በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መካከል
***********************************************************************
በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መካከል በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ፊርማ ተከናወነ፡፡ ሁለቱ ተቋማት የተቋቋሙበት የየራሳቸው ራዕይና ተልዕኮ ያላቸው ሲሆን በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኩል ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን
የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ ተግባራት መካከል ተቋማት የዘመነ አሰራር እንዲዘረጉና የተቋቋሙበትን አላማ በቅልጥፍና፣ በፍጥነት እና በጥራት ለመተግበር እንዲችሉ የሚያደርጉ አሰራሮችን፣ ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ መደገፍና የተለያዩ የክህሎት ክፍተቶችን በስልጠናዎች መድፈን አንደኛው ነው፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በበኩሉ በሀገራችን የኢንዱስትሪ ፓርኮች እየተስፋፉ መምጣታቸውን ተከትሎ የተቋቋመ መንግስታዊ ድርጅት ሲሆን ከዘርፉ ሊገኝ የሚገባውን ሀገራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና በዘርፉ ወጥና ዘመናዊ የሆነ አሰራር እንዲኖር ለማድረግ ብሎም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ዙሪያ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ሀገራችን ኢትዮጵያ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንድትሆን ከፍተኛ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
የስምምነት ፊርማ መርሃ ግብሩ ላይ በስምምነቱ ዙሪያ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ሳንዶካን ደበበ የስምምነት ሰነዱን የመፈረም ፋይዳ እና አስፈላጊነት እንዲሁም ተቋማቱ በጋራ ተብባብረው የመስራት ቁርጠኝነት አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አመራሮቹ ሁለቱ ተቋማት ከዚህ በፊትም የተለያዩ ስራዎችን በጋራ የሰሩ እና እየሰሩ ያሉ መሆኑን ገልጸው ስምምነቱ በጋራ የመስራት አቅማቸውን እንደሚያሳድግላቸው እና በመካከላቸው ያለዉን ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በስምምነት ሰነድ ፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይም ከየተቋማቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ፕሮፌሰር ሸለመ በየነ፤ ክፍል ፩
===========
ስለ ትጉህ መምህርነታቸው፣ አውንታዊ አመለካከታቸውና በሰዓት አጠቃም ላይ ያላቸው ወግ አጥባቂነት በቅርብ የሙያ አጋሮቻቸው ይመሰከርላቸዋል፤ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአፈር ጥናትና ምርምር ምሁር የሆኑት ፕ/ር ሸለመ በየነ፡፡ ከተለያዩ የምርምር ስራዎቻቸው ባሻገር በመምህርነት ቆይታቸው 15 የዶከትሬት እና 113 የማስተርስ ምሩቃንን ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ያፈሩት ፕ/ር ሸለመ ዛሬም ብዝ አላሳካውም ብዙ መለወጥ የሚገባኝ ነገርም አለ ሲሉ ትጋታቸውን (ብሎም ትህትናቸውን) በሚያሳብቅ አንደበት ስለ ሙያዊ ጉዞዋቸው ይናገራሉ፡፡ በተለይም ሀገራቸውን ከረሀብ ማላቀቅ ባለመቻላቸው የሚሰማቸውን ሙያዊ ቁጭት አልደበቁንም፡፡
ውድ የገፃችን ተከታታዮች ለዛሬ ከጥቂት ጊዜያት በፊት በሳምንታዊው የቴክ ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራማችን ላይ ከእናንተው ጋር አስተዋውቀናቸው የነበሩት እኚህን ምሁር ዳግም በገፃችን ልናደርስዎ ወደድን፡፡ በዚህ የመጀመሪያው ክፍልም ከወደ ሸዋ ወሊሶ አቅራቢያ አንስቶ ከተዘረጋው የሕይወት መስመራቸው፣ የልጅነት ውጣ ውረዳቸው፣ የሙያ መነሳሻ ስለሆነላቸው ነገር እንዲሁም የህይወት ፍስፍናቸውን ያጋሩናል፤ አብራችሁን ቆዩ፡፡
ዘውትር ቅዳሜ ከቀኑ 10 ሰዓት እንዲሁም በድጋሚ ዕለተ ማክሰኞ በተመሳሳይ ሰዓት በMOE tv ላይ ያገኙናል፡፡ ከታች በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት የዩትዩብ ገፃችንን ሰብስክራይብ በማድረግም ሙሉ የቴክ ሳይንስ ፕሮግራማችንን ጨምሮ ሌሎች የሳይንስ ቴክኖጂ እና ኢኖቬሽን መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
👉 https://www.youtube.com/watch?v=Uqo6uks4E4k

YouTube
ቆይታ ከፕሮፌሰር ሸለመ በየነ ጋር ክፍል አንድ
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ በአፈር ሳይንስ ዙሪያ ተመራማሪ ከሆኑት ፕሮፌሰር ሸለመ በየነ ጋር ስለ ህይወት ተሞክሯቸዉ፣ስለ ቤተሰብ ሁኔታቸዉ፣ስለ ምረምሮቻቸዉ፣ስለ ገጠመኞቻቸዉ እናወጋለን::
መልካም ቆይታ……
አዘጋጅ ጀሚላ አደም
መልካም ቆይታ……
አዘጋጅ ጀሚላ አደም
ቅዳሜን በምን ያሳልፋሉ?
=======
እንደው ድንገት በስራ ተጠምደው ከዘነጉት ለማስታወስ ያህል ነገ ቅዳሜ ነውና ቀንዎን ከቴክ-ሳይንስ ጋር የማይሻር ዕውቀትን በመገብየት እንዲያሳልፉ ግብዣችንን እናቅርብልዎ፡፡ ታድያ ስነ-ህዝባዊ ትሩፋት ምንድን ነው? እንዴት እናሳካዋለን? ለዚህ ምላሽ የሚሆን ትንታኔን በአብይ ፕሮግራማችን ይዘንልዎ የምንመጣ ይሆናል፡፡
ለእርስዎም ሆነ ልጆችዎ መነሳሳትን ይቀሰቅስ ዘንድም ካሳለፍነው አንድ ዓመት ጀምሮ ለትልቅ እውቅና የበቃው ወጣቱ የፈጠራ ባለሙያና የአይከን አፍሪካ መስራች እንዲሁም የ36 ፈጠራ ስራዎች ባለቤት ኢዘዲን ካሚልን በብላቴናት መስኮት ይዘንልዎ እንቀርባለን፡፡
የተመራማሪዎች ታሪክም አልተረሳም፤ የቀድሞው የሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ፕ/ር ጨመዳ ፊኒንሳ ይዞ በክፍል ሁለቱ ተሰናድቷል፡፡ የቴክኖሎጂ ታሪክም የቤት ውስጥ አየር ማሞቂያ (ሂተር) ቴክኖሎጂን ይዞ በሰዓቱ ይቀርባል፡፡
ያስታውሱ፤ ቴክ ሳይንስ ዘውትር ቅዳሜ በ10 ሰዓት እንዲሁም በድጋሚ ማክሰኞ በ10 ሰዓት በMOE tv ትቀርባለችና ይጠብቋት፡፡
የዩትዩብ ቻናላችንንም ሰብስክይብ በማድረግ የቤተሰባችን አካል ይሁኑ፡፡ 👉https://www.youtube.com/.../UC6jvUOLRSkVEQtc5Ann.../featured

የልጃቸውን የእይታ ችግር በቴክኖሎጂ ያስተካከሉ ወላጆች
*****************************************
*********
ስፔናውያን ጥንዶች የእይታ ችግር ላለበት ልጃቸው ባለ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ መነጸርን ሰርተው የተሻለ እይታ እንዲኖረው ማድረጋቸው ተሰማ፡፡ ጥንዶቹ የልጃቸውን የአይን ችግር ያስተዋሉት በሁለት አመቱ በተደጋጋሚ የመውደቅ አጋጣሚ ሲከሰትበትና መራመድ ከተለማመደ በኋላ ደግሞ አነስተኛ ደረጃዎችን መውጣት ሲያዳግተው ተመልክተው ነው፡፡ ከዚያም የችግሩን ምንነት ለማረጋገጥ ጥንዶቹ ልጃቸውን ወደ ህክምና ተቀቋም ወሰዱት፡፡ ብዙ ሃኪሞችን ካማከሩና ምርመራዎችን ካደረጉ በኋላ ህጻኑ የተወሰነ የማየት አቅም (low vision) እንዳጋጠመው ይህም ችግር መደበኛ ተግባራትን እንዳይከውን እንዳደረገው ማወቅ ቻሉ፡፡
ይህ አይነቱ ችግር በመነጸርም ሆነ በቀዶ ህክምና የሚስተካከል ባለመሆኑ የቢል ወላጆች ሌሎች መፍሔዎችን መፈለግ ጀመሩ፡፡ እነዚህ ወላጆች በሙያቸው ኤሌክትሪካል ኢንጅነርና ዶክተር ሲሆኑ እናትየዋ በልጇ ስም ደካማ እይታ ላላቸው ህጻናት የተለያዩ አጋዥ መነጸሮችን የሚያቀርብ ድርጅት ከፍታ መስራት ጀመረች፡፡
የቢል አይነት ችግር ላለባቸው ሰዎች ከምርኩዝ (cane) እና አይነ-ስውራንን መምራት ከተማሩ ውሾች ውጭ መፍትሔ የሚሆኑ ነገሮች አለመኖራቸውን ያስተዋሉት ስፔናውያኑ ጥንዶች የበለጸገ የማያ ዘዴን (augmented reality glasses) ለልጃቸው ችግር መፍትሔ እንዲሆን አድርገዋል፡፡ ቴክኖሎጂው ህጻኑ የተለያዩ ጽሁፎችን፣ ምስሎችንና ቪዲዮዎችን እንደሚመለከት በማስቻል የጥገኝነት መጠኑን በእጅጉ ቀንሶለታል፡፡
ወላጆቹም ‹‹ለልጃችን ሙሉ ህክምና ባናገኝም ችግሮችን ሊያቀልለት የሚችል መፍትሔ ማግኘታችን ትልቅ ነገር ነው›› ሲሉ ተሰምተዋል፡፡ አጋዥ መነጸሩን ለመስራት ዘጠኝ መቶ ሺህ ይሮ (አንድ ሚሊዮን ዶላር) የጨረሰ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ጥንዶቹ 65 ሺህ ይሮውን ሲሸፍኑ ቀሪውን ከተለያዩ ድጋፎች አግኝተዋል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-07-spanish-couple-high-tech-specs-son.html

Tech Xplore
Spanish couple develop high-tech specs to help son see
When their two-year-old son Biel started falling over a lot and had difficulty climbing stairs after learning to walk, Jaume Puig and his wife sought medical help to figure out the problem.
ፕላስቲክን መበጣጠስ የሚያስችል ንጥረ ነገር ከከብቶች ሆድ
********************
ፕላስቲኮች በተለይ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉት አካባቢን በመበከል ደረጃ ከፍተኛ ድርሻ አላቸው፡፡ የፕላስቲኮቹን ጉዳት የከፋ የሚያደርገው ለመበስበስ ወይም ወደ አፈርነት ለመለወጥ ረጅም አመት የሚወስድባቸው መሆኑ ነው፡፡ ይህን ችግር የተመለከቱ ተመራማሪዎች በተለያዩ ጊዜያት በዘርፉ የተለያዩ ምርምሮችን ያከናወኑ ሲሆን ፕላስቲኮቹን አለመጠቀምን የሚያስንቅ ውጤት ግን እስካሁን አላገኙም፡፡
በኦስትሪያ ተፈጥሮ ሀብትና የስነ-ህይወት ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ወጣ ምርምር ታድያ የላሞች ሆድ ውስጥ የሚገኙት ሩመን የተባሉ ባክቴሪያዎች የሚያመርቷቸው ኢንዛይሞች የሰው ልጅ በብዛት የሚጠቀምባቸው ፕላስቲኮችን ማደድቀቅ እንደሚችሉ አዲስ አመላከተ፡፡ ጊኦርግ ጉኢቤትዝ የሚመራው የጥናት ቡድን ያቀረበው ግኝት ፕላስቲክን ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል አዲስ መንገድን ይዞ የሚመጣ ሊሆን እንደሚችል ተነግሮለታል፡፡
የጥናት ቡድኑ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ቄራ በማምራት ነበር ከአንድ በሬ ላይ ፈሳሽ የሩመን ናሙናዎችን ወስዶ ምርምሩን ያከናወነው፡፡ በውጤቱም ፈሳሹ ኪዩቲኔስን ጨምሮ የተለያዩ አይነት ኢንዛይሞችን መያዙን ማወቅ ችለዋል፡፡ ቡድኑ እነዚህ ኢንዛይሞች ከኮዳ እስከ ጨርቃጨርቅና ቦርሳ ድረስ ድረስ በስፋት ጥቅም ላይ የምናውላቸው ፖሊያትሊን ትሬፍትሌት (PET)፣ ፖሊቢዩትሊን አዲፔት ትሬፍትሌት (PBAT) እና ፖሊያትሊን ፊዮራኖኤት (PEF) የተሰኙ የፕላስቲክ አይነቶችን መሰባበር እንደሚችል አስመስክረዋል፡፡ ኢንዛይሞቹ ፕላስቲኮቹን ለመሰባበር ከአንድ እስከ ሦስት ቀን ሲፈጅባቸው ይህን ለመተግበርም ከላም ሆድ ጋር በተቀራረበ የ40 ዲ.ሴ ሙቀት መቀመጥ እንዳለባቸው ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ግኝት ላይ በመመስረት ወደፊት ኢንዛይሞቹን ተጠቅሞ ፕላስቲኮችን የመሰባበር ስራ ላይ በስፋት ማዋል እንደሚቻል ጊኦርግ ጉኢቤትዝ ይናገራል፡፡ ይህ ታድያ ቢያንስ አሁን ጥቅም ላይ ከሚውሉት ፕላስቲክን ማቀነባበሪያ መሳርያዎች አንፃር በዋጋ የረከሰ ሊሆን እንደሚችልም ጠቅሷል፡፡ ሆኖም ይህ መፈተሽ ያለበት እይታ ስለመሆኑ ሌሎች አጥኚዎች ይናገራሉ፡፡ የሚሺጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ምሁሩ ራማኒ ናራያን እንደሚለው አስቀድሞ አዲሱ ግኝት ገበያ ላይ ካለው ቴክኖሎጂ አንፃር በተመሳሳይ አልያም የበለጠ ውጤታማ መሆኑን ማስመስከር የሚጠበቅበትና ግኝቱን በስፋት ጥቅም ላይ ከማዋል አንፃርም ገና ብዙ ስራዎች የሚቀሩት ነው፡፡
ፕላስቲኮችን ሰባብሮ ዳግም ጥቅም ላይ ማዋል ቁሱ ባለው የተለያዩ ሞለኪውል አይነቶች ሳብያ አስቸጋሪ ስራ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጥቅም ላይ ከሚውለው ፕላስቲክ መካከል የተወሰነው ብቻ ዳግም ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ እ.አ.አ 2014 ላይ የወጣ አንድ መረጃ የሚያመላክተውም 19 በመቶ የሚሆነው ፕላስቲክ ብቻ ዳግም ጥቅም ላይ የሚውል መሆኑን ነው፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ግን የፕላስቲክ ምርት በአውሮፓውያኑ 2050 በ70 በመቶ አድጎ 600 ሚሊዮን ቶን አመታዊ የምርት መጠን ላይ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፤ New Scientist እና Science
ለተጨማሪ፤ https://www.newscientist.com/article/2282950-common-plastics-can-be-broken-down-by-enzymes-found-in-cow-stomachs/?utm_term=Autofeed&utm_campaign=echobox&utm_medium=social&utm_source=Twitter&fbclid=IwAR0nZvn4Bg95StOUTLry3WK02MMoSqRFl-M7grUF6MvVsuqXXa1yIAEpXWs#Echobox=1625216719 እና https://www.sciencemag.org/news/2021/07/could-plastic-eating-microbes-take-bite-out-recycling-problem?utm_campaign=NewsfromScience&utm_source=Social&utm_medium=Twitter

New Scientist
Common plastics can be broken down by enzymes found in cow stomachs
The bacteria in a cow's stomach produce enzymes that can break down the plastic used to make bottles and bags, and could one day be used to process such plastics after use
ናሳ የሰራው የአቶሚክ ሰዓት ከሌሎች በ10 እጥፍ የበለጠ ውጤታማ መሆኑ ተረጋገጠ
=============
የአሜሪካኑ ጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ ተመራማሪዎች የሰሩት አዲስ የአቶሚክ ሰዓት አሁን ካሉ ሌሎች መሰል ሰዓች በ10 እጥፍ በበለጠ ትክክለኝነት እንደሚሰራ አረጋገጡ፡፡ በኤሪክ በርት አማካኝነት በተመራው በዚህ ምርምር ላይ ሰዓቱ ለአንድ ዓመት ያህል ጠፈር ላይ ሆኖ ምድርን እንዲዞራት በማድረግ ሙከራ የተከናወነበት ሲሆን በዚህም በከፍተኛ ደረጃ አስቸጋሪ የሆኑ የአየር ንብረት ሁኔታዎችን መቋቋም የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
በምድር ላይ ስንኖር የአቅጣጫ ማመለካከቻ ወይም ጂፒኤስን ተጠቅመን የጉዞ መንገዳችንን ማወቅ እንችላለን፡፡ ሆኖም ከምድር ወጥተው በህዋ የሚጓዙ ተጓዦች እኛ ምድር ላይ የምንጠቀመውን ቴክኖሎጂ ተጠቅመው አቅጣጫቸውን ማግኘት ስለማይችሉ የጉዞ ሲግናሎች ከምድር ተለቀው እነርሱ ጋር የማድረስና ነጥሮ ወደ ምድር እንዲመለስ የማድረግ ስልትን ለመጠቀም ይገደዳሉ፡፡ የአቶሚክ ሰዓቶች ታድያ በብርሃን ፍጥነት የሚጓዙት ሲግናሎቹ ከምድር ተነስተው የጠፈር ተጓዦቹ ጋር የሚደርሱና ነጥረው ወደ ምድር የሚመለሱበትን ትክክለኛ ሰዓት ስለሚያሳውቁ የጠፈር ተመራማሪዎች ይህን አስልተው የጠፈር ተጓዦቹ ያሉበትን ቦታ፣ የሚጓዙበትን ፍጥነት እንዲሁም አቅጣጫቸውን እንዴት ማስተካከል እንደሚቻል ይደርሱበታል፡፡ እዚህ ላይ ግን የጠፈር ተጓዦቹ ከምድር በራቁ ቁጥር ሲግናሎቹም ከምድር ተልከው እነርሱ ጋር የሚደርሱበትና ነጥረው የሚመለሱበት ሰዓት እየረዘመ ይመጣል፡፡ ስለዚህም ተጓዦቹ እጅግ ውጤታማ የሆነ የአቶሚክ ሰዓትን መያዛቸው ፍጥነትና አቅጣጫቸውን በቶሎ እንዲሁም በቀላሉ እንዲረዱ ያስችላቸዋል፡፡
ይህን የህዋ ጉዞ ተግዳሮት ለመፍታት ያቀደው ናሳ በአውሮፓወያኑ 2019 “ዲፕ ስፔስ አቶሚክ ክሎክ” ብሎ የሰየመው ይህን ሰዓት ለሙከራ ወደ ጠፈር አስልኮ ነበር፡፡ በጠፈር ላይ ሙከራው ወቅት በሰዓቱ ውስጥ ያሉት አተሞች የመንቀጥቀጥ ችግርን እየፈጠሩ ሲያስቸግሩ ትራፕድ አዮን በተባለ ስልት አማካኝነት አተሞቹን በኤሌክትሮማግኔቲካዊ ገደብ ውስጥ በማስቀመጥ ችግሩ ተቀርፏል፡፡
ጥናቱን አስመልክቶ በኔቸር ጆርናል ላይ ታትሞ የወጣው ፅሁፍ እንደሚያመላክትው ሰዓቱ በአጭር ጊዜም ሆነ ረጅም ጊዜ ተረጋግቶ በመስራት ረገድ በአሁኑ ጊዜ ካሉ ሌሎች መሰል ሰዓቶች ሁሉ በ10 እጥፍ የላቀና ወደ ጥልቁ ህዋ (deep space) የሚደረግ ጉዞን እውን በማድረግ ረገድም አንድ እርምጃን ያራመደ መሆኑን ነው፡፡
ምንጭ፤ Cosmos
ለተጨማሪ፤ https://cosmosmagazine.com/space/exploration/deep-space-atomic-clock-is-truly-next-gen/?utm_content=buffer42371&utm_medium=social&utm_source=twitter.com&utm_campaign=buffer

Cosmos
From the vault: Deep Space Atomic Clock is truly next-gen
The future of space navigation is almost here – NASA scientists have reported that its Deep Space Atomic Clock is up to 10 times more accurate than any other
ኢትዮጵያዊ መፅሐፍትን ለትረካ የሚያበቃው አዲስ አገልግሎት
==============
ኦል ራይትስ ቴክኖሎጂስ “ተራኪ” የተሰኘ በዋናነት ኢትዮጵያውያዊ የድምፅ ይዘቶችን የሚያዘጋጅና የሚያሰራጭ ዲጂታል የድምፅ ይዘቶች ማቅረቢያ አገልግሎትን ይፋ አድርጓል፡፡ በናሆም ጸጋዬ እና አቤል ግርማ አማካኝነት በአውሮፓውያኑ 2020 የተመሰረተው ተራኪ በውስጡ ካካተታቸው የድምፅ ይዘቶች መካከል በድምፅ የተቀረፁ መፅሐፍት፣ የራዲዮን ሾው፣ ፖድካስት እና የተለያዩ ትረካዎች ይገኙበታል፡፡
እንደ ተራኪ መስራቾች ከሆነ በአሁኑ ሰዓት አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ የድምፅ ይዘቶችን አግኝቶ መጠቀሙ አስቸጋሪ ሲሆን የድምፅ ይዘቶቹ ባለቤቶችም ቢሆን ስራቸውን ገበያ ላይ አውለው ለመጠቀም ይቸገራሉ፡፡ ይህን የአቅራቢ እና ተደራሽ አለመገናኘት በመመልከት በአድማጮች ፍላጎት ላይ የተመሰረተና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ የድምፅ ስርጭት ስርዓትን ይዘው ሊመጡ መቻላቸው ተጠቅሷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ፅሁፍና መሰል ይዘት ያላቸው ሰዎች ስራዎቻቸው ወደ ድምፅ እንዲለወቱ ከሚያደርጉ ባለሙያዎች ጋር የማገናኘት ስራንም የሚራው ተራኪ መፅሐፍቶቻቸው ስቱዲዮዎች ውስጥ በጥራት እየተነበቡ እንዲቀረፁ ያደርግላቸዋል፡፡ በሌላ በኩል እነዚህ ወደ ድምፅ ይዘት የተቀየሩት ስራዎችም ሆነ ሌሎች ኢትዮጵያዊ የራዲዮን እና መሰል የድምፅ ይዘት ያላቸው ዝግጅቶች ተራኪ በተባለው የስልክ መተግበሪያ አማካኝነት ለተጠቃሚዎች የሚደርሱ ይሆናል፡፡
ተጠቃሚዎች ማግኘት ከሚችሏቸው የድምፅ ይዘቶች መካከል በክፍያ ብቻ ተደራሽ የሚሆኑ ሲኖሩ የተቀሩት ግን በነፃ ቀርበዋል፡፡ በክፍያ የሚቀርቡትን ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርዶችን በመጠቀም ማግኘት እንደሚቻልና በቅርቡም ከሀገር ውስጥ ዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር የማስተሳሰር ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆናቸው የተራኪ መስራቾች ይናገራሉ፡፡ ለአሁኑ ግን ተጠቃሚዎች 100 ያህል የድምፅ ይዘቶችን ከአንድሮይድ መተግበሪያው (በቅርብ በiOS ይቀርባል) ላይ በነፃ አውርደው መጠቀም የሚችሉ ይሆናል፡፡
የአገልግሎቱ መስራቾች ናሆም እና አቤል ከዚህ ቀደምም ሲቲፋርምስ የተሰኘ ሽቅብ የከተማ እርሻ አገልግሎት እንዲሁም ሽርሽር ተብሎ የሚጠራ የጉዞ ኤጀንሲን መስርተዋል፡፡ የተራኪ አገልግሎትም የተጀመረው ከሽርሽር በተገኘ ትርፍ ላይ በመንተራስ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
ይህን ሊንክ በመጠቀም መተግበሪያውን ከጎግል ፕሌይ ማውረድና መጠቀም ይችላሉ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.terakiapp.teraki
ምንጭ፤ Shega
ለተጨማሪ፤ https://shega.co/post/teraki-launches-its-audio-content-streaming-platform/

Google Play
Teraki - Audiobooks & Podcasts - Apps on Google Play
Discover and enjoy Ethiopian Audiobooks and Podcasts.
7 ሚሊዮን ህፃናትን ያባረረው ቲክቶክ
===========
ቲክቶክ ዕድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች ናቸው ብሎ የጠረጠራቸው ከ7 ሚሊዮን በላይ አካውንቶችን በያዝነው የፈረንጆች ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ውስጥ ብቻ ከገፁ ማንሳቱ ተገለፀ፡፡ በቻይናዊያን ባለቤትነት የሚንቀሳቀሰው መተግበሪያው ጥላቻን፣ የራቁት ምስል የህዳጣን ደህንነት አደጋ ውስጥ የሚከቱና ሌሎችም ማህበረሰባዊ እሴቶችን የሚንዱ 62 ሚሊዮን ገደማ ቪዲዮዎችንም በነዚህ ወራት ውስጥ ማጥፋቱ ተነግሯል፡፡
ድርጅቱ እንዳስታወቀው እርምጃውን ለመውሰድ ዕድሜ በማጭበርበር የተጠረጠሩ ተጠቃሚዎችን ዕድሜ ከሚያጣራ ቡድን አንስቶ ሌሎች የተለያዩ መንገዶችን ተጠቅሟል፡፡ አሜሪካን ውስጥ ያሉ እድሜያቸው 12 ዓመት ወይም ከዚያ በታች የሆኑ ታዳጊዎች ለታዳጊዎች ወደተዘጋጀው የቲክቶክ አይነት ተወስደዋል፡፡
የቲክቶክ ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሚፈቀደው እድሜ በታች ከሆኑት ባሻገር ሌሎች 4 ሚሊዮን ተጠቃሚዎቹንም የአጠቃቀም መመርያዎችን ጥሳችኋል በሚል አካውንታቸው እንዲጠፋ ተደርጓል፡፡ እንደ ድርጅቱ ከሆነ አውቶማቲክ የቁጥጥር ስርዓቱ 91.3 በመቶ የሚሆኑትን የአጠቃቀም መመርያ የጣሱ ቪዲዮዎች ሌሎች ተጠቃሚዎች ሪፖርት ከማድረጋቸውም አስቀድሞ ከገፁ ላይ ሲያነሳ 81.8 በመቶው ማንም ሳያያቸው 93.1 በመቶው ደግሞ በተፖሰቱ 24 ሰዓታት ውስጥ ነው የተነሱት፡፡
በወጣት የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ቲክቶክ በዓለም ዙርያ አንድ ቢሊዮን የሚሆኑ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ይነገርለታል፡፡
ምንጭ፤ Tech Xplore
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-06-tiktok-million-underage-users.html?fbclid=IwAR1wINdx_Gxp39eQNKAeD5_KI3DMdFBVNtxBkhn4h_YLMMpECbqE6hFbj3s

በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት እንዲሰጥ ፈቃድ ያገኘው ጥምረት ዋና አስተዳዳሪውን ይፋ አደረገ
============
በኬኒያው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ሳፋኮም ፊት አውራሪነት የሚመራውና በቅርቡ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ ያገኘው ሕብረት አንዋር ሱሳን የጥምረቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አድርጎ ሹሟል፡፡ ሹመቱ ለአንዋር ሱሳ መሰጠቱን በትናንትናው ዕለት ያስታወቁት የሳፋሪኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ንዴግዋ ናቸው፡፡
የግሪክ ዜግነት ያላቸው አንዋር ሱሳ ከዚህ ቀደም በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የቮዳኮም ማኔጂንግ ዳይሬክተር የነበሩ ሲሆን ከአውሮፓውያኑ 2017 አንስቶም የቮዳካሽ ሊቀ መንበር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ቮዳፎንን ከመቀላቀላቸው አስቀድሞም በዩጋንዳ እና ቻድ የኤርቴል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ሲሰሩ በደቡብ አፍሪካው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ኤምቲኤን ውስጥም ቆይታ ነበራቸው፡፡
የደቡብ አፍሪካው ቮዳኮም እና የብሪታኒያው ቮዳፎን ቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያዎችን በውስጡ አቅፎ የተቋቋመው ጥምረቱ ከእነዚህ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች ባሻገርም ብሪታኒያዊ የልማት ፋይናንስ ተቋም የሆነው ሲዲሲ ግሩፕ እና የጃፓኑ ሶሚቶሞ ኮርፖሬሽንን በአጋርነት ይዟል፡፡ በኢትዮጵያ የመንቀሳቀሻ ፈቃዱን ያገኘው ተፎካከሪውን በልጦ 850 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ በማቅረብ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ከዚህም ባሻገር ታድያ ጥምረቱ በመጪዎቹ ዓመታት ውስጥ እስከ 8.5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ መዋለ ነዋይ በኢትዮጵያ መሰረተ ልማት ግንባታ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ለማፍሰስ አቅዷል፡፡
በአፍሪካ ከናይጄሪያ በመቀጠል ትልቁን የህዝብ ብዛት የያዘችው ኢትዮጵያ እስከ ቅርብ ጊዜያት ድረስ የቴሌኮም ገበያቸውን ዝግ አድርገው ከቆዩ ጥቂት ትላልቅ የዓለማችን ሀገራት አንዷ ነበረች፡፡ ለብዙዎች የሥራ እድልን እንደሚፈጥር ከታመነበት ገበያውን ክፍት የማድረግ እርምጃ ባሻገር ለአመታት በመንግስት ባለቤትነት ስር ብቸኛው የሀገር ውስጥ ቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ሆኖ የቆየው ኢትዮ ቴሌኮምን 45 በመቶ ድርሻ ለመሸጥም እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡
ምንጭ፤ Reuters
ለተጨማሪ፤ https://www.reuters.com/article/kenya-safaricom-idAFL5N2OH2CP

U.S.
Consortium led by Safaricom appoints MD of new Ethiopian unit
A consortium led by Kenyan telecoms operator Safaricom has appointed Anwar Soussa as managing director of its Ethiopian unit, which is scheduled to start operations next year, Safaricom Chief Executive Peter Ndegwa said on Monday.
በኤሌክትሪክ የሚሰራ አውቶቢስ በደቡብ አፍሪካ
************************************************
የትራንስፖርት አገልግሎት ማህበረሰቡን ከቦታ ቦታ በማንቀሳቀስ ሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት እንዲኖረው ከዚያም አነስ ሲል ሰዎች እለታዊ ተግባራቸውን በአግባቡ መከወን እንዲችሉ ያደርጋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ለትራንስፖርት የምንጠቀምባቸው መጓጓዣዎች ከተፈጥሮ ጋር የማይስማማ መገለጫ አላቸው ይኸውም የአየር ብክለት ነው፡፡ በአለማችን የተለያዩ ሀገራት ያላቸውን የካርቦን ልቀት ለመቀነስ ወይም ዜሮ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል በካይ ያልሆኑ መጠቀሚያዎችን ወደ አገልግሎት ማቅረብ አንደኛው ነው፡፡
በመጓጓዣው ዘርፍ ከመኪኖች የሚወጣው በካይ ጋዝ ከፍተኛ የሆነ የአየር ብክለት በተለከይ በከተሞች አካባቢ እንዲኖር ያደርጋል፡፡ በመሆኑም በከተሞች አካባቢ የህዝብ ትራንስፖርትን መጠቀም እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ይህም በመንገድ ላይ የሚንቀሳቀሱ የትራንስፖር አማራጮችን ቁጥ በመቀነስ የአካባቢን የመበከል መጠን መቀነስ ያስችላል፡፡
የህዝብ ትራንስፖርትን መጠቀም የብክለት መጠንን ቢቀንስም ሙሉ ለሙሉ ስለማይስቀር አሁንም ሌሎች አማራጮችን መጠቀም በጣም ተገቢ ነው፡፡ ለዚህ ነው የተለያዩ ሀገራት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የህዝብ ትራንስፖርት መኪኖችን ለመጠቀም ጥረቶችን እያደረጉ ያሉት፡፡ የአህጉራችን ባለ ከፍተኛ ኢኮኖሚ ሀገር ደቡብ አፍሪካም ይህንን የአየር ብክለትን ለመቀነስ የሚደረግ ጥረትን የተቀላቀለች ይመስላል፡፡ ደቡብ አፍሪካ ለሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ አውቶቢስ የህዝብ አውቶቢስ ስራ አስጀምራለች፡፡
ለ12 ወራት ያክል ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሁለት አውቶቢሶች በሙከራ የቆዩ ሲሆን ብዙ አስቸጋሪ ነገሮችን እንዳሳለፉም ተነግሯል፡፡ ሆኖም ግን የሙከራ ጊዜው የተሳካ እና ተገልጋዮች ትራንስፖርቱን በሚጠቀሙበት ጊዜ ምቾት እንደሚሰማቸው ጎልደን አሮው የተሰኘው የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት ተናግሯል፡፡ ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት ከ 1000 በላይ አውቶቢሶችን እያስተዳደረ ሲሆን በቀንም እስከ 250 ሺህ ተጓዦችን ለማመላለስ አቅዷል፡፡
ምንጭ cgtn
ተጨማሪ ንባብ https://africa.cgtn.com/2021/07/06/south-africas-first-active-electric-bus-launched-in-cape-town/?fbclid=IwAR2-ra7vlDYs7Cg3vCYiie-XhBr7ByiJvkCR2OrZhQQRJYeayXlfqZiqHCc

CGTN Africa
South Africa’s first active electric bus launched in Cape Town
The first electric bus in active service in South Africa was officially launched here on
ቻይና የወባ በሽታን ሙሉ ለሙሉ ማጥፋቷን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
===========
የዓለም ጤና ድርጅት ቻይና የወባ በሽታን ከምድሯ ሙሉ ለሙሉ ማጥፋቷን ባሳለፍነው ሳምንት አስታውቋል፡፡ ቻይና ሙሉ ለሙሉ የወባ በሽታን ካስወገዱ ሀገራት ውስጥ ስሟ የሰፈረላት 40 ኛዋ የዓለማችን ሀገር ስትሆን በምዕራብ ፓስፊክ አካባቢም ከአውሮፓውያኑ 1987 በኋላ ይህን እውቅና ያገኘች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡
ምንም እንኳን ከአውሮፓውያኑ 2017 አንስቶ በቻይና ውስጥ ምንም ዓይነት በወባ የተያዘ ሰው ተገኝቶ ባያውቅም የዓለም ጤና ድርጅት የወባ ነፃ ዕውቅናን የሚሰጠው የሀገር ውስጥ የወባ ስርጭት ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ሳይመዘገብ ሲቀር በመሆኑ ነው ዕውቅናው እስካሁን የዘገየው፡፡ በተጨማሪም ዕውቅናውን ለማግኘት አንድ ሀገር በሽታው ዳግም እንዳይከሰት የማድረጊያ ዕቅድ ሊኖራት ያስፈልጋል፡፡ ታድያ ይህ የዓለም ጤና ድርጅት ዕውቅና በሀገሪቱ ደቡብ ምዕራባዊ ክፍል የሚገኘው ዩናን ግዛት የበሽታው ስርጭት አሁንም ድረስ ካለባቸው ሦስት የጎረቤት ሀገራት ጋር የሚዋሰን እንደመሆኑ የዕውቅናውን ቦታ ከፍ አድርጎታል፡፡
ዘገባዎች እንደሚያሳዩት የዛሬ ስልሳና ሰባ ዓመታት ገደማ ቻይና 30 ሚሊዮን ያህል ዜጎቿ በየዓመቱ በወባ በሽታ ይያዙባትና ከመካከላቸውም አንድ በመቶ የሚሆኑት ለህልፈተ ህይወት ይዳረጉ ነበር፡፡ ባለፉት ሰባት አስርት ዓመታት ውስጥ ታድያ ሀገሪቱ የወባን ስርጭት የሚገድቡና በሽታውን የሚያክሙ ልዩ ልዩ ስትራቴጂዎችን ቀርፃ ተንቀሳቅሳለች፡፡ ከነዚህም ውስጥ የሀገሪቱ መንግስት በአውሮፓውያኑ 1967 ያስተዋወቀው ፕሮጀክት 523 ተብሎ የሚጠራው 500 ያህል ተመራማዎችን ከመላው ቻይና በማሰባሰብ የተከወነ ምርምር ይገኝበታል፡፡ እንቅስቃሴው ውጤታማ የሆነ ፀረ ወባ እንዲገኝ ሲያደርግ ግኝቱም በ2015 በህክምናው ዘርፍ የኖቤል ሽልማት እንዲቀዳጅ ሆኗል፡፡ በተጨማሪም ቻይና የዓለም ጤና ድርጅት እንኳን አጎበሮችን እንደ መከላከያ መንገድ መጠቆም ከመጀመሩ በፊት ነው 1980ዎቹ በፀረ ወባ የታከሙ አጎበሮችን በመላው ሀገሪቱ ማሰራጨት የጀመረችው፡፡
እነዚህ ሁሉ ፀረ ወባ እንቅስቃሴዎች ተደማምረው በ1990ዎቹ በቻይና ያለው በወባ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በ95 በመቶ ቢቀንስም ወባ ችግር መሆኑ ግን አልቆመም ነበር፡፡ ከ10 ዓመት በፊት 2011 የሀገሪቱ መንግስት ወባን ጨርሶ የማጥፋት ዕቅድን ይፋ ሲያደርግ ከአንድ አመት በኋላ ደግሞ 1-2-7 የተባለ ስትራቴጂን አስተዋወቀ፡፡ በ1-2-7 ስትራቴጂ መሰረት በየአካባቢው የሚገኙ የጤና ተቋማት በወባ የተያዙ ሰዎች ሲገኙ በአንድ ቀን ውስጥ እንዲያሳውቁ፣ በሦስት ቀናት ውስጥ ምርመራ እንዲያደርጉ እንዲሁም በሰባት ቀናት ውስጥ ስርጭትን የሚገድቡ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ይገደዳሉ፡፡
ይህ የቻይና በረጅም ዓመታት ተከታታይ ስራዎች የተገኘው ድል በአሁኑ ሰዓት የዓለማችን 94 በመቶውን የወባ በሽታ ስርጭት መገኛ ለሆኑት የአፍሪካ ሀገራት በምሳሌነት ተወስዶ ሊሰራበትና ልምድ ሊሆን እንደሚገባ ተነግሯል፡፡
ምንጭ፤ The Scientist
ለተጨማሪ፤ https://www.the-scientist.com/news-opinion/china-is-malaria-free-says-world-health-organization-68938?utm_content=171635895&utm_medium=social&utm_source=twitter&hss_channel=tw-18198832

The Scientist Magazine®
China Is Malaria-Free, Says World Health Organization
The certification, a major accomplishment for the world’s most populous nation, may serve as an example to other countries struggling with malaria eradication.
በትንፋሽ ብቻ ኮቪድ 19 እንዳለብን የሚነግረን ስማርት ማስክ
===========
የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ እና ማሳቹሴት ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ አጥኚዎች የሰሩት አዲስ ማስክ እራስን ከኮቪድ 19 ከመጠበቅም ባሻገር በትንፋሽ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ (ሳርስ-ኮቭ-2) መኖሩን ማረጋገጥ ይችላል፡፡ አጥኚዎቹ ይህን ማድረግ የቻሉት ባዮ ሴንሰሮችን ከማስኩ ጋር በማገናኘት ሲሆን ማስኩም በቤተ-ሙከራ ከሚሰራ ምርመራ ጋር የሚስተካከል ውጤትን በ90 ደቂቃዎች ውስጥ ብቻ እንደሚሰጥ ተነግሮለታል፡፡
ባዮሴንሰሮች ከዚህ ቀደምም በሌላ የህክምና መሳርያ ላይ ጥቅም ላይ ውለው የነበሩ ቢሆንም መሳርያው በህይወት ያሉ የታነፁ ባክቴሪያዎችን ተጠቅሞ ነው የባዮሎጂያዊ ሪያክሽንን የሚቀሰቅሰውና በሽታ አስተላላፊ አካላት መኖራቸውን የሚያመላክተው፡፡ ሆኖም ባክቴሪያዎቹን ለተራዘመ ጊዜ በህይወቴ ማቆየቱ አስቸጋሪ ስለሆነ የመሳርያውን ብቃት ገድቦት ቆይቷል፡፡
በሀርቫርድ እና ማሳቹሴት ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ አጥኚዎች ታድያ ከህዋሶቹ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑትን ባዮሎጂያዊ ቁሶች በማውጣት አቀዝቅዘው አደረቋቸው፤ በሂደቱም ከባዮሎጂያዊ ቁሶቹ ውስጥ ውሃውን በመምጠጥ አወጡት፡፡ በዚህም ውሃ ሲጨመርበት ብቻ ዳግም የሚነቃ ባዮሎጂያዊ ቁስ መፍጠር ችለዋል፡፡
ማስኩ አንድን ቁልፍ ተጭኖ ውሃን በመልቀቅ ብቻ ሦስት የተለያዩ ባዮሎጂያዊ ሪአክሽኖች በተከታታይ ይሰጣል፡፡ የመጀመሪያው ሪአክሽን የሳርስ-ኮቭ-2 ቫይረሶችን ሜንብሬን በመስበር አርኤንኤያቸውን ያጋልጣል፡፡ ሁለተኛው ሪአክሽን ደግሞ የቫይረሱ የፕሮቲን እሾሆችን ኢንኮድ የሚያደርገውን በራሒ ኮፒ ሲያደርግ ሦስተኛው በበኩሉ የእሾሆቹን በራሂ በመለየት የፍሎረሰንት ሞለኪውሎችን አክቲቬት ያደርጋል፡፡
ሆኖም ቴክኖሎጂው የራሱ ውስንነቶች አሉበት፡፡ ለምሳሌ ባዮሴንሰሮቹ አንዴ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆኑ በእርጥበታማ አየር ውስጥም እንደልብ ላይሰሩ ይችላሉ፡፡ በአንፃሩ ዋጋቸው አነስተኛ መሆኑ በከፍተኛ መጠን ማምረቱን ቀላል አድርጎታል፡፡
ምንጭ፤ Cosmos
ለተጨማሪ፤ https://cosmosmagazine.com/health/covid/smart-masks-to-detect-covid-19/?utm_content=buffere055e&utm_medium=social&utm_source=twitter.com&utm_campaign=buffer

Cosmos Magazine
Smart masks to detect COVID-19
What if biosensors woven into your mask could detect if you have been infected with COVID-19?