TechIn2
1.16K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ለምድር ቀርባ የምታልፈው አስትሮይድ
***************
ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 15 አንድ አስትሮይድ ለምድር ቀርባ እንደምታልፍ ተገለፀ፡፡ 1.4 ኪ.ሜ ስፋት ያላት አስትሮይዷ በሰዓት 94,208 ኪ.ሜ የምትምዘገዘግ ሲሆን ለምድር 3,427,445 ኪ.ሜ ቀርባ እንደምታልፍ ይጠበቃል፡፡

2016ኤጄ193 የተሰኘችው ይህች አስትሮይድ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12፡10 ሲል ነው በምድር በኩል የምታልፈው፡፡ የአሜሪካኑ ህዋ ምርምር ተቋም ናሳ አስትሮይዷ ምድር ላይ ጉዳት የማድረስ አቅም ያላት ሲል የገለፃት ሲሆን የተቋሙ ተመራማሪዎችም ከዛሬ አንስቶ እስከ መጪው ሰኞ ድረስ እንቅስቃሴዋን እየተከታተሉ ይቆያሉ፡፡ ምንም እንኳን የአስትሮይዷ የእንቅስቃሴ ምህዋር ሲታይ ምድር ላይ ጉዳት የምታደርስ አለመሆኗ ቢታወቅም ጉዳት የማደረስ አቅም ያላት ተብላ የተቀመጠችው በህዋ ምርምር እይታ አስትሮይዷ ለምድር ቀርባ የምታልፍበት ርቀት ቅርብ ነው ተብሎ ስለሚታወቅ ነው፡፡

የአስትሮይዷ ስያሜ የህዋ ተመራማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ከተመለከቷት ወቅት ማለትም ከአውሮፓውያኑ 2016 ጋር ተያይዞ የተሰጣት ነው፡፡ ተመራማሪዎቹ በአሜሪካኑ የሄላካላ ኦብዘርቫቶሪ ውስጥ ባለው ፓኖራሚክ ሰርቬይ ቴሌስኮፕ እና ራፒድ ሪስፖንስ ሲስተም አማካኝት ነው የተመለከቷት፡፡ እንደ ናሳ ከሆነ አስትሮይዷ ሞላላ ቅርፅ ባለው ምሕዋሯ ላይ ሆና ፀሐይን ለመዞር 2,160 ቀናት ወይም 5.91 ዓመታት ይፈጁባታል፡፡ በተጨማሪም ለመሬት ቀርባ የምትገኝበት ርቀር ጨረቃ ካላት ርቀት ጋር ሲነፃፀር በ8.9 እጥፍ የላቀ ነው፡፡

የአስትሮይዷን መጠን በንፅፅር ለማቅረብ ያህል በዱባይ ከሚገኘው የዓለማችን ረጅሙ ህንፃ ቡርጅ ከሊፋ በግማሽ፣ ከፓሪሱ ኤፍል ማማ 4.5 እጥፍ እንዲሁም እዚሁ አዲስ አበባ እየተገነባ ካለው የንግድ ባንክ ህንፃ ደግሞ በሰባት እጥፍ የምትልቅ ናት፡፡

ምንጭ፤ TECH2
ለተጨማሪ፤ https://www.firstpost.com/tech/science/asteroid-bigger-than-burj-khalifa-will-pass-by-earth-on-21-august-9858991.html
ደማችን ለመከላከያ ሰራዊታችን
*******************
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ቤተሰቦች “ደማችን ለመከላከያ ሰራዊታችን” በሚል መርህ ዛሬ ነሐሴ 14 2013 ዓ.ም የደም ልገሳን አከናውነዋል፡፡ ከኃላፊዎች አንስቶ ቁጥራቸው የበዛ የተቋሙ ቤተሰቦች በከፍተኛ ተነሳሽነት በተሳተፉበት በዚህ መርሀ ግብር ለመከላከያ ሰራዊቱ ይሆን ዘንድ በርካታ ዩኒት ደም መሰብሰብ ተችሏል፡፡

ከዚህ ቀደም ለተከታታይ ዓመታት የቴክኖለሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ቤተሰቦች ደማቸውን ለወገን በመለገስ ለተጎዱ ደራሽነታቸውን ሲያሳዩ የቆዩ ቢሆንም የዛሬው የደም ልገሳ መርሀ ግብር ሲካሄድ ግን አሁን ላይ የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊቱ ሀገራዊ ግዴታ ውስጥ ባለበት ሰዓት በመደረጉና ልገሳውም ይህን ታሳቢ በማድረግ የተከናወነ መሆኑ መርሃ ግብሩን ልዩ አድርጎታል፡፡ በዚህም ለወትሮ ከነበረውም ከፍ ባለ መልኩ የለጋሽ ቤተሰቦችን ቀልብ በመሳብ በተሻለ ቁጥር ተሳታፊ አድርጎ አልፏል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ቤተሰቦች ከደም ልገሳ ባሻገርም በተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ በመሰማራት ሀገርን የሚጠቅም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ለዓብነትም የተቸገሩ ወገኖችን ከመርዳት አንስቶ እስከ አረንጓዴ ልማት ስራዎች ይጠቀሳሉ፡፡
ኤልጂ የ6ጂን ሲግናሎችን ታይቶ በማይታወቅ ርቀት ማስተላለፍ ቻለ
ኤልጂ የ6ጂን ሲግናሎችን ታይቶ በማይታወቅ ርቀት ማስተላለፍ ቻለ
====================
የ5ጂ ቴክኖሎጂ ገና ባደጉት ሀገራት እንኳን በቅጡ ባልተዘረጋበት በአሁኑ ወቅት የተለያዩ የኮምዩኒኬሽን ኩባንያዎች የቀጣዩ ትውልድ ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የሆነው 6ጂን ለመስራት በጥድፊያ ላይ ናቸው፡፡ ከነዚህ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ግዙፉ የኮሪያ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ኤልጂ ከጀርመኑ የምርምር ተቋም ፍራንሆፈር ጌዜልሻፍት ጋር በመተባበር ለቴክኖሎጂው አንድ እምርታ በሆነ መልኩ የ6ጂ ሲግናሎችን በ100 ሜትር ርቀት ውስጥ ማስተላለፍ ችሏል፡፡

የ6ኛው ትውልድ የኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ በራሱ እጅግ በጣም ፈጣን ከሆነው ከ5ጂ ጋር እንኳን ሲነፃፀር መረጃን በበይነ መረብ የማስተላለፍ ፍጥነቱ በ50 እጥፍ የላቀ ሲሆን የመረጃዎች የመዘግየት ልኬትንም (latency) በ10 በመቶ እንደሚቀንስና የሚላከው መረጃ ጥራትንም እንደሚያሳድግ ይጠበቃል፡፡ እነዚህ የቴክኖሎጂው እምርታዎች ተደማምረው ታድያ በቤት ውስጥም ሆነ በስራ ቦታ ከበይነ መረብ ጋር ያለውን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሳድጉት ተገምቷል፡፡

ሲግናሎቹ በሚተላለፉበት ወቅት የኃይል እጥረት ስለሚያጋጥማቸውና በዚህም ምክንያት የሚጓዙት ርቀት የተገደበ መሆኑ የ6ኛው ትውልድ ቴክኖሎጂን እውን ማድረግ ቀድመው ከነበሩት ትውልዶችም በላይ አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ በዚህ ሳብያ ቴክኖሎጂውን በበቂ ሁኔታ አድጎ ለገበያ ሲውል ለማየት ቢያንስ እ.አ.አ ከ2025 እስከ 2029 ድረስ ወይም ከዚያ በላይ መጠበቅ እንደሚገባ የባለድርሻዎች ግምት ነው፡፡

ኤልጂ ከጥቂት ወራት በፊት ሌላኛው ግዙፍ ኮሪያዊ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሳምሰንግ የ6ጂ ሲግናሎችን በ15 ሜትር ርቀት ውስጥ በማስተላለፍ የያዘውን ክብረ ወሰን ነው አሁን ላይ ከአንድ ህንፃ ጣርያ ወደ ሌላኛው በማስተላለፍ በከፍተኛ መጠን ያሻሻለው፡፡ እንደ ኩባንያው ከሆነ ሲግናሎቹ ይህን ያህን ርቀት እንዲጓዙለት ያስቻለው ከፍራንሆፈር ጌዜልሻፍት ጋር በመሆን ያበለፀገውና በ155 እና 175 ጊጋ ሀርዝ መካከል ባለ ፍሪኩዌንሲ ውስጥ እስከ 15 ዴሲቤል ሚሊዋት ድረስ የሚለኩ የተረጋጉ ሲግናሎችን መላክ የሚያስችለው አዲስ አምፕሊፋየር ነው፡፡

በተጨማሪም የጋራ ጥናት ቡድኑ እንደተቀባዩ አቀማመጥ መተላለፊያዎችም እንዲለዋወጡ የሚያስችለው የአዳፕቲቭ ቢምፎርሚንግ ሰርተው ያሳዩ ሲሆን የተለያዩ ሲግናሎችን አቀናጅቶ ወደሚፈለገው አንቴና ለመላክ የሚያስችል ስልትንም ተጠቅመዋል፡፡
ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-08-lg-6g-transmission-meters.html
የተገለበጡ ክንፎች ያሉት ተዋጊ ጀት
***********************
በአለማችን የአቪየሽን ታሪክ ውስጥ በተለያየ አጋጣሚ ለተለያየ አገልግሎት አስደናቂ ቅርጽና ቴክኖሎጂ ያላቸው አውሮፕላኖች እንደተሰሩ ይታወቃል፡፡ የዘርፉ ሰዎች የናሳውን የውጊያ ጀት የሚወዳደር የለም ይላሉ፡፡ ይህም Grumman X-29 የተሰኘው ተዋጊ ጀት ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ አየር ላይ የወጣው በ1984 ዓም ነው፡፡ ይህንን ተዋጊ ጀት ተመራማሪዎች ከፍተኛ ምርምር የተደረገበትና እንዲህ ነው ተብሎ በቀላሉ የማይገለጥ ኤሮዳይናሚክስ አውሮፕላን ነው ይሉታል፡፡

በናሳው የአርምስትሮንግ በረራ ማዕከል የታሪክ ተመራማሪ የሆኑት ክርስቲና ግሌዘር ስለ አውሮፕላኑ የበረራ አቅጣጫውን በሰከንድ ለ40 ያክል ጊዜ መቀያየር የሚችል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ይህንንም ሲያደርግ ያለምንም ዲጂታል የበረራ ኮምፒውተር እንደሆነ ታውቋል፡፡

ከመደበኛው የክንፍ አቀማመጥ በተቃራኒው የሆነ ክንፍ ያላቸው አውሮፕላኖች በጣም ጥቂት ሲሆኑ X-29 ግን ብቸኛው አይደለም፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1944 የበረረው የጀርመን ቦምብ ጣይ አውሮፕላንም በተመሳሳይ የተገለበጡ ክንፎች የነበሩት ነው፡፡

ይህ የአውሮፕላን አይነት ከ1984 እስከ 1992 ድረስ 422 በረራዎችን ለምርምር ያደረገ ሲሆን በኋላ ላ ግን ቅርስ ሆኖ ለታሪክ እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡

ምንጭ cnn
ተጨማሪ ንባብ http://edition.cnn.com/style/article/grumman-x-29-nasa-darpa-fighter-plane/index.html?utm_term=link&utm_medium=social&utm_source=fbCNNi&utm_content=2021-08-22T14%3A38%3A05&fbclid=IwAR1zGbsor8eNclEJH5nDqIxWXqH9f0ZdutAy3u5QPK2e7Zdm2G-J2yfX4DQ
ከአልማዝ የጠነከረ መስታውት ተሰራ
================
በቻይናው የያንሸን ዩኒቨርሲቲ ዘንድ በሚገኙ ምሁራን የሚመራ አንድ ዓለም አቀፍ የተመራማሪዎች ቡድን ለየት ያለ የኬሚካል መዋቅር እና የምርት ሂደትን ተጠቅሞ በጥንካሬው ከተፈጥሮ አልማዝ የሚስተካከል መስታውት መስራቱን አስታውቋል፡፡ ተመራማሪዎቹ ኤኤም-3 (AM-III) ብለው የሰየሙት ይህ መስታውት በጥንካሬው ከአልማዝ ውጭ ተወዳዳሪ የሌለው፡፡

በተደራጀ ውስጣዊ መዋቅሩ አማካኝነት ጥንካሬን ካገኘው ከአልማዝ አንፃር ለየት የሚለው ኤኤም-3 ይህን ጥንካሬውን ሊያገኝ የቻለው በሞለኪውል ደረጃ ባለው የተዘበራረቀ ትስስር ነው፡፡ መስታውቱን ለመስራት ተመራማሪዎቹ ፉለሪን የተባሉትን ባለ ሞላላ ቅርፅ የካርበን ሞለኪውሎችን 1,200 ዲ.ሴ በሚለካ ሙቀት አግለው እና ለሰዓታት ከፍተኛ በሆነው የ25 ጊጋፓስካል ግፊት ውስጥ እንዲሰባበሩ አደረጓቸው፡፡ ሆኖም ሂደቱ ከሚገባው በላይ ሄዶ ካርበኖቹ በተደራጀ አኳሀን የሚቀመጡ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ይህ የመስታውቱ ጥንካሬ የሚቀንስ እና የሴሚኮንዳክተርነት ይዘቱንም ሊያጣ ይችል ነበር፡፡ በዚህ ሂደት ነው ተመራማሪዎቹ ጥንካሬው ሲለካ ሌሎች ቁሶችን በመሰባበር ከሚታወቀው የተፈጥሮ አልማዝም በላይ ሆኖ የተገኘውን ይህን መስታውት ሰርተው ለማቅረብ የቻሉት፡፡

ታድያ ይህ የመስታውቱ ጥንካሬ በራሱ ስኬት ከመሆንም ባሻገር ጠንካራ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፓኔል እና ሴሚኮንዳክተሮች እንዲመረቱ በማስቻል የአረንጓዴ ኃይል ምርትን በማሳደግ እንቅስቃሴ ውስጥ የራሱን በጎ ሚና ይጫወታል ተብሎለታል፡፡

ምንጭ፤ ፊውቸሪዝም እና ኢንዲፔንደንት
ለተጨማሪ፤ https://futurism.com/the-byte/glass-strong-diamond እና https://www.independent.co.uk/news/science/china-strongest-glass-diamond-scientists-b1899243.html?utm_source=reddit.com
ከአልማዝ የጠነከረ መስታውት ተሰራ
አታላዩ እባብ
=======
አደገኛ መርዝ ያላቸው የራትል እባቦች ድንገተኛና ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ጭራቸውን የማንቀጥቀጥ ድምፅን በማሰማት የሰው ልጆችንም ሆነ ሌሎች እንስሳትን በእነርሱና እባቦቹ መካከል ካለው ርቀት ባነሰ በጣም የቀረቡ እንዲመስላቸው በማድረግ እንደሚያታልሉ አዲስ ጥናት ጠቆመ፡፡ በዋናነት በደቡብ እና ሰሜን አሜሪካ አህጉራት ውስጥ የሚኖሩትና ከግማሽ እስከ 2.5 ሜትር ርዝማኔ ያላቸው እነዚህ የእባብ ዝርያዎች ልክ አንደ መኪና ወደኋላ ሲነዳ ወደ አንድ አካል በተጠጋ ቁጥር የሚያወጣው የተቆራረጠ ድምፅ እየጨመረ እንደሚመጣው ሁሉ እነርሱም ድምጻቸውን ቀስ በቀስ በመጨመር በድንገት ከፍተኛ ፍጥነት ወዳለው አስደንጋጭ የመንቀጥቀጥ ድምፅ ይለውጡታል፡፡ ሆኖም ከመኪና በተቃራኒ እባቦቹ ይህን እየጨመረ የሚሄድ ድምፅ የሚያሰሙት ከሚቀርባቸው አካል ጋር በጣም ተቀራርበው ሳይሆን ምናልባትም ከአንድ ሜትር ርቀት በላይ ሆነው ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የማታለል ስራ እባቡ በሚያልፍ ሰው ከመረገጥ ወይም ለእርሱ እጅግ አስፈላጊ የሆነው መርዙን ከማባከን ይጠብቀዋል፡፡

በኦስትሪያው የግራዝ ዩኒቨርሲቲ የሚያገለግለው ቦሪስ ቻግናድ ከጥቂት ዓመታት በፊት በሙኒክ ቴክኒካል ዩኒቨርሱቲ ያለውን የራትል እባቦች መኖርያ በተመለከተበት ጊዜ እባቦቹ አንድ አካል በቀረባቸውና በራቃቸው ቁጥር የጭራ መንቀጥቀጥ ፍጥነታው እንደሚለዋውጡ መመልከት ከቻለ በኋላ ነው ወደዚህ ጥናት ያመራው፡፡ ከሌሎች የምርምር ባልደረቦቹ ጋር በመሆን 30 ዌስተርን ዳይመንድባክ ራትል እባቦችን (Crotalus Atrox) በሰው አምሳል የተሰራ ቁስ በሚንሸራተት ሀዲድ ላይ ሆኖ እንዲቀርባቸው በማድረግ እና በአንድ ስክሪን ላይ እያደገ የሚመጣ ጥቁር ነጥብን በማኖር ሙከራ አድርገዋል፡፡ በሁለቱም ሙከራዎች ወቅት እባቦቹ ጭራቸውን የማንቀጥቀጥ ድምፅ የሚያሰሙበትን ፍጥነት ቀስ በቀስ በሴኮንድ ወደ 40 መንቀጥቀጥ እያደገ የመጣ ሲሆን ከዚያም ይህ የጭራ መንቀጥቀጥ በድንገት በሴኮንድ ከ60 እስከ 100 መካከል በቋሚነት እንዲቆይ ሆኖ እንዲገኝ አድርገውታል፡፡

ከዚህ ሙከራ በኋላ የጥናት ቡድኑ የቨርቹዋል ሪያሊቲን በመጠቀም ሰዎችን የተለያየ ድምፅ በሚሰማበት የሳር ምድር እየተጓዙ እንዲመስላቸው የማድረግ ሙከራን አከናወነ፡፡ በሙከራው ላይ ተሳታፊዎቹ የሚሰሙት ድምፅ ለእነርሱ በጣም የቀረበ ሆኖ ሲሰማቸው የሚጫኑት ቁልፍ የተሰጣቸው ሲሆን በዚህም ተሳታፊዎቹ ለእባቡ የማታለያ የመንቀጥቀጥ ፍጥነት በቀላሉ ተሸውደው ታይተዋል፡፡ ምንም እንኳን ተሳታፊዎቹ የእባቡን የጭራ መንቀጥቀጥ ድምፅ የሰሙት ከአራት ሜትር አካባቢ ርቀት ላይ ቢሆንም በአንድ ሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ያህል ተሰምቷቸው ነበር፡፡

የጥናቱ ውጤት እባቦች ከሰው ልጆች እና ሌሎች እንስሳት ጋር ባላቸው ግንኙነት ውስጥ በአስደናቂ ሁኔታ የማስመሰል ችሎታን እያጎለበቱ መምጣታቸውን ያሳየ ነው ተብሎለታል፡፡

ምንጭ፤ ኒው ሳይንቲስት
ለተጨማሪ፤ https://www.newscientist.com/article/2287748-rattlesnakes-use-auditory-illusion-to-make-us-think-they-are-nearby/?utm_term=Autofeed&utm_campaign=echobox&utm_medium=social&utm_source=Twitter#Echobox=1629517576
አታላዩ እባብ
ታይታኒክ እንዴት ልትሰመጥ ቻለች
*********************************
አንድ አዲስ ጥናት ተይታኒክ የተባለችው መርከብ የሰመጠችው በበረዶ ግግር ምክንያት እንዳልሆነ አመለከተ፡፡ መርከቧ በሚያዚያ ወር 1912 ከሳውዝአምፕተን ወደ ኒዮርክ በፍጥነት ጎዞ በማድረግ ላይ ሳለች ካልታሰበ የበረዶ ግግር ጋር ተጋጭታ እንደሰመጠች ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ ከጊዜ በኋላ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ለመርከቧ መስመጥ ትክክለኛው መንስኤ ፍጥነቷ ወይም የበረዶ ግግር አይደለም የሚሉ ናቸው፡፡

ስለ ታይታኒክ በብዛት በመጻፍ የሚታወቁት አይርላንዳዊ ሴናን ሞሎኒ ለመርከቧ አደጋ መነሻ ምክንያት የሆነው በረዶ ሳይሆን እሳት ነው ይላሉ፡፡ ታይምስ ለተባው መጽሔት ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የታሪክ ጸሐፊ መርከቧ የሰመጠችው በእሳት፣ በረዶና ከፍተኛ ቸልተኝነት ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

መርከቧ ከወደቧ ብዙም ሳትርቅ ከከሰል ማንደጃው ውስጥ እሳት መቀጣጠል እንደጀመረ የሚናገሩት ሞሎኒ ይህ እሳት በመርከቧ የውስጠኛ ክፍል የሚገኝን 9 ሜትር የሚረዝም የብረት ምሰሶ እንደለበለበው የሚያሳዩ መረጃዎች መገኘታቸውን አስገንዝበዋል፡፡ ስለ መርከቧ መስመጥ አዲስ የተባለው መረጃም ከዚህ ግኝት ጋር የተያዘ ነው፡፡

ይህ እሳት የተነሳበት የመርከቧ ክፍል ደግሞ ከበረዶ ግግሩ ጋር በቀጥታ የተላተመው ክፍል እንደሆነ ይታመናል፡፡ እሳቱ የመርከቧን ተጋላጭ ክፍል አዳክሞት የነበረ በመሆኑ የበረዶው ግግር መርከቧን ሊጎዳት እንደቻለ ሞሎኒ እምነታቸውን አስረድተዋል፡፡ አክለውም እሳቱ ምንም እንኳን ከነመሻው የታወቀ ቢሆንም መርከቧ መነሳት ከነበረባት ሰዓት ለሁለት ጊዜያት ያክል በመዘግየቷ የተማረሩ ተጓዦች ለአደጋ ይጋለጣሉ በሚል ምክንያት ይፋ ሳይደረግ ተደብቆ ቆይቷል ብለዋል፡፡

ይህ የእሳት መላምት በ2004 በፕሮፌሰር ሮበርት ኢስንሀይ ከተሰራው ምርምር ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡ አሁን ላይ ብዙ የታሪክ ተመራማሪዎች መርከቧ ውስጥ እሳት መነሳቱን ቢያምኑም ይህ አዲስ በፎቶግራፍ የተደገፈ ግኝ ግን በትክክል እሳቱ የት ላይ እንደተነሳ እና ከመርከቧ መስመጥ ጋር እንዴት እንደሚገናኝ የሚያብራራ ነው፡፡

ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/editors-blog/new-evidence-suggests-the-titanic-wasnt-just-sunk-by-an-iceberg/?fbclid=IwAR1H04Cf4H2ltVP8J1aWEOJlazVOS6MXo95fjsj_oBGOszHP_0gsm-homi4
ታይታኒክ እንዴት ልትሰመጥ ቻለች
የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና የህፃናት የአእምሮ እድገት
የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና የህፃናት የአእምሮ እድገት
=======================
ባለንበት ክፍለ ዘመን የተሻለ የመረዳት እና የአስተሳሰብ ችሎታ እንዲኖር ከፍተኛውን አስተዋፅኦ እያደረጉ የሚገኙት የቴክኖሎጂ ውጤቶች መሆናቸውን በተለያዩ መንገዶች መመልከት ይቻላል፡፡ ቴክኖሎጂን መጠቀም የሰው ልጅን የአዕምሮ ተግባራት ውስን እንዲሆን አድርጓል የሚል አመለካከት በብዙዎች ቢኖርም፤ እንደዘርፉ ባለሙያዎች ገለፃ ከቴክኖሎጂ ውጭ መኖር በማይቻልበት በዚህ ዘመን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በአግባቡ እንዲጠቀሙባቸው በማድረግ በልጆች የአዕምሮ እድገት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ማሳደር እንደሚቻል ይገልፃል፡፡ የአስተሳሰብ ወይም የአረዳድ ችሎታ የሰው ልጅ ካለው የእውቀት፣ የግንዛቤ እና የአስተዳደግ ሁኔታ ጋር የሚያያዝ መሆኑን የተለያዩ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡ ይህ ደግሞ የሚጀምረው በልጅነት እድሜያችን በአካባቢያችን ከምናየው፣ ከምንሰማው እና ከምንማረው ሁነቶች ነው፡፡ በመሆኑም በልጅነታችን አልፈነው የምንመጣው ልምምድ አሁን ለሚኖረን ማንነት እና ማህበራዊ ግንኙነት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው እሙን ነው፡፡

ቴክኖሎጂን አግባብነት ባለው መልኩ እና አትራፊ በሚያደርገን መንገድ ከተጠቀምነው ለልጆች ሁለንተናዊ እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ብዙ ማሳያዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ በዘርፉ ባለሙያዎች የተሰሩት አብዛኞቹ ጥናቶች እንዳሳዩትም በቴክኖሎጂ መስፋፋት የተነሳ ህፃናት አዕምሯቸውን ፈጣን እንዲሆን፣ የተሳትፎ መጠናቸው እንዲጨምር እና በጥልቀት ማሰብን እንዲለማመዱ የተክኖሎጂ እገዝ ቀላል እንደማይሆን በብዙ መንገድ ተገልጦ ይገኛል፡፡

ለምሳሌ ቀደም ባለው ትውልድ ልጆች ጊዜያቸውን በንባብ ሲያሳልፉ የተፃፈውን ብቻ የሚያነቡ እና ተሳታፊ ከማያደርጋቸው ነገሮች ጋር የሚውሉ በመሆናቸው ትኩረታቸው እንዲከፋፈል፣ በአንድ ነገር ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ እንዲሁም ምናባዊ እንዲሆኑ ያደርጋቸው ነበር፡፡

በሌላ በኩል ግን በቴሌቭዥን፣ በኢንተርኔት እና በሌሎችም የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚዘጋጁ የተለያዩ ቪዲዮዎች፣ ጌሞች እና መሰል ነገሮች ላይ የሚሳተፉ ልጆች በእያንዳንዱ ተግባራት ተሳታፊ በመሆናቸው የተከፋፈለ ትኩረትን እና ምናብን ከመፍጠር ይልቅ የማስተዋል፣ ችግርፈቺ የመሆን፣ ምክንያታዊ የመሆን፣ በትኩረት የማሰብ፣ የተሻለ የቋንቋ አጠቃቀም የመኖር እንዲሁም ብልህ እና ፈጣን እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡ ይህም በአዕምሮ እድገታቸው ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ይታመናል፡፡ በመሆኑም የተመረጡ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በአግባቡ በመጠቀም የልጆቻችንን የአዕምሮ እድገትን ማፋጠን እና ነገን የተሻለ መድረግ ከወላጆች የሚጠበቅ ትልቅ ሃላፊነት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ምንጭ፡ Psychology Today እና wgu
https://www.wgu.edu/blog/impact-technology-kid-today-tomorrow1910.html#close
ውሃ አብዝቶ መጠጣት የልብ ድካምን ይከላከላል ተባለ
ውሃ አብዝቶ መጠጣት የልብ ድካምን ይከላከላል ተባለ
==============
አዲስ የወጣ ጥናት እንዳመላከተው የበዛ ውሃ መጠጣት የብዙዎቻችንን በልብ ድካም የመጠቃት እድል እንደሚቀንሰው ጠቁሟል፡፡ በአውሮፓ የልብ ህክምና ማህበረሰብ ጉባኤ ላይ የቀረበው ይህ ጥናት እንዳመላከተው ትክክለኛ የሆነ የሰውነት ውስጥ ፈሳሽ መጠን (ሀይድሬሽን) ላይ መድረስና ይህንንም አስጠብቆ መቆየት በልብ ድካም የመጠቃት ዕድልን መቀነስ ማስቻሉን ነው፡፡ በጥናቱ መሰረት ለሴቶች በቀን ከ1.6 እስከ 2.1 ሊትር ለወንዶች ደግሞ ከ2 እስከ 3 ሊትር ፈሳሽ መውሰድ ሲችሉ ነው በቂ ደረጃ ላይ ደርሰዋል የሚባለው፡፡ ሆኖም ጥናቱን በሰሩት ባለሙያዎች የተሰራ ሌላ ምልከታ በዓለም ዙርያ ያለው ሰው በአብዛኛው ይህን የልብ ህመምን ሊከላከል በሚችል ረገድ ተገቢውን ውሃ እየጠጣ አለመሆኑን አመላክቷል፡፡

ጥናቱ ዕድሜያቸው ከ44 እስከ 66 የሆኑ 15,792 ሰዎችን መልምሎ ተሳታፊ በማድረግ የተከናወነ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ዕድሜያቸው ከ70 እስከ 90 እስከሚደርስ ድረስ ከአምስት ጊዜ በላይ የህክምና ክትትል ተደርጎላቸዋል፡፡ ይህም በጉልምስና ወቅት የሚኖር የሶዲየም አወሳሰድን ተመልክቶ በሰውነት ውስጥ የሚገኝ የውሃ መጠንን በመመልከት ከ25 ዓመት በኋላ እየተፈጠረ የሚመጣ የልብ ድካምን የሚቃኝ ነው፡፡ በተጨማሪነትም ተመራማሪዎቹ በሰውነት ውስጥ ባለ የፈሳሽ መጠን እና ዋናው የደም መርጫ በሆነው ግራኛው የልብ ከፍል (Left ventricular hypertrophy) ያለው ግድግዳ እየወፈረ ከመምጣቱ ጋር ያለውን ግንኙነትንም መርምረዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ ጥናቱ ላይ የተሳተፉት በመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ በተደረገላቸው ምርመራ ወቅት የታየባቸውን የሴሪየም ሶዲየም መጠን ተመልክቶ በአራት ቡድኖች በመክፈል ነው፡፡ ጥናቱ ከተጀመረ ከ25 ዓመታት በኋላም በእያንዳድዱ የተሳታፊዎች ቡድን ውስጥ ምን ያህሉ የልብ ድካም እና የግራ ክፍል ግድግዳ መወፈር እንዳጋጠማቸው ተመልክተዋል፡፡

በውጤቱም እንደ ዕድሜ፣ የደም ግፊት፣ የኩላሊት ሁኔታ ያሉት ከግምት ገብተውም የሴሪየም ሶዲየም መጠን ከልብ ድካም ጋር የተያያዘ መሆኑን ነው፡፡ ጥናቱ እንዳመላከተው በጉልምድና ወቅት በሰውነት ውስጥ ያለው የሴሪየም ሶዲየም መጠን በሊትር ከ142 ሚሊሞል (mmol/l) ሲያልፍ የግራ ደም መርጫ ክፍል ግድግዳዎች እየወፈሩና ለልብ ድካምም ያለው ተጋላጭነት እየጨመረ እንደሚሄድ ነው፡፡

የሴሪየም ሶዲየም መጠን በሰውነት ውስጥ ያለን የፈሳሽ መጠን የሚያመላክት ሲሆን ሰዎች የሚወስዱት ፈሳሽ ባነሰ ቁጥር በሰውነት ውስጥ ያለው የሴሪየም ሶዲየም መጠንም የሚጨምር ይሆናል፡፡

ምንጭ፤ ሳይንስ ዴይሊ
ለተጨማሪ፤ https://www.sciencedaily.com/releases/2021/08/210824104113.htm
5 በመቶ የኃይል ማመንጫዎች ለ73% የአለም የካርቦን ልቀት ተጠያቂ ናቸው
=======================
የዓለማችን የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀት ከኢንዱስትሪ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ይበልጥ እያደገ እና ትልቅ ስጋት እየወለደ ይገኛል፡፡ አብዛኞቹ ኢንዱስትሪዎች በቀጣዮቹ 20 እና 30 ዓመታት የካርቦን ልቀት መጠንን በከፍተኛ ደረጃ ለማቀነስ እየሰራን ቢሉም አሁን ያላቸው የካርቦን ልቀት ከአመታት በኋላ የታቀደውን እቅድ ምናባዊ ያደርገዋል፡፡ ተመራማሪዎች ይህ የካርቦን ልቀት መጠን በሚፈለገው ደረጃ ለመቀነስ እነዲቻል ከፍተኛ የግሪንሀውስ ጋዝ የሚያወጡ ግዙፍ የሃይል ማመንጫዎች ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ይላሉ፡፡ በኮሎራዶ ቡልድር ዩኒቨርስቲ የሚገኙት ተመራማሪዎች በአለማችን በከፍተኛ ደረጃ የካርቦን ልቀት የሚስከትሉ ግዙፍ የሃይል ማመንጫዎች ለመለየት ባከናወኑት ጥናት 5 በመቶ የሚሆኑት የኃይል ማመንጫዎች 73 በመቶ ለሚሆነው የአለም የካርቦን ልቀት ዋና ተጠያቂ መሆናቸውን ያነሳሉ፡፡

አንደተመራማሪዎቹ ጥናት ለአለማችን የካርቦን ልቀት መጨመር ከድንጋይ ከሰል ጋር የተያያዙ የሃይል ማመንጫ ኢንዱስትሪዎች ትልቁን ሚና ይጫወታሉ፡፡ ታዲያ በዚህ ዘርፍ ላይ ተሰማርተው የዓለማችን የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀት እያባባሱ ከሚገኙ ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች መካከል አስሩ ለአለማችን የካርቦን ዳዮክሳይድ ልቀት ሶስት አራተኛውን ይሸፍናሉ፡፡ በዚህ ልየታ ውስጥ የእስያ ስምንት ሀገራት ዋና ተጠቃሽ ሲሆኑ፤ በዚህም ደቡብ ኮሪያ 3 በመያዝ፣ ቻይና ጃፓንና ህንድ ደግሞ የተቀረውን በማስመዝገብ በቁንጮነት ተቀምጠዋል፡፡ በአውሮፓ የፖላንዱ ቤልቻቶ ከሁሉም የኃይል ማመንጫ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛውን የካርቦን ልቀት በማስመዝገብ በቀዳሚነት ሲቀመጥ በጀርመን መቀመጫውን ያደረገ ሌላ የሃይል ማመንጫ ድርጅት እንዲሁ ከፍተኛ የካርቦን ልቀት በማስመዝገብ በተከታይነት ተቀምጧል፡፡

ተመራማሪዎች እንደሚያነሱት የዓለማችንን የካርቦን ልቀት መጠን በሚፈለገው ደረጃ ለመቀነስ ከፍተኛ የግሪንሀውስ ጋዝ የሚያወጡ እንዲህ ያሉ ግዙፍ የሃይል ማመንጫዎች ኢንዱስተሪዎች ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ ያስቀምጣሉ፡፡ የዓለምን የኢነርጂ ገበያ ብዙም በማያቃውስ መልኩ ከፍተኛ የካርቦን ልቀት በሚያስመዘግቡ መሰል ተቋማት ላይ አስፈላጊውን ቁጥጥር ማድረግ እና አንጻራዊ ቅነሳ እንዲያደርጉ መግፋት በዓለማችን የካርቦን ልቀት ምጣኔ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡

ለአብነት ቻይና ብዛት ያላቸው ከድንጋይ ከሰል ጋር የተያያዙ የሃይል ማመንጫ ኢንዱስትሪዎች ቢኖሯተም የሚስመዘግቡት የካርቦን ልቀት በአንጻራዊነት እጅግ ዝቅ ያለ ነው፡፡ በቻይና ከፍተኛ የግሪንሀውስ ጋዝ የሚያወጡ አምስት በመቶ የሃይል ማመንጫዎች በሀገር ደረጃ ያላቸው የካርቦን ዳይኦክሳድ ልቀት ምጣኔ 25 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ይሁንና በአለም አቀፍ ደረጃ 73 በመቶ ለሚሆነው የአለም የካርቦን ልቀት ዋና ተጠያቂ የሚሆኑት የደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን፣ ህንድ እና ጀርመን ያሉ ሀገራት በቁንጮነት ባስመዘገቧቸው የኃይል ማመንጫዎች ከፍተኛ የግሪንሀውስ ጋዝ የሚያወጡ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ከዚህ አንጻር በእነዚህ ተቋማት ላይ አስፈላጊውን ቁጥጥር እና ግፊት ማድረግ እየተባባሰ የሚመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ አደጋ በመጠኑም ቢሆን ለመቀነስ እንደሚያግዝ ተማራማሪዎች ያስረዳሉ፡፡
ምንጭ፡ zmescience
https://www.zmescience.com/ecology/renewable-energy-ecology/world-power-plants-emissions-17082021/