TechIn2
1.16K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
በኤሌክትሪክ የሚሰራ አውቶቢስ በደቡብ አፍሪካ
በኤሌክትሪክ የሚሰራ አውቶቢስ በደቡብ አፍሪካ
************************************************
የትራንስፖርት አገልግሎት ማህበረሰቡን ከቦታ ቦታ በማንቀሳቀስ ሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት እንዲኖረው ከዚያም አነስ ሲል ሰዎች እለታዊ ተግባራቸውን በአግባቡ መከወን እንዲችሉ ያደርጋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ለትራንስፖርት የምንጠቀምባቸው መጓጓዣዎች ከተፈጥሮ ጋር የማይስማማ መገለጫ አላቸው ይኸውም የአየር ብክለት ነው፡፡ በአለማችን የተለያዩ ሀገራት ያላቸውን የካርቦን ልቀት ለመቀነስ ወይም ዜሮ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል በካይ ያልሆኑ መጠቀሚያዎችን ወደ አገልግሎት ማቅረብ አንደኛው ነው፡፡

በመጓጓዣው ዘርፍ ከመኪኖች የሚወጣው በካይ ጋዝ ከፍተኛ የሆነ የአየር ብክለት በተለከይ በከተሞች አካባቢ እንዲኖር ያደርጋል፡፡ በመሆኑም በከተሞች አካባቢ የህዝብ ትራንስፖርትን መጠቀም እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ይህም በመንገድ ላይ የሚንቀሳቀሱ የትራንስፖር አማራጮችን ቁጥ በመቀነስ የአካባቢን የመበከል መጠን መቀነስ ያስችላል፡፡

የህዝብ ትራንስፖርትን መጠቀም የብክለት መጠንን ቢቀንስም ሙሉ ለሙሉ ስለማይስቀር አሁንም ሌሎች አማራጮችን መጠቀም በጣም ተገቢ ነው፡፡ ለዚህ ነው የተለያዩ ሀገራት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የህዝብ ትራንስፖርት መኪኖችን ለመጠቀም ጥረቶችን እያደረጉ ያሉት፡፡ የአህጉራችን ባለ ከፍተኛ ኢኮኖሚ ሀገር ደቡብ አፍሪካም ይህንን የአየር ብክለትን ለመቀነስ የሚደረግ ጥረትን የተቀላቀለች ይመስላል፡፡ ደቡብ አፍሪካ ለሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ አውቶቢስ የህዝብ አውቶቢስ ስራ አስጀምራለች፡፡

ለ12 ወራት ያክል ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሁለት አውቶቢሶች በሙከራ የቆዩ ሲሆን ብዙ አስቸጋሪ ነገሮችን እንዳሳለፉም ተነግሯል፡፡ ሆኖም ግን የሙከራ ጊዜው የተሳካ እና ተገልጋዮች ትራንስፖርቱን በሚጠቀሙበት ጊዜ ምቾት እንደሚሰማቸው ጎልደን አሮው የተሰኘው የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት ተናግሯል፡፡ ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት ከ 1000 በላይ አውቶቢሶችን እያስተዳደረ ሲሆን በቀንም እስከ 250 ሺህ ተጓዦችን ለማመላለስ አቅዷል፡፡
ምንጭ cgtn
ተጨማሪ ንባብ https://africa.cgtn.com/2021/07/06/south-africas-first-active-electric-bus-launched-in-cape-town/?fbclid=IwAR2-ra7vlDYs7Cg3vCYiie-XhBr7ByiJvkCR2OrZhQQRJYeayXlfqZiqHCc
ቻይና የወባ በሽታን ሙሉ ለሙሉ ማጥፋቷን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
===========
የዓለም ጤና ድርጅት ቻይና የወባ በሽታን ከምድሯ ሙሉ ለሙሉ ማጥፋቷን ባሳለፍነው ሳምንት አስታውቋል፡፡ ቻይና ሙሉ ለሙሉ የወባ በሽታን ካስወገዱ ሀገራት ውስጥ ስሟ የሰፈረላት 40 ኛዋ የዓለማችን ሀገር ስትሆን በምዕራብ ፓስፊክ አካባቢም ከአውሮፓውያኑ 1987 በኋላ ይህን እውቅና ያገኘች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡
ምንም እንኳን ከአውሮፓውያኑ 2017 አንስቶ በቻይና ውስጥ ምንም ዓይነት በወባ የተያዘ ሰው ተገኝቶ ባያውቅም የዓለም ጤና ድርጅት የወባ ነፃ ዕውቅናን የሚሰጠው የሀገር ውስጥ የወባ ስርጭት ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ሳይመዘገብ ሲቀር በመሆኑ ነው ዕውቅናው እስካሁን የዘገየው፡፡ በተጨማሪም ዕውቅናውን ለማግኘት አንድ ሀገር በሽታው ዳግም እንዳይከሰት የማድረጊያ ዕቅድ ሊኖራት ያስፈልጋል፡፡ ታድያ ይህ የዓለም ጤና ድርጅት ዕውቅና በሀገሪቱ ደቡብ ምዕራባዊ ክፍል የሚገኘው ዩናን ግዛት የበሽታው ስርጭት አሁንም ድረስ ካለባቸው ሦስት የጎረቤት ሀገራት ጋር የሚዋሰን እንደመሆኑ የዕውቅናውን ቦታ ከፍ አድርጎታል፡፡
ዘገባዎች እንደሚያሳዩት የዛሬ ስልሳና ሰባ ዓመታት ገደማ ቻይና 30 ሚሊዮን ያህል ዜጎቿ በየዓመቱ በወባ በሽታ ይያዙባትና ከመካከላቸውም አንድ በመቶ የሚሆኑት ለህልፈተ ህይወት ይዳረጉ ነበር፡፡ ባለፉት ሰባት አስርት ዓመታት ውስጥ ታድያ ሀገሪቱ የወባን ስርጭት የሚገድቡና በሽታውን የሚያክሙ ልዩ ልዩ ስትራቴጂዎችን ቀርፃ ተንቀሳቅሳለች፡፡ ከነዚህም ውስጥ የሀገሪቱ መንግስት በአውሮፓውያኑ 1967 ያስተዋወቀው ፕሮጀክት 523 ተብሎ የሚጠራው 500 ያህል ተመራማዎችን ከመላው ቻይና በማሰባሰብ የተከወነ ምርምር ይገኝበታል፡፡ እንቅስቃሴው ውጤታማ የሆነ ፀረ ወባ እንዲገኝ ሲያደርግ ግኝቱም በ2015 በህክምናው ዘርፍ የኖቤል ሽልማት እንዲቀዳጅ ሆኗል፡፡ በተጨማሪም ቻይና የዓለም ጤና ድርጅት እንኳን አጎበሮችን እንደ መከላከያ መንገድ መጠቆም ከመጀመሩ በፊት ነው 1980ዎቹ በፀረ ወባ የታከሙ አጎበሮችን በመላው ሀገሪቱ ማሰራጨት የጀመረችው፡፡
እነዚህ ሁሉ ፀረ ወባ እንቅስቃሴዎች ተደማምረው በ1990ዎቹ በቻይና ያለው በወባ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በ95 በመቶ ቢቀንስም ወባ ችግር መሆኑ ግን አልቆመም ነበር፡፡ ከ10 ዓመት በፊት 2011 የሀገሪቱ መንግስት ወባን ጨርሶ የማጥፋት ዕቅድን ይፋ ሲያደርግ ከአንድ አመት በኋላ ደግሞ 1-2-7 የተባለ ስትራቴጂን አስተዋወቀ፡፡ በ1-2-7 ስትራቴጂ መሰረት በየአካባቢው የሚገኙ የጤና ተቋማት በወባ የተያዙ ሰዎች ሲገኙ በአንድ ቀን ውስጥ እንዲያሳውቁ፣ በሦስት ቀናት ውስጥ ምርመራ እንዲያደርጉ እንዲሁም በሰባት ቀናት ውስጥ ስርጭትን የሚገድቡ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ይገደዳሉ፡፡
ይህ የቻይና በረጅም ዓመታት ተከታታይ ስራዎች የተገኘው ድል በአሁኑ ሰዓት የዓለማችን 94 በመቶውን የወባ በሽታ ስርጭት መገኛ ለሆኑት የአፍሪካ ሀገራት በምሳሌነት ተወስዶ ሊሰራበትና ልምድ ሊሆን እንደሚገባ ተነግሯል፡፡
ምንጭ፤ The Scientist
ለተጨማሪ፤ https://www.the-scientist.com/news-opinion/china-is-malaria-free-says-world-health-organization-68938?utm_content=171635895&utm_medium=social&utm_source=twitter&hss_channel=tw-18198832
ቻይና የወባ በሽታን ሙሉ ለሙሉ ማጥፋቷን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
በትንፋሽ ብቻ ኮቪድ 19 እንዳለብን የሚነግረን ስማርት ማስክ
በትንፋሽ ብቻ ኮቪድ 19 እንዳለብን የሚነግረን ስማርት ማስክ
===========
የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ እና ማሳቹሴት ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ አጥኚዎች የሰሩት አዲስ ማስክ እራስን ከኮቪድ 19 ከመጠበቅም ባሻገር በትንፋሽ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ (ሳርስ-ኮቭ-2) መኖሩን ማረጋገጥ ይችላል፡፡ አጥኚዎቹ ይህን ማድረግ የቻሉት ባዮ ሴንሰሮችን ከማስኩ ጋር በማገናኘት ሲሆን ማስኩም በቤተ-ሙከራ ከሚሰራ ምርመራ ጋር የሚስተካከል ውጤትን በ90 ደቂቃዎች ውስጥ ብቻ እንደሚሰጥ ተነግሮለታል፡፡
ባዮሴንሰሮች ከዚህ ቀደምም በሌላ የህክምና መሳርያ ላይ ጥቅም ላይ ውለው የነበሩ ቢሆንም መሳርያው በህይወት ያሉ የታነፁ ባክቴሪያዎችን ተጠቅሞ ነው የባዮሎጂያዊ ሪያክሽንን የሚቀሰቅሰውና በሽታ አስተላላፊ አካላት መኖራቸውን የሚያመላክተው፡፡ ሆኖም ባክቴሪያዎቹን ለተራዘመ ጊዜ በህይወቴ ማቆየቱ አስቸጋሪ ስለሆነ የመሳርያውን ብቃት ገድቦት ቆይቷል፡፡
በሀርቫርድ እና ማሳቹሴት ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ አጥኚዎች ታድያ ከህዋሶቹ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑትን ባዮሎጂያዊ ቁሶች በማውጣት አቀዝቅዘው አደረቋቸው፤ በሂደቱም ከባዮሎጂያዊ ቁሶቹ ውስጥ ውሃውን በመምጠጥ አወጡት፡፡ በዚህም ውሃ ሲጨመርበት ብቻ ዳግም የሚነቃ ባዮሎጂያዊ ቁስ መፍጠር ችለዋል፡፡
ማስኩ አንድን ቁልፍ ተጭኖ ውሃን በመልቀቅ ብቻ ሦስት የተለያዩ ባዮሎጂያዊ ሪአክሽኖች በተከታታይ ይሰጣል፡፡ የመጀመሪያው ሪአክሽን የሳርስ-ኮቭ-2 ቫይረሶችን ሜንብሬን በመስበር አርኤንኤያቸውን ያጋልጣል፡፡ ሁለተኛው ሪአክሽን ደግሞ የቫይረሱ የፕሮቲን እሾሆችን ኢንኮድ የሚያደርገውን በራሒ ኮፒ ሲያደርግ ሦስተኛው በበኩሉ የእሾሆቹን በራሂ በመለየት የፍሎረሰንት ሞለኪውሎችን አክቲቬት ያደርጋል፡፡
ሆኖም ቴክኖሎጂው የራሱ ውስንነቶች አሉበት፡፡ ለምሳሌ ባዮሴንሰሮቹ አንዴ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆኑ በእርጥበታማ አየር ውስጥም እንደልብ ላይሰሩ ይችላሉ፡፡ በአንፃሩ ዋጋቸው አነስተኛ መሆኑ በከፍተኛ መጠን ማምረቱን ቀላል አድርጎታል፡፡
ምንጭ፤ Cosmos
ለተጨማሪ፤ https://cosmosmagazine.com/health/covid/smart-masks-to-detect-covid-19/?utm_content=buffere055e&utm_medium=social&utm_source=twitter.com&utm_campaign=buffer
የአሜሪካን ጦር ኃይል እርጅናን የሚያስቀሩ መድሃኒቶችን ሊሞክር ነው
የአሜሪካን ጦር ኃይል እርጅናን የሚያስቀሩ መድሃኒቶችን ሊሞክር ነው
=============
በቴክኖሎጂ በተራቀቀው በዚህ ዘመን ቀድሞ በሆሊውድ ፊልሞች አልያም ሳይንሳዊ ልብ ወለድ መፅሐፍት ላይ የተመለከትናቸው ምዕናባዊ ፈጠራዎችን ከዓመታት በኋላ በእውኑ አለም ተግባራዊ ሲሆኑ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ ከወደ አሜሪካንም ተመራማሪዎች ለወትሮ በፊልም ላይ የምናውቀውን ሳይንሳዊ ግኝት እውን ለማድረግ በመንደርደር ላይ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡
በአሜሪካን ጦር ኃይል ስር የሚገኘው የልዩ ተልእኮ እዝ (SOCOM) ከቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት አንስቶ እርጅና በወታደሮቹ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕንዖ ያጠፋሉ የተባለላቸውን ኪኖኖች መሞከር እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡ የሰው ልጆችን አካላዊ አቅም የማሳደግና ወታደሮችንም ጤናማና ለረጅም ጊዜያት በከፍተኛ ብቃት እንዲያገለግሉ የማድረግ አላማን አንግቦ የተነሳው ሙከራው ውጤታማነቱ ታይቶ ምናልባትም ለሲቪሎች ህክምናም ሊውል እንደሚችል ተዘግቧል፡፡
ኪኒኖቹ ስራቸውን የሚሰሩት ከሰው ልጅ እርጅና እና የአካል ብቃት መውረድ ጋር የሚያያዘውን ኒኮቲናማይድ አዴኒን ዲኒውክላታይድ (NAD+) የተሰኘ ኮኤንዛይም በማጠናከር ነው፡፡ የልዩ ተልእኮ እዙ ታድያ በወታደሮቹ የሰውነት ስርዓት ውስጥ ተጨማሪ ኒኮቲናማይድ አዴኒን ዲኒውክላታይድን በማከል ከዕድሜ ጋር የተያያዙ ጉዳቶችን ለመቀነስ ብሎም አካላዊና አዕምሮአዊ ዝግጁነትን በማሻሻል በእድሜ ብዛት እየቀነሰ የሚመጣ የወታደሮች ብቃት መውረድን ለመከላከል አቅዷል፡፡
እንደ እዙ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር ሊሳ ሳንደርስ ምልከታ ሙከራው ስኬታማ የሚሆን ከሆነ እርጅናን በማዘግየትና በእድሜ አመሻሽ ላይ የሚከሰት ጉዳትን በመቀነስ የሚያስደንቅ ልዩነት ፈጣሪ ይሆናል፡፡
ምንጭ፤ Futurism
ለተጨማሪ፤ https://futurism.com/neoscope/military-test-antiaging-pill
የሩሲያው የቴክኖሎጂ ካምፓኒ ሮቦት
*********************************
የሩሲያው ያንዴክስ የቴክኖሎጂ ካምፓኒ የተለያዩ መልእክቶችን ወደ ሰዎችና ተቋማት የሚያደርስ ሮቦትን በአሜሪካ ስራ ሊያጀምር እንደሆነ ተነገረ፡፡ ካምፓኒው ራስ ነድ የሆኑ ሮቦቶችን በተለያዩ ኮሌጆች ውስጥ ለማሳመራት ማቀዱን ነው ያሳወቀው፡፡ በመግለጫውም የሩሲያው ካምፓኒ በአሜሪካ ከ250 በላይ የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ግቢዎች ውስጥ የእቃ ማድረስ አገልግሎት እየሰጠ ካለው ግሩብሃብ ጋር በጋራ ለመስራት ማቀዱን ተናግሯል፡፡
የያንዴክሱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዲሜትሪ ፖሊሽቸክ ብዛት ያላቸው ሮቦቶችን በመጠቀም የቴክኖሎጂ ምርቶቹን በስፋት ለማስተዋወቅ ማቀዳቸውን አሳውቀዋል፡፡ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሮቦቱ መድረሱን በመልዕክት የሚያውቅ ሲሆን የስልክ መተግበሪያን በመጠቀም የሮቦቱን እቃ ማስቀመጫ መክፈት ይችላል፡፡ ይሀንንም በማድረግ የተላከለትን እቃ ይረከባል፡፡
ከግሩብሀብ በኩል ደግሞ ከሩሲያው ካምፓኒ ጋር በመሆን ተማሪዎች በተለይ ምግብ ለማስመጣት ያለባቸውን ችግር ለመቅረፍ በሰፊው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ በኮሌጆች ውስጥ የሚገኙ መንገዶች መኪና ለማሳለፍ የማይበቁ ቢሆኑም የሩሲያው የቴክኖሎጂ ካምፓኒ ምርት ግን በቀላሉ መንቀሳቀስ እንዲችል ተደርጎ የተሰራ መሆኑን የካምፓኒው ባለቤቶች ይፋ አድርገዋል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-07-russia-yandex-delivery-robots.html
ዶናልድ ትራምፕ አፈና አድርጋችሁብኛል ሲሉ ፌስቡክ፣ ጉግል እና ትዊተርን ከሰሱ
ዶናልድ ትራምፕ አፈና አድርጋችሁብኛል ሲሉ ፌስቡክ፣ ጉግል እና ትዊተርን ከሰሱ
=============
የቀድሞው የአሜሪካን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያለ አግባብ ድምፄን አፍናችኋል በማለት በፌስቡክ፣ ትዊተር፣ እና ጉግል ላይ ክስ መመስረታቸውን አስታወቁ፡፡ በካፒቶሉ ነውጥ የተነሳ የማህበራዊ ገፆቻቸውን ማገዳቸውን ተከትሎ ለወራት ከነዚህ ታላላቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር እሰጣገባ ውስጥ የቆዩት የ75 ዓመቱ ሪፐብሊካን ተቋማቱ ሕገ-ወጥ እና ሕገ-መንግስታዊ ያልሆነ አፈናን ወደማድረግ ተሸጋግረዋል ሲሉ ወቅሰዋቸዋል፡፡

ፌስቡክ የካፒቶሉ ነውጥ በተነሳ በማግስቱ ነበር ነውጡን አነሳስተዋል ሲል የቀድሞ ፕሬዘዳንቱን የፌስቡክ ገፅ ያገደው፡፡ ብዙም ሳይቆይ ትዊተርም ይህን የፌስቡክ ውሳኔ በመከተል ተጨማሪ አመፅ እንዳይነሳ ያሰጋል በሚል ምክንያት እንዲሁ አግዷቸዋል፡፡ በገለልተኛ ቦርድ አማካኝነት ውሳኔውን መለስ ብሎ የተመለከተው ፌስቡክ ታድያ የዛሬ ወር ገደማ እገዳውን በ2 ዓመት ማፅናቱ ይታወሳል፡፡ ከነዚህ በተጨማሪም ዩትዩብ እና ባለቤት ድርጅቱ ጉግል ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተያያዙ ተንቀሳቃሽ ምስሎቼን አጥፍተዋል ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ ይከሳሉ፡፡

ጉግል፣ ፈፌስቡክ እና ትዊተር አባል የሆኑበት የኮምፒውተር እና ኮምዩኒኬሽን ሕብረት የዲጂታል አገልግሎት ሰጪዎች የራሳቸውን ደንቦች ተፈፃሚ የማድረግ መብት እንዳላቸው ይናገራል፡፡ በአንፃሩ ደቡባዊ ፍሎሪዳ ውስጥ በሚገኝ ፍርድ ቤት ክሳቸውን ያቀረቡት ዶናልድ ትራምፕ “ማሸነፍ የምንችልበት ሙግት ውስጥ ነው የገባነው” ብለዋል፡፡ አክለውም ይህ ገና ጅማሮው ነው ባሉት ክስ “ስለ እያንዳንዱ አሜሪካዊ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በመቆም ለአሜሪካን ዲሞክራሲ እየቆምን ነው” ብለዋል፡፡

ሆኖም በሕገ አዋቂዎች ዘንድ ክሱ ያን ያህል ፍሬ አያፈራም የሚል አስተያየትን አስተናግዷል፡፡ በሳንታ ክላራ ዩኒቨርሲቲ የሀይ ቴክ ሎው ኢንስቲትዩት ዳይሬክተሩ ኤሪክ ጎልድማን እንደሚሉት በህገ መንግስቱ ላይ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ጭምር የሚደነግጉት የመጀመሪያ ማሻሻያ ተብለው የሚታወቁት የሕግ ማዕቀፎች የመንግስት አካላትን እንጂ የግል ተቋማትን አይመለከቱም በማለት ከዚህ ቀደም ሌሎች ተመሳሳይ ክሶችም ውድቅ መደረጋቸውን በምሳሌነት ያነሳሉ፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ያነሱት ክስ ታድያ እገዳውን ያስተላለፉት የቴክኖሎጂ ተቋማት ከፌደራል መንግስቱ ጋር በትብብር እንደመስራታቸው ስፍራቸውን ከግል ኩባንያነት ወደ ሀገራዊ ሚና ተጫዋችነት ተሸጋግረዋል ሲል ይሞግታል፡፡

ምንጭ፤ Tech Xplore
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-07-trump-anti-censorship-lawsuit-facebook-twitter.html
በርካታ ፈጠራዎችን ይዞ የመጣው ታዳጊ የፈጠራ ባለሙያ፤ ኢዘዲን ካሚል
===========
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገራችን ብቅ ብቅ ካሉ ተስፈኛ የፈጠራ ባለሙያዎች ውስጥ ስሙ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፤ ኢዘዲን ካሚል፡፡ ከልጅነት ጊዜው አንስቶ ትርፍ ጊዜውን ከጨዋታ ይልቅ ወደ ፈጠራ የሚያውለው ዛሬ ላይ በአራት የተለያዩ ዘርፎች 36 የፈጠራ ስራዎች እና 8 የተንቀሻቃሽ ስልክ መተግበሪያዎችን ማበርከት ችሏል፡፡ ለዚህም የተለያዩ አድናቆት እና ሽልማቶችን ከሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር አንስቶ እስከ አለም አቀፍ ተቋማት ደረስ አግኝቷል፡፡
ከነዚህ የኢዘዲን ፈጠራዎች መካከል በፀሐይ እና ኤሌክትሪክ ቻርጅ የሚንቀሳቀስና አንድ ጊዜ ቻርግ ተደርጎ እስከ 46 ኪ.ሜ መጓዝ የሚችል ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪ እንዲሁም የስብሰባ አዳራሾች፣ እምነት ተቋማት እና ሌሎችም የድምፅ ረብሻ በማይወደድባቸው ስፍራዎች ውስጥ ሲገባ የስልክ መጥሪያ ድምፅን የሚያጠፋ ቴክኖሎጂ ይገኙበታል፡፡ ታድያ እነዚህን የፈጠራ ስራዎች ሰርቶ ከማስቀመጥ ባሻገር ወደ ምርት እና አገልግሎት ተለውጠው ችግር እንዲፈቱ፣ ስራ እንዲፈጥሩና ሐብት እንዲያመነጩ በማሰብ አይከን አፍሪካ የተባለ የራሱን ድርጅት አቋቁሞ እየሰራ ይገኛል፡፡
ውድ ተከታታዮቻችን ለዛሬ ከሳምንታዊው ቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራማችን የወሰድነውን ይህን ባለ ብሩህ ተስፋ ታዳጊ የሚያስቃኝ አጭር መሰናዶ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ በዛሬው የክፍል ፩ መሰናዶዋችን ስለ ፈጠራ ስራዎቹ፣ ጊዜ አጠቃቀሙ እንዲሁም የፈጠራ ስራዎችን እንዲሰራ ያነሳሱት ሁለት አባይት ጉዳዮችን እንመለከታለን፡፡
የዩትዩብ ቻናላችንን በመጎብኘት ሌሎች ይህን መሰል ተስፈኛ ታዳጊዎችን መመልከት ይችላሉ https://www.youtube.com/watch?v=iKPpZWnoxiI&t=17s
ቻይና የአዳዲስ ህንፃዎቿ ቁመት ከ500 ሜትር እንዳያልፍ አገደች
ቻይና የአዳዲስ ህንፃዎቿ ቁመት ከ500 ሜትር እንዳያልፍ አገደች
====================
ቻይና በምድሯ የሚገነቡ አዳዲስ ህንፃዎቿ ቁመታቸው ከ500 ሜትር እንዳያልፍ የሚያግድ ደንብ አወጣች፡፡ በብሔራዊ ልማት እና ሪፎርም ኮሚሽን አማካኝነት የወጣው ይህ እገዳ በተጨማሪነትም ቁመታቸው ከ250 ሜትር በላይ የሆኑ ህንፃዎች መገንባትን የገደበ ሲሆን ህንፃዎች ከዚህ ቁመት በላይ እንዲገነቡ ከተፈቀደላቸውም ከእሳት አደጋ ደህንነትና ሌሎች ጉዳዮች አንፃር ንድፋቸው በሀገሪቱ የቤት እና ከተማ-ገጠር ልማት ሚኒስቴር አስገምግመው ይሆናል፡፡ ከ100 ሜትር በላይ ሆነው የሚገነቡ ረጃጅም ህንፃዎችም ቢሆን መሬት መንቀጥቀጥን ከመቋቋም አንፃር ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚገጥማቸው ተነግሯል፡፡

ካለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ወዲህ የብዙ ረጃጅም ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ባለቤት የሆነችው ቻይና የተለያዩ ሪል እስቴት አልሚዎች ቁመታቸው ከ600 እስከ 800 ሜትር የሚደርሱ ንድፎችን በተደጋጋሚ ይዘው ለግንባታ የሚሯሯጡባት ሀገር ነች፡፡ ምንም እንኳን የዓለማችን ረጅሙ ህንፃ በዱባይ የተገነባው ባለ 828 ሜትሩ ቡርጅ ከሊፋ ይሁን እንጂ ከዓለማችን 10 ረጃጅም ህንፃዎች ውስጥ 5ቱ መገኛቸው ሀገረ ቻይና ነው፡፡ እነዚህም ውስጥ ቡርጅ ከሊፋን ተከትሎ በ632 ሜትር ቁመት የዓለማችን ሁለተኛው ረጅሙ ህንፃ የሆነው ሻንጋይ ታወር፣ የሸንዘኑ ፒን አን ፋይናንስ ማዕከል (599 ሜትር) እና በቤጂንግ ያለው ሲአይቲአይሲ ታወር (527.7 ሜትር) ይገኙበታል፡፡ ከዚህም ባሻገር ቻይና በዓለማችን ከሚገኙት ቁመታቸው 200 ሜትርን የሚበልጡ 1,478 ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ውስጥ 678ቱን ይዛለች፡፡

አዲስ የወጣው ደንብ እንዳመላከተው የየአካባቢው አስተዳደሮች የግንባታ ስራዎች ጥራት ያላቸውና ደህንነታቸው የተጠበቀ ከማድረግ አንፃር መልካም ስራ እየሰሩ ቢሆንም አሁንም ግን የደህንነት ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ ክፍተቶች እንዳሉ ይገልፃል፡፡ አያይዞም የሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ቁመት ከሚገነቡበት ከተማ ትልቀት እና እሳት አደጋን የመቆጣጠር ብቃት ጋር መስማማት መቻል እንዳለባቸው ቢሮው አስታውቋል፡፡

ምንጭ፤ Xinhuanet እና Global Times
ለተጨማሪ፤ http://www.xinhuanet.com/english/2021-07/08/c_1310049617.htm እና https://www.globaltimes.cn/content/1187981.shtml
የመጸዳጃ ቤት ቆሻሻን ወደ ሀይል ምንጭነት
********************************************
በደቡብ ኮሪያ አንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መጸዳጃ ቤት መጠቀም የቡና ወጭን መሸፈን የሚያስችል ገቢ እንደሚያስገኝ ተነገረ፡፡ በደቡብ ኮሪያ የኡልሳን ብሔራዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ፕሮፌሰር የሆኑት ቾ ጂ ዌኦን ከአካባቢ ጋር ተስማሚ የሆነና በተመሳሳይ ጊዜ ሐይልንና ተፈጥሯዊ ማዳበሪያን ማስገኘት የሚችን ስልትን ከህዝብ መጸዳጃ ቤት መስራት ችለዋል፡፡

ከመጸዳጃ ቤቱ ጋር የተያያዘው ቱቦ ጽዳጁን ወደ ተዘጋጀለት የምድር ውስጥ ማጠራቀሚያ ያስተላልፈዋል፡፡ ከዚያም የተጠራቀመው ጽዳጅ በደቂቅ ዘአካላት አማካኝነት በመብላላት ወደ ሚቴን ጋዝነት ይለወጣል፡፡ ይህ ጋዝም ባዮጋዝ በመሆን ለተለያዩ የሀይል ፍላጎቶች እንዲውል ይደረጋል፡፡

አንድ ሰው በአማካኝ በቀን 500 ግራም ጽዳጅ ያስወግዳል፡፡ ይህም በተሰራው ቤተ-ሙከራ አማካኝነት 50 ሊትር ሚቴን ጋዝ ማምረት ያስችላል፡፡ 50 ሊትር ሚቴን ጋዝ 0.5 kWh ኤሌክትሪክ ማመንጨት ያስችላል፡፡

በመሆኑም አንድ ሰው በዚህ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ሲጠቀም Ggool የተሰኘ ቨርቹዋል ክፍያ ያገኛል፡፡ ጂጉል በኮሪያ ቋንቋ ማር ማለት ነው፡፡ በቨርቹዋል ክፍያው ተከፋዩ ቡና ወይም ሙዝ መግዛት እንዲችል ተመቻችቷል፡፡ አንድ ሰው በመጸዳጃ ቤቱ ሲጠቀም 10 ጂጉል ያገኛል፡፡
ምንጭ Reuters
ተጨማሪ ንባብ https://www.reuters.com/world/asia-pacific/south-korean-toilet-turns-excrement-into-power-digital-currency-2021-07-09/?utm_campaign=trueAnthem%3A%20Trending%20Content&utm_medium=trueAnthem&utm_source=facebook&fbclid=IwAR1MINB3uR
በዛሬው የቴክ-ሳይንስ ዝግጅታችን
===========
ወደ ድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ አቅንተን በዩኒቨርሲቲው የተሰራውን የኢ-ለርኒንግ ኮምፒውተር ሲስተም የምናሳያችሁ ሲሆን እንዲሁ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አምርተንም ኢታኖልን አስመልክቶ በዩኒቨርሲቲው እየተሰራ ያለውን የምርምር ስራ እንመለከታለን፡፡

ከዩኒቨርሲቲዊቻችን ብዙም ሳንርቅ በተቋማት መሰናዶ አንጋፋው የሀረማያ ዩኒቨርሲቲን የምንዳስስና የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ፕ/ር ጨመዳ ፊኒንሳ ላይ የሚያተኩረው የተመራማሪዎች ታሪክ ሦስተኛ ክፍልም የሚቀርብ ይሆናል፡፡

በቴክኖሎጂ ታሪክም አለማችንን በእጅጉ እንደሚለውጥ ስለሚነገርለት የ5ጂ ቴክኖሎጂ የሚያውጠነጥን ዝግጅታችን ሰዓቱን ጠብቆ ወደ እናንተው ይደርሳል፡፡

እነዚህን አስተማሪ ዝግጅቶቻችንን ዛሬ ቅዳሜ በ10 ሰዓት MOE ቲቪ እንዲሁም በድጋሚ ማክሰኞ በተመሳሳይ ቻናል በተመሳሳይ ሰዓት ሊያገኙን ይችላሉ፡፡

ወደ ዩትዩብ ቻናላችንም ጎራ በማለት አዳዲሶቹን ጨምሮ እስከዛሬ የተሰሩትን ፕሮግራሞች በሙሉ መመልከት ይችላሉ https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg ፡፡
ወንዶች እንደ ሴት አርግዘው ልጅ የሚወልዱበት የእንስሳት ዓለም
ወንዶች እንደ ሴት አርግዘው ልጅ የሚወልዱበት የእንስሳት ዓለም
===========
ዓለማችን በብዙ ድንቅና አስራሚ ተፈጥሮአዊ ሁነቶች የተሞላች ናት፤ ሁሌም ጠልቀን በቃኘናት ቁጥር ይበልጥ አፍ በሚያስከፍት ተአምሯ የምትቀበለን ልዩ ትንግርት፡፡ ታድያ ለዛሬ ከነዚህ በተፈጥሮ በተለይም ከእንስሳት ዓለም ዘንድ ካሉ አስገራሚ የሚባልላቸው ነገሮች ውስጥ ወንዶች ልጆችን የሚያረግዙባቸውን እንስሳት በአጭሩ እናስቃኝዎ፡፡

በተለምዶ ከምንሰማው ውጪ ወንዶች የሚያረግዙት ሲንግናታዳይ ተብሎ በሚጠራው ቤተሰበ ውስጥ ያሉ ሦስት የዓሣ ዝርያዎች ማለትም የባህር ፈረስ፣ ፓይፕፊሽ እና የባህር ድራጎን አሳዎች ናቸው፡፡ የባህር ፈረስ እና ፓይፕፊሾቹ ልጆቻቸውን ሰውነታቸው ውስጥ ባለ የማሳደግያ ቦርሳቸው ውስጥ በማድረግ በኃይል እንደተሞላ ስብ ያሉ ልዩ ልዩ ንጥረ ነገሮችን በሕብረ ህዋሶቻቸው በኩል እየመገቡ በስተመጨረሻም ምስሉ ላይ እንደሚታየው ይወልዷቸዋል (የምር ይወልዳሉ)፡፡ የባህር ድራጎኖች በበኩላቸው እንቁላሎቹ በውጪኛው የጭራቸው ክፍል ላይ በማጣበቅ ነው ልጆቹን የሚያሳድጉት፡፡

የወንዶች ማርገዝ ጥቅሙ ምን ላይ ይሆን? ብለው ከጠየቁ ምላሹ ሴቶቹ ትኩረታቸውን በዋናነት እንቁላሎችን በማምረት ላይ ብቻ እንዲያደርጉና ልጅ የማሳደጉን ኃላፊነት ወንዶች እንዲወስዱት ለማድረግ ነው፡፡ እዚህ ላይ ግን ሌላው ግርምታን የሚያጭረው ጉዳይ የባህር ፈረሶች ጠዋት ላይ ልጃቸውን በሰላም ተገላግለው ማታ ላይ በድጋሚ ማርገዝ መቻላቸው ነው፡፡ ይህ ታድያ የዝርያው ቁጥር በማብዛት ህይወትን የማስቀጠል እድላቸውን እንዲያሳድጉ ይረዳቸዋል፡፡

ወንዶቹ ልጆቹን መያዛቸው ሴቶቹ እንቁላልን በመስጠት ላይ እንዲያተኩሩ ከማስቻልም ባሻገር ኃይል እንዲቆጥቡም ያደርጋቸዋል፡፡ እንቁላልን ለማምረት ሴቶቹ የሚያስፈልጋቸው ኃይል ወንዶቹ የዘር ፈሳሽን ለማምረት ከመያስፈልጋቸው የላቀ ነው፡፡ እናም እንቁላሎቹን የመንከባከቡን ድርሻ ወደ ወንዶቹ ማሻገሩ የኃይል አጠቃቀሙ በሁለቱ ፆታዎች መካከል በፍትሀዊነት እንዲከፋፈል ያደርገዋል፡፡

ታድያ አንባቢያችን፤ ሴቶች ልጅን በሆዳቸው አርግዘውና ለወራት ተሸክመው በስተመጨረሻም በስቃይ ከመውለድም ባሻገር አብዛኛውን ቤተሰባዊ ኃላፊነት ጫንቃቸው ላይ በሚወድቅባቸው በዚህ ዓለም ከዚህ የላቀ የጾታ እኩልነትን ምሳሌን ከየት ማግኘት ይቻላል?

ምንጭ፤ live science
ለተጨማሪ፤ https://www.livescience.com/weird-animals-evolution.html
እርሻ በሰማይ
እርሻ በሰማይ
=======
ታላቋ የሆንግ ኮንግ ከተማ ውስጥ በዝተው ከሚገኙት ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች መካከል አንዱ በሆነው የባንክ ኦፍ አሜሪካን ታወር ላይ የቢሮው ሰራተኞች በህንፃው ጣርያ የሚገኘውን የካሮት እና ሌሎች ፍራፍሬዎች እርሻን ሲንከባከቡ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ 150 ሜትር ቁመት ባለው ይህ በከተማዋ የፋይናንስ እምብርት ቦታ በቆመው ህንፃ ላይ የተዘረጋው እርሻ በአርማታና መስታውት ለተሞላው የህንፃው ገፅታ ልዩ ተጨማሪ መልክን አላብሶታል፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ይህ አይነት በጣርያቸው ላይ እርሻ የገነቡ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎችን ከዓለማችን ቀዳሚ የፋይናንስ እና ምጣኔ ሐብት ማዕከል ከሆኑ ከተሞች አንዷ በሆነችውና በሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ብዛት አቻ የሌላት ሆንግ ኮንግ ዘንድ መመልከት እየተለመደ መጥቷል፡፡ ምስጋና መሰል ተግባራትን የማስፋፋት ስራ ለሚሰራው ሩፍቶፕ ሪፐብሊክ የተሰኘ ተቋም ይሁንና ከአውሮፓውያኑ 2015 በኋላ እንኳን 60 የሚሆኑ የከተማይቱ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች በጣርያቸው ላይ የከተማ እርሻ ማከናወኑን ተያይዘውታል፡፡ እነዚህም በተለይ ቀድሞ ከተማዋን ቁልቁል ለመመልከቻ ማማ፣ ሄሊኮፍተር ማረፍያ እንዲሁም የገበያ ማዕከልነት ታልመው የነበሩ ቦታዎች ናቸው አሁን ላይ አገልግሎታቸው ተለውጦ አረንጓዴ ሸማ የለበሱት፡፡
እንደ ከተማይቱ አስተዳደር ከሆነ ሆንግ ኮንግ በየዕለቱ 3,500 ቶን ወይም ክብደቱ ከ250 ባለ ፎቅ አውቶብሶች ጋር የሚመጣጠን ምግብን ታስወግዳለች፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን 7.5 ሚሊዮን የሚሆነው የከተማይቱ ነዋሪ ከ90 በመቶ በላይ ምግቡን የሚገኘው በዋናነት ከተቀረው የቻይና ክፍል ነው፡፡ ታድያ ምንም እንኳን በሰው እና ህንፃ እጅጉን ከተጨናነቁ የምድራችን ከተሞች አንዷ ብትሆንም ሰባት ሚሊዮን ካሬ ሜትር የሚሆነው የሆንግ ኮንግ መሬት እርሻ ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ ይህ ታድያ 6 ሚሊዮን ካሬ ሜትር የሚሸፍነው የከተማይቱ ህንፃዎች ጣርያን ሳያጠቃልል ነው፡፡ ሩፍቶፕ ሪፐብሊክም ይህን በህንጻ ጣርያዎች ላይ ያለ እምቅ አቅምን ለመጠቀም ከኪነ ህንፃ ባለሙያዎች፣ የህንፃ ባለቤቶች እና ሪል ስትቴት አልሚዎች ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም ባንክ አፍ አሜሪካን ታወርን ጨምሮ በከተማው ያሉ ሌሎች ህንፃዎችን ጣርያ ወደ ከተማ እርሻነት መለወጥ ችሏል፡፡
እነዚህ ተግባራት በተለይ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ የሚቆረቁራቸው የከተማይቱ ወጣት ሰራተኞች ስጋትን መከላከያ ሆኖ እያገለገለ ሲሆን በሌላ መልኩ ከስራቸው በጡረታ የተገለሉ ሰዎች ጊዜ ማሳለፍያና አዲስ ክህሎትን መማርያ ሆኖላቸዋል፡፡
ውድ አንባብያን፤ ይህ ስልት ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ህንፃዎች ጫካነት እየጠለወጡ በመጡትና ለከተማ እርሻ ሊውል የሚችል ክፍት መሬትን ማግኘት አዳጋች እየሆነባቸው ባሉት የሀገራችን ከተሞች ቢተገበር ምን ይመስላችኋል? መልካም ቀን፡፡
ምንጭ፤ Tech Xplore
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-07-hong-kong-urban-farms-gardens.html
ከፍተኛ ሀይል ያለው የፀሐይ ሞገድ መሬትን እየተጠጋት ነው
*************************************************************
መነሻውን ከፀሐይ ከባቢ አየር እንዳደረገ የተነገረለት ከፍተኛ የፀሐይ ሙቀትን የያዘ ሞገድ ወደ ምድራችን 1.6 ሚሊዮን ኪሎሜትሮችን በሰዓት እየተምዘገዘገ እየመጣ እንደሆነ ስፔስ ዌይዘር ዶት ኮምን ጠቅሶ ሂንዱስታን ታይምስ ዘግቧል፡፡ ይህ የሙቀት ማዕበል በመሬት ስበት በተሸፈኑ የምድራችን ክፍሎቸ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችል እየተጠበቀ ነው፡፡
በሰሜንና በደቡብ ዋልታዎች አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በዚህ ሊጨምር ይችላል በተባለ ፍጥነት ውስጥ እየተምዘገዘገ ያለውን የፀሐይ ሞገድ ማዕበል ወጋገንን በምሽት በግልጽ ያዩታል ሲል የመረጃ ምንጫችን አስነብቧል፡፡ በዚህ ከፍኛ ሙቀት ምክንያት የላይኛው የምድራችን ከባቢ አየር ሊቃጠልና በሳተላይቶች ላይ ጉዳት ሊደርስ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋትም ተሰምቷል፡፡
ሙቀቱ በጂፒኤስ ምሪቶች፣ የተንቀሳቃሽ ስልኮች ግንኙነትና የሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭቶች ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችልም ተነግሯል፡፡
የፊታችን እሁድ ወይም ሰኞ የምድራችን የላይኛው ክፍል ላይ እንደሚደርስም እየተጠበቀ ነው፡፡
ምንጭ Hindustan times
ተጨማሪ ንባብ https://www.hindustantimes.com/science/powerful-solar-storm-approaching-earth-can-impact-gps-cell-phone-signals-101625969315026.html