TechIn2
1.16K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ቻይና የአዳዲስ ህንፃዎቿ ቁመት ከ500 ሜትር እንዳያልፍ አገደች
====================
ቻይና በምድሯ የሚገነቡ አዳዲስ ህንፃዎቿ ቁመታቸው ከ500 ሜትር እንዳያልፍ የሚያግድ ደንብ አወጣች፡፡ በብሔራዊ ልማት እና ሪፎርም ኮሚሽን አማካኝነት የወጣው ይህ እገዳ በተጨማሪነትም ቁመታቸው ከ250 ሜትር በላይ የሆኑ ህንፃዎች መገንባትን የገደበ ሲሆን ህንፃዎች ከዚህ ቁመት በላይ እንዲገነቡ ከተፈቀደላቸውም ከእሳት አደጋ ደህንነትና ሌሎች ጉዳዮች አንፃር ንድፋቸው በሀገሪቱ የቤት እና ከተማ-ገጠር ልማት ሚኒስቴር አስገምግመው ይሆናል፡፡ ከ100 ሜትር በላይ ሆነው የሚገነቡ ረጃጅም ህንፃዎችም ቢሆን መሬት መንቀጥቀጥን ከመቋቋም አንፃር ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚገጥማቸው ተነግሯል፡፡

ካለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ወዲህ የብዙ ረጃጅም ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ባለቤት የሆነችው ቻይና የተለያዩ ሪል እስቴት አልሚዎች ቁመታቸው ከ600 እስከ 800 ሜትር የሚደርሱ ንድፎችን በተደጋጋሚ ይዘው ለግንባታ የሚሯሯጡባት ሀገር ነች፡፡ ምንም እንኳን የዓለማችን ረጅሙ ህንፃ በዱባይ የተገነባው ባለ 828 ሜትሩ ቡርጅ ከሊፋ ይሁን እንጂ ከዓለማችን 10 ረጃጅም ህንፃዎች ውስጥ 5ቱ መገኛቸው ሀገረ ቻይና ነው፡፡ እነዚህም ውስጥ ቡርጅ ከሊፋን ተከትሎ በ632 ሜትር ቁመት የዓለማችን ሁለተኛው ረጅሙ ህንፃ የሆነው ሻንጋይ ታወር፣ የሸንዘኑ ፒን አን ፋይናንስ ማዕከል (599 ሜትር) እና በቤጂንግ ያለው ሲአይቲአይሲ ታወር (527.7 ሜትር) ይገኙበታል፡፡ ከዚህም ባሻገር ቻይና በዓለማችን ከሚገኙት ቁመታቸው 200 ሜትርን የሚበልጡ 1,478 ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ውስጥ 678ቱን ይዛለች፡፡

አዲስ የወጣው ደንብ እንዳመላከተው የየአካባቢው አስተዳደሮች የግንባታ ስራዎች ጥራት ያላቸውና ደህንነታቸው የተጠበቀ ከማድረግ አንፃር መልካም ስራ እየሰሩ ቢሆንም አሁንም ግን የደህንነት ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ ክፍተቶች እንዳሉ ይገልፃል፡፡ አያይዞም የሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ቁመት ከሚገነቡበት ከተማ ትልቀት እና እሳት አደጋን የመቆጣጠር ብቃት ጋር መስማማት መቻል እንዳለባቸው ቢሮው አስታውቋል፡፡

ምንጭ፤ Xinhuanet እና Global Times
ለተጨማሪ፤ http://www.xinhuanet.com/english/2021-07/08/c_1310049617.htm እና https://www.globaltimes.cn/content/1187981.shtml
የመጸዳጃ ቤት ቆሻሻን ወደ ሀይል ምንጭነት
********************************************
በደቡብ ኮሪያ አንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መጸዳጃ ቤት መጠቀም የቡና ወጭን መሸፈን የሚያስችል ገቢ እንደሚያስገኝ ተነገረ፡፡ በደቡብ ኮሪያ የኡልሳን ብሔራዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ፕሮፌሰር የሆኑት ቾ ጂ ዌኦን ከአካባቢ ጋር ተስማሚ የሆነና በተመሳሳይ ጊዜ ሐይልንና ተፈጥሯዊ ማዳበሪያን ማስገኘት የሚችን ስልትን ከህዝብ መጸዳጃ ቤት መስራት ችለዋል፡፡

ከመጸዳጃ ቤቱ ጋር የተያያዘው ቱቦ ጽዳጁን ወደ ተዘጋጀለት የምድር ውስጥ ማጠራቀሚያ ያስተላልፈዋል፡፡ ከዚያም የተጠራቀመው ጽዳጅ በደቂቅ ዘአካላት አማካኝነት በመብላላት ወደ ሚቴን ጋዝነት ይለወጣል፡፡ ይህ ጋዝም ባዮጋዝ በመሆን ለተለያዩ የሀይል ፍላጎቶች እንዲውል ይደረጋል፡፡

አንድ ሰው በአማካኝ በቀን 500 ግራም ጽዳጅ ያስወግዳል፡፡ ይህም በተሰራው ቤተ-ሙከራ አማካኝነት 50 ሊትር ሚቴን ጋዝ ማምረት ያስችላል፡፡ 50 ሊትር ሚቴን ጋዝ 0.5 kWh ኤሌክትሪክ ማመንጨት ያስችላል፡፡

በመሆኑም አንድ ሰው በዚህ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ሲጠቀም Ggool የተሰኘ ቨርቹዋል ክፍያ ያገኛል፡፡ ጂጉል በኮሪያ ቋንቋ ማር ማለት ነው፡፡ በቨርቹዋል ክፍያው ተከፋዩ ቡና ወይም ሙዝ መግዛት እንዲችል ተመቻችቷል፡፡ አንድ ሰው በመጸዳጃ ቤቱ ሲጠቀም 10 ጂጉል ያገኛል፡፡
ምንጭ Reuters
ተጨማሪ ንባብ https://www.reuters.com/world/asia-pacific/south-korean-toilet-turns-excrement-into-power-digital-currency-2021-07-09/?utm_campaign=trueAnthem%3A%20Trending%20Content&utm_medium=trueAnthem&utm_source=facebook&fbclid=IwAR1MINB3uR
በዛሬው የቴክ-ሳይንስ ዝግጅታችን
===========
ወደ ድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ አቅንተን በዩኒቨርሲቲው የተሰራውን የኢ-ለርኒንግ ኮምፒውተር ሲስተም የምናሳያችሁ ሲሆን እንዲሁ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አምርተንም ኢታኖልን አስመልክቶ በዩኒቨርሲቲው እየተሰራ ያለውን የምርምር ስራ እንመለከታለን፡፡

ከዩኒቨርሲቲዊቻችን ብዙም ሳንርቅ በተቋማት መሰናዶ አንጋፋው የሀረማያ ዩኒቨርሲቲን የምንዳስስና የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ፕ/ር ጨመዳ ፊኒንሳ ላይ የሚያተኩረው የተመራማሪዎች ታሪክ ሦስተኛ ክፍልም የሚቀርብ ይሆናል፡፡

በቴክኖሎጂ ታሪክም አለማችንን በእጅጉ እንደሚለውጥ ስለሚነገርለት የ5ጂ ቴክኖሎጂ የሚያውጠነጥን ዝግጅታችን ሰዓቱን ጠብቆ ወደ እናንተው ይደርሳል፡፡

እነዚህን አስተማሪ ዝግጅቶቻችንን ዛሬ ቅዳሜ በ10 ሰዓት MOE ቲቪ እንዲሁም በድጋሚ ማክሰኞ በተመሳሳይ ቻናል በተመሳሳይ ሰዓት ሊያገኙን ይችላሉ፡፡

ወደ ዩትዩብ ቻናላችንም ጎራ በማለት አዳዲሶቹን ጨምሮ እስከዛሬ የተሰሩትን ፕሮግራሞች በሙሉ መመልከት ይችላሉ https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg ፡፡
ወንዶች እንደ ሴት አርግዘው ልጅ የሚወልዱበት የእንስሳት ዓለም
ወንዶች እንደ ሴት አርግዘው ልጅ የሚወልዱበት የእንስሳት ዓለም
===========
ዓለማችን በብዙ ድንቅና አስራሚ ተፈጥሮአዊ ሁነቶች የተሞላች ናት፤ ሁሌም ጠልቀን በቃኘናት ቁጥር ይበልጥ አፍ በሚያስከፍት ተአምሯ የምትቀበለን ልዩ ትንግርት፡፡ ታድያ ለዛሬ ከነዚህ በተፈጥሮ በተለይም ከእንስሳት ዓለም ዘንድ ካሉ አስገራሚ የሚባልላቸው ነገሮች ውስጥ ወንዶች ልጆችን የሚያረግዙባቸውን እንስሳት በአጭሩ እናስቃኝዎ፡፡

በተለምዶ ከምንሰማው ውጪ ወንዶች የሚያረግዙት ሲንግናታዳይ ተብሎ በሚጠራው ቤተሰበ ውስጥ ያሉ ሦስት የዓሣ ዝርያዎች ማለትም የባህር ፈረስ፣ ፓይፕፊሽ እና የባህር ድራጎን አሳዎች ናቸው፡፡ የባህር ፈረስ እና ፓይፕፊሾቹ ልጆቻቸውን ሰውነታቸው ውስጥ ባለ የማሳደግያ ቦርሳቸው ውስጥ በማድረግ በኃይል እንደተሞላ ስብ ያሉ ልዩ ልዩ ንጥረ ነገሮችን በሕብረ ህዋሶቻቸው በኩል እየመገቡ በስተመጨረሻም ምስሉ ላይ እንደሚታየው ይወልዷቸዋል (የምር ይወልዳሉ)፡፡ የባህር ድራጎኖች በበኩላቸው እንቁላሎቹ በውጪኛው የጭራቸው ክፍል ላይ በማጣበቅ ነው ልጆቹን የሚያሳድጉት፡፡

የወንዶች ማርገዝ ጥቅሙ ምን ላይ ይሆን? ብለው ከጠየቁ ምላሹ ሴቶቹ ትኩረታቸውን በዋናነት እንቁላሎችን በማምረት ላይ ብቻ እንዲያደርጉና ልጅ የማሳደጉን ኃላፊነት ወንዶች እንዲወስዱት ለማድረግ ነው፡፡ እዚህ ላይ ግን ሌላው ግርምታን የሚያጭረው ጉዳይ የባህር ፈረሶች ጠዋት ላይ ልጃቸውን በሰላም ተገላግለው ማታ ላይ በድጋሚ ማርገዝ መቻላቸው ነው፡፡ ይህ ታድያ የዝርያው ቁጥር በማብዛት ህይወትን የማስቀጠል እድላቸውን እንዲያሳድጉ ይረዳቸዋል፡፡

ወንዶቹ ልጆቹን መያዛቸው ሴቶቹ እንቁላልን በመስጠት ላይ እንዲያተኩሩ ከማስቻልም ባሻገር ኃይል እንዲቆጥቡም ያደርጋቸዋል፡፡ እንቁላልን ለማምረት ሴቶቹ የሚያስፈልጋቸው ኃይል ወንዶቹ የዘር ፈሳሽን ለማምረት ከመያስፈልጋቸው የላቀ ነው፡፡ እናም እንቁላሎቹን የመንከባከቡን ድርሻ ወደ ወንዶቹ ማሻገሩ የኃይል አጠቃቀሙ በሁለቱ ፆታዎች መካከል በፍትሀዊነት እንዲከፋፈል ያደርገዋል፡፡

ታድያ አንባቢያችን፤ ሴቶች ልጅን በሆዳቸው አርግዘውና ለወራት ተሸክመው በስተመጨረሻም በስቃይ ከመውለድም ባሻገር አብዛኛውን ቤተሰባዊ ኃላፊነት ጫንቃቸው ላይ በሚወድቅባቸው በዚህ ዓለም ከዚህ የላቀ የጾታ እኩልነትን ምሳሌን ከየት ማግኘት ይቻላል?

ምንጭ፤ live science
ለተጨማሪ፤ https://www.livescience.com/weird-animals-evolution.html
እርሻ በሰማይ
እርሻ በሰማይ
=======
ታላቋ የሆንግ ኮንግ ከተማ ውስጥ በዝተው ከሚገኙት ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች መካከል አንዱ በሆነው የባንክ ኦፍ አሜሪካን ታወር ላይ የቢሮው ሰራተኞች በህንፃው ጣርያ የሚገኘውን የካሮት እና ሌሎች ፍራፍሬዎች እርሻን ሲንከባከቡ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ 150 ሜትር ቁመት ባለው ይህ በከተማዋ የፋይናንስ እምብርት ቦታ በቆመው ህንፃ ላይ የተዘረጋው እርሻ በአርማታና መስታውት ለተሞላው የህንፃው ገፅታ ልዩ ተጨማሪ መልክን አላብሶታል፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ይህ አይነት በጣርያቸው ላይ እርሻ የገነቡ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎችን ከዓለማችን ቀዳሚ የፋይናንስ እና ምጣኔ ሐብት ማዕከል ከሆኑ ከተሞች አንዷ በሆነችውና በሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ብዛት አቻ የሌላት ሆንግ ኮንግ ዘንድ መመልከት እየተለመደ መጥቷል፡፡ ምስጋና መሰል ተግባራትን የማስፋፋት ስራ ለሚሰራው ሩፍቶፕ ሪፐብሊክ የተሰኘ ተቋም ይሁንና ከአውሮፓውያኑ 2015 በኋላ እንኳን 60 የሚሆኑ የከተማይቱ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች በጣርያቸው ላይ የከተማ እርሻ ማከናወኑን ተያይዘውታል፡፡ እነዚህም በተለይ ቀድሞ ከተማዋን ቁልቁል ለመመልከቻ ማማ፣ ሄሊኮፍተር ማረፍያ እንዲሁም የገበያ ማዕከልነት ታልመው የነበሩ ቦታዎች ናቸው አሁን ላይ አገልግሎታቸው ተለውጦ አረንጓዴ ሸማ የለበሱት፡፡
እንደ ከተማይቱ አስተዳደር ከሆነ ሆንግ ኮንግ በየዕለቱ 3,500 ቶን ወይም ክብደቱ ከ250 ባለ ፎቅ አውቶብሶች ጋር የሚመጣጠን ምግብን ታስወግዳለች፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን 7.5 ሚሊዮን የሚሆነው የከተማይቱ ነዋሪ ከ90 በመቶ በላይ ምግቡን የሚገኘው በዋናነት ከተቀረው የቻይና ክፍል ነው፡፡ ታድያ ምንም እንኳን በሰው እና ህንፃ እጅጉን ከተጨናነቁ የምድራችን ከተሞች አንዷ ብትሆንም ሰባት ሚሊዮን ካሬ ሜትር የሚሆነው የሆንግ ኮንግ መሬት እርሻ ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ ይህ ታድያ 6 ሚሊዮን ካሬ ሜትር የሚሸፍነው የከተማይቱ ህንፃዎች ጣርያን ሳያጠቃልል ነው፡፡ ሩፍቶፕ ሪፐብሊክም ይህን በህንጻ ጣርያዎች ላይ ያለ እምቅ አቅምን ለመጠቀም ከኪነ ህንፃ ባለሙያዎች፣ የህንፃ ባለቤቶች እና ሪል ስትቴት አልሚዎች ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም ባንክ አፍ አሜሪካን ታወርን ጨምሮ በከተማው ያሉ ሌሎች ህንፃዎችን ጣርያ ወደ ከተማ እርሻነት መለወጥ ችሏል፡፡
እነዚህ ተግባራት በተለይ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ የሚቆረቁራቸው የከተማይቱ ወጣት ሰራተኞች ስጋትን መከላከያ ሆኖ እያገለገለ ሲሆን በሌላ መልኩ ከስራቸው በጡረታ የተገለሉ ሰዎች ጊዜ ማሳለፍያና አዲስ ክህሎትን መማርያ ሆኖላቸዋል፡፡
ውድ አንባብያን፤ ይህ ስልት ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ህንፃዎች ጫካነት እየጠለወጡ በመጡትና ለከተማ እርሻ ሊውል የሚችል ክፍት መሬትን ማግኘት አዳጋች እየሆነባቸው ባሉት የሀገራችን ከተሞች ቢተገበር ምን ይመስላችኋል? መልካም ቀን፡፡
ምንጭ፤ Tech Xplore
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-07-hong-kong-urban-farms-gardens.html
ከፍተኛ ሀይል ያለው የፀሐይ ሞገድ መሬትን እየተጠጋት ነው
*************************************************************
መነሻውን ከፀሐይ ከባቢ አየር እንዳደረገ የተነገረለት ከፍተኛ የፀሐይ ሙቀትን የያዘ ሞገድ ወደ ምድራችን 1.6 ሚሊዮን ኪሎሜትሮችን በሰዓት እየተምዘገዘገ እየመጣ እንደሆነ ስፔስ ዌይዘር ዶት ኮምን ጠቅሶ ሂንዱስታን ታይምስ ዘግቧል፡፡ ይህ የሙቀት ማዕበል በመሬት ስበት በተሸፈኑ የምድራችን ክፍሎቸ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችል እየተጠበቀ ነው፡፡
በሰሜንና በደቡብ ዋልታዎች አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በዚህ ሊጨምር ይችላል በተባለ ፍጥነት ውስጥ እየተምዘገዘገ ያለውን የፀሐይ ሞገድ ማዕበል ወጋገንን በምሽት በግልጽ ያዩታል ሲል የመረጃ ምንጫችን አስነብቧል፡፡ በዚህ ከፍኛ ሙቀት ምክንያት የላይኛው የምድራችን ከባቢ አየር ሊቃጠልና በሳተላይቶች ላይ ጉዳት ሊደርስ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋትም ተሰምቷል፡፡
ሙቀቱ በጂፒኤስ ምሪቶች፣ የተንቀሳቃሽ ስልኮች ግንኙነትና የሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭቶች ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችልም ተነግሯል፡፡
የፊታችን እሁድ ወይም ሰኞ የምድራችን የላይኛው ክፍል ላይ እንደሚደርስም እየተጠበቀ ነው፡፡
ምንጭ Hindustan times
ተጨማሪ ንባብ https://www.hindustantimes.com/science/powerful-solar-storm-approaching-earth-can-impact-gps-cell-phone-signals-101625969315026.html
ምዕራባዊ አሜሪካንን እየናጠ ያለው የሙቀት ማዕበል
ምዕራባዊ አሜሪካንን እየናጠ ያለው የሙቀት ማዕበል
=============
በምዕራባዊው የአሜሪካን ክፍል የተከሰተው የሙቀት ማዕበል የከባቢ ሙቀት መጠኑን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ከፍ አድርጎታል፡፡ በአሜሪካኗ የካሊፎርኒያ ግዛት የሚገኘው የሞት ሸለቆ ወይም በሀገሬው አጠራር ዴዝ ቫሊም ትናንት ዕለተ እሁድ ክብረወሰን የሆነ 54 ዲግሪ ሴሊሺየስ አስመዝግቦ ሲውል በምድር ላይ ተመዝግቦ የማያውቅ ነውም ተብሎለታል፡፡ ብዙውን ጊዜ ከይፋዊ የአየር ንብረት መግለጫዎች ከፍ ያለ ሆኖ የሚገኘው የፓርኩ ሙቀት መለኪያ ታድያ ከዚህ ከፍ ያለ ሙቀትን መዝግቧል፡፡
ከባዱ ሙቀት በሰሜን ምዕራባዊ አሜሪካን የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን የተጫነና የተለያዩ ሰደድ እሳቶችንም ያስነሳ ሆኗል፡፡ ከተነሱት ሰደድ እሳቶች መካከል እሁድ በፍሬሞንት ዊነማ ብሔራዊ ደን እና አካባቢው የተቀሰቀሰው የቡትሌግ ሰደድ እሳት 580 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚሆን መሬትን ሲሸፍን በደቡባዊ ኦሪጎን የከሰተው እሳትም 1,200 ቤቶችን አደጋ ውስጥ ጥሏል፡፡ የቡትሌግ እሳት እጅጉን አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሳም 926 የእሳት አደጋ ሰራተኞች አካባቢውን ጥለው እንዲያፈገፍጉ አስገድዷል፡፡ ሆኖም እስካሁን የሞት አደጋን አላስተናገደም፡፡ በተጨማሪም አሳት አደጋዎቹ ኦሪጎንን ከካሊፎርኒያ የሚያገናኙ የኃይል ማስተላለፊያዎችን ማቃጠል መጀመራቸውም የሁለቱ ግዛቶች ኃላፊዎችን ሀሳብ ላይ ጥሏል፡፡
እሳት አደጋው በተነሳባቸው አካባቢዎች ያሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች እቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ አስገዳጅ ትእዛዝ ከመንግስት ተላልፎባቸዋል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀባት የኦሪጎን ግዛት ሌሎች ተጨማሪ ቤተሰቦችም ከቤታቸው ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል፡፡
ሆኖም የሙቀቱ ነገር የሳባቸው የአሜሪካን ሀገር ጎብኚዎች ወደ ሙት ሸለቆ በማምራት ሙቀቱን ሲያዩና ከሙቀት መለኪያው ጎን ሆነው ፎቶ ሲነሱ ውለዋል፡፡ የብሔራዊ አየር ፀባይ አገልግሎት በበኩሉ ሙቀቱ ለጤና አደገኛና በተለይ ህፃናት ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ነው ሲል ማስጠንቀቂያ አውጥቷል፡፡
ምንጭ፤ Reuters
ለተጨማሪ፤ https://www.reuters.com/business/environment/us-west-scorches-under-heat-wave-death-valley-reaches-130-degrees-2021-07-12/?taid=60ebdcc2b9a11500017c22ab&utm_campaign=trueAnthem:+Trending+Content&utm_medium=trueAnthem&utm_source=twitter
በዱባይ የተገነባው የውሃ ውስጥ ከተማ
በዱባይ የተገነባው የውሃ ውስጥ ከተማ
==============
የዓለማችን ረጅሙ ሰማይ ጠቀስ ህንፃ እንዲሁም ግዙፉ የገበያ ሞል ባለቤት የሆነችው ዱባይ አሁን ደግሞ በዓለማችን ቀዳሚው የሆነውን ጥልቅ የመዋኛ ገንዳ ከፍታለች፡፡ ከመሬት በታች 60 ሜትር ጥልቀት ያለው ገንዳው ከዚህ ቀደም በ45 ሜትር ጥልቀቱ ቀዳሚ ስፍራ ላይ ይቀመጥ የነበረውን የፖላንዱን ጥልቅ መዋኛ በመቅደም ነው ስፍራውን የተቆናጠጠው፡፡
ዲፕ ዳይቭ ዱባይ የተሰኘው ይህ ገንዳ በ14 ሚሊዮን ሊትር ውሃ ተሞልቷል፤ ስድስት የኦሎምፒክ መዋኛ ገንዳዎች ከሚይዙት ጋር የሚስተካከል መሆኑ ነው፡፡ የገንዳው ውሃ ለጠላቂ ዋናተኞች ምቹ በሆነ የ30 ዲግሪ ሴሊሺየስ ሙቀት እንዲረጋ ተደርጓል፡፡ ከምቾት ባለፈ ግን የጠላቂ ዋናተኞቹን ደህንነት ለማረጋገጥ በመላው የገንዳው ክፍል 56 የደህንነት ካሜራዎች ሲገጠሙለት የህክምና ስፍራም ተዘጋጅቶለታል፡፡
የገንዳው አስደናቂ ገፅታ ታድያ ውሃ ውስጥ በሰመጠች ከተማ አምሳያ የተገነቡት ህንፃዎች ከግሩም የመብረቅ እና ድምፅ ስርዓቶች ጋር ተጣምሮ ልዩ የሆነ ከባቢን መፍጠሩ ነው፡፡ በተጨማሪ ገንዳው የውሃ ውስጥ ፊልም ስቱዲዮ ሆኖም ያገለግላል፤ በአቅራቢያውም የሚዲያ አርትኦት ክፍል ተገንብቶለታል፡፡
ለጀማሪም ሆነ የእውቀና ሰርተፊኬት ላላቸው ጠላቂ ዋናተኞች ስልጠና የሚያቀርበው ዲፕ ዳይቭ ዱባይ ጠላቂ ዋናተኞች ገንዳውን በደንብ ከሚያውቅ ጠላቂ ዋናተኛ ጋር አንዴ ተዟዙሮ ካዩ በኋላም በራሳቸው ሊዘዋወሩበት ይችላሉ፡፡
ገንዳው ዋናተኞችን ብቻ አይደለም እንዲያዝናና የታለመው፤ በተለያዩ አቅጣጫዎች ትላልቅ መስኮት እና የቴሌቪዥን ስክሪኖች ስለተገጠሙለት ውሃው ውስጥ ሳይገቡም ገንዳውን መቃኘት ይቻላል፡፡ አሁን ላይ ግን በግብዣ ብቻ ነው እንግዶችን የሚቀበለው፡፡
ታድያ ጎብኚዎች ገንዳውን ከጎበኙ በኋላ ከ300 ሜትር በላይ ቁመት ያላቸው ህንፃዎች ላይ ለመውጣት ቢያንስ ከ18 እስከ 24 ሰዓታት እንዲቆዩ ዲፕ ዳይቭ ዱባይ ምክሩን ይለግሳል፡፡ ሆኖም ረጅም ህንፃዎችን ከጎበኙ በኋላ ወደ ገንዳው ማምራት ምንም ችግር እንደሌለው ተቀምጧል፡፡
ምንጭ፤ CNN
ለተጨማሪ፤ https://edition.cnn.com/travel/article/deep-dive-dubai-worlds-deepest-dive-pool/
በአሜሪካ እንቅልፍን እንዲቆጣጠር ፈቃድ ያገኘው አማዞን ዶት ኮም
*********************
አማዞን ዶት ኮም ኢንክ በአሜሪካ የደንበኞቹን እንቅልፍ መከታተል የሚስችለውን ራዳር እንዲጠቀም ፈቃድ ተሰጠው፡፡ የአሜሪካ የፌዴራል ኮሚኒኬሽን ኮሚሽን ለአማዞን የሰጠው ፈቃድ እንቅስቃሴን የሚከታተልና የራዳር ሴንሰርን በመጠቀም ያለንክኪ የሚተገበር የእንቅልፍ መከታተያ ነው፡፡
ቴክኖሎጂው እንደ አማዞን መረጃ እንቅስቃሴን ከሶስት አቅጣጫ በመከታተል ደንበኛው ምልክቶችንና የሰውነት እንቅስቃሴውን በመጠቀም ቀጣይ ሁኔታዎችን መረዳት እንዲችል ያደርገዋል፡፡ በሌላ አገላለጽ በተለይ እንደ እንቅስቃሴ፣ ንግግርና ሌሎች አካላዊ ጉዳቶች ያሉባቸውን ሰዎች የሚያግዝና የተስተካከለ የእንቅልፍ ልምድ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው፡፡
የራዳር ሴንሰሩ በተጨማሪም ስለ እንቅልፍ ጠቀሜታ እና ክትትል የተለያዩ መረጃዎችን የሚሰጥና ከእንቅልፍ ጋር የተያያዙ ጤና ነክ ጉዳዮችን የሚያስገነዝብ ዝንደሆነ የመረጃ ምንጫችን ጠቆሟል፡፡ ስለ ቴክኖሎጂው ተጨማሪ ጥያቄዎችን ተጠይቆ መልስ መስጠት ያልፈለገው አማዞን ቴክኖሎጂው ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዳልሆነ ግን አሳውቋል፡፡
ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ አማዞን ከሰዎች ጤናና ደህንነት ጋር የተያያዙ ቴክኖሎጂዎችን በመስራት ላይ መጠመዱ የሚታወቅ ነው፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-07-amazon.html
ችግሩ የቀጠለው የ787 አውሮፕላን ምርት
*****************
ቦይንግ ኩባንያ በ787 አውሮፕላን ላይ ከዚህ ቀደም ከተገኘበት በተጨማሪ ሌላ መዋቅራዊ ችግር በመገኘቱ በብዛት እንዳይመረት እገዳ ጣለ፡፡ በአሁኑ ወቅት በወር 5 ጀቶችን እያመረተ ያለው ቦይንግ ትክክለኛ ቁጥሩን ባይናገርም የምርት ሂደቱን እንደሚቀንስ አሳውቋል፡፡

በተያዘው አመት ውስጥ 156 አውሮፕላኖችን ከተለያዩ አይነት ሞዴሎች ያመረተ ሲሆን በ2020 በአጠቃላይ 157 አውሮፕላኖችን አምርቶ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት እንደ አሜሪካው የአቪየሽን አስተዳደር መረጃ ከሆነ በአውሮፕላን ክፍሎች መገጣጠሚያዎች አካባቢ የተለያዩ ክፍተቶች በምርመራ ተገኝተዋል፡፡ በዚህም ቦይንግ ችግሩ የተገኘባቸውን አውሮፕላኖች እንደገና እንዲያያቸው አሳስቧል፡፡

በአሜሪካ የሚመረቱት 737 ማክስና ቦይንግ 787 ከኤሌክትሪክ እና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ካለፈው አመት ጀምሮ ታግደው የቆዩ ሲሆን ከአምስት ወራት ቆይታ በኋላ የ787 የምርት ሂደት ቀጥሎ ነበር፡፡

የአውሮፕላን አምራች ድርጅቱ 146 ጄቶችን ትእዛዝ የተቀበለ ሲሆን ይህም በገዥዎች የተሰረዙና የሞዴል ለውጥ የተደረገባቸውን ትዕዛዞች ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡
ምንጭ Reuters
ተጨማሪ ንባብ https://www.reuters.com/business/aerospace-defense/boeing-cuts-787-production-new-structural-problem-discovered-2021-07-13/?utm_campaign=trueAnthem%3A%20Trending%20Content&utm_medium=trueAnthem&utm_source=facebook&fbclid=IwAR1eCtxmPPy2k1Hs7E1olkOxFNPO5dB7MfvaggzAbYeWX_X0Ps35UkvBRpQ
እንደ ወረቀት የሚተጣጠፈው በረዶ
እንደ ወረቀት የሚተጣጠፈው በረዶ
============
ለወትሮው በረዶዎችን ለማጠፍ መሞከር ሰባብሮ ከመጣል ባለፈ የሚያመጣው ውጤት አልነበረም፡፡ ሆኖም በረዶዎች እጅግ ትንሽ ሆነው ሲሰሩ ቀድሞ ከምናውቀው ተሰባሪነታቸው በተቃረነ መልኩ መተጣጠፍ እንደሚችሉ አዲስ ጥናት አረጋገጠ፡፡ ከዚህም ባለፈ ተጣጣፊውን በረዶ ያገኙት ተመራማሪዎች ግኝቱ የበረዶዎችን ተፈጥሮ በልዩ መልኩ ለመረዳትና ለተሻሻለ የብርሃን ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂ መነሻ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
በሀሳብ ደረጃ ከተመለከትነው በተፈጥሮ ተገኝቶ በመላው ዓለም ተሰራጭቶ ያለው በረዶ ተመራማሪዎቹ እንደሰሩት በረዶ ሁሉ ተጣጣፊ መሆን የሚችል ቢሆንም እንደ ስንጥቃት ያሉ ችግሮች ለመሰባበር ቅርብ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
አንድ በረዶ ለመተጣጠፍ የሚያስችል ቁመና ያለው የበረዶው ይዘት 15 በመቶ ነው፡፡ ይህ ማለት አንድ በረዶ የቁመቱን 15 በመቶ በሚሆን ልክ መታጠፍ ይችላል፡፡ ከዚህ ቀደም ግን አንድን በረዶ ማጠፍ የተቻለው በ0.3 በመቶ ብቻ ነበር፡፡ በአዲሱ ጥናት ላይ ታድያ ተመራማሪዎቹ በበረዶውቹ ውስጥ ያሉ መዋቅራዊ ተግዳሮቶችን በተቻለ መጠን ካስወገዱ በኋላ የበረዶ ማይክሮ ፋይበሮቹ በ10.9 በመቶ መታጠፍ እንዲችሉ አድርገዋቸዋል፡፡
ይህን ተጣጣፊ በረዶን ለመስራት ተመራማሪዎቹ ከዜሮ በታች 50 ዲግሪ ሴሊሺየስ በሆነው እጅጉን ቀዘቀዛ የበረዶው ክፍል ውስጥ ውሃ ተከውበታል፡፡ የውሃ ሞለኪውሎች ጥቂትም ቢሆን የሀይድሮጅን አተሞቻቸው በሚገኙበት ስፍራ ፖዘቲቭ ቻርጅ፤ የኦክስጅን አተም ባለበት ሌላኛው በኩል ደግሞ ኔጋቲቭ ቻርጅ ያላቸው ሲሆን ይህም በቻርጅ አማካኝነት ስፋታቸው በተወሰኑ ማይክሮ ሜትሮች የሚለካ አነስተኛ ፋይበሮችን ይፈጥራል፡፡
አነስተኛ መጠን በመያዛቸውና በፍጥነት የሚዋቀሩ በመሆናቸው ፋይበሮቹ ያላቸውን መዋቅራዊ ጉድለት ሊቀንስ ችሏል፡፡ ተመራማሪዎቹም ፋይበሮቹን ከዜሮ በታች ከ70 እስከ 150 ዲግሪ ካቀዘቀዙ በኋላ በረዶዎቹ 180 ዲግሪ ወይም ግማሽ ክብ በሚሆን መጠን መታጠፍ እንደሚችሉ አረጋግጠዋል፡፡ የበረዶውን መዋቅር በመመርመርም የፋይበሩ ክፍሎች ጫና ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ የተለየና የተጠቀጠቀ ቅርፅን እንደሚይዙ ቡድኑ አሳይቷል፡፡ ይህም ነው እንደ ተመራማሪዎቹ ድምዳሜ ጫናን እንዲቋቋሙ ያስቻላቸው፡፡
ከዚህም ባለፈ ተመራማሪዎቹ በረዶዋቸው እንደ መስታውት የጠራ በመሆኑ በአንዱ ጫፍ ብርሃን አብርተውበት ብርሃኑን አስተላልፎ በሌላኛው ጫፍ ማሳየት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፤ Live Science
ለተጨማሪ፤ https://www.livescience.com/scientists-make-bendy-ice.html
ሁለት የኮቪድ ዝርያዎች በአንድ ላይ
ሁለት የኮቪድ ዝርያዎች በአንድ ላይ
***************
አንዲት ሴት በአንድ ጊዜ በሁለት የኮቪድ ዝርያዎች በመያዟ መሞቷ ተነገረ፡፡ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ በአለማችን ላይ ከፍተኛ የሰው ህይወት መጥፋት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች ያደረሰ እና በማድረስ ላይ ያለ ወረርሽኝ ነው፡፡ ለወረርሽኙ የተለያዩ ክትባቶች ተገኝተው በተለይ ያደጉ ሀገራት ዜጎቻቸውን ከአንዴም ሁለቴ መከተብ መቻላቸውና አሁንም እየከተቡ ያሉ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ቫይረሱ ባህሪውን እየለወጠና ዝርያውን እያሻሻለ ጉዳት ማድረሱን ቀጥሏል፡፡

ሰሞኑን የወጣ አንድ መረጃ ደግሞ እስካሁን ከተሰሙት ለያት ያለ ሆኗል፡፡ ይኸውም አንዲት ቤልጄማዊት እናት በሁለት የተለያዩ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች በአንድ ጊዜ በመያዟ ህይወቷ አልፏል የሚል ነው፡፡ ከአውሮፓ ክሊኒካ ማይክሮ ባዮሎጂና ተላላፊ በሽታዎች ኮንግረስ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የወረርሽኙ መከሰት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ የታወቀ ተመሳሳይ ክስተት የለም፡፡

የ90 አመቷ አዛውንት ሴት በመጋቢት ወር ወደ ሆስፒታል የተወሰደች ሲሆን ከቆይታ በኋላ በተደረገላት ጥብቅ ምርመራ በመጀመሪያ በእንግሊዝ የተከሰተው አልፋ የተሰኘ ዝርያ ሲገኝባት በተጨማሪ ምርመራም በደቡብ አፍሪካ የተገኘው ቤታ ዝርያ ተገኝቶባታል፡፡ በወቅቱ ሁለቱ የቫይረስ ዝርያዎች በቤሊጀም ውስጥ ተስፋፍተው ነበር፡፡

አዛውንቷ መጀመሪያ ሆስፒታል ሲገቡ ከተወሰነ የመተንፈሻ አካል ችግር ውጭ እምብዛም የህመም ስሜት ያልነበራት ቢሆን ሆስፒታል ከገባች በኋላ ግን በከባድ ህመም መሰቃየት ጀምራለች፡፡ ሆስፒታል ከገባች በኋላ በአምስተኛው ቀን ያረፈችው ቤልጄማዊቷ በፍጥነት ለተባባሰው የጤና ሁኔታዋ ብሎም ለሞት የዳረጋት ሁለት የኮቪድ ዝርያዎች በአንድ ላይ መገኘታቸው እንደሆነ ተመራማሪዎች ይፋ አድርገዋል፡፡
ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/health-and-medicine/a-woman-has-died-after-being-infected-with-two-covid19-variants-at-once/?fbclid=IwAR3_YZ-FsPt4dtoX3FpWIElcdNA9vAU74kBTluqGXMLws-Yng4EKa7ZFk_w