የአፍጋን ሴቶች የሮቦቲክስ ቡድን ተማፅኖ
========================
አድሜያቸው ከ12 እስከ 18 የሚደርሱ 20 ሴት ወጣቶች የመሰረቱት የአፍጋኒስታን ሴቶች የሮቦቲክስ ቡድን በ2017 ኸርት ወርልድዋይድ የተባለውን አለምአቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር አሸንፎ ሲመጣ በጊዜው የነበሩ የመንግስት መሪዎች፣ የሄራት ከተማ ነዋሪ እና አጠቃላይ የአፍጋኒስታን ህዝብ በትልቅ ክብር ተቀብሏቸው ነበር፡፡ የታሊባን መንግስት ከስልጣን በተነሳበት ከ2001 በኋላ የተወለዱት እነዚህ ወጣቶች በሀገሪቱ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን መድሎ በመቋቋም ሴት ልጅ ትልቅ ቦታ መድረስ እንደምትችል በእውን ያሳዩ እና ለብዙ የአፍጋኒስታን ሴቶች ትልቅ ምሳሌ የሆኑ ወጣቶች ነበሩ፡፡
የታሊባን ቡድን ከ20 አመት ቆይታ በኋላ የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠሩ ሲታወቅ እንደአብዛኛው የሀገሪቱ ዜጋ እነዚህ የሮቦቲክስ ቡድን አባላትም ሊመጣ የሚችለውን አደጋ በመፍራት የካናዳ መንግስት ከአፍጋኒስታን እንዲያስወጣቸው በመማፀን ላይ ይገኛሉ፡፡ በሃገሪቱ የሰበዓዊ መብት ጥበቃ ዙሪያ እንቀስቃሴዎችን የምታደርገው ኪምበርሊ አንደምትናገረው ወጣቶቹ እንባ እየታናነቃቸው የካናዳ መንግስት እርዳታ እንዲያደርግላቸው እና የኮሌጂ ትምህርታቸውን ለመማር እንደሚፍለጉ መማጸናቸውን ተናግራለች፡፡ እነዚህ ሴት ወጣቶች ከራሳቸው በላይ ለሃገራቸው ትልቅ ተስፋን የሰነቁና ትልቅ ህልም ያላቸው በመሆናቸው የካናዳ መንግስት ትብብር እንዲያደርጋላቸው የጠየቀችው ኪምበርሊ በተለይም የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አፋጣኝ እርዳታ አንዲደርጋለቸው ተማፅናለች፡፡
የአፍጋኒስታን ባለህልሞች የሚል ቅፅል ስም የወጣላቸው አነዚህ የሮቦቲክስ ቡድን አባላት ከ2017 ጀምሮ በአለም አቀፍና በአውሮፓ በተሰናዱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውድድሮች ላይ ጥሩ ውጤት በማምጣታቸው በ2018 በካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ግብዣ ተደርጎላቸው ነበር፡፡ በግብዣው ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ወጣቶቹ በሮቦቲክስ ዘርፍ የሚሰሩትን የተለያዩ ስራዎች እንደሚደንቁና እገዛ እንደሚደርጉም ቃል ገብተውላቸው ነበር፡፡
በተለያዩ የሮቦቲክስ ውድድሮች ላይ ከመወዳደር አልፎ ለሀገራቸው አዳዲስ ፈጠራዎችን በማበርከት ላይ የነበሩት የሮቦቲክስ ቡድኑ አባላት ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት የመኪና መለዋወጫን በመጠቀም ለኮቪድ-19 ህሙማን የመተንፈሻ መሳሪያ መስራት ችለው ነበር፡፡ እነዚህ ወጣቶች በሀገራቸው ለሴቶች የሚሰጠውን የተዘባ አመለካከት በመቀየር ብዙ ሴቶች ቡድኑን ተቀላቅለው አዳዲስ ሴት መሃንዲሶችንና ቴክኖሎጂስቶችን ለማውጣት ሲሰሩ እንደነበረ የምታስረዳው የሰበዓዊ መብት ጠበቃ ኪምበርሊ አሁን ግን የታሊባን መንግስት መምጣት የወጣቶቹን ህልም እንዳጨለመው ትናገራለች፡፡
የታሊባን ቡድን እንደአውሮፓውያኑ ከ1996 እስከ 2001 ሀገሪቱን በመራበት ጊዜያት ሴቶች ወደትምህርት ቤት እነዳይሄዱ በመከልከል ትልቅ አድሎ ይፈፅም እንደነበር ይነገራል፡፡ አሁን ላይ ከ20 አመት ቆይታ በኋላ የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠሩ የቻለው የታሊባን ቡድን ቀድሞ ከነበረው ሁኔታ ራሱን እንዳሻሻለ በተደጋጋሚ ቢገልፅም አብዛኞቹ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ለሀገሪቱ ሴት ወጣቶች ተስፋ የሚሰጥ ምንም ነገር እንደሌለ ያስረዳሉ፡፡
ምንጭ፡ Independent
ተጨማሪ https://www.independent.co.uk/asia/south-asia/canada-afghanistan-girls-robotics-team-b1903884.html

The Independent
Afghanistan’s all-girls robotics team ‘begging’ Canada to help escape Taliban
The 20-member team, known as the ‘Afghan Dreamers’, comprise of girls between ages 12 and 18
ጂምናስቱ ሮቦት
************
በውሻ አምሳል በሰራቸው ሮቦቶቹ የሚታወቀው ቦስተን ዳናሚክስ አሁን ደግሞ በሰው ቁመና ተሰርተው ልክ እንደሰው የጅምናስቲክ እንቅስቃሴዎችን ጭምር መከወን የሚችሉ ሮቦቶቹን ሰርቶ አቅርቧል፡፡ ኩባንያው ከዚህ ቀደም እነዚህ በዓለማችን ወደር የለሽ የሰው አምሳል ሮቦት ናቸው ያላቸውና አትላስ የተሰኙት ሮቦቶቹ ደረጃ ሲወርዱና ሲወጡ እንዲሁም በር ሲከፍቱ ያስመለከተ ሲሆን አሁን ደግሞ ሮቦቶቹ ሲዘሉ እና በዝግታ ሲሮጡ አዲስ በለቀቀው ቪዲዮ አሳይቷል፡፡
አዲስ በተለቀቀወ ቪዲዮ ሮቦቶቹ በመሰናክሎች መሃል ሲተላለፉና በጎርበጥባጣ ቦታዎች ላይ ሲሮጡ ታይቷል፡፡ በተጨማሪም ሁለቱም ሮቦቶች የጋራ እንቅስቃሴን እኩል በመከወን አንድ ላይ ሲዞሩ፣ ሲሽከረከሩና አየር ላይ ሲገለባበጡ ታይተዋል፡፡ ታድያ ከዚህ ቀደም በቦስተን ዳይናሚክስ የተለቀቁ ምስሎች ሮቦቶቹ የተሰጣቸውን ተግባር ማከናወን ላይ ወድያው ስኬታማ እንደማይሆኑ አሳይቶ ነበር፡፡ የአትላስ ቁጥጥር ኃላፊ የሆነው ቤንጃሚን ስቴፈንስ እንደሚለውም በሙከራዎች ወቅት ሮቦቶቹ በተደጋጋሚ ግጭት ሊገጥማቸው ስራውም አሰልቺ ሊሆን ይችላል፡፡ ተግባሩ ልክ አንዳንድ ስፖርቶች ላይ አንድ አስደናቂ ትርዒትን ለማሳየት የወጠኑ ስፖርተኞቹ እንቅስቃሴውን ለመቶዎች ጊዜ ደጋግመው እንደሚሰሩትና እንደሚለማመዱት ሁሉ ሮቦቶቹም የብቃታቸው ጣርያ ላይ ይደርሱ ዘንድ ተደጋጋሚ ሙከራን እንደሚያደርጉ ቤንጃሚን ገለጿል፡፡
የቦስተን ዳይናሚክስ ተመራማሪዎች ሮቦቶቹ በዚህ መልኩ የጋራ ትርኢት እንዲያቀርቡ ያስቻሏቸው ገና ከሁለት ሳምንታት በፊት ነው፡፡ በተጨማሪም ሁለቱ ሮቦቶች አንድ ላይ ሆነው እንቅስቃዎቹን እየከወኑ ሲቀረፁ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው፡፡
ኩባንያው ከዚህ ቀደም ሰርቶ ያቀረባቸው ስፖት የተሰኙ የሮቦት ውሻዎች ሰፊ እውቅናን ያተረፉ ሲሆን አንዳንድ የፖሊስ ተቋማትም እነዚህ የሮቦት ውሻዎቹን ሮንድ ለመዞር መጠቀም ጀምረዋል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=tF4DML7FIWk
ምንጭ፤ ቴክስፕሎር

YouTube
Atlas | Partners in Parkour
Parkour is the perfect sandbox for the Atlas team at Boston Dynamics to experiment with new behaviors. In this video our humanoid robots demonstrate their whole-body athletics, maintaining its balance through a variety of rapidly changing, high-energy activities.…
ለጃፓን አዲስ ደሴት ያስገኘው የገሞራ ፍንዳታ
*****************************
በጃፓን ከውሃ ስር ፈንቅሎ የወጣ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ አዲስ ደሴት አስገኝቷል፡፡ ጃፓን ወደ 6852 የሚደርሱ ደሴቶች እንዳሏት ይነገራል፡፡ በያዝነው ሳምንት የተሰማው መረጃ እንደሚያመለክተው ጃፓን ያሏትን ደሴቶች ቁጥር በአንድ ከፍ የሚያደርግ የውሃ ውስጥ እሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡ ፍንዳታው ከቶኪዮ 745 ማይሎች ርቀት ላይ አይዎ ጂማ ከሚባለው ደሴት አቅራቢያ የተከሰተ ነው፡፡
ፍንዳታው በተከሰተበት ወቅት 15 ኪሎ ሜትር ያክል ርቀት ላይ ከፍተኛ የእንፋሎት ጭስ ተስተውሏል፡፡ አሁን ላይ ጨቅላዋ ደሴት አንድ ኪሎ ሜትር መጠነ ዙሪያ ያላት ሲሆን የጃፓን ሜቴዮሮሎጂ ኤጀንሲ ፍንዳታው አሁንም ያልተቋረጠ በመሆኑ መጠኑ ሊጨምር እንደሚችል መረጃ አውጥቷል፡፡
ይህ በገሞራ ፍንዳታ ምክንያት የተፈጠረ አዲስ ደሴት በጃፓን ደቡባዊ ጽንፍ የተፈጠረና ከጃፓኑ ኦጋሳዋራ ደሴትና በቻይናው ቦኒን ደሴት መካከል የተፈጠረ በመሆኑ ጃፓንን የግዛት ማስፋፋት ጥያቄ ውስጥ ሊከታት ይችላል ተብሏል፡፡ በመሆኑም በአካባቢው የሚገኙ ሚዲያዎች ደሴቱን እንደ ጥሩ እድል አልቆጠሩትም፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በ1904፣ 1914 እና 1986 የነበረን የታሪክ አጋጣሚን በመጥቀስ አንዳንዶች አዲሱ ደሴት ከጥቂት ቆይታ በኋላ ሊሰወር ይችላል የሚል ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ በተጠቀሱት አመታት በገሞራ ፍንዳታ ምክንያት አነስተኛ ደሴቶች በጃፓን ተፈጥረው የነበረ ቢሆንም ሁሉም ከቆይታ በኋላ ተሰውረዋል፡፡
መሰወር ብቸኛ ታሪክ እንዳልሆነ ደግሞ በ2013 የተፈጠረውና በአካባቢው ካለው ደረቅ መሬት ጋር በመጋጠም ለአለማችን ስኖፒ የተባለ ደሴትን ያስገኘውን አጋጣሚ ማስታወስ በቂ ነው፡፡
ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/environment/japan-has-a-new-island-thanks-to-underwater-volcano-eruption/?fbclid=IwAR3oyfb-0bPhOOjtJ6t5StmnxoLfGWl_80O3LPLzwUR7i7LUMu-270SGxKY

IFLScience
Japan Has A New Island Thanks To Underwater Volcano Eruption
There are canonically 6,852 islands that make up Japan, which is probably more than you would have expected. But as of this week that number has increased
ለምድር ቀርባ የምታልፈው አስትሮይድ
***************
ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 15 አንድ አስትሮይድ ለምድር ቀርባ እንደምታልፍ ተገለፀ፡፡ 1.4 ኪ.ሜ ስፋት ያላት አስትሮይዷ በሰዓት 94,208 ኪ.ሜ የምትምዘገዘግ ሲሆን ለምድር 3,427,445 ኪ.ሜ ቀርባ እንደምታልፍ ይጠበቃል፡፡
2016ኤጄ193 የተሰኘችው ይህች አስትሮይድ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12፡10 ሲል ነው በምድር በኩል የምታልፈው፡፡ የአሜሪካኑ ህዋ ምርምር ተቋም ናሳ አስትሮይዷ ምድር ላይ ጉዳት የማድረስ አቅም ያላት ሲል የገለፃት ሲሆን የተቋሙ ተመራማሪዎችም ከዛሬ አንስቶ እስከ መጪው ሰኞ ድረስ እንቅስቃሴዋን እየተከታተሉ ይቆያሉ፡፡ ምንም እንኳን የአስትሮይዷ የእንቅስቃሴ ምህዋር ሲታይ ምድር ላይ ጉዳት የምታደርስ አለመሆኗ ቢታወቅም ጉዳት የማደረስ አቅም ያላት ተብላ የተቀመጠችው በህዋ ምርምር እይታ አስትሮይዷ ለምድር ቀርባ የምታልፍበት ርቀት ቅርብ ነው ተብሎ ስለሚታወቅ ነው፡፡
የአስትሮይዷ ስያሜ የህዋ ተመራማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ከተመለከቷት ወቅት ማለትም ከአውሮፓውያኑ 2016 ጋር ተያይዞ የተሰጣት ነው፡፡ ተመራማሪዎቹ በአሜሪካኑ የሄላካላ ኦብዘርቫቶሪ ውስጥ ባለው ፓኖራሚክ ሰርቬይ ቴሌስኮፕ እና ራፒድ ሪስፖንስ ሲስተም አማካኝት ነው የተመለከቷት፡፡ እንደ ናሳ ከሆነ አስትሮይዷ ሞላላ ቅርፅ ባለው ምሕዋሯ ላይ ሆና ፀሐይን ለመዞር 2,160 ቀናት ወይም 5.91 ዓመታት ይፈጁባታል፡፡ በተጨማሪም ለመሬት ቀርባ የምትገኝበት ርቀር ጨረቃ ካላት ርቀት ጋር ሲነፃፀር በ8.9 እጥፍ የላቀ ነው፡፡
የአስትሮይዷን መጠን በንፅፅር ለማቅረብ ያህል በዱባይ ከሚገኘው የዓለማችን ረጅሙ ህንፃ ቡርጅ ከሊፋ በግማሽ፣ ከፓሪሱ ኤፍል ማማ 4.5 እጥፍ እንዲሁም እዚሁ አዲስ አበባ እየተገነባ ካለው የንግድ ባንክ ህንፃ ደግሞ በሰባት እጥፍ የምትልቅ ናት፡፡
ምንጭ፤ TECH2
ለተጨማሪ፤ https://www.firstpost.com/tech/science/asteroid-bigger-than-burj-khalifa-will-pass-by-earth-on-21-august-9858991.html

Tech2
Asteroid bigger than Burj Khalifa will pass by Earth on 21 August
With a highly elliptical orbit, asteroid 2016 AJ193 orbits the Sun every 2,160 days or every 5.91 years.
ደማችን ለመከላከያ ሰራዊታችን
*******************
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ቤተሰቦች “ደማችን ለመከላከያ ሰራዊታችን” በሚል መርህ ዛሬ ነሐሴ 14 2013 ዓ.ም የደም ልገሳን አከናውነዋል፡፡ ከኃላፊዎች አንስቶ ቁጥራቸው የበዛ የተቋሙ ቤተሰቦች በከፍተኛ ተነሳሽነት በተሳተፉበት በዚህ መርሀ ግብር ለመከላከያ ሰራዊቱ ይሆን ዘንድ በርካታ ዩኒት ደም መሰብሰብ ተችሏል፡፡
ከዚህ ቀደም ለተከታታይ ዓመታት የቴክኖለሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ቤተሰቦች ደማቸውን ለወገን በመለገስ ለተጎዱ ደራሽነታቸውን ሲያሳዩ የቆዩ ቢሆንም የዛሬው የደም ልገሳ መርሀ ግብር ሲካሄድ ግን አሁን ላይ የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊቱ ሀገራዊ ግዴታ ውስጥ ባለበት ሰዓት በመደረጉና ልገሳውም ይህን ታሳቢ በማድረግ የተከናወነ መሆኑ መርሃ ግብሩን ልዩ አድርጎታል፡፡ በዚህም ለወትሮ ከነበረውም ከፍ ባለ መልኩ የለጋሽ ቤተሰቦችን ቀልብ በመሳብ በተሻለ ቁጥር ተሳታፊ አድርጎ አልፏል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ቤተሰቦች ከደም ልገሳ ባሻገርም በተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ በመሰማራት ሀገርን የሚጠቅም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ለዓብነትም የተቸገሩ ወገኖችን ከመርዳት አንስቶ እስከ አረንጓዴ ልማት ስራዎች ይጠቀሳሉ፡፡

ኤልጂ የ6ጂን ሲግናሎችን ታይቶ በማይታወቅ ርቀት ማስተላለፍ ቻለ
====================
የ5ጂ ቴክኖሎጂ ገና ባደጉት ሀገራት እንኳን በቅጡ ባልተዘረጋበት በአሁኑ ወቅት የተለያዩ የኮምዩኒኬሽን ኩባንያዎች የቀጣዩ ትውልድ ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የሆነው 6ጂን ለመስራት በጥድፊያ ላይ ናቸው፡፡ ከነዚህ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ግዙፉ የኮሪያ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ኤልጂ ከጀርመኑ የምርምር ተቋም ፍራንሆፈር ጌዜልሻፍት ጋር በመተባበር ለቴክኖሎጂው አንድ እምርታ በሆነ መልኩ የ6ጂ ሲግናሎችን በ100 ሜትር ርቀት ውስጥ ማስተላለፍ ችሏል፡፡
የ6ኛው ትውልድ የኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ በራሱ እጅግ በጣም ፈጣን ከሆነው ከ5ጂ ጋር እንኳን ሲነፃፀር መረጃን በበይነ መረብ የማስተላለፍ ፍጥነቱ በ50 እጥፍ የላቀ ሲሆን የመረጃዎች የመዘግየት ልኬትንም (latency) በ10 በመቶ እንደሚቀንስና የሚላከው መረጃ ጥራትንም እንደሚያሳድግ ይጠበቃል፡፡ እነዚህ የቴክኖሎጂው እምርታዎች ተደማምረው ታድያ በቤት ውስጥም ሆነ በስራ ቦታ ከበይነ መረብ ጋር ያለውን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሳድጉት ተገምቷል፡፡
ሲግናሎቹ በሚተላለፉበት ወቅት የኃይል እጥረት ስለሚያጋጥማቸውና በዚህም ምክንያት የሚጓዙት ርቀት የተገደበ መሆኑ የ6ኛው ትውልድ ቴክኖሎጂን እውን ማድረግ ቀድመው ከነበሩት ትውልዶችም በላይ አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ በዚህ ሳብያ ቴክኖሎጂውን በበቂ ሁኔታ አድጎ ለገበያ ሲውል ለማየት ቢያንስ እ.አ.አ ከ2025 እስከ 2029 ድረስ ወይም ከዚያ በላይ መጠበቅ እንደሚገባ የባለድርሻዎች ግምት ነው፡፡
ኤልጂ ከጥቂት ወራት በፊት ሌላኛው ግዙፍ ኮሪያዊ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሳምሰንግ የ6ጂ ሲግናሎችን በ15 ሜትር ርቀት ውስጥ በማስተላለፍ የያዘውን ክብረ ወሰን ነው አሁን ላይ ከአንድ ህንፃ ጣርያ ወደ ሌላኛው በማስተላለፍ በከፍተኛ መጠን ያሻሻለው፡፡ እንደ ኩባንያው ከሆነ ሲግናሎቹ ይህን ያህን ርቀት እንዲጓዙለት ያስቻለው ከፍራንሆፈር ጌዜልሻፍት ጋር በመሆን ያበለፀገውና በ155 እና 175 ጊጋ ሀርዝ መካከል ባለ ፍሪኩዌንሲ ውስጥ እስከ 15 ዴሲቤል ሚሊዋት ድረስ የሚለኩ የተረጋጉ ሲግናሎችን መላክ የሚያስችለው አዲስ አምፕሊፋየር ነው፡፡
በተጨማሪም የጋራ ጥናት ቡድኑ እንደተቀባዩ አቀማመጥ መተላለፊያዎችም እንዲለዋወጡ የሚያስችለው የአዳፕቲቭ ቢምፎርሚንግ ሰርተው ያሳዩ ሲሆን የተለያዩ ሲግናሎችን አቀናጅቶ ወደሚፈለገው አንቴና ለመላክ የሚያስችል ስልትንም ተጠቅመዋል፡፡
ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-08-lg-6g-transmission-meters.html

Tech Xplore
LG sets new record for 6G transmission of data at 100 meters
A team of researchers at Korea's LG Electronics, working with a group at Fraunhofer-Gesellschaft, has successfully sent data 100 meters over a 6G signal. Officials at LG have posted details of their test ...
የተገለበጡ ክንፎች ያሉት ተዋጊ ጀት
***********************
በአለማችን የአቪየሽን ታሪክ ውስጥ በተለያየ አጋጣሚ ለተለያየ አገልግሎት አስደናቂ ቅርጽና ቴክኖሎጂ ያላቸው አውሮፕላኖች እንደተሰሩ ይታወቃል፡፡ የዘርፉ ሰዎች የናሳውን የውጊያ ጀት የሚወዳደር የለም ይላሉ፡፡ ይህም Grumman X-29 የተሰኘው ተዋጊ ጀት ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ አየር ላይ የወጣው በ1984 ዓም ነው፡፡ ይህንን ተዋጊ ጀት ተመራማሪዎች ከፍተኛ ምርምር የተደረገበትና እንዲህ ነው ተብሎ በቀላሉ የማይገለጥ ኤሮዳይናሚክስ አውሮፕላን ነው ይሉታል፡፡
በናሳው የአርምስትሮንግ በረራ ማዕከል የታሪክ ተመራማሪ የሆኑት ክርስቲና ግሌዘር ስለ አውሮፕላኑ የበረራ አቅጣጫውን በሰከንድ ለ40 ያክል ጊዜ መቀያየር የሚችል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ይህንንም ሲያደርግ ያለምንም ዲጂታል የበረራ ኮምፒውተር እንደሆነ ታውቋል፡፡
ከመደበኛው የክንፍ አቀማመጥ በተቃራኒው የሆነ ክንፍ ያላቸው አውሮፕላኖች በጣም ጥቂት ሲሆኑ X-29 ግን ብቸኛው አይደለም፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1944 የበረረው የጀርመን ቦምብ ጣይ አውሮፕላንም በተመሳሳይ የተገለበጡ ክንፎች የነበሩት ነው፡፡
ይህ የአውሮፕላን አይነት ከ1984 እስከ 1992 ድረስ 422 በረራዎችን ለምርምር ያደረገ ሲሆን በኋላ ላ ግን ቅርስ ሆኖ ለታሪክ እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡
ምንጭ cnn
ተጨማሪ ንባብ http://edition.cnn.com/style/article/grumman-x-29-nasa-darpa-fighter-plane/index.html?utm_term=link&utm_medium=social&utm_source=fbCNNi&utm_content=2021-08-22T14%3A38%3A05&fbclid=IwAR1zGbsor8eNclEJH5nDqIxWXqH9f0ZdutAy3u5QPK2e7Zdm2G-J2yfX4DQ

ከአልማዝ የጠነከረ መስታውት ተሰራ
================
በቻይናው የያንሸን ዩኒቨርሲቲ ዘንድ በሚገኙ ምሁራን የሚመራ አንድ ዓለም አቀፍ የተመራማሪዎች ቡድን ለየት ያለ የኬሚካል መዋቅር እና የምርት ሂደትን ተጠቅሞ በጥንካሬው ከተፈጥሮ አልማዝ የሚስተካከል መስታውት መስራቱን አስታውቋል፡፡ ተመራማሪዎቹ ኤኤም-3 (AM-III) ብለው የሰየሙት ይህ መስታውት በጥንካሬው ከአልማዝ ውጭ ተወዳዳሪ የሌለው፡፡
በተደራጀ ውስጣዊ መዋቅሩ አማካኝነት ጥንካሬን ካገኘው ከአልማዝ አንፃር ለየት የሚለው ኤኤም-3 ይህን ጥንካሬውን ሊያገኝ የቻለው በሞለኪውል ደረጃ ባለው የተዘበራረቀ ትስስር ነው፡፡ መስታውቱን ለመስራት ተመራማሪዎቹ ፉለሪን የተባሉትን ባለ ሞላላ ቅርፅ የካርበን ሞለኪውሎችን 1,200 ዲ.ሴ በሚለካ ሙቀት አግለው እና ለሰዓታት ከፍተኛ በሆነው የ25 ጊጋፓስካል ግፊት ውስጥ እንዲሰባበሩ አደረጓቸው፡፡ ሆኖም ሂደቱ ከሚገባው በላይ ሄዶ ካርበኖቹ በተደራጀ አኳሀን የሚቀመጡ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ይህ የመስታውቱ ጥንካሬ የሚቀንስ እና የሴሚኮንዳክተርነት ይዘቱንም ሊያጣ ይችል ነበር፡፡ በዚህ ሂደት ነው ተመራማሪዎቹ ጥንካሬው ሲለካ ሌሎች ቁሶችን በመሰባበር ከሚታወቀው የተፈጥሮ አልማዝም በላይ ሆኖ የተገኘውን ይህን መስታውት ሰርተው ለማቅረብ የቻሉት፡፡
ታድያ ይህ የመስታውቱ ጥንካሬ በራሱ ስኬት ከመሆንም ባሻገር ጠንካራ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፓኔል እና ሴሚኮንዳክተሮች እንዲመረቱ በማስቻል የአረንጓዴ ኃይል ምርትን በማሳደግ እንቅስቃሴ ውስጥ የራሱን በጎ ሚና ይጫወታል ተብሎለታል፡፡
ምንጭ፤ ፊውቸሪዝም እና ኢንዲፔንደንት
ለተጨማሪ፤ https://futurism.com/the-byte/glass-strong-diamond እና https://www.independent.co.uk/news/science/china-strongest-glass-diamond-scientists-b1899243.html?utm_source=reddit.com

THE_BYTE.
Scientists Create Glass That's as Strong as a Diamond
A new glass called AM-III is so hard it can scratch the surface of diamonds and could be used in new ultra-sturdy solar panels.
አታላዩ እባብ
=======
አደገኛ መርዝ ያላቸው የራትል እባቦች ድንገተኛና ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ጭራቸውን የማንቀጥቀጥ ድምፅን በማሰማት የሰው ልጆችንም ሆነ ሌሎች እንስሳትን በእነርሱና እባቦቹ መካከል ካለው ርቀት ባነሰ በጣም የቀረቡ እንዲመስላቸው በማድረግ እንደሚያታልሉ አዲስ ጥናት ጠቆመ፡፡ በዋናነት በደቡብ እና ሰሜን አሜሪካ አህጉራት ውስጥ የሚኖሩትና ከግማሽ እስከ 2.5 ሜትር ርዝማኔ ያላቸው እነዚህ የእባብ ዝርያዎች ልክ አንደ መኪና ወደኋላ ሲነዳ ወደ አንድ አካል በተጠጋ ቁጥር የሚያወጣው የተቆራረጠ ድምፅ እየጨመረ እንደሚመጣው ሁሉ እነርሱም ድምጻቸውን ቀስ በቀስ በመጨመር በድንገት ከፍተኛ ፍጥነት ወዳለው አስደንጋጭ የመንቀጥቀጥ ድምፅ ይለውጡታል፡፡ ሆኖም ከመኪና በተቃራኒ እባቦቹ ይህን እየጨመረ የሚሄድ ድምፅ የሚያሰሙት ከሚቀርባቸው አካል ጋር በጣም ተቀራርበው ሳይሆን ምናልባትም ከአንድ ሜትር ርቀት በላይ ሆነው ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የማታለል ስራ እባቡ በሚያልፍ ሰው ከመረገጥ ወይም ለእርሱ እጅግ አስፈላጊ የሆነው መርዙን ከማባከን ይጠብቀዋል፡፡
በኦስትሪያው የግራዝ ዩኒቨርሲቲ የሚያገለግለው ቦሪስ ቻግናድ ከጥቂት ዓመታት በፊት በሙኒክ ቴክኒካል ዩኒቨርሱቲ ያለውን የራትል እባቦች መኖርያ በተመለከተበት ጊዜ እባቦቹ አንድ አካል በቀረባቸውና በራቃቸው ቁጥር የጭራ መንቀጥቀጥ ፍጥነታው እንደሚለዋውጡ መመልከት ከቻለ በኋላ ነው ወደዚህ ጥናት ያመራው፡፡ ከሌሎች የምርምር ባልደረቦቹ ጋር በመሆን 30 ዌስተርን ዳይመንድባክ ራትል እባቦችን (Crotalus Atrox) በሰው አምሳል የተሰራ ቁስ በሚንሸራተት ሀዲድ ላይ ሆኖ እንዲቀርባቸው በማድረግ እና በአንድ ስክሪን ላይ እያደገ የሚመጣ ጥቁር ነጥብን በማኖር ሙከራ አድርገዋል፡፡ በሁለቱም ሙከራዎች ወቅት እባቦቹ ጭራቸውን የማንቀጥቀጥ ድምፅ የሚያሰሙበትን ፍጥነት ቀስ በቀስ በሴኮንድ ወደ 40 መንቀጥቀጥ እያደገ የመጣ ሲሆን ከዚያም ይህ የጭራ መንቀጥቀጥ በድንገት በሴኮንድ ከ60 እስከ 100 መካከል በቋሚነት እንዲቆይ ሆኖ እንዲገኝ አድርገውታል፡፡
ከዚህ ሙከራ በኋላ የጥናት ቡድኑ የቨርቹዋል ሪያሊቲን በመጠቀም ሰዎችን የተለያየ ድምፅ በሚሰማበት የሳር ምድር እየተጓዙ እንዲመስላቸው የማድረግ ሙከራን አከናወነ፡፡ በሙከራው ላይ ተሳታፊዎቹ የሚሰሙት ድምፅ ለእነርሱ በጣም የቀረበ ሆኖ ሲሰማቸው የሚጫኑት ቁልፍ የተሰጣቸው ሲሆን በዚህም ተሳታፊዎቹ ለእባቡ የማታለያ የመንቀጥቀጥ ፍጥነት በቀላሉ ተሸውደው ታይተዋል፡፡ ምንም እንኳን ተሳታፊዎቹ የእባቡን የጭራ መንቀጥቀጥ ድምፅ የሰሙት ከአራት ሜትር አካባቢ ርቀት ላይ ቢሆንም በአንድ ሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ያህል ተሰምቷቸው ነበር፡፡
የጥናቱ ውጤት እባቦች ከሰው ልጆች እና ሌሎች እንስሳት ጋር ባላቸው ግንኙነት ውስጥ በአስደናቂ ሁኔታ የማስመሰል ችሎታን እያጎለበቱ መምጣታቸውን ያሳየ ነው ተብሎለታል፡፡
ምንጭ፤ ኒው ሳይንቲስት
ለተጨማሪ፤ https://www.newscientist.com/article/2287748-rattlesnakes-use-auditory-illusion-to-make-us-think-they-are-nearby/?utm_term=Autofeed&utm_campaign=echobox&utm_medium=social&utm_source=Twitter#Echobox=1629517576

New Scientist
Rattlesnakes use auditory illusion to make us think they are nearby
Western diamondback rattlesnakes use their rattles to produce an auditory illusion, creating the sensation that they are far closer than they really are
ታይታኒክ እንዴት ልትሰመጥ ቻለች
*********************************
አንድ አዲስ ጥናት ተይታኒክ የተባለችው መርከብ የሰመጠችው በበረዶ ግግር ምክንያት እንዳልሆነ አመለከተ፡፡ መርከቧ በሚያዚያ ወር 1912 ከሳውዝአምፕተን ወደ ኒዮርክ በፍጥነት ጎዞ በማድረግ ላይ ሳለች ካልታሰበ የበረዶ ግግር ጋር ተጋጭታ እንደሰመጠች ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ ከጊዜ በኋላ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ለመርከቧ መስመጥ ትክክለኛው መንስኤ ፍጥነቷ ወይም የበረዶ ግግር አይደለም የሚሉ ናቸው፡፡
ስለ ታይታኒክ በብዛት በመጻፍ የሚታወቁት አይርላንዳዊ ሴናን ሞሎኒ ለመርከቧ አደጋ መነሻ ምክንያት የሆነው በረዶ ሳይሆን እሳት ነው ይላሉ፡፡ ታይምስ ለተባው መጽሔት ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የታሪክ ጸሐፊ መርከቧ የሰመጠችው በእሳት፣ በረዶና ከፍተኛ ቸልተኝነት ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
መርከቧ ከወደቧ ብዙም ሳትርቅ ከከሰል ማንደጃው ውስጥ እሳት መቀጣጠል እንደጀመረ የሚናገሩት ሞሎኒ ይህ እሳት በመርከቧ የውስጠኛ ክፍል የሚገኝን 9 ሜትር የሚረዝም የብረት ምሰሶ እንደለበለበው የሚያሳዩ መረጃዎች መገኘታቸውን አስገንዝበዋል፡፡ ስለ መርከቧ መስመጥ አዲስ የተባለው መረጃም ከዚህ ግኝት ጋር የተያዘ ነው፡፡
ይህ እሳት የተነሳበት የመርከቧ ክፍል ደግሞ ከበረዶ ግግሩ ጋር በቀጥታ የተላተመው ክፍል እንደሆነ ይታመናል፡፡ እሳቱ የመርከቧን ተጋላጭ ክፍል አዳክሞት የነበረ በመሆኑ የበረዶው ግግር መርከቧን ሊጎዳት እንደቻለ ሞሎኒ እምነታቸውን አስረድተዋል፡፡ አክለውም እሳቱ ምንም እንኳን ከነመሻው የታወቀ ቢሆንም መርከቧ መነሳት ከነበረባት ሰዓት ለሁለት ጊዜያት ያክል በመዘግየቷ የተማረሩ ተጓዦች ለአደጋ ይጋለጣሉ በሚል ምክንያት ይፋ ሳይደረግ ተደብቆ ቆይቷል ብለዋል፡፡
ይህ የእሳት መላምት በ2004 በፕሮፌሰር ሮበርት ኢስንሀይ ከተሰራው ምርምር ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡ አሁን ላይ ብዙ የታሪክ ተመራማሪዎች መርከቧ ውስጥ እሳት መነሳቱን ቢያምኑም ይህ አዲስ በፎቶግራፍ የተደገፈ ግኝ ግን በትክክል እሳቱ የት ላይ እንደተነሳ እና ከመርከቧ መስመጥ ጋር እንዴት እንደሚገናኝ የሚያብራራ ነው፡፡
ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/editors-blog/new-evidence-suggests-the-titanic-wasnt-just-sunk-by-an-iceberg/?fbclid=IwAR1H04Cf4H2ltVP8J1aWEOJlazVOS6MXo95fjsj_oBGOszHP_0gsm-homi4

New Evidence Suggests The Titanic Wasn't Just Sunk By An Iceberg
Ever since the RMS Titanic sunk en route to New York from Southampton in April 1912, we’ve always thought it was caused by the ship traveling too fast and