቢትኮይንን ህጋዊ መገበያያ ያደረገች ብቸኛ ሀገር ያደርጋታል፡፡
ህጉ ውሳኔ ከተላለፈበት በኋላ የሃገሪቱ ዜጎች በቀላሉ የንግድ ልውውጥ ለማድረግ እንዲመቻቸው የቢትኮይን ሳንቲምን ወደ ዶላር የሚቀይሩ 200 የኤት ኤ ኤም ማሽኖችን ያስገጠመው የሃገሪቱ መንግስት በመደበኛው ገንዘብ ሲተመን 21 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ 400 የቢትኮይን ዲጂታል ገንዘብ ከአለም አቀፍ ገበያው እንደገዛም ተዘግቧል፡፡ የኤልሳልቫዶር ፕሬዝዳንት ናይብ ቡኬሌ ቢትኮይንን የሃገሪቱ መገበያያ የማድረጉ ውሳኔ በረሚታንስ የኢኮኖሚ ዘርፉ ላይ ትልቅ መሻሻሎችን እንደሚያመጣ ቢናገሩም በውሳኔው ላይ አስተያየት የተጠየቁ ብዙ የሃገሪቱ ዜጎች ቢትኮይንን ህጋዊ መገበያያ የማድረጉ እርምጃ ግራ ኣጋቢ እንደሆነባቸው እንስተዋል፡፡
አወዛጋቢ በሆነው የቢትኮይን ገበያ ብዙ የአለም መንገስታት ዲጂታል ገንዘቡን ለማስተዳደር የሚያስችሉ ማዕቀቦችን እና ልዩ አሰራሮችን እያበጁ ቢሆንም በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ መንግስታት ደግሞ ይህን የዲጂታል ገንዘብ እንደ ህጋዊ መገበያያ ለማድረግ መወሰናቸው ክርክሮችን እያስነሳ ይገኛል፡፡ እንደ ቻይና ያሉ ሀገራት የቢትኮይን ገበያ ቁጥጥር ውስጥ ለማድረግ እየሰሩ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የኤልሳልቫዶርን ውሳኔ ተከትለው ቢትኮይንን ህጋዊ መገበያያ ለማድረግ እየጣሩ ያሉት ፓራጓይ እና ኩባ በአለም አቀፍ መድረክ ትልቅ መነጋገሪያ አድርጓቸዋል፡፡
https://www.cnbc.com/2021/09/07/el-salvador-buys-400-bitcoin-ahead-of-law-making-it-legal-currency.html

CNBC
El Salvador bought $21 million of bitcoin as it becomes first country to make it a legal currency
El Salvador's bitcoin law, which was passed in June, took effect on Tuesday, making the world's most popular cryptocurrency legal tender.
የሩሲያ ተመራማሪዎች ይዘውት የመጡት አዲስ የካንሰር ህክምና ስልት
========================
በሩሲያው የቶምስክ ፖሊቴኒክ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ እንዲሁም ሌሎች ሩሲያውያን ተመራማሪዎች አክቲኒየም-225 በመጠቀም በ40 በመቶ የበለጠ ውጤታማ የሆነ የካንሰር ህክምናን አስተዋወቁ፡፡ እንደ ተመራማሪዎቹ ከሆነ ለአክቲኒየሙ ልዩ የሆነ የናኖ ማሸግያ በማዘጋጀት ከ6 እስከ 10 እጥፍ በላቀ የሰውነት አካልን ከመርዛማ ዲግሬድ ያደረጉ ንጥረ ነገሮች (degradation products) የመጠበቅ አቅም አለው፡፡
አክቲኒየም-225 መጀመሪያ የዩራኒየም-233 ዲግሬድ ያደረገ ንጥረ ነገር ሆኖ የተገኘ የራዲዮአክቲቭ አይዞቶፕ ነው፡፡ የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች እንደሚሉትም ይህ ዲግሬድ ያደረገ ንጥረ ነገር ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱትን ጨምሮ የተለያዩ አይነት ካንሰሮችን ለማከም ሊውል የሚችል የህክምና ራዲዮኮምፓውንድ (ራዲዮፋርማቱቲካል) ነው፡፡
ይህ በተለይም አክቲኒየም አልፋ ፓርቲክሎችን ስለሚለቅና ይህም ጤናማ ህዋሳትን ሳይነካ የካንሰር ሴሎችን ለይቶ የመምታት ብቃቱ የበለጠ ውጤታማ ስለሚያደርገው ነው፡፡ ሆኖም አክቲኒየምም እንደ ፍራንሲየም-221 እና ቢስሙዝ-213 ያሉ በጉበት፣ ኩላሊት እና ጣፍያ ውስጥ የሚጠራቀሙ መርዛማ ዲግሬድ ያደረጉ ንጥረ ነገሮችን ይሰጣል፡፡ ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነም ይህ ነው አክቲኒየም በህክምናው በስፋት ጥቅም ላይ እንዳይውል የሚያግደው፡፡
ለዚህ መፍትሄ ይሆን ዘንድ ታድያ ተመራማሪዎቹ ለየት ያለ አይሶቶፕን ወደ ፖሊመር-ካፕሱሎች የማሸግ ስልትን አስተዋውቀዋል፡፡ እንደተመራማሪዎቹ ከሆነም ይህ መንገድ መርዛማ አይሶቶፖችን ለማርከስ እና የአክቲኒየም ውጤታማነትንም ለመጨመር ያስችላል፡፡ በእንስሳት ላይ የተደረጉ ሙከራዎች እንዳመላከቱትም በኩላሊት ውስጥ የሚቀረው ከ5 በመቶ የማይበልጥ ሲሆን ይህም አሁን ያሉ የህክምና መንገዶች ከ30 እስከ 50 በመቶ የሚሆነውን እንደማስቀረታቸው ትልቅ መሻሻል ነው፡፡
ተመራማሪዎቹ ካፕሱሎቹን ለመስራት ኬሚካላዊ መንገድን ተጠቅመው በመጀመሪያ አክቲኒየሙን የፕሮቲን ሞለኪውል ከሆነው ከአልቡሚን ጋር በማጣበቅ በፖሊመር ውህዱ ውስጥ አስቀምጠውታል፡፡ አልቡሚኒኑ ከፖሊመሩ ጋር በደምብ ተጣምረውም ለአይሶቶፑ ከለላ ይሰሩለታል፡፡
ምንጭ፤ ስፑትኒክ
ለተጨማሪ፤ https://sputniknews.com/20210903/russian-scientists-create-universal-cure-for-cancer-1083789334.html

Sputnik International
Russian Scientists Create Universal Cure for Cancer
Scientists from Tomsk Polytechnic University (TPU) along with other researchers from Russia have managed to make cancer treatment with radioactive actinium-225 40% more effective.
የሮቦት ፖሊሶችን በሲንጋፖር ስራ ጀመሩ
===========
ሲንጋፖር ራስ ገዝ ሮቦቶች በመጠቀም በተማይቱ ማጨስን እና የኮቪድ 19 ደንቦችን መተላለፍን ጨምሮ ልዩ ልዩ ያልተፈለጉ ማህበራዊ ባህርያትን የመቆጣጠር ሙከራን እያከናወነች ትገኛለች፡፡ ዣቨር የተሰኙት ሮቦቶቹ 360 ዲግሪ መመልከት የሚያስችል ካሜራ ያላቸው ሲሆን በተጨማሪም በካሜራቸው የሚመለከቱትን ነገር በመተንተን ጥሰቶችን እዲለዩ የሚያስችል ሴንሰር ተገጥሞላቸዋል፡፡
ሮቦቶቹ ያልተፈለጉትን ማህበራዊ ባህርያት በሚመለከቱበት ጊዜ ወደ ቁጥጥር ማዕከሉ መረጃ በመላክ ማዕከሉ ውስጥ የሚገኙት ፖሊሶች በሮቦቱ በኩል አልያም በግንባር ተገኝተው እርምጃ እንዲወስዱ ያስችላል፡፡ 5 ያህል የሀገሪቱ ተቋማት ተሳታፊ የሆኑበት ይህ ሙከራ ፖሊሶች የግድ ለሁሉም ጉዳይ በአካል ለመገኘት እንዳይገደዱና ስራዎችም በተሻለ መልኩ እንዲሰሩ ያችላል ተብሎለታል፡፡
ሮቦቱ ቁጥጥር የሚያደርግባቸው ያልተፈለጉ ማህበዊ ባህርያት የሚከተሉት ናቸው፤ በተከለከለበት ቦታ ላይ ማጨስ፣ ሕገ-ወጥ ንግድ፣ አግባብ ባልሆነ መልኩ ብስክሌቶችን ማቆም፣ የኮቪድ 19 ደንብን በመጣስ ለ5 ወይም ከዚያ በላይ መሰብሰብ እንዲሁም በእግረኛ መንገድ ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች፡፡
ሲንጋፖር ከዚህ ቀደምም እንዲሁ በህዝባዊ መናፈሻዎች ውስጥ የኮቪድ ሕግጋት መጣስ አለመጣሳቸውን በሮቦቶች አማካኝነት ለመቆጣጠር ሙከራ አድርጋ ነበር፡፡ ለዚህ ሙከራም በቦስተን ዳይናሚክስ አማካኝነት የተፈበረኩትን እና ከ1 ሜትር በታች ተቀራርበው በተገኙ ሰዎች ላይ ልክ እንደ እውነተኛ ውሻ የሚጮሁ የሮቦት ውሻዎችን ተጠቅማ ነበር፡፡ እነዚህ የሮቦት ውሻዎችን ተጠቅሞ አንዳንድ የፖሊስ ስራዎችን የመስራት ሙከራ በአሜሪካንም ተከናውኖ የነበረ ሲሆን በተለይ በኒውዮርክ ከተማ ግን ከህዝብ በገጠመው ተቃውሞ ምክንያት ሙከራው ሊቋረጥ ችሏል፡፡
ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-09-singapore-robots-patrol-streets-undesirable.html

Singapore is testing robots to patrol the streets for 'undesirable' behavior like smoking
Singapore is in the midst of a three-week trial for a pair of autonomous robots that patrol the public for "undesirable social behaviors" that include smoking in prohibited areas and violating COVID-19 ...
ካርቦንን ለመቀነስ ተብሎ የተሰራው ፋብሪካ
********************************************
ለወትሮው ግዙፋን ኢንዱስትሪዎች በተገነቡ ቁጥር ትልቁ አሳሳቢ ጉዳይ በከባቢ አየር ላይ የሚኖራቸው ተጽዕኖ ነበር፡፡ ይኸውም ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ የሆነ ካርቦንን ወደ ከባቢ አየር ስለሚለቁ በቀጥታ የከባቢ አየር ደህንነት ስጋቶች በመሆናቸው ነው፡፡ ይህኛው መረጃ ግን ከዚህ በተቃራኒው ካርቦንን ለመቀነስ ግዙፍ ፋብሪካ ስራ መጀመሩን የሚናገር ነው፡፡
ይህ ኦርካ የተሰኘ ፋብሪካ በአለማችን በግዝፈቱ የሚተካከለው የለም የተባለ ሲሆን ስራውም ከከባቢ አየር ውስጥ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድን ብቻ ለይቶ በመምጠጥ ከአለት ጋር እንዲቀላቀል የሚያደርግ ነው፡፡ ስያሜውም በአይስላንድ ቋንቋ "orka" ከሚለው የተወሰደ ሲሆን ‹ሀይል› የሚል ፍች አለው፡፡
የስዊዘርላንድ እና የአይስላንድ በሆኑ ሁለት ድርጅቶች የተገነባው ይህ ፋብሪካ በየአመቱ 4000 ቶን ካርቦንዳይ ኦክሳይድን ከከባቢ አየር ውስጥ ለይቶ እንደሚያወጣ ተሰምቷል፡፡ እንደ አሜሪካው የአካባቢ ጥበቃ ተቋም መረጃ ይህ መጠን ከ870 መኪኖች የሚለቀቅን በካይ ጋዝ የሚያክል ነው፡፡
የመረጃ ምንጫችን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስን ጠቅሶ ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው የተሰበሰበው ካርቦን በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ ካለፈ በኋላ ከውሃ ጋር ተቀላቅሎ 1000 ሜትር ወደሚጠልቅ አለታማ አካባቢ ይለቀቃል፡፡ በዚህም ሂደት ካርቦኑ በጥልቅ አለታማ አፈር ውስጥ ተውጦ ይቀራል፡፡
ካርቦንን የመሰብሰብንና የማከማቸትን ሀሳብ የሚደግፉ ሙያተኞች ይህ ቴክኖሎጂ አለማችን ከከባቢ አየር ለውጥ ጋር በተያየዘ እየገጠማት ያለውን ችግር ለመቅረፍ አጋዥ መንገድ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ቴክኖሎጂው ውድ በመሆኑና የሚታይ ለውጥ ለማምጣት ብዙ ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ ተገቢነቱ ላይ ጥያቄ ያላቸው ሰዎች እንዳሉ ተሰምቷል፡፡
ምምጭ sciencealert
ለተጨማሪ ንባብ https://www.sciencealert.com/world-s-largest-project-for-turning-carbon-dioxide-into-rock-has-begun?fbclid=IwAR0miX8Y-YWaQi6e4JkXm_jFHlG7GE2J4eONJ9onljo30QVjeqs3u8yFuhY

ScienceAlert
The World's Largest Carbon-Sucking Plant Just Became Operational
The world's largest plant designed to suck carbon dioxide out of the air and turn it into rock started running on Wednesday, the companies behind the plant said.
አዲስ አበባና ዙርያዋ ላሉ ገበሬዎች አገልግሎት የሚሰጥ ዲጂታል የግብርና ባንክ ሊጀመር ነው
================
አሊያንስ ማይክሮ ፋይናንስ ከየኖርዌይየከተማ ቤተ ክርስቲያን እርዳታ ተቋም፣ ባከን እና ባከን እንዲሁም ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ጋር በመተባበር ግብርናን ኢላማ ያደረገ ዲጂታል የግብርና ባንክ ሊያስጀምር ነው፡፡ ከኖርዌይ የልማት ትብብር ኤጀንሲ (NORAD) ድጋፍ የሚደረግለት ይህ ፕሮጀክት በዲጂታል የግብርና ባንኩ አማካኝነት በአዲስ አበባ እና አካባቢው ባሉ ከተሞች ውስጥ ለሚገኙ ገበሬዎች የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት እና የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚሰራ ነው፡፡
አሊያንስ ማይክሮፋይናንስ ለትርፍ ያልተቋቋመ ኩባንያ ሲሆን በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ውስጥ ለሚገኙ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ዘንድ የፋይናንስ ተደራሽነትን በማስፋፋት አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን የመደገፍ ስራን የሚሰራ ነው፡፡ ኩባንያው የዚህ ፕሮጀክት ዋና ባለ ድርሻ ሲሆን የማስተዳደር ኃላፊነቱንም የሚወጣው እርሱ ይሆናል፡፡ ቤከን እና ቤከንን ያየን እንደሆን በቅርቡ በኖርዌይ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘውን ቪፖስ የተሰኘ የክፍያ ስርዓትን ያስተዋወቀ የዲጂታል ምርቶች አቅራቢ ኩባንያ ነው፡፡ ይህ ኩባንያም በዚህ ፕሮጀክት ላይ ዲጂታል መፍትሄዎችን የማምጣቱን ድርሻ እንደሚወጣ ተዘግቧል፡፡ ሌላው የዚህ ትብብር አካል የሆነውና በኢትዮጵያ አሉ ከሚባሉ የኢንዱስትሪ አንቀሳቃሾች መካከል የሚመደበው ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግስ ገበሬዎች የሚያመርቱትን ምርት የማሰራጨቱን ድርሻ ወስዷል፡፡
የትብብሩ መሪ አሊያንስ ማይክሮ ፋይናንስ ይህ የተቋማቱ ቅንጅታዊ ስራ በፕሮጀክቱ ተደራሽ የሚሆኑት ገበሬዎችን ገቢ ከማሳደግም ባሻገር አዳዲስ የስራ እድሎችንም እንደሚፈጥር ተናግሯል፡፡
ምንጭ፤ ሸጋ
ለተጨማሪ፤ https://shega.co/post/amas-to-launch-a-digital-agri-bank-in-ethiopia/

Shega
AMAS To Launch a Digital Agri-bank in Ethiopia - Shega
AMAS To Launch a Digital Agri-bank in Ethiopia AgriTech Shega
ካሜራ የተገጠመለት መነጸር ከፌስቡክ
***************************
እውቁ የማህበራዊ ድረ-ገጽ ፌስቡክ ካሜራ የተገጠመለት ልዩ መነጸር ሰርቶ አቀረበ፡፡ መነጸር በሰዎች ዘንድ ለተለያዩ አገልግሎቶች ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በዋናነት የሚጠቀሰው ከእይታ ችግርና ከአይን ደህንነት ጋር የተያያዘው ጥቅሙ ነው፡፡
በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን የሚሰጡ በቴክኖሎጂ የዳበሩ መነጸሮችን ሰርተው አስተዋውቀዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ ፌስቡክ በዘርፉ አዲስ ነገርን ይዞ እንደመጣ ተነግሯል፡፡
መነጸሩ ከታዋቂው የመነጸር አምራች ድርጅት ሬይ ባን እና የአውሮፓ ካምፓኒ ከሆነው ኢስሎርሊክሳቲካ ጋር በጥምረት የተሰራ ሲሆን ሰዎች በቀላሉ ሊለብሲት የሚችሉት እና ፎቶዎችን ማንሳት የሚችሉበት ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡
መነጸሩ ከዚህ በተጨማሪ መናገሪያ እና ማዳመጫ የተገጠመለት ሲሆን በዚህም ተጠቃሚው የስልክ መልዕክቶችን መለዋወጥ ይችላል ተብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አንድ መተግበሪያ ያለውና ሐይል መሙላት የሚያስችል ክፍል ተሰርቶለታል፡፡
መነጸሩ አሁን ላይ በአሜሪካ፣ በእንግሊዝ፣ ካናዳ፣ አይርላንድና አውስትራሊያ ለገበያ የቀረበ ሲሆን 299 የአሜሪካ ዶላርም ተቆርጦለታል፡፡ በጉዳዮ ላይ መረጃ የሰጠው ፌስቡክ መነጸሩ ሰዎች እያንዳንዱን እንቅስቃሴዎቻቸውን በምስል ማስቀረት እንደሚያስችላቸው ተናግሯል፡፡ አክሎም ሙዚቃ ማዳመጥ፣ ስልክ ማነጋገር፣ ፌስቡክ መጠቀም እንዲሆም በማህበራዊ ሚዲያ ምስልችንና ቪዲዮዎችን ለሰዎች ማጋራት ያስችላቸዋል ሲል ተናግሯል፡፡
ፌስቡክና ሬይ ባን የአውሮፓ ካምፓኒ ከሆነው ኢስሎርሊክሳቲካ ጋር በትብብር የሰሩት መነጸር ለአመታት የሚሆን የስምምነት ፊርማ ተደርጎበታል፡፡ ምንም እንኳን መነጸሩ የተለያዩ ነገሮችን በአንድ አካቶ የተሰራ ቢሆን ተጠቃሚዎች ሙሉ ቀን ለብሰውት የመዋላቸው ጉዳይ አጠራጣሪ እንደሚሆን ከድርጅቶቹ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/.../2021-09-facebook-ray-ban-smart...

እስራኤል ሰራሹ የሮቦት ወታደር
==========
ሬክስ ኤምኬአይአይ የተሰኘው እስራኤላዊ የኤሮስፔስ ኩባንያ በውጊያ አካባቢዎች ላይ ቅኝት የሚያደርግ፣ ጠላትን የሚከታተልና የሚተኩስ ታጣቂ ሮቦትን ይፋ አድርጓል፡፡ ከርቀት ባለ ሰው እየተመራ የሚንቀሳቀሰውን ይህ ሰው አልባ ሮቦት ውጊያን እየቀየሩ ካሉት ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጋር ተደምሯል፡፡ ሆኖም እንዲህ አይነት በተወሰነ መልኩ ራሳቸውን የሚያዙ መሳርያዎችን መስራቱ ሮቦቶች የሰዎችን በህይወት የመኖር አለመኖር እጣ እንዲወስኑ የሚያደርግ አደገኛ እርምጃ ነው በሚል እየተተቸ ይገኛል፡፡
እንደ ኩባንያው ኃላፊዎች ከሆነ በታብሌት አማካኝነት እየተመራ የሚንቀሳቀሰው ሮቦቱ ሁለት መትረየሶች፣ የተለያዩ ካሜራዎች እና ሴንሰሮችን መያዝ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ለእግረኛ ወታደሮች የሚሆን መረጃን የመሰብሰብ፣ የተጎዱ ወታደሮችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን የማመላለስ ስራን መወጣት እንዲችል ተደርጎ ተሰርቷል፡፡ በታብሌቱ አማካኝነት ሮቦቱን ማንቀሳቀሱ እንደተጠበቀ ሆኖ እንቅስቃሴው እና የስለላ ስርዓቱን ጨምሮ አብዛኛው ስራዎቹን ግን ሮቦቱ በራሱም ማድረግ እንዲችል ሆኖ ተሰርቷል፡፡
ሆኖም እንዲህ አይነት እንቅስቃሴዎች የወታደሮችን ህይወት በተሻለ የሚጠብቁ ቢሆንም የታጠቁ ሮቦቶች ውሳዎችን በራሳቸው እንዲያስተላልፉና ባስ ሲልም አልመው እንዲተኩሱ ያደርጋሉ እየተባሉ ይወቀሳሉ፡፡ ይህን ሮቦት የሰራው ኩባንያም ቢሆን ታጣቂ ሮቦቶች በራሳቸው ውሳኔ መተኮስ እንዲችሉ አድርጎ የመስራት አቅም መኖሩን ይገልፃል፤ ምንም እንኳን ይህን የመስራት ውስኔው በሰው ልጆች እጅ ላይ ቢሆንም፡፡ ነባር የሂውማን ራይትስ ዋች አጥኚ የሆኑት ቦኒ ዶቸርቲ እንደነዚህ አይነት ራስ ገዝ መሳርያዎች ተዋጊን ከንፁሀን ለይቶ በማየት እንዲሁም የሚሰነዝሩት ጥቃት በንፁሀን ላይ ሊያደርስ ስለሚችለው ጉዳት አገናዝቦ በመንቀሳቀስ ረገድ እምነት ሊጣልባቸው እንደማይችል ይገልፃሉ፡፡ ቦኒ ከዚህ ቀደም አውጥተውት በነበረው ሪፖርታቸው ላይም ማሽኖች የሰው ህይወት ያለውን ውድ ዋጋ ስለማይረዱ የሰውን ሰብአዊ ክብር እና መብቶችን ሊጥሱ እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡
ከቴክኖሎጂ አንፃርም በአየር እና ውሃ ላይ ከሚንቀሳቀሱት አንፃር ራስ ገዝ የየብስ ላይ ተሽከርካሪዎች ወደኋላ መቅረታቸው ይነገራል፡፡ ለዚህም በየበስ ላይ መንቀሳቀሱ ሲበዛ ውስብስብ እና በተለያዩ የመሬት አቀማመጥ እና ሌሎች በርካታ ተግዳሮቶች የተሞላ መሆኑ በምክንያትነት ይጠቀሳል፡፡ በሌላ መልኩ ራስ ገዝ መኪኖችን እንኳን ብናይ በቴስላና ሌሎች ኩባንያዎች የተሰሩ ራስ ገዝ መኪናዎች የሰው ህይወትን ጭምር ያሳጡ አደጋዎችን ማድረሳቸው አሳሳቢ ሆኗል፡፡
በአሁኑ ሰዓት የእስራኤል ጦር አነስ ያሉ ግን ደግሞ ተመሳሳይ ግልጋሎት የሚሰጡትን ጃግዋር የተሰኙ ተሽከርካሪ ሮቦቶችን በጋዛ ሰርጥ አካባቢ ያለውን ድንበር ለመቆጣጠር እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ ጦሩ እንደሚገልፀው ከሆነ እነዚህ በበከፊል ራስ ገዝ የሆኑ ሮቦቶች መትረየስን የታጠቁና ድንበሩን የሚጠብቁ ወታደሮች የአደጋ ተጋላጭነትንም የሚቀንሱ ናቸው፡፡ ከእስራኤል ባሻገር ግን እንደ አሜሪካን፣ ብሪታኒያ እና ሩሲያ ያሉ ሀገራትም መሰል ሰው አልባ ተሸከርካሪዎችን በመጠቀም የማጓጓዝ፣ ፈንጂ ማምከን እና የመተኮስ ስራዎችን በመስራት ላይ ናቸው፡፡
ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-09-israeli-firm-unveils-armed-robot.html

Israeli firm unveils armed robot to patrol volatile borders
An Israeli defense contractor on Monday unveiled a remote-controlled armed robot it says can patrol battle zones, track infiltrators and open fire. The unmanned vehicle is the latest addition to the world ...
ሰው ሰራሽ እስስት
=========
የደቡብ ኮርያ ተመራማሪዎች ልክ እንደ እስስት ቀለሙን በመቀያየር ዙርያውን መምሰል የሚችል ቆዳ መሰል ነገርን መስራታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በሶል ዩኒቨርሲቱ የሜካኒካል ምህንድስና ምሁር በሆነው ኮ ሱን ኋን በሚመራ አንድ የጥናት ቡድን የተሰራው ይህ ቆዳ በሙቀት አማካኝነት መልኩን የሚቀያይናር እጅግ አነስተኛ እንዲሁም ተጣጣፊ የሆነ ማሞቅያ የተገጠመለት ቀለምን (ink) የያዘ ነው፡፡
የጥናት ቡድኑ የቴርሞክሮሚክ ሊኩዊድ ክሪስታል (TLC) ቀለምን እና ተነባብረው የተቀመጡ ባለ ናኖ ገመድ የብር ማሞቂያዎችን በመጠቀም የተሰራውን ይህን ሰው ሰራሽ ቆዳ ቀለምን መለየት የሚችል ሴንሰር በተገጠመለትና በእስስት አምሳያ በተሰራ ሮቦት ላይ አልብሶ አሳይቶታል፡፡ ሴንሰሮቹ በዙርያቸው ስላለው ቀለም የሰበሰቡትን መረጃ ወደማይክሮፕሮሰሰሩ ከዚያም ወደ ማሞቅያው ይላካል፡፡ ማሞቅያው በበኩሉ የተወሰነ የሙቀት ደረጃ ላይ በሚያደርስበት ሰዓት ፈሳሹ ቀለሙን ይቀይራል፡፡ በዚህም የሮቦቱ ቀለምን መለያ ሴንሰሮች በዙርያቸው ያለውን ቀለም ባዩ ጊዜ ቆዳው ያንን ቀለም እንዲይዝ ያርጉታል፡፡ ሌላው አስገራሚ ነገር ሮቦቱ የተላበሰው ይህ ሰው ሰራሽ ቆዳ የተለያየ ንብርብር ያለው ቢሆንም አጠቃላይ ውፍረቱ ግን ከ 0.1 ሚ.ሜ ያነሰ ነው፡፡ ይህም ከሰው ልጅ ፀጉርም የሳሳ ያደርገዋል፡፡
የሮቦቱን ቀለም የመቀየር ብቃት በሚያሳይ አንድ ምስል ላይ ሮቦቱ በሰማያዊ እንዲሁም አረንጓዴ ወለሎች ላይ እንዲቀመጥ ሲደረግና እርሱም ወድያው የወለሉን ቀለም መስሎ ሲገኝ ታይቷል፡፡
እንደ ተመራማሪዎቹ ከሆነ ሰው ሰራሽ ቆዳው እንደ ተለባሽ ሆኖ ለፋሽን ግብዓትነት አልያም ለወታደሮች ልብስነት፣ የመኪና ውጫዊ ገፅታ፣ ህንፃዎችን ለማስዋብ እንዲሁም ለሌሎች መሰል አገልግሎቶች መዋል ይችላል፡፡
ምንጭ፤ ሮይተርስ
ለተጨማሪ፤ https://www.reuters.com/lifestyle/science/south-korean-researchers-create-chameleon-like-artificial-skin-2021-09-09/?taid=613986caeca2670001c480a3&utm_campaign=trueanthem&utm_medium=trueanthem&utm_source=twitter

Reuters
South Korean researchers create chameleon-like artificial "skin"
South Korean researchers say they have developed an artificial skin-like material, inspired by natural biology, that can quickly adjust its hues like a chameleon to match its surroundings.
ከባድ የሶላር ሱናሜ የአለምን ኢንተርኔት ሊያጠፋ ይችላል
===========================
ከፀሀይ የሚነሱ ሞቃት ነፋሳት የሚገድባቸው ነገር እስካላገኙ ድረስ ህዋ ውስጥ ይጉዋዛሉ። እነዚህን ነፋሳት ሊያቆሟቸው የሚችሉት ከሚጉዋዙበት ፍጥነት በበለጠ እና በተቃራኒ አቅጣጫ የሚነፍሱ ነፋሳት ብቻ ናቸው። የምድራችን መግነጢሳዊ መስክ (magnetic field) ከፀሃይ ውስጠኛ ክፍል በከፍተኛ ፍጥነት የሚመጡትን ሞቃትማ ነፋሳት የሚያግድ ቢሆንም በጥለቁ የህዋ ክፍል የሚገኙ ሌሎች የበይነኮከባዊ ነፋሳት (Interstellar winds) ከፀሀያችን የሚወጡትን ሞቃታማ ነፋሳት የምድራችን ካባቢ አየር ጋር ከመድረሳቸው በፊት ፍጥነታቸውን በእጅጉ እንዲቀንስ ያደርጓቸዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የብዙ ፕላኔቶች የመግነጢሳዊ መስክ መገኛ በሆነ የህዋ ክፍል የምድራችን መግነጢሳዊ መስክ የበላይነት ይዞ የሚገኝበት እና በብዙ ሺ ኪሎሜትሮች ምድራችንን ሸፍኖ የሚገኘው ንጣፍ ማግኔቶስፌር (magnetosphere) ተብሎ ይጠራል፡፡
ከባህር ወለል በላይ ብዘ መቶ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ በጥልቁ የህዋ ክፍል እስከ አስረሽ ሺ ኪሎ ሜትሮች ድረስ የሚዘረጋው የማግኔቶስፌር ንጣፍ የምድራችን መግነጢሳዊ መስክ እና ከፀሀያችን የሚነሱ ፕላስማ የተሰኙ ፖርቲክሎች ከፍተኛ ግንኙነት የሚያድረጉበት የህዋ ክልል ነው፡፡ ምድርን ሸፍኖ የሚገኘው የማግኔቶስፌር ንጣፍ ወይም ሌየር ከፀሃይ የሚመጣውን ቻርጅድ ፓርቲክልስ የመቋቋም አቅሙ ከፍተኛ ቢሆንም አልፎ እልፎ በከፍተኛ መጠን የሚመጣው የሶላር ስቶርም ወይም በሳይንሳዊ አጣራሩ (geomagnetic storm) በምድራችን የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ አደጋን ሊያስከትከል ይችላል፡፡
በፀሃይ የመግነጢሳዊ መስክ ዙሪያ በሚኖር አለመረጋጋት በከፍተኛ መጠን ወደ ህዋ ክፍል የሚሰራጨው በቢሊዮን ቶን የሚለካ ከፍተኛ ሙቀት ያለው ጋዝ ለምድራችን ስጋት ሊሆን እንደሚችል የሚናገሩት ተመራመሪዎች ይህም ከዚህ ቀድም በተለያዩ ጊዚያት ተከስቶ ለነበረው coronal mass ejection (CME) ዋና ምክንያት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የሚገኙትና በዚህ ጉዳይ ላይ በቅርቡ የምርምር ጽሁፍ ያሳተሙት ፕሮፌሰር አርቪንና ረዳቶቻቸው እንደሚሉት በተለያየ የጊዜ ኡደት ወደ ህዋ ክፍሎች የሚሰራጨው ከባድ የሶላር ሱናሜ የምድራችንን መግነጢሳዊ መስክ በማጥቃት በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈጥረው ችግር የአለማችንን ኢንተርኔት ወይም በይነ-መረብ የማጥፋት አቅም አንዳለው ይናገራሉ፡፡ በተለይም በዓለምችን የበይነመረብ መሠረተ ልማት ውስጥ ወሳኝ አካል የሆኑት ከባህር በታች ያሉ የኢንተርኔት ኬብሎች በሶላር ስቶርም የተነሳ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስባቸው ከማቻሉ አንጻር የአለምን ኢንተርኔት በቀጥታ የመጥፋት እድል እንደሚኖረው ተመራማሪዎች ያስረዳሉ፡፡
እንዲህ ያሉ ክስተቶች ቀድም ባሉት ጊዜያት አልፎ አልፎ የመከሰት እድል ቢኖራቸውም ኡሁን ባለው ደረጃ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች በአለም ላይ ባለመስፋፋታቸው ጉዳቱን አነስተኛ አንዲሆን ማድረጉን የሚናገሩት ተመራማሪዎች የበይነ-መረብ ዝርጋታ ከመጀመሩ በፊት እንደአውሮፓውያኑ በ1989 የተከሰተው የ coronal mass ejection አደጋ ለብዙ ሰዓታት የኤሌክትሪክ አቅርቦት እንዲቋረጥ ያደረገበት ሁኔታ እንደምሳሌ የሚጠቀስ መሆኑን ያነሳሉ፡፡ አሁን ላይ ለበይነ-መረብ መስፋፋት ከባህር በታች ያሉ የኢንተርኔት ኬብሎች (undersea internet cables) ዋና መሰረተ ልማት ከመሆናቸው አንጻር እነሱ ላይ በቀጥታ ሊደርስ የሚችል አደጋ የሰዎችን የበይነ-መረብ ግንኙነት በማቋረጥ ለአለማችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ትልቅ ጉዳትን ሊያመጣ ይችላል፡፡ በብዙ አመታት አንዴ ሊያጋጥም ይችላል የሚባለው ይህ ከባድ የሶላር ሱናሜ ምድራችንን በ1859፣ በ1921 እና በቅርቡ በ1989 እንዳጠቃት የሚናገሩት ተመራማሪዎች አሁን ካለው የቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማት መስፋፋፈት ጋር ተያይዞ አደጋው እጅግ የከፋ እንዳይሆን ተገቢውን ትከረት መስጠት እና ምርምሮች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈል ይናገራሉ፡፡
ምንጭ infomance
https://www.infomance.com/a-solar-tsunami-could-knock-out-global-internet-heres-what-that-means/