የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ያሰገነባው የህፃናት ሳይንስ ማዕከል ተመረቀ
===============
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ከጎተ ኢንስቲትዩት እና ጀርመን ከሚገኘው ፓኖሜንታ ሳይንስ ማዕከል ጋር በመተባበር በቅጥር ግቢው ያስገነባው የልጆች ሳይንስ ማዕከልን በትናንትናው ዕለት አስመርቋል፡፡
በሦስት ክፍሎች ተደራጅቶ የተገነባውና በሀገራችን በዓይነቱ የመጀመሪያ መሆኑ የተነገረለት ማዕከሉ ታዳጊዎች በፅንሰ ሀሰብ ደረጃ በክፍል ውስጥ የተማሯቸውን ትምህርቶች በተግባር የሚያሳዩ በርካት የፊዚክስ፣ ሒሳብ እና መሰል የሳይንስ ማስተማርያ መሳርያዎችን ይዟል፡፡ ህፃናቱም በተለይ ምላሽ ሳይነገራቸው ከመሳርያዎቹ በስተጀርባ ያለው ሳይንስ እንደሚቃኙበት ተገልጿል፡፡
የአካዳሚው ሳይንስ ማዕከል ንዑስ ክፍል በመሆን የተከፈተው የህፃናት ሳይንስ ማዕከሉ ህፃናት በሳይንስ፣ ቴከኖሎጂ እና ሒሳብ የትምህርት ዘርፎች ጠንካራ ይሆኑ ዘንድ በጨዋታ መልኩ የትምህርት ዘርፎቹን ዕውቀት የሚያስጨብጥ መሆኑን የአካዳሚው ቦርድ ፕሬዘዳንት ፕ/ር ፅጌ ገ/ማርያም ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም አቅም በፈቀደ መልኩ ለማስፋፋት እና በየትምህርት ቤቱ መሰል ተቋማትን ለመገንባት እንደሚሰራም ፕ/ር ፅጌ ገልፀዋል፡፡
የዕለቱ ክብርት እንግዳ ሆነው ማዕከሉን መርቀው የከፈቱት የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚንስትር ደኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞት በበኩላቸው ህፃናት ለሳይንስ ያላቸው ፍላጎት የሚወሰነው በልጅነት ዕድሜያቸው እንደመሆኑ በዙርያቸው ያሉ ነገሮችን ለማወቅ የሚያደርጉትን ጥረት መደገፍና መሰል የሳይንስ ማዕከላትን ማደራጀት የወደፊቶቹን ተመራማሪዎች በመፍጠር ረገድ የማይተካ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡ መንግስት ለሳይንስ በሰጠው ትኩረት ሳብያ በሀገር አቀፍ ደረጃ በርካታ ውጤታማ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው ያሉት ክብርት ሚኒስትር ደኤታዋ በኢትዮጵያ በዓይነቱ ልዩ የሆነው ይህ ማዕከል በመከፈቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ከአስር ዓመት በፊት 49 የሀገራችን ምሁራንን በማሰባሰብ የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነና ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም ነው፡፡ አካዳሚው በመንግስት እና ሌሎች አጋሮች ድጋፍ ሲንቀሳቀስ የተፈጥሮ፣ ማህበራዊ እና ጤና ሳይንስን ጨምሮ በስድስት የተለያዩ ዘርፎች ላይ ሀገራዊ ዕውቀትን የማስፋፋት እና በማስረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ የማቅረብ ስራን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ተቋሙ ኢዚሁ አዲስ አበባ ጉለሌ አካባቢ ቀድሞ የብላቴ ጌታ ህሩይ ወልደ ሥላሴ መኖርያ በነበረው ግቢ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በስራቸው የላቁ 180 ምሁራንንም በአባልነት አቅፏል፡፡

መላው ዓለም ላይ ሲሰልል የቆየው የእስራኤል ኩባንያ
===========
አንድ እስራኤላዊ የግል ኩባንያ የስልክ ሶፍትዌርን ተጠቅሞ በመላው ዓለም የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶችን ሲሰልል እንደቆየ ተዘገበ፡፡ የእስራኤሉ ኤንኤስኦ ግሩፕ ፔጋሴስ በተሰኘው ሶፍትዌሩ አማካኝነት ስለላውን ሲያከናውን መቆየቱን እንደ ዋሽንግተን ፖስት እና ዘ ጋርዲያን ያሉ አለም ዓቀፍ ሚዲያዎች የተሳተፉበት አፈትላኪ መረጃ ምርመራ አሳይቷል፡፡
አፈትሎኮ የወጣው መረጃ እንዳመላከተው ከአውሮፓውያኑ 2016 አንስቶ 50 ሺህ ያህል ስልክ ቁጥሮች በኤንኤስኦ ግሩፕ ደንበኞች ተፈላጊ ሆነው መለየታቸውን ነው፡፡ ሆኖም ከ50 ሺው ውስጥ ሁሉም ሀክ አልተደረጉም፤ ጥቃት የደረሰባቸው ዝርዝር ግን በቅርብ ቀናት ውስጥ ይፋ እንደሚሆን ተዘግቧል፡፡ ታድያ በድርጅቱ ስለላ ሲደረግባቸው ከነበሩት ጋዜጠኞች መካከል በታላላቆቹ አለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት፤ በአዣንስ ፍራንስ ፕረስ፣ ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል፣ ሲኤንኤን፣ ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ አል ዤዚራ፣ ፍራንስ 24፣ ራዲዮ ፍሪ ዩሮፕ፣ ሚዲያፓርት፣ ኢል ፓሪስ፣ ዘ አሶሺዬትድ ፕረስ፣ ሌ ሞንዴ፣ ብሉምበርግ፣ ዘ ኢኮኖሚስት፣ ሮይተርስ እና የአሜሪካን ድምፅ ውስጥ የሚሰሩት ይገኙበታል፡፡
በዝርዝር ውስጥ ስልካቸው ከተገኙት መከላከልም በሳውዲ መንግስት ለተገደለው የሳውዲ ተወላጅ ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ቅርብ የሆኑ ሁለት ሴቶች እንዲሁም ኋላ ላይ ግድያ የተፈፀመበት ሜክሲአዊ የፍሪላንስ ጋዜጠኛ ይገኝበታል፤ ምንም እንኳን ስልኩ ሀክ ተደርጎ ይሁን አይሁን ባይታወቅም፡፡ እንደ ዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ከሆነ ደግሞ ዝርዝሩ ውስጥ ከተገኙት መካከል የሀገር መሪዎች፣ የአረብ ንጉሳዊ ቤተሰብ አባላት፣ ዲፕሎማቶች፣ ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች እና የንግድ ተቋማት ኃላፊዎች እንደሚገኙበት ተጠቅሷል፡፡
ዝርዝሩ የትኞቹ የድርጅቱ ደንበኞች የስልክ ቁጥሮቹን እንዳስገቡ ባይገልፅም በዋናነት ግን ከ10 ሀገራት ማለትም አዘርባጃን፣ ባህሬን፣ ሀንጋሪ፣ ህንድ፣ ካዛኪስታን፣ ሜክሲኮ፣ ሞሮኮ፣ ሩዋንዳ፣ ሳውዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች መሆናቸውን ተዘግቧል፡፡ ኤንኤስኦ ሶፍትዌሩ በወንጀለኞች እና አሸባሪዎች ላይ እንዲውል መሰራቱን ቢገልፅም የዘ ጋርዲያን ዘገባ እንደሚያሳየው ፔጋሴስ መጠነ ሰፊና ያልተቋረጠ ስለላን እንደሚያከናውን ነው፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ፎርቢድን ስቶሪስ ያፈተለከውን መረጃ በማግኘት ቀዳሚዎቹ ነበሩ፤ ኋላ ላይም መረጃውን ለሚዲያዎች አጋርተውታል፡፡ ሆኖም ድርጅቱ የቀረቡበትን ክሶች የተጋነኑና መሰረት ቢስ ናቸው ሲል ተችቷል፡፡
ከዚህ ቀደም ሶፍትዌርን በመጠቀም የግዙፉ ሚዲያ ተቋም አል ዤዚራ ሪፖርተሮችን እና ሞሮኮአዊያን ጋዜጠኞች ስልክ ስለመጠለፉ በካናዳው የዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቶሮንቶ የሚገኘው ሲቲዝን ላብ የተሰኘ የጥናት ማዕከል እንዲሁም አምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳውቀው ነበር፡፡
ምንጭ፤ Tech Xplore
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-07-private-israeli-malware-spy-journalists.html

Tech Xplore
50,000 phone numbers worldwide on list linked to Israeli spyware: reports
An Israeli firm accused of supplying spyware to governments has been linked to a list of tens of thousands of smartphone numbers, including those of activists, journalists, business executives and politicians ...
የአለማችን የመጀመሪያው የ3ዲ ህትመት ድልድይ
***************************************************
በአለማችን የመጀመሪያ የሆነው በ3ዲ ህትመት የተሰራ የብረት ድልድይ በአምስተርዳም ጥቅም ላይ ዋለ፡፡ ከሁለት አመታት በፊት በMX3D ካምፓኒ የተሰራው የብረት ድልድይ ጥቅም ላይ ሳይውል ቢቆይም ከጥንታዊያን የአምስተርዳም የውሃ መተላለፊያዎች በአንዱ ላይ ተገጥሞ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
በድልድይ ምህንድስና ረገድ ለወደፊት ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ይህ የ3ዲ ህትመት የብረት ድልድይ የተለያዩ ሽልማቶችን ለፈጠራ ባለቤቶቹ አስገኝቶላቸዋል፡፡ የድልድዩ ፕሮጀክት በ2015 የተጀመረ ሲሆን ከፍተኛ መጠን ያላቸውን መገልገያዎች በ3ዲ ህትመት የመስራት እና በስነ ህንጻ ዘርፍ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን የማቅረብ አላማ አለው፡፡
የ MX3D አዲስ ፈጠራ በኔዘርላንዷ ንግስት ማክሲማ አማካኝነት ባሳለፍነው ሳምንት በይፋ ተመርቋል፡፡ ድልድዩ ከአርት ሴንሰር በይነ መረብ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ የተለያ መረጃዎችን መሰብሰብ የሚያስችል ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡ ከዚህ የሚገኘውም መረጃ በህንጻ ምህንድስና ዘርፍ ውስጥ የአይ ኦ ቲን ግልጋሎት ለማጥናት ጥቅም ላይ ይውላል ሲል የመረጃ ምንጫችን አስነብቧል፡፡
ምንጭ Design boom
ተጨማሪ ንባብ https://www.designboom.com/design/world-first-3d-printed-steel-bridge-amsterdam-canals-mx3d-07-16-2021/

ሩሲያ በማርስ ላይ የኒውክለር ኃይል ማመንጫ ልትገነባ ነው
=================
የሩሲያው የጠፈር ምርምር ኤጀንሲ ሮስኮሞስ እህት ተቋም የሆነው የጦር መሳርያዎች ዲዛይን ቢሮ ሀገሪቱ ወደፊት ማርስ ላይ ለምትገነባው ጣብያ የኃይል ምንጭ እንዲሆን በማሰብ የኒውክለር ኃይል ማመንጫ ጣብያ ለመገንባት ማቀዱን የሀገሪቱ የዜና ተቋም ስፑትኒክ ዘገበ፡፡ ተቋሙ ለኒውክለር ኃይል ማመንጫ ጣብያው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ዜነስ በተባለቸው የጠፈር ላይ ማጓጓዣ (Space Tug) አማካኝነት አጓጉዞ ለማሟላት አቅዷል፡፡
ግዙፎቹን የጣብያው ግንባታ ቁሳቁሶች ከመሬት አንስቶ ወደ ማርስ የምታደርሰው ዜነስ በኒውክለር ኤሌክትሪክ ግፊት አማካኝነት የምትንቀሳቀስ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡ ግብዓቶቹ በዜነስ አማካኝነት ወደ ማርስ አየር ካቀኑ በኋላም በፓራሹት ወደ ምድሯ የሚለቀቁ ይሆናል፡፡ ታድያ የኒውክለር ኃይል ማመንጫ ጣብያ ቁሳቁሶችን ከማጓጓዝ ባሻገር ግን ዜነስ ለሌላ ስራም ታጭታለች፤ ከወራት በፊት የሮስኮሞስ ኃላፊው ዲሚትሪ ራጎዚን ምናልባትም የሌላው አለም ፍጡራን እዚያ ይገኙ እንደሆን ለመመርመር እንደ ጁፒተር ያሉ ሌሎች ፕላኔቶች ጋርም ልትሄድ እንደምትችል ጠቁመው ነበር፡፡
ሩሲያ የአሜሪካኑ የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ ከሚጠቀመው ከአንድ አስረኛም ያነሰ በጀት ቢኖራትም የሩሲያ ጠፈር ምርምር ተቋም ግን በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ ገቢር ይሆናሉ ያላቸውን ታላላቅ እቅዶች አስቀምጧል፡፡ ከነዚህ ታላላቅ እቅዶቹ መካከል ሀገሪቱ የራሷ የጠፈር ምርምር ጣብያ እንዲኖራት ማድረግ፣ ሰው የጫኑና ሰው አልባ ተጓዦችን ወደ ጨረቃ መላክ፣ እንዲሁም ከቻይና ጋር በመተባበር ጨረቃ ላይ ሰፈር መገንባት ይገኙበታል፡፡ ታድያ የኒውክለር ኃይል ማመንጫን ወደ ማርስ የመላኩና ሰዎችንም በዚያ የማስፈሩ ጉዳይ ብዙ ስራ የሚቀረው ውጥን ቢሆንም በአግባቡ ከተመራ ግን ሊሳካ እንደሚችል ተነግሮለታል፡፡
ምንጭ፤ Futurism
ለተጨማሪ፤ https://futurism.com/the-byte/russia-proposes-nuclear-power-plant-mars

THE_BYTE.
Russia Proposes Nuclear Power Plant on Mars
A subsidiary of Russia’s Roscosmos space agency is proposing to send a nuclear power station to Mars to power a future Russian base.
በሰዓት 600 ኪ.ሜ የሚከንፈው አዲሱ የቻይና ባቡር
===========
ቻይና በሰዓት 600 ኪ.ሜ መጓዝ የሚችል ተንሳፋፊ የማግኔት ባቡር (Maglev Train) ትናንት ይፋ አደረገች፡፡ በቻይናውያን ባለሙያዎች ቺንዳኦ ከተማ ውስጥ የተፈበረከው ባቡሩ ፍጥነቱ በምድር ላይ አቻ የለውም ተብሎለታል፡፡
የማግኔት ባቡሮች ከባቡር ሀዲዱ ጋር ምንም አይነት አካላዊ ግንኙነት ሳይኖራቸው የኤሌክትሮ ማግኔቲክ ኃይልን በመጠቀም ተንሳፈው የሚጓዙ ባቡሮች ናቸው፡፡ ቻይናም ይህን ቴክኖሎጂ በተወሰነ መልኩ ይሁን እንጂ ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ስትጠቀምበት ኖራለች፡፡ ለምሳሌ ሻንጋይ ውስጥ ኤርፖርቱን ከከተማው የሚያገናኝና በሰዓት 431 ኪ.ሜ መክነፍ የሚችል አነስተኛ የማግኔት ባቡር መስመር ከአውሮፓውያኑ 2004 አንስቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው፡፡ እንዲህ እንዲህ ካሉ አነስተኛ መስመሮች ባለፈ ከተማን ከከተማ አልያም አንዱን ግዛት ከሌላኛው የሚያገናኝ ተንሳፋፊ የማግኔት ባቡር ባትዘረጋም እንደ ሻንጋይ እና ቼንዱ ያሉት ከተሞቿ ግን በዘርፉ ላይ ምርምር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
በሰዓት 600 ኪ.ሜ የሚምዘገዘገው አዲሱ ባቡርም ታድያ ሁለቱ ግዙፍ የቻይና ከተሞች በሆኑት ቤጂንግ እና ሻንጋይ መካከል ያለውን ከአንድ ሺህ ኪ.ሜ የሚበልጥ ርቀር በ2 ሰዓት ተኩል ጊዜ ውስጥ ተጉዞ መጨረስ ይችላል፡፡ ለንፅፅር ያህል አውሮፕላንን ተጠቅሞ ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላኛው ለመጓዝ 2 ሰዓት ፈጣን ባቡርን ተጠቅሞ ለመጓዝ ደግሞ 5 ሰዓት ተኩል ይፈጃል፡፡
መሰል የማግኔት ባቡር መስመሮችን የመገንባት ሩጫ ውስጥ የገባችው ቻይና ብቻ አይደለችም፡፡ እንደ ጃፓን እና ጀርመን ያሉ ሀገራትም የማግኔት ባቡር መስመሮችን የመገንባት ዕቅድ አላቸው፡፡ ሆኖም የዋጋው መናርና ባቡሮቹም አሁን ባለው የባቡር ሀዲድ ላይ መጓዝ የማይችሉ መሆናቸው ለውጥኑ ስኬት መሰናክል ሆኖ ይገኛል፡፡
ቻይና ከ140 ሺህ ኪ.ሜ በላይ ርዝመት ያለው የባቡር መስመርን በመላው ሀገሪቱ ዘርግታ ትገኛለች፡፡ ከዚህም ውስጥ 38 ሺህ ኪሜ የሚሆነው የፍጥነት ባቡር መስመር ነው፡፡
ምንጭ፤ Reuters እና South China Morning Post
ለተጨማሪ፤ https://www.reuters.com/world/china/china-unveils-600-kph-maglev-train-state-media-2021-07-20/ እና https://www.scmp.com/news/china/science/article/3141769/superfast-maglev-train-key-chinas-smart-transport-network-rolls

መልካም ዜና፤ ለዩትዩበሮች
=========
ዪትዩብ “ሱፐር ታንክስ” የተሰኘ የአንድ ቻናል አድናቂዎች ለቻናሉ ስጦታና ድጋፍ የሚያበረክቱበት አዲስ ገፅታን በትናንትናው ዕለት አስተዋውቋል፡፡ ከዚህ ቀደም ተመልካቾች በሱፐር ቻት፣ ሱፐር ስቲከር እና ቻናል ሰብስክሪብሽን አማካኝነት ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ አመቻችቶ የነበረው ዩትዩብ በአዲሱ መንገድ ደግሞ ተመልካቾች በቀጥታ ስርጭት እየተላለፉ ላልሆኑ ቪዲዮዎች ድጋፋቸውን እንዲሰጡ የሚያደርግ ሆኗል፡፡ በዚህም ተመልካቾች ከ2 አንስቶ እስከ 50 የአሜሪካን ዶላር ድረስ ለሚያደንቋቸው ቻናሎች መስጠት ይችላሉ፡፡
እስከዛሬ ተመልካቾች ለቪዲዮዎቹ ባለቤቶች ድጋፍ የሚያደርጉበትን መንገድ በማመቻቸት ረገድ ዩትዩብ ወደኋላ ይቀር ነበር፡፡ ይህ ግን በ “ሱፐር ታንክስ” የተለወጠ መስሏል፤ የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ቀጥታ ስርጭት በሚኖርበት ጊዜ ለቪዲዮው ባለቤት ድጋፍ ማድረጊያ መንገድ ቢኖራቸውም በዚህ መልኩ አድናቂዎች ድጋፍ የሚያደርጉበት መንገድ ግን የላቸውም፡፡ በተጨማሪም ዩትዩብ በተመልካቾች አማካኝነት ለአድናቂዎች ከሚበረከቱ ድጋፎች ውስጥ 30 በመቶ ሲቆርጥ እንደ ትዊች ያሉ ተፎካካሪዎች ግን 50 በመቶ የግላቸው ያደርጋሉ፡፡
ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት ከ10 ሚሊዮን በላይ የዩትዩብ ተመልካቾች በሱፐር ቻት፣ ሱፐር ስቲከር አልያም ቻናል ሰብስክሪብሽን ላይ ተሳትፈው ነበር፡፡ አብዛኛው ገቢያቸውን ከእንደዚህ አይነት ድጋፎች የሚያገኙ ቻናሎች ብዛትም እ.አ.አ 2019 ላይ ከነበረበት በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ በሦስት እጥፍ አድጓል፡፡
ከትናንት ጀምሮ “ሱፐር ታንክስ” የዩትዩብ ፓርትነር ፕሮግራም አባል በሆኑ 68 ሀገራት ውስጥ በሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ቻናሎች ላይ መምጣት የጀመረ ሲሆን በቀጣይም ፕሮግራሙ ውስጥ በተካተቱ ሌሎች ሀገራት የሚስፋፋ ይሆናል፡፡
ምንጭ፤ Tech Crunch
ለተጨማሪ፤ https://techcrunch.com/2021/07/20/youtubes-newest-monetization-tool-lets-viewers-tip-creators-for-their-uploads/?guccounter=1&guce_referrer=aHR0cHM6Ly93d3cuZ29vZ2xlLmNvbS8&guce_referrer_sig=AQAAAJhGZwEaSQhdhud-rrjzD1u5BM7hlfB6-unN82NE8z8TovAG2G1c_Q2SJnBrpl_-axWpl0kfoQDHG3wmVNwdGfAR5DLwW4eaTi-x6eTtBDhFyQDbl0Y_pfWItoxOz6JVfxTHLgcenhsyahIP--nwMI-iJuPihOlzfh_kEYkgaaoH

TechCrunch
YouTube’s newest monetization tool lets viewers tip creators for their uploads
YouTube announced its latest feature, Super Thanks, on Tuesday. This is YouTube’s fourth Paid Digital Good, which is what the platform calls any product that lets fans directly pay creators. So far, these tools include Super Chat, Super Stickers and channel…
በኮቪድ የተፈተነውን የቶኪዮ ኦሎምፒክ በቴክኖሎጂ…
*****************************************************
የ2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ ይካሄድ ከነበረበት ወቅት አንድ አመት ያክል ዘግይቶ ያለ ተመልካች ሊከናወን ቀናቶች ቀርተውታል፡፡ የቶኪዮ ኦሎምፒክ በተለይ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ብሎም ለአህጉራችን አፍሪካ ትልቅ ትዝታ ያለው ነው፡፡ ለዚህም ጀግናው አትሌት ሻምበል አበበ ብቄላ ትልቅ ምክንያት ነው፡፡
የኦሎምፒክ ውድድሩ ያለ ተመልካችና በጥቂት የመገናኛ ብዙሃን አማራጮች ብቻ ሊከናወን ቀን ተቆርጦለት ተወዳዳሪዎች ከተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ወደ ውድድሩ ስፍራ አምርተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ስፖርታዊ ውድድሮች ያለ ተመልካች ያን ያክል ድምቀት አይኖራቸውም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተመልካቾች በቤታቸው ሆነው መመልከት ቢችሉም ትክክለኛውን ስሜት ማግኘትና ማጣጣም አይችሉም፡፡ ይህንን ያስተዋሉ የቴክኖሎጂ ሰዎች የውድድሩ ተመልካቾች ከመደበኛ ቴሌቪዥኖች በተሸለ የውድድሩን ድባብና ስሜት ሊያጋቡ የሚችሉ ከፍኛ ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙ ቴሌቪዥኖችን ሰርተው አቅርበዋል፡፡
ከ2008 ጀምሮ የኦሎምፒክ ብሮድካስቲንግ አገልግሎት ውድድሮችን በምስልና ድምጽ በመቅዳት የማሰራጨት ሀላፊነትን ወስዶ እየሰራ ነው፡፡ ነገር ግን በኮቪድ 19 ምምንያት እስካሁን ተጠቅሞት የማያውቀውን የቴክኖሎጂ አማራጭ ለመጠቀም ተገድዷል፡፡
የብሮድካስት ቡድኑ በ2020 የኦሎምፒክ ውድድር 9500 ሰዓታት የሚደርስ የውድድር ቀረጻ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን ይህም ከ2016ቱ በ30 በመቶ ከፍ ያለ ነው፡፡ ይህ ቀረጻም ያማሰራጨት መብት ለተሰጣቸው በአለም ላሉ የቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያዎች ይሰጣል፡፡ የኦሎምፒክ ብሮድካስቲንግ አገልግሎት ስራውን በ1936 በሶስት ካሜራዎች በመታገዝ በቅርብ ርቀት ለሚገኙ ተመልካቾች ብቻ በማሰራጨት ጀምሯል፡፡
የቴሌቪዥን ስርጭት ተቋማት አሁን ላይ ለደንበኞቻቸው ወደ እውነታ የተቃረበ፣ የተሻሻለ የምስልና ድምጽ አቅርቦት (augmented) ስርጭትን ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለማስተላለፍ እንዳቀዱ ተናግረዋል፡፡ በኦሎምፒክ ብሮድካስት አገልግሎትም በ3ዲ የታገዘ የአትሌቶችን እንቅስቃሴ የሚቀርጽ ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ታስቧል፡፡ ይህም በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ በመሆኑ ተመልካቾች ከሁሉም አንግል ምስሎችን እንንመለከቱ ያስችላቸዋል፡፡
የብሮድካስት አገልግሎቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የ4ኬ ምስልን ለመቅዳት ያሰበ ሲሆን ከጃፓን ሆነው ውድድሩን የሚከታተሉ ሰዎች 8ኬ የምስልና ድምጽ ጥራት ባላቸው ቴሌቪዥኖች ውድድሮችን መከታተል የሚችሉበት ሁነታ ተመቻችቷል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-07-high-tech-tv-fan-free-tokyo-olympics.html

High-tech TV tricks for fan-free Tokyo Olympics
There'll be no fans in the stands, and less media on the ground, so when it comes to covering the Tokyo Olympics, broadcasters are relying on technology to give viewers a more vivid experience.
ድሮኖች ፖሊስ ሊሆኑ ነው
=========
የዱባይ ፖሊስ ችግር በተፈጠረበት ማንኛውም የከተማው ክፍል በአንድ ደቂቃ ውስጥ መድረስ የሚያስችለውን የድሮን አገልግሎት ይፋ አደረገ፡፡ ከእስራኤሉ የኤሮቦቲክ ኩባንያ ተገዝተው የቀረቡት ባለ አራት ሽክርክር ድሮኖቹ መጪው ጥቅምት ላይ በሚጀመረውና ከኦሎምፒክ እና ዓለም ዋንጫ ቀጥሎ ትልቁ ሁነት ተደርጎ በሚወሰደው የ2020 ኤክስፖ ላይ አገልግሎታቸውን መስጠት የሚጀምሩ ይሆናል፡፡ ከማስቀመጫ ጣብያቸው ወጥተው የሚንቀሳቀሱበት ፍጥነትም እንደ ዱባዩ መሪ ሸኢክ ቢን ሞሐመድ ቢን ረሺድ አል ማክቱም ከሆነ ቀድሞ ፖሊስ በከተማዋ አንድ ችግር ሲከሰት ቦታው ላይ ለመድረስ ይፈጅበት የኘበረውን የ4.4 ደቂቃ ጊዜን ወደ 1 ደቂቃ ያወረደ ነው፡፡
እንዳንዱ የድሮኖች ጣብያ ተንሸራታች ጣርያ ያለው በመሆኑ ድሮኖቹ በቀላሉ እንዲወጡና እንዲገቡ ያስችላቸዋል፡፡ በተጨማሪም ድሮኖቹ ቀድሞ በታቀደላቸው መሰረት የቁጥጥር ስራ ለመስራት ከተማው ውስጥ ይዞራሉ አልያም በአንድ ተወስኖ በተሰጣቸው አካባቢ ላይ ይሰማራሉ፡፡ በዚህም በማዕከላዊ ፅ/ቤት ያሉ ተቆጣጣሪ ፖሊሶች ችግር በተፈጠረበት ቦታ ያለውን ሁኔታ እንዲመለከቱ ወይም ተጠርጣሪ የሆነ ሰው እና መኪናን በመከታተል ለተለያዩ የፖሊስ ክፍሎች መረጃ የሚያስተላፉ ይሆናል፡፡
1.8 ሜትር ስፋት ያላቸው ድሮኖቹ ገበያ ላይ ከሚውሉ ሌሎች ድሮኖች አንፃር ተለቅ ያሉ ናቸው፡፡ ከበረራ መልስም ቻርጅ ማድረግ ሳያስፈልጋቸው ባትሪያቸውን በፍጥነት በመለወጥ ወድያው ለዳግም በረራ ዝግጁ የሚያደርጓቸው ሮቦቶች በየጣብያው ተገጥመውላቸዋል፡፡
መሰል በተዘጋጀላቸው ቦታ የሚቀመጡ ራስ ገዝ ድሮኖች (drones-in-a-box) በተለያዩ ሀገራት ለተለያዩ ስራዎች ሲውሉ መመልከት አዲስ ነገር አይደለም፤ ለምሳሌ፡- ሲንጋፖር ውስጥ ኮቪድ-19ን ተከትሎ የተላለፉ ደንቦች አፈፃፀምን ለመመልከትና ሰዎች ይህን በመጣስ ሰብሰብ ብለው ተገኝተው እንደሆን ለማረጋገጥ ሁለት ድሮኖች ስራ ላይ ውለው ነበር፡፡ ሆኖም እንዲህ ባለ ከተማ አቀፍ ፖሊሳዊ ስራ ላይ ሲሰማሩ ግን የመጀመሪያው ነው፡፡
ምንጭ፤ New Scientist
ለተጨማሪ፤ https://www.newscientist.com/article/2284387-dubai-police-will-use-citywide-network-of-drones-to-respond-to-crime/?utm_medium=social&utm_campaign=echobox&utm_source=Twitter#Echobox=1626688958

New Scientist
Dubai police will use citywide network of drones to respond to crime
Dubai police will be able to respond to an incident anywhere in the United Arab Emirates city within a minute, thanks to a network of pre-positioned drone bases
በኤሌክትሪክ የሚሰራ የውሃ ላይ መጓጓዣ ከወደ ሞስኮ
*****************************************
*******
በመኪኖች ብዛት ምክንያት በሚፈጠር የትራንስፖርት መጨናነቅ የተማረረችው ሞስኮ በኤሌክትሪክ የሚሰራ የኤሌክትሪክ ጀልባን ለማቅረብ ተዘጋጅታለች፡፡ ከወደ ከተማዋ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ከከባቢ አየር ጋር ካለው መጣጣም በተጨማሪ የመንገድ ላይ መጨናነቆችን ለመቅረፍ ወሳኝ ነው፡፡ ሞስኮ ከዚህም በተጨማሪ የውሃ ላይ መጓጓዣዎችን መጠቀም በመኪኖች ላይ ያለውን ጥገኝነት በእጅጉ ይቀንሰዋል ብላ ታስባለች፡፡
የኤሌክትሪክ ጀልባዎቹ 42 መቀመጫዎች ያሏቸው ሲሆን በአማካኝ 22 ሜትር ርዝመት ያላቸው ናቸው፡፡ በውስጣቸውም ሀይል መሙያ ዩኤስ ቢ፣ ዋይ ፋይ፣ ለስኩተሮችና ለሳይክሎች ማስቀመጫ እንዲሁም የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችሉ ጠረጴዛዎች ያሏቸው ናቸው፡፡
ወደ አገልግሎት የሚቀርቡት ጀልባዎች ትክክለኛ ቁጥራቸው ባይታወቅም የሞስኮ ትራንስፖርት ግን ለጊዜው በቀን 16 ሺህ ሰዎችን ማጓጓዝ የሚችሉ ሁለት ጀልባዎች መዘጋጀታቸውን ይፋ አድጓል፡፡ በሞስኮ የትራንስፖር ዘርፍ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ማክሲም ሊክሱቶቭ በቀጣይ አመት ከየትኛውም የህዝብ ትራንስፖር በአምስት እጥፍ የሚፈጥን የትራንስፖርት አገልግሎት ለመጀመር እንደሚችሉ እና ከግል መኮኖች በእጥፍ የሚፈጥን ተመራጭ የትራንስፖር ዘርፍ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት በሞስኮው ከንቲባ ጎብኝት የተደረገበት አዲሱ የኤሌክትሪክ ጀልባ በተለያዩ ወርሃዊና አመታዊ የክፍያ አማራጮች አገልግሎቱን ለመስጠት ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡ ባለፈው ጥር ወር የወጣው የቶም ቶም ትራፊክ ኢንዴክስ እንደሚያመለክተው ሞስኮ የአለማችን የተጨናነቀች ከተማ ደረጃ ውስጥ መግባቷ ይታወቃል፡፡
ሀገራት ለከተሞቻቸው የመጨናነቅ ችግር የተለያዩ መፍትሔዎችን እያፈላለጉ ሲሆን ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተሸሉ ውጤቶችን የሚያስገኝ መሆኑን ከሞስኮ፣ ኒውዝላንድ፣ አውክላንድ እና ሰቶኮልም ትልቅ ምሳሌዎች ናቸው፡፡
ምንጭ cities-today
ተጨማሪ ንባብ https://cities-today.com/moscow-to-launch-electric-ferry-service-next-year/?fbclid=IwAR1EmK5559Qb_Q2K4coh4hWyLtaXy8nocGTMo24e8hQxc6x8TiVKIZtBzrU

Cities Today
Moscow to launch electric ferry service next year - Cities Today
The 42-seater boats will be equipped with USB charging, Wi-Fi, places for scooters and bicycles, and tables for working commuters.