የሳይበር ደህንነት ማስገንዘቢያ መርሃ-ግብር ታከሄደ
=========================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በየሳምንቱ ሃሙስ የሚያዘጋጀው የቴክኢን ሴሚናር በዛሬው ዕለትም የሳይበር ደህንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ተካሂዷል፡፡ በዛሬው የመወያያ መድረክ በኢንስቲትዩቱ ውስጥ በተመራማሪነት እያገለጉ ያሉት አቶ ገብሬ ኩታኖ ስለ ሳይበር ምህዳርና ደህንነት፣ ያሳይበር ስጋት በአለም አቀፍና በሃገር ውስጥ ምን መልክ እንዳለው፣ የሳይበር ጥቃቶች በምን መልኩ እየተፈጸሙ እንደሚገኝ እና ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ተቋም ድረስ የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል ምን መደረግ አንደሚኖርበት በሚሉት ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
የሳይበር ደህንነት አውታረ-መረቦችን፣ መሣሪያዎችን፣ የሶፍትዌር ፕሮግራሞችን እና መረጃዎችን ከሳይበር ጥቃቶች ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑ ቴክኖሎጂ እና ሂደቶችን በመያዝ የሚሰራ መሆኑን ያስረዱት አቶ ገብሬ በተቋም ደረጃ ለሳይበር ጥቃት ሊያጋልጡን የሚችሉ ማንኛውንም ክፍተቶችን በመድፈን እና ሊወሰዱ የሚገቡ አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን በማድረግ ከማንኛውም የሳይበር ጥቃት ራስንና ተቋምን መከላከል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
አቶ ገብሬ አክለውም የሳይበር ጥቃት ሆን ተብሎ ያልተፈቀዱ የኮምፒውተር ስርዓቶች፣ መሰረተ-ልማቶች እና ኔትዎርኮች ላይ አጥፊ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም በህገወጥ መንገድ ዳታዎችን የመበዝበዝ እና አገልግሎት የማስተጓጎል መጥፎ ተግባር በመሆኑ ማንኛውም በሳይበር ምህዳር ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰቦች ድርጅታችን አነስተኛ ስለሆነ የሳይበር ጥቃት ሊደርስበት አይችልም የሚል የተሰሳሳተ ሃሳብ ከማራመድ አንስቶ ሌሎች አጋላጭ አመለካከቶችን በመቅረፍ ሊደርስ የሚችልን ጉዳት መቀነስ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብዙ የመንግስት ተቋማት ተዳጋግሞ እየታ ያለው እና እየጨመረ የመጣውን የሳይበር ጥቃት ለመከላከል በሃገር አቅፍ ደረጃ የተለያዩ የሳይበር ደህንነት ማስገንዘቢያ መርሃ-ግብሮች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡ የስራ ዘርፋቸው ከበይነ-መረብ ግንኙነት ጋር ብዙም ያልራቀ የመንግስት ተቋማት ለማንኛውም የሳይበር ጥቃት ተጋላጭ የመሆን እድል ስለሚኖራቸው መሰል መርሃግብሮች ተጠናክረው መቀጠላቸው እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በተለይም ሀገራችን የዲጂታል ምጣኔ ሃብት ግንባታ ላይ ሰፊ እቅድ ይዛ በምትንቀሳቀስበት በአሁን ወቅት የትኛውም ከዲጂታል ትግበራዎች በዋናነት ከመረጃና የመረጃ መሰረተ ልማት ጋር የሚያያዙ በመሆናቸው ለየትኛውም የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነታቸው ሰፊ ነው።
ከዚህ አንጻር ሁለም የመንግስት ተቋማት እና ባለድርሻ አካለት እየጨመረ የመጣውን የዲጂታል የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሚመጥን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ይዘው እንዲገኙ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ብዙ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ፕሮግራሞችን በመቅረፅ የተለያዩ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ በውይይቱ ላይ የተሳተፉት አቶ ሱራፌል ማሃሪ ተናግረዋል፡፡

ኢ ኢንቫይሮመንት እና የተፈጥሮ መጎዳት
======================
አየር ላይ የተለያዩ በካይ ወይም መጥፎ ጋዞች ሲገኙና እነሱን ተከትሎ ዝናብ ሰወርድ የሚወርደውን ዝናብ አሲዳማ ዝናብ እንለዋለን። ልክ እንደሌሎቹ ችግሮች አሲዳማ ዝናብም ከኢንዱስትሪ በሚወጡ ጭሶችና አንዳንዴ ከሚከሰት እሳተገሞራ ውስጥ በሚወጡ ጋዞች ይከሰታል። አሲዳማ ዝናብ ለሰዎች ጤንነት፣ ለዱር ሕይወትና በውሃ ውስጥ ለሚኖሩ ፍጥረቶች አደገኛ ስጋት አለው። ከላይ የተጠቀሱትን በዓለም ላይ በመከሰት ያሉ ትልልቅ ችግሮችን ስንመለከት ከፍተኛ አደጋ ውስጥ እንዳለን መመልከት ይቻላል።
የሰው ልጅ በዚህ ጥፋቱ ከቀጠለ ወደፊቱ ለሚመጣው ቀጣይ ትውልድ ጥሎ የሚያልፈው ነገር ከባድ ሊሆን ይችላል። የዓለም ህዝብ ቀን ከቀን ያለውን የአኗኗር ዘይቤውን መቀየርና የዓለም መንግስታቶች ችግሮቹ ላይ በትኩረትና በሃቅ መረባረብ ካልቻሉ የምድራችን መጎዳት ይበልጥ እየባሰ መምጣቱ አይቀርም። ይህ ሲባል ታዲያ በዓለም ላይ እየተፈጠሩ ያሉትን የአካባቢ ችግሮች በአንድ ቀን ማቆም እንችላለን ማለት ሳይሆን በተቻለን አቅምና ባለን እውቀት የምንችለውን ያህል ማድረግ እንደሚጠበቅብን ለማስገንዘብ ነው። ይህን ደግሞ የምናከናውነው በተለይ በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂ ባደገበት ጊዜ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን በመጠቀም አካባቢያችንን ከተለያዩ ችግሮች መጠበቅና ሌሎችንም ማስተማር ስንችል ብቻ ነው። እዚህ ላይ የኢ ኢንቫይሮመንት (E-Environment) ሃሳብ በብዙዎች የሚነሳ ጉዳይ ነው፡፡
ኢ ኢንቫይሮመንት የአካባቢ ጥበቃንና የተፈጥሮ ሀብትን በተገቢ ሁኔታ አዘውትሮ ለመጠቀም የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ስርዓት ሲሆን ይህም ስርዓት የአካባቢን ሁኔታ፣ የተፈጥሮ ሀብቶችን፣ የአካባቢ ብክለት የሚያስከትሉ በካይ አካላትን እና ተቆጣጣሪ ስርዓቶችን ለመለየትና ለማበልፀግ፣ ሰው ሰራሽ ጥፋቶችን ለመቆጣጠርና ወደ ፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ሁኔታዎችን ለመተንበይ የሚያስችል ነው። አገልግሎታቸውን በጨረሱና በሚጣሉ የኮምፒውተሮችና ሌሎች የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች ተረፈ ምርቶች አማካኝነት የሚከሰተው የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት እንደ ሌሎች ከፋብሪካ እንደሚለቀቁ አየር በካይ ጋዞች ባይሆንም ለዓለም ሙቀት መጨመር እንዲሁም ብክለት ቀላል የማይባል አስተዋፅዖ አለው። ከዚህ አንጻር ኢ ኢንቫይሮመንት በሰው ልጆች አማካኝነት ወይም በሌሎች ምክንያቶች ሊከሰቱ ለሚችሉ ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት ለመከላከልና ከተፈጠሩም በኋላ ለመቆጣጠር ምቹ የሆኑ ሁኔታዎችን የሚፈጥር ቴክኖሎጂ ሲሆን ከዚሁ ጋር የሚያያዙት ሌሎች የቴክኖሎጂ ትግበራዎችም አካባቢ ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመከላከል ያግዛሉ።
https://www.sciencedirect.com/.../S1877042814060327/

ዘመናዊ የትራፊክ አስተዳደር ስርዓት
===================
የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ስርዓት ለዓለም ከተዋወቀበት ከ1920ዎቹ አንስቶ ያሳየው እድገት ከዕድሜው አንጻር አነስተኛ የሚባል እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ዘርፉን ለማሳደግ አውቶማቲክ የቁጥጥር ስርዓቶች በልዩ ልዩ የፈጠራ ባለሙያዎች ተሰርተው ተግባራዊ የሆኑባቸው አጋጣሚዎች አሉ:: እነዚህ ስርዓቶች በዋናነት የመንገዶችን አቅጣጫና ርዝመት፣ ከመንገዶቹ ጋር የተያያዙ አቅርቦቶች እንዲሁም ወቅታዊ ክስተቶችን በተመለከተ ዲጂታይዝ የተደረገ የመረጃ ቋት ከማደራጀት ይነሳሉ:: የሚሰጡትም አገልግሎት አሽከርካሪዎች ካሉበት ቦታ ተነስተው ወዳሻቸው ቦታ ለመድረስ ከሚኖሩት አማራጮች የትኛው መስመር አጭር እንደሆነ መጠቆም የሚችሉ ነበሩ።
የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርን ለማቀላጠፍ መንገዶች የሚያስተናግዱትን የተሽከርካሪ ብዛት አስመልክቶ መረጃዎችን መሰብሰብ ከትራንስፖርት አስተዳደር ጋር ለተያያዙ ስራዎች ከፍተኛ አገልግሎት ይኖረዋል። ይህንን መረጃና ዲጂታል የመንገድ ካርታዎችን በማዋሃድ ለተሽከርካሪዎች የሚሰጠው የመንገድ ጥቆማዎች ከመስመሩ አጭርነት ባለፈ ከትራፊክ ፍሰቱ ጋር የተገናዘበ ጥቆማ መስጠት እንዲችሉ ሆነው በተሸሻሉበት ወቅት መሬት ላይ ከሚታየው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተቀራረበ መረጃ ለመስጠት አስችለዋል።
የትራፊክ ቁጥጥር ስርዓቶችን በማሳደጉ ረገድ የግሎባል ፖሲሺኒንግ ሲስተም (ጂፒኤስ) ቴክኖሎጂ ተሽከርካሪዎች ያሉበትን ስፍራ በተቀራረበ ሁኔታ ለማወቅ በማስቻሉ ዘርፉ ከፍተኛ እመርታ ለማሳየቱ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ከጂፒኤስ ሌላ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢንደስትሪ የመረጃ ልውውጥ ፍጥነት (ዴታ ትራንስፈር) ላይ የተሸሻሉ መሳሪያዎችና ቴክኒኮች እያደጉ መምጣታቸው የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር ስርዓቱ የሚያቅፋቸው መረጃዎች አስተማማኝና ዝርዝር ጉዳዮችን እንዲይዝ አስችሎታል። ለማሳያም ያህል፣ ከዲጂታል ካርታና ከትራፊክ ፍሰት በተጨማሪ መንገዶች በጥገና፣ በድንገተኛ ግጭት እና በሌላ ባልታወቀ ምክንያት ለጊዜው የተዘጉ መስመሮችን አስመልክቶ መረጃዎችን ለአሽከርካሪዎች ባሉበት ስፍራ በማድረስ የትራፊክ ቁጥጥርን ለማሻሻል ያስቻሉ ቴክኖሎጂዎች ትልቅ ሚና ይወጣሉ።
ከዚህ በተጨማሪም ከትራፊክ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ የተሽከርካሪ ግጭቶችን በተመለከተ የደረሱ ጉዳቶችን አይነት (በሰው ላይ የደረሰ ጉዳትና በንብረት ላይ የተፈጠረ ውድመት በሚመለከት)፣ ግጭቶች የደረሱበትን አካባቢ በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ማለትም በአካባቢው የነበረውን የአየር ጸባይ፣ በግጭቱ ምክንያት ሊከሰት የቻለውን የትራፊክ መጨናነቅ የሚመለከት መረጃ የመሳሰሉትን መሰብሰብ ያስፈልጋል። እነዚህ መረጃዎች አንድም በመንገዶች ላይ በሚተከሉ መሳሪያዎች የሚሰበሰብ ሲሆን በሌላም ደሞ ተሽከርካሪዎች ላይ በሚገጠሙ መሳሪያዎች አማካኝነት ሊሰበሰቡ ይችላሉ::
ምንጭ bbntimes እና tech science
https://www.bbntimes.com/technology/traffic-management-with-modern-technologie

ቤተሰባዊ ቆይታ፤ በላምባዲና
===========
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሶሻል ኮሚቴ የሆነው ላምባዲና አማካኝነት መላው የኢንስቲትዩቱን ቤተሰቦች ያሰባሰበ የቡና ጠጡ መሰናዶ በዛሬው ዕለት ሸጎሌ አካባቢ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ጽ/ቤት አዘጋጅቷል፡፡ ከኢንስቲትዩቱ የተለያዩ ማዕከላት የተውጣጡ በርካታ ሰራተኞችን አካቶ በተሰናዳው ዝግጅቱ ላይ ላለፉት ሁለት ዓመታት ኮሚቴውን ሲመሩ የቆዩ የኮሚቴው አባላት አዲስ ለተመረጡት የኮሚቴ አባላት ኃላፊነታቸውን አስረክበዋል፡፡
የኮሚቴውን የሁለት ዓመት ቀይታ የተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት የኮሚቴው አባል በሆነችው ወ/ት ዮዲት አማካኝነት በዕለቱ ቀርቧል፡፡ በሰራተኞች መካከል ቤተሰባዊ ቅርበትን ከሚፈጥሩ መሰናዶወዎች ባሻገር በሁለቱ ዓመታት ውስጥ ከሰራተኞች እና ሌሎች ምንጮች በተሰበሰበ ገንዘብ አማካኝመነት ህፃናትን ከማሳደግ አንስቶ የተቸገሩ ወገኖችን እስከመደገፍ ያሉ ኮሚቴው የሰራቸውን በርካታ የበጎ አድራጎት ተግባራት በሪፖርቱ ተካተው ለሰራተኞች ተብራርቷል፡፡
ከኮሚቴው ቀዳሚ አባላት መካከል የሆነው አቶ ሰልማን መሐመድ በበኩላቸው ኮሚቴው ከምስረታው አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ባሳለፋቸው ሰባት ዓመታት ውስጥ ሰፈራተኞችን አቀራርቦ የተለያዩ ተግባራትን በሕብረት በማከናወን ረገድ ያደረጋቸው መልካም እንቅስቃሴዎችን በዝግቱ ላይ ገልፀዋል፡፡
በዛሬው መሰናዶ በቅርቡ ጎጆ ለቀለሱ አዳዲስ ባለትዳር ሰራተኞች እንዲሁም ከኢንስቲትዩቱ ለተሰናበቱ ሰራተኞች የስጦታና ሽኝት ዝግጅት ተደርጓል፡፡

ባቢሎናዊያን ከግሪኮች ቀድመው የፓይታጎረስ ቲዎረምን ይጠቀሙ እንደነበር አዲስ ጥናት አመላከተ
====================
በባቢሎን ምድር የተገኘ ዕድሜው ወደ 3,700 የሚጠጋ አንድ የድንጋይ ላይ ፅሁፍ እንዳሳየወድ ባቢሎናውያን የፓይታጎረስ ቲዮረም ፈጣሪ ነው ከሚባልለት የግሪኩ ፈላስፋ ፒታጎራስ ውልድት 1ሺህ ዓመታትን ቀድመው የፓይታጎረስ ቲዮረምን ያውቁትና ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ሲ.427 (Si.427) ተብሎ የሚጠራው የድንጋይ ላይ ፅሁፉ ጥንታውያኑ ባቢሎናውያን በእርሻ መሬቶቻቸው መካከል ትክክለኛውን ድንበር ለማስመር ይረዳቸው ዘንድ ሦስት ማዕዘኖን ይጠቀሙ እንደነበር ያሳየ ነው፡፡ ይህም የድንጋይ ላይ ፅሁፉን በዕድሜ ቀዳሚው የአፕላይድ ጂኦሜትሪ ምሳሌ አድርጎታል፡፡
የፈረንሳያውያን አርኪዮሎጂስቶች ቡድን ይህን የተሰራበት ዓመት ከ1900 እስከ 1600 ዓ.ዓ እንደሆነ የሚገመት የድንጋይ ላይ ፅሁፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘው በአውሮፓውያኑ 1894 የአሁኗ ሀገረ ኢራቅ ውስጥ ሲሆን አሁን ግን ፅሁፉ በቱርክ አርኪዮሎጂያዊ ቤተ መዘክር ውስጥ ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ይህ ይሁን እንጂ ተመራማሪዎች በድንጋይ ፅሁፉ ላይ የሰፈረውን ነገር ጥቅም የተረዱት አሁን ገና ነው፡፡
ከዚህ ቀደም ባለ ሦስት ማዕዘኖችን የሚቃኘው የሒሳብ ክፍል ሰማይን በምሽት በሚያጠኑ ግሪካውያን አማካኝነት እንደተጀመረ ሲነገር ቆይቷል፡፡ ሆኖም በአዲሱ ግኝገት መሰረት የድንጋይ ላይ ፅሁፉ አሁን ላይ በስፋት ከሚታወቀው የፓይታጎስ ቲዎሪየም ጋር ፍፁም ተመሳሳይ ነገርን ባይገልፅም ባቢሎናውያን የራሳቸው የሦስት ማዕዘኖችን መጠቀምያ ሒሳባዊ ስልትን ይጠቀሙ እንደነበረ አሳይቷል፡፡ የድንጋይ ፅሁፉ ገፅ ላይ ያለው ዝርዝር ማማዎችን ጨምሮ የተለያዩ ህንፃዎች የተገነቡበት አንድ ረግረጋማ ሜዳን ያሳያል፡፡ የድንጋይ ፅሁፉ በሦስት የፓይታጎረስ ሦስትዮሾች፤ ማለትም የሁለት እኩያ ስኩዌሮች ድምር ከሦስተኛው ጋር እኩል መሆኑን የሚያመላክቱ ሦስት ሙሉ ቁጥሮች ላይ ተመስርቶ የተቀረፀ ነው፡፡ በላዩ ላይ የተቀረፁትና መሬት ላይ የሚገኝ ድንበርን ለመለየት ጥቅም ላይ ውለው ሊሆን ይችላሉ የተባለላቸው እነኚህ ቁጥሮች 3፣ 4፣ 5፤ 8፣ 15፣ 17 እንዲሁም 5፣ 12፣ 13 ናቸው፡፡
ምንም እንኳን ከባቢሎናውያኑ 1 ሺህ ዓመት በኋላ የፓይታጎረስ ሕጎች በስነ ስርዓት ተቀምጠው እስካሁንም እያንዳንዳችን በትምህርት ቤት ቆይታችን ተምረን እንድናልፋቸው ቢደረግም ግሪኮች ግን የሒሳብ አስተምሮትን ከግብፆች፤ ግብፆች ደግሞ ከባቢሎናውያን መውረሳቸው በምሁራኑ ዓለም ለረጅም ጊዜ ታውቆ የቆየ ሀቅ ነው፡፡ ሆኖም በአዲሱ ግኝት ላይ አስገራሚ ሆኖ የተገኘው ነገር ባቢሎናውያኑ በነዚያ የሰው ልጅ ሥልጣኔ ገና ጅማሮውን እያደረገ በነበረባቸው ወቅቶች በሒሳቡ ላይ የነበራቸው ውስብስብ መረዳት ነው፡፡
ምንጭ፤ Live Science
ለተጨማሪ፤ httpswww.livescience.comearliest-form-of-pythagorean-triplet

ቴስታ መግጨትና የጤና መዘዙ
===========
ከዚህ ቀደም በግላስኮ ዩኒቨርሲቲ ተሰርቶ የወጣ አንድ ጥናት እንዳመላከተው እግር ኳስ ተጫዋቾች ከሌላው ሰው አንፃር ደሜንሻ በተሰኘው የአዕምሮ በሽታ የመሞት እድላቸው በ3.5 እጥፍ የላቀ መሆኑን በአልዛይመር ወይም የመርሳት በሽታ የመያዝ እድላቸውም በ5 እጥፍ የላቀ መሆኑን አመላክቶ ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ለምን ሊሆን እንደቻለ ግን አመላከተም፡፡
ታድያ ከአውሮፓውያኑ 1930 እስከ 1998 ድረስ እግር ኳስን ሲጫወቱ በነበሩ 7676 የቀድሞ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ የተጠናውን ጥናት መሰረት በማድረግ የተደረገ ሌላ አዲስ ምልከታ እንዳሳየው ደግሞ በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ኳስን ከግብ ክልል ለማራቅ በተደጋጋሚ ቴስታ የሚገጩት የተከላካይ መስመር ተጫዋቾች ከሌላ ማንኛውም ሰው አንፃር በአዕምሮ በሽታ የመያዝ እድላቸው በ5 እጥፍ የላቀ መሆኑንና የመሀል መስመር ተጫዋቾችም ከዚህ ብዙ ያላነሰ መሆኑን አመላክቷል፡፡ ከተከላካዮች እና መሀል ሜዳ ተጫዋቸፖች በመቀጠል አጥቂወዎች 2.79 እጥፍ የላቀ በአዕምሮ በሽታ የመያዝ ዕድል ሲኖራቸው ብዙም ኳስን በግንባራቸው የማይጫወቱት ግብ ጠባቂዎች ግን በአዕምሮ በሽታ የመያዝ ዕድላቸው ከማንኛውም ሰው ያልተለየ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
እግር ኳስ ተጫዋቾች ከሚጫወቱበት ቦታ ባለፈም የሚጫወቱበት ዓመት ብዛትም በአዕምሮ ጤናቸው ላይ ተፅዕንዖው የጎላ ነው፡፡ በዚህም 15 ዓመታትን እና ከዚያ በላይ እግር ኳስን በመጫወት ያሳለፉት ተጫዋቾች ደሜንሻን ጨምሮ በተለያዩ የአዕምሮ በሽታዎችን የመታመም ዕድላቸው በአምስት ዕጥፍ የላቀ ሆኖ ተገኝተዋል፡፡
የአዕምሮ በሽታ ላይ ከወደቁት የእግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል የቀድዎቹ ስኮትላንዳዊያን የሴልቲክ ተጫዋቾች ቢሊ ማክኔል እና ስቲቭ ቻመርስ፣ የቀድሞው የስኮትላንድ እና ማንቼስተር ዩናይትድ ተከላካይ ጎርደን ማክዊን እንዲሁም የእንግሊዝ እግር ኳስ ጀግናው ሰር ቦቢ ቻርልተን ይገኙበታል፡፡
ከሁለት ዓመታት በፊት ግር ኳስ ተጫዋቸች በጤናቸው ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ከሌሎች እግር ኳስን እንጀራ ብለው ተጫውተው ከማያውቁ 23,028 ሰዎች ጋር በማነፃፀር የተሰራው ጥናቱ የተሳታፊዎችን ፆታ፣ የትውልድ ዓመት፣ ማህበራዊ-ምጣኔ ሀብታዊ ሁናቴ እንዲሁም የመኖርያ አድራሻን ጭምር ከግንዛቤ ያስገባ ነው፡፡ ከ23 ሺው እግር ኳስ ተጫዋች ያልሆኑ የጥናቱ ተሳታፊዎች ውስጥ 366ቱ የአዕምሮ በሽታው ሲገኝባቸው በአንፃሩ አነስ ያለ ቁጥር ያላቸው እግር ኳስ ተጫዋች የጥናቱ ተሳታፊዎች (7676) መካከል ግን 386ቱ የአዕምሮ በሽታዎች ተጠቂ ሆነው ተገኝተዋል፡፡
በሁሉም ሀገራት ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ በመላው ዓለም ባሉ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው እግር ኳስ ከስፖርቶች ሁሉ ቀዳሚው ነው፡፡ ታድያ የጥናቱ ተሳታፊ ባለሙዎችም ይህን ዝነኛ ስፖርት በበላይነት የሚመራው ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ወይም ፊፋ ለእግር ኳስ ተጫዋቾች ጤና ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራና ተጫዋቾችም በዚህ ረገድ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክረዋል፡፡
ምንጭ፤ The Herald
ለተጨማሪ፤ https://www.heraldscotland.com/news/homenews/19485256.glasgow-university-dementia-football-study-reveals-risk-five-fold-defenders/

HeraldScotland
Football dementia risk five times higher for defenders
Footballers should be warned about the risk of dementia, a brain injury expert has said, as landmark Scottish research found defenders were five…