TechIn2
1.16K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የተሻሻሉ የመንገደ ዳር መገልገያዎች ለከተሞች ዘመናዊነት
************************************************************
የአለማችን ዘመናዊ ከተሞች ዘመናዊነታቸው ከሚለካባቸው መገለጫዎች መካከል ዋነኛው ለነዋሪዎቻቸው ያላቸው ምቹነት ነው፡፡ የነዋሪዎች እና የእንግዶች ምቹነት ሀሳብ ሲነሳ ምቹና ተደራሽ የሆነ የመሰረተ ልማት አማራጭ በከተሞቹ ውስጥ መዘርጋት ቀዳሚው ተጠቃሽ ጉዳይ ነው፡፡ የከተማ ነዋሪዎች በሚኖሩበት ከተማ ምቹነት መጠን ልክ ያላቸው የአኗኗር ዘይቤ የተሻሻለ ወይም የጎሰቆለ ሊሆን ይችላል፡፡ ለዛሬ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ሰፋፊ ከተሞች ላይ ሊኖሩ ስለሚገባቸው የመንገድ ዳር የህዝብ መገልገያዎች ለማንሳት ወደናል፡፡

ለዚህ ጽሁፍ ማሳያነትና ምሳሌነት የሀገራችን ኢትዮጵያ ብሎም የአህጉራችን መዲና የሆነችውን አዲስ አበባችንን እናነሳለን፡፡ ከተማችን አዲስ አበባ ከጥቂት አመታት ወዲህ ፈርሳ በሚያስብል መልኩ እየተሰራች መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ በስራሂደቷም በቅርብ ጊዜያት እያስተዋልናቸው ካሉ ጅማሮዎች ውስጥ ዘመናዊ የሆኑ የመንገድ ዳር የህዝብ መገልገያዎች በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያክልም የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች፣ የመኪና ማቆሚያዎች፣ የመንገድ ዳር ማረፊያ ወንበሮችና ምቹና ሰፋፊ የሆኑ የእግረኛ መንገዶች ይገኙበታል፡፡

እንደነዚህ አይነት መገልገያዎች ከመሰራታቸው ባሻገር ለአጠቃቀም ያላቸው ምቹነትና ዘመናዊነታቸው ሊታሰብበት የሚገባ መሆኑ በአለማችን ያሉ ሰፋፊ ከተሞች ልምድ ያሳየናል ለምሳሌ በአውስትራሊያ ከተሞች እየተተገበሩ ያሉ የመንገድ ዳር መገልገያዎች ስማርት የሆኑና የተለያዩ ዲጂታል መረጃዎችን ማመንጨት ብሎም መሰብሰብ የሚያስችሉ ናቸው፡፡ እነዚህም መቀመጫዎችን፣ ኪዮስኪዮችን፣ የመብራት ምሶሶዎችን እና የአውቶብስ መቆሚያዎችን የሚያጠቃልሉ ናቸው፡፡ የመንገድ ዳር መገልገያዎቹን ዘመናዊ ከሚያሰኛቸው ነገሮች መካከል እርስ በርሳቸው በኔትወርክ የተገናኙ መሆናቸው ነው፡፡

በአውስትራሊያ ከተሞች እየተተገበሩ ያሉ የከተማ ማዘመኛ የመንገድ ዳር መገልገያዎች ከመደበኛ አገልግሎታቸው በተጨማሪ የዋይ ፋይ አገልግሎት፣ ዲጂታል ማስታወቂያ፣ አቅጣጫ መፈለጊያ የአደጋ ጊዜ መጥሪያዎች፣ ስልኮችና ስልኮችንና የተለያዩ ኤሌክትሮኖክሶችን ቻርግ ማድረጊያ ግብአቶችን ሁሉ ያሟሉ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን የግለሰባዊ ደህንነት ተቃውሞ እየገጠመው ቢሆንም የመንገድ ዳር ካሜራዎችም የዘመናዊ ከተሞች መገላጫ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡

ከተማችን አዲስ አበባ ብሎም ሌሎች ከተሞቻችን ዘመናዊነትን የተላበሱ እና ለኑሮ የሚመቹ እንዲሆኑ ከአውስትራሊያ ከተሞች ብዙ መማር ያለብን ነገር እንዳለ ይሰማናል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-06-smart-street-furniture-australia-surveillance.html?fbclid=IwAR3RC5lzdEukYj5RX4EdxEK1H2Bh2qkpP_aQiWFUW3RJkgWGpshda_pnXdM
እባብ አድነው የሚመገቡት ሸረሪቶች
እባብ አድነው የሚመገቡት ሸረሪቶች
========
መርዛማ ሸረሪቶች ከእነርሱ በብዙ እጥፍ የሚገዝፉ መርዛማ እባቦችን አድነው እንደሚመገቡ አዲስ ጥናት አመላከተ፡፡ አዲሱ ጥናት ለ319 ጊዜያት ያህል ሸረሪቶች እባቦችን አድነው ሲመገቡ የተመለከተ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 297 የሚሆነው በዱር ውስጥ የተቀረው ደግሞ ሆን ተብሎ እንዲገናኙ ከተተደረገ በኋላ የተካሄደ ነው፡፡

ነገሩን ለየት የሚያደርገው እባቦችን አድኖ መብላቱ ቁጥራቸው ከ30 በላይ በሚሆን በተለያዩ የሸረሪት ዝርያዎች በዱር ሌሎች 11 ደግሞ በተመደረከ ግንኙነት ላይ የታየ መሆኑ ነው፡፡ ከነዚህ ውስጥ አስፈሪዎቹን ብላክ ዊንዶው (Latrodectus mactans, L. Hesperus, L. variolus) እና አፍሪካን በተን (L. indistinctus) ያሉ ሸረሪቶች የሚገኙበት የዊንዶው ሸረሪቶች ቤተሰብ ነው፤ ከአደኖቹ ውስጥ የግማሽ ድርሻን በመውሰድ፡፡ እነዚህ 1.1 ሴ.ሜ ብቻ የሚረዝሙ ሽረሪቶች ብዙውን ጊዜ ትናንሽና ታዳጊ እባቦችን የሚያድኑ ቢሆንም በውስጣቸው የያዙት መርዝ ግን ትላልቆቹ እንስሳቶችንም ቢሆን ለማንበርከክ በቂ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጡት እባብ አዳኝ ሸረሪቶች ግዙፎቹ የታራንቱላ ቤተሰብ ሸረሪቶች ሲሆኑ ድርን የማይዘረጉ ቢሆንም ከአደኑ ውስጥ የ10 በመቶ ድርሻን ወስደዋል፡፡ በጠንካራ ድራቸው እንዲሁም ከዚህ ቀደም የሌሊት ወፍ እና ሌሎች ወፎችን አድነው በመመገብ የሚታወቁ የኦብዌቨር ሸረሪቶች በበኩላቸው 8.5 በመቶ የሚሆነውን የእባብ አደን ፈፅመዋል፡፡

ከእባቦች ዘንድም ብዙዎቹ ህፃናትና ከግራም ያነሱ ቢሆንም በጥናቱ ከተመዘገቡት ውስጥ ግን ግዙፉ 100 ሴ.ሜ የሚረዝም እባብ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የብላክ ዊንዶው ሸረሪቶች ከእነርሱ ክብደት በ30 እጥፍ የላቁት እባቦችን ያድናሉ፡፡ በአንድ ወቅት ደግሞ የኮብዌብ ሸረሪቶች ከእነርሱ በ355 እጥፍ የሚገዝፉ እባቦችን አድነው ሲመገቡ ተገኝተዋል፡፡ በሸረሪቶቹ ጥቃት ከደረሰባቸው እባቦች መካከል 86 በመቶው ህይወታቸው ሲያልፍ ከነዚህ ውስጥ 30 በመቶ የሚሆኑት መርዛማ እባቦች ናቸው፡፡ 1.5 በመቶ የሚሆኑት እባቦች ብቻ በራሳቸው ከጥቃቱ ማምለጥ ሲችሉ ሌሎች 11 በመቶ ደግሞ በሰዎች አማካኝነት ህይወታቸው ሊድን በቅቷል፡፡ ታድያ ሸረሪቶቹ ማዕዳቸውን ተመግበው ለመጨረስ ቀናት ሊፈጅባቸው ይችላል፡፡

እባቦችን አድነው የሚመገቡ ሸረሪቶች ከአንታርክቲካ በቀር በሁሉም የምድራችን አህጉራት ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፤ Live Science
ለተጨማሪ፤ https://www.livescience.com/spiders-prey-on-snakes.html
ቅዳሜዎን ከቴክ-ሳይንስ ጋር ያሳልፉ
=========
በዚህ ሳምንት የቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራማችንም ለእርስዎም ሆነ መላው ቤተሰብዎ አስተማሪ ናቸው ያልናቸውን ልዩ ልዩ ዝግጅቶች አሰናድተን ከናንተው ዘንድ ለማድረስ ነገ ቅዳሜ 10 ሰዓትን እየተጠባበቅን እንገኛለን፡፡

የግብርና ባዮቴክኖሎጂ የሚዳስስ ዝግጅት አብይ ፕሮግራማችን ላይ የምናቀርብላችሁ ሲሆን ግልገል ጊቤ ሰዉ ሰራሽ ሀይቅንም በተቋማት መሰናዶ እናስተዋውቃችኋለን፡፡

እንደ ሁል ጊዜው ታዳጊ የፈጠራ ባለሙያዎችን ስራ ለእናንተው በምናደርስበት የብላቴናት ዝግጅታችንም ቬንትሌተር የሰራውን ታዳጊ፤ የቴክኖሎጂ ታሪክም ስለ ናኖ ቴክኖሎጂ የሚያውጠነጥን ዘገባ የሚያቀርቡላችሁ ይሆናል፡፡

ያስታውሱ ዘውትር ቅዳሜ 10 ሰዓት በድጋሚ ደግሞ ማክሰኞ በተመሳሳይ ሰዓት በMOE TV ላይ ያገኙናል፡፡

ያለፉ ፕሮግራሞች ተሟልተው የተቀመጡበት የዩትዩብ ቻናላችንንም ሊንኩን ተጠቅመው ሰብስክራይብ ማድረጉን እንዳይረሱ https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg
ከክትባት በኋላ በኮቪድ መያዝ
ከክትባት በኋላ በኮቪድ መያዝ
******************************
በማሳቹሴት ግዛት 4000 የሚደርሱ ሰዎች ሙሉ የኮቪድ ክትባት ከወሰዱ በኋላ ባደረጉት ምርመራ የኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው ታውቋል፡፡ የአሜሪካው የማህበረሰብ ጤና ክፍል እንዳወጣው መረጃ ከሆነ እስካለፈው ሰኔ 12 ድረስ በማሳቹሴት ሙሉ ክትባቱን ከወሰዱ ሰዎች መካከል 3791 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች የፋይዘርና ቢዮን ቴክ ክትባትን የወሰዱ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

የቦስተን ዩኒቨርሲቲው ተመራማሪ ዴቪድሰን ሃመር በእነዚህ ሰዎች የተከሰተው የኮቪድ ቫይረስ መጠን በጣም አነስተኛ ሲሆን ቆይታውም አጭር ነው ብለዋል፡፡ እንደ አሜሪካው የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል መረጃ ከሆነ የቫይረሱ ክትባት ብዙዎችን ከቫይረሱ የጠበቃቸው ሲሆን ውጤታማነቱ ግን መቶ በመቶ አይደለም፡፡

ሲዲሲ ያወጣው መረጃ ሁለት ጊዜ መከተብ የሚያስፈልጋቸው ፋይዘርና ሞደርና 90 በመቶ የሚጠጋ ውጤታማነት ሲያሳዩ አንደፍ ጊዜ ብቻ የሚሰጠው የጆንሰን ክትባት ደግሞ 72 በመቶ ውጤታማነት አስመዝግቧል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በአሜሪካ contagious Delta የተሰኘ ክፍለ/ውሉደ ቫይረስ ስጋት እንዳየለ እና ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ሙያተኞች እየተናገሩ ነው፡፡

እስካሁን ድረስ በአሜሪካ 150 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ሙሉ የኮቪድ ክትባት ተከትበዋል፡፡
ምንጭ Fox news
ተጨማሪ ንባብ https://www.foxnews.com/health/4000-fully-vaccinated-tested-positive-virus-massachusetts?cmpid=fb_fnc&fbclid=IwAR1hlkuI58CGv3hHNROkPxnwLm30136mIiB2VFSGjfS6L-W5tsS5neFEldI
እንዲጠፋ የተደረገው የኮሮና ቫይረስ ዘረመል መረጃ
እንዲጠፋ የተደረገው የኮሮና ቫይረስ ዘረመል መረጃ
****************************************************
በአለማችን ለ3.9 ሚሊዮን ሰዎች መሞት እና ለብዙ ማህበራዊ ቀውሶች ምክንያት የሆነው ኮሮና ቫረስ አሁንም ክትባቶች እየተሰጡ ስጋትነቱ አላቆመም፡፡ በቻይና በኩል ለመጀመሪያ ጊዜ ቫየህረሱ የተከሰተበት ትክክለኛ አካባቢና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ማንነት በፍጥነት አለመገለጽ ይህ ሁሉ ችግር እንዲከሰት አድርጎታል ብለው ብዙዎች ይናገራሉ፡፡

የችግሩን መነሻ ለማወቅ አሁንም የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ሲሆን አንድ ተመራማሪ ጎግልን በመጠቀም በሰራው ምርምር ከጎግል ክላውድ ላይ እንዲጠፋ የተደረገ በውሃን ከተማ ከመጀመሪያዎቹ የቫይረሱ ተጠቂዎች ጋር የተያዙ 13 የሚሆኑ መረጃዎችን ማግኘቱን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ መረጃ ተመራማሪው ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ ያመለጠ ነው ወይም በተፈጥሮ የመጣ ነው የሚለውን ክርክር ለመደገፍም ሆነ ለመቃወም አልሞ አልሰራም፡፡ ይልቁንም ለመጀመሪያ ጊዜ የበሽታው ታማሚ ይፋ ከመደረጉ በፊት ቫይረሱ ከሰዎች ወደ ሰዎች ሲተላለፍ እንደነበር የሚያሳይ መረጃ ነው፡፡ የአንድን ወረርሽኝ ትክክለኛ መነሻ ለማወቅ ተመራማሪዎች progenitor virus ወይም የሁሉም መነሻ የሆነውን ቫይረስ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡ አሁን ላይ ባለው መረጃ በውሃን ከተማ በታህሳት 2019 መጨረሻ ላይ የተመዘገቡት ናሙናዎች ናቸው መነሻ ተደርገው እየተወሰዱ ያሉት፡፡

በዚህኛው መረጃ ግን የቫይረሱ መነሻ ከውሃን የገበያ ስፍራ ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነና ቀደም ብሎ በህዳር ወር የተከሰተ እንደሆነ የሚያመላክት ነው፡፡ ለዚህም በገበያ ስፍራው የተገኘው የቫይረስ ናሙና ሶስት ደረጃዎች ያለፉት እንደሆነ መታወቁ በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡
ምንጭ sciencealert
ተጨማሪ ንባብ https://www.sciencealert.com/sequences-recovered-from-deleted-files-show-pandemic-started-earlier-than-thought?fbclid=IwAR2o7Eng8HqUUO0A9JnCPEZ4YukakwzrE_xdzX-Al_Zq7HZAi6fzBKgK8aw
የማይክሮ ሶፍት አዲስ የዊንዶው አማራጭ ለአንዲሮይድ መተግበሪያዎች
****************************************************************
የአለማችን ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት ለአመታት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን የኮምፒውተር ዊንዶው ፕሮግራም (10) የሚተካ ተከታይ ፕሮግራም ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ኩባንያው በያዝነው ሳምት ሀሙስ ይፋ እንዳደረገው መረጃ ከሆነ መሰረታቸውን በጎግል ላይ ደረጉ የአንዲሮይድ መተግበሪያዎችም ይህንን አዲሱን የዊንዶው 11 ፕሮግራም መጠቀም የሚችሉ መሆኑ ተገልጧል፡፡

ተቋሙ አክሎም በመጪዎቹ ጊዜያት አሁን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘውን ዊንዶው 10 ለማደስ እንዲቻል ዊንዶው 11 በነጻ ይቀርባል ብሏል፡፡ ይህም የመጥውን ጊዜ የኮምፒውቲንግ እንቅስቃሴ በእጅጉ የሚያሻሽል እንደሚሆን ተቋሙ እምነቱን አሳውቋል፡፡

በዊንዶው 11 ውስጥ የተካተቱ መገለጫዎች በአንዲሮይድ መተግበሪያወች ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረቡ ሲሆን ይህም የግል ኮምፒውተር ተጠቃሚዎች ከአማዞን የመተግበሪያ መገኛ በቀላሉ እንዲያገኙት ያስችላቸዋል፡፡ ማይክሮሶፍትም የሽያጭ ማዕከሉን በቀላሉ የሚገኝና ለተለያዩ መተግበሪያዎች የሚመች እንዲሆን በማድረግ አስተካክሎታል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-06-microsoft-windows-android-apps.html?fbclid=IwAR2FlF0sWUN8zG-uGXoKTudUn4KDh4-UTnrK_Ea_gO--_61cVtqZbIKx1U4
አዘውትረው ቡና የሚጠጡ ሰዎች በተራዘመ የጉበት በሽታ የመሞት ዕድላቸውን በግማሽ ይቀንሳሉ ተባለ
============
አዘውትረው ቡናን የመጠጣት ልምድ ያላቸው ሰዎች በተራዘመ የጉበት በሽታ የመታመም ዕድላቸው ያነሰ እንደሚሆን ተነገረ፡፡ በእንግሊዙ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሳውዝሀምፕተን የሚያገለግለው ኦሊቨር ኬኔዲ እና የሙያ አጋሮቹ የ384,818 ቡና ጠጪዎችን እና 109,767 የማይጠጡ ሰዎችን መረጃ ካነፃፀሩ በኋላ ነው እዚህ ድምዳሜ ላይ ሊደርሱ የቻሉት፡፡
በጥናቱ ላይ ግለሰቦቹ በአማካኝ ለ10.7 ዓመታት ጉበታቸው ላይ ስለሚኖር የጤና እክል እንዲሁም ተያያዥ ሞት ክትትል ተደርጎባቸዋል፡፡ በዚህም ቡናን አዘውትረው በአማካኝ ሁለት ጊዜ የሚጠጡት የጥናቱ ተሳታፊዎች ላይ የተራዘመ ጉበት ችግር የመከሰት ዕድሉ በ21 በመቶ ከማይጠጡት ሲነፃጠር ደግሞ በ20 በመቶ ያነሰ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በተጨማሪም በተራዘመ ጉበት በሽታ የመሞት ዕድላቸው በ49 በመቶ ያነሰ ነው ተብሏል፡፡
የጥናት ውጤቱን አስመልክቶ አስተያየቱን የሰጠው የጣልያኑ ማኒያ ግሬቻ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ሉዶቪኮ አቤናቮሊ ምን ያህል ቡና ብንጠጣ ይህን ጥቅም ልናገኝ እንችላለን የሚለው ትክክለኛ ምላሽ እንድናገኝ የሚያደርግ ጥናት መጠናት እንዳለበት ይገልፃል፡፡ በማከልም ሰፊ የህብረተሰብ መረጃዎችን ከመመልከት ባለፈ የህክምና ሙከራዎች ሊከናወኑ እንደሚገባም ተናግሯል፡፡
ምንጭ፤ New Scientist
ለተጨማሪ፤ https://www.newscientist.com/article/2281765-drinking-coffee-or-decaf-may-help-avoid-chronic-liver-disease/?utm_medium=social&utm_campaign=echobox&utm_source=Twitter#Echobox=1624468227-1
ምቹና በቀላል ዋጋ የቀረበ ጉዞ ወደ ህዋ
ምቹና በቀላል ዋጋ የቀረበ ጉዞ ወደ ህዋ
***************************************
አንድ አዲስ የህዋ ጉዞ ድርጅት ምቹና በቀላል ዋጋ የቀረበ ወደ ህዋ የሚደረግ ጉዞን ይዞ እንደቀረበ ተነገረ፡፡ በዚህ ዘመናዊ በተባለው የህዋ ላይ ጉዞ ከምድር ወደ ህዋ ለመሻገር መጓጓዣ ሆኖ የቀረበው ዘመናዊ ባሉን ነው፡፡ ባሉኑ ወደ ህዋ መምጠቅ እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ሲሆን በአንድ ጉዞ 12 ሰዎችን ማጓጓዝ የሚያስችል ነው፡፡ ምድርን ከ30 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ ሆኖ ለመጎብኘት ድርጅቱ 125 ሺህ የአሜሪካን ዶላርን እንደተመነም ተሰምቷል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ለሶስት የመጀመሪያ ዙር ተጓዦች የጉዞ ትኬት ተቆርጦ ያለቀ ሲሆን ሁሉም በረራዎች በ2024 የሚደረጉ ይሆናል፡፡ ይህ ስፔስ ፐርስፔክቲቭ የተሰኘው ተቋም ታብለር ማካለም እና ጄን ፖይንተር በተባሉ ሰዎች በጥምረት ተቋቁሞ በጥምረት የሚመራ ነው፡፡ ሁለቱ ሰዎች ለሁለት አመታት ከሌሎች ስድስት ሰዎች ጋር በመሆን በአሪዞና በረሃ ውስጥ የተለያዩ ችግሮችን ለመቋቋም ሲለማመዱ የቆዩ ሲሆን ይህም በማርስ ላይ ለመኖር እንደ ሙከራ አድርገው ወስደውታል፡፡
ስፔስ ፐርስፔክቲቭ የተሰኘው የቱሪስት (የጉብኝት) ጉዙ ከሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት በብዙ መልኩ የሚለይ ሲሆን ከእነዚህም አንዱ በትክክል ህዋ ላይ የማይደርስ መሆኑ ነው፡፡ በረራውም እንደ ህዋ ላይ በረራ የተጓዦች ቅድመ በረራ ልምምድ የማይፈልግ ሲሆን በጣም ቀላልና ምቹ እንደሆነም ተነግሮለታል፡፡
ምንጭ Bloomberg
ተጨማሪ ንባብ https://www.bloomberg.com/news/articles/2021-06-23/how-can-i-go-to-space-space-perspective-balloons-launch-2024?utm_medium=social&utm_source=facebook&cmpid=socialflow-facebook-business&utm_content=business&utm_campaign=socialflow-organic&fbclid=IwAR2jv6Kj0nBG6KZ2wvMK8H3sduejCigVyN5CwccGPtbPJxLO6WSpQilcG3M
የአለማችን የመጀመሪያው በቤተ-ሙከራ የተሰራ ስጋ ፋብሪካ
የአለማችን የመጀመሪያው በቤተ-ሙከራ የተሰራ ስጋ ፋብሪካ
**************************************************************
በአለማችን የመጀመሪያ የሆነ ስጋን በቤተሙከራ በማበልጸግ የሚያመርት ፋብሪካ ስራ ጀመረ፡፡ የእስራኤል ባዮ ቴክኖሎጂ ካፓኒ በአለማችን ስጋን ከእንስሳት ውጭ ወይም በፋብሪካ ለማምረት የሚያስችለውን ዝግጅት ጨርሶ ስራ እንደጀመረ ተናግሯል፡፡

ፋብሪካውም በቀን 1100 ፓውንድ የቤተ-ሙከራ ስጋን እንደሚያመርት ይፋ አድርጓል፡፡ የድርጅቱን መከፈት ይፋ ባደረጉበት ወቅት ሀላፊ የሆኑት ሮም ኩሽክ የፋብሪካው መከፈት የወደፊት በገበያ ውስጥ የሚፈለገውን የስጋ ቴክኖሎጂ በ2022 እውን ለማድረግ ያግዘናል ብለዋል፡፡

ከእንስሳት ስጋ ውጭ መሰረታዊ ግብዓታቸውን በአትክልት ያደረጉ የተለያዩ ምርቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ይህኛው ምርትም ገበያውን በመቀላቀል ተፈላጊነቱ ይጨምራል የሚል እምነት ተጥሎበታል፡፡ አዲሱ ምርት ከብክለት፣ ከቦታ እና ከግብዓት አንጻር እጅግ አዋጭ እንደሚሆንም ድርጅቱ ይፋ አድድጓል፡፡ ፋብሪካውም ህዋሳዊ መሰረት ያላቸው የተለያዩ የስጋ ምርቶችን እንደሚያቀርብ ተሰምቷል፡፡

ድጅቱ ይፋ እንዳደረገው መረጃ ከሆነ እንስሳትን ለማሳደግ ከሚወስደው ጊዜ እጅግ ያነሰ የምርት ጊዜ የሚወስድና እንስሳትን ከማረድ የተሸለ አማራጭ ነው፡፡
ምንጭ futurism
ተጨማሪ ንባብ https://futurism.com/the-byte/worlds-first-lab-grown-meat-factory?fbclid=IwAR38rD4WkzgcSx0NYoZ_koMkz8Q58jIhfvboY1vFrX71Qu3TuviSfw_9nMA
በባንክ ቤቶች ዉስጥ የኮቪድ-19 ስርጭን ለመቀነስ የተሰራ ፈጠራ
==========
እዝቅኤል ካንኮ ይባላል፤ የሳውላ ፍሬ የሆነው ይህ ታዳጊ በዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ስርዓት አማካኝነት ደንበኞች በየ ባንክ ቤቱ ጤናቸው ተጠብቆ ብሎም ሳይጉላሉ እንዲስተናገዱ የሚያደርግ ፈጠራን ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ በዚህም በባንክ ደብተሮች አማካኝነት የሚፈጠረውን የደንበኞች እርስ በእርስ ንክኪ በማስቀረት ለኮቪድ-19 ያላቸውን ተጋላጭነት እንደሚቀንስ እዝቅኤል ይገልፃል፡፡
ስለ ፈጠራው የሚያብራራበት ሙሉውን ምስል እንዲመለከቱ ግብዣችንን እያቀረብን የተለያዩ ዓባይት ብሎም ወቅታዊ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን መረጃዎችን ያገኙ ዘንድ ቀጥሎ የተቀመጠውን ሊንክ ተጠቅመው ወደ ዩትዩብ ቻናላችን ጎራ በማለት ለህይወት ዘመን ስንቅ የሚሆን ዕውቀትን ይገብዩ ዘንድ ጥሪያችን ነው፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=ZUJETzftZxk&t=2s
ምግብን ያሉበት ቦታ በሰዓቱ የሚያደርሰው አዲስ ኢትዮጵያዊ ተቋም
ምግብን ያሉበት ቦታ በሰዓቱ የሚያደርሰው አዲስ ኢትዮጵያዊ ተቋም
============
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የእለት ተእለት ኑሮን ቀለል የሚያደርጉ ቴክኖሎጂ ተኮር ኩባንያዎች በሀገራችን ብቅ ብቅ በማለት ላይ ናቸው፡፡ የዛሬ ወር ገደማ በስድስት ወጣቶች አማካኝነት ተመስርቶ ገበያውን የተቀላቀለው ትኩስ የተሰኘ ሳይክል እና የኤሌክትሪክ ሳይክሎችን በመጠቀም ብቻ ምግብን በያሉበት የሚያደርስ አዲስ ምግብ አቅራቢ አገልግሎት ሰጪ ከነዚህ አንዱ ነው፡፡ በአቬኒር ቴክኖሎጂስ አማካኝነት የቀረበው ይህ አገልግሎት ምግብን ፍጥነት፣ ተመጣጣኝ ዋጋ እና ጥራት ባለው መልኩ ከተጠቃሚዎች ዘንድ ለማድረስ ያለመ ነው፡፡

ትኩስ አገልግሎቱን የሚያቀርበው የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያን ተጠቅሞ ምግብ ፈላጊዎችን ከባለ ምግብ ቤቶች በማገናኘት ነው፡፡ መተግበሪያው አሁን በአንድሮይድም ሆነ አይኦኤስ ስልኮች ላይ እንዲሰራ ተደርጎ የቀረበ ሲሆን ተጠቃሚዎችም መተግበሪያውን ተጠቅመው ሬስቱራንቶችን በማፈላለግ ምግብ የሚያዙና ምግባቸው ሲመጣም መከታተል የሚችሉ ይሆናል፡፡ ከመተግበሪያ ባሻገር ግን ተጠቃሚዎች 9133 ላይ በመደወል ትእዛዝ መስጠት ይችላሉ፡፡

የትኩስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አሚር ሬድዋን እንደሚለው የሚጠቀሟቸው ሳይክሎች ነዳጅ የማይፈልጉ በመሆናቸው ምግብን የማድረሻ ዋጋው በኪ.ሜ 6 ብር ብቻ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ከዚህም ባሻገር ይህ መንገድ ስራው ለከባቢ የተስማማ እንዲሆን እንዳደረገው አሚር ይናገራል፡፡

ድርጅቱ ምግቦቹን የሚያደርስበት ዋጋ አነስተኛ ከመሆንም ባሻገር ምግቦቹ በተቀመጠላቸው ሰዓት የሚደርሱና ለማጓጓዝ የሚጠቀሙበት መያዣም ምግቡ ሳይበርድ ለተመጋቢዎች እንዲደርስ እንደሚያደርግ ይናገራል፡፡ እስከ አሁን ከ50 ያህል በአዲስ አበባ ከሚገኙ ሬስቱራንቶች ጋር በጋራ እየሰራ ይገኛል፡፡ በቅርቡ ደግሞ ይህን አብሯቸው የሚሰራቸው በከተማይቱ የሚገኙ ሬስቱራንቶችን ቁጥር በአራት እጥፍ ለማሳደግ አቅዷል፡፡

በስራ ፈጠራ ረገድም በአንድ አመት ውስጥ ብቻ ለ1ሺህ ሰዎች የስራ እድልን ለመፍጠር አቅዶ እየሰራ ነው፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ በትኩስ ታቅፈው ለመስራት ለሚፈልጉ ሰዎች ሳይክሎችን በ10 በመቶ ቅናሽ መግዛት እንዲችሉና የመግዣ ብድርም እንዲመቻችላቸው የሚያደርግ መንገድን አዘጋጅቷል፡፡

ምንጭ፤ shega
ለተጨማሪ፤ https://shega.co/post/this-ethiopian-startup-delivers-your-food-by-bicycle/
የአለማችን ፈጣኑ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል
*********************************************
በእንግሊዝ የሚገኝ አንድ የሞተር ሳይክል አምራች ድርጅት በምድር ላይ ከሚደረጉ የተሸከርካሪ ጎዞዎች ሁሉ እጅግ ፈጣን የሆነ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ለመስራት ማቀዱን አሳውቋል፡፡ አሁን ላይ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሎች ሀይልን በፍጥነት ከመሙላት ጀምሮ የተለያዩ ዘመናዊ የሚያደርጋቸውን ማሻሻያዎች እየተሰራላቸው ለውድድርም ሆነ ለመደበኛ አገልግሎት እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡
በአለማችን ከተደረጉ የሞተርሳይክል ፍጥነት ውድድሮች ውስጥ በጣም ፈጣን የተባለው ሰዓት ማክስ ቢያጊ የተሰኘ ተወዳዳሪ ቮክሳን ዋትማን የተሰኘውን የሞተር አይነት 254 ኪሎ ሜትር ማሽከርከር የቻለበት ነው፡፡ አዲሱ የሞተር ሳይክል አይነትም የሚደረግለት ማሻሻያ የአለማችን እጅግ ፈጣኑ የኤሌክትሪክ ሞተር እንዲሆን ያስችለዋል፡፡ ከሚደረግለት ማሻሻያ ውስጥም በእንቅስቃሴ ጊዜ የሚኖርን ነፋስ የሞተሩን ጉልበት በማይቀንስ መልኩ ሞተሩ እንዲንቀሳቀስ የሚያስችለው ነው፡፡ ሞተሩ አሁን ባለው ይዞታ በንፋስ ምክንያት የሚደርስበትን የፍጥነት ገደብ በሚሰራለት ማሻሻያ በ70 በመቶ መቀነስ ይችላል ሲል ድርጅቱ አሳውቋል፡፡
ምንጭ Engadget
ተጨማሪ ንባብ https://www.engadget.com/electric-motorcycle-land-speed-record-100503362.html?src=rss&fbclid=IwAR11lokyJC01QfNuiEOiR9uNWe3fykyMjrSK339DK_jnuEW451bYisXQ3WA
እንግሊዝ ውስጥ በኮቪድ 19 እየሞቱ ካሉት አብዛኛው የተከተቡ መሆናቸው ተነገረ
እንግሊዝ ውስጥ በኮቪድ 19 እየሞቱ ካሉት አብዛኛው የተከተቡ መሆናቸው ተነገረ
==========
ከጥቂት ቀናት በፊት የወጣ አዲስ መረጃ እንደሚያመላክተው እንግሊዝ ውስጥ ቢ.1.617.2 ተብሎ በሚጠራው የኮቪድ 19 አይነት ከሞቱት 117 ሰዎች ውስጥ 50ዎቹ ወይም 43 በመቶ የሚሆኑት የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባትን የተከተቡ መሆናቸውን ነው፡፡

ሁኔታው የተከሰተው በተለይም ክትባቶቹን የሚወስደው ሰው ላይ የሚኖራቸው ውጤታማነት እንደ ሰውዬው እድሜና ክትባቱን የተቀበለበት መንገድ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡ ክትባቶቹ በኮቪድ 19 የመሞት ዕድልን በ94 በመቶ የሚከላከሉ ቢሆንም በኮቪድ የመሞት ምጣኔው ግን በተለየ መልኩ እድሜ ላይ ጥገኛ ነው፡፡ እንበልና በኮቪድ 19 የተያዘ አንድ ሰው ዕድሜው በስድስት ወይም በሰባት ዓመት በጨመረ ቁጥር በቫይረሱ የመሞት ዕድሉም በግማሽ ይጨምራል፡፡ ይህም አንድ ዕድሜው 80 ላይ የሚገኝ ክትባቱን የወሰደ ሰው በኮቪድ አማካኝነት የመሞት እድሉ እድሜው 50ዎቹ ውስጥ ሆኖ ግን ደግሞ ክትባትን ካልወሰደ ሰው ጋር እኩል ነው እንደማለት ነው፡፡

መረጃው እንደሚያሳየውም በተጠቀሰው የኮሮና ቫይረስ አይነት ተጠቅተው ከሞቱት ውስጥ አንድ ሦስተኛው ዕድሜያቸው 50ን የተሻገረ ነው፡፡ ታድያ በሀገሪቱ እድሜያቸው ከ65 እስከ 69 ከሆኑት ውስጥ ከ93 በመቶ የሚልቁት ክትባቱን የወሰዱ ናቸው፡፡

ምንጭ፤ The Guardian
ለተጨማሪ፤ https://www.theguardian.com/theobserver/commentisfree/2021/jun/27/why-most-people-who-now-die-with-covid-have-been-vaccinated?utm_source=dlvr.it&utm_medium=twitter&fbclid=IwAR2ZauoFZWTA1Qbe5rkCZPlM8OP-697iNjkbIbhp5tRTqwovfOd-7dVFWnQ