TechIn2
1.16K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
አዲሱ የአይፎን ስልክ የሳተላይት ግንኙነትን አካቷል፣ ይህ ምን ማለት ይሆን
=========================
አፕል በቅርቡ ይፋ የሚያደርገው የአይፎን ስልክ የሳተላይት ግንኙነትን የሚያስቸል በመሆኑ ለስልኩ ተጠቃሚዎች አስፈላጊው የአውታር-መረብ ሽፋን (cellular coverage) በሌለባቸው ቦታዎች መደበኛ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚስችል ነው፡፡ የማክሩመርስ ዘጋቢ ሚንግ ቺኩዎ እንደጠቀሰው አይፎን 13 የተባለው አዲሱ የአፕል ስልክ በተካተተለት የሳተላይት ግንኙነት ገፅታ የኔትወርክ ሽፋን አስቸጋሪ በሚሆንባቸው አካባቢዎች ተጣቃሚዎች ስልክ መደውል እንዲችሉ እና መልዕክት መላላክ እንዲችሉ የሚያግዝ ነው ብሏል፡፡

አዲሱ የአፕል ምርት የ4ጂ፣ 5ጂ እና ሌሎች የኔትዎርክ ሽፋኖች በሌሉባቸው ቦታዎች እንደ ስልክ መደውል እና መልዕክት መላላክ ያሉ መደበኛ አገልግሎቶችን ተጠቃሚዎች እንዲያገኙ የሚያስችለው በቀድሞ የገመድ ስልኮች ይገጠም የነበረ የዘመነ ሃንድሴት ሃርድዌር በማከሉ ነው፡፡ በአይፎን 13 ስልክ ላይ የሚገጠመው የዘመነ የሃንድሴት ሃርድዌር ዝቅተኛ የምድር ምህዋር ሳተላይቶች (low-Earth orbiting satellites) ጋር በቀላሉ ለመገናኛት ስለሚያስችለው የአውታር-መረብ ሽፋን (cellular coverage) በሌለባቸው ቦታዎች መደበኛ አገልግሎት አንዲሰጥ ያደርገዋል፡፡ የሳተላይት ግንኙነቱ ከስልኩ ጋር በደንብ እንዲግባባ Qualcomm X60 የተሰኘ የቤዝባንድ ቺፕ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ይህም አጠቃላይ የግንኙነት ስርኣቱን የሚያፋጥንና የሚደግፍ ይሆናል፡፡

ዝቅተኛ የምድር ምህዋር ሳተላይቶች ላይ የሚሰራው ግሎባል ስታር የተሰኘው የሳተላይት ግንኙነት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት አፕል በቅርቡ ይፋ ለሚያደርገው የስልክ ምርት የቴክኖሎጂና የኔትወርክ ሽፋን በመስጠት በጋራ የሚሰራ ነው፡፡ ግሎባል ስታር ዝቅተኛ የምድር ምህዋር (LEO) ላይ ብዙ ሳተላይቶችን በማሰማራት አገልግሎቱ ለሚያስፈልጋቸው ድርጅቶች ለብዙ አመታት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ድርጅት እንደነበር በዘገባው ተገልጿል፡፡ በዚህ ዘርፍ ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙ ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኘው የስፔስ ኤክስ ኩባንያ የኔትወርክ ሽፋን ባልተሟላላቸው በሁሉም የአለማችን ክፍሎች የ LEO ሳተላይቶችን በስፋት ጥቅም ላይ በማዋል በየትም ቦታ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ዘጋቢው ሚንግ ቺኩዎ ተናግሯል፡፡

አንዲህ ያሉ የቃጣይ ትውልድ የቴክኖሎጂ አማራጮች የኔተዎርክ ሽፋን በሌለባቸው ቦታዎች የሚኖሩ ብዙ ሚሊዮን ሰዎችን በእጅጉ የሚረዳ እና በብዙ የአለማችን ክፍሎች በግንኙነት እጥረት ምክንያት አስፈላጊውን እርዳታ ለማያገኙ ሰዎች ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡ ይሁንና በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ለተጠቃሚዎች ይፋ ይደረጋል የሚባለው አይፎን 13 በተሟላ ሁኔታ የተባለውን አገልግሎት ለመስጠት ጊዜ እንደሚወስድበት የሚናገሩ አንዳንድ ባለሙያዎች የአገልግሎት አይነቱ መልክዕክት በመላክ የተወሰነ እና በተለይም አንደ አውሮፕላን አደጋ፣ የመርከብ መስጠምና ሌሎች ከባድ አደጋዎች ሲደርሱ በአጭር የፅሁፍ መልክት ለማሳወቅ የሚያስችል ብቻ መሆኑን ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡
ምንጭ፡ macrumors
https://www.macrumors.com/2021/08/29/iphone-13-to-feature-leo-to-make-calls-and-text/
የአስትራ ሮኬት የማስወንጨፍ ሙከራ ከሸፈ
የአስትራ ሮኬት የማስወንጨፍ ሙከራ ከሸፈ
======================
በአሜሪካ የአየር ሃይል ክፍል ውስጥ አንድ ቅርንጫፍ በሆነው የስፔስ ፎርስ ፈንድ አድራጊነት ቅዳሜ ዕለት ወደ ጠፈር ሊወነጨፍ የነበረው የአስትራ ሮኬት በኢንጅን ክፍሎቹ ላይ ባጋጠመ ብልሽት አጠቃላይ የማስወንጨፍ ሙከራው ሊከሽፍ እንደቻለ ተነግሯል፡፡ አላስካ በሚገኘው የፓሲፊክ ስፔስፖርት ኮምፕሌክስ ሊወነጨፍ የነበረው የአስትራ 3.3 ሮኬት ለሁለት ደቂቃ ከግማሽ ወደላይ በመነሳት 50 ኪሎ ሜትሮችን ከተጓዘ በኋላ ከአምስቱ የኢንጅን ክፍሎች በአብዛኞቹ ላይ ባጋጠመ ብልሽትና የመጥፋት ችግር የማስወንጨፍ ሙከራው ከሽፎ ወደምድር እንደሚለስ መደረጉን ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘግቧል፡፡

LV0006 የተባለች አነስተኛ የሳተለያት ቬክል ተሸኮሞ የነበረው የአስትራ ሮኬት ከዚህ በፊት በተያያዥ ምከንያቶች የተነሳ መሰል ችግር አጋጥሞት የነበረ ሲሆን ይህ አጋጣሚም ወደምህዋር ለመድረስ ከላካቸው እና ሳይሳኩ ከቀሩት የማስወንጨፍ ሙከራዋቹ ሶስተኛው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ሮኬቱ ላይ ከደረሰው ከስተት በኋላ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጠው የአስትራ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክሪስ ኬምፕ የተፈጠረው ነገር ለምን ሊከሰት እንደቻለ እየመረመርን ቢሆንም የማስወንጨፍ ሙከራው ገና እንደተጀመረ በሰከንዶች ልዩነት በአምስቱ የመጀመሪያ የኢንጅን ስቴጅ ክፍሎች ላይ ችግር አንዳጋጠመ ተመልክተናል ብሏል፡፡

የአስትራ 3.3 ሮኬት የኢንጅን መጥፋት ችግር ያጋጠመው ገና በሰከንዶች ልዩነት ቢሆንም ይህን ተቋቁሞ ለሁለት ደቂቃ በላይ ወደላይ በመነሳት 50 ኪሎ ሜትሮችን ከተጓዘ በኋላ ከአምስቱ የኢንጅን ክፍሎች በአብዛኞቹ ላይ ባጋጠመ ብልሽትና ሙሉ ለሙሉ የመጥፋት ችግር ሰዎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ ኮዳያክ በተባለ ዴሴት ላይ ሊከሰከስ ችሏል፡፡ የማስወንጨፍ ሙከራው በተጀመረ በሰከንዶች ልዩነት የኢንጅን መጥፋት ችግር አጋጥሞትም እንኳን ለሁለት እና ከዚያ በላይ ደቂቃ መጓዝ ያቻለበት ሁኔታ አስገራሚ የጋይዳንስ ስርዓት እንደነበር የሚያመላክት ነው የሚለው የኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክሪስ ኬምፕ ከዚህ በላይ ደግሞ በሰዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ ሮኬቱን ወደ ምድር ማውረድ መቻሉ ስራውን ሲያከናውኑ የነበሩ የባለሙያዎች ቡድን የሚያመስሰግን ነው ብሏል፡፡

ሮኬት የማስወንጨፍ ሙከራ ቢሊዮን ዶላሮች የሚንቀሳቀሱበት ከባድ ቢዝነስ ከመሆኑ አንጻር ለሶስተኛ ጊዜ የማስወንጨፍ ሙከራው የከሸፈበት የአስትራ ኩባንያ ከባድ ክስረት እንደሚሆንበት ተገልጿል፡፡ ከዚህ በፊት በነበሩት ጊዜያት ብዙ ኩባንያዎች የራሳቸውን ሳተላይት ወደ ምህዋር ለማስገባት እጅግ ይቸገሩ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደ ስፔስ ኤክስ፣ ኦርቢት እና አስትራ ያሉ ግዙፍ የግል ኩባንያዎች እየተስፋፉ መምጣታቸው ሮኬት የማስወንጨፍ ሙከራን ይበልጥ እንዲዘምንና አንዲቀል አድርጎታል፡፡
ምንጭ፡ spacenews
https://spacenews.com/astra-rocket-3-3-launch-fails/
ዊንዶው 11 ቀን ተቆረጠለት
*************************
የዊንዶው 10 ተከታይ የሆነው ዊንዶው 11 የተሰኘው መጠቀሚያ በመጪው የፈረንጆቹ ጥቅምት 5 ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተነገረ፡፡ ላለፉት ጥቂት ወራት ሙከራ ሲደረግበት የነበረው ይህ ፕላትፎርም ከዚህ በፊት የነበረንን መጠቀሚያዎች ለማሻሻልና እንደ ዴል፣ ሌኔቮ ሌሎች የኮምፒውተር አይነቶች ላይ ተጭኖ እንደሚቀርብ ተነግሯል፡፡

በቀጠሮው እለት የሚቀርበውን ማሻሻያ የተደረገበትን የዊንዶው አይነት እንደቀድሞው (አሁን ላይ ጥቅም እየሰጠ ያለው ዊንዶው 10) ተመሳሳይ ማሻሻሎች (updates) ያሉት ሲሆን የቫይረስ ተጋላጭነቱ ዝቅተኛ ነው ሲል ማይክሮሶፍት አሳውቋል፡፡ ወደ ዊንዶው 11 ማሳደጊያውም በነጻ የቀረበ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

ዊንዶው 11 እንደሚጫንበት የኮምፒውተር አይነት የተለያየ ቢሆንም ሁሉም የኮምፒውተር አይነቶች በነጻ የቀረበውን ማሳደጊያ እስከ 2022 አጋማሽ ድረስ መጠቀም እንደሚችሉ ይፋ ተደርጓል፡፡ የምንጠቀመው ኮምፒውተር ለአዲሱ ዊንዶው የተፈቀደለት ከሆነ በማይክሮሶፍት በኩል ማሳወቂያ ይላካል ተብሏል፡፡

ይሁን እንጂ ሰዎች አዲሱን ዊንዶው መጠቀም ካልቻሉ ዊንዶው 10 እስከ ጥቅምት 2025 ድረስ አገልግሎት እንደሚሰጥ ማይክሮሶፍት አሳውቋል፡፡ ተቋሙ አክሎም የተለያዩ የአንዲሮይድ መተግበሪያዎችን ከዊንዶው 11 ጋር ለማቀናጀት ከአማዞንና ከኢንቴል ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አሳውቋል፡፡

በተለያዩ አማራጮች ይከታተሉን
ዩትዩብ youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg
ትዊተር twitter.com/TechinEthiopia

ምንጭ Digital trends
ለተጨማሪ ንባብ https://www.digitaltrends.com/computing/windows-11-set-for-october-5-general-availaiblity/?utm_source=facebook&utm_medium=social&utm_content=socialorg_computing&fbclid=IwAR3ExNhGIerYwCmeK3gDt43-H0uB0DxM6SEMQKACqe6hU_EEovFZ6weiCP4
ከፍተኛ ብክለት ያለው የእርሳስ ነዳጅ ከዓለም ተወግዷል
========================
የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ፕሮግራም እንዳስታወቀው ለዘመናት በምድራችን ላይ አደጋ ሲያስከትል የነበረው የእርሳስ ነዳጅ (leaded petrol) ከብዙ አመታት ዘመቻዎች በኋላ በየትኛውም ሃገር ጥቅም ላይ የማይውልበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ይፋ አድርጓል፡፡ ይህን መርዛማ ነዳጅ ለመጨረሻ ጊዜ አከማችታ ትሸጥና ትጠቀም የነበረቸው የሰሜን አፍሪካዋ ሃገር አልጄሪያ በሃምሌ ወር መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ ክምችቷ መጠናቀቁን ተከትሎ ይህ የነዳጅ አይነት ከአለማችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊወገድ ችሏል፡፡
በእርሳስ ውህድ የሚታከም ወይም የሚቀየጥ ነዳጅ (Tetraethyl lead) ቀደም ላሉት የጭነትና ሌሎች የመኪና ሞዴሎች የሞተር ማንኳኳትን (engine knocking) በመቀነስ የኢንጅኑን የመፈፀም አቅም ለመጨመር ታስቦ ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ሲሆን፤ እንደአውሮፓውያኑ ከ1920 ጀምሮ በብዙ የዓለማችን ክፍሎች ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ከዚህ መርዛማ ነዳጅ የሚወጣው በካይ ነገር በከባቢ አየር፣ በአፈር እና በወንዞችም ጭምር ለአንድ መዕተ አመት ጊዜ ያክል ከፍተኛ ብክለት በአለማችን ላይ ሲያስከትል ቆይቷል፡፡
ይህ ነደጃ በሚስከትለው ችግር ምክንያት ብዙ ሚሊዮኖች በልብ በሽታ፣ በካንሰር እና በስትሮክ እንደተጠቁ የሚነገር ሲሆን በህጻናት የአዕምሮ እድገት ላይ ከባድ ተፅዕኖ እንደነበረውም ይገለጻል፡፡ እንደአውሮፓውያኑ ከ1924 ጀምሮ እንዲህ ያለ ነዳጅን ጥቅም ላይ ማዋል ከፍተኛ ጉዳት እንደሚኖረው እየታወቀ ቢመጣም እስከ 1970ዎቹ ድረስ ብዙ ሀገራት ከእርሳስ ጋር የተቀላቀለ ነዳጅን ሲያመርቱና ሲሸጡ ቆይተዋል፡፡ በ1980ዎቹ በአለም አቀፍ ዘመቻና በሌሎች የማንቃት ፕሮግራሞች ብዙ ሀገራት ይህን ነዳጅ ከመጠቀም እየተቆጠቡ ቢመጡም የፈንጆቹ ሚሊኒየም እስኪገባ ድረስ በ86 ሀገራት ከእርሳስ ጋር የተቀላቀለ ነደጅ ጥቅም ላይ ይውል ነበር፡፡ ከ2002 በኋላ የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ፕሮግራም ከአለም ሀገራት፣ ከግል ኩባንያዎች እና ከሌሎች የሲቪኪ ማህበራት ጋር በህብረት ባካሄዱት ዘመቻ ባለፉት ሃያና አስራ አምስት አመታት ከፍተኛ ስኬት ማምጣት እንደተቻለ ይነገራል፡፡ ባለፉት ሶስት አመታት ይህን መርዛማ ነዳጅ መጠቀም ካቆሙት ኢራቅ፣ የመን እና አልጂሪያ በፊት በ2016 የነዳጁ ከፍተኛ ተጠቃሚ የነበሩት ሰሜን ኮሪያ፣ ማይናማር እና አፍጋኒስታን በሀገራቸው ነዳጁን መሸጥ ማቆማቸውን ተከትሎ ብዙ አመታት የወሰደው የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ፕሮግራም ዘመቻ በስኬት እንዲጠናቀቅ አድርጎታል፡፡
ከፍተኛ ብክለት የነበረው የእርሳስ ነዳጅ ከዓለማችን መወገዱን ተከትሎ በልብ፣ በካንሰር እና በስትሮክ በሽታ በየዓመቱ ህወታቸቀው ሊያልፍ ይችሉ የነበሩ አንድ ሚሊዮን ሰዎችን መታደግ እንደሚቻል የሚናገሩት የተባበሩት መንግስታት ዋና ፃሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ይህ የአለም አቀፍ ስኬት ሌሎች በምድራችን ላይ ያንዣበቡ ከባድ ስጋቶችን በህብረት መቀርፍ እንደምንችል የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡
ምንጭ፡ ቢቢሲ
https://www.bbc.com/news/world-58388810
ሉሲ እንድትገኝ ያስቻለው ተመራማሪ አረፈ
================
እውቁ የስነ ምድር ባለሙያና በሀገራችን ኢትዮጵያ አፋር ውስጥ ያለው የሀዳር ሸለቆ አፈጣጠርን በማግኘት ለአውስትራሎፒቲከስ አፋሬንሲስ ወይም በሌላ ስሟ ሉሲ መገኘት ትልቅ አስተዋፅዖ ያደረገው ሞውሪስ ታይብ በ86 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

ሞውሪስ ታይብ ከ86 ዓመት በፊት ነበር በአውሮፓውያኑ ወርሀ ሐምሌ 1935 ቱኒዚያ ውስጥ የተወለዱት፡፡ የወጣትነት ጊዜያቸውንም እዚሁ አህጉራችን አፍሪካ ውስጥ ከነጋዴ አጎታቸው ጋር በመዘዋወር ነበር ያሳለፉት፡፡ በኋላም ወደ እናታቸው ሀገር ፈረንሳይ በማምራት በስነ ምድር የዶክትሬት ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡

ሞውሪስ በአውሮፓውያኑ 1968 አሰሳ ላይ ባሉበት ወቅት ሀዳር ሸለቆ በሚባለው ስፍራ ላይ የቀንድ አውጣ ቅሪትን ያገኛሉ፡፡ ይህም ቦታው ለቴክቶኒክ ፕሌቶች መገናኛ ካለው ቅርበት አንፃር ሌሎች በርካታ ቅሪቶችን ምናልባትም ጥንታዊ የሰው ልጅ ቅሪቶችንም ይይዝ ይሆናል ብለው እንዲጠረጥሩ አድርጓቸዋል፡፡ በዚህም ሳብያ ፓሊዮአንትሮፖሎጂስቶች (የጥንታዊ ሰው የሰውነት አካሎች እድገት ተመራማሪዎች) ቦታውን እንደዲመረምሩት ጥሪ አደረገላቸው፡፡ ከዚያም ከ4 ዓመታት በኋላ በ1972 ዓለም አቀፍ የአፋር ጥናት አሰሳን (IARE) ቡድንን በመመስረት አካባቢውን መመርመር ተያያዘ፡፡ ታድያ ከሁለት ዓመታት የጥናት ጉዞ በኋላ በሰው ልጅ የዝግመተ ለውጥ ጥናት መስክ እጅጉን ጠቃሚ ከሚባሉ ግኝቶች መካከል የሆነውን የሉሲ ቅሪተ አካል ከቡድኑ አስተባባሪዎች፣ እንዲሁም ከፓሊዮአንትሮፖሎጂስቶቹ ዶናልድ ጆንሰን እና ኢቭ ኮፐንስ ጋር በመሆን ሊያገኝ ችሏል፡፡

ከ2.9 እስከ 3.9 ሚሊዮን ዓመት እድሜ እንዳለው የሚገመተው 52ቱ የሉሲ አፅም ስብርባሪ በተገኙበት ወቅት ሞውሪስ እና ኢቭ በዶናልድ የመስክ ጥናት ቡድን ስር ሆነው ይሰሩ ነበር፡፡ ግኝቱ ከወገብ በላይ ያለው የሉሲ ክፍል አነስተኛ አንጎል እንዳላትና ከጦጣ ዝርያዎች ጋር እንደምትመሳሰል ሲያሳይ ከወገብ በታች ያለው ክፍሏ ግን በሁለት እግሯ የምትራመድ ስለመሆኗ አመላክቷል፡፡ ታድያ በወቅቱ “ሉሲ ኢን ዘ ስካይ ዊዝ ዳይመንድስ” የተሰኘው በዝነኛው የቢትልስ ባንድ የተቀነቀነ ሙዚቃ በካምፑ በስፋት ይደመጥ ስለነበር ሉሲም ከዚህ ሙዚቃ መነሻነት ስያሜዋን ልታገኝ ቻለች፡፡

የቅርብ ጓደኛው እና የስራ አጋሩ ዶናልድ ጆንሰን እንደሚለው ሞውሪስ በአፋር ኢትዮጵያ ያደረገው አሰሳ በቀጣይ በርካታ ባለሙያዎች የእርሱን ዱካ ተከለትለው በስፍራው ምርምር እንዲያደርጉ አድርጓል፡፡ ይህም 6 ሚሊዮን አመታትን የሚዘረጋው የአፋር የሰው ልጅ ታሪክ ዳራ በስፋት እንዲጠናና የኋላ ኋላም በርካታ ጥንታዊ ቅሪቶች ከስፍራው እንዲገኙ ማስቻሉን ዶናልድ ይናገራል፡፡

ምንጭ፤ ዘ ሳይንቲስት
ለተጨማሪ፤ https://www.the-scientist.com/news-opinion/maurice-taieb-geologist-who-discovered-lucy-site-dies-at-86-69134?utm_content=178244671&utm_medium=social&utm_source=twitter&hss_channel=tw-18198832
ትዊተር ለተጠቃሚዎቹ ገቢ ማስገኛ ስርዓት አዘጋጀ
*****************************************
****
ትዊተር የተባለው የማህበራዊ ሚዲያ አማራጭ ሱፐር ፎሎውስ የተሰኘ ብዙ ተከታይ ያላቸው ሰዎች ተከታዮቻቸውን እንደ ገቢ ምንጭ የሚጠቀሙበትን ስርዐት መዘርጋት ማሰቡን ይፋ አድርጓል፡፡ በተለይም በተለያዩ ዘርፎች ከዋክብት የሆኑና ተወዳጅ የሆኑ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተከታይ ያላቸው በመሆኑ ትዊተር እነዚህን ሰዎች አላማ አድርጎ የክፍያ ስርዓቱን ዘርግቷል፡፡
ለምሳሌ ሜካፕ አርቲስቶችና የስፖርት ተንታኞች ‹ከመጋረጃ ጀርባ› የሚባሉ ሁነቶችን ለተከታዮቻቸው ከ3 እስከ 10 ዶላር በሚደርስ ዋጋ እንዲያቀርቡ ሁኔታወችን ትዊተር አመቻችቷል፡፡ በሱፐር ፎሎው የትዊተር ተጠቃሚዎችና ብዙ ተከታይ ያላቸው ሰዎች ለተከታዮቻቸው የሚቀርቡ የተለያዩ ውይይቶችን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን በዚህም ገቢ ማግኘት ይችላሉ፡፡
እንደ ትዊተር መረጃ ከሆነ እንዲህ አይነት እድሎች ሊኖሯቸው የሚችሉ ተጠቃሚዎች አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ሙዚቀኞች፣ ጸሐፊዎች፣ የውበት ሙያተኞችና የመሳሰሉ ታዋቂ ሰዎች ናቸው፡፡ አሁን ላይ ትዊተር አዲሱን ስርዓት በመሞከር ላይ ሲሆን በሰሜን አሜሪካ የተወሰኑ የትዊተር ፈጣሪዎችን (creators) ወደ ስራ አስገብቷል፡፡ ሌሎች የአፕል ሞባየይልን የሚጠቀሙ የትዊተር ተጠቃሚዎች ሱፐር ፎሎውን በመጭዎቹ ሳምንታት ሊጠቀሙ እንደሚችሊ ተነግሯል፡፡
ትዊተር አንድ ሰው ከተከታዮቹ ከሚያገኘው ከ3 በመቶ በላይ እንደማይወስድ የተናገረ ሲሆን ይህም አንድ ተጠቃሚ በተዘረጋው ፕላት ፎርም 50 ሺህ ዶላር እስኪያገኝ ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡ መሰረቱን በሳንፍራሲስኮ ያደረገው ካምፓኒ ከ50 ሺህ በኋላ ድርሻውን ወደ 20 በመቶ እንደሚሳድግም አሳውቋል፡፡ በዚህም በአሁኑ ሰዓት 200 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ድርጅት ብዙ ማስታወቂያዎችን ሳይሰራ ገቢውን ማሳደግ የሚያስችለው አሰራር መዘርጋቱ ተነግሯል፡፡
ምንጭ techxplore
ለተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/
2021-09-twitter-star-users-money-subscriptions
.html
ቻይና 1 ኪ.ሜ የሚረዝም የህዋ ላይ መጓጓዣ ልትገነባ ነው?
==================
በተለያዩ የሆሊውድ ሳይንሳዊ ልብወለድ ፊልሞች ላይ እጅግ ግዙፍ የሆኑ የህዋ ላይ መጓጓዣ ወይም ስፔስሺፖችን አይተናል፡፡ ታድያ እነዚህን ግዙፍ የህዋ ላይ መጓጓዣዎች ከፊልምም ባሻገር እውን እንዲሆኑ የሚያስችል እንቅስቃሴ በቻይና ተጀምሯል፡፡ ሀገሪቱ 1 ኪ.ሜ የሚረዝም የህዋ ላይ መጓጓዣን መስራት ስለሚቻልበት መንገድ ጥናት ጀምራለች፡፡
ስራውን አስመልክቶ ይፋ የተደረገው ፅሁፍ እንዳመላከተው ይህ ግዙፍ የህዋ ላይ መጓጓዣ ወደፊት የህዋ ሀብትን ለመጠቀም፣ ድብቁን የዩኒቨርስ ከባቢ ለማሰስ እንዲሁም ረዘም ላለ ጊዜ ለመኖር የሚያገለግል ነው፡፡ አሁን ላይ መጓጓዣውን አስመልክቶ 2.3 ሚሊዮን ዶላር የሚያስወጣ የአዋጭነት ጥናት ለማከናወን ሲታቀድ ተመራማሪዎችም ወደ ህዋ ተልኮ ለግንባታው የሚውለውን ግብዓት በሚቀንስ መልኩ ቀለል ያለ ንድፍ እንዲሰሩ ይፈለጋል፡፡
ግን ይቻላል?
ይህን የሚያክል የህዋ ላይ መጓጓዣ መስራቱ በሳይንሳዊ ልብ ወለድ ፊልሞች ላይ ብቻ የሚሳካ ነገር ቢመስልም የዘርፉ ተመራማሪዎች ግን ከሳይንስ አንፃር እንዳይሳካ የሚያደርግ ተግዳሮት እንደሌለው ይገልፃሉ፡፡ ሆኖም በእንዲህ አይነት ግንባታ ላይ አንዱ ተግዳሮት ከስራው ግዝፈት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የምህንድስና ስራ ነው፡፡ ሌላውና ትልቁ ተግዳሮት ግን የወጪው ጉዳይ ነው፡፡ በተለይም የግንባታ ቁሳቁሰሶችን ወደ ህዋ ማጓጓዙ ሲበዛ ውድ ነው፡፡ ለምሳሌ ወደ ጎን 110 ሜትር የሚረዝመው ዓለም አቀፉ የህዋ ምርምር ጣብያን (ISS) ለመገንባት 100 ቢሊዮን ዶላር ፈጅቷል፡፡ አዲሱ እቅድ ከዚህ 10 እጥፍ የሚረዝም አካል መገንባት መሆኑን ከግምት ስናስገባ ወጪውን ጭንቅላት የሚያዞር ያደርገዋል፡፡ የህዋ ላይ ማጓጓዣው ሰዎችን እንዲይዝ ተደርጎ የሚሰራ ከሆነ ደግሞ ወጪውን ይባስ ያንረዋል፡፡
ነገር ግን ወጪው በዋናነት የህዋ ላይ መጓጓዣው እንዲገነባ ከታሰበበት ንድፍ ጋር ይያያዛል፡፡ የግንባታ ስልቶችም እንዲሁ ወጪውን ሊቀንሱት ይችላሉ፡፡ በተለይ በ3ዲ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ከመሬት ውጪ የሚገኝ ግብአትን ተጠቅሞ መዋቅሩን መስራት የተለመደው የተፈበረኩ አካላትን ከመሬት አስልኮ እዚያው ህዋ ላይ የመገጣጠም ስልትን ሊቀይር ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ ከመሬት አንፃር ጨረቃ ላይ ያለው የስበት ኃይል አነስተኛ በመሆኑ ከዚያ ግብዓቶችን አስፈንጥሮ መውሰድ ቀለል ያለ ነው፡፡
ከግንታው ባሻገር ግን ይህን አይነት ግዙፍ አካል ለሌሎች ችግሮችም ተጋላጭ ነው፡፡ በዚህ መጠን የገዘፈ የህዋ ላይ መጓጓዣ በሚንቀሳቀስበት እና ከሌሎች መሰል መጓጓዣዎች ጋርም በሚነካካበት ወቅት የሚገጥመው ኃይል በመጓጓዣው ውስጥ በቶሎ የማይቆም ከፍተኛ መንቀጥቀጥ እንዲነሳና መጓጓዣው እንዲጣመምም ጭምር ሊያደርገው ስለሚችል ይህን መቆጣጠርያ ቴክኖሎጂ ያስፈልገዋለ፡፡ በተጨማሪም የህዋ ላይ መጓጓዣው ከመሬት ርቆ የሚንሳፈፍበት ርቀትም እንዲሁ የራሱ ተግዳሮት አለው፡፡ መጓጓዣው ወደ ምድር በቀረበ ቁጥር የሚጎትተው ኃይል እያየለ ስለሚመጣ እራሱን ከዚህ ለማውጣት ሞተሮቹን ተጠቅሞ በተቃራኒ አቅጣጫ ራሱን መግፋት አለበት፤ ይህ ደግሞ ከፍተኛ ነዳጅን ይጠይቃል፡፡ በሌላ መልኩ ከምድር ርቆ በሄደ ቁጥር ወጪውም በጣም እየናረ ይመጣል፡፡ በዚያ ላይ ከከባቢ አየር በራቁ ቁጥር ጨረሩም ከፍተኛ እየሆነ መምጣቱ በመጓጓዣው ውስጥ ሰዎች ካሉ ለእነርሱ አደገኛ ይሆንባቸዋል፡፡
ምንጭ፤ ላይቭ ሳይንስ
ለተጨማሪ፤ livescience.com/mega-spaceship-china-proposal.html
በውሃ ላይ ማኮብኮብ የሚችለው የቻይና አውሮፕላን
*******************************
የቻይናው AG600 የተሰኘ አዲስ አውሮፕላን ከመሬት ወደ ውሃ አካላት ማረፍ የሚችልና ከውሃ አካላት መነሳት የሚችል ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡ አውሮፕላኑ በመነሻነት በአስቸጋሪ የአየር ጠባይ ሁኔታዎች ውስጥ በረራዎችን ለማድረግ ታልሞ የተሰራ ሲሆን በቻይና 13ኛው አለማቀፍ የአቪየሽን ኢግዚቪሽን ላይ ከምድር ወደ ውሃ እንዴት ማረፍ እንደሚችል የሚያሳይ ይሆናል፡፡
አውሮፕላኑን ያበለጸገው የቻይይና አቪየሽን ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን እንዳወጣው መረጃ አውሮፕላኑ ያለውን እሳት አደጋን የመቆጣጠር ብቃት በበረራው ወቅት ያሳያል ተብሏል፡፡ ለአውሮፕላኑ የተሰጠው የኮድ ስምም በቻይና የአደጋ መከላከል ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ጥቅም ያለውን ቁስ ምክንያት ያደረገ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ በዚህም አውሮፕላኑ በእሳት አደጋ፣ የባህር ላይ አደጋ እና ሌሎች ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋ ሲያጋጥም አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ያስችላል፡፡
የመጀመሪያ በረራውን በ2017 በስኬት ያጠናቀቀው አውሮፕላኑ ለግድብ ከተከማቸ ውሃ (a water reservoir) በ2018 አኮብኩቦ መነሳት የቻለ ሲሆን በ2020 ደግሞ መነሻውን ከውቅያኖስ ላይ አድርጎ በረራውን አካሂዷል፡፡ የዚህ አመት የቻይና የበረራ ኤግዚቢሽን ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 3 ድረስ በደቡባዊ የቻይና ክፍል ጓንግዶንግ እንደሚከናወን ታውቋል፡፡
በዝግጅቱም ከ40 ሀገራና አካባቢዎች የተውጣጡ 700 የሚደርሱ ካምፓኒዎች በቀጥታም በመስመር ላይም እንደሚሳተፉ ተነግሯል፡፡ ለአብነትም አሜሪካን ጨምሮ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ሩሲያ ካናዳ እና ብራዚል ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡
የቻይናው አቪየሽን ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን እስካሁን 150 የሚደርሱ የበረራ ምርቶችን በብቸኝነት መስራት የቻለ ሲሆን በዚህኛው ኤግዚቢሽን ከ AG600 በተጫማሪ AC-series ሄሊኮፕተሮችና AG-series ሌሎች አውሮፕላኖች ትእይንቶችን ያቀርባሉ፡፡
ምንጭ Xinhua net
ለተጨማሪ ንባብ http://www.news.cn/english/2021-09/03/c_1310166200.htm
የጤና ባዮቴክኖሎጂ በዘመናዊ የጤና ጥበቃ ስርዓት
የጤና ባዮቴክኖሎጂ በዘመናዊ የጤና ጥበቃ ስርዓት
==========================
የጤና ባዮቴክኖሎጂ ከሥነ ሕይወት አካላትና ሂደት ጋር የተያያዘና ከዚያ የሚገኝን ዕውቀት፤ ዘዴ ወይም ውጤት ለጤና አገልግሎት የማዋል ትግበራ ነው፡፡ ዘመናዊ የጤና ባዮቴክኖሎጂ የዘረመል ምንነት ከተገለጠበት ከ1960ዎቹ ጀምሮ በተለይም በ1970ዎቹና በ1980 ዎቹ ውስጥ በፍጥነት እያደገ የመጣ ነው።፡ አዳዲስ መድኃኒቶች፤ ፈጣን የመመርመሪያ ዘዴዎች፤ ክትባቶችና የተሻሻሉ የሕክምና መሣሪያዎችን አስገኝቷል። በዚህ የምርምር ዘርፍ አዳዲስ የዕውቀት አድማሶች እየተከፈቱ በመሄዳቸው የባዮቴክኖሎጂ ግስጋሴ እየጨመረ እንደሚሄድና የነገውን የጤና አገልግሎት ባህርይ የሚወስን ሚና እንደሚኖረው ይገመታል።

የጤና ባዮቴክኖሎጂ ልማት የሕዝብን ጤንነት በማሻሻል በተዘዋዋሪ ከሚያስገኘው የኢኮኖሚ አቅም ሌላ በቀጥታም ለኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዖ ያደርጋል። የወቅቱ የሕክምና ደረጃ የሚጠይቃቸው የበሽታ መመርመሪያዎች፣ መድኃኒቶች፣ ክትባቶች፣ ማከሚያዎችና የመሳሰሉት የጤና ባዮቴክኖሎጂ ምርት ውጤቶች ለሕዝብ ጤና አገልግሎት መዳረስና ጥራት ሲባል የግድ አስፈላጊ ናቸው።

የጤና ባዮቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት ለሕዝብ ጤንነት መሻሻል ፤ ለጤና ዕውቀት አድማስ መስፋትና ለቀጣይ ግኝቶች መሠረት ለመጣል፤ የሕዝብን ደህንነትና የአገርን ህልውና ለመጠበቅ፤ ለተለያዩ የልማት ዘርፎች (ግብዓት በመሆን የሚያጠናክር) አቅም ለመፍጠር የጎላ ሚና እየወሰደ የሚቀጥል፣ ከሌሎች የባዮቴክኖሎጂ ዘርፎች ጋር መተኪያ የሌለው የዘመኑ ሕብረተሰብ የኢኮኖሚና የማሕበረሰብ ብልፅግና መሰረት እየሆነ የመጣ መሣሪያ ነው።

የጤና ባዮቴክኖሎጂ የሕዝብን ጤንነት በማሻሻል በተዘዋዋሪ ከሚያስገኘው የኢኮኖሚ አቅም ሌላ በቀጥታም ለኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዖ ያደርጋል። በሽታዎችን በተሻለ ፍጥነትና በተለይም የሕክምና አገልግሎት ባልተዳረሰባቸው ቦታዎች ተደራሽ በሆነ ዘዴ አጥንቶ ማከም መቻል ስርጭትን በመቀነስ፣ ወጪን በመቆጠብና አገልግሎቶችን በማስፋት የኢኮኖሚ አቅምን መገንባት፤ በክትባት፣ በመድኃኒት፣ በሕክምና ዘዴ መሻሻልና በመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎችን ወደ አገራችን አስገብቶ በማላመድ በሚመች መልክ አዘጋጅቶ በመጠቀም ህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግ የተሻለ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ የማድረግ አስተዋፅዖ ከፍተኛ ነው።
https://www.wgu.edu/blog/medical-biotechnology-advancements-ethics111.html#close
የጳጉሜ አመጣጥና ምንነት
የጳጉሜ አመጣጥና ምንነት
***************************
ጳጉሜ ማለት ተረፍ፣ ትርፍ፣ ተውሳክ፣ ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ከመስከረም አንድ እስከ ነሐሴ ሰላሳ ድረስ ሰላሳ ሰላሳ እለታት ያሏቸው 12 ወራት አሉ፡፡ በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር መሰረት አንድ እለት የሚባለው 24 ሰዓታትን የያዘ ነው፡፡ 12ቱ ቀን ሲባል 12ቱ ደግግ ሌሊት ይባላል፡፡ ከዚህ ከሀያ አራት ሰዓት ተጫማሪ ወይም ትርፍ የሆኑ 52 ካልኢትና 31 ሳልሲት አሉ፡፡ አንድ ካልኢት ማለት 24 ሴኮንድ ማለት ነው፡፡

በመሆኑም 52 ካልኢትን በ24 ስናባዛው 1248 ሴኮንድ ይሆናል፡፡ 1248 ሴኮንድ ደግሞ 20 ደቂቃ ከ48 ሴኮንድ ይሆናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አንድ ሴኮንድ 2.5 ሳልሲት ነው፡፡ ከአንድ ቀን የሚተርፈውን 31 ሳልሲት ወደ ሴኮንድ ስንቀይረው 12.4 ሴኮንድ ይሆናል በአጠቃላይ በአንድ ቀን ውስጥ 21 ደቂቃ ከ0.4 ሴኮንድ ትርፍ አለ ማለት ነው፡፡ ይህ 21 ደቂቃ ከ0.4 ሴኮንድ የእለት ትርፍ በመሆንና በመጠራቀም ጳጉሜን ይወልዳል፡፡ በዚህም ምክንያት ነው አጭሯ ወር ትርፍ ተብላ የተጠራችው፡፡

ይህን በወር የሚተርፈውን ለማግኘት በ30 ማባዛት በአንድ ወር ውስጥ 10 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ይተርፋል፡፡ ይህ በ3 ወር ውስጥ 30 ሰዓት ከ90 ደቂቃ ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ አንድ እለት ከ7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ይሆናል፡፡

ከመስከረም 1 እስከ ህዳር 30 አንድ እለት ከ7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ትርፍ
ከታህሳስ 1 እስከ የካቲት 30 አንድ እለት ከ7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ትርፍ
ከመጋቢት 1 እስከ ግንቦት 30 አንድ እለት ከ7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ትርፍ
ከሰኔ 1 እስከ ነሐሴ 30 አንድ እለት ከ7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ትርፍ

በዚህም 4 እለት 28 ሰዓት 120 ደቂቃ በአመት ይተርፋል ማለት ነው፡፡ ሰዓትና ደቂቃውን ስንደምረው 30 ሰዓት ይሆናል ይህም አንድ እለት ከስድስት ሰዓት ነው፡፡ አንዱ እለት ጳጉሜ 5ትን የሚሰጥ ሲሆን ቀሪው ስድስት ሰዓት ደግሞ በ4 ዓመት ውስጥ 24 ሰዓት በመሆን ጳጉሜ ስድስትን ይሰጠናል፡፡

በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር አንድ አመት የሚባለው 365 እለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልኢት ነው፡፡ 15 ኬክሮስ ማለት ስድስት ሰዓት ማለት ነው፡፡ በየ 4 ዓመቱ አንድ እለት እየሆነች ጳጉሜ ስድስትን የምታመጣ ናት፡፡ ቀሪዋ 6 ካልኢት 144 ሴኮንድ ማለት ናት፡፡ ይህችም በ600 ዓመት ውስጥ 24 ሰዓት የምትሆን ናት፡፡ እንዲህ ቢባልም ጳጉሜ 7 ታስባ የምትውል እንጂ የማትቆጠር እንደሆነች የዘርፉ ምሁራን ያስተምራሉ፡፡

ምንጭ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የዘመን አቆጣጠር ትምህርት