TechIn2
1.16K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
በኤሌክትሪክ የሚሰራ የውሃ ላይ መጓጓዣ ከወደ ሞስኮ
በኤሌክትሪክ የሚሰራ የውሃ ላይ መጓጓዣ ከወደ ሞስኮ
*****************************************
*******
በመኪኖች ብዛት ምክንያት በሚፈጠር የትራንስፖርት መጨናነቅ የተማረረችው ሞስኮ በኤሌክትሪክ የሚሰራ የኤሌክትሪክ ጀልባን ለማቅረብ ተዘጋጅታለች፡፡ ከወደ ከተማዋ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ከከባቢ አየር ጋር ካለው መጣጣም በተጨማሪ የመንገድ ላይ መጨናነቆችን ለመቅረፍ ወሳኝ ነው፡፡ ሞስኮ ከዚህም በተጨማሪ የውሃ ላይ መጓጓዣዎችን መጠቀም በመኪኖች ላይ ያለውን ጥገኝነት በእጅጉ ይቀንሰዋል ብላ ታስባለች፡፡
የኤሌክትሪክ ጀልባዎቹ 42 መቀመጫዎች ያሏቸው ሲሆን በአማካኝ 22 ሜትር ርዝመት ያላቸው ናቸው፡፡ በውስጣቸውም ሀይል መሙያ ዩኤስ ቢ፣ ዋይ ፋይ፣ ለስኩተሮችና ለሳይክሎች ማስቀመጫ እንዲሁም የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችሉ ጠረጴዛዎች ያሏቸው ናቸው፡፡
ወደ አገልግሎት የሚቀርቡት ጀልባዎች ትክክለኛ ቁጥራቸው ባይታወቅም የሞስኮ ትራንስፖርት ግን ለጊዜው በቀን 16 ሺህ ሰዎችን ማጓጓዝ የሚችሉ ሁለት ጀልባዎች መዘጋጀታቸውን ይፋ አድጓል፡፡ በሞስኮ የትራንስፖር ዘርፍ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ማክሲም ሊክሱቶቭ በቀጣይ አመት ከየትኛውም የህዝብ ትራንስፖር በአምስት እጥፍ የሚፈጥን የትራንስፖርት አገልግሎት ለመጀመር እንደሚችሉ እና ከግል መኮኖች በእጥፍ የሚፈጥን ተመራጭ የትራንስፖር ዘርፍ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት በሞስኮው ከንቲባ ጎብኝት የተደረገበት አዲሱ የኤሌክትሪክ ጀልባ በተለያዩ ወርሃዊና አመታዊ የክፍያ አማራጮች አገልግሎቱን ለመስጠት ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡ ባለፈው ጥር ወር የወጣው የቶም ቶም ትራፊክ ኢንዴክስ እንደሚያመለክተው ሞስኮ የአለማችን የተጨናነቀች ከተማ ደረጃ ውስጥ መግባቷ ይታወቃል፡፡
ሀገራት ለከተሞቻቸው የመጨናነቅ ችግር የተለያዩ መፍትሔዎችን እያፈላለጉ ሲሆን ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተሸሉ ውጤቶችን የሚያስገኝ መሆኑን ከሞስኮ፣ ኒውዝላንድ፣ አውክላንድ እና ሰቶኮልም ትልቅ ምሳሌዎች ናቸው፡፡
ምንጭ cities-today
ተጨማሪ ንባብ https://cities-today.com/moscow-to-launch-electric-ferry-service-next-year/?fbclid=IwAR1EmK5559Qb_Q2K4coh4hWyLtaXy8nocGTMo24e8hQxc6x8TiVKIZtBzrU
ናይልስትሪም፤ አዲስ የድምፅ ማሰራጫ ለኢትዮጵያ
=========
ሰላም ውድ ተከታታዮቻችን፤ ለዛሬ ናይልስትሪም የተሰኘውን የድምፅ ይዘቶችን የሚያሰራጭ አዲስ መተግበሪያ ልናስተዋውቃችሁ ወደድን፡፡ ናይል ስትሪም በወጣት ተማሪና የፈጠራ ባለሙያዎች የቀረበ ሙዚቃን ጨምሮ የተለያዩ አይነት የድምፅ ይዘቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያሰራጭ መተግበሪያ መሆኑን ከመተግበሪያው ፈጣሪዎች አንዷ የሆነችው ተማሪ ኤልሻዳይ ትናገራለች፡፡ እንደ ኤልሻዳይ ከሆነ ተጠቃሚዎች በወር 15 ብር በመክፈል ብቻ ሁሉንም የድምፅ ይዘቶች በጥራት ማግኘት ይችላሉ፡፡
ከዋጋ ተመጣጣኝነት ባለፈም ግን መተግበሪያው የማህበራዊ ሚዲያ አይነት ይዘት ያለውና አርቲስቶችም ከተከታታዮቻቸው ጋር ትስስርን እንዲፈጥሩ የሚያስችል አቀራረብ ያለው ነው፡፡ በተጨማሪም ለአርቲስቶቹ ስለ ተከታታዮቻቸው መረጃን እንደሚሰጣቸው ኤልሻዳይ ገልፃልናለች፡፡
ስለ መተግበሪያው ሙሉ መረጃውን ተማሪ ኤልሻዳይ እንደሚከተለው ታብራራዋለች፤ ተከታተሏት፡፡
የዩትዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ከሀገር ውስጥ እና መላው ዓለም የተውጣጡ ልዩ ልዩ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን መረጃዎችን ያግኙ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=9YZAo36Hmfg&t=38s
የስማርት ስልክ ስክሪኖችን የአፈርና ውሃ ብክለትን ለመለየት
*****************************************
**************
በአለማችን ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ የስማርት ስልክ ስክሪኖች (touchscreen) የተለየ ማሻሻያ ሳይደረግላቸው የአፈርንና ውሃ ብክለትን መለየት የሚያስችል ብቃት እንዳላቸው ተነገረ፡፡ አንድ በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የተሰራ ጥናት እንዳመለከተው የስማርት ስልክ ስክሪኖች ያላቸው ከፍተኛ የሆነ ሴንስ የማድረግ ብቃት የአፈርንም ሆነ የውሃን ብክለት መለየት እንደሚያስችላቸው ጠቁሟል፡፡
በሙከራ ወቅትም የፈሳሽ ናሙና በስክሪኖቹ ላይ በማድረግ ናሙናው የተወሰደበት አፈርም ሆነ ውሃ የተበከለ መሆኑንና አለመሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ እንደ ተመራማሪዎቹ ሀሳብ ከሆነ ይህ ጅምር ለወደፊት ለጤና አገልግሎት የሚውል የባዮሴንሲንግ እና የምርመራ አገልግሎትን ሰዎች በስልካቸው ወይም በኪሳቸው ማግኘት እንዲችሉ የሚያደርግ ነው፡፡
በንክኪ የሚሰሩ የስልክ ስክሪኖች በአሁኑ ወቅት በሁሉም የአለማችን ክፍሎች ጥቅም ላይ እየዋሉ ሲሆን ስክሪኑ የተሸፈነባቸው ኤሌክትሮዶች በእጣት ሲነኩ ስልኩ የተለያዩ ትዕዛዞችን እንዲፈጽም ያስችለዋል፡፡ በካምብሪጅ የማኑፋክቸሪንግ ምርምር ተቋም ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ሮናን ዳሊ የስማርት ስልክ ስክሪንን በተለያዩ መንገዶች ጥቅም ላይ ለማዋል ጥረት እያደረጉ እንደሆነና ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ኤሌክትሮ ላይቶችን በመጠቀም መስራት መቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በሀሳብ ደረጃ የዚህ ቴክኖሎጂ እውን መሆን አንድ ሰው ውሃ ከመጠጣቱ በፊት ስማርት ስልኩ ላይ ጠብ በማድረግ ሊጠጣ ያሰበው ውሃ የተበከለ መሆኑንና አለመሆኑን ማረጋገጥ የሚያስችለው ነው፡፡ አሁን ላይ ያለው የስማርት ስልኮች ስክሪን በብዛት በቀላሉ የሚግባባው ከእጣታችን ጋር ሲሆን ከስልኩ አንድ ጎን ብቻ የተወሰኑ የኤሌክትሮድ ውቅሮችን በማስተካከል የስልኩን ሴንስ የማድረግ ብቃት ማሻሻል እንደሚቻል ተመራማሪዎቹ አሳውቀዋል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-07-smartphone-screens-effective-sensors-soil.html
ተራማጁ ዓሣ
=======
የውሃ ውስጥ እንስሳት ብዙዎቸቹ አየርን ከውሃው ወስደው የሚተነፍሱ መሆናቸው አንድ ቢያደርጋቸውም በአካላዊ ቅርፅ፣ መጠን እና የአኗኗር ዘይቤ ግን እጅጉን የተለያዩ የሚሆኑበት አጋጣሚ አለ፡፡ እነዚህ የሜክሲኮ ተራማጅ ዓሣ ወይም አኪሎሪሰስ በሚል ስያሜ የሚታወቁት እነዚህ ዓሣዎች በሰውነታቸው ላይ ካለው ሹል ሆኖ የቆመ እሾሀማ ፀጉር ባሻገር ልክ እንደስማቸው በመራመድ ችሎታቸውም ይታወቃሉ፡፡ የዓሣ ዝርያዎቹ በተለይ አንድ ውሃ አካል የታችኛው ወለል ላይ ሲገኙ አራት እግሮቻቸውን ከጎናቸው በማውጣት በሜክሲኮ ከተማ ባሉት ረግረጎች ይጠቀሙባቸዋል፡፡
ታድያ እነዚህ ዓሣዎች የውሃ ውስጥ ፍጠራን እንደመሆናቸው እንዴት እግርን ሊታደሉ ቻሉ የሚል ጥያቄ ያነሱ ይሆናል፤ ለዚህ ምላሹ ዓሣዎቹ ስሪታቸው ከእንቁራሪት መሰል ዝርያዎች (Amphibian) መሆኑ ነው፡፡ እነዚህ የእንቁራሪት እና መሰል ዝርያዎች ብዙውን ጊዜ የህይወት ጉዞዋቸውን የሚጀምሩት በውሃ ውስጥ ለመተንፈስ የሚያስችላቸውን ጊል ይዘው ነው፡፡ በጊዜ ሂደት ካደጉ በኋላ ግን ይህ ጊላቸው ጠፍቶ በየብስ ላይ ኑሮን ይመሰርታሉ፡፡ ሆኖም አኪሎሪሰሶች በዚህ የተፈጥሮ ሂደት ከመገዛት ይልቅ ጊላቸውን ይዘው እዛው ውሃ ውስጥ መቆየትን ይመርጣሉ፡፡ ይህ በሳይንሱ ዓለም ኒኦቴኒ በመባል የሚታወቅ ሁነት ነው፡፡
አኪሎሪሰስ ኪቺሚለኮ በተሰኘው ከሜክሲኮ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ሀይቅ ውስጥ ኑሮዋቸውን መስርተው ለአንዴም ሀይቁን ለቀው ሳይወጡ በዚያው ይኖራሉ፡፡ እስከ 30 ሴ.ሜ ድረስ የሚረዝሙት ዓሣዎቹ ትናንሽ ነፍሳትን ተመጋቢ ናቸው፡፡ የሜክሲኮ ተራማጅ ዓሣዎቹን ለወትሮው የሀይቁ ንጉስ የነበሩ ቢሆንም ቲላፒያ እና ክራፕ የተባሉት ወራሪ የዓሣ ዝርያዎች ህፃናት ልጆቻቸወውን በመብላት ጭምር የመጥፋት አደጋ ጋርጠውባቸው ይገኛሉ፡፡
ምንጭ፤ live science
ልናዳብራቸው የሚገቡ የአይ.ሲ.ቲ ክህሎቶች
======================
ምንም እንኳን ቴክኖሎጂ የተቋማትን የአሰራር ስርዓት በማዘመን ውጤታማነትን በቃላሉ እንዲያገኙ ያስቻለ ቢሆንም አሁንም ብዙ ድርጅቶች እና ኩባንያዎች ቴክኖሎጂን በተሟላ ሁኔታ የሚተገብሩበት ሂደት አልተጀመረም፡፡ በኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ውስጥ የሚጠቃለሉትን እንደስልክ፣ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ያሉ ቀድምት የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል እንደ አይ.ሲ.ቲ ክህሎቶች የሚቆጠሩ ቢሆንም በዚህ ላይ ዘመናዊው ክህሎት የማይታከልበት ከሆነ የተሟላ የአይ.ሲ.ቲ ክህሎት ሊባል አይችልም፡፡ አሁን ላይ ሁሉም ዘርፍ ሊባል በሚችል መልኩ የተሟላ የአይ.ሲ.ቲ ክህሎቶችን የሚፈልግበት ጊዜ ሲሆን ሂደቱም ቴክኒካል እና ቴክኒካል ባልሆነ መንገድ ሊፈፀም ይችላል፡፡
ማህበራዊ ሚዲያን በአግባቡ መጠቀም (Social Media Management)
ምንም አይነት ሚና ይኑርን አሁን ባለው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና የአይ.ሲ.ቲ ስርዓት ማህበራዊ ሚዲያን በአግብባቡ እና ልናተርፍበት በምንችለው መንገድ ካልተጠቀምነው ብዙ ነገር እያጣን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ መረጃን የማጋራት አቅም፣ ከደንበኞች ጋር የመወዳጀት እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ተግባራቶችን ለማከናወን የዚህ ክህሎት አስፈላጊነት እንዲህ በቀላሉ አይገለፅም፡፡
መረጃን የማደረጃት ክህሎት (Data Management and Queries)
እንደ ኤክሴል ያሉ የመረጃ ማደራጃ ወይም (Spreadsheet) መተግበሪያዎችን እንደየሁኔታው መጠቀም እና ስራ ላይ ማዋል ከተማሪዎች አንስቶ በተቋማት ውስጥ ተቀጥረው እስከሚሰሩ ሰራተኞች ድረስ ይህ ክህሎት እጅግ ዘመናዊ እና መሰረታዊ ከመሆኑም ባለፈ የስራ ምርታማነትን ለማምጣትም እጅግ ወሳኝ የሚባል ነው፡፡ መረጃን ተንትኖ እንደአስፈላጊነቱ አደራጅቶ ማስቀመጥ የምንሰራውን ስራ በቀላሉ ለማጎልበት እና ደካማ ጎኑን ለይቶ ላመስቀመጥ በእጅጉ ይረዳል፡፡
ፅሁፍ የማቀናበር እና የአቀራረብ ችሎታ (Word Processing and Presentation skills)
ብዙ ነገሮች በዲጂታል መንገድ በሚፈፀሙበት እና አብዛኞቹ የማንዋል ስራዎች እየቀሩ በመጡበት በአሁኑ ሰዓት ፅሁፍን በሚገባ አቀናብሮ በዲጂታል መሳሪያዎች ማስቀመጥ እና ሌሎች አስፈላጊ የቴክኒካል ዝርዝሮችን አሟጦ መጠቀም በዘመናዊው የ አይ.ሲ.ቲ ክህሎት በቀዳሚነት የሚቀመጥ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈም የዲጂታል መሳሪያዎችን በመጠቀም የአቀራረብ ክህሎቶችን ማዳበር እና የተሻለ ስልት መተግበር በዚህ ሂደት ውስት በዋናነት የሚካተት ነው፡፡
የኪቦርድ አጠቃቀም እና የመተየብ ፍጥነት
ሁሉንም የኪቦርድ አማራጮች በሚገባ መረዳት እና በፍጥንት ሊያሰሩ የሚችሉትን ቀላል አማራጮች በስራ ላይ ማዋል ሌላው መሰረታዊ የአይ.ሲ.ቲ ክህሎት ነው፡፡ ይህን በማድረግ ሂደት የመተየብ ፍጥነታችን ሌላው ተያያዥ ክህሎት ሲሆን የምንሰራውን ስራ በፍጥነት ለማጠናቀቅ እና የተሻለ ውጤት እንድናስመዘግብም በእጅጉ የሚረዳን ነው፡፡
የኦንላይን ምርምር እና የኢሜል አጠቃቀም
የተለያዩ የመፈለጊያ መሳሪያዎችን ተግባር ላይ በማዋል ስለምንሰራው ስራ ተጨማሪ መረጃዎችን ማፈላለግ እና በበየነ-መረብ አማካኝነት ቀላል ምርምሮችን መካሄድ በአይ.ሲ.ቲ ክህሎት ላይ በዋናነት የሚካተት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንደ ኢሜል፣ ጎግል እና ሊንኪድን ያሉ ግላዊ የመገናኛ አካውንቶችን በመፍጠር መሰረታዊውን የመላላክ ሂደት መጀመር እና ስራዎችን በዚህ መሳሪያ ለመስራት መሞከር ሌላው የአይ.ሲ.ቲ ክህሎት ነው፡፡
ከለውጦች ጋር ራስን ማሻሻል
በምንጠቀማቸው እያንዳንዱ ቴክኖሎጂዎች እና የአይ.ሲ.ቲ ክህሎቶች ላይ አዳዲስ ነገሮች ሲጨመሩ ራስን በማስተማር እና ሁሌም ዝግጁ በመሆን ከጊዜው ለውጥ ጋር እራስን አብሮ ማስኬድ እጅግ መሰረታዊ ነው፡፡ ያለ አዳዲስ ክህሎቶች ስራን በፍጥነት ለመስራት እና ተፈላጊውን ውጤት ማምጣት ስለማይቻል ራስን ለአዳዲስ ለውጥ ዝግጁ ማድረግ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡
ምንጭ፡ The balance careers
ተጨማሪ https://www.thebalancecareers.com/information-and...
የሸዋርዝቻይልድ ቀመርና የብላክ ሆል ብያኔ
=====================
ብላክ ሆሎች በኮስሞሎጂ ጥናት ውስጥ በጣም አወዛጋቢ ከሚባሉት ግኝቶች ውስጥ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። አብዛኞቹ በመጠነይዘታቸው ከምድራችን በጣም የሚያንሱ ቢሆኑም በዙሪያቸው የሚፈጥሩት የስበት ሀይል እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ማንኛውም ቁስ አካል (ብርሀንም ቢሆን) ውስጣቸው ከገባ በፍፁም ሊወጣ አይችልም።
እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1920ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ካርል ሸዋርዝቻይልድ የተባለ የጀርመን ተወላጅ የፊዚክስ ምሁር አንድ ቁስ አካል ከብላክ ሆል ለማምለጥ የሚያስፈልገውን ትንሽ ርቀት ለመወሰን የሚያስችል ቀመር እንዳገኘ ይነራል። ይህ የፊዚክስ ቀመር በሳይንሱ አለም የሸዋርዝቻይልድ ራዲየስ (Shwarzchild's radius) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን እንደአውሮፓውያኑ በ1916 በዚሁ ተመራመሪ እንደተገኘ ይነገራል፡፡ ቀመሩ R=2GM/C^2 ተበሎ የሚታወቅ ሲሆን ይህም R ራዲያስን (radius) ሲወከል G የብላክ ሆል የስበት ሀይል፣ M የቁስ አካሉ ክብደትን፣ C ደግሞ የብርሀን ፍጥነትን ይወክላል፡፡ በፊዚክሱ አለም ትልቅ እውቅና ያለው ይህ ቀመር ከብላክ ሆል የስበት ሀይል ለማምለጥ የሚያስፈልገውን ትንሹን ርቀት በማብራራት ምን አይነት የብላክ ሆል ብያኔ መስጠት እንደሚቻል ያሳያል።
እንደተመራማሪዎች ገለጻ ከብላክ ሆል የስበት ሀይል ለማምለጥ የሚያስፈልገው ፍጥነት ስኬፕ ቬሎሲቲ (Escape velocity) ተብሎ ይታወቃል። ከዚህ አንጻር ከላይ በተጠቀሰው ቀመር መሰረት ምድራችን የሸዋርዝቻይልድ ራዲየሱዋ 2ሳ.ሜ እስኪያክል ድረስ ብናፍጋት (dense) ወደ ብላክ ሆል የመቀየር እድል እንደሚኖራት ይነገራል። ይህም የሚሆነው ከመጠነ ይዘቱዋ አንፃር የሚኖራት የስበት ሀይል እጅግ ከፍተኛ ስለሚሆን ነው።
https://astronomy.swin.edu.au/cosmos/S/Schwarzschild+Radius
የአንድሮይድ ተቀባይነት በዓለም ዙሪያ
===================
አፕል የሚያስተዳድረው የአይፎን ስልክ ሲስተም እንደአውሮፓውያኑ በ2007 በተዋወቀ በጥቂት ወራት ውስጥ በመስከረም 23 2008 የአንድሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ለአለም ይፋ ሲደረግ የአፕሉ መስራች ሲቲቭ ጆብስ ሊቀናቀነው የመጣውን ይህን የጎግል ምርት በፍጥነት ለመርታት ብዙ ሙከራዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ትንቅንቁ ከጀመረበት 2008 አንስቶ የገበያ ፉክክሩ እስከቀጠለበት እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ሁለቱም ምርቶች የተጠቃሚውን ልብ ያሸንፋል ያሉትን ማዘመኛ እያካተቱ መተዋል፡፡
አሁን ላይ የሁለቱ ምርቶች የገበያ ውድድር በአንድሮይድ የበላይነት የተያዘ ቢሆንም በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች የአይፎን ፈላጊዎችና ተጠቃሚዎች ብዛት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ከሰሞኑ ኤሌክትሮኒክ ሃብ የተባለ የቴክኖሎጂ አማካሪ ድርጅት በአንድሮይድ እና በአይፎን መካከል በአለም አቀፍ ዙሪያ ስላለለው ተቀባይነት እና የገበያ ተደራሽነት የሚያሳይ መረጃ ይፋ አደርጎ ነበር፡፡ እንደድርጅቱ የስታቲክስ መረጃ የሁለቱ ምርቶች የገበያ ውድድር ሰርቬው በተካሄደባቸው 142 ሀገራት መነሻ አደርጎ የተካሄደ ሲሆን በዚህም በ74 ሀገራት የሚገኙ የስልክ ተጠቃሚዎች የአንድሮይድ ተጠቃሚ እንደሆኑ ያሳያል፡፡ በአንጻሩ ሰርቬው ከተካሄደባቸው 142 ሀገራት 65 የሚሆኑት የበለጠ የአይፎን ተጠቃሚ መሆናቻውን የሚያሳይ ሲሆን ከሁለቱም ሊመደቡ ያልቻሉ ሶስት ሀገራት (ቤላሩስ፣ ፊጂ እና ፔሩ) በገለልተኝነት ተመዝገበዋል፡፡
የአንድሮይድ ምርት ተቀባይነት በዚህ ሰርቬ መሰረት በሰሜን አሜሪካ፣ በደቡብ አሜሪካ፣ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ አካባቢዎች ይበልጥ ቁጥሩ አይሎ የሚገኝ ሲሆን በአውሮፓ ብቻ ሰርቬው ከተደረገባቸው 37 ሀገራት ሃያውን በመያዝ የአይፎን ምርት ብላጨውን ይወስዳል፡፡
በአፍሪካ ከሁዋዌ ምርቶች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የአንድሮይድ ተቀባይነት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሲሆን በተለይም በኢትዮጵያ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያለው ብዙ ቁጥር ያለው ተጠቃሚ የአንድሮይድ ተቀባይነትን በእጅጉ አሳድጎታል፡፡ ሁዋዌ በአህጉሪቱ ከፍተኛ የስልክ ሽያጭ የሚያካሂድ ኩባንያ ከመሆኑ አንፃር አሁን እየተጠቀመበት ካላው የአንደሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እራሱ ወዳበለጸገው ሃርመኒየ የተሰኘ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ሲሸጋገር አለም አቀፍ ገበያው ላይ ትልቅ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡ bigthink
ተጨማሪ https://bigthink.com/strange-maps/android-vs-apple
ሴት እስከምትሆኚ ድረስ ወንድ ነሽ፤ ፆታቸውን በሚቀይሩት ኤሊዎች ዓለም
ሴት እስከምትሆኚ ድረስ ወንድ ነሽ፤ ፆታቸውን በሚቀይሩት ኤሊዎች ዓለም
=====================
ሁሉም ባለ ለስላሳ ቅርፊት ወይም ሶፍትሼል ኤሊዎች ህይወታቸውን ወንድ ሆነው እንደሚጀምሩ ግን ደግሞ የአየር ሙቀቱ እና ፕሮቲን ይዘቱ እየተስተካከለ ሲመጣ ከመፈልፈላቸው በፊት ሴት እንዲሆኑ የተመረጡት ወደ ሴትነት እንደሚለወጡ ስፒይኒ በተሰኙት ዝርያዎች ላይ የተሰራ አዲስ ጥናት አመላከተ፡፡

በኒኮል ቫሌንዙዌላ የሚመራው የአዮዋ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጥናት ቡድን የደረሰበት ድምዳሜ እንደሚያመላክተው እንስሳቱ ከመፈልፈላቸው አስቀድሞ ፆታቸውን የሚወሰነው ባላቸው የክሮሞሶም ብዛት እና አይነት ከመሆን ይልቅ በክሮሞሶሞቹ አማካኝነት በሚመረተው ፕሮቲን መጠን ላይ በመንተራስ ነው፡፡ ይህ ታድያ በሳይንሱ ሴክስ ክሮሞሶም ዶሴጅ ኮምፐንሴሽን ተብሎ የሚጠራ ሁነት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ታድያ ከፕሮቲን ምርትም ባለፈ የመፈልፈል ሂደቱ እንቁላሎቹ ባሉበት አካባቢ ሙቀት ላይ የሚወሰን በመሆኑ ፆታቸውም እንደ አየሩ ሊቀያየር ይችላልም ተብሏል፡፡ ለምሳሌ የከባቢ ሙቀቱ ከፍ ባለ ጊዜ የወንዶቹ ቁጥር ከፍ ይላል እንደማለት ነው፡፡

የፆታ ልየታ ውስብስብ እና ከአንዱ እንስሳ ወደ ሌላኛው የተለያየ ሂደት ነው፡፡ ለምሳሌ የሰው ልጅ እና አብዛኛዎቹ አጥቢ እንስሳት ፆታ የሚወሰነው እንቁላሉ በሚያድግበት ጊዜ በውስጡ በያዛቸው የተለያዩ ክሮሞዞሞች አማካኝነት ነው፡፡ ሆኖም እንደ አዞና ኤሊ ባሉት እንስሳት ዘንድ የእንስሳው ፆታ የሚወሰነው እንቁላሉ ሳይፈለፈል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን ደግሞ ካደገ በኋላ ነው፡፡

እያንዳንዱ ክርሞሶም ለተለያዩ ባህርያት ምክንያት የሚሆኑ ፕሮቲኖችን የማምረት ስራን ይሰራል፡፡ ስለዚህም የክሮሞዞሙ ዓይነት የሚሰሩ ፕሮቲኖች መጠንን ይወስናል፡፡ በሌላ መልኩ የሰው ልጆች X እና Y ክሮሞዞም አላቸው፤ ሆኖም ሴት ባለ ለስላሳ ቅርፊት ኤሊዎችን የተመለከትበን እንደሆነ ሴቶቹ ZW ክሮሞዞም ይዘዋል፡፡ ወንዶቹ ደግሞ አንድ ወይም ሁለት Z ክሮሞዞም አላቸው፤ የሰው ልጆች በዚህ መልኩ አንድ ክርሞዞም ካላቸው ከባድ የጤና ችግር ይኖረዋል፡፡

ነገሩን የመረመሩት ተመራማሪዎቹ ZW ክሮሞዞም ያላቸው ኤሊዎች በእድገታቸው ጅማሮ ላይ ከወንዶቹ ጋር ተመሳሳይ መጠን ያለው የZ ፕሮቲንን እንደሚያመርቱና በዚህም ከወንዶቹ ጋር ተመሳሳይ እንደሚሆኑ አረጋግጠዋል፡፡ ሆኖም በዕድገት ውስጥ ሳሉ የሚከሰቱ ለውጦች ኋላ ላይ ሴት ሆነው እንዲፈለፈሉ ያደርጓቸዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም አጥኚዎቹ እንቁላሎቹ ያሉበት አካባቢ ሙቀቱ በጨመረ ቁጠር ወንድ መስለው የሚፈለፈሉት እንቁላሎች እንደሚበዙ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ጥናቱ የተደረገባቸው ስፒይኒ የተሰኙት ባለ ለስላሳ ቅርፊት ኤሊ ዝርያዎች (Apalone Spinifera) በሰሜን አሜሪካ ባሉት ጨዋማ ያልሆኑ ውሃ አካላት ውስጥ ከሚገኙት ኤሊዎች ትልቆቹ ናቸው፡፡ በውሃ አካሉ አጠገብ ባሉ ፀሐይ የሚያገኛቸው የአሸዋ አልያም ጠጠር ቦታዎች ላይ የሚጥሏቸው እንቁላሎች ከ60 እስከ 80 ቀናትን ጠብቀው ይፈለፈላሉ፡፡
ምንጭ፤ Cosmos
ለተጨማሪ፤ https://cosmosmagazine.com/nature/animals/for-softshell-turtles-youre-male-until-youre-female/?utm_content=buffer8c9e9&utm_medium=social&utm_source=twitter.com&utm_campaign=buffer
በአካባቢ ብክለት ምክንያት ወደ ሮዝ የተቀየረው ሃይቅ
----------------------------------------
በአርጀንቲና የደቡብ ፓታጎኒያ ግዛት በሚገኘው ትንሽዬ ሃይቅ ላይ የተፈጠረው የሰሞኑ ክስተት ብዙዎችን አነጋግሯል፡፡ በዘገባው እንደተገለፀው የሃይቁ ጠቅላላ ክፍል ጎጂ ሊባል በሚችል የአካባቢ ብክለት ምክንያት ወደ ደማቅ ሮዝ ቀለም ሊቀየር እንደቻለ እና ጥልቀቱ አነስተኛ ከሆነው ከዚህ ሃይቅ አጠገብ ያለ ወንዝ ደግሞ መጥፎ ሽታ ማምጣቱ ተነግሯል፡፡
በአካባቢው ምርምሮችን ሲያደርጉ የነበሩ ሳይንቲስቶችና የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች እንደገለፁት የሃይቁ ቀለም ወደ ሮዝ ሊቀየር የቻለው በአካባቢው የሚገኙ የአሳ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በሃይቁ አቅራቢያ በሚገኝ ወንዝ ላይ በሚለቁት ጎጂ የኬሚካል ውጋጅ እንደሆነ አንስተዋል፡፡ ጥልቀቱ አነስተኛ ለሆነው ለዚህ ሃይቅ እንደገባር የሚያገለግለው ወንዝ ላይ ለብዙ ጊዜያት ሲለቀቅ የቆየው እንደሶዲየም ሰልፌት ያለ የጸረ ባክቴሪያ ኬሚካል ውጋጅ የችግሩ መነሻ መሆኑን የሚነሱት እነዚህ ባለሙያዎች ሰዎች በቸልተኘነት የሚፈፅሟቸው ተግባራት በተፈጥሮ ላይ የሚያስከትለውን ትልቅ ጥፋትም የሚሳይ ነው ይላሉ፡፡
በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች በሃይቁ ላይ እየተፈጠረ ያለውን የቀለም ለውጥ እና በወንዙ ስፍራ የተከሰተውን መጥፎ የጠረን ሽታ ያስታወቁ ቢሆኑም የሰማቸው እንዳልነበረ የሚናገሩት ከአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ፓብሎ ላዳ ለቀለሙ መለወጥ ምክያት የሆነው የኬሚካል ውጋጅ ወደ ወንዙ ከመቀላቀሉ በፊት ቀላል ህክምና ቢደረግለት ኖሩ ችግሩን ቀድሞ መከላከል ይቻል እንደነበር ይናገራሉ፡፡
በአካባቢ ብክለት ምክንያት ወደ ሮዝ የተቀየረው ይህ የአርጀንቲና ሃይቅ ለየት ያለ አጋጣሚ ቢሆንም በአለማችን ሮዝ ቀለም ያላቸው ተፈጥሮኣዊ ሃይቆች በተለያዩ ቦታዎች እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ ለአብነት በሴኔጋል የሚገኘው የሬብታ ሃይቅ፣ የቦሊቪያው ላጉና ኮሎራዳ ሃይቅ እና የአዎስታራሊያው ሂሊር ሃይቅ በተፈጥሮ ሮዝ ቀለም ያላቸው ታዋቂ የውሃ አካላት ሲሆኑ፤ በውስጣቸው ያለው ከፍተኛ የጨዋማነት ይዘት ይህን ቀለም እንዲይዙ እንደሚያደርጋቸውም ሳይንቲስቶች ይናገራሉ፡፡
ምንጭ፡ outsider
ተጨማሪ https://outsider.com/.../photo-argentina-lake-bright.../
አትሌቱ ሮቦት
አትሌቱ ሮቦት
=======
በአሜሪካን የተሰራው ካሴ የተሰኘ ባለ ሁለት እግር ሮቦት የ5 ኪ.ሜ ጉዞን 53 ደቂቃ ከ3 ሴኮንድ በሆነ ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ታሪክ ሰርቷል፡፡ 1 ሚሊዮን ዶላር ፈጅቶ በ16 ወራት ውስጥ ተሰርቶ የተጠናቀቀው ሮቦቱ በአንድ ጊዜ ቻርጅ ነው ጉዞውን ለማጠናቀቅ የቻለው፡፡

አዲሱ ሮቦት በአጂሊቲ ሮቦቲክስ ኩባንያ አማካኝነት ኦሪጎን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተሰራ ነው፡፡ ልክ እንደ ሰጎን ጉልበቱ ከወደ ጀርባ የሆነው ካሴ ዲፕ ሪኢንፎርስመንት ለርኒንግ አልጎሪዝም በተሰኘው ቀመር አማካኝነት እራሱን በራሱ መሮጥ አስተምሯል፡፡ ሩጫ በከፍተኛ ፍጥነት ውስጥ ሚዛንን ጠብቆ መቆየትን የሚፈልግ እንደመሆኑ መጠን ካሴም በሩጫ ወቅት ሚዛኑን መጠበቅን ተምሯል፡፡ በተጨማሪም ሮቦቱ ደረጃን መውጣት እና መውረድን ከዚህ ቀደም አከናውኖ ነበር፡፡

ሮቦቱ የ5 ኪ.ሜ ሩጫውን ባከናወነባቸው 53 ደቂቃዎች ውስጥ ሁለት ጊዜ ችግር አጋጥሞት ለ6 ደቂቃዎች ያህል ለመቆም ተገዶ ነበር፡፡ የመጀመሪያው ኮምፒውተሩ ከሚገባው በላይ በመሞቁ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መታጠፊያ ቦታ ላይ ከሚፈለገው በላይ እየፈጠነ እንዲያልፍ ታዞ ስለነበር ነው፡፡

መሰል ባለ ሁለት እግር ሮቦቶች እቃን የማጓጓዝ ስራን ከመስራት ባሻገር ሰዎችን የሚረዳ የአስተውሎት እና ደህንነት ብቃትን እንዲላበሱ ይደረጋል፡፡ ከአጂሊቲ ሮቦቲክስ መስራቾች አንዱ እንደሆነው ጆናታን ኸርስት አባባል ከሆነም ሁላችን የሰው ልጆችም በእለት ተእለት ህይወታችን ከሮቦቶች ጋር የምንገናኝና ህይወታችንን በሚያሻሽል መልኩም በጋራ የምንሰራበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም፡፡
ምንጭ፤ Tech Xplore
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-07-bipedal-robot-history-5k.html
አዲስ አበባን የሸፈናት ጉም ምንድነው?
አዲስ አበባን የሸፈናት ጉም ምንድነው?
=============
ዛሬ በጠዋቱ መዲናችን አዲስ አበባ ባልተለመደ መልኩ የተለያዩ ክፍሎቿ በጉም ተሸፍነው በቅርብ ርቀት ያሉ ህንፃዎችን ጭምር ማየት እንዲሳነን ሆነናል፡፡ ታድያ እኛም ይህን ክስተት አስታከን ጥቂት ስለ ጉም ልናጫውታችሁ ወደድን፤ አብራችሁን ሁኑ፡፡

ጉም እንደ ማንኛውም ደመና ሆኖ መሬትን የሚነካ መሆኑ ግን ለየት የሚያደርገው ነው፡፡ ይህ ጉም አንዳንዴ ስስ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወፍራም ሆኖ ሊያጋጥመን ይችላል፡፡ ታድያ ጉሙ ወፈር ብሎ ሲገኝ ነው አሻግሮ ማየትን ባስ ሲልም በቅርብ ርቀት መተያየት እስኪያስቸግር ድረስ እይታን በነጭ መጋረጃ የሚጋርደው፡፡ በዚህም ትላልቅ ህንፃዎች፣ ባለ ግርማ ሞገስ ተራሮች እና ሌሎችም ግዙፋን አካላት በቦታው የሌሉ እስኪመስል ድረስ ሙሉ በሙሉ ሊጋረዱ ይችላሉ፡፡

የጉም አፈጣጠር ተኖ ጋዝ የሆነ ውሃ ወደ ፈሳሽነት በሚለወጥበት ጊዜ (Condensation) ሞለኪውሎቹ ተጣምረው እጅግ ጥቃቅን የሆኑና በዚህም ሳብያ በአየር ላይ የሚንሳፈፉ ውሃዎችን ሲፈጥሩ ነው፡፡ ጉሙን የምናየውም በነዚህ ጥቃቅን ፈሳሽ ውሃዎች ምክንያት ነው፤ አለበለዚያ የተነነው ውሃ ጋዝ በመሆኑ ላይታየን ይችል ነበር፡፡

ይህ በእዲህ እንዳለ ግን አንድ ጉም ተፈጥሮ ዙርያችንን ለመክበብ የከባቢያችን አየር እጅጉን እርጥበት አዘል መሆንና በፍተኛ መጠን በተነነ ውሃ የተሞላ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም እንደ አቧራ አልያም ሌላ አየሩን የሚበክሉ ጥቃቅን ቁሶችም በአየሩ ውስጥ መገኘት አለባቸው፡፡ በዚህም የተነነው ውሃ በእነዚህ ጥቃቅን ቁሶች ላይ ሆኖ ወደ ፈሳሽነት ይቀየራል፡፡ በጨዋማ የውሃ አካላት አካባቢ ደግሞ የተነነው ውሃ በጨው ብናኞች ላይ ሆኖ ሲቀየር የባህር ጉም (Sea Fog) ተብሎ የሚጠራውን ጉም ይፈጥራል፡፡ ታድያ በአየር ላይ ባለው እርጥበት የሚወሰን ቢሆንም ጉሞች በድንገት ሊከሰቱና በዚያው ፍጥነት ሊሰወሩም ይችላሉ፡፡

በምድራችን የተለያዩ አይነት ጉሞች ሲከሰቱ እናያለን፡፡ እነዚህም እንደሚከተለው ቀርበዋል፤

የራዲዬሽን ጉም፤ በምሽት የሚፈጠር ሲሆን መሬት በቀን ውሎዋ ያጠራቀመችውን ሙቀት ወደ አየሩ ስትለቅ የሚከሰት ነው፡፡ ሙቀቱ ከምድር ወደ አየር በሚሸጋገርበት ጊዜ የውሃ ጠብታዎች መፈጠራቸው ለዚህ ምክንያት ይሆናል፡፡

አድቬኬሽን ጉም፤ ይህ ዓይነት ጉም ደግሞ ሞቃታማና እርጥበት አዘል አየር በቀዝቃዛ አካል ላይ ሲያልፍ የሚከሰት ነው፡፡ እርጥበታማ እና ሞቃታማ አየሩ ከቀዝቃዛው የመሬቱ አየር ጋር ሲነካካ የተነነው ውሃ መልኩን ቀይሮ ፈሳሽ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ይህ ሂደትም በሳይንሳዊ አጠራሩ አድቬክሽን ተብሎ ሲጠራ ብዙውን ጊዜ የትሮፒካል አየር ከቀዝቃዛ የውቅያኖስ ውሃ ጋር ሲነካካ የሚፈጠር ነው፡፡

የሸለቆ ጉም፤ ብዙውን ጊዜ በክረምት ወራቶች ተራራና ሸለቆዎች ውስጥ የሚፈጠር ነው፡፡ አፈጣጠሩም ተራሮች አልያም ሸለቆች ውስጥ የተጠቀጠቀውን አየር እንዳያልፍ አግደው ሲያስቀሩት የሚከሰት ነው፡፡ አንዳንዴ ሁኔታው አደገኛ ሊሆንም ይችላል፡፡ ለምሳሌ ከ90 ዓመታት በፊት በቤልጅየሙ የሚዩስ ሸለቆ ውስጥ የተነነ ውሃ በበካይ የአየር ቁሶች ላይ ሆኖ በመቀየሩ ሳብያ ከ60 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተው ነበር፡፡

የቅዝቃዜ ጉም፤ በተለምዶው ደመና በሸፈናቸው ተራሮች ላይ የሚከተው ይህ ዓይነት ጉም ፈሳሽ የደመና ጠብታዎች በአንድ ቁስ ላይ ቀዝቅዘው ሲቀሩ የሚፈጠር ነው፡፡ ይህ አይነት ቀዝቃዛ ጉም ከአካባቢው ተነስቶ ከሄደ በኋላ ምድሩም ሆነ ዛፎች እና እንደ ሸረሪት ድር ያሉ አካላት ጭምር ስስ የበረዶ ሽፋን ተነስንሶባቸው ልናገኝ እንችላለን፡፡ መሰል ጉሞች ቀዝቃዛና እርጥበታማ አየር ፀባይ ባላቸው እንደ ስካንዲኔቪያ እና አንታርክቲካ ባሉ አካባቢዎች ላይ በብዛት መመልከቱ የተለመደ ነው፡፡

ስለ ጉም ካወራን አይቀር ከጉም ላይ ውሃን ስለመሰብሰብም ጥቂት እንበልዎ፡፡ በተለያዩ ማህበረሰቦች ጉም ሲከሰት ትላልቅ የውሃ ማስቀመጫዎችን ከዛፍ ስር በማስቀመጥ በዛፉ ላይ የሚወርደውን ውሃ በመሰብሰብ ጥቂት ውሃን የማግኘት ባህል ነበር፡፡ አሁን ላይ ታድያ የዘመናችን ባለሙያዎች ውሃን ከጉም ላይ የመሰበሰብ ስልትን በዘመናዊ መንገድ ተግባራዊ አያደረጉ ይገኛል፡፡ ታድያ አንዳንድ አካባቢዎችም ዋነኛ የውሃ አቅርቦታቸውን ከጉሞች ላይ በመሰብሰብ እስከማግኘት ደርሰዋል፡፡

ምንጭ፤ National Geographic
ለተጨማሪ፤ https://www.nationalgeographic.org/encyclopedia/fog/