የዓለማችንን መልክ የቀየሩት 20ዎቹ የምንግዜም ታላላቅ ኢኖቬሽኖች
========================
በሰው ልጆች ረዥም የህይወት ጉዞ ውስጥ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚና እንዲ በቀላሉ የሚገለፅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ሰዎች ወደዚች ምድር ከመጡ አንስቶ አካላዊውን ዓለም ለመግራት የሚያስችሉ የተለያዩ ፈጠራዎችንና የኢኖቬሽን ውጤቶች ያለማቋረጥ ሲተገብሩ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ መሳሪያዎች አለም አሁን ያላትን መልክ ያጎናፀፏት እና የቀጣዩንም ትውልድ እጣ ፋንታ በበጎም ይሁን በክፉ የመወሰን አቅማቸው በእጅጉ የተጠበቀ ነው፡፡ አለማችን እስካሁን ያየቻቸውን የኢኖቬሽን ውጤቶች ለሰው ልጆች ከሰጡት ግልጋሎት እና በታሪክ ውስጥ ካላቸው የገዘፈ ተጽዕኖ አንፃር የሚከተሉት ኢኖቬሽኖች ከምንግዜም ታላላቆቹ መካከል ይገኙበታል፡፡ በዘመን ቅደም ተከተል እንመልከታቸው፡
1. እሳት (FIRE) - ስለእሳት ስናነሳ ብዙዎች የሚከራከሩበት ጉዳይ ቢኖር እሳት ተፈለሰፈ ከሚባል ይልቅ ተገኝቷል የሚለው ሃሳብ እጅግ ተስማሚ መሆኑን ነው፡፡ ቀደምት የሰው ዘሮች እሳትን እንዴት መፍጠር እና መቆጣጠር እንደሚችሉ ከማወቃቸው በፊት የእሳትን አደጋዎች በየአጋጣሚው ተመልክተው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የእሳትን ምንነት ከተረዱና የሚሰጣቸውን ጥቅም ካወቁ በኋላ እሳትን እንደ አንድ ትልቅ መገልገያ መጠቀም ጀምረዋል፡፡ አንዳንድ የአርኪዎሎጂ አጥኝዎች እሳት ጥቅም ላይ የዋለው ከ2 ሚሊዮን አመት በፊት ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ 125 ሺ አመታት እንዳስቆጠረ ይገልፃሉ፡፡ ይህ ክርክር ምንም ተባለ ምንም በሰው ልጆች ታሪክ ታላቅ ግኝት የሆነው እሳት ሰዎች ራሳቸውን ከተለያዩ ነገሮች እንዲከላከሉ እና ማብሰል የሚባለውን ትልቅ ክህሎት እንዲረዱ ያስቻል አስገራሚ ግኝት ነው፡፡
2. ተሽከርካሪ ጎማ (WHEEL) - ይህ ፈጠራ የተገኘው በ3500 ዓመተ ዓለም (B.C) በሜሶፖታሚያ የስልጣኔ ዘመን ነበር፡፡ የሜሶፖታሚያ ህዝቦች ይህንን አስገራሚ ፈጠራ የሸክላ ቁሳቁሶችን ለማበጃጀት ሲጠቀሙበት የቆየ ቢሆንም ከሶስትና አራት መቶ አመታት በኋላ ፈጠራው ለሰረገላ ማሽከርከሪያ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ የመሳሪያው ተፅዕኖ እጅግ እየናኘ ሄዷል፡፡ ተሽከርካሪ ጎማ ለሰው ልጆች የመጓጓዣ እና የንድግ ስርዓት መፈጠር ትልቅ ሚና ያለው ግኝት ነው፡፡
3. ኦፕቲካል ሌንሶች (OPTICAL LENSES) - የሰዎችን የእይታ አቅም ይበልጥ ለመጨመር እንደ ኦፕቲካል ሌንሶች ያሉ አስገራሚ ግኝቶች እጅግ ወሳኝ ነበሩ፡፡ ረዥም የፈጠራ ሂደት የነበራቸው እነዚህ ግኝቶች በጥንቱ የግብፅ እና የሜሶፖታሚያ የስልጣኔ ዘመን እንደበለፀጉ የሚታመን ሲሆን ከግሪክ የተገኙት የብርሃን ንድፈ ሃሳቦች ደግሞ ለግኝቱ እውን መሆን ትልቅ ሚና ነበራቸው፡፡ ኦፕቲካል ሌንሶች እንደቴሊቭዥን፣ ፎቶግራፍ እና ፊልም ያሉ ትልልቅ የሚዲያ ቴክኖሎጂዎች እንዲፈጠሩ መንገድ የጠረጉም ናቸው፡፡
4. ኮምፓስ (COMPASS) - ይህ እንቅስቃሴን ለመምራት የተዘየደው የቴክኖሎጂ ግኝት የሰው ልጆችን የአሰሳ ጥበብና አቅም ወደ አዲስ ምዕራፍ በመወሰድ ተተኪ የማይገኝለት አስገራሚ ግኝት ነው፡፡ የመጀሪያዎቹ ኮምፓሶች በተፈጥሮ የመግነጢሳዊ ይዘት ባላቸው የማዕድን ቁራጮች ወይም (lodestone) አማካኝነት የተሰሩ ሲሆን፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 300 እና 200 አመተ አለም አካባቢ በቻይና እንደተሰሩም ይነገራል፡፡
5. ወረቀት (PAPER) - በ100 ዓመተ አለም አካባቢ በቻይና የተፈለሰፈው ይህ ግኘት የሰው ልጆችን የፅህፈት እና ሃሳብን የማጋራት ልምድ በእጅጉ የቀየረ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ከዚህ ጊዜ በፊት በግብፅ እና በሜክሲኮ የስልጣኔ ዘመናት የተፈለሰፉት እንደ ፓፒረስና አሜት ያሉ የመፃፊያ ቁሶች ለወረቅት መፈጠር አስተዋፅዖ ቢኖራቸውም በቻይና የነበረው ግኝት ግን አሁን ላለው የወረቀት ቴክሎጂ ትልቅ መሰረት የጣለ ነው፡፡
6. ባሩድ (GUNPOWDER) - ከተለያዩ የኬሚካል ንጥረ ነገሮች ተቀይጦ የሚሰራው ይህ ተቀጣጣይ ፈንጂ በ9ኛው ክፍለ ዘመን በቻይና እንደተፈለሰፈ የሚነገር ሲሆን ለዘመናዊው የጦር ቴክኖሎጂ መስፋፋትም ፈር ቀዳጅ የሚባል ነው፡፡ ይህ ግኘት በሰው ልጆች የውጊያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ ያሳደረ መሆኑም ይነገርለታል፡፡
7. ማተሚያ (PRINTING PRESS) - እንደአውሮፓውያኑ በ1439 በጀርመናዊው ዮሃንስ ጉተንበርግ የተፈጠረው ይህ መሳሪያ ለሰው ልጆች የአዲስ ህይወት መጀመሪያ ዘመን ተደርጎ በብዙዎች ይወሰዳል፡፡ ይህ አስገራሚ ቴክኖሎጂ በሰዎች እጅ እየተፃፈ የሚሰራጨውን አድካሚ የፅህፈት ስርዓት በሜካናይዝድ ማሽን በመተካት የእውቀት አድማስ በሰዎች ዘንድ በቀላሉ እንዲሰፋፋ እና የሃይማኖት አስተምህሮዎች በአለም ላይ በፍጥነት እንዲናኙ ያስቻለ አስገራሚ ግኘት ነው፡፡
8. ኤሌክትሪክ (ELECTRICITY) - የኤሌክትሪክ ፈጠራ ብዙ ብሩህ አዕምሮዎች ለሺህና ከዚያ በላይ አመታት አስተዋፅዖ ያደረጉበት እፁብ ድንቅ የሆነ የቴክኖሎጂ ግኝት ነው፡፡ በ18ኛው ክፍለ ዘመን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ቤንጃሚን ፍራንክሊን ስለኤሌክትሪክ የነበረውን የአለም መረዳት አንድ እርምጃ ያራመደ የመሪነት አበርክቶት እንደነበረው የሚገለፅ ሲሆን በምርምር ዘርፍ ደረጃ ለመስኩ የሰጠው ሁለንተናዊ ትኩረት የቴክኖሎጂውን እድገት በእጅጉ አፋጥኖታል፡፡ ከዚህ ሂደት በማስከተል በ1879 የቶማስ ኤዲሰን የብርሃን አምፖል መፈጠር የኤሌክትሪክ ቴክኖሎጂ ይበልጥ ወደሰዎች እንዲቀርብ ያስቻለ ክስተት ነው፡፡ ይህ የምንግዜም ታላቅ ፈጠራ የሰው ልጆችን የህይወት መንገድ እስከወዲያኘው የቀየረ ግሩም ቴክኖሎጂ ነው፡፡
9. የእንፋሎት ሞተር (STEAM ENGINE) - በስኮትላንዳዊው የፈጠራ ባለሙያ ጀምስ ዋት ከ1763 እስከ 1775 ተሰራ የሚባለው የእንፋሎት ሞተር ሌላኛው ለሰው ልጆች ትልቅ መሰረት የጣለ አስደናቂ የፈጠራ ውጤት ነው፡፡ ይህ የቴክኖሎጂ ግኝት በጊዜው ለነበሩት ባቡሮች፣ መርከቦች እና በጠቅላለው ለኢንዱስትሪው አብዮት ዋና የሃይል ምንጭ በመሆን ተከትሎ ለመጣው የሰው ልጅ አብርሆት ታላቅ ውለታ ያደረገ አስገራሚ ፈጠራ ነው፡፡
10. የነዳጅ ሞተር (INTERNAL COMBUSTION ENGINE) - በ19ኛው ክፍለዘመን የተዋወቀው ይህ የቴክኖሎጂ ፈጠራ በመጀመሪያ በቤልጄሚያዊው ኢንጅነር ኢትየን ሌኖየር (በ1859) የተፈጠረ ሲሆን ከጥቂት አመታት በኋላ በጀርመናዊው ኒኮላስ ኦቶ ይበልጥ ሊሻሻል ችሏል፡፡ ይህ አስገራሚ ፈጠራ የኬሚካል ኢነርጂን ወደ ሜካኒካል ኢነርጂ በመቀየር ቀድሞ የእንፋሎት ሞተር ሲሰጥ የነበረውን ግልጋሎት በተሻለ ሁኔታ በመተካት ለዘመናዊ መኪናዎችና አውሮፕላኖች ማገልገል የቻለ አስገራሚ ፈጠራ ነው፡፡
11. ስልክ (TELEPHONE) - የስኮትላንድ ተወላጁ አሌግዛንደር ግርሃም ቤል በሰው ልጆች የመገናኛ ጥበብ ውስጥ ትልቅ አብዮት የፈጠረውን የስልክ ቴክኖሎጂ በራሱ ስም ያስመዘገበ ታላቅ የፈጠራ ባለሙያ ቢሆንም ከሱ ቀደምና እሱ በነበረበት ዘመንም ብዙ የፈጠራ ባለሙያዎች ለቴክኖለጂው ማበብ የራሳቸውን አሻራ ጥለዋል፡፡ አሌግዛንደር ግርሃም ቤል አንደአውሮፓውያኑ በ1876 በኤሌክተሪክ ስልክ የመጀመሪያውን ፓትንት ካገኘ በኋላ የሰው ልጆች እርስ በእርስ የመገናኘት ልምድ እስወዲያኛው ተቀይሯል፡፡
12. ክትባት (VACCINATION) - የክትባት ግኘት ለአንዳንዶች አከራካሪ ፈጠራ ቢሆንም ብዙዎች እንደሚገልፁት ከሆነ ግን በአለም ላይ የተከሰቱ በሽታዎችን በማጥፋት እና የሰው

ልጆችን በመታደግ በኩል እስካሁን ከታዩ አስደናቂ ግኝቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው፡፡ በአለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ክትባት እንደአውሮፓውያኑ በ1796 ለፈንጣጣ (smallpox) በሽታ የተሰራው ክትባት ሲሆን ኤድዋርድ ጄነር በተባለ ተመራማሪ የተገኘ ነው፡፡ ከዚህ ክትባት በኋላ በ1885 በፈረንዊው ኬሚስትና ባዮለጂስት ሊዩስ ፓስተር የተሰራው የሬቢስ (rabies) ቫይረስ ክትባት ደግሞ ለዘመናዊው የመድሃኒት ቴክኖሎጂ ትልቅ በር የከፈተ ነበር፡፡
13. መኪና (CARS) - ተሽከርካሪ መኪናዎች የሰዎችን የጉዞ ስርዓት እና ተያይዞ የመጣውን የከተሞች ባህሪ እስከወዲያኛው የቀየረ ግሩም የቴክኖሎጂ ፈጠራ ነው፡፡ ተሽከርካሪ መኪናዎች በዘመናዊው ቅርፃቸው በአለም ላይ ብቅ ማለት የጀመሩት በ19ነኛው ክፍለ ዘመን የመጨረሻ አመታት ላይ ሲሆን በዋናነት በጀርመናዊው ካርል ቤንዝ እና ባልደረቦቹ የተከናወኑ ናቸው፡፡ ካርል ቤንዝ እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር በ1885 የመጀመሪያዋን ሞተር ብስክሌት ተግባራዊ ካደረገ በኋላ የመኪና ቴክኖሎጂ በአለም ላይ እየናኘ ሄዷል፡፡
14. አውሮፕላን (AIRPLANE) - በ1903 በአሜሪካውያን ወንድማማቾች ለውጤት የበቃው ይህ አስገራሚ ቴክኖሎጂ የሰው ልጆችን የረዥም ርቀት ጉዞ ፈጣን አማራጭ በመስጠት የትራንስፖረት ኢንዱስትሪን እስከወዲያኛው የቀየረ ነው፡፡ የአውሮፕላን ቴክኖሎጂ የአለም ሰዎችን ይበልጥ እንዲቀራረቡ በማድረግ የባህል፣ የምጣኔ ሃብት እና የእውቀት ልውውጦችን ይበልጥ ያዳበረ ቢሆንም በቴክኖሎጂው የማብሰሪያ ጊዚያት በአለም ላይ ለተከሰተው አለምአቀፍ ጦርነት ሌላ አባባሽ ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
15. ፔኒሲሊን (PENICILLIN) - እንደአውሮፓውያኑ በ1928 በስኮትላንዳዊው ሳይንቲስት አሌክዛንደር ፍሌሚንግ የተቀመረው ይህ ግኘት የፋርማሲዩቲካል ዘርፉን አንድ እርምጃ በማራመድ የመጀመሪያውን አንቲባዮቲክ መድሃኒት ለአለም ያስተዋወቀ ነው፡፡ ፔኒሲሊን እጅግ ብዛት ያላቸው ተላላፊ ባክቴሪያዎችን በመከላከል ለረዥም ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለ አንቲባዮቲክ ሲሆን ለዘመናዊው የመድሃኒት ቴክኖሎጂም ፈር ቀዳጅ የሚባል ነው፡፡
16. ሮኬቶች (ROCKETS) - ቀደምት የሚባለው የሮኬት ቴክኖሎጂ ሙከራ በቻይና የስልጣኔ ዘመናት እንደነበር የሚወሱ የታሪክ ማዛግብቶች ቢኖሩም አሁን ላይ የሚታወቀው ዘመናዊ የሮኬት ቴክኖሎጂ ግን በ20ኛው ክፍለ ዘመን የተዋወቀ ነው፡፡ ይህ ግኝት በሰው ልጆች የህዋ ምርምር እና የጠፈር አሰሳ ላይ ትልቅ አበርክቶት የነበረው ፈጠራ ሲሆን በወታደራዊው ዘርፍም የማይናቅ አስተዋፅኦ ያለው ነው፡፡
17. የኒውክለር ማብሊያ (NUCLEAR FISSION) - አተሞችን ይበልጥ ጥቃቅን ወደሆኑ ቅንጣቶች መከፋፈል እና በዚህም ከፍተኛ መጠን ያለው ኢነርጂ የመፍጠር ሂደት የኒውክለር ኃይል ማመንጫዎች እና አቶሚክ ቦምቦች እንዲፈጠሩ አስችሏል፡፡ ይህ አስገራሚ ግኘት በ20ኛው ክፍለ ዘመን በዚህ ዘርፍ ዙሪያ ሲሰሩ በነበሩ ስመጥር የፊዝክስ ሊቃውንት የተከናወነ ቢሆንም የኒውክለር ማብሊያውን በዋናነት በመስራት ረገድ ጀርመናውያኑ ኦቶ ሃን እና ፍሪትዝ ስታስመን አንዲሁም የኦስትሪያ ተወላጅ የሆኑት ሊዝ ማይትነር እና ኦቶ ፍሪሲች በቀዳሚነት ይጠቃሳሉ፡፡
18. ሴሚኮንዳክተሮች (SEMICONDUCTOR) - የአሜሪካ ወይም የአለም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ማዕከል ከሆነችወ ሲልከን ቫሊ ቅጽል ስም ጀርባ የሚገኘው የሴሚኮንዳክተር ግኘት ብዙ ነገሩ ከሲልከን የተሰራ ሲሆን የአፈጣጠር ሁኔታውም በኤሌክትሪክ ዘመን እና እየመጣ በሚገኘው ዲጂታል ዘመን መካከል ላይ ነበር፡፡ የመጀመሪያው የሴሚኮንዳክተር ቁስን የያዘ መሳሪያ እንደአውሮፓውያኑ በ1947 የተዋወቀ ሲሆን በአሜሪካውያኑ ጆን ባርደን እና ዋልተር ብራታን የተሰራ ነው፡፡
19. የግል ኮምፒውተሮች (PERSONAL COMPUTER) - አንደአውሮፓውያኑ በ1970ዎቹ የተፈጠሩት የግል ኮምፒውተሮች የሰው ልጀችን ሁለንተናዊ አቅም በማሳደግ በኩል ተወዳዳሪ አልነበራቸውም፡፡ በ1974 በማይክሮ ኢኒስትሩመንቴሽን እና ቴሌሜትሪ ሲስተም (MITS) የመጀመሪያ የሚባለው የግል ኮምፒውተር ከተዋወቀ በኋላ ቀጥለው የመጡት እንደ አፕል፣ ማይክሮሶፍት እና አይ ቢ ኤም ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎች ዘርፉን እስከወዲያኛው አራቀውታል፡፡
20. በይነ መረብ (INTERNET) - አሁን አሁን የሰው ልጅ እስትንፋስ እስከመሆን የደረሰው ይህ አስገራሚ ግኘት ከ1960ዎቹ ጀምሮ ሙከራዎች ሲደረጉበት የቆየ ቢሆንም አሁን በምናውቀም መልኩ ለሰው ልጆች መድረስ የጀመረው ከ1990ዎቹ ጀምሮ ነው፡፡ በጊዜው አንግሊዛዊው ቲም በርነር-ሊ የመጀመሪያውን የበይነ መረብ መግባቢያ የአለም አቀፍ ድር (WWW) ከቀመረ በኋላ አጠቃላይ የአለም መልክ ሊቀየር ችሏል፡፡ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ንግዳችን፣ ፖለቲካችን፣ መዘናኛችን የፈለጋችሁን ስም ስጡት ብቻ ሁለ ነገራችን በኢንተርኔት እና በኢንተርኔት ሁኗል፡፡
ምንጭ፡ Bigthink
https://bigthink.com/paul-ratner/top-20-greatest-inventions-of-all-time

Big Think
Top 20 greatest inventions of all time
The most impactful technology inventions in history are ranked.
የአየር ንብረት ለውጥ እና የምግብ ዋስትና
======================
የምግብ ዋስትና በመሰረታዊነት አደጋ ውስጥ ሊገባባቸው ከሚችሉ ብዙ ምክንያቶች መካከል የአየር ንብረት ለውጥ በቀዳሚነት ይቀመጣል፡፡ በቅርቡ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በተሰራ አንድ ጥናት ይህ የአየር ንብረት ለውጥ በምን ያህል መጠን የሰብል ምርታማነትን እና አለም አቀፍ የምግብ ዋስትናን እየተፈታተነ እንደሆነ ለማመልከት ሞክሯል፡፡
በሚኒሶታ ዩኒቨርስቲ የአካባቢ ጥናት ቡድን የተሰራው ይህ ምርምር በዓለም ዙሪያ በሰብል ምርታማነት ላይ ለአራት ዓመታት መረጃ በመሰብሰብ በምን ያክል መጠን በአየር ንብረት ለውጥ ወስጥ ያሉ ጉዳዮች የምግብ ዋስትናን እየተፈታተኑት እንዳለ ለማሳየት የሚሞክር ነው፡፡ የጥናት ቡድኑ በአለም ዙሪያ የፍጆታ መጠናቸው ከፍተኛ በሆኑ አስር የሰብል ምርቶች ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ እንደ በቆሎ፣ ሩዝ፣ ስንዴ እና ማሽላ ያሉ በአብዛኛው የአለም ክፍል የሚበቅሉ ታዋቂ ሰብሎች በምርምሩ ላይ ሊካተቱ ችለዋል፡፡ በአለማችን ላይ ከፍተኛ የፍጆታ መጠን ያላቸው እነዚህን አስር የሰብል ምርቶች 83 በመቶ የሚሆነውን የምግብ ካሎሪን የሚስገኙ የምርት አይነቶች እንደሆኑም ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡
በአጭር አመታት ውስጥ በፍጥነት እየተቀያየረ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ የጥናት ቡድኑ በለያቸው 10 የሰብል ዝርያዎች ላይ ቀላል የማይባል ተፅዕኖ እያሳደረ ቢሆንም በተወሰኑ የአለም ክፍሎችና የሰብል ዝርያዎች ላይ ያለው የምርት ሁኔታ ተነፃፃሪ እድገት የሚይበት ሆነ ተገኝቷል፡፡ ይሁንና እንደአጠቃለይ ያለው ውጤት ሲታይ በአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ በአብዛኛው የአለም ክፍል ከፍተኛ ምርት የሚታይባቸው ሰብሎች ቀንሰው ሲገኙ፤ እንደ ሩዝና ስንዴ ያሉ ዋና ዋና የምግብ ዓይነቶች ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ደረጃ ምርታቸው ቀንሶ የተገኘ ነው፡፡
የጥናት ቡድኑ 20,000 በሚደርሱ በተለያዩ ሀገራቱ በተመረጡ መገኛዎች የሙቀት እና ዝናብ ተፅዕኖዎችን በመተንተን የሰብል ምርታማነት እንዴት በቀጥታ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት አደጋ ውስጥ እንደሚገባ ለማመልከት ሞክሯል፡፡ ከጥናቱ የተገኙ ውጤቶች ከቦታውና ከሰብል ዝርያዎች ጋር በተያየዘ አንዱ ከአንዱ ልዩነት ቢኖራቸውም እንደአጠቃላይ ከምርምሩ የተገኘው ውጤት እንደሚያመለከተው በአለማችን ከፍተኛ ምርት የሚታይባቸው ዋና ዋና የሰብል አይነቶች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በመቀነስ ላይ መሆናቸውን ነው፡፡ ለአብነት በጥናቱ መሰረት የሩዝ ምርት በየዓመቱ ከ0.3% በላይ የምርት መቀነስ የታየበት ሲሆን በአለምአቀፍ ደረጃ የስንዴ ምርትም በየአመቱ በአማካኝ 0.9% እየቀነሰ እንደሚገኝ ጥናቱ ያሳያል፡፡ ይህም በቀጥታ የምግብ ዋስታናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በብዙ ፈርጆች እየተፈታተነው የሚገኝ ነው፡፡ ከአብዛኞቹ የሰብል ምርቶች ድርቅን እና የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅም ያለው የማሽላ ምርት ከሌሎቹ በተለየ ሁኔታ መጠነኛ እድገት የታየበት ሲሆን፤ በተለይም ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት፣ በደቡብ ምስራቅ እስያ እና በሌሎች አንዳንድ ቦታዎች ከ0.7 እስከ 0.9 እድገት የታየበት ምርት እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡
ምንጭ፡ Theconversation
ለተጨማሪ https://theconversation.com/to-what-extent-does-climate-change-affect-food-insecurity-what-we-found-in-lesotho-15652

በስፖርቱ ዘርፍ ለሚከሰት ሙስናና ማጭበርበር የቀረበ መፍትሔ
***************************************
በፖርትስሞውዝ ዩኒቨርሲቲ የተሰራ አንድ ጥናት በስፖርታዊ ውድድሮች ጊዜ የሚፈጠርን ሙስናና ማጭበርበር ለመከላከል የሚያስችሉ መፍትሔዎችን አቀረበ፡፡ በአለማችን በሚከናወኑ ግዙፋን እንደ ኦሎምፒክ፣ የአለም ዋንጫ እና ሻምፒዮንስ ሊግ ያሉ ውድድሮች እንደ ሙስና ካሉ የውድድሮቹን ድምቀት ከሚያደበዝዙ ችግሮች መጠበቅ የሚያስችል መፍትሔን ነው ምርምሩ ያቀረበው፡፡
በስፖርቱ ዘርፍ ከሚስተዋሉ የሙስናና የማጭበርበር ድርጊቶች መካከል ስልጣንን ያለ አግባብ መጠቀም፣ የገንዘብ ድለላ፣ የሀሰት ፍርድ እና የተሳሳተ ምርጫ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ስፖርት ኢን ሶሳይቲ በሚባል ህትመት ይፋ የተደረገው የምርምር ውጤት በስፖርቱ ዘርፍ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸውን የስፖርት አስተዳደር ሰዎች፣ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ የቡድን መሪዎች እና ጋዜጠኞችን ያካተተ ጥናት የተደረገበት ነው፡፡
ጥናቱን ያደረገችው የፖርትስሞውዝ ዩኒቨርሲቲዋ ክርስቲና ፍሊፖ በዘርፉ ሙስናና የተለያዩ ህገ-ወጥ ድርጊቶች እንደተበራከቱ ተናግራለች፡፡ ተመራማሪዋ አክላም በዘርፉ ስላለው ህገ-ወጥ አሰራር እጅግ ብዙ ጥናት የተደረገ ቢሆን የመፍትሔ ሀሳብ ያላቸው ግን እምብዛም አይስተዋሉም ትላለች፡፡
ይህም ጥናት የስፖርቱን ዘርፍ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ሪፎርም የሚሰራበትን የመፍትሔ ሀሳብ ያቀረበ ነው፡፡ ተመራማሪዋ ከ6 ሀገራ የተውጣጡ 39 ተሳታፊዎችን ያካተተ ጥናት ከ2018 እስከ 2020 ድረስ አካሂዳለች፡፡ በዚህም እንደ ተጠያቂነት፣ የሀላፊነት ስሜትና የውሳኔ አሰጣጥ ችግሮች በብዛት የሚስተዋሉ ችግሮች እንደሆኑ ጥናቱ አመልክቷል፡፡
ይህች የጸረ- ሙስና ኤክስፐርት የሆነችው ተመራማሪ እንደምትለው ከሆነ የስፖርቱ ዘርፍ አስተዳደር ሀላፊነት የተጣለባቸው ሰዎች በፖለቲከኞች ውስጥ እንዳለው የውስጥ መመሪያና ቁጥጥር ስርዓት ሊዘረጋላቸው ይገባል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለሚፈጠሩ ጥፋቶችን የአሰራር ግድፈቶች ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድባቸው አሰራሮች ሊዘረጉ ይገባል ስትል በጥናቷ አመላክታለች፡፡
በአጠቃላይም በጥናቱ የገንዘብ ነክ (በስጦታ፣ በትርፍ እና ወጭ) ምዝገባ፣ ገለልተኛ የሆነ የሶስተኛ ወገን ክትትል፣ ታማኝ የሆነ የጨረታ ስርዓት፣ ተአማኒ የሆነ የቅጥርና የምደባ ስርዓት፣ ተገቢ የሆነ የቅሬታ አካሄድ ስርዓት እና ሌሎች ተጨማሪ የመፍትሔ ሀሳቦች ተመላክተዋል፡፡
ምንጭ phys.org
ተጨማሪ ንባብ https://phys.org/news/2021-08-reforms-bribery-corruption-major-sporting.html

phys.org
Study suggests reforms to prevent bribery and corruption at major sporting events
Bribery and corruption at huge sporting events—such as the Olympics, World Cups and UEFA club competition finals—can and must be prevented, a new paper from the University of Portsmouth argues.
አረንጓዴ አሻራን በአረንጓዴዋ ቡራዩ
***************************
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ቤተሰቦች ዛሬ ነሐሴ 6 በኦሮሚያ ክልል የቡራዩ ከተማ ልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በመገኘት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን አከናውነዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ከኢንስቲትዩቱ የተለያዩ ማዕከላት የተውጣጡ በርካታ ሰራተኞች እና የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኞች ከዚህ ቀደምም የበጎ ፍቀድ አገልግሎት አንድ አካል አድርገው ለበርካታ ተከታታይ ዓመታት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡ ለአብነት ያህል በአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ፣ አለልቱ እና ሸጎሌ የተከናወኑት የችግኝ መትከል መርሃ ግብሮች ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ታድያ ለዚህ ሀገርን አረንጓዴ ሸማ የማልበስ በጎ ተግባር አዲስ ያልሆኑት የኢንስቲትዩታችን ቤተሰቦች ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህም አረንጓዴ አሻራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ሲከናወን በቆየው ሀገራዊ የችግኝ ተከላ እንቅስቃሴ ላይም ይህ ተቋማዊ ባህል ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በ6 ወር ውስጥ ብቻ ቁመቱ በ30 ሜትር ያደገው ተራራ
==================
በአህጉረ አውሮፓ ረጅሙ እና ንቁ እሳተ ገሞራ ያለበት የኤትና ተራራ በ6 ወራት ውስጥ ብቻ ቁመቱ በ30 ሜትር ማደጉን ከሳተላይት የተወሰዱ ምስሎች አረጋገጡ፡፡ በጣልያኗ ሲሲሊ አቅራብያ የሚገኘው ተራራው ካሉት አራት ጫፎች መካከል በእድሜ ትንሹ እና ንቁ እሳተ ገሞራ ያለበት አንደኛው ጫፍ አሁን ላይ ቁመቱ ከባህር ጠለል በላይ 3,357 ሜትር ደርሶ ከአራቱ የተራራው ጫፎች በቁመት ቀዳሚው ሆኗል ሲል የጣልያን ብሔራዊ ጂኦፊዚክስ እና ስነ እሳተ ገሞራ ኢንስቲትዩት (INGV) አስታውቋል፡፡
ይህ ድንገተኛ የቁመት መርዘም የተከሰተው በተራራው ደቡባዊ ክፍል አካባቢ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 50 ያህል የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎች ከመፈጠራቸውና የእሳተ ገሞራው ቅርፅም እንዲለወጥ ከማድረጋቸው ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ይህ ፈጣን እድገት ታድያ ላለፉት 40 ዓመታት የኤትና ተራራ ረጅሙ ጫፍ የነበረው ሰሜናዊ ክፍሉን በቁመት እንዲበልጠው አስችሎታል፡፡
ከዚህ ቀደም በአውሮፓውያኑ 1980 እና 1981 በሰሜን ምስራቃዊ የተራራው ክፍል የፈነዳው እሳተ ገሞራ ይህኛው የተራራው ክፍል ከባህር ጠለል በላይ ያለው ቁመት 3,350 ሜትር እንዲደርስ አድርጎት ነበር፡፡ ሆኖም ከዚያ ቀጥሎ ባሉት ዓመታት ውስጥ የተራራው ጫፎች መደርመስ መጀመራቸውን ተከትሎ የዚህኛው ተራራ ክፍል ቁመትም እያሽቆለቆለ እንዲመጣ ሆኗል፡፡ አሁን ላይ ይህ ሰሜናዊ የተራራው ክፍል ቁመቱ ወደ 3,326 ሜትር ወርዷል፡፡
የኤትና ተራራ ቀድሞ አጠገቡ ባለው ባህር ውስጥ የነበረና እሳተ ገሞራ እንደነበረና ኋላ ላይ የሚተፋውን የቀለጠ አለት ተጠቅሞ እራሱን በማደላደል ቀስ በቀስ ቁመቱን እየጨመረ ወደ የብስ ተራራነት እንደተለወጠ ይታመናል፡፡ አሁን ላይ ተራራው ላለፉት 300 ሺህ ዓመታት ከእሳተ ገሞራው ሲለቅ በቆየው ቅልጥ አለት ተሸፍኖ ይገኛል፡፡
ምንጭ፤ Live Science
ለተጨማሪ፤ https://www.livescience.com/mount-etna-grows-100-feet.html

livescience.com
Mount Etna is 100 feet taller than it was 6 months ago
It's the result of about 50 eruptions over the past half year.
ብዙ ሚሊዮኖችን ዘርፈው የመለሱት ሃከሮች
========================
በሳለፍነው ሳምንት የመረጃ መንታፊዎች ወይም ሃከሮች በዲጂታል ገንዘብ ታሪክ በአንድ ጊዜ የተፈጸመ እና እጅግ ግዙፍ የተባለዉን 600 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚተመን ክሪፕቶከረንሲ መዝረፋቸዉ ሲነገር ነበር። ይህ ከበድ ያለ የሳይበር ጥቃት በብሎክቼን ዘርፍ ላይ በተሰማራውና ፖሊ ኔትወርክ በተባለው ግዙፍ ድርጅት ያጋጠመ ሲሆን፤ በሲስተሙ ላይ ባጋጠመ መጠነኛ ተጋላጭነት በሺዎች የሚቆጠሩ የዲጂታል ገንዘቦች የተዘረፈበት ክስተት ነው፡፡
ከደረሰው የሳይበር ጥቃት በኋላ ድርጅቱ በቲውተር ገፁ እንደጠቀሰው የተካሄደበት የክሪፕቶከረንሲ ዝርፊያ በመደበኛው ገንዘብ ሲተመን እስካሁን ካጋጠሙ ስርቆቶች ተወዳዳሪ እንደሌለው እና ዝርፊያውም በ10 ሺ የሚቆጠሩ የክሪፕቶ ደንበኞቹን በቀጥታ የሚያጠቃ መሆኑን አንስቷል፡፡ ደርጅቱ አክሎም ዝርፊውን ያካሄዱ የመረጃ ጠላፊዎች በየትኛውም ሀገር ህግ ትልቅ የኢኮኖሚ ወንጀል መፈፀማቸውን ተረድተው መፍትሄ ሊያመጣ የሚችል ስምምነት ከድርጅቱ ጋር እንዲመሰርቱ በቲዊተር መግለጫው አስታውቋ ነበር፡፡
አሁን ላይ ይህን የሳይበር ጥቃት ያካሄዱ ሰዎች የዘረፉትን 600 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው የዲጂታል ገንዘብ ምንም አይነት ድርድር ሳያደርጉ ለድርጅቱ መመለሳቸው ታውቋል፡፡ Mr. White Hat በሚል ስም የተጠቀሱት የሳይበር ጥቃት አድራሾች እንዲህ ያሉ የደህንነት ጉድለቶችን ለማስተማር እና የግንዛቤ ስራ ለመስራት የሚንቀሳቀሱ ethical hacker መሆናቸውም ተነግሯል፡፡
የብሎክቼን ፎረንሲክ ምርመራ ላይ የሚሰራው ቼንአናሊስስ እንደጠቀሰው እስካሁን ከተፈፀሙት የሳይበር ጥቃቶች ከባድ በሆነው በዚህ ጥቃት ላይ የተሳተፉ ሀከሮች የሰረቁትን ገንዘብ ለመውሰድ ምንም አላማ እንዳልነበራቸው እና የድርጅቱን የብሎክቼን ስርዓት ለመፈተሽና ከፍተቱን ለመለየት ያደረጉት ሙከራ መሆኑን አንስቷል፡፡ የፖሊ ኔትወርክ ኩባንያ በብሎክቼን ሲስተሙ ላይ የነበረውን የደህንነት ተጋላጭነት ለጠቆሙት ለእነዚህ ሰላማዊ የመረጃ ጠላፊዎች የግማሽ ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ቢያቀርብም ጥቃቱን ያደረሱት ሃከሮች ምንም አይነት ገንዘብ መቀበል እንደማይፈልጉ ቼንአናሊስስ አስታውቀዋል፡፡
በብሎክቼን ያልተማከለ የዲጂታል መዝገብ ስርዓት እንዳንዱ ግብይቶች በይፋ የሚታወቁ በመሆናቸው ማንነቱ ያልታወቀ የመረጃ ጠላፊ የወሰደውን ገንዘብ በቀላሉ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚቸገር መሆኑን እነዚሁ የብሎክቼን ፎረንሲክ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
ምንጭ፡ CNN
ተጨማሪ https://edition.cnn.com/.../poly-network-hack.../index.html

በግሪክ የተከሰተው ሰደድ እሳት በሳተላይት ምስል
========================
በሜዲትራንያን ባህር አካባቢ በሚገኙ ሃገራት ያጋጠመውን ከፍተኛ የሙቀት መጠን ተከትሎ የተቀሰቀሰው የእሳት ሰደድ ከባድ ጉዳቶችን ሲስከትል እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህ ከፍተኛ የሰደድ እሳት ላለፉት 10 ቀናት በእጅጉ ስትፈተን የቆየችው ግሪክ ባጋጠማት አደጋ ከፍተኛ ስነ ምህዳራዊ ጉዳትን አስተናግዳለች፡፡ በሰደድ እሳቱ የግሪክ ጥንታዊ የኦሎምፒክ ስፍራዎች ጭምር አደጋ ላይ ወድቀው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በትንሹ 50 ሺ ሄክታር የሚሸፍን ደን በቃጠሎው ወድሟል፡፡
የሰደድ እሳቱ ተከስቶ በነበረባቸው የሃገሪቱ አካባቢዎች ዝናብ መጣሉንና የሙቀት መጠኑ መቀነሱን ተከትሎ የእሳቱ መጠን እያነሰ እና በቁጥጥር ስር እየዋለ እንደሚገኝ የሃገሪቱ የዜጎች ጥበቃ የድንገተኛ እና እሳት አደጋዎች ዲፓርትመንት አስታውቋል፡፡ ኢቪያ በምትባለው የግሪክ ደሴት የተነሳውን ሰደድ እሳት በሳተላይት ምስል ያቀረበው የኮፐርኒከስ ሳተይላት የአለማችን ስጋት በሆነው የሙቀት መጨመር ምክንያት የተነሳው ሰደድ እሳት ያስከተለውን ከፍተኛ ጉዳት በቀላሉ ያስመለከተ ነው፡፡
ከኮፐርኒከስ ሳተይላት የተገኘው ምስል ብዙ የቃል ማብራራሪየዎች ሳያስፈልጉ የምድራቸን ሙቀት መጨመር እያስከተለ ያለውን ትልቅ አደጋ እና የደቀነውን የወደፊት ስጋት የሚያሳይ ነው፡፡ በደሴቲቷ ለ10 ቀን ብቻ በቆየው ሰደድ እሳት 50,910 ሄክታር መሬት ደን መጥፋቱ እና ከፍተኛ የስነ ምህዳር መዛባት መፍጠሩ ለአለማችን ከባድ መልእክት ይኖረዋል፡፡
ከሶስት አስርት አመታት በኋላ በታሪኩ እጅግ ከባድ የተባለውን የሰደድ እሳት ያስተናገደችው ግሪክ በአሰቃቂው አደጋ ብዙ ቤቶች፣ የንግድ ተቋማት እና ድርጅቶች ከተቃጠሉባት በኋላ የሰደድ እሳቱን መቆጣጠር የቻለችው እሳቱ ተከስቶ በነበረባቸው የሃገሪቱ አካባቢዎች ዝናብ መጣሉን ተከትሎ ነው፡፡ ይሁንና አሁንም በሙቀቱ የተነሳ ዳግም ሊከሰት ይችላል የሚባለው የሰደድ እሳት ከተፈጥሮ ዝናብ ውጪ በሰዎች ርብርብ ብቻ ለማጥፋት አስቸጋሪ መሆኑ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡
https://interestingengineering.com/satellite-images...

የመሬት መንሸራተት እና መንስኤዎቹ
************************************
ከሰሞኑን በሀገራችን ሁለት የተለያዩ የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ተከስተው መወያያ ጉዳይ ሆነው ነበር፡፡ ባሳለፍነው ሐሙስ ዓባይ በረሃ ውስጥ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር የሚወስደውን መንገድ ዘግቶት ቆይቷል፡፡ ከዚያ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ነሐሴ 5 2013 ዓ.ም በምስራቅ ወለጋ ባኮ-ሻምቡ መንገድ ላይ ያጋጠመ መሬት መንሸራተትም እንዲሁ የተሸከርካሪ እንቅስቃሴን ሲያስተጓጉል ተመልክተናል፡፡ ለዛሬ እኛም እነዚህ ክስተቶችን ሰበብ አድርገን ስለ አስደናቂው መሬት መንሸራተት የተወሰኑ ነገሮችን ልንላችሁ ወደናልና አብራችሁን ቆዩ፡፡
የመሬት መንሸራተት የሚባለው መሬቱ፣ አለቶች፣ ወይም ስብርባሪ/ውጋጅ በቁልቁለታማ አካባቢ ላይ ወደታች ሲንቀሳቀስ ነው፡፡ እነዚህ የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ክስተቶች በዋናነት ዝናብ፣ ድርቅ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ እሳተ ገሞራ ወይም ሌሎች ቁልቁለታማ ቦታው ተረጋግቶ እንዳይቀመጥ በሚያደርጉ ሁናቴዎች ምክንያት ይፈጠራሉ፡፡
የመሬት መንሸራተቶች ከሌሎች የስነ-ምድር (Geological) ክስተቶች በተለየ በብዙ አካባቢዎች ተደጋግመው የሚታዩ ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ ህዝብ ተሰብስቦ በሚኖርባቸው አካባቢዎች የሚከሰቱ የመሬት መንሸራተቶች ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመትን ሲያስከትሉ ይታያል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ከአውሮፓውያኑ 1998 እስከ 2017 ድረስ ባሉት 20 ዓመታት ውስጥ ብቻ የመሬት መንሸራተት አደጋዎች በዓለማችን 4.8 ሚሊዮን ሰዎች ላይ ተፅዕንኦ ያደረሱ ሲሆን ቁጥራቸው ከ18 ሺህ የሚልቁትንም ህይወት ቀጥፈዋል፡፡
የመሬት መንሸራተቶች ሦስት አባይት መቀስቀሻ ምክንያቶች አሏቸው፤ ስነ-ምድራዊ፣ ስነ-ቅርፃዊ (Morphology) እና የሰው ልጅ ተግባራት፡፡ ስነ-ምድራዊ ምክንያት ሲባል መሬቱ ወይም አለቱ ጠንካራ ያልሆነ፣ የተሰነጣጠቀ አልያም ደግሞ የመሬቱ ንብርብር ንጣፎች አንዱ ከሌላው የተለያየ ጥንካሬ እና ጫናን የመቋቋም አቅም (Stiffness) ሲኖራቸው የሚከሰት ነው፡፡
ስነ-ቅርፃዊ በበኩሉ በተለይም እላያቸው ላይ የነበሩትን እፅዋት በእሳት አልያም ድርቅ ሳብያ የተገፈፉ ቁልቁለታማ ስፍራዎች ለመሬት መንሸራተት ይበልጥ ተጋላጭ ከመሆናቸው ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ይህም ቀድሞ ዛፍም ሆነ ሌሎች እፅዋት በስራቸው አማካኝነት አፈሩን ቆንጥጠው ይዘውት ይቆዩ የነበር በመሆኑ የእነርሱ በስፍራው አለመኖር መሬቱ እንዲንሸራተት ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሆኖም ከዕፅዋት መጥፋት ባሻገር በቀዳሚነት የሚጠቀሰው የመሬት መንሸራተት ከመሬት መሸርሸርና በአየር ንብረቱ ሳብያ ከሚመጣ የመሬት ጥንካሬ መኮሰስ መንስኤነት የሚከሰተው የመሬት መንሸራተት ነው፡፡
በሀገራችን የሚቀሰቀሱ የመሬት መንሸራተቶችም ብዙውን ጊዜ መሰል በከባድ ዝናብ ምክንያትነት የተቀሰቀሱ መሆናቸውን በተለያዩ ዘገባዎች ሰምተናል፡፡ እንዲሁ አንድ ወቅት ላይ በአሜሪካኗ የዩታህ ግዛት በዘነበ ከባድ ዝናብ እና በፍጥነት እየቀለጠ የነበረውን በረዶ ተከትሎ የተከሰተ የመሬት መንሸራተት 305 ሜትር ወደ ጎን የሚሰፋ፣ 1.6 ኪ.ሜ የሚረዝምና 61 ሜትር የሚወፍር ግዙፍ የመሬት መንሸተትን አስከትሎ ነበር፡፡ ይህ በአውዳሚነቱ በሀገሪቱ እስከዛሬ ወደር ያልተገኘለት የመሬት መንሸራተት ታድያ ከበታቹ ይገኝ የነበረ ወንዝ ፍሰትን ከመገደብም ባሻገር የባቡር መንገድ እና አውራ ጎዳናን በመዝጋት 400 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ውድመትን አምጥቶ ነበር፡፡
የሰው ልጆች ምክንያት የሆኑበት የመሬት መንሸራተት አደጋዎችን ያየን እንደሆን በዋናነት እንደ ግብርና እና ግንባታ ባሉት እንቅስቃሴዎች ሳብያ የሚከሰቱትን ይመለከታል፡፡ የመስኖ እርሻ፣ ደን ምንጣሮ፣ ቁፋሮ እና ድንገተኛ የውሃ ፍሰት ቁልቁለቱ እንዳይረጋጋና ጠንካራ ሆኖ እንዳይቀጥል በማድረግ ለመሬት መንሸራተት ያጋልጡታል፡፡
ልክ እንደ መንስኤያቸው ሁሉ የመሬት መንሸራተቶች በአይነታቸውም ይለያያሉ፡፡ ለምሳሌ በእንቅስቃሴያቸው ረገድ ካየን የሚንሸራተት መሬት በመውደቅ፣ መናድ፣ መፍሰስ ወዘተ… መልኩ ሊንቀሳቀስ ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ የመሬት መንሸራተቶች በደረጃ ቅርፅ እና ትራንዝሌሽናል መልኩም ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ፡፡
ትራንዝሌሽናል የመሬት መንሸራተት፤ በመሬቱ ገፅ ላይ ያሉት ቁሶች በውስጥ ካሉት ጠንካራ የመሬቱ ክፍሎች ተለይተው የሚንሸራተቱበት ነው፡፡ በዚህ አይነቱ የመሬት መንሸራተት ከላይ ያለው ለስላሳ ክፍል በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከጠንካራው የታችኛው ክፍል ሊለያይ ይችላል፡፡
የደረጃ ቅርፅ ያላቸው መሬት መንሸራተቶች፤ ይህ በመሬቱ ገፅ ላይ ያሉት ቁሶች ወደጎን ወይም መወጣጫ ደረጃ የሚመስል ቅርፅ ሰርተው ሲንቀሳቀሱ ይፈጠራል፡፡ ይህም እንደ መሬት መንቀጥቀጥ ያለ ጠንካራ ኃይል ምድሩ ልክ እንደ ውሃ በፍጥነት ሲንጠው የሚከሰት ነው፡፡
ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው እነዚህ የመሬት መንሸራተቶች ሲነሱ በውስጣቸው ድንጋይ፣ አፈር፣ እፅዋት ወይም ውሃን በመያዝ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በተራራ ጫፍ ላይ የተነሳ መሬት መንሸራተትን ስናይ ደረቅና እየቀለጠ ያለ በረዶን በውስጡ ይዞ ሊነጉድ ይችላል፤ በአካባቢው አየር ንብረት እና የተራራው ከፍታ የሚወሰን ቢሆንም፡፡ የመሬት መንሸራተቱ የተነሳው በእሳተ ገሞራ ሳብያ ሲሆን ደግሞ ከፍንዳታው የሚወጣ አመድ እና ቅልጥ አለትን ይዞ ይወርዳል፡፡
እዚህ ላይ ለመጥቀስ በእሳተ ገሞራ ሳብያ የሚነሱት የመሬት መንሸራተቶች ላሀራስ በሚል ስያሜ የሚጠሩና ከመሬት መንሸራተቶችም እጅግ አደገኛ የሚባሉት ናቸው፡፡ ለምሳሌ እስከዛሬ በምድራችን ከተመዘገቡት የመሬት መንሸራተቶች ሁሉ ቀዳሚ የሆነው የቅድስት ሄለንስ ተራራ መሬት መንሸራተት ለዚህ ማሳያ ነው፡፡ ይህ በአሜሪካኗ የዋሽግተን ግዛት የተፈጠረ እሳተ ገሞራ አመጣሽ መሬት መንሸራተት 2.9 ኪዩቢክ ኪ.ሜ የሚሆንና 62 ካሬ ኪ.ሜ ቦታን የሚሸፍን የአመድ፣ አለት፣ አፈር፣ እፅዋት እና ውሃ ድብልቅን ከተራራው ላይ ተገምሶ እንዲንሸራተት አድርጓል፡፡ ይህ የተንሸራተተው የተራራው አካል የሸፈነውን መሬት ከሀገራችን ከተሞች ስፋት ጋር ብናነፃፅረው ከሀዋሳ እና መቐለ የበለጠ፣ የጎንደር አንድ ሦስተኛ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባን አንድ ስምንተኛ መሬት የሚሸፍን ነው፡፡ ይህን መሰል እሳተ ገሞራ አመጣሽ የመሬት መንሸራተቶች መርዛማ ንጥረ ነገርን በውስጣቸው የያዙ መሆናቸውም ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡
ሌላው አንዱ መሬት መንሸራተት ከሌላኛው የሚለይበት ጉዳይ የሚንሸራተቱበት ፍጥነት ነው፡፡ አንዳንዶቹ በሴኮንድ በርካታ ሜትሮችን በሚጓዝ ከባድ ፍጥነት ሲንሸራተቱ ሌሎቹ ደግሞ ዘገምተኛ ሆነው በዓመት አንድ እና ሁለት ሴ.ሜ ብቻ ይንቃሰቀሳሉ፡፡ ለዚህ በውስጣቸው ይዘውት የሚንሸራተቱት የውሃ፣ በረዶ እና አየር መጠን መለያየት የራሱን ሚና ይጫወታል፡፡ ለምሳሌ የጭቃ መንሸራተት ተብለው የሚታወቁት የመሬት መንሸራተቶች በውስጣቸው ከፍተኛ ውሃ የያዙና እንቅስቃሴያቸውም በጣም ፈጣን ነው፡፡ በሌላ መልኩ የተለያየ ዓይነት ቁስ ይዘው የሚንቀሳቀሱና በውስጣቸው ያለው የእንቅስቃሴ አይነትም የተዘበራረቀ የሆኑ ውስብስብ የመሬት መንሸራተቶች አሉ፡፡