TechIn2
1.16K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ባዮቴክኖሎጂን ለግብርናው እድገት ጥቅም ላይ ማዋል
===========================
ከቴክኖሎጂ አቅርቦት አንፃር የአገራችን የምርምር ፖሊሲ አቅጣጫ በአጭር ጊዜ ለሀገራችን የሚስማሙ ቴክኖሎጅዎችን ከሌሎች ሀገራት አፈላልጎ በማምጣትና በማላመድ ከሀገራችን ሥነ ምህዳርና ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ መጠቀምን ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን ጎን ለጎን ደግሞ የምርምር አቅማችንን በአስተማማኝ ደረጃ በመገንባት በራስ አቅም ቴክኖሎጂን ማመንጨትና የቴክኖሎጂ ባለቤት መሆን ነው።
ስለሆነም በየጊዜው እያደገና እየተለዋወጠ የሚሄደውን የግብርና ምርት ፍላጎት ለማሟላት ልማቱ ይህንን ያገናዘበ ሆኖ ጥራት ያለው ከፍተኛ ምርት በቀጣይነት እንዲኖር በራስ አቅም የላቀ ቴክኖሎጂ የመፍጠር ብቃት በማጎልበት ተወዳዳሪነትን ማረጋገጥ የሚያስችል መሰረት መገንባት ያስፈልጋል። በየጊዜው የሚከሰት የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ በርካታ የልማት ማነቆዎች መፍትሄ በመስጠት ቀጣይነት ያለው በዓለም ገበያ ተመራጭ የሆነ የግብርናና የአግሮ-ኢንደስትሪው ምርት ማቅረብ ፈታኝ ቢሆንም እንደ ባዮቴክኖሎጂ የተሻሻለና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የምርምርንና የልማቱን አሰራር በአስተማማኝ ሁኔታ ማጠናከር ወሳኝ የመፍትሄ አቅጣጫ ሆኖ ይታያል።
ባዮቴክኖሎጂ በአለም አቀፍ ደረጃ በተለይ በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ በምግብ አቅርቦት፣ ለኢንደስትሪው ጥሬ ዕቃ በማቅርብ፣ ለገበያ የሚሆን ምርት በማቀበል እጅግ ከፍተኛና ፈጣን ውጤት እየተመዘገበበት ያለ መስክ ሲሆን በተለይም ያደጉ ሀገራትም ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የመጪውን ዘመን የግብርናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ አቅርቦት ከአሁኑ በማሟላት ላይ ይገኛሉ፡፡ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ጥልቀት ያለውን የሥነ-ህይወታዊ ሂደቶችንና ባህሪያታቸዉን በሳይንስ መሠረታዊ ትንታኔ ላይ ተመርኩዞ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የመረጃ መገኛና መተንተኛ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሰብልን፤ እንሰሳትንና ደቂቅ ዘአካላት ለማጥናት፤ ለመረዳትና ለማበልፀግ የዝርያውን የውርስ ሂደት ወይም መስተጋብር በዘረመል ደረጃ ባሉ መረጃዎች በመተንተን ወደ ውጤት ለማድረስና በጥራት ላይ የተመሰረተ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ልማትን ለማፋጠን በእጅጉ የሚያግዝ ዘርፍ ነው።
የሰብልና እንስሳት ምርትና ምርታማነት እንደዚሁም የበሽታና የአየር ለውጥ ተጽኖዎች የመቋቋም ችሎታ ከማሻሻል አኳያ፣ የምርት ጥራትና የገበያ ተወዳዳሪነት ከማሳደግ አንጻር እንደዚሁም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ሊኖረው የሚችለው ሀገራዊ ጠቀሜታ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ከዚህ በመለስ ደግሞ ማንኛውም የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች እንደሚሰጡት ትሩፋት ሁሉ መጠነኛ ጉዳት ሊኖራቸው ስለሚችል የአጠቃቀም ሁኔታን ይበልጥ በማሻሻል እና ተሞክሮዎችን በመቀመር የቴክኖሎጂውን ፍሬ በበልሃት መጠቀም ግድ ይላል፡፡ ታዲያ ባዮቴክኖሎጂ ምርታማነትን ይበልጥ የሚያሳድግ እና ወቅቱን የዋጀ ቴክኖሎጂ መሆኑን ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር በአጠቃቀም ሂደቱ ላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡ Theconversation
የጂ.አይ.ኤስ ቴክኖሎጂ ዘርፈ ብዙ ግልጋሎት
======================
ጂዮግራፊካል ኢንፎርሜሽን ሲስተም ኋላቀር ወይም የተለመደውን የአሰራር ስርዓት በመቀየር ወደ ተሻሻለና ዘመናዊ የመረጃ አሰጣጥ በመለወጥ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ ይገኛል። በብዛት አገልግሎት እየሰጠ ከሚገኝባቸው ዘርፎች መካከል የሚከተሉትን ማንሳት ይቻላል።
የተፈጥሮ ጋዝን ለመፈለግ- ብዙ የሳይንስ ሊቃውንት የተፈጥሮ ጋዝ ከረጅም ዘመናት በፊት በባሕር ውስጥ የሚገኙ ጥቃቅን ዕፅዋትን ጨምሮ ከእንስሳት ቅሪተ አካላትና ከዕፅዋት ብስባሽ ስብስብ እንደሚገኝ ያምናሉ። ታዲያ የጋዝ ክምችቶች ያሉበትን ቦታ ለማወቅ እንዲረዳቸው ጂዮግራፊካል ኢንፎርሜሽን ሲስተምን በመጠቀም ግሎባል ፖዚሽኒንግ ሲስተም (ጂ.ፒ.ኤስ) ከሚባለው አቅጣጫ ጠቋሚ መሣሪያ ጋር በማገናኘትና በኮምፒውተሮች በመታገዝ የተፈጥሮ ጋዝ የሚገኝበትን ስፍራ ይበልጥ ትክክለኛ በሆነ መንገድ ለመገመት ችለዋል።
የጉዞ አቅጣጫን ለማወቅ- በአሁኑ ጊዜ ብዙ የመኪና አሽከርካሪዎችና አውሮፕላን አብራሪዎች እንዲሁም የመርከብ ካፒቴኖች ከግሎባል ፖዚሽኒንግ ሲስተም (GPS) ጋር ግንኙነት ባላቸው የጂዮግራፊካል ኢንፎርሜሽን ሲስተም ሶፍትዌር በመታገዝ የመንገዳቸውን አቅጣጫ ለማወቅ አስችሏቸዋል። የአንድን ቦታ አድራሻ ለማወቅ ቢያስፈልግ የቦታውን ስም በመፃፍ ብቻ የት አካባቢ እንዳለ በጥቂት ሴኮንዶች ውስጥ ማወቅ የሚቻል ሲሆን ይህ የሚሆነው ግን የምንፈልገው ቦታ በትክክል ጂ.አይ.ኤስ ሲስተም ላይ ከተመዘገበ ብቻ ነው።
ለንግድ ሥራ አገልግሎት- ጂ.አይ.ኤስ በእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ በምናከናውናቸው የግብይት ልውውጥና አገልግሎቶች አዎንታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መጥቷል። በመሆኑም የግብይት ስርዓቱ የተስተካከለና ተዓማኒነት ያለው እንዲሆን በማድረግ የንግድ ድርጅቶች ያሉበትን ቦታ ከማወቅ ጀምሮ እስከሚሰጡት አገልግሎት ድረስ ሰዎች ባሉበት ቦታ ሆነው መረጃን ማግኘት እንዲችሉ የሚያደርግ ሲሆን ጊዜን፣ ጉልበትንና የሀብት ብክነትን ይቀንሳል።
ለደህንነት አገልግሎት- የደህንነት መሪዎች መረጃዎችን ከየትና እንዴት ያገኛሉ የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ጂዮግራፊካል ኢንፎርሜሽን ሲስተም ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል። በዚህም ምክንያት የጦር ሀይል አስተዳዳሪዎች በቀላሉ ጠላትን ለመቆጣጠር፣ በየትኛው አካባቢ ጠላትን ለማሸነፍ አመቺ እንደሆነ ለመለየት፣ የጠላትን መረጃ ወስዶ ለመጠቀም እና ለመሰለል በመጨረሻም የተጣሩ ፣የተሻሻሉ፣ ፈጣንና በአነስተኛ ወጪ ብዙ መረጃዎችን ለማግኘት ያስችላል።
ምንጭ፡ geoinfolink
ተጨማሪ https://geoinfolink.blogspot.com/.../application-of-gis...
የአሰልጣኞች ስልጠና በጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
***********************************
ሐገራችን ኢትዮጵያ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ የዳበረ የክህሎት እና የአመለካከት ብቃትና ተነሳሽነት ያለው ትውልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ስራዎችን እየሰራች መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ለዚህ አላማ ስኬትም በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች የሚገኙ አሰልጣኞች የሚጠበቀውን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት በቂ እውቀትና ክህሎት ያደበሩ መሆን እንደሚገባቸው ይታመናል፡፡ ለዚህም ነው የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በኮሌጁ ለሚገኘ አሰልጣኞች ለአምስት ቀናት የቆየ ስልጠናን የሰጠው፡፡
ስልጠናውን በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በኩል የሴክተር ሞደርናይዜሽን ዳይሬክቶሬት ያቀረበው ሲሆን የምርምርና ልማት እንዲሁም የኳሊቲ ኢንጅነሪንግ ዳይሬክቶሬቶች ተሳትፈውበታል፡፡ ስልጠናውም የሴክተር ሞደርናይዜሽን ክፍል በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ማላመድ፣ ምርምርና ሪሰርች ዴቨሎፕመንት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለሚሰራው ስራ ማሳያ እንደሚሆን ከዳይሬክቶሬቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በስልጠናው መዝጊያ ላይም የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲን የሆኑት አቶ ጸጋየ ተቋማቸው በዋናነት ሶስት መሰረታዊ ተልዕኮዎችን ለመወጣት የተቋቋመ ኮሌጅ መሆኑን ገልጸው በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲቲዩት በኩል ለተደረገላቸው ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ እንደ አቶ ጸጋየ ገለጻ ከሆነ ኮሌጁ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ተነሳሽነት ያላቸው ዜጎች የኢንዱስትሪውን ዘርፍ እንዲቀላቀሉ ማድረግ፣ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አማካኝነት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተለያዩ ድጋፎችን ማድረግና ማህበረሰባዊ ሀላፊነትን መወጣት ሶስቱ መሰረታዊ የኮሌጁ አላማዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም ስልጠናው ኮሌጁ ይህንን ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ የሚያስችለው እንደሆነ አቶ ጸጋየ ተናግረዋል፡፡
በዚህ የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የሴክተር ሞደርናይዜሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰልማን ሞሐመድ ማህበረሰቡን መሰረት ያደረጉ ምርምሮች እና ቴክኖሎጂዎች በኢኖቬሽን ታግዘው እና ከስራ እድል ፈጠራ ጋር ተያይዘው ውጤት እንዲያመጡ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ አቶ ሰልማን አክለውም ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን ክህሎትና እውቀት በመጠቀም በዘርፉ ለሚጠበቀው ውጤት የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
በሌሎች ተመሳሳይና ተከታታይ ስልጠናዎች ግንኙነቱ እንደሚቀጥል ለሰልጣኞችና ለኮሌጁ አመራሮች የገለጹት አቶ ሰልማን በስልጠናው ለተሳተፉ የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎችና አስተባባሪዎች በጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የተዘጋጀውን የምስክር ወረቀት በማስረከብ የዝግጅቱ ፍጻሜ ሆኗል፡፡
የቶዮታ አዳዲስ የመፈጸም አቅም ያላቸው የቤት ውስጥ ሮቦቶች
*****************************************
****************
ቶዮታ የተሰኘው የምርምር ተቋም የተሸለ የቤት ውስጥ ተግባር የመፈጸም ብቃት ያላቸው ሮቦቶችን በኢንጅነሮቹ አማካኝነት ማበልጸጉን ተናገረ፡፡ ከእነዚህ አዳዲስ ክህሎቶች መካከል የተለያዩ መገልገያዎችን ማጽዳት እና ተሰባሪ ቁሳቁሶችን በጥንቃቄ መጠቀምና ስራ መስራት ይጠቀሳሉ፡፡ መረጃው ይፋ በሆነበት ወቅት ሮቦቱ ስማርት ስልክን ከጠረጴዛ ላይ አንስቶ ሰልፊ (የራሱን ምስል ፎቶ ማንሳት) እንደሚችል አሳይቷል፡፡
በጃፓን የሚገኙ እንደ ቶዮታና ሌሎች የሮቦቲክስ ተቋማት በመጪዎቹ ጊዜያት በቤት ውስጥ ሆነው የተለያዩ ስራዎችን የመ ከያግዙ ሮቦቶችን ለማበልጸግ ያላቸውን እቅድ ይፋ አድርገው እየሰሩ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ጃፓን ጥንታውያን ከሚባሉ ሀገራት መካከል ስትሆን በ2040 65 በመቶ የሚሆኑ ህዝቦቿ በእድሜ ከፍ ያሉ እንደሚሆኑ ተገምቷል፡፡ የሮቦት ቴክኖሎጂውም ከእርጅና ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችልን የድጋፍ ፍላጎት ለማሳካት ያለመ እንሆነም ተነግሯል፡፡
በጃፓንና በሌሎች ሀገራት የሚገኙ የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ኢንጅነሮች እቃ ማጠብ፣ ወለል ማጽዳት፣ ልብስ ማስተካከልና ተመሳሳይ ስራዎችን መስራት የሚችሉ የተለያዩ ሮቦቶችን በማበልጸግ ላይ ናቸው፡፡ በዚህኛው ግኝት ውስጥ ሮቦቶች ከአንጸባራቂ እና ብርሃን አስተላላፊ ቁሶች ጋር በተያያዘ የነበረባቸውን ችግር የሚቀርፍ ውጤት መገኘቱን የምርምር ተቋሙ መረጃ ያመለክታል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-06-toyota-capabilities-domestic-robots.html?fbclid=IwAR0HtK9M3StLLuC3i_oqwy3AosNADvF2_180bCEZ0LPInDuPYwopm8HQSm0
ከ18 አመት በታች ለሆኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች
******************************************************
ከ18 አመት በታች የሆኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በተለያየ አጋጠሚ በበይነ መረብ የተለቀቁ ያልተገቡ ምስሎቻቸውንና ቪዲዮዎቻቸውን ከኢንተርኔት ላይ ማስወገድ የሚያስችል አሰራር ተዘረጋ፡፡ ይህ በኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን እና ቻይልድላይን አማካኝነት የቀረበው አገልግሎት ያለ ፈቃዳቻው በወላጆቻቸውም ሆነ በሌሎች ሰዎች እንዲሁም በራሳቸው የተለጠፉ ምስሎቻቸውን ማስነሳት እንዲችሉ የሚያስችላቸው ነው፡፡

የተዘረጋው አሰራር በአለም የመጀመሪያው እንደሆነና ሪፖርት የተደረገባቸውን ምስሎች ከህግ አንጻር በማገናዘብ ተገቢ ያለሆኑ ምስሎችን ያስወግዳል፡፡ በመሆኑም አሰራሩ ከህጻናት ደህንነት አንጻር ተገቢ ያልሆኑ ምስሎችንና ቪዲዮዎችን ከኢንተርኔት ያስወግዳል፡፡
ኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን (IWF) እንደሚለው ህጻናትና መካከለኛ እድሜ ያላቸው ልጆች የተለየዩ ምስሎቻቸውን ባማወቅ ኦንላይን ላይ ይለቃሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ለሳቅ ለጨዋታ በሚመስል መልኩ ለጓደኞቻቸው ያልተገቡ ምስሎችን ኢንተርኔትን በመጠቀም ይለቃሉ ብሏል፡፡ እንደ ፋውንዴሽኑ መረጃ ከሆነ በተያዘው የፈረንጆች አመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት ውስጥ 38,000 የሚደርሱ የተለያዩ ምስሎች ሪፖርት የተደረገባቸው ሲሆን ሁሉም በልጆች የተለጠፉ ናቸው፡፡ ይህም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ያደገ ነው፡፡

በመሆኑም እንዲህ አይነት ችግር የገጠማቸው እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ልጆች የNSPCC ን ቻይልድላይን አገልግሎት ዌብ ሳይት በመጠቀም በይነ መረብ ላይ ያሉ እና በሂደት ወደ በይነ መረብ ይሰራጫል ብለው የሚያስቡትን ምስል ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ስጋት ያለባቸው ልጆች እድሜያቸውንና ሌሎች መረጃዎችን በማረጋገጥ ማንነታቸው ይፋ ሳይደረገደ ሪፖርት ማድረግ የሚችሉበት አሰራር ተዘርግቷል፡፡

ከዚህ ቀደም አንድ ምስል ወይም ቪዲዮ በበይነ መረብ ካልወጣ እና ይወጣል የሚል ስጋት ካለ ለቻይልድ ላይን ሪፖርት በማድረግ ሀሽ በተሰኘ የዲጂታል አሻራ አማካኝነት ከህግ ሙያተኞችና ከቴክኖሎጂ ባለቤቶች ጋር በመነጋገር ሪፖርት የተደረገበት ምስል እንዳይለቀቅ ማድረግ እንደሚቻል የመረጃ ምጫችን የሰራው ዘገባ ያመለክታል፡፡
ምንጭ BBC
ተጨማሪ ንባብ https://www.bbc.com/news/uk-57562152
image_2021-06-25_08-28-15.png
515.6 KB
ከ18 አመት በታች ለሆኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች
ቀርከሀን ከዘመን ያዋደደው ኢትዮጵያዊው አክሊል
==========
በኢትዮጵያ ያለው የቀርከሃ ሀብት የመላውን አፍሪካ ሁለት ሦስተኛ እንደሚይዝ ጥናቶች ቢያመላክቱም ይህ ሀብት ከጥቂት ባህል ቀመስ ቤተ መብሎች ወንበርና ጠረቤዛነት ባሻገር ወደ ሰፊ እንጀራ ሲለወጥ ብዙም አይታይም፡፡ አክሊል የተሰኘው ሀገር በቀል ተቋም ታድያ ይህን ልማድ ሊያስቀር በሚመስል መልኩ ቀርከሀን ተጠቅሞ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማምረት ላይ ይገኛል፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት ከተፈጥሮ የተዋደዱ ግብዓቶች ተጠቅሞ በመስራት ፍቅር በወደቀችው ዪዲዲያ ዳምጠው መስራችነት የተቋቋመው ድርጅቱ ሼባ ብሎ የሰየማቸው ከቀርከሃ የተሰሩ ካልሲዎችን ለገበያ በማቅረብ ነበር ስራውን ሀ ብሎ የጀመረው፡፡ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ትራስ እና ምንጣፎችን ከቀርከሃ በመስራት ለገበያ ማቅረቡን ቀጥሏል፡፡ ድርጅቱ በዚህ ልክ ቀርከሃ ላይ አተኩሮ ለመንቀሳቀሱ በምክያትነት የሚያስቀምጠው ግብዓቱ መበስበስ የመቻሉና ለከባቢም የመስማማቱን ነገር ነው፡፡

በቀጣይም ድርጅቱ በዋናነት የቀርከሃ ቃጫን ተጠቅሞ ስራውን በከፍተኛ ደረጃ ለገበያ ማቅረብን ያልማል፡፡ ለዚህም ይረዳው ዘንድ አሁን ላይ ትኩረቱን አዳዲስ ምርቶችን በማውጣትና ግንዛቤን በመፍጠር ላይ አድርጓል፡፡ በቅርቡም አደይ አበባ የተሰኙት የክብር ምንጣፎች በአዲስ አበባ ግዙፍ የግንባታ ስራዎች ምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ውለው ዓይን ማረፍያ ሆነውለት ነበር፡፡

ምንጭ፤ shega
ዝነኛው የኮምፒውተር ቫይረስ መከላከያ ሶፍትዌር ፈጣሪ ትናንት ሞቶ ተገኘ
ዝነኛው የኮምፒውተር ቫይረስ መከላከያ ሶፍትዌር ፈጣሪ ትናንት ሞቶ ተገኘ
=============
ታዋቂው የቴክኖሎጂ ስራ ፈጣሪ ጆን ማካፊ በግብር ማጭበርበር ክስ ለአሜሪካን ተላልፎ እንዲሰጥ ከተወሰነበት በኋላ ትናንት በባርሴሎና እስር ቤት ውስጥ እራሱን አጥፍቶ መገኘቱ ተዘገበ፡፡ የማካፊ ጠበቃ እንደተናገረው ከዘጠኝ ወራት እስር በኋላ ባጋጠመው የተስፋ ማጣት ነው ይህ የኮምፒውተር ቫይረሶች መከላከያ መንገድ ቀያሽ እራሱን በመስቀል ያጠፋው፡፡

ማካፊ እ.አ.አ በ1987 በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ በገበያ የቀረበውን የኮምፒውተር ቫይረስ መከላከያ ከማቋቋሙ አስቀድሞ ናሳ ዜሮክስ እና ሎክሄድማርቲን በተሰኙት ታላላቅ ተቋማት ውስጥ ይሰራ ነበር፡፡ ከ10 ዓመት በፊት እስካሁን ድረስ የእርሱም ስም በመጠርያነት የሚጠቀመውና በመላው ዓለምም ከ500 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን የያዘው የሶፍትዌር ኩባንያውን ለኢንቴል ከሸጠ በኋላ ግን ዳግም በኢንዱስትሪው ላይ ተሳትፎን ሳያደርግ ቆይቷል፡፡

ማካፊ ከክሪፕቶ ከረንሲዎች ጋር በተያያዘ ለዓመታት ከአሜሪካን የግብር ኃላፊዎች ሲሸሸግ ቆይቶ ሳለ ነበር የዛሬ ዘጠኝ ወር ገደማ የብሪታኒያን ፓስፖርት በመያዝ ወደ ኢስታንቡል ሊሻገር ሲል ባርሴሎና ኤርፖርት ውስጥ የተያዘው፡፡ የዛሬ ወር ገደማ በነበረው የፍርድ ቤት ውሎም የ75 ዓመት እድሜ ባለፀጋው ማካፊ ጥፋተኛ ተብሎ ከተወሰነበት ቀሪ ዕድሜውን በሙሉ በእስር እንደሚያሳልፍ በመጠቆም ችሎቱን ሲለማመን ነበር፡፡

እንደ ጠበቃው ከሆነ ማካፊ ጥፋተኛ ቢባል እንኳን ይግባኝ የሚጠይቅበት እድል ቢኖረውም ከዚህ በላይ በእስር መቆየት አልተቻለውም፡፡ በማከልም ክስተቱ ይህን ሰው ያለምክንያት በእስር ያቆየው ጨካኝ ስርዓት ውጤት ነው ሲል የፍትህ ስርዓቱን ኮንኗል፡፡

47 ልጆች አሉኝ የሚለው ማካፊ የትዳር አጋሩንም በዚህ ዓመታትን በፈጀ ሽሽት ውስጥ እንተዋወቃት ይናገራል፡፡

ምንጭ፤ Reuters
ለተጨማሪ፤ https://www.reuters.com/legal/government/john-mcafee-found-dead-prison-after-spanish-court-allows-extradition-2021-06-23/?fbclid=IwAR27HZeHoMAW1uW5GG5fQFAKFIP1h8rAvtqtcpZzShcA4f2z-r-0LHwAEtA
የተሻሻሉ የመንገደ ዳር መገልገያዎች ለከተሞች ዘመናዊነት
የተሻሻሉ የመንገደ ዳር መገልገያዎች ለከተሞች ዘመናዊነት
************************************************************
የአለማችን ዘመናዊ ከተሞች ዘመናዊነታቸው ከሚለካባቸው መገለጫዎች መካከል ዋነኛው ለነዋሪዎቻቸው ያላቸው ምቹነት ነው፡፡ የነዋሪዎች እና የእንግዶች ምቹነት ሀሳብ ሲነሳ ምቹና ተደራሽ የሆነ የመሰረተ ልማት አማራጭ በከተሞቹ ውስጥ መዘርጋት ቀዳሚው ተጠቃሽ ጉዳይ ነው፡፡ የከተማ ነዋሪዎች በሚኖሩበት ከተማ ምቹነት መጠን ልክ ያላቸው የአኗኗር ዘይቤ የተሻሻለ ወይም የጎሰቆለ ሊሆን ይችላል፡፡ ለዛሬ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ሰፋፊ ከተሞች ላይ ሊኖሩ ስለሚገባቸው የመንገድ ዳር የህዝብ መገልገያዎች ለማንሳት ወደናል፡፡

ለዚህ ጽሁፍ ማሳያነትና ምሳሌነት የሀገራችን ኢትዮጵያ ብሎም የአህጉራችን መዲና የሆነችውን አዲስ አበባችንን እናነሳለን፡፡ ከተማችን አዲስ አበባ ከጥቂት አመታት ወዲህ ፈርሳ በሚያስብል መልኩ እየተሰራች መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ በስራሂደቷም በቅርብ ጊዜያት እያስተዋልናቸው ካሉ ጅማሮዎች ውስጥ ዘመናዊ የሆኑ የመንገድ ዳር የህዝብ መገልገያዎች በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያክልም የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች፣ የመኪና ማቆሚያዎች፣ የመንገድ ዳር ማረፊያ ወንበሮችና ምቹና ሰፋፊ የሆኑ የእግረኛ መንገዶች ይገኙበታል፡፡

እንደነዚህ አይነት መገልገያዎች ከመሰራታቸው ባሻገር ለአጠቃቀም ያላቸው ምቹነትና ዘመናዊነታቸው ሊታሰብበት የሚገባ መሆኑ በአለማችን ያሉ ሰፋፊ ከተሞች ልምድ ያሳየናል ለምሳሌ በአውስትራሊያ ከተሞች እየተተገበሩ ያሉ የመንገድ ዳር መገልገያዎች ስማርት የሆኑና የተለያዩ ዲጂታል መረጃዎችን ማመንጨት ብሎም መሰብሰብ የሚያስችሉ ናቸው፡፡ እነዚህም መቀመጫዎችን፣ ኪዮስኪዮችን፣ የመብራት ምሶሶዎችን እና የአውቶብስ መቆሚያዎችን የሚያጠቃልሉ ናቸው፡፡ የመንገድ ዳር መገልገያዎቹን ዘመናዊ ከሚያሰኛቸው ነገሮች መካከል እርስ በርሳቸው በኔትወርክ የተገናኙ መሆናቸው ነው፡፡

በአውስትራሊያ ከተሞች እየተተገበሩ ያሉ የከተማ ማዘመኛ የመንገድ ዳር መገልገያዎች ከመደበኛ አገልግሎታቸው በተጨማሪ የዋይ ፋይ አገልግሎት፣ ዲጂታል ማስታወቂያ፣ አቅጣጫ መፈለጊያ የአደጋ ጊዜ መጥሪያዎች፣ ስልኮችና ስልኮችንና የተለያዩ ኤሌክትሮኖክሶችን ቻርግ ማድረጊያ ግብአቶችን ሁሉ ያሟሉ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን የግለሰባዊ ደህንነት ተቃውሞ እየገጠመው ቢሆንም የመንገድ ዳር ካሜራዎችም የዘመናዊ ከተሞች መገላጫ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡

ከተማችን አዲስ አበባ ብሎም ሌሎች ከተሞቻችን ዘመናዊነትን የተላበሱ እና ለኑሮ የሚመቹ እንዲሆኑ ከአውስትራሊያ ከተሞች ብዙ መማር ያለብን ነገር እንዳለ ይሰማናል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-06-smart-street-furniture-australia-surveillance.html?fbclid=IwAR3RC5lzdEukYj5RX4EdxEK1H2Bh2qkpP_aQiWFUW3RJkgWGpshda_pnXdM
እባብ አድነው የሚመገቡት ሸረሪቶች
እባብ አድነው የሚመገቡት ሸረሪቶች
========
መርዛማ ሸረሪቶች ከእነርሱ በብዙ እጥፍ የሚገዝፉ መርዛማ እባቦችን አድነው እንደሚመገቡ አዲስ ጥናት አመላከተ፡፡ አዲሱ ጥናት ለ319 ጊዜያት ያህል ሸረሪቶች እባቦችን አድነው ሲመገቡ የተመለከተ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 297 የሚሆነው በዱር ውስጥ የተቀረው ደግሞ ሆን ተብሎ እንዲገናኙ ከተተደረገ በኋላ የተካሄደ ነው፡፡

ነገሩን ለየት የሚያደርገው እባቦችን አድኖ መብላቱ ቁጥራቸው ከ30 በላይ በሚሆን በተለያዩ የሸረሪት ዝርያዎች በዱር ሌሎች 11 ደግሞ በተመደረከ ግንኙነት ላይ የታየ መሆኑ ነው፡፡ ከነዚህ ውስጥ አስፈሪዎቹን ብላክ ዊንዶው (Latrodectus mactans, L. Hesperus, L. variolus) እና አፍሪካን በተን (L. indistinctus) ያሉ ሸረሪቶች የሚገኙበት የዊንዶው ሸረሪቶች ቤተሰብ ነው፤ ከአደኖቹ ውስጥ የግማሽ ድርሻን በመውሰድ፡፡ እነዚህ 1.1 ሴ.ሜ ብቻ የሚረዝሙ ሽረሪቶች ብዙውን ጊዜ ትናንሽና ታዳጊ እባቦችን የሚያድኑ ቢሆንም በውስጣቸው የያዙት መርዝ ግን ትላልቆቹ እንስሳቶችንም ቢሆን ለማንበርከክ በቂ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጡት እባብ አዳኝ ሸረሪቶች ግዙፎቹ የታራንቱላ ቤተሰብ ሸረሪቶች ሲሆኑ ድርን የማይዘረጉ ቢሆንም ከአደኑ ውስጥ የ10 በመቶ ድርሻን ወስደዋል፡፡ በጠንካራ ድራቸው እንዲሁም ከዚህ ቀደም የሌሊት ወፍ እና ሌሎች ወፎችን አድነው በመመገብ የሚታወቁ የኦብዌቨር ሸረሪቶች በበኩላቸው 8.5 በመቶ የሚሆነውን የእባብ አደን ፈፅመዋል፡፡

ከእባቦች ዘንድም ብዙዎቹ ህፃናትና ከግራም ያነሱ ቢሆንም በጥናቱ ከተመዘገቡት ውስጥ ግን ግዙፉ 100 ሴ.ሜ የሚረዝም እባብ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የብላክ ዊንዶው ሸረሪቶች ከእነርሱ ክብደት በ30 እጥፍ የላቁት እባቦችን ያድናሉ፡፡ በአንድ ወቅት ደግሞ የኮብዌብ ሸረሪቶች ከእነርሱ በ355 እጥፍ የሚገዝፉ እባቦችን አድነው ሲመገቡ ተገኝተዋል፡፡ በሸረሪቶቹ ጥቃት ከደረሰባቸው እባቦች መካከል 86 በመቶው ህይወታቸው ሲያልፍ ከነዚህ ውስጥ 30 በመቶ የሚሆኑት መርዛማ እባቦች ናቸው፡፡ 1.5 በመቶ የሚሆኑት እባቦች ብቻ በራሳቸው ከጥቃቱ ማምለጥ ሲችሉ ሌሎች 11 በመቶ ደግሞ በሰዎች አማካኝነት ህይወታቸው ሊድን በቅቷል፡፡ ታድያ ሸረሪቶቹ ማዕዳቸውን ተመግበው ለመጨረስ ቀናት ሊፈጅባቸው ይችላል፡፡

እባቦችን አድነው የሚመገቡ ሸረሪቶች ከአንታርክቲካ በቀር በሁሉም የምድራችን አህጉራት ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፤ Live Science
ለተጨማሪ፤ https://www.livescience.com/spiders-prey-on-snakes.html
ቅዳሜዎን ከቴክ-ሳይንስ ጋር ያሳልፉ
=========
በዚህ ሳምንት የቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራማችንም ለእርስዎም ሆነ መላው ቤተሰብዎ አስተማሪ ናቸው ያልናቸውን ልዩ ልዩ ዝግጅቶች አሰናድተን ከናንተው ዘንድ ለማድረስ ነገ ቅዳሜ 10 ሰዓትን እየተጠባበቅን እንገኛለን፡፡

የግብርና ባዮቴክኖሎጂ የሚዳስስ ዝግጅት አብይ ፕሮግራማችን ላይ የምናቀርብላችሁ ሲሆን ግልገል ጊቤ ሰዉ ሰራሽ ሀይቅንም በተቋማት መሰናዶ እናስተዋውቃችኋለን፡፡

እንደ ሁል ጊዜው ታዳጊ የፈጠራ ባለሙያዎችን ስራ ለእናንተው በምናደርስበት የብላቴናት ዝግጅታችንም ቬንትሌተር የሰራውን ታዳጊ፤ የቴክኖሎጂ ታሪክም ስለ ናኖ ቴክኖሎጂ የሚያውጠነጥን ዘገባ የሚያቀርቡላችሁ ይሆናል፡፡

ያስታውሱ ዘውትር ቅዳሜ 10 ሰዓት በድጋሚ ደግሞ ማክሰኞ በተመሳሳይ ሰዓት በMOE TV ላይ ያገኙናል፡፡

ያለፉ ፕሮግራሞች ተሟልተው የተቀመጡበት የዩትዩብ ቻናላችንንም ሊንኩን ተጠቅመው ሰብስክራይብ ማድረጉን እንዳይረሱ https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg
ከክትባት በኋላ በኮቪድ መያዝ