TechIn2
1.16K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የሸዋርዝቻይልድ ቀመርና የብላክ ሆል ብያኔ
=====================
ብላክ ሆሎች በኮስሞሎጂ ጥናት ውስጥ በጣም አወዛጋቢ ከሚባሉት ግኝቶች ውስጥ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። አብዛኞቹ በመጠነይዘታቸው ከምድራችን በጣም የሚያንሱ ቢሆኑም በዙሪያቸው የሚፈጥሩት የስበት ሀይል እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ማንኛውም ቁስ አካል (ብርሀንም ቢሆን) ውስጣቸው ከገባ በፍፁም ሊወጣ አይችልም።
እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1920ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ካርል ሸዋርዝቻይልድ የተባለ የጀርመን ተወላጅ የፊዚክስ ምሁር አንድ ቁስ አካል ከብላክ ሆል ለማምለጥ የሚያስፈልገውን ትንሽ ርቀት ለመወሰን የሚያስችል ቀመር እንዳገኘ ይነራል። ይህ የፊዚክስ ቀመር በሳይንሱ አለም የሸዋርዝቻይልድ ራዲየስ (Shwarzchild's radius) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን እንደአውሮፓውያኑ በ1916 በዚሁ ተመራመሪ እንደተገኘ ይነገራል፡፡ ቀመሩ R=2GM/C^2 ተበሎ የሚታወቅ ሲሆን ይህም R ራዲያስን (radius) ሲወከል G የብላክ ሆል የስበት ሀይል፣ M የቁስ አካሉ ክብደትን፣ C ደግሞ የብርሀን ፍጥነትን ይወክላል፡፡ በፊዚክሱ አለም ትልቅ እውቅና ያለው ይህ ቀመር ከብላክ ሆል የስበት ሀይል ለማምለጥ የሚያስፈልገውን ትንሹን ርቀት በማብራራት ምን አይነት የብላክ ሆል ብያኔ መስጠት እንደሚቻል ያሳያል።
እንደተመራማሪዎች ገለጻ ከብላክ ሆል የስበት ሀይል ለማምለጥ የሚያስፈልገው ፍጥነት ስኬፕ ቬሎሲቲ (Escape velocity) ተብሎ ይታወቃል። ከዚህ አንጻር ከላይ በተጠቀሰው ቀመር መሰረት ምድራችን የሸዋርዝቻይልድ ራዲየሱዋ 2ሳ.ሜ እስኪያክል ድረስ ብናፍጋት (dense) ወደ ብላክ ሆል የመቀየር እድል እንደሚኖራት ይነገራል። ይህም የሚሆነው ከመጠነ ይዘቱዋ አንፃር የሚኖራት የስበት ሀይል እጅግ ከፍተኛ ስለሚሆን ነው።
https://astronomy.swin.edu.au/cosmos/S/Schwarzschild+Radius
የአንድሮይድ ተቀባይነት በዓለም ዙሪያ
===================
አፕል የሚያስተዳድረው የአይፎን ስልክ ሲስተም እንደአውሮፓውያኑ በ2007 በተዋወቀ በጥቂት ወራት ውስጥ በመስከረም 23 2008 የአንድሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ለአለም ይፋ ሲደረግ የአፕሉ መስራች ሲቲቭ ጆብስ ሊቀናቀነው የመጣውን ይህን የጎግል ምርት በፍጥነት ለመርታት ብዙ ሙከራዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ትንቅንቁ ከጀመረበት 2008 አንስቶ የገበያ ፉክክሩ እስከቀጠለበት እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ሁለቱም ምርቶች የተጠቃሚውን ልብ ያሸንፋል ያሉትን ማዘመኛ እያካተቱ መተዋል፡፡
አሁን ላይ የሁለቱ ምርቶች የገበያ ውድድር በአንድሮይድ የበላይነት የተያዘ ቢሆንም በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች የአይፎን ፈላጊዎችና ተጠቃሚዎች ብዛት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ከሰሞኑ ኤሌክትሮኒክ ሃብ የተባለ የቴክኖሎጂ አማካሪ ድርጅት በአንድሮይድ እና በአይፎን መካከል በአለም አቀፍ ዙሪያ ስላለለው ተቀባይነት እና የገበያ ተደራሽነት የሚያሳይ መረጃ ይፋ አደርጎ ነበር፡፡ እንደድርጅቱ የስታቲክስ መረጃ የሁለቱ ምርቶች የገበያ ውድድር ሰርቬው በተካሄደባቸው 142 ሀገራት መነሻ አደርጎ የተካሄደ ሲሆን በዚህም በ74 ሀገራት የሚገኙ የስልክ ተጠቃሚዎች የአንድሮይድ ተጠቃሚ እንደሆኑ ያሳያል፡፡ በአንጻሩ ሰርቬው ከተካሄደባቸው 142 ሀገራት 65 የሚሆኑት የበለጠ የአይፎን ተጠቃሚ መሆናቻውን የሚያሳይ ሲሆን ከሁለቱም ሊመደቡ ያልቻሉ ሶስት ሀገራት (ቤላሩስ፣ ፊጂ እና ፔሩ) በገለልተኝነት ተመዝገበዋል፡፡
የአንድሮይድ ምርት ተቀባይነት በዚህ ሰርቬ መሰረት በሰሜን አሜሪካ፣ በደቡብ አሜሪካ፣ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ አካባቢዎች ይበልጥ ቁጥሩ አይሎ የሚገኝ ሲሆን በአውሮፓ ብቻ ሰርቬው ከተደረገባቸው 37 ሀገራት ሃያውን በመያዝ የአይፎን ምርት ብላጨውን ይወስዳል፡፡
በአፍሪካ ከሁዋዌ ምርቶች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የአንድሮይድ ተቀባይነት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሲሆን በተለይም በኢትዮጵያ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያለው ብዙ ቁጥር ያለው ተጠቃሚ የአንድሮይድ ተቀባይነትን በእጅጉ አሳድጎታል፡፡ ሁዋዌ በአህጉሪቱ ከፍተኛ የስልክ ሽያጭ የሚያካሂድ ኩባንያ ከመሆኑ አንፃር አሁን እየተጠቀመበት ካላው የአንደሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እራሱ ወዳበለጸገው ሃርመኒየ የተሰኘ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ሲሸጋገር አለም አቀፍ ገበያው ላይ ትልቅ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡ bigthink
ተጨማሪ https://bigthink.com/strange-maps/android-vs-apple
ሴት እስከምትሆኚ ድረስ ወንድ ነሽ፤ ፆታቸውን በሚቀይሩት ኤሊዎች ዓለም
ሴት እስከምትሆኚ ድረስ ወንድ ነሽ፤ ፆታቸውን በሚቀይሩት ኤሊዎች ዓለም
=====================
ሁሉም ባለ ለስላሳ ቅርፊት ወይም ሶፍትሼል ኤሊዎች ህይወታቸውን ወንድ ሆነው እንደሚጀምሩ ግን ደግሞ የአየር ሙቀቱ እና ፕሮቲን ይዘቱ እየተስተካከለ ሲመጣ ከመፈልፈላቸው በፊት ሴት እንዲሆኑ የተመረጡት ወደ ሴትነት እንደሚለወጡ ስፒይኒ በተሰኙት ዝርያዎች ላይ የተሰራ አዲስ ጥናት አመላከተ፡፡

በኒኮል ቫሌንዙዌላ የሚመራው የአዮዋ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጥናት ቡድን የደረሰበት ድምዳሜ እንደሚያመላክተው እንስሳቱ ከመፈልፈላቸው አስቀድሞ ፆታቸውን የሚወሰነው ባላቸው የክሮሞሶም ብዛት እና አይነት ከመሆን ይልቅ በክሮሞሶሞቹ አማካኝነት በሚመረተው ፕሮቲን መጠን ላይ በመንተራስ ነው፡፡ ይህ ታድያ በሳይንሱ ሴክስ ክሮሞሶም ዶሴጅ ኮምፐንሴሽን ተብሎ የሚጠራ ሁነት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ታድያ ከፕሮቲን ምርትም ባለፈ የመፈልፈል ሂደቱ እንቁላሎቹ ባሉበት አካባቢ ሙቀት ላይ የሚወሰን በመሆኑ ፆታቸውም እንደ አየሩ ሊቀያየር ይችላልም ተብሏል፡፡ ለምሳሌ የከባቢ ሙቀቱ ከፍ ባለ ጊዜ የወንዶቹ ቁጥር ከፍ ይላል እንደማለት ነው፡፡

የፆታ ልየታ ውስብስብ እና ከአንዱ እንስሳ ወደ ሌላኛው የተለያየ ሂደት ነው፡፡ ለምሳሌ የሰው ልጅ እና አብዛኛዎቹ አጥቢ እንስሳት ፆታ የሚወሰነው እንቁላሉ በሚያድግበት ጊዜ በውስጡ በያዛቸው የተለያዩ ክሮሞዞሞች አማካኝነት ነው፡፡ ሆኖም እንደ አዞና ኤሊ ባሉት እንስሳት ዘንድ የእንስሳው ፆታ የሚወሰነው እንቁላሉ ሳይፈለፈል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን ደግሞ ካደገ በኋላ ነው፡፡

እያንዳንዱ ክርሞሶም ለተለያዩ ባህርያት ምክንያት የሚሆኑ ፕሮቲኖችን የማምረት ስራን ይሰራል፡፡ ስለዚህም የክሮሞዞሙ ዓይነት የሚሰሩ ፕሮቲኖች መጠንን ይወስናል፡፡ በሌላ መልኩ የሰው ልጆች X እና Y ክሮሞዞም አላቸው፤ ሆኖም ሴት ባለ ለስላሳ ቅርፊት ኤሊዎችን የተመለከትበን እንደሆነ ሴቶቹ ZW ክሮሞዞም ይዘዋል፡፡ ወንዶቹ ደግሞ አንድ ወይም ሁለት Z ክሮሞዞም አላቸው፤ የሰው ልጆች በዚህ መልኩ አንድ ክርሞዞም ካላቸው ከባድ የጤና ችግር ይኖረዋል፡፡

ነገሩን የመረመሩት ተመራማሪዎቹ ZW ክሮሞዞም ያላቸው ኤሊዎች በእድገታቸው ጅማሮ ላይ ከወንዶቹ ጋር ተመሳሳይ መጠን ያለው የZ ፕሮቲንን እንደሚያመርቱና በዚህም ከወንዶቹ ጋር ተመሳሳይ እንደሚሆኑ አረጋግጠዋል፡፡ ሆኖም በዕድገት ውስጥ ሳሉ የሚከሰቱ ለውጦች ኋላ ላይ ሴት ሆነው እንዲፈለፈሉ ያደርጓቸዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም አጥኚዎቹ እንቁላሎቹ ያሉበት አካባቢ ሙቀቱ በጨመረ ቁጠር ወንድ መስለው የሚፈለፈሉት እንቁላሎች እንደሚበዙ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ጥናቱ የተደረገባቸው ስፒይኒ የተሰኙት ባለ ለስላሳ ቅርፊት ኤሊ ዝርያዎች (Apalone Spinifera) በሰሜን አሜሪካ ባሉት ጨዋማ ያልሆኑ ውሃ አካላት ውስጥ ከሚገኙት ኤሊዎች ትልቆቹ ናቸው፡፡ በውሃ አካሉ አጠገብ ባሉ ፀሐይ የሚያገኛቸው የአሸዋ አልያም ጠጠር ቦታዎች ላይ የሚጥሏቸው እንቁላሎች ከ60 እስከ 80 ቀናትን ጠብቀው ይፈለፈላሉ፡፡
ምንጭ፤ Cosmos
ለተጨማሪ፤ https://cosmosmagazine.com/nature/animals/for-softshell-turtles-youre-male-until-youre-female/?utm_content=buffer8c9e9&utm_medium=social&utm_source=twitter.com&utm_campaign=buffer
በአካባቢ ብክለት ምክንያት ወደ ሮዝ የተቀየረው ሃይቅ
----------------------------------------
በአርጀንቲና የደቡብ ፓታጎኒያ ግዛት በሚገኘው ትንሽዬ ሃይቅ ላይ የተፈጠረው የሰሞኑ ክስተት ብዙዎችን አነጋግሯል፡፡ በዘገባው እንደተገለፀው የሃይቁ ጠቅላላ ክፍል ጎጂ ሊባል በሚችል የአካባቢ ብክለት ምክንያት ወደ ደማቅ ሮዝ ቀለም ሊቀየር እንደቻለ እና ጥልቀቱ አነስተኛ ከሆነው ከዚህ ሃይቅ አጠገብ ያለ ወንዝ ደግሞ መጥፎ ሽታ ማምጣቱ ተነግሯል፡፡
በአካባቢው ምርምሮችን ሲያደርጉ የነበሩ ሳይንቲስቶችና የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች እንደገለፁት የሃይቁ ቀለም ወደ ሮዝ ሊቀየር የቻለው በአካባቢው የሚገኙ የአሳ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በሃይቁ አቅራቢያ በሚገኝ ወንዝ ላይ በሚለቁት ጎጂ የኬሚካል ውጋጅ እንደሆነ አንስተዋል፡፡ ጥልቀቱ አነስተኛ ለሆነው ለዚህ ሃይቅ እንደገባር የሚያገለግለው ወንዝ ላይ ለብዙ ጊዜያት ሲለቀቅ የቆየው እንደሶዲየም ሰልፌት ያለ የጸረ ባክቴሪያ ኬሚካል ውጋጅ የችግሩ መነሻ መሆኑን የሚነሱት እነዚህ ባለሙያዎች ሰዎች በቸልተኘነት የሚፈፅሟቸው ተግባራት በተፈጥሮ ላይ የሚያስከትለውን ትልቅ ጥፋትም የሚሳይ ነው ይላሉ፡፡
በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች በሃይቁ ላይ እየተፈጠረ ያለውን የቀለም ለውጥ እና በወንዙ ስፍራ የተከሰተውን መጥፎ የጠረን ሽታ ያስታወቁ ቢሆኑም የሰማቸው እንዳልነበረ የሚናገሩት ከአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ፓብሎ ላዳ ለቀለሙ መለወጥ ምክያት የሆነው የኬሚካል ውጋጅ ወደ ወንዙ ከመቀላቀሉ በፊት ቀላል ህክምና ቢደረግለት ኖሩ ችግሩን ቀድሞ መከላከል ይቻል እንደነበር ይናገራሉ፡፡
በአካባቢ ብክለት ምክንያት ወደ ሮዝ የተቀየረው ይህ የአርጀንቲና ሃይቅ ለየት ያለ አጋጣሚ ቢሆንም በአለማችን ሮዝ ቀለም ያላቸው ተፈጥሮኣዊ ሃይቆች በተለያዩ ቦታዎች እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ ለአብነት በሴኔጋል የሚገኘው የሬብታ ሃይቅ፣ የቦሊቪያው ላጉና ኮሎራዳ ሃይቅ እና የአዎስታራሊያው ሂሊር ሃይቅ በተፈጥሮ ሮዝ ቀለም ያላቸው ታዋቂ የውሃ አካላት ሲሆኑ፤ በውስጣቸው ያለው ከፍተኛ የጨዋማነት ይዘት ይህን ቀለም እንዲይዙ እንደሚያደርጋቸውም ሳይንቲስቶች ይናገራሉ፡፡
ምንጭ፡ outsider
ተጨማሪ https://outsider.com/.../photo-argentina-lake-bright.../
አትሌቱ ሮቦት
አትሌቱ ሮቦት
=======
በአሜሪካን የተሰራው ካሴ የተሰኘ ባለ ሁለት እግር ሮቦት የ5 ኪ.ሜ ጉዞን 53 ደቂቃ ከ3 ሴኮንድ በሆነ ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ታሪክ ሰርቷል፡፡ 1 ሚሊዮን ዶላር ፈጅቶ በ16 ወራት ውስጥ ተሰርቶ የተጠናቀቀው ሮቦቱ በአንድ ጊዜ ቻርጅ ነው ጉዞውን ለማጠናቀቅ የቻለው፡፡

አዲሱ ሮቦት በአጂሊቲ ሮቦቲክስ ኩባንያ አማካኝነት ኦሪጎን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተሰራ ነው፡፡ ልክ እንደ ሰጎን ጉልበቱ ከወደ ጀርባ የሆነው ካሴ ዲፕ ሪኢንፎርስመንት ለርኒንግ አልጎሪዝም በተሰኘው ቀመር አማካኝነት እራሱን በራሱ መሮጥ አስተምሯል፡፡ ሩጫ በከፍተኛ ፍጥነት ውስጥ ሚዛንን ጠብቆ መቆየትን የሚፈልግ እንደመሆኑ መጠን ካሴም በሩጫ ወቅት ሚዛኑን መጠበቅን ተምሯል፡፡ በተጨማሪም ሮቦቱ ደረጃን መውጣት እና መውረድን ከዚህ ቀደም አከናውኖ ነበር፡፡

ሮቦቱ የ5 ኪ.ሜ ሩጫውን ባከናወነባቸው 53 ደቂቃዎች ውስጥ ሁለት ጊዜ ችግር አጋጥሞት ለ6 ደቂቃዎች ያህል ለመቆም ተገዶ ነበር፡፡ የመጀመሪያው ኮምፒውተሩ ከሚገባው በላይ በመሞቁ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መታጠፊያ ቦታ ላይ ከሚፈለገው በላይ እየፈጠነ እንዲያልፍ ታዞ ስለነበር ነው፡፡

መሰል ባለ ሁለት እግር ሮቦቶች እቃን የማጓጓዝ ስራን ከመስራት ባሻገር ሰዎችን የሚረዳ የአስተውሎት እና ደህንነት ብቃትን እንዲላበሱ ይደረጋል፡፡ ከአጂሊቲ ሮቦቲክስ መስራቾች አንዱ እንደሆነው ጆናታን ኸርስት አባባል ከሆነም ሁላችን የሰው ልጆችም በእለት ተእለት ህይወታችን ከሮቦቶች ጋር የምንገናኝና ህይወታችንን በሚያሻሽል መልኩም በጋራ የምንሰራበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም፡፡
ምንጭ፤ Tech Xplore
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-07-bipedal-robot-history-5k.html
አዲስ አበባን የሸፈናት ጉም ምንድነው?
አዲስ አበባን የሸፈናት ጉም ምንድነው?
=============
ዛሬ በጠዋቱ መዲናችን አዲስ አበባ ባልተለመደ መልኩ የተለያዩ ክፍሎቿ በጉም ተሸፍነው በቅርብ ርቀት ያሉ ህንፃዎችን ጭምር ማየት እንዲሳነን ሆነናል፡፡ ታድያ እኛም ይህን ክስተት አስታከን ጥቂት ስለ ጉም ልናጫውታችሁ ወደድን፤ አብራችሁን ሁኑ፡፡

ጉም እንደ ማንኛውም ደመና ሆኖ መሬትን የሚነካ መሆኑ ግን ለየት የሚያደርገው ነው፡፡ ይህ ጉም አንዳንዴ ስስ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወፍራም ሆኖ ሊያጋጥመን ይችላል፡፡ ታድያ ጉሙ ወፈር ብሎ ሲገኝ ነው አሻግሮ ማየትን ባስ ሲልም በቅርብ ርቀት መተያየት እስኪያስቸግር ድረስ እይታን በነጭ መጋረጃ የሚጋርደው፡፡ በዚህም ትላልቅ ህንፃዎች፣ ባለ ግርማ ሞገስ ተራሮች እና ሌሎችም ግዙፋን አካላት በቦታው የሌሉ እስኪመስል ድረስ ሙሉ በሙሉ ሊጋረዱ ይችላሉ፡፡

የጉም አፈጣጠር ተኖ ጋዝ የሆነ ውሃ ወደ ፈሳሽነት በሚለወጥበት ጊዜ (Condensation) ሞለኪውሎቹ ተጣምረው እጅግ ጥቃቅን የሆኑና በዚህም ሳብያ በአየር ላይ የሚንሳፈፉ ውሃዎችን ሲፈጥሩ ነው፡፡ ጉሙን የምናየውም በነዚህ ጥቃቅን ፈሳሽ ውሃዎች ምክንያት ነው፤ አለበለዚያ የተነነው ውሃ ጋዝ በመሆኑ ላይታየን ይችል ነበር፡፡

ይህ በእዲህ እንዳለ ግን አንድ ጉም ተፈጥሮ ዙርያችንን ለመክበብ የከባቢያችን አየር እጅጉን እርጥበት አዘል መሆንና በፍተኛ መጠን በተነነ ውሃ የተሞላ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም እንደ አቧራ አልያም ሌላ አየሩን የሚበክሉ ጥቃቅን ቁሶችም በአየሩ ውስጥ መገኘት አለባቸው፡፡ በዚህም የተነነው ውሃ በእነዚህ ጥቃቅን ቁሶች ላይ ሆኖ ወደ ፈሳሽነት ይቀየራል፡፡ በጨዋማ የውሃ አካላት አካባቢ ደግሞ የተነነው ውሃ በጨው ብናኞች ላይ ሆኖ ሲቀየር የባህር ጉም (Sea Fog) ተብሎ የሚጠራውን ጉም ይፈጥራል፡፡ ታድያ በአየር ላይ ባለው እርጥበት የሚወሰን ቢሆንም ጉሞች በድንገት ሊከሰቱና በዚያው ፍጥነት ሊሰወሩም ይችላሉ፡፡

በምድራችን የተለያዩ አይነት ጉሞች ሲከሰቱ እናያለን፡፡ እነዚህም እንደሚከተለው ቀርበዋል፤

የራዲዬሽን ጉም፤ በምሽት የሚፈጠር ሲሆን መሬት በቀን ውሎዋ ያጠራቀመችውን ሙቀት ወደ አየሩ ስትለቅ የሚከሰት ነው፡፡ ሙቀቱ ከምድር ወደ አየር በሚሸጋገርበት ጊዜ የውሃ ጠብታዎች መፈጠራቸው ለዚህ ምክንያት ይሆናል፡፡

አድቬኬሽን ጉም፤ ይህ ዓይነት ጉም ደግሞ ሞቃታማና እርጥበት አዘል አየር በቀዝቃዛ አካል ላይ ሲያልፍ የሚከሰት ነው፡፡ እርጥበታማ እና ሞቃታማ አየሩ ከቀዝቃዛው የመሬቱ አየር ጋር ሲነካካ የተነነው ውሃ መልኩን ቀይሮ ፈሳሽ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ይህ ሂደትም በሳይንሳዊ አጠራሩ አድቬክሽን ተብሎ ሲጠራ ብዙውን ጊዜ የትሮፒካል አየር ከቀዝቃዛ የውቅያኖስ ውሃ ጋር ሲነካካ የሚፈጠር ነው፡፡

የሸለቆ ጉም፤ ብዙውን ጊዜ በክረምት ወራቶች ተራራና ሸለቆዎች ውስጥ የሚፈጠር ነው፡፡ አፈጣጠሩም ተራሮች አልያም ሸለቆች ውስጥ የተጠቀጠቀውን አየር እንዳያልፍ አግደው ሲያስቀሩት የሚከሰት ነው፡፡ አንዳንዴ ሁኔታው አደገኛ ሊሆንም ይችላል፡፡ ለምሳሌ ከ90 ዓመታት በፊት በቤልጅየሙ የሚዩስ ሸለቆ ውስጥ የተነነ ውሃ በበካይ የአየር ቁሶች ላይ ሆኖ በመቀየሩ ሳብያ ከ60 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተው ነበር፡፡

የቅዝቃዜ ጉም፤ በተለምዶው ደመና በሸፈናቸው ተራሮች ላይ የሚከተው ይህ ዓይነት ጉም ፈሳሽ የደመና ጠብታዎች በአንድ ቁስ ላይ ቀዝቅዘው ሲቀሩ የሚፈጠር ነው፡፡ ይህ አይነት ቀዝቃዛ ጉም ከአካባቢው ተነስቶ ከሄደ በኋላ ምድሩም ሆነ ዛፎች እና እንደ ሸረሪት ድር ያሉ አካላት ጭምር ስስ የበረዶ ሽፋን ተነስንሶባቸው ልናገኝ እንችላለን፡፡ መሰል ጉሞች ቀዝቃዛና እርጥበታማ አየር ፀባይ ባላቸው እንደ ስካንዲኔቪያ እና አንታርክቲካ ባሉ አካባቢዎች ላይ በብዛት መመልከቱ የተለመደ ነው፡፡

ስለ ጉም ካወራን አይቀር ከጉም ላይ ውሃን ስለመሰብሰብም ጥቂት እንበልዎ፡፡ በተለያዩ ማህበረሰቦች ጉም ሲከሰት ትላልቅ የውሃ ማስቀመጫዎችን ከዛፍ ስር በማስቀመጥ በዛፉ ላይ የሚወርደውን ውሃ በመሰብሰብ ጥቂት ውሃን የማግኘት ባህል ነበር፡፡ አሁን ላይ ታድያ የዘመናችን ባለሙያዎች ውሃን ከጉም ላይ የመሰበሰብ ስልትን በዘመናዊ መንገድ ተግባራዊ አያደረጉ ይገኛል፡፡ ታድያ አንዳንድ አካባቢዎችም ዋነኛ የውሃ አቅርቦታቸውን ከጉሞች ላይ በመሰብሰብ እስከማግኘት ደርሰዋል፡፡

ምንጭ፤ National Geographic
ለተጨማሪ፤ https://www.nationalgeographic.org/encyclopedia/fog/
ፕላስቲክ ውጋጅን ወደ ምግብ ለሚቀይረው ምርምር 1 ሚሊዮን ዩሮ
------------------------------------------
የሰው ልጅ ያገለግሉኛል ብሎ ፈጥሯቸው የጥቅማቸውን ያህል ለጥፋቱ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ግኝቶች አሉ፡፡ ለሰዎች እንደፕላስቲክ የቆሻሻ ችግር በረዥም የጊዜ ሂደት ውስጥ ትልቅ አደጋ የደቀነ ችግር ላይገኝ ይችላል፡፡ በሰዎች የየዕለት እንቅስቃሴ ጥቅም ላይ የሚውለው የፕላስቲክ ምርት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መቶ አሁን ላይ ከ8 ሚሊዮን ቶን በላይ የፕላስቲክ ወጋጅ በውቂያኖሶች ላይ ይጣላል፡፡ ለብዙ አመታት በአካባቢ ላይ ተንሰራፍተው የሚገኙ የፕላስቲክ ቆሻሻዎች የምድራችንን ስነምህዳር በማዛባት እና የአለምን ሙቀት በመጨመር የኋላ ኋላ ለሰው ልጆች አደጋ መሆናቸው የማይቀር ነው፡፡ ይህን አለም አቀፍ ችግር በሚቻለው አቅም ለማቅለልና ለመቅረፍ ከተለያዩ ስፍራዎችና የአለም ክፍሎች ልዩ ልዩ የመፍትሄ ሀሳብና የምርምር ስራ ሲቀርብ ይታያል፡፡

ከሰሞኑ የፕላስቲክ ውጋጅን ልዩ በሆነ ሳይንሳዊ ሙከራ ለምግብነት ሊውል ወደሚችል የፕሮቲን ይዘት ለሚቀየረው የሁለት ሳንቲስቶች ምርምር መርክ ግሩፕ በሚያዘጋጀው ፉዩቸር ኢንሳይት ፕራዝ ላይ አሸናፊ ሆኗል፡፡ አለማችን ላይ የተከሰቱ ትልልቅ ችግሮችን ለመቅረፍ በየዓመቱ የ1 ሚሊዮን ዩሮ ለተመራማሪዎች ድጋፍ የሚደርገው መርክ ግሩፕ በዚሁ የ2021 ፈንዱም ፕላስቲክን ለምግብነት ሊውል ወደሚችል የፕሮቲን ይዘት ለሚቀየረው የሁለት ሳንቲስቶች ምርምር ላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በአሜሪካ በሚገኙት የኢሊኒዮስ ዩኒቨርስቲ እና ሚቺጋን ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የተወጣጡት ፕሮፌሰር ቲንግ ሉ እና ረዳት ፕሮፌሰር ስቴቨን ቴክትመን የምርምር ስራው ባለቤቶች ሲሆኑ የምግብ ‹ጀነሬተር› ብለው በሰየሙት በዚህ ፅነሰ ሃሳብ ላይ የረዥም ጊዜ ምርምር በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ተማራማሪዎቹ እንደሚሉት ይህ የረዥም ጊዜ ምርምር የፕላስቲከው ውጋጆችን በተለያዩ የኬሚካል ጥምረቶች በማሳለፍ እና ከፍተኛ ሙቀት (pyrolysis) በመጠቀም ለምግብነት ሊያገለግል ወደሚችል የፕሮቲን ዱቄት እና ቅባቶች መለወጥ እንደሚሆን ይናገራሉ፡፡

ገና በመነሻ ላይ ያለው ይህ የምርምር ስራ ረዥም ጊዜ እና ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ሊወስድ ከመቻሉ አንጻር ከመርክ ግሩፕ የተገኘው የፋይናንስ ድጋፍ ትልቅ እድል መሆኑን የተናገሩት ፕሮፌሰር ስቴቨን የምርምር ስራውን አሁን ከላበት ደረጃ ይበልጥ ለማሳደግ ፈንዱ ትልቅ አገዛ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡ የመርክ ግሩፕ ከዚህ የረዥም ጊዜ ምርምር የሚገኘው ውጤት ለአለማችን ጥቅም እንደሚኖረው በማንሳት በምርምሩ ለሚሳተፉ ተመራመሪዎች መልካም እድልን ተመኝተዋል፡፡
https://washingtonnewsday.com/us-politics/plastic-trash-is-turned-into-edible-protein-using-a-generator/
ሪከርድ ሰባሪዎቹ ጫማዎች
ሪከርድ ሰባሪዎቹ ጫማዎች
==============
ለእኛ ኢትዮጵያውያን የክብር እና ድል መቀዳጃ ከሆኑን ዓለም አቀፍ የፍልሚያ መድረኮች መካከል አትሌቲክስ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ ወትሮም ትኩረታችንን የሚስበው ይህ ውድድር ከሰሞኑን ደግሞ የቶኪዮ ኦሎምፒክ ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ ይበልጡን ሀሳባችንን እየተቆጣጠረው በመምጣት ላይ ነው፡፡ ታድያ በዚህኛው የኦሎምፒክ ውድድር ላይ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ጎልተው ይተገበራሉ ከሚባሉት ቴክኖሎጂዎች መካከል በቀዳሚነት በአሜሪካኑ የስፖርት ትጥቅ አቅራቢ ኩባንያ ናይኪ አማካኝነት ተዋውቀው የነበሩት ሱፐር ጫማ (Super Shoe) የተሰኙ የመሮጫ ጫማዎች ይገኙበታል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በውድድር መድረኩ ላይ እየተዘወተሩ የመጡት ሱፐር ጫማዎች የቤት ውስጥ እና ጎዳና ላይ አትሌቲክስ ውድድሮችን በከፍተኛ ደረጃ እየቀየሩ ይገኛሉ፡፡ ከሪዮ ኦሎምፒክ በኋላ እንኳን ጫማዎቹ በርካታ የዓለም ሩጫ ክብረ ወሰኖች፣ የሀገር ክብረ ወሰኖች እንዲሁም የግል ምርጥ ሰዓቶች እንዲመዘገቡም አድርገዋል፡፡ መጪው አርብ በሚጀመረው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይም ብዙ አትሌቶች እነዚህን እጅግ ቀላልና በውስጣቸውም አትሌቶቹን ወደፊት በተሻለ እንዲስፈነጠሩ የሚያስችሉ ልዩ ፎም እና ብዙም የማይታጠፉ ዝርግ ቁስን የያዙት ጫማዎችን በስፋት እንደምናያቸው ይጠበቃል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በጫማዎቹ ውስጥ ያለው ቴክኖሎጂ እንደ ፎሙ ውህረት መጠን ያሉ ልዩ ልዩ ልኬቶች ተቀምጠውለት በዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እውቅናን አግኝቷል፡፡ ጫማዎቹም በተለይ ከ800 እስከ 10,000 ሜትር ድረስ ባሉት ሩጫዎች ላይ ከፍተኛ ልዩነትን ያመጣሉ ሲባሉ በ5,000 ሜትር ሩጫ ላይ እንኳን የ15 ሴኮንድ ልዩነትን እንደሚያመጡ ይነገራል፡፡ ጫማዎቹን ተጠቅማ በ5,000 እና 10,000 ሜትር ውድድሮች ላይ ክብረወሰኑን የጨበጠችውና በያዝነው ኦሎምፒክ ለውጠየት እየተበቅናት ያለቸው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በቅርቡ 29 ደቂቃ ከ1.03 ሴኮንድ በማስመዝገብ በ10,000 ሜትር ክብረ ወሰንን ያሻሻለችው ቀድሞ የግል ምርጥ ሰዓቷ ከነበረው ላይ 1 ደቂቃ ያህል ልዩነት በማምጣት ነበር፡፡
ሆኖም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የረጅምር ርቀት ሩጫ ክብረ ወሰኖቹ ለመሰባበራቸው ከጫማዎቹ ባሻገር አትሌቶች የኮቪድ 19 ወረርሺኝን ተከትሎ ረዘም ያለ ረፍት ካረፉ በኋላ ወደ ሩጫ መመለሳቸው የራሱ አስተዋፅዖ እንዳለው ባለሙያዎችን የሚያስማማ ጉዳይ ነው፡፡

ምንም እንኳን እነዚህ ጫማዎች በየቦታው የተሻሉ ክብረ ወሰኖች እንዲመዘገቡ ማድረጋቸው ቢነገርላቸውም ጫማዎች እንደ ሜካኒካዊ አበረታች ዕፅ ናቸው የሚል ወቀሳ እየቀረበባቸው ይገኛል፡፡ የጫማዎቹ ደጋፊዎች በበኩላቸው ከብዙ አስርት ዓመታት የለውጥ አልባ ጉዞ በኋላ የተገኙ ዓብዮታዊ የቴክኖሎጂ እምርታዎች ናቸው ሲሉ ውዳሴያቸውን ያቀርቡላቸዋል፡፡ ቀስ በቀስ ታድያ ጫማዎቹ መጀመሪያ ሲተዋወቁ ከገጠማቸው ተቃውሞ ይልቅ ተቀባይነትን እያገኙ ስለመሆናቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ይመሰክራሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በያዝነው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የዓለም ክብረ ወሰኖች ሲሰበሩ ብዙም ላናይ እንችላለን ተብሏል፡፡ ለዚህም በምክንያትነት ሪከርድ የሚሰበሩባቸው ሩጫዎች በጣም ታክቲካዊና እጅግ ተስማሚ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ የሚከናወኑ መሆናቸውና በአንፃሩ እንደ ኦሎምፒክ ያሉት ግን ከዚህ የተለዩ በመሆናቸው ነው ተብሏል፡፡
ምንጭ፤ Tech Xplore
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-07-record-setting-super-experts.html
ከ65 ዓመታት በኋላ መንቀሳቀስ የቻለው ግዙፉ ባቡር
ከ65 ዓመታት በኋላ መንቀሳቀስ የቻለው ግዙፉ ባቡር
=====================
በእንፋሎት ይሰራ የነበረ የሎኮሞቲቭ ተጎታች ባቡር ያለስራ ቆሞ ከነበረበት ከ65 ዓመታት በኋላ ከሃያ ዓመት በላይ በተደረገለት መሉ እድሳት ከሰሞኑ መንቀሳቀስ ጀምሯል፡፡ በ1999 በታሪካዊ የባቡር ስራዎች ላይ የሚንቀሳቀስ የበጎ ፍቃድ ማህበር እንደፕሮጀክት ይዞ ሲሰራው የነበረው ይህ የባቡሩ እድሳት በአሜሪካ የኒው ሜክሲኮ ግዛት የሚገኝ ግዙፍ ባቡር ነበር፡፡ በእድሳት ስራው የተሳተፉ ባለሙያዎች ባበሩ ስራ አቁሞ ከነበረበት የኒው ሜክሲኮ ግዛት አልቡኪርካይ ፓርክ ላይ በ1999 ባበሩን በግዥ ከተረከቡ በኋላ ለድፍን 20 ዓመታት እድሳት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

እንደአውሮፓውያኑ ከ1956 በኋላ ምንም አይነት ጉዞ ማድረግ ያልቻለው ይህ ግዙፍ ባቡር ለ20 ዓመታት ሲደረግለት ከቆየው የእድሳትና የጥገና ስራ በኋላ በሃምሌ 24 2021 ከ65 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን ጉዞ ማድረግ ችሏል፡፡ Santa Fe 2926 የሚል ስያሜ ያለው ይህ ግዙፍ ባቡር ከ250 ቶን በላይ የሚመዝን ሲሆን ለመንገደኞች ከተሰሩ ግዙፍ ባቡሮች መካከል በመጀመሪያዎቹ ደረጃ የሚገኝ ነው፡፡

ይህ የባቡር ስሪት እንደአብዛኞቹ በእንፋሎት የሚሰሩ ባቡሮች በድንጋይ ከሰል የሚንቀሳቀስ ሳይሆን በነዳጅ የሚሰራ መሆኑ ለየት የሚደርገው ነው፡፡ እንደአውሮፓውያኑ በ1944 ባልድዊን ሎኮሞቲቭ በተባለ ኩባንያ ለመንገደኞች መጓጓዣና ለእቃ ጭነት እንዲውል ተደርጎ የተሰራው ይህ ግዙፍ ባቡር አሁን ላይ በኒው ሜክሲኮ ግዛት እንዲንቀሳቀስ እና እንዲጓዝ የተፈቀደለት ርዝመት ከ300 ጫማ የማይበልጥ ነው፡፡

ባለሙያዎች እንደሚገለፁት እንዲህ ያሉ የባቡር የትራንስፖርት አማራጮች ከሌሎች የአየርና የመርከብ መጓጓዣዎች አንፃር ዝቅተኛ የአየር ብክለት ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ይበልጥ ተመራጭ ያደርገዋል፡፡ Santa Fe 2926 ባቡር በ1950ዎቹ ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት ካቆመና ከ65 ዓመታት ቆይታ በኋላ ታሪካዊውን ጉዞ ከተማዋ ውስጥ በሚገኝ የባቡር ሃዲዲ መስጠት መጀመሩን የሲኤንኢቲ ዘገባ ያሳያል፡፡
https://www.cnet.com/.../see-a-giant-steam-locomotive.../
የሰው ልጅ ስልጣኔ ወደ ፍፃሜው እያመራ ነው ሲል አዲስ ጥናት አመላከተ
የሰው ልጅ ስልጣኔ ወደ ፍፃሜው እያመራ ነው ሲል አዲስ ጥናት አመላከተ
=====================
በአውሮፓውያኑ 1972 የማሳቹሴት ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ተመራማሪዎች ያጠኑት ጥናት የያዝነው ኢንዱስትሪያዊ ስልጣኔ በ21ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ እንደሚቋጭ መላምቱን አስቀምጦ ነበር፡፡ ጥናቱ በጊዜው ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው ቢሆንም አሁን ላይ የወጣ አዲስ ጥናት ግን የቀድሞው ጥናት ትንበያ በአሳሳቢ ሁኔታ እውነት እየሆነ መምጣቱን አመላክቷል፡፡

በያል ጆርናል ኦፍ ኢንዱስትሪያል ኢኮሎጂ ላይ የወጣው አዲሱ ጥናት የ1972ቱን ጥናት ተመልክቶና ከእርሱ በኋላ ነገሮች በምን መልኩ እየሄዱ እንደሆነ በምጣኔ ሐብት እድገት እና ሐብት አጠቃቀም ላይ ያተኮሩ ተጨባጭ መረጃዎችን በመመርመር ነው የተከናወነው፡፡ በዚህም የሰው ልጅ ስልጣኔ እውነትም ወደ ፍፃሜው እየገሰገሰ መሆኑንና ምናልባትም በጣም ቀረበ ከተባለ ይህ ለሺህ ዓመታት የዘለቀ የስልጣኔ ጉዞ ከ20 ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በአውሮፓውያኑ 2040 ሊገታ ይችላል ብሏል፡፡ ሆኖም ይህ የሚሆነው የምድርን ሀብት አሁን በምናደርገው ልክ እየበዘበዝን የምንቀጥል ከሆነ ብቻ መሆኑን አስቀምጧል፡፡

ሆኖም የሰው ልጅ ስልጣኔ ያበቃል ማለት የሰው ልጅ ይጠፋል ማለት እንዳልሆነ ተመራማሪዎቹ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ምጣኔ ሐብታዊ እና ኢንዱስትሪያዊ እድገት ቆሞ የቁልቁለት ጉዞ ጅማሬ ይሆናል ብሎም የህይወት ዘይቤያችን በከባዱ ይጎዳል እንደማለት ነው፡፡ በዚህ የቁልቁለት ጉዞ ውስጥ የምግብ ምርት እና የሰው ልጆች ኑሮ ደረጃ ተጎጂዎች ይሆናሉም ተብሏል፡፡

በተቃራኒው ግን እስካሁን ስንከተል የቆየነውን አካሄድ በማስተካከል መጓዝ ከጀመርን የሰው ልጅ ስልጣኔ አሁንም ተስፋ ያለው መሆኑ በአዲሱ በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡
ምንጭ፤ Futurism
ለተጨማሪ፤ https://futurism.com/the-byte/mit-prediction-civilization-collapse-on-track
ከፓርክ አምልጣ ወደ ከተማ የገባችው አንበሳ