TechIn2
1.16K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ኢትዮጵያ በ2021 የቴክኖሎጂ ፈር-ቀዳጅ ከሆኑ 100 ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተካተተች
********************************************
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓውያኑ 2021 የቴክኖሎጂ ፈር-ቀዳጅ ከሆኑ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ገብታለች። የዓለም ምጣኔ ኃብት ጉባዔ በዓለም ላይ 100 በቴክኖሎጂ ፈር-ቀዳጅ የሆኑ ድርጅቶችን ሲመርጥ ኢትዮጵያን አንዷ አድርጓታል።
ኢትዮጵያ የተወከለችው ካምብሪጂ ኢንደስትሪስ በተባለ ተቋም አማካኝነት ሲሆን የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ቆሻሻን ወደ ኃይል ምንጭነት ለመቀየር የሚያስችሉ ዘላቂ የከተማ መሰረተ ልማቶችን እያለማ መሆኑ ተጠቁሟል።
በዚህ አመት ሳይበር ሴክዩሪቲ፣ ሮቦቲክስ እና ሌሎች ሰው ሰራሽ አስተውህሎትን (የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን) በመጠቀም በጤና እንክብካቤ እና የፋይናንስ ተደራሽነትን ለመሙላት የተጠቀሙ በሚል ዝርዝሩን ይፋ ተደርጓል።
ኢትዮጵያ፣ ዝምባብዌ እና ኤልሳልቫዶር ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ዘርፍ ስማቸው የተካተተ ሲሆን ከተመረጡት ኩባንያዎች ውስጥ 30 በመቶ በላይ የሚሆኑት በሴቶች የሚመሩ ናቸው። በዚህ ዘርፍ ከአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዝምባብዌ፣ ናይጄሪያ፣ ኬንያ እና ጋና ተካተዋል።
ከ40 በላይ ተቋማትን በማስመረጥ ቀዳሚዋ ሀገር አሜሪካ ስትሆን እስራኤል፣ እንግሊዝ፣ ጃፓን፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ቻይና የቴክኖሎጂ ተቋሞቻቸውን አስመርጠዋል ሲል የዘገበው EBC ነው።
የክላዉድ ኮምፒዩቲንግ ጥቅሞችና የአገልግሎት አይነት
ክላዉድ ኮምፒዩቲንግ ከሌሎች በአንድ ስፍራ ላይ ከተሰባሰቡ ሰርቨሮችና የማከማቻ መሳሪያዎች በተሻለ ተደራሽ የሆነና ፍጥነት ያለው አገልግሎት ለማግኘት ያስችላል። አስተማማኝ የሆነ በቀጥታ የሚገኝ የዲጂታል ፋይሎች ስብስብ እንዲኖር እና ይህም ሉላዊነትን ከማሳለጥ አንፃር የበኩሉን ድርሻ ይወጣል። አብዛኛዉን ጊዜ ትላልቅ የማከማቻ መሳሪያዎች ሳይኖራቸው በኢንተርኔት አማካኝነት በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ኢንተርኔት ካፌ ለሚጠቀሙ ተገልጋዮች እርዳታ ያቀርባል።
ድረ-ገፅን መሰረት ካደረጉ የሃርድዌር (Hardware) መሳሪያዎች መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ከማስቻሉም ባለፈ የመተግበሪዎችን ወይም (Software) መዋለ ንዋይ እንዲሁም የድጋፍ ወጪዎችን ለመቀነስ፣ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የኢንፎርሜሽን ነፃነትን ለማስጠበቅ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማቀላጠፍ በእጅጉ ይረዳል።
የክላዉድ ኮምፒዩቲንግ አይነቶች ክላዉዶችን በተለያየ መልኩ ሊስተናገዱባቸዉና ሊገለገሉባቸው የሚያስችል ሲሆን፤ የተጠቃሚዉን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ሊገለገሉባቸው የሚችሉ የክላዉድ አይነቶች በተያየ መልኩ ይገኛሉ። ለምሳሌ የግል ክላዉድ ለተወሰነ ቡድን ወይም ድርጅት የሚሰጥና አገልግሎቱም ለተወሰነው ቡድን ወይም ድርጅት የተገደበ የክላውድ ስርዓት ሲሆን በዚህ ሂድት ውስጥ እንደ eBay ያሉ ፕላትፎርሞች እንደምሳሌ ይጠቀሳሉ፡፡
በአንጻሩ የሕዝብ ክላዉድ ማንኛዉም ደንበኛ የበይነ መረብና የክላዉድ ምህዳር አገልግሎት ማግኘት እስከቻለ ድረስ ለመጠቀም ክፍት የሆነ ስርዓት ሲሆን እንደ Amazaon፣ Google Apps፣ Windows Azure ማሳያ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ሃይብሪድ ወይም ድብልቅ ክላዉድ ተብሎ የሚጠቀሰው የክላውድ አይነት ቢያንስ ሁለት የክላዉድ ውህዶች የጋራ የሚፈጥሩት የክላዉድ አይነት ሲሆን፤ ዉህደቱም የግል፣ የህዝብ፣ ወይም የተመሳሳይ ክላዉድ ቅልቅል ሊሆን ይችላል። በዚህ ሂደት ውስጥ እንደ IBM እና Juniper ያሉ ፕላትፎርሞች እንደምሳሌ ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
https://cloud.illinois.edu/types-of-cloud-computing-private-public-and-hybrid-clouds/
ሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ፣ አውቶሜሽንና ስማርት ሲስተም ለኢንዱስትሪዉ ዘርፍ እድገት
****************************************
በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የስልጠናና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት በዛሬዉ እለት በሮቦቲክስ፣ አዉቶሜሽንና ስማርት ሲስተም በሚል ርእስ ሴሚናር ተካሄደ፡፡ በሴሚናሩም የኢንስቲትዩቱ አባላት የተሳተፉ ሲሆን በተመረጡት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የመነሻ ሀሳብ በረዳት መምህር በኩረጽዮን ጸጋዬ አማካኝነት ቀርቧል፡፡ ረዳት መምህሩ በገለጻቸው ወቅት አንዳሉት በሮቦቲክስ ቴክኖሎጂና አዉቶሜሽን ላይ ትኩረት ሰቶ መስራት ለኢንዱስትሪዉ ዘርፍ ለዉጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ለተሳታፊዎች አስገንዝበዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ፣ አውቶሜሽንና ስማርት ሲስተም ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚሰሩ ሶስት የስልጠና ቡድኖች ተዋቅረው ወደ ስራ መገባቱን አቅራቢው አመላክተዋል፡፡ እነዚህ የስልጠና ቡድኖች በዋነኛነት የተሰማሩት በጥገና፣ ምርትን ሊያሻሽሉ በሚችሉ ማሽነሪዎች ላይ ትኩረት ሰቶ በመስራትና አዳዲስ ተመራቂ ወጣቶች ተነሳሽነት ኖሯቸዉ ወደ ስራ በመስገባት ላይ መሆኑም ተገልጧል፡፡

ይህንንም በማድረግ ሀገራችን ለማሽነሪ ጥገናና ለልዩ ልዩ መሰል ተግባራት የምታወጣውን የውጭ ምዛሬ ማስቀረት እደሚቻል ታምኖበታል፡፡ ስለሆነም ወደ ፊት ይህ ስራ የበለጠ ፍሬያማና ዉጤታማና እንዲሆን ከተፈለገ በስልጠና፤ በሰዉ ሀይልና በግብዓት ረገድ ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ መስራት አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቀረበውም የመነሻ ሀሳብ ዙሪያ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
ባዮቴክኖሎጂን ለግብርናው እድገት ጥቅም ላይ ማዋል
===========================
ከቴክኖሎጂ አቅርቦት አንፃር የአገራችን የምርምር ፖሊሲ አቅጣጫ በአጭር ጊዜ ለሀገራችን የሚስማሙ ቴክኖሎጅዎችን ከሌሎች ሀገራት አፈላልጎ በማምጣትና በማላመድ ከሀገራችን ሥነ ምህዳርና ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ መጠቀምን ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን ጎን ለጎን ደግሞ የምርምር አቅማችንን በአስተማማኝ ደረጃ በመገንባት በራስ አቅም ቴክኖሎጂን ማመንጨትና የቴክኖሎጂ ባለቤት መሆን ነው።
ስለሆነም በየጊዜው እያደገና እየተለዋወጠ የሚሄደውን የግብርና ምርት ፍላጎት ለማሟላት ልማቱ ይህንን ያገናዘበ ሆኖ ጥራት ያለው ከፍተኛ ምርት በቀጣይነት እንዲኖር በራስ አቅም የላቀ ቴክኖሎጂ የመፍጠር ብቃት በማጎልበት ተወዳዳሪነትን ማረጋገጥ የሚያስችል መሰረት መገንባት ያስፈልጋል። በየጊዜው የሚከሰት የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ በርካታ የልማት ማነቆዎች መፍትሄ በመስጠት ቀጣይነት ያለው በዓለም ገበያ ተመራጭ የሆነ የግብርናና የአግሮ-ኢንደስትሪው ምርት ማቅረብ ፈታኝ ቢሆንም እንደ ባዮቴክኖሎጂ የተሻሻለና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የምርምርንና የልማቱን አሰራር በአስተማማኝ ሁኔታ ማጠናከር ወሳኝ የመፍትሄ አቅጣጫ ሆኖ ይታያል።
ባዮቴክኖሎጂ በአለም አቀፍ ደረጃ በተለይ በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ በምግብ አቅርቦት፣ ለኢንደስትሪው ጥሬ ዕቃ በማቅርብ፣ ለገበያ የሚሆን ምርት በማቀበል እጅግ ከፍተኛና ፈጣን ውጤት እየተመዘገበበት ያለ መስክ ሲሆን በተለይም ያደጉ ሀገራትም ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የመጪውን ዘመን የግብርናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ አቅርቦት ከአሁኑ በማሟላት ላይ ይገኛሉ፡፡ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ጥልቀት ያለውን የሥነ-ህይወታዊ ሂደቶችንና ባህሪያታቸዉን በሳይንስ መሠረታዊ ትንታኔ ላይ ተመርኩዞ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የመረጃ መገኛና መተንተኛ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሰብልን፤ እንሰሳትንና ደቂቅ ዘአካላት ለማጥናት፤ ለመረዳትና ለማበልፀግ የዝርያውን የውርስ ሂደት ወይም መስተጋብር በዘረመል ደረጃ ባሉ መረጃዎች በመተንተን ወደ ውጤት ለማድረስና በጥራት ላይ የተመሰረተ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ልማትን ለማፋጠን በእጅጉ የሚያግዝ ዘርፍ ነው።
የሰብልና እንስሳት ምርትና ምርታማነት እንደዚሁም የበሽታና የአየር ለውጥ ተጽኖዎች የመቋቋም ችሎታ ከማሻሻል አኳያ፣ የምርት ጥራትና የገበያ ተወዳዳሪነት ከማሳደግ አንጻር እንደዚሁም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ሊኖረው የሚችለው ሀገራዊ ጠቀሜታ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ከዚህ በመለስ ደግሞ ማንኛውም የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች እንደሚሰጡት ትሩፋት ሁሉ መጠነኛ ጉዳት ሊኖራቸው ስለሚችል የአጠቃቀም ሁኔታን ይበልጥ በማሻሻል እና ተሞክሮዎችን በመቀመር የቴክኖሎጂውን ፍሬ በበልሃት መጠቀም ግድ ይላል፡፡ ታዲያ ባዮቴክኖሎጂ ምርታማነትን ይበልጥ የሚያሳድግ እና ወቅቱን የዋጀ ቴክኖሎጂ መሆኑን ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር በአጠቃቀም ሂደቱ ላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡ Theconversation
የጂ.አይ.ኤስ ቴክኖሎጂ ዘርፈ ብዙ ግልጋሎት
======================
ጂዮግራፊካል ኢንፎርሜሽን ሲስተም ኋላቀር ወይም የተለመደውን የአሰራር ስርዓት በመቀየር ወደ ተሻሻለና ዘመናዊ የመረጃ አሰጣጥ በመለወጥ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ ይገኛል። በብዛት አገልግሎት እየሰጠ ከሚገኝባቸው ዘርፎች መካከል የሚከተሉትን ማንሳት ይቻላል።
የተፈጥሮ ጋዝን ለመፈለግ- ብዙ የሳይንስ ሊቃውንት የተፈጥሮ ጋዝ ከረጅም ዘመናት በፊት በባሕር ውስጥ የሚገኙ ጥቃቅን ዕፅዋትን ጨምሮ ከእንስሳት ቅሪተ አካላትና ከዕፅዋት ብስባሽ ስብስብ እንደሚገኝ ያምናሉ። ታዲያ የጋዝ ክምችቶች ያሉበትን ቦታ ለማወቅ እንዲረዳቸው ጂዮግራፊካል ኢንፎርሜሽን ሲስተምን በመጠቀም ግሎባል ፖዚሽኒንግ ሲስተም (ጂ.ፒ.ኤስ) ከሚባለው አቅጣጫ ጠቋሚ መሣሪያ ጋር በማገናኘትና በኮምፒውተሮች በመታገዝ የተፈጥሮ ጋዝ የሚገኝበትን ስፍራ ይበልጥ ትክክለኛ በሆነ መንገድ ለመገመት ችለዋል።
የጉዞ አቅጣጫን ለማወቅ- በአሁኑ ጊዜ ብዙ የመኪና አሽከርካሪዎችና አውሮፕላን አብራሪዎች እንዲሁም የመርከብ ካፒቴኖች ከግሎባል ፖዚሽኒንግ ሲስተም (GPS) ጋር ግንኙነት ባላቸው የጂዮግራፊካል ኢንፎርሜሽን ሲስተም ሶፍትዌር በመታገዝ የመንገዳቸውን አቅጣጫ ለማወቅ አስችሏቸዋል። የአንድን ቦታ አድራሻ ለማወቅ ቢያስፈልግ የቦታውን ስም በመፃፍ ብቻ የት አካባቢ እንዳለ በጥቂት ሴኮንዶች ውስጥ ማወቅ የሚቻል ሲሆን ይህ የሚሆነው ግን የምንፈልገው ቦታ በትክክል ጂ.አይ.ኤስ ሲስተም ላይ ከተመዘገበ ብቻ ነው።
ለንግድ ሥራ አገልግሎት- ጂ.አይ.ኤስ በእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ በምናከናውናቸው የግብይት ልውውጥና አገልግሎቶች አዎንታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መጥቷል። በመሆኑም የግብይት ስርዓቱ የተስተካከለና ተዓማኒነት ያለው እንዲሆን በማድረግ የንግድ ድርጅቶች ያሉበትን ቦታ ከማወቅ ጀምሮ እስከሚሰጡት አገልግሎት ድረስ ሰዎች ባሉበት ቦታ ሆነው መረጃን ማግኘት እንዲችሉ የሚያደርግ ሲሆን ጊዜን፣ ጉልበትንና የሀብት ብክነትን ይቀንሳል።
ለደህንነት አገልግሎት- የደህንነት መሪዎች መረጃዎችን ከየትና እንዴት ያገኛሉ የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ጂዮግራፊካል ኢንፎርሜሽን ሲስተም ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል። በዚህም ምክንያት የጦር ሀይል አስተዳዳሪዎች በቀላሉ ጠላትን ለመቆጣጠር፣ በየትኛው አካባቢ ጠላትን ለማሸነፍ አመቺ እንደሆነ ለመለየት፣ የጠላትን መረጃ ወስዶ ለመጠቀም እና ለመሰለል በመጨረሻም የተጣሩ ፣የተሻሻሉ፣ ፈጣንና በአነስተኛ ወጪ ብዙ መረጃዎችን ለማግኘት ያስችላል።
ምንጭ፡ geoinfolink
ተጨማሪ https://geoinfolink.blogspot.com/.../application-of-gis...
የአሰልጣኞች ስልጠና በጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
***********************************
ሐገራችን ኢትዮጵያ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ የዳበረ የክህሎት እና የአመለካከት ብቃትና ተነሳሽነት ያለው ትውልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ስራዎችን እየሰራች መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ለዚህ አላማ ስኬትም በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች የሚገኙ አሰልጣኞች የሚጠበቀውን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት በቂ እውቀትና ክህሎት ያደበሩ መሆን እንደሚገባቸው ይታመናል፡፡ ለዚህም ነው የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በኮሌጁ ለሚገኘ አሰልጣኞች ለአምስት ቀናት የቆየ ስልጠናን የሰጠው፡፡
ስልጠናውን በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በኩል የሴክተር ሞደርናይዜሽን ዳይሬክቶሬት ያቀረበው ሲሆን የምርምርና ልማት እንዲሁም የኳሊቲ ኢንጅነሪንግ ዳይሬክቶሬቶች ተሳትፈውበታል፡፡ ስልጠናውም የሴክተር ሞደርናይዜሽን ክፍል በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ማላመድ፣ ምርምርና ሪሰርች ዴቨሎፕመንት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለሚሰራው ስራ ማሳያ እንደሚሆን ከዳይሬክቶሬቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በስልጠናው መዝጊያ ላይም የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲን የሆኑት አቶ ጸጋየ ተቋማቸው በዋናነት ሶስት መሰረታዊ ተልዕኮዎችን ለመወጣት የተቋቋመ ኮሌጅ መሆኑን ገልጸው በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲቲዩት በኩል ለተደረገላቸው ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ እንደ አቶ ጸጋየ ገለጻ ከሆነ ኮሌጁ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ተነሳሽነት ያላቸው ዜጎች የኢንዱስትሪውን ዘርፍ እንዲቀላቀሉ ማድረግ፣ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አማካኝነት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተለያዩ ድጋፎችን ማድረግና ማህበረሰባዊ ሀላፊነትን መወጣት ሶስቱ መሰረታዊ የኮሌጁ አላማዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም ስልጠናው ኮሌጁ ይህንን ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ የሚያስችለው እንደሆነ አቶ ጸጋየ ተናግረዋል፡፡
በዚህ የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የሴክተር ሞደርናይዜሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰልማን ሞሐመድ ማህበረሰቡን መሰረት ያደረጉ ምርምሮች እና ቴክኖሎጂዎች በኢኖቬሽን ታግዘው እና ከስራ እድል ፈጠራ ጋር ተያይዘው ውጤት እንዲያመጡ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ አቶ ሰልማን አክለውም ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን ክህሎትና እውቀት በመጠቀም በዘርፉ ለሚጠበቀው ውጤት የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
በሌሎች ተመሳሳይና ተከታታይ ስልጠናዎች ግንኙነቱ እንደሚቀጥል ለሰልጣኞችና ለኮሌጁ አመራሮች የገለጹት አቶ ሰልማን በስልጠናው ለተሳተፉ የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎችና አስተባባሪዎች በጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የተዘጋጀውን የምስክር ወረቀት በማስረከብ የዝግጅቱ ፍጻሜ ሆኗል፡፡
የቶዮታ አዳዲስ የመፈጸም አቅም ያላቸው የቤት ውስጥ ሮቦቶች
*****************************************
****************
ቶዮታ የተሰኘው የምርምር ተቋም የተሸለ የቤት ውስጥ ተግባር የመፈጸም ብቃት ያላቸው ሮቦቶችን በኢንጅነሮቹ አማካኝነት ማበልጸጉን ተናገረ፡፡ ከእነዚህ አዳዲስ ክህሎቶች መካከል የተለያዩ መገልገያዎችን ማጽዳት እና ተሰባሪ ቁሳቁሶችን በጥንቃቄ መጠቀምና ስራ መስራት ይጠቀሳሉ፡፡ መረጃው ይፋ በሆነበት ወቅት ሮቦቱ ስማርት ስልክን ከጠረጴዛ ላይ አንስቶ ሰልፊ (የራሱን ምስል ፎቶ ማንሳት) እንደሚችል አሳይቷል፡፡
በጃፓን የሚገኙ እንደ ቶዮታና ሌሎች የሮቦቲክስ ተቋማት በመጪዎቹ ጊዜያት በቤት ውስጥ ሆነው የተለያዩ ስራዎችን የመ ከያግዙ ሮቦቶችን ለማበልጸግ ያላቸውን እቅድ ይፋ አድርገው እየሰሩ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ጃፓን ጥንታውያን ከሚባሉ ሀገራት መካከል ስትሆን በ2040 65 በመቶ የሚሆኑ ህዝቦቿ በእድሜ ከፍ ያሉ እንደሚሆኑ ተገምቷል፡፡ የሮቦት ቴክኖሎጂውም ከእርጅና ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችልን የድጋፍ ፍላጎት ለማሳካት ያለመ እንሆነም ተነግሯል፡፡
በጃፓንና በሌሎች ሀገራት የሚገኙ የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ኢንጅነሮች እቃ ማጠብ፣ ወለል ማጽዳት፣ ልብስ ማስተካከልና ተመሳሳይ ስራዎችን መስራት የሚችሉ የተለያዩ ሮቦቶችን በማበልጸግ ላይ ናቸው፡፡ በዚህኛው ግኝት ውስጥ ሮቦቶች ከአንጸባራቂ እና ብርሃን አስተላላፊ ቁሶች ጋር በተያያዘ የነበረባቸውን ችግር የሚቀርፍ ውጤት መገኘቱን የምርምር ተቋሙ መረጃ ያመለክታል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-06-toyota-capabilities-domestic-robots.html?fbclid=IwAR0HtK9M3StLLuC3i_oqwy3AosNADvF2_180bCEZ0LPInDuPYwopm8HQSm0
ከ18 አመት በታች ለሆኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች
******************************************************
ከ18 አመት በታች የሆኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በተለያየ አጋጠሚ በበይነ መረብ የተለቀቁ ያልተገቡ ምስሎቻቸውንና ቪዲዮዎቻቸውን ከኢንተርኔት ላይ ማስወገድ የሚያስችል አሰራር ተዘረጋ፡፡ ይህ በኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን እና ቻይልድላይን አማካኝነት የቀረበው አገልግሎት ያለ ፈቃዳቻው በወላጆቻቸውም ሆነ በሌሎች ሰዎች እንዲሁም በራሳቸው የተለጠፉ ምስሎቻቸውን ማስነሳት እንዲችሉ የሚያስችላቸው ነው፡፡

የተዘረጋው አሰራር በአለም የመጀመሪያው እንደሆነና ሪፖርት የተደረገባቸውን ምስሎች ከህግ አንጻር በማገናዘብ ተገቢ ያለሆኑ ምስሎችን ያስወግዳል፡፡ በመሆኑም አሰራሩ ከህጻናት ደህንነት አንጻር ተገቢ ያልሆኑ ምስሎችንና ቪዲዮዎችን ከኢንተርኔት ያስወግዳል፡፡
ኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን (IWF) እንደሚለው ህጻናትና መካከለኛ እድሜ ያላቸው ልጆች የተለየዩ ምስሎቻቸውን ባማወቅ ኦንላይን ላይ ይለቃሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ለሳቅ ለጨዋታ በሚመስል መልኩ ለጓደኞቻቸው ያልተገቡ ምስሎችን ኢንተርኔትን በመጠቀም ይለቃሉ ብሏል፡፡ እንደ ፋውንዴሽኑ መረጃ ከሆነ በተያዘው የፈረንጆች አመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት ውስጥ 38,000 የሚደርሱ የተለያዩ ምስሎች ሪፖርት የተደረገባቸው ሲሆን ሁሉም በልጆች የተለጠፉ ናቸው፡፡ ይህም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ያደገ ነው፡፡

በመሆኑም እንዲህ አይነት ችግር የገጠማቸው እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ልጆች የNSPCC ን ቻይልድላይን አገልግሎት ዌብ ሳይት በመጠቀም በይነ መረብ ላይ ያሉ እና በሂደት ወደ በይነ መረብ ይሰራጫል ብለው የሚያስቡትን ምስል ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ስጋት ያለባቸው ልጆች እድሜያቸውንና ሌሎች መረጃዎችን በማረጋገጥ ማንነታቸው ይፋ ሳይደረገደ ሪፖርት ማድረግ የሚችሉበት አሰራር ተዘርግቷል፡፡

ከዚህ ቀደም አንድ ምስል ወይም ቪዲዮ በበይነ መረብ ካልወጣ እና ይወጣል የሚል ስጋት ካለ ለቻይልድ ላይን ሪፖርት በማድረግ ሀሽ በተሰኘ የዲጂታል አሻራ አማካኝነት ከህግ ሙያተኞችና ከቴክኖሎጂ ባለቤቶች ጋር በመነጋገር ሪፖርት የተደረገበት ምስል እንዳይለቀቅ ማድረግ እንደሚቻል የመረጃ ምጫችን የሰራው ዘገባ ያመለክታል፡፡
ምንጭ BBC
ተጨማሪ ንባብ https://www.bbc.com/news/uk-57562152
image_2021-06-25_08-28-15.png
515.6 KB
ከ18 አመት በታች ለሆኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች
ቀርከሀን ከዘመን ያዋደደው ኢትዮጵያዊው አክሊል
==========
በኢትዮጵያ ያለው የቀርከሃ ሀብት የመላውን አፍሪካ ሁለት ሦስተኛ እንደሚይዝ ጥናቶች ቢያመላክቱም ይህ ሀብት ከጥቂት ባህል ቀመስ ቤተ መብሎች ወንበርና ጠረቤዛነት ባሻገር ወደ ሰፊ እንጀራ ሲለወጥ ብዙም አይታይም፡፡ አክሊል የተሰኘው ሀገር በቀል ተቋም ታድያ ይህን ልማድ ሊያስቀር በሚመስል መልኩ ቀርከሀን ተጠቅሞ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማምረት ላይ ይገኛል፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት ከተፈጥሮ የተዋደዱ ግብዓቶች ተጠቅሞ በመስራት ፍቅር በወደቀችው ዪዲዲያ ዳምጠው መስራችነት የተቋቋመው ድርጅቱ ሼባ ብሎ የሰየማቸው ከቀርከሃ የተሰሩ ካልሲዎችን ለገበያ በማቅረብ ነበር ስራውን ሀ ብሎ የጀመረው፡፡ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ትራስ እና ምንጣፎችን ከቀርከሃ በመስራት ለገበያ ማቅረቡን ቀጥሏል፡፡ ድርጅቱ በዚህ ልክ ቀርከሃ ላይ አተኩሮ ለመንቀሳቀሱ በምክያትነት የሚያስቀምጠው ግብዓቱ መበስበስ የመቻሉና ለከባቢም የመስማማቱን ነገር ነው፡፡

በቀጣይም ድርጅቱ በዋናነት የቀርከሃ ቃጫን ተጠቅሞ ስራውን በከፍተኛ ደረጃ ለገበያ ማቅረብን ያልማል፡፡ ለዚህም ይረዳው ዘንድ አሁን ላይ ትኩረቱን አዳዲስ ምርቶችን በማውጣትና ግንዛቤን በመፍጠር ላይ አድርጓል፡፡ በቅርቡም አደይ አበባ የተሰኙት የክብር ምንጣፎች በአዲስ አበባ ግዙፍ የግንባታ ስራዎች ምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ውለው ዓይን ማረፍያ ሆነውለት ነበር፡፡

ምንጭ፤ shega
ዝነኛው የኮምፒውተር ቫይረስ መከላከያ ሶፍትዌር ፈጣሪ ትናንት ሞቶ ተገኘ