TechIn2
1.16K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የአለማችን ፈጣኑ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል
*********************************************
በእንግሊዝ የሚገኝ አንድ የሞተር ሳይክል አምራች ድርጅት በምድር ላይ ከሚደረጉ የተሸከርካሪ ጎዞዎች ሁሉ እጅግ ፈጣን የሆነ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ለመስራት ማቀዱን አሳውቋል፡፡ አሁን ላይ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሎች ሀይልን በፍጥነት ከመሙላት ጀምሮ የተለያዩ ዘመናዊ የሚያደርጋቸውን ማሻሻያዎች እየተሰራላቸው ለውድድርም ሆነ ለመደበኛ አገልግሎት እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡
በአለማችን ከተደረጉ የሞተርሳይክል ፍጥነት ውድድሮች ውስጥ በጣም ፈጣን የተባለው ሰዓት ማክስ ቢያጊ የተሰኘ ተወዳዳሪ ቮክሳን ዋትማን የተሰኘውን የሞተር አይነት 254 ኪሎ ሜትር ማሽከርከር የቻለበት ነው፡፡ አዲሱ የሞተር ሳይክል አይነትም የሚደረግለት ማሻሻያ የአለማችን እጅግ ፈጣኑ የኤሌክትሪክ ሞተር እንዲሆን ያስችለዋል፡፡ ከሚደረግለት ማሻሻያ ውስጥም በእንቅስቃሴ ጊዜ የሚኖርን ነፋስ የሞተሩን ጉልበት በማይቀንስ መልኩ ሞተሩ እንዲንቀሳቀስ የሚያስችለው ነው፡፡ ሞተሩ አሁን ባለው ይዞታ በንፋስ ምክንያት የሚደርስበትን የፍጥነት ገደብ በሚሰራለት ማሻሻያ በ70 በመቶ መቀነስ ይችላል ሲል ድርጅቱ አሳውቋል፡፡
ምንጭ Engadget
ተጨማሪ ንባብ https://www.engadget.com/electric-motorcycle-land-speed-record-100503362.html?src=rss&fbclid=IwAR11lokyJC01QfNuiEOiR9uNWe3fykyMjrSK339DK_jnuEW451bYisXQ3WA
እንግሊዝ ውስጥ በኮቪድ 19 እየሞቱ ካሉት አብዛኛው የተከተቡ መሆናቸው ተነገረ
እንግሊዝ ውስጥ በኮቪድ 19 እየሞቱ ካሉት አብዛኛው የተከተቡ መሆናቸው ተነገረ
==========
ከጥቂት ቀናት በፊት የወጣ አዲስ መረጃ እንደሚያመላክተው እንግሊዝ ውስጥ ቢ.1.617.2 ተብሎ በሚጠራው የኮቪድ 19 አይነት ከሞቱት 117 ሰዎች ውስጥ 50ዎቹ ወይም 43 በመቶ የሚሆኑት የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባትን የተከተቡ መሆናቸውን ነው፡፡

ሁኔታው የተከሰተው በተለይም ክትባቶቹን የሚወስደው ሰው ላይ የሚኖራቸው ውጤታማነት እንደ ሰውዬው እድሜና ክትባቱን የተቀበለበት መንገድ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡ ክትባቶቹ በኮቪድ 19 የመሞት ዕድልን በ94 በመቶ የሚከላከሉ ቢሆንም በኮቪድ የመሞት ምጣኔው ግን በተለየ መልኩ እድሜ ላይ ጥገኛ ነው፡፡ እንበልና በኮቪድ 19 የተያዘ አንድ ሰው ዕድሜው በስድስት ወይም በሰባት ዓመት በጨመረ ቁጥር በቫይረሱ የመሞት ዕድሉም በግማሽ ይጨምራል፡፡ ይህም አንድ ዕድሜው 80 ላይ የሚገኝ ክትባቱን የወሰደ ሰው በኮቪድ አማካኝነት የመሞት እድሉ እድሜው 50ዎቹ ውስጥ ሆኖ ግን ደግሞ ክትባትን ካልወሰደ ሰው ጋር እኩል ነው እንደማለት ነው፡፡

መረጃው እንደሚያሳየውም በተጠቀሰው የኮሮና ቫይረስ አይነት ተጠቅተው ከሞቱት ውስጥ አንድ ሦስተኛው ዕድሜያቸው 50ን የተሻገረ ነው፡፡ ታድያ በሀገሪቱ እድሜያቸው ከ65 እስከ 69 ከሆኑት ውስጥ ከ93 በመቶ የሚልቁት ክትባቱን የወሰዱ ናቸው፡፡

ምንጭ፤ The Guardian
ለተጨማሪ፤ https://www.theguardian.com/theobserver/commentisfree/2021/jun/27/why-most-people-who-now-die-with-covid-have-been-vaccinated?utm_source=dlvr.it&utm_medium=twitter&fbclid=IwAR2ZauoFZWTA1Qbe5rkCZPlM8OP-697iNjkbIbhp5tRTqwovfOd-7dVFWnQ
በአለማችን በግዙፍነቱ ሁለተኛ የሆነው የውሃ ሀይል ማመንጫ
በአለማችን በግዙፍነቱ ሁለተኛ የሆነው የውሃ ሀይል ማመንጫ
***********************************************************
ቻይና በአለማችን በግዝፈቱ ሁለተኛ የሆነውን የውሃ ሀይል ማመንጫ ስራ ማስጀመሯ ተነገረ፡፡ ይህ ግዙፍ የውሃ ሀይል ማመንጫ ግንባታ ቻይና ከካርቦን ነጻ የሆነ ቀጠናን ለመፍጠር የምታደርገው ጥረት አካ መሆኑ ተነግሯል፡፡ በቻይና ደቡብ ምዕራብ ክፍል የሚገነባው የሀይል ማመንጫው 289 ሜትር ከፍታ ያለው ነው፡፡
ባይሄታን የተሰኘው የቻይና ግዙፉ የሀይል ማመንጫ ባሳለፍነው ሰኞ በከፊል ስራ የጀመረ ሲሆን በአጠቃላይ 16 ሺህ ሜጋ ዋት ሐይል እንዲያመነጭ ታልሞ የተገነባ ነው፡፡ የመረጃ ምንጫችን ሲሲ ቲቪን ጠቅሶ ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በአንድ ቀን የሚያመነጨው ሀይል የአምስት መቶ ሺህ ሰዎችን የአመት የሐይል ፍላጎት ማሟላት የሚችል ነው፡፡ ይህም በአለማችን ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር ለያዘችው ሀገረ ቻይና እያደገ የመጣውን ከፍተኛ የሆነ የሀይል ፍላጎት ለማሟላት የምታደርገውን ጥረት ለማሳካት እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡
በስራ ማስጀመሩ ዝግጅት ላይ የተገኙት የቻይናው ፕሬዘዳንት ሺ ዢንፒንግ የፕሮጀክቱ ተጠናቅቆ ስራ መጀመር በዋናነት ከካርቦን ነጻ የሆነች ቻይናን ብሎም አለምን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ ያግዘዋል ብለዋል፡፡ ባለፈው አመት ፕሬዘዳንቱ ለ2060 የተቀጠረውን ከካርቦን ነጻ ቀጠና የመፍጠር እቅድ በማስታወስ የግንባታ ስራው እንዲፋጠን ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡
ይህ የቻይናውን ረጅሙን ወንዝ ያንግቲዝን መሰረት አድርጎ የተሰራው ግዙፍ የሀይል ማመንጫ ለሀይል አቅርቦት ካለው አዋጭነት በተቃራኒ ከእጽዋት ዝርያ መጥፋት፣ ከወንዝ ዳርና የወንዝ ውስጥ ተፈጥሯዊ ሁኔታ መለወጥና በለውጡም ምክንያት ሊከሰት የሚችልን የሰዎችና አጠቃላይ አካባቢያዊ ጤና መቃወስን በሚመለከቱ ጉዳዩች ከአካባቢ ጥበቃ ሙያተኞችና ተመሳሳይ ተመራማሪዎች በኩል ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡
አለማችን የሀይል አቅርቦቷን ለማሳደግ ብሎም የህዝቦቿን ይህወት ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረት በምታደርግበት በዚህ ዘመን የኛውም እንደ ወተት እንደ ማር ጠብቀን ተንከባክበን ልንጠቀምበት ይገባን በነበረው ወንዛችን አባይ ላይ የምንሰራው ግድብ በቶሎ ተጠናቅቆ በሚሰጠን በረከት ወደ ልማትና ወደ ተሻለ ሀገራዊ እድገት መጓዝ እንድንችል ሁላችንም ሀገራዊ አንድነታችንን እንጠብቅ፡፡ ከዚህም ባሻገር ለግድቡ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቅ የሚጠበቅብንን እንወጣ፡፡ (የጸሐፊው መልእክት ነው)
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-06-world-second-largest-hydropower-online-china.html?fbclid=IwAR3m5eD8mmsPMDEDuHiYuzjBb5G2pzpqrgL2zGn7k2BfPUUcTVaCrChBAlk
አዲሱ የክብደት መቀነሻ ቴክኖሎጂ
አዲሱ የክብደት መቀነሻ ቴክኖሎጂ
*******************************
ተመራማሪዎች የሰዎችን አፍ የመከፈት አቅም በእጅጉ የመኒቀንስ አዲስ የክብደት መቀነሻ ቴክኖሎጂ መስራታቸውን ይፋ አደረጉ፡፡ ቴክኖሎጂው በሰዎች አፍ ውስጥ የሚገጠም እና የላይ ኛውንና የታችኛውን አገጭ የመላቀቅ መጠን ወይም የአፍን የመከፈት መጠን የሚቀንስ ነው፡፡ አላማውም ሰዎች ምግብ የመብላት ፍላጎታቸውንና ችሎታቸውን በመቀነስ ፈሳሽ ነገሮችን ብቻ እዲወስዱ የሚያደርግ ነው ተብሎለታል፡፡
የአገጭ ማጣበቂያ ቁሱ ዴንታልስሊም የምግብ ፍላጎት መቆጣጠሪያ የሚባል ሲሆን በላይኛውና በታችኛው መንጋጋ የሚጣበቅ ማግኔት ያለው ነው፡፡ ይህም አፍ ከ2 ሚሊሜትር በላይ እንዳይከፈት የሚያደርግ ነው፡፡ ይሁን እንጂ መረጃውን በቲውተር በኩል የሰሙ የቲውተር ደንበኞች የተለያዩ ተቃውሞዎችን እያሰሙ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ከሞራል እና ከእውናዊነት አንጻር የተነሱ ጥያቄዎች ይገኙበታል፡፡
ቴክኖሎጂው በኒውዝላንዱ የኦታጎ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተሰራ ሲሆን በሙከራ ጊዜ በሰባት ፈቃደኞች ላይ ጥናት ተካሂዶበታል፡፡ ሰባቱ ሰዎች መሳሪያውን ካስገጠሙ በኋላ የተለያዩ ፈሳሾችን ብቻ የወሰዱ ሲሆን በሁለት ሳምንት ውስጥ በአማካኝ 6.36 ኪሎግራም መቀነስ ችለዋል፡፡ ቴክኖሎጂው ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የማያስከትልና በቀዶ ህክምናና በተለያዩ መድሃኒቶች ከሚደረግ የክብደት ቅነሳ ቴክኖሎጂ እጅግ የተሸለ እንደሆነ ተመራማሪዎቹ አሳውቀዋል፡፡
በቲውተር በኩል እጅግ ብዙ በሆኑ ሰዎች ትችት የደረሰበት የኦታጎ ዩኒቨርሲቲ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ተገድዷል፡፡ በዚህም መሳሪያው የረጅም ጊዜ ወይም የአጭር ጊዜ የክብደት መቀነሻ አማራጭ ሳይሆን ክብደታቸውን በቀዶ ህክምና ለመቀነስ የተገደዱ ሰዎች ለዚህ የሚሆን ወጭ ወይም ገንዘብ በማይኖራቸው ጊዜ ሊጠቀሙት የሚችሉት እንደሆነ ተናግሯል፡፡
ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/health-and-medicine/scientists-develop-weightloss-device-that-locks-peoples-jaws-shut-and-twitter-is-not-happy/?fbclid=IwAR1jKTVfnhEvO4e1tF5R5KTEGc_RN29a7TzmVpnAI_sDZYU2CB519U5utbQ
እስራኤል ውስጥ ከዚህ ቀደም የማይታወቁ ጥንታዊ የሰው ልጅ ዝርያዎች ተገኙ
እስራኤል ውስጥ ከዚህ ቀደም የማይታወቁ ጥንታዊ የሰው ልጅ ዝርያዎች ተገኙ
ከዚህ ቀደም የማይታወቁ ጥንታዊ የሰው ልጅ ዝርያዎች በእስራኤል ለመቶ ሺዎች ዓመታት ይኖሩ እንደነበረ አዲስ ጥናት አመላከተ፡፡ እነዚህ ዝርያዎች ታድያ ከዘመናዊ የሰው ልጅ ጎን ለጎን ይኖሩ እንደነበርና የተለያዩ ክህሎቶችንም ይማማሩ ነበረ ነው የተባለው፡፡ በተጨማሪም አዲስ የተገኙት ዝርያዎች ኋላ ላይ አውሮፓንና ምዕራባዊ እሲያን እንዳጥለቀለቁና መነሻቸውም በዚያው በምዕራባዊ እሲያ መሆኑ የሚነገርላቸው የሰው ልጅ ዝርያዎች ቅድመ አባት መሆናቸውን ጥናቱን ያጠናው ቡድን ይናገራል፡፡
የጥንታዊ ሰዎቹ ቅሪት የተገኘው ነሺር ራምላህ ውስጥ በሲሚንቶ ፋብሪካ ቁጥጥር ስር ባለ ቦታ ላይ ነው፡፡ ቦታው ከዚህ ቀደም ዝቅተኛ ስፍራ የነበረ ሲሆን ኋላ ላይ በአፈር ሊሞላ ችሏል፡፡ ቅሪቶቹን ሸፍኖ የተገኘው አፈርም ዕድሜው ከ140,000 እስከ 120,000 የሚገመት ነው፡፡
ተመራማሪዎቹ ታድያ አዲስ የተገኙትን ቅሪቶች ወስደው ቅርፃቸውን ከሌሎች ጥንታዊ የሰው ልጅ ዝርያዎች ጋር ቢያነፃፅሩም በቀላሉ ሆሞ ሳፒያን አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ችለዋል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ ቅሪቶቹ ከሌላ ከማንኛውም በጊዜው ከነበረ ጥንታዊ የሰው ልጅ ዝርያ ቡድን ጋር የማይገናኙ መሆናቸውን ጭምር አወቁ፡፡
ሆኖም ቅሪቶቹ ከጊዜው ቀደም ብለው በእስራኤልና ሰሜናዊ ስፔን ውስጥ ይኖሩ ከነበሩ የቅድመ ታሪክ ዝርያዎች እንዲሁም ቻይና እና ህንድ ውስጥ ይኖሩ ከነበሩ ጥንታዊ ዝርያዎች ጋር መመሳሰልን ስለማሳየታቸው በተመራማሪዎቹ ተነግሯል፡፡ በሌላ መልኩ የጥናት ቡድኑ አሁን የተገኙት ዝርያዎች በመምዕራባዊ እሲያ ውስጥ ከዛሬ 420,000 እስከ 120,000 ዓመታት በፊት ይኖሩ ከነበሩት ጥንታዊ የሰው ልጅ ዝርያዎች ጋር በአንነት እንታዩ ጠይቀዋል፡፡
ምንጭ፤ New Scientist
ለተጨማሪ፤ https://www.newscientist.com/article/2282141-newly-identified-ancestor-of-neanderthals-complicates-the-human-story/?utm_term=Autofeed&utm_campaign=echobox&utm_medium=social&utm_source=Twitter#Echobox=1624750356
አዲስ ስልክ ወይም ላፕቶፕ ሲገዙ ሊያደርጓቸው የሚገቡ አራት የመጀመሪያ ነገሮች
አዲስ ስልክ ወይም ላፕቶፕ ሲገዙ ሊያደርጓቸው የሚገቡ አራት የመጀመሪያ ነገሮች
*************************************************************
እየተሻሻለ በመጣው የቴክኖሎጂ አለም በየጊዜው ዘመናዊ የሆኑ የቴክኖሎጂ መጠቀሚያ ቁሶችን እየቀረቡ መሆናቸው ሚታወቅ ነው፡፡ ለምሳሌ ስለሞባይል ስልክ እንኳን ቢነሳ በጣም አስገራሚ የሆነ መሻሻሎች ተደርገዋል፡፡ ታዲያ በየጊዜው የሚመጡ የተሸሻሉ ስልኮችን ወይም ላፕቶፖችን መግዛት ከጊዜው ጋር ለመዘመን የምናደርገውን ጥረት በእጅጉ ያግዘዋል፡፡

አንድን አዲስ ስልክ ስልክ ወይም ላፕቶፕ ከገዛን በኋላ የተለያዩ አገልግሎቶችን መጠቀም ከመጀመራችን በፊት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አራት መሰረታዊ ነገሮች በቅድሚያ መፈጸም ይኖርብናል፡፡

የመጀመሪያው የተለያዩ የመተግበሪያ እና የፕሮግራም እድሳቶችን ማድረግ (Install all updates) ነው፡፡ ይህም ስልኩ አገልግሎት ከመጀመሩ በፊት የተለያየ ነገር ታክሎባቸው የቀረቡ የተለያዩ መተግበሪያዎችና ፕሮግራሞች ካሉ በአዲስ መልክ ስራቸውን እንዲሰሩ ያስችላቸዋል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ የመረጃ ደህንነት ማስተካከያ (Set up security) መስራት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ አዳዲስ መጠቀሚያዎች ምንም አይነት የደህንነት ገደብ ስለማያስቀምጡ በስልኩ ውስጥ ወይም አዲስ በገዛነው ቁስ ውስጥ የተለያዩ ግላዊ መረጃዎችን ለማከማቸት በቅድሚያ የደህንነት ማስተካከያ መስራት ተገቢ ነው፡፡ የስልክ ወይም የታብሌት ደህንነት የሚጀምረው ጠንካራ የስክሪን መቆለፊያ በመጠቀም ነው፡፡

ለኮምፒውተር ደግሞ ለእያንዳንዱ መተግበሪያ የሚሆኑ የተለያዩ የመቆለፊያ ዘዴዎች ስላሉ እነሱን መጠቀም በጣም ተመራጭ ነው፡፡
ኮምፒውተሮች በተለያዩ የደህንነት ኮዶች በመጠቀም ከሚደረግላቸው ጥበቃ በተጨማሪ የጸረ ቫይረስ መተግበሪያዎችንና ፕሮግራሞችን በመጠቀም ደህንነታቸውን መጠበቅ የሚበጅ ነው፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ የተለያዩ መረጃዎችን ከቀድሞ መጠቀሚያዎቻችን ወደ አዲሶቹ መገልበጥ ነገሮችን እንደ አዲስ እንዳንጀምር ያደርገናል፡፡

አንድን መረጃ በስልካችን ወይም በላፕቶፓችን ውስጥ መያዝ ሁሌም ከእኛ ጋር ለመሆኑ ማረጋገጫ ስለማይሆን በአራተኛ ደረጃ የመጠባበቂያ ዘዴን (back up) መጠቀም ጥሩ ነው፡፡ ይህም በስልካችን ወይም በላፕቶፓችን ላይ ያልተጠበቀ ብልሽት ወይም መጥፋት ቢያዳኝም ባዶ እጃችንን እንዳንቀር የሚያደርገን ነው፡፡ ለዚህም የተለያዩ የክላውድ ማከማቻ አማራጭ መንገዶች አሉ፡፡
ምንጭ Popular Science
ተጨማሪ ንባብ https://www.popsci.com/set-up-new-gadget/?utm_campaign=trueAnthem%3A%20Trending%20Content&utm_medium=trueAnthem&utm_source=facebook&fbclid=IwAR2ICYlCG2O58RcfNl7a_P_VumnIO-mZFqZZ4fN1spPz3xY9E853dTxMFVc
80 ሺህ ቤቶችን የሚያበራው ሰማይ ጠቀስ የነፋስ ኃይል ማመንጫ
80 ሺህ ቤቶችን የሚያበራው ሰማይ ጠቀስ የነፋስ ኃይል ማመንጫ
================
አንድ የኖርዌይ ጥምረት በአንድ ጊዜ ለ80 ሺህ ቤቶች የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ ይችላል ያለውን ግዙፍ የነፋስ ኃይል ማመንጫ ንድፍ ሰርቶ ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ በአስቢዮን ኔየስ ንድፉ ተሰርቶ የቀረበው የነፋስ ኃይል ማመንጫ በአግባቡ ይሰራ ዘንድ ቁመቱ በትንሹ ከ300 ሜትር በላይ ሆኖ መገንባት ያለበት ሲሆን ይህም በንፃሬ እንኳን ብናየው እውቅ ከሆነው የፓሪሱ ኤፍል ማማ የላቀ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
አሁን ላይ በዋናነት ጥቅም ላይ የሚውሉት የነፋስ ኃይል ማመንጫዎች ሆሪዞንታል አክሲስ ዊንድ ተርባይን (HAWT) ተብለው የሚጠሩት በረጅም ዘንግ እና እርሱ ላይ የሚተከል በንፋስ የሚሽከረከር ተርባይን ያላቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ተለምዶአዊ የነፋስ ኃይል ማመንጫዎች ታድያ የራሳቸው የሆኑ ድክመቶች አሉባቸው፡፡ ከነዚህ መካከል የዋጋቸው ነገር አንዱ ሲሆን ለጥገና ብቻ በየዓመቱ ከ42 እስከ 48 ሺህ ዶላር ወጪን ይጠይቃሉ፡፡ አዲሱ ፈጠራ ታድያ ተርባይኖቹን የመጠገኑን ስራ የቀለለ በማድረግ ይህን ወጪ እንደሚቀንስ ተነግሮለታል፡፡
ኃይል በማመንጨት ረገድም ተለምዶአዊዎቹ ተርባይኖች ከመጠን በላይ የሚፈጥኑ ከሆነ የሚሰናከሉ በመሆናቸው ፍጥነታቸው እንዲገደብ ይገደዳሉ፡፡ በዚህ ረገድ አዲሱ ቴክኖሎጂ ላይ የሚተከሉት ተርባይኖች በመጠናቸው አነስተኛ ከመሆናቸው የተነሳ በከፍተኛ ፍጥነት መሽከርከርና ተለምዶአዊዎቹ ተርባይኖች ከሚሽከረከሩበት በሴኮንድ 12 ሜትር እጅጉን በተሻለ የ17 እና 18 ሜትር ፍጥነት መሽከርከር እንደሚችሉ የፈጠራው አፍላቂዎች ይናገራሉ፡፡ እንደ ቴክኖሎጂው ፈጣሪዎች ከሆነ አነስተኛ ሽክርክሮችን በዛ አድርጎና አጠጋግቶ ማስቀመጡ አንድ ግዙፍ ሽክርክርን አስቀምጦ ከሚገኘው የላቀ ኃይልን እንደሚሰጥ በሙከራ አረጋግጠዋል፡፡
ሌላው በአዲሱ ቴክኖሎጂ ይቀረፋል የተባለለት የነፋስ ኃይል ማመንጫዎች ችግር ወፎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት ነው፡፡ በአሜሪካን ብቻ በየዓመቱ ከ140 እስከ 500 ሺህ ወፎች በነፋስ ኃይል ማመንጫ ሽክርክሮች ተገጭተው ይሞታሉ፡፡ ይህን ይቀንስ ዘንድ አዲሱ ስልት መዋቅሩ ከተለምዶው ወጣ ባለ መልኩ ጥቁር ቀለም እንደሚቀባና ለወፎቹም ይበልጥ የሚታይ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ቴክኖሎጂው ገና በሂደት ላይ ያለና ለተግባር ይበቃ ዘንድም ልዩ ልዩ ስራዎች ገና የሚቀሩት ነው፡፡
ምንጭ፤ Daily Mail
ለተጨማሪ፤ https://www.dailymail.co.uk/sciencetech/article-9726193/Offshore-Windcatcher-stacks-turbines-taller-Eiffel-Tower-power-80-000-homes.html
ለ125 ዓመታት የጠፋችው አይጥ ተገኘች
ለ125 ዓመታት የጠፋችው አይጥ ተገኘች
===========
ከ125 ዓመታት በፊት ዝርያዋ መጥፋቱ የተነገረላት የጉልድ አይጥ (Pseudomys gouldii) አውስትራሊያ ውስጥ መኖሯ ተረጋገጠ፡፡ በኤሚሊ ሮይክሮፍት የሚመራው የተመራማሪዎች ቡድን የአይጥ ዝርያዎች ዘረ መላዊ ብዛ ህይወትን ለማጥናት በወጡበት ጊዜ ነው ይህች ለነዚህ ሁሉ ዓመታት ተሰውራ የቆየችው የአይጥ ዝርያን በአንድ የአውስትራሊያ ደሴት ውስጥ አግኝተው አሁንም ምድር ላይ መኖሯን ያረጋገጡት፡፡

አይጧ እራሷ ዝርያዋ መሆኗን ለማወቅ ተመራማሪዎቹ የዘረ መል ናሙናዎችን ከአይጧ ላይ ወስደው በብሪታኒያ እና አውስትራሊያ ሙዚየሞች ውስጥ ካሉ ናሙናዎች ብሎም በህይወት ካሉ የቅርብ ዝርያዎች ጋር በማነፃፀር ነው እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሱት፡፡ ባልተጠበቀ ሁኔታም ምርምሩ የሻርክ ቤይ አይጥ ይባሉ የነበሩት ዝርያዎች ጉልድ አይጦች መሆናቸውን ማሳየት ችሏል፡፡ ከዚህም ባሻገር የጉልድም ሆነ ሌሎች በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተሰበሰቡና አሁን ከምድረ ገፅ የጠፉ አይጦች ዘረ መላዊ ብዛ ህይወት በአካባቢው ከፍተኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

የጥናቱ ውጤት ልዩ ልዩ የአይጥ ዝርያዎች ከመጥፋታቸው በፊት በቁጥር በዛ ብለው የተረጋጋ ህይወትን ይመሩ እንደነበር ጥቁምታን ሰጥቷል፡፡ ታድያ ለነዚህ አይጥ ዝርያዎች መጥፋት የአውሮፓውያን ቅኝ ግዛትና ወደ አውስትራሊያ ሲመጡ ይዘዋቸው የመጧቸው እንደ ድመትና ቀበሮ ያሉ አዳኝ እንስሳት፣ የሰደድ እሳት ቁጥጥር ስልት መቀየር፣ የአዳዲስ በሽታዎች መተዋወቅ እንዲሁም ኢንዱስትሪና ግብርናን በማለም የተከናወኑ የመሬት ማጥራት ስራዎች ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችል ተቀምጧል፡፡ ዳግም የተገኙት የጉልድ አይጥ ዝርያዎችም በህይወት ለመቆየታቸው ምክንያቱ የመኖርያ ስፍራቸው ድመትና ቀበሮ ከማይደርሱባቸው የባህር ዳርቻዎች በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፤ New scientist
ለተጨማሪ፤ https://www.newscientist.com/article/2282406-an-australian-mouse-thought-to-be-extinct-still-survives-on-an-island/?utm_term=Autofeed&utm_campaign=echobox&utm_medium=social&utm_source=Twitter#Echobox=1624911424
ያለ ሰው ለ24 ሰዓታት መስራት የሚችለው ራስ ገዝ የኤክስካቫተር ስርዓት
ያለ ሰው ለ24 ሰዓታት መስራት የሚችለው ራስ ገዝ የኤክስካቫተር ስርዓት
============
በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሜሪላንድ የሚገኙ ተመራመሪዎች ያለ ሰው ልጅ ጣልቃ ገብነት በራሱ መስራት የሚችል ራስ ገዝ የኤክስካቫተር ስርዓትን አስተዋውቀዋል፡፡ ስርዓቱ በስራ ላይ ለመሰማራት ቀዳሚ ከሆኑ ሰው አልባ የቁፋሮ መሳርያ ስርዓቶች አንዱ ሲሆን ያለማቋረጥ ለ24 ሰዓት በመስራትም ለግንባታ ኢንዱስትሪው ላቅ ያለ ትርፈፍን እንደሚያስገኝ ተነግሮለታል፡፡
ኤክስካቫተሮች በመሰረተ ልማት ግንባታ፣ መዓድን ማውጣት እንዲሁም ነፍስ አድን ስራዎች ውስጥ የማይተካ ሚናን ይጫወታሉ፡፡ በዚህም የተነሳ በአውሮፓውያኑ 2018 ብቻ ዓለም አቀፍ የኤክስካቫተር ገበያ 44.12 ቢሊዮን ዶላር ደርሶ የነበረ ሲሆን ይህ አሃዝ ከአምስት ዓመታት በኋላ በ2026 ወደ 63.14 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያድግ ተተንብይዋል፡፡ ይህን የገበያ እድገት ተከትሎ ታድያ በዓለም ዙርያ ያሉ የግንባታ ኩባንያዎች ኤክስካቫተሮችን የሚያንቀሳቅስ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት እያጋጠማቸው ይገኛል፡፡ ከዚህም ባሻገር ስራው በተለይም እንደ መደርመስ ያሉ አደጋዎችን የሚያስከትል ከመሆኑ ጋር በተያያዘም ባለሙያዎችን በከፍተኛ የጤናና ደህንነት ስጋት ውስጥ የሚከት መሆኑ ሌላኛው ችግር ነው፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካን ብቻ ከኤክስካቫተር ጋር በተያያዘ በየዓመሩ 200 የሰው ልጆች ሞት ይከሰታል፡፡ በነዚህ ተግዳሮቶች መነሻነት ኢንዱስትሪው ፊቱን ወደ ቴክኖሎጂ እንዲያዞር እየተገደደ ይገኛል፡፡
ከሌሎች ሮቦቶች በተለየ መልኩ ራስ ገዝ ኤክስካቫተሮች በአደገኛ ከባብያዊ ሁኔታዎች ውስጥ መስራት መቻልና ቁሶችን መለየት፣ እንቅፋቶችን መሻገር፣ በቁጥጥር ስር ሊሆኑ በማይቻሉ ሁኔታዎች ውስጥ መስራት እንዲሁም በአስቸጋሪ የአየር ፀባዮች ውስጥ ስራቸውን ማከናወን አለባቸው፡፡ አዲሱ ስርዓትም በፍጥነት የሚሰሩ ቀመሮችን ተጠቅሞ የምልከታ፣ ዕቅድ ማቀድ እና መቆጣጠር ተግባራትን ከራስ ገዝነት ጋር በማዋሀድ ተገንብቷል፡፡ በዚህም ከባቢውን ከፍተኛ የምስል ጥራት ባለው በባለ ሦስት እይታ ተመልክቶ ተፈላጊ ቁሶችን እንዲለይና እንዲሰራ የሚያስችሉት የጨረር መመልከቻ (LiDAR)፣ ካሜራ እና ሴንሰሮች ተገጥመውለታል፡፡ እንዲሁም ስርዓቱ ከትናንሾቹ የ6.5 እና 7.5 ሜትሪክ ቶን ኤክስካቫተሮች አንስቶ እስከ ግዙፎቹ የ49 ሜትሪክ ቶን ኤክስካቫተሮች ድረስ ተገጥሞ በብቃት መስራት ይችላል ተብሎለታል፡፡
ተመራማሪዎቹ የስርዓቱን ውጤታማነት ለመለካት በደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ላይ ወስደው የሞከሩት ሲሆን በውጤቱም የሴንሰሮችን ብቃት ያወርዳል በሚባልበት የከፍተኛ ብርድ ውስጥ ጭምር ያልተቋረጠ የ24 ሰዓት አገልግሎትን ሲሰጥና በሁሉም የአየር ፀባይ ሁኔታዎች ሳይለዋወጥ በሰዓት የ67.1 ኪዩቢክ ሜትር ቁፋሮ ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
ምንጭ፤ Tech Xplore
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/news/2021-06-autonomous-excavators-ready-clock-real-world.html?fbclid=IwAR1ysVJCD3nyMZ524c44nEnpSc08LjuykIAZNBwStkrMGrTdrmoiBwxKLLM
በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መካከል
በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መካከል
***********************************************************************
በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መካከል በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ፊርማ ተከናወነ፡፡ ሁለቱ ተቋማት የተቋቋሙበት የየራሳቸው ራዕይና ተልዕኮ ያላቸው ሲሆን በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኩል ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን
የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ ተግባራት መካከል ተቋማት የዘመነ አሰራር እንዲዘረጉና የተቋቋሙበትን አላማ በቅልጥፍና፣ በፍጥነት እና በጥራት ለመተግበር እንዲችሉ የሚያደርጉ አሰራሮችን፣ ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ መደገፍና የተለያዩ የክህሎት ክፍተቶችን በስልጠናዎች መድፈን አንደኛው ነው፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በበኩሉ በሀገራችን የኢንዱስትሪ ፓርኮች እየተስፋፉ መምጣታቸውን ተከትሎ የተቋቋመ መንግስታዊ ድርጅት ሲሆን ከዘርፉ ሊገኝ የሚገባውን ሀገራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና በዘርፉ ወጥና ዘመናዊ የሆነ አሰራር እንዲኖር ለማድረግ ብሎም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ዙሪያ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ሀገራችን ኢትዮጵያ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንድትሆን ከፍተኛ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
የስምምነት ፊርማ መርሃ ግብሩ ላይ በስምምነቱ ዙሪያ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ሳንዶካን ደበበ የስምምነት ሰነዱን የመፈረም ፋይዳ እና አስፈላጊነት እንዲሁም ተቋማቱ በጋራ ተብባብረው የመስራት ቁርጠኝነት አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አመራሮቹ ሁለቱ ተቋማት ከዚህ በፊትም የተለያዩ ስራዎችን በጋራ የሰሩ እና እየሰሩ ያሉ መሆኑን ገልጸው ስምምነቱ በጋራ የመስራት አቅማቸውን እንደሚያሳድግላቸው እና በመካከላቸው ያለዉን ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በስምምነት ሰነድ ፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይም ከየተቋማቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡