45 የእግር ኳስ ሜዳ የሚያህለው ግዙፍ ተንሳፋፊ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ
============
ሲንጋፖር በዓለማችን በግዝፈታቸው ቀዳሚውን ስፍራ ከሚይዙት ተንሳፋፊ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች መካከል የሆነውና 45 የእግር ኳስ ሜዳ ስፋት ያለው የፀሐይ ኃይል ማመንጫዋን የይፋ አደረገች፡፡ የሀገሪቱን በካይ ጋዝ ልቀት የመቀነስ እንቅስቃሴ አካል የሆነው ፕሮጀክቱ 122 ሺህ የሶላር ፓኔሎችን በመያዝ የከተማይቱን አምስት የውሃ ማጣርያዎች ኃይል ፍላጎት የሚያሟላ ነው ተብሎለታል፡፡
ሀገርም ከተማም የሆነችው ሲንጋፖር በነፍስ ወከፍ ደረጃ ካየነናት በእሲያ ቀዳሚዋ ካርበን ዳይ ኦክሳይድ ለቃቂ ናት፡፡ ያለባት የመሬት ውስንነት ደግሞ ታዳሽ የኃይል አማራጮች ማስፋፋቱን አዳጋች አድርጎባታል፡፡ ታድያ በባህር ዳርቻ ላይ የምትገኘው ይህች ባለፀጋ ሀገር ምድሯ ላይ ባለውና በከበባት ውሃ ላይ ከተከለቻቸው የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎቿ የምታገኘውን ኃይል በአራት አመታት ውስጥ አራት እጥፍ አሳድጋለው ብላ እየሰራች ትገኛለች፡፡ ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም ከማሌዢያ ጋር የሚለያያት የውሃ አካል ላይ እንዲሁም በተወሰነው የየብስ ክፍሏ ላይ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎችን ተክላለች፡፡ አዲሱ ማመንጫም 60 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ሰባት ሺህ መኪኖች ከሚለቁት ጋር የሚስተካከል በካይ ጋዝን የሚያስቀር ይሆናል፡፡
ከተማይቱ ከብክለት የፀዳ ሀገር ለመሆን ወጥና እየሰራች ሲሆን መንግስቷም እንደ ዛፍ መትከል፣ ወደ ቆሻሻ መጣያ የሚሄዱ ውጋጆችን መቀነስ እንዲሁም የኤሌክትሪክ መኪናን የሚያበረታቱ ቻርጅ ማድረጊያ ጣብያዎችን ማስፋፋት ላይ ያተኮረ አረንጓዴ ልማት እቅድ ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ሲንጋፖር ከሌሎች የበለፀጉ ሀገራት አንፃር የአረንጓዴ ልማት እቅዶቿን በሚጠበቅባት ልክ ማሳካት አልቻለችም በሚል ከትችት አላመለጠችም፡፡
ምንጭ፤ Tech Xplore
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-07-singapore-unveils-world-biggest-solar.html

Tech Xplore
Singapore unveils one of world's biggest floating solar farms
Singapore Wednesday unveiled one of the world's biggest floating solar power farms, covering an area the size of 45 football pitches, as part of the city-state's push to cut greenhouse gas emissions.
የሀዘን ዜና
======
በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የሚዲያና መረጃ ስርጭት ክፍል ውስጥ በጋዜጠኝነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ይበልጣል ሽመልስ (1979-2013 ዓ.ም) በተወለዱ በ34 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ትናንት ሐምሌ 7 2013 ዓ.ም ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ለህልፈት የበቁት አቶ ይበልጣል (1979-2013 ዓ.ም) ነገ ስርዓተ ቀብራቸው ይፈፀማል፡፡
ከ2012 ዓ.ም አንስቶ በኢንስቲትዩታችን በትጋት እና መልካም ስነ ምግባር ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ይበልጣል በየወራቱ በምትወጣው የቴክ ሳይንስ መፅሔት የተለያዩ ቅፆች ላይ በአዘጋጅነት በመሳተፍ በርካታ የሳይንስ ዘገባዎችን አስነብበውናል፡፡
አቶ ይበልጣል ባለ ትዳር እና የአንድ ልጅ አባት ነበሩ፡፡
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በባልደረባችን ድንገተኛ ህልፈት በእጅጉ ማዘናችንን እየገለፅን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን !!!

ከጥቅሙ ጉዳቱ ማመዘን የጀመረው የአማዞን ጫካ
=========
ደኖች ከፍተኛ መጠን ያለው ካርበን ዳይ ኦክሳይድን ከከባቢ አየር ላይ በመምጠጥ እና የአየር ንብረት ለውጥት በመዋጋት ረገድ ትልቅ ሚናን ይጫወታሉ፡፡ ሆኖም የደኖች ሁሉ ንጉስ የሆነው የአማዞን ጫካ ከከባቢ ላይ ከሚመጠው ካርበን ዳይ ኦክሳይድ ይልቅ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀው መብዛቱን አዲስ ጥናት አመላከተ፤ ምስጋና ለሰው ልጅ አጥፊ እጆች ይሁንና፡፡ በኔቸር ጆርናል ላይ ታትሞ የወጣው ይህ ጥናት እንሚያሳየው ጫካው በየዓመቱ ከ1 ቢሊዮን ቶን የበለጠ ካርበን ዳይ ኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር መልቀቅ ጀምሯል፡፡
ይህ ሊሆን የቻለው የሰው ልጆች በጫካው ውስጥ እያደረጉ ያለው ወረራና መሬቱም ለእርሻ አልያም ኢንዱስትሪ አገልግሎቶች ይውል ዘንድ ደኑን በመያባራ እሳት እያቀጣጠሉ ከፍተኛ ካርበን ዳይ ኦክሳይድ እንዲለቀቅ በማድረጋቸው መሆኑ ጥናቱ ላይ ሰፍሯል፡፡ በተጨማሪም በካይ ጋዝ ልቀቱ የአማዞን ሞቃታማና ደረቅ ወቅቶች እንዲረዝሙ በማድረግም ሌላ ተጨማሪ እሳት እንዲነሳና በካይ ጋዝ እንዲለቀቅ ምክንያት እየሆነም ነው፡፡ በዚህም ላለፉት ከ40 በላይ አመታት የሰው ሰራሽ እሳት ሰለባ ሲሆን የቆየው ምስራቃዊ የአማዞን ክፍል ይበልጡን ሞቃት እና ደረቃማ ወደመሆን መሸጋገሩን ጥናቱ አረጋግጧል፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ ናው ታድያ ደኑ በየዓመቱ ግማሽ ቢሊዮን ቶን ካርበን ዳይ ኦክሳይድ ከከባቢ አየር ሲመጥ የሚለቀው ግን በአንፃሩ 1.6 ቢሊዮን ቶን ሆኗል፡፡
የጥናቱ መሪና የብራዚሉ ናሽናል ኢንስቲትዩት ፎር ስፔስ ሪሰርች ተመራማሪ ሉሲያና ጋቲ ጫካው በየዓመቱ ከሚመጠው የካርበን መጠን በሦስት እጥፍ በሚበልጥ መጠን የሚለቅ ሲሆን የደን ጭፍጨፋው ከ30 በመቶ በላይ በሆነባቸው የጫካው አካባቢዎች ደግሞ ጭፍጨፋው ከ20 በመቶ በታች ከሆነባቸው አንፃር በ10 እጥፍ የላቀ ነው ስትል ለሳይንሱ አለም መርዶ አርድታለች፡፡
የአማዞን ጫካ 7.2 ሚሊዮን ካሬ ኪ.ሜ (ከኢትዮጵያን ቆዳ ስፋት በ6 አጥፍ ገደማ የሚበልጥ) መሬት የሚሸፍን ነው፡፡ ይህ ስፋቱ በምድራችን ከቀረው የምድር ወገብ አካባቢ ደን ግማሹን እጅ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
ምንጭ፤ Live Science
ለተጨማሪ፤ https://www.livescience.com/amazon-rainforest-accelerate-climate-change.html

livescience.com
The Amazon rainforest is officially creating more greenhouse gases than it is absorbing
The rainforest was a carbon sink. Now, humans have turned it into a carbon factory.
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ያሰገነባው የህፃናት ሳይንስ ማዕከል ተመረቀ
===============
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ከጎተ ኢንስቲትዩት እና ጀርመን ከሚገኘው ፓኖሜንታ ሳይንስ ማዕከል ጋር በመተባበር በቅጥር ግቢው ያስገነባው የልጆች ሳይንስ ማዕከልን በትናንትናው ዕለት አስመርቋል፡፡
በሦስት ክፍሎች ተደራጅቶ የተገነባውና በሀገራችን በዓይነቱ የመጀመሪያ መሆኑ የተነገረለት ማዕከሉ ታዳጊዎች በፅንሰ ሀሰብ ደረጃ በክፍል ውስጥ የተማሯቸውን ትምህርቶች በተግባር የሚያሳዩ በርካት የፊዚክስ፣ ሒሳብ እና መሰል የሳይንስ ማስተማርያ መሳርያዎችን ይዟል፡፡ ህፃናቱም በተለይ ምላሽ ሳይነገራቸው ከመሳርያዎቹ በስተጀርባ ያለው ሳይንስ እንደሚቃኙበት ተገልጿል፡፡
የአካዳሚው ሳይንስ ማዕከል ንዑስ ክፍል በመሆን የተከፈተው የህፃናት ሳይንስ ማዕከሉ ህፃናት በሳይንስ፣ ቴከኖሎጂ እና ሒሳብ የትምህርት ዘርፎች ጠንካራ ይሆኑ ዘንድ በጨዋታ መልኩ የትምህርት ዘርፎቹን ዕውቀት የሚያስጨብጥ መሆኑን የአካዳሚው ቦርድ ፕሬዘዳንት ፕ/ር ፅጌ ገ/ማርያም ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም አቅም በፈቀደ መልኩ ለማስፋፋት እና በየትምህርት ቤቱ መሰል ተቋማትን ለመገንባት እንደሚሰራም ፕ/ር ፅጌ ገልፀዋል፡፡
የዕለቱ ክብርት እንግዳ ሆነው ማዕከሉን መርቀው የከፈቱት የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚንስትር ደኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞት በበኩላቸው ህፃናት ለሳይንስ ያላቸው ፍላጎት የሚወሰነው በልጅነት ዕድሜያቸው እንደመሆኑ በዙርያቸው ያሉ ነገሮችን ለማወቅ የሚያደርጉትን ጥረት መደገፍና መሰል የሳይንስ ማዕከላትን ማደራጀት የወደፊቶቹን ተመራማሪዎች በመፍጠር ረገድ የማይተካ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡ መንግስት ለሳይንስ በሰጠው ትኩረት ሳብያ በሀገር አቀፍ ደረጃ በርካታ ውጤታማ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው ያሉት ክብርት ሚኒስትር ደኤታዋ በኢትዮጵያ በዓይነቱ ልዩ የሆነው ይህ ማዕከል በመከፈቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ከአስር ዓመት በፊት 49 የሀገራችን ምሁራንን በማሰባሰብ የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነና ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም ነው፡፡ አካዳሚው በመንግስት እና ሌሎች አጋሮች ድጋፍ ሲንቀሳቀስ የተፈጥሮ፣ ማህበራዊ እና ጤና ሳይንስን ጨምሮ በስድስት የተለያዩ ዘርፎች ላይ ሀገራዊ ዕውቀትን የማስፋፋት እና በማስረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ የማቅረብ ስራን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ተቋሙ ኢዚሁ አዲስ አበባ ጉለሌ አካባቢ ቀድሞ የብላቴ ጌታ ህሩይ ወልደ ሥላሴ መኖርያ በነበረው ግቢ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በስራቸው የላቁ 180 ምሁራንንም በአባልነት አቅፏል፡፡

መላው ዓለም ላይ ሲሰልል የቆየው የእስራኤል ኩባንያ
===========
አንድ እስራኤላዊ የግል ኩባንያ የስልክ ሶፍትዌርን ተጠቅሞ በመላው ዓለም የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶችን ሲሰልል እንደቆየ ተዘገበ፡፡ የእስራኤሉ ኤንኤስኦ ግሩፕ ፔጋሴስ በተሰኘው ሶፍትዌሩ አማካኝነት ስለላውን ሲያከናውን መቆየቱን እንደ ዋሽንግተን ፖስት እና ዘ ጋርዲያን ያሉ አለም ዓቀፍ ሚዲያዎች የተሳተፉበት አፈትላኪ መረጃ ምርመራ አሳይቷል፡፡
አፈትሎኮ የወጣው መረጃ እንዳመላከተው ከአውሮፓውያኑ 2016 አንስቶ 50 ሺህ ያህል ስልክ ቁጥሮች በኤንኤስኦ ግሩፕ ደንበኞች ተፈላጊ ሆነው መለየታቸውን ነው፡፡ ሆኖም ከ50 ሺው ውስጥ ሁሉም ሀክ አልተደረጉም፤ ጥቃት የደረሰባቸው ዝርዝር ግን በቅርብ ቀናት ውስጥ ይፋ እንደሚሆን ተዘግቧል፡፡ ታድያ በድርጅቱ ስለላ ሲደረግባቸው ከነበሩት ጋዜጠኞች መካከል በታላላቆቹ አለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት፤ በአዣንስ ፍራንስ ፕረስ፣ ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል፣ ሲኤንኤን፣ ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ አል ዤዚራ፣ ፍራንስ 24፣ ራዲዮ ፍሪ ዩሮፕ፣ ሚዲያፓርት፣ ኢል ፓሪስ፣ ዘ አሶሺዬትድ ፕረስ፣ ሌ ሞንዴ፣ ብሉምበርግ፣ ዘ ኢኮኖሚስት፣ ሮይተርስ እና የአሜሪካን ድምፅ ውስጥ የሚሰሩት ይገኙበታል፡፡
በዝርዝር ውስጥ ስልካቸው ከተገኙት መከላከልም በሳውዲ መንግስት ለተገደለው የሳውዲ ተወላጅ ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ቅርብ የሆኑ ሁለት ሴቶች እንዲሁም ኋላ ላይ ግድያ የተፈፀመበት ሜክሲአዊ የፍሪላንስ ጋዜጠኛ ይገኝበታል፤ ምንም እንኳን ስልኩ ሀክ ተደርጎ ይሁን አይሁን ባይታወቅም፡፡ እንደ ዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ከሆነ ደግሞ ዝርዝሩ ውስጥ ከተገኙት መካከል የሀገር መሪዎች፣ የአረብ ንጉሳዊ ቤተሰብ አባላት፣ ዲፕሎማቶች፣ ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች እና የንግድ ተቋማት ኃላፊዎች እንደሚገኙበት ተጠቅሷል፡፡
ዝርዝሩ የትኞቹ የድርጅቱ ደንበኞች የስልክ ቁጥሮቹን እንዳስገቡ ባይገልፅም በዋናነት ግን ከ10 ሀገራት ማለትም አዘርባጃን፣ ባህሬን፣ ሀንጋሪ፣ ህንድ፣ ካዛኪስታን፣ ሜክሲኮ፣ ሞሮኮ፣ ሩዋንዳ፣ ሳውዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች መሆናቸውን ተዘግቧል፡፡ ኤንኤስኦ ሶፍትዌሩ በወንጀለኞች እና አሸባሪዎች ላይ እንዲውል መሰራቱን ቢገልፅም የዘ ጋርዲያን ዘገባ እንደሚያሳየው ፔጋሴስ መጠነ ሰፊና ያልተቋረጠ ስለላን እንደሚያከናውን ነው፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ፎርቢድን ስቶሪስ ያፈተለከውን መረጃ በማግኘት ቀዳሚዎቹ ነበሩ፤ ኋላ ላይም መረጃውን ለሚዲያዎች አጋርተውታል፡፡ ሆኖም ድርጅቱ የቀረቡበትን ክሶች የተጋነኑና መሰረት ቢስ ናቸው ሲል ተችቷል፡፡
ከዚህ ቀደም ሶፍትዌርን በመጠቀም የግዙፉ ሚዲያ ተቋም አል ዤዚራ ሪፖርተሮችን እና ሞሮኮአዊያን ጋዜጠኞች ስልክ ስለመጠለፉ በካናዳው የዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቶሮንቶ የሚገኘው ሲቲዝን ላብ የተሰኘ የጥናት ማዕከል እንዲሁም አምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳውቀው ነበር፡፡
ምንጭ፤ Tech Xplore
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-07-private-israeli-malware-spy-journalists.html

50,000 phone numbers worldwide on list linked to Israeli spyware: reports
An Israeli firm accused of supplying spyware to governments has been linked to a list of tens of thousands of smartphone numbers, including those of activists, journalists, business executives and politicians ...
የአለማችን የመጀመሪያው የ3ዲ ህትመት ድልድይ
***************************************************
በአለማችን የመጀመሪያ የሆነው በ3ዲ ህትመት የተሰራ የብረት ድልድይ በአምስተርዳም ጥቅም ላይ ዋለ፡፡ ከሁለት አመታት በፊት በMX3D ካምፓኒ የተሰራው የብረት ድልድይ ጥቅም ላይ ሳይውል ቢቆይም ከጥንታዊያን የአምስተርዳም የውሃ መተላለፊያዎች በአንዱ ላይ ተገጥሞ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
በድልድይ ምህንድስና ረገድ ለወደፊት ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ይህ የ3ዲ ህትመት የብረት ድልድይ የተለያዩ ሽልማቶችን ለፈጠራ ባለቤቶቹ አስገኝቶላቸዋል፡፡ የድልድዩ ፕሮጀክት በ2015 የተጀመረ ሲሆን ከፍተኛ መጠን ያላቸውን መገልገያዎች በ3ዲ ህትመት የመስራት እና በስነ ህንጻ ዘርፍ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን የማቅረብ አላማ አለው፡፡
የ MX3D አዲስ ፈጠራ በኔዘርላንዷ ንግስት ማክሲማ አማካኝነት ባሳለፍነው ሳምንት በይፋ ተመርቋል፡፡ ድልድዩ ከአርት ሴንሰር በይነ መረብ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ የተለያ መረጃዎችን መሰብሰብ የሚያስችል ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡ ከዚህ የሚገኘውም መረጃ በህንጻ ምህንድስና ዘርፍ ውስጥ የአይ ኦ ቲን ግልጋሎት ለማጥናት ጥቅም ላይ ይውላል ሲል የመረጃ ምንጫችን አስነብቧል፡፡
ምንጭ Design boom
ተጨማሪ ንባብ https://www.designboom.com/design/world-first-3d-printed-steel-bridge-amsterdam-canals-mx3d-07-16-2021/

ሩሲያ በማርስ ላይ የኒውክለር ኃይል ማመንጫ ልትገነባ ነው
=================
የሩሲያው የጠፈር ምርምር ኤጀንሲ ሮስኮሞስ እህት ተቋም የሆነው የጦር መሳርያዎች ዲዛይን ቢሮ ሀገሪቱ ወደፊት ማርስ ላይ ለምትገነባው ጣብያ የኃይል ምንጭ እንዲሆን በማሰብ የኒውክለር ኃይል ማመንጫ ጣብያ ለመገንባት ማቀዱን የሀገሪቱ የዜና ተቋም ስፑትኒክ ዘገበ፡፡ ተቋሙ ለኒውክለር ኃይል ማመንጫ ጣብያው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ዜነስ በተባለቸው የጠፈር ላይ ማጓጓዣ (Space Tug) አማካኝነት አጓጉዞ ለማሟላት አቅዷል፡፡
ግዙፎቹን የጣብያው ግንባታ ቁሳቁሶች ከመሬት አንስቶ ወደ ማርስ የምታደርሰው ዜነስ በኒውክለር ኤሌክትሪክ ግፊት አማካኝነት የምትንቀሳቀስ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡ ግብዓቶቹ በዜነስ አማካኝነት ወደ ማርስ አየር ካቀኑ በኋላም በፓራሹት ወደ ምድሯ የሚለቀቁ ይሆናል፡፡ ታድያ የኒውክለር ኃይል ማመንጫ ጣብያ ቁሳቁሶችን ከማጓጓዝ ባሻገር ግን ዜነስ ለሌላ ስራም ታጭታለች፤ ከወራት በፊት የሮስኮሞስ ኃላፊው ዲሚትሪ ራጎዚን ምናልባትም የሌላው አለም ፍጡራን እዚያ ይገኙ እንደሆን ለመመርመር እንደ ጁፒተር ያሉ ሌሎች ፕላኔቶች ጋርም ልትሄድ እንደምትችል ጠቁመው ነበር፡፡
ሩሲያ የአሜሪካኑ የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ ከሚጠቀመው ከአንድ አስረኛም ያነሰ በጀት ቢኖራትም የሩሲያ ጠፈር ምርምር ተቋም ግን በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ ገቢር ይሆናሉ ያላቸውን ታላላቅ እቅዶች አስቀምጧል፡፡ ከነዚህ ታላላቅ እቅዶቹ መካከል ሀገሪቱ የራሷ የጠፈር ምርምር ጣብያ እንዲኖራት ማድረግ፣ ሰው የጫኑና ሰው አልባ ተጓዦችን ወደ ጨረቃ መላክ፣ እንዲሁም ከቻይና ጋር በመተባበር ጨረቃ ላይ ሰፈር መገንባት ይገኙበታል፡፡ ታድያ የኒውክለር ኃይል ማመንጫን ወደ ማርስ የመላኩና ሰዎችንም በዚያ የማስፈሩ ጉዳይ ብዙ ስራ የሚቀረው ውጥን ቢሆንም በአግባቡ ከተመራ ግን ሊሳካ እንደሚችል ተነግሮለታል፡፡
ምንጭ፤ Futurism
ለተጨማሪ፤ https://futurism.com/the-byte/russia-proposes-nuclear-power-plant-mars

THE_BYTE.
Russia Proposes Nuclear Power Plant on Mars
A subsidiary of Russia’s Roscosmos space agency is proposing to send a nuclear power station to Mars to power a future Russian base.
በሰዓት 600 ኪ.ሜ የሚከንፈው አዲሱ የቻይና ባቡር
===========
ቻይና በሰዓት 600 ኪ.ሜ መጓዝ የሚችል ተንሳፋፊ የማግኔት ባቡር (Maglev Train) ትናንት ይፋ አደረገች፡፡ በቻይናውያን ባለሙያዎች ቺንዳኦ ከተማ ውስጥ የተፈበረከው ባቡሩ ፍጥነቱ በምድር ላይ አቻ የለውም ተብሎለታል፡፡
የማግኔት ባቡሮች ከባቡር ሀዲዱ ጋር ምንም አይነት አካላዊ ግንኙነት ሳይኖራቸው የኤሌክትሮ ማግኔቲክ ኃይልን በመጠቀም ተንሳፈው የሚጓዙ ባቡሮች ናቸው፡፡ ቻይናም ይህን ቴክኖሎጂ በተወሰነ መልኩ ይሁን እንጂ ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ስትጠቀምበት ኖራለች፡፡ ለምሳሌ ሻንጋይ ውስጥ ኤርፖርቱን ከከተማው የሚያገናኝና በሰዓት 431 ኪ.ሜ መክነፍ የሚችል አነስተኛ የማግኔት ባቡር መስመር ከአውሮፓውያኑ 2004 አንስቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው፡፡ እንዲህ እንዲህ ካሉ አነስተኛ መስመሮች ባለፈ ከተማን ከከተማ አልያም አንዱን ግዛት ከሌላኛው የሚያገናኝ ተንሳፋፊ የማግኔት ባቡር ባትዘረጋም እንደ ሻንጋይ እና ቼንዱ ያሉት ከተሞቿ ግን በዘርፉ ላይ ምርምር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
በሰዓት 600 ኪ.ሜ የሚምዘገዘገው አዲሱ ባቡርም ታድያ ሁለቱ ግዙፍ የቻይና ከተሞች በሆኑት ቤጂንግ እና ሻንጋይ መካከል ያለውን ከአንድ ሺህ ኪ.ሜ የሚበልጥ ርቀር በ2 ሰዓት ተኩል ጊዜ ውስጥ ተጉዞ መጨረስ ይችላል፡፡ ለንፅፅር ያህል አውሮፕላንን ተጠቅሞ ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላኛው ለመጓዝ 2 ሰዓት ፈጣን ባቡርን ተጠቅሞ ለመጓዝ ደግሞ 5 ሰዓት ተኩል ይፈጃል፡፡
መሰል የማግኔት ባቡር መስመሮችን የመገንባት ሩጫ ውስጥ የገባችው ቻይና ብቻ አይደለችም፡፡ እንደ ጃፓን እና ጀርመን ያሉ ሀገራትም የማግኔት ባቡር መስመሮችን የመገንባት ዕቅድ አላቸው፡፡ ሆኖም የዋጋው መናርና ባቡሮቹም አሁን ባለው የባቡር ሀዲድ ላይ መጓዝ የማይችሉ መሆናቸው ለውጥኑ ስኬት መሰናክል ሆኖ ይገኛል፡፡
ቻይና ከ140 ሺህ ኪ.ሜ በላይ ርዝመት ያለው የባቡር መስመርን በመላው ሀገሪቱ ዘርግታ ትገኛለች፡፡ ከዚህም ውስጥ 38 ሺህ ኪሜ የሚሆነው የፍጥነት ባቡር መስመር ነው፡፡
ምንጭ፤ Reuters እና South China Morning Post
ለተጨማሪ፤ https://www.reuters.com/world/china/china-unveils-600-kph-maglev-train-state-media-2021-07-20/ እና https://www.scmp.com/news/china/science/article/3141769/superfast-maglev-train-key-chinas-smart-transport-network-rolls

መልካም ዜና፤ ለዩትዩበሮች
=========
ዪትዩብ “ሱፐር ታንክስ” የተሰኘ የአንድ ቻናል አድናቂዎች ለቻናሉ ስጦታና ድጋፍ የሚያበረክቱበት አዲስ ገፅታን በትናንትናው ዕለት አስተዋውቋል፡፡ ከዚህ ቀደም ተመልካቾች በሱፐር ቻት፣ ሱፐር ስቲከር እና ቻናል ሰብስክሪብሽን አማካኝነት ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ አመቻችቶ የነበረው ዩትዩብ በአዲሱ መንገድ ደግሞ ተመልካቾች በቀጥታ ስርጭት እየተላለፉ ላልሆኑ ቪዲዮዎች ድጋፋቸውን እንዲሰጡ የሚያደርግ ሆኗል፡፡ በዚህም ተመልካቾች ከ2 አንስቶ እስከ 50 የአሜሪካን ዶላር ድረስ ለሚያደንቋቸው ቻናሎች መስጠት ይችላሉ፡፡
እስከዛሬ ተመልካቾች ለቪዲዮዎቹ ባለቤቶች ድጋፍ የሚያደርጉበትን መንገድ በማመቻቸት ረገድ ዩትዩብ ወደኋላ ይቀር ነበር፡፡ ይህ ግን በ “ሱፐር ታንክስ” የተለወጠ መስሏል፤ የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ቀጥታ ስርጭት በሚኖርበት ጊዜ ለቪዲዮው ባለቤት ድጋፍ ማድረጊያ መንገድ ቢኖራቸውም በዚህ መልኩ አድናቂዎች ድጋፍ የሚያደርጉበት መንገድ ግን የላቸውም፡፡ በተጨማሪም ዩትዩብ በተመልካቾች አማካኝነት ለአድናቂዎች ከሚበረከቱ ድጋፎች ውስጥ 30 በመቶ ሲቆርጥ እንደ ትዊች ያሉ ተፎካካሪዎች ግን 50 በመቶ የግላቸው ያደርጋሉ፡፡
ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት ከ10 ሚሊዮን በላይ የዩትዩብ ተመልካቾች በሱፐር ቻት፣ ሱፐር ስቲከር አልያም ቻናል ሰብስክሪብሽን ላይ ተሳትፈው ነበር፡፡ አብዛኛው ገቢያቸውን ከእንደዚህ አይነት ድጋፎች የሚያገኙ ቻናሎች ብዛትም እ.አ.አ 2019 ላይ ከነበረበት በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ በሦስት እጥፍ አድጓል፡፡
ከትናንት ጀምሮ “ሱፐር ታንክስ” የዩትዩብ ፓርትነር ፕሮግራም አባል በሆኑ 68 ሀገራት ውስጥ በሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ቻናሎች ላይ መምጣት የጀመረ ሲሆን በቀጣይም ፕሮግራሙ ውስጥ በተካተቱ ሌሎች ሀገራት የሚስፋፋ ይሆናል፡፡
ምንጭ፤ Tech Crunch
ለተጨማሪ፤ https://techcrunch.com/2021/07/20/youtubes-newest-monetization-tool-lets-viewers-tip-creators-for-their-uploads/?guccounter=1&guce_referrer=aHR0cHM6Ly93d3cuZ29vZ2xlLmNvbS8&guce_referrer_sig=AQAAAJhGZwEaSQhdhud-rrjzD1u5BM7hlfB6-unN82NE8z8TovAG2G1c_Q2SJnBrpl_-axWpl0kfoQDHG3wmVNwdGfAR5DLwW4eaTi-x6eTtBDhFyQDbl0Y_pfWItoxOz6JVfxTHLgcenhsyahIP--nwMI-iJuPihOlzfh_kEYkgaaoH

TechCrunch
YouTube’s newest monetization tool lets viewers tip creators for their uploads
YouTube announced its latest feature, Super Thanks, on Tuesday. This is YouTube’s fourth Paid Digital Good, which is what the platform calls any product that lets fans directly pay creators. So far, these tools include Super Chat, Super Stickers and channel…