የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት የሳይንስና ቴክኖሎጂ አመላካች ጥናቶችን ሊያከናውን ነው ====================================
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሐገራዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሁኔታ-አመላካች የሆኑ የኢኖቬሽን ዳሰሳ እንዲሁም የማህበረሰቡን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ግንዛቤ ዳሰሳ ጥናት ከመጋቢት 23 ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ወራት በመላው ሐገሪቱ በሚገኙ 408 ቀበሌዎች ይከናወናል፡፡
የኢኖቬሽን ዳሰሳ ጥናት፤ በሃገሪቱ በሚገኙ የንግድ ተቋማት የኢኖቬሽን ተግባራትን የሚዳስስ ሲሆን ጥናቱ ሲጠናቀቅ ለመንግስት አካላት፣ ፖሊሲ አውጪዎች እንዲሁም ለከፍተኛ የትምህርት እና የምርምር ተቋማት ግብዓት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
የማህበረሰቡን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ግንዛቤ ላይ ትኩረት ተደርጎ የሚሰራው ጥናት ማህበረሰቡ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዙሪያ ያለውን ዕውቀት፣ ዝንባሌ፣ ፍላጎት እንዲሁም አመለካከት በመዳሰስ በሐገራችን ያለውን የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ደረጃ ያመላክታል፡፡
ጥናቶቹ ለሐገሪቱ የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ዕድገት፤ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ሰጪነት ላይ የላቀ አስተዋፅም ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡
ኢኒስቲትዩቱ ህብረተሰቡ ይህን በመገንዘብ ወደ እነርሱ ለሚመጡ የጥናት ቡድኖች ተገቢውን ድጋፍ እና መረጃ በመስጠት ሐገራዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ በአክብሮት ጠይቋል፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ዕርዳታ፤ ለትራፊክ አደጋ
=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=
ሐገራችንን ጨምሮ በመላው ዓለም ሚሊዮኖች በየዓመቱ ህይታቸውን በትራፊክ አደጋ ያጣሉ፡፡ ለዚህ የአደጋው መከሰት ዋነኛው ምክንያት ቢሆነም ከአደጋው በኋላ ያለ የተጎጂዎች ዕርዳታ አሰጣጥም የራሱን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ለዛሬ የትራፊክ ዓደጋ ለሚያጋጥማቸው ሁሉ እንዴት የመጀመሪያ ዕርዳታ መስጠት እንዳለብን እንይ፡፡
• የመጀመሪያ ዕርዳታ በመስጠረት ውስጥ ቀዳሚው እርምጃ ሊሆን የሚገባው እራስን ከተጨማሪ አደጋ መጠበቅ ነው፡፡ ወደ አደጋው ስፍራ ሲያመሩ በዙሪያዎ የሚንቀሳቀሱ መኪኖች አለመኖራቸውን ያረጋግጡ፡፡
• ከደረሱም በኋላ የነዳጅ መፍሰስና ሌሎች እሳት አደጋን ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎች ካሉ የመኪናውን ሞተር ያጥፉ፡፡
• በአጠገብዎ ሌሎች ሰዎች ካሉ ወደ አንቡላንስ እንዲደውሉልዎ ያድርጉ፡፡ ሆኖም ብቻዎን ከሆኑ ተጎጂው ለህልፈት ሊያበቁ ከሚችሉ ሁናቴዎች ካላቀቁ በኋላ ወደ አንቡላንስ ይደውሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ በአደጋው የተሳተፉ መኪኖችን እና በውስጣቸው ያለውን ተጎጂ ሁኔታ በአፅንዖት ይገምግሙ፡፡
• ቀዳሚ ትኩረትዎን ድምፅ እያሰሙ ያልሆኑ ወይም እንቅስቃሴ የማያደርጉ ተጎጂዎች ላይ በማድረግ መተንፈስ አለመተንፈሳቸውን ምላሽ መስጠት አለመስጠታቸውን ያረጋግጡ፡፡
• እየተነፈሱ ሳለ እንቅስቃሴ ካላከናወኑ በእርጋታ በትክክል በሚተነፍሱበት አቀማመጥ ላይ ያድርገዋቸው፡፡ ታድያ ይህን ሲያደርጉ ተጎጂውን ለማዋራት መሞከርዎን እንዳያቋርጡ፡፡
• ሆኖም ተጎጂው አደጋ ውስጥ (የእሳት፣ ጎርፍ፣ ፍንዳታ…) ካልሆኑ በስተቀረ የህክምና ባለሙያ እስከሚደርስ ካሉበት ባያወጧቸው ይመረጣል፡፡ የግድ ከሆነ ግን እንደ ስልክ ያሉ መንገዶችን በመጠቀም ከህክምና ባለሙያዎች እርዳታ በማግኘት ጭምር ያውጧዋቸው፡፡
• የጀርባ አጥንት ላይ ጉዳት ሊደርስ ስለሚችል የተጎጂዎቹን አንገት አያንቀሳቅሱ፤ እየደማ ያለ የሰውነት አካል ካለም ጓንትን ተጠቅመው በጨርቅ የደም ፍሰቱን ማስቆም፡፡
• በቦታው ላይ ማንም ሰው እንዳያጨስና ለተጎጂዎቹም ምንም አይነት መጠጥም ሆነ ምግብ እንዳይሰጥ ያድርጉ፡፡
• ተጎጂው የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ከሆነና እራሱን ከሳተ ሂልሜታቸውን በጥንቃቄ ያውልቁት፡፡ ሆኖም እራሳቸውን ካልሳቱ የፊት መስታውቱን በመክፈት ብቻ እርዳታ ይስጧቸው፡፡
• ተጎጂው በመኪና ተገጭቶ የወደቀ እግረኛ ከሆነ ከሌሎች ጋር በመተባበርና የጀርባ አጥንቱን በማይጎዳ አኳሃን ቀጥ ብለው እንዲተኙ በማድረግ ምቹ የአተነፋፈስ ሁኔታን መፍጠር ይገባል፡፡ ተጎጂው በመኪና ተገጭተው አሊያም ከመኪና ውስጥ በግጭቱ ተወርውረው የወጡ ከሆኑና እራሳቸውን ካልሳቱ እንደነቁ እንዲቆዩ ያበረታቷቸው፤ ሙቀት ወዳለበት ስፍራም ይውሰዷቸው፡፡
• ይህን ሁሉ ከሲያደርጉ ቀድሞ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በዙሪያዎያለን የትራፊክ እንቅቃሴ በማስቆም አሊያም የሚያስተናብር ግለሰብ በመሰየም እራስዎን እና ተጎጂን ከተጨማሪ አደጋ ይታደጉ፡፡
ሼር በማድረግ ሃላፊነትዎን ይወጡ
ምንጭ፡ First Aid For Life

በዓይነቱ ልዩ የሆነው አውሮፕላን
=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=
ጀማሪ የቴክኖሎጂ ተቋም የሆነው ፋራዳየር ኤሮስፔስ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን ባለ አስራ ስምንት መቀመጫ የባዮኤሌክትሪክ ሃይብሪድ (ቅልቅል) አውሮፕላን ዲዛይኑን ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ አውሮፕላኑንም ባዮ ኤሌክትሪክ ሃይብሪድ ኤርክራፍት (BEHA) ሲል ሰይሞታል፡፡ ሞዴሉም ኤም 1 ኤች ሲባል ሶስት ባለ ሳጥን ቅርፅ ክንፍ ይኖረዋል፡፡
ኤም 1 ኤች በሚነሳበት እና በሚያርፍበት ወቅት የኤሌክትሪክ ሞተሩን ይጠቀማል፡፡ ይህም የተለምዶዎቹ የጀት አውሮፕላኖች ከሚያወጡት 140 ዴሲ ቤል በእጅጉ ያነሰ የ60 ዴሲ ቤል ድምፅ እንዲያወጣ ያደርገዋል፡፡ አውሮፕላኑ እንዲነሳና እንዲያርፍ የሚያስችለውን ሞተር ቻርጅ ለመሙላት እንዲሁም እንዲበር ያደርገው ዘንድ 1,600 የፈረስ ጉልበት ያለው የቱርቦፕሮፕ ሞተር ይገጠምለታል፡፡ እንደ ተቋሙ ገለፃ ከሆነ ከተለምዶው አውሮፕላን ያነሰ የመንደርደሪያ ቦታንም ይፈልጋል (ሶስት መቶ ሜትር ብቻ)፡፡ ይህ እንዲሆን ያስቻሉት በተቃረነ አቅጣጫ የሚዞሩ ሽክርክሮሾቹ በሚያመነጩት የቬክትረም ትረስት፣ የክንፎቹ ዲዛይን እና በተሰራበረት የካርበን ንጥረ-ነገሮች ሳቢያ አውሮፕላኑ የተላበሰው ቀላል ክብደት አማካኝነት ነው፡፡ በተጨሪም አውሮፕላኑ በሰዓት እስከ 370 ኪ.ሜ ድረስ የመክነፍ ብቃት እንደሚኖረው ታውቋል፡፡
በዚህ ስራ ላይ የስዋንሲዩኒቨርሲቲን በአጋርነት ያቀፈው ይህ ተቋም አውሮፕላኖቹን በ2025 ወደ አገልግሎት እንደሚያስገባ ገልጿል (አውሮፕላኖቹን አነስተኛ የአየር መንገዶች እንደሚሸምቱ በመጠበቅ መሆኑ ነው)፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ አውሮፕላኑ የሚበረው የባዮፊውልን በመጠቀም መሆኑና የኤሌክትሪክ ሞተሩን ለማኮብኮብ መገልገሉ ለከባቢ አየር ተስማሚ ብሎም ወጪ ቆጣቢ አማራጭ እንደሚያደርገው ተነግሮለታል፡፡ በሚያጓጉዘው ጭነት ረገድም አውሮፕላኑ ከተሳፋሪዎች ጫኝ አውሮፕላንነት ወደ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላንነት ለመለወጥ አስራ አምስት ደቂቃዎችን ብቻ መውሰዱ ልዩ ያደርገዋል፡፡
ምንጭ፡ Techxplore

አማዞን የፈጣን በይነ-መረብ አቅራቢ ሳተላይቶችን ሊያመጥቅ ነው
===============================================
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሳተላይት ላይ የተመሰረተ የበይነ-መረብ (Internet) ዓገልግሎትን ለማቅረብ ታላላቅ የቴክኖሎጂ ተቋማት በመሽቀዳደም ላይ ናቸው፡፡ በትናንትናው ዕለትም አማዞን የ3,236 ሳተላይቶች እርስበእርስ ግንኙነትን በመዘርጋት ፈጣን የበይነ-መረብ አገልግሎትን ለመላው ዓለም ለማዳረስ እንደሚሰራ በመግለፅ ሩጫውን ተቀላቅሏል፡፡ ፕሮጀክት ኩኢፐር የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ስራ ሳተላይቶቹን በዝቅተኛው የምድራችን ምህዋር በማስፈር አነስተኛ የመዘግየት መጠን ያለውን ፈጣን የበይነ-መረብ ዓገልግሎት በይነ-መረብ በበቂ ሁኔታ አሊያም ሙሉ ለሙሉ ባልተዳረሰባቸው የዓለማችን ስፍራዎች ላይ ለማዳረስ እንደሚሰራ አማዞን ገልጿል፡፡
ታላላቆቹ የቴክኖሎጂ ተቋማትን ትኩረት እየሳበ በመጣው በዚህ ዘርፍ ላይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የበይነ-መረብ አገልግሎት ላልደረሳቸው 3.8 ቢሊዮን የዓለማችን ነዋሪዎች ከአገልግሎቱ እንደሚያስተዋውቁ ሲጠበቅ ለኩባንያዎቹም ጠቀም ያለ ትርፍን እንደሚያስገኙ ይነገርላቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ ከወራት በፊትም ዋን ዌብ የተሰኘ ኩባንያ መሰል ፈጣን የበይነ-መረብ አገልግሎትን አቅራቢ የሳተላይቶች ትስስርን ለመመስረት ይረዳው ዘንድ የመጀመሪያ ሳተላይቱን ማምጠቁ ይታወሳል፡፡ ሌላኛው ስመ ጥር የህዋ ምርምር እና ቴክኖሎጂ ተቋም ስፔስ ኤክስም ለተቋማቱ ሳተላይቶችን የማምጠቅ ስራን ከመስራቱም በተጓዳኝ የራሱን መሰል የሳተላይት ትስስር ለመገንባት ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ እስካሁንም ሁለት ሰርቶ ማሳያ ሳተላይቶችን ማምጠቅ ችሏል፡፡ ፌስቡከልም ቢሆን ከዚህ አልቦዘነም፤ ከስፔስ ኤክሱ የስታርሊንክ ሳተላይት አስር እጥፍ መረጃን የማስተላለፍ ፍጥነት ያለውን አተና የተሰኘ ሳተላይቱን ለዚህ ተግባር በማሰብ እያበለፀገ ይገኛል፡፡
ይህች የአማዞኗ ኩኢፐር ሳተላይት የንድፍ፣ ማበልፀግ እና ወደ ህዋ የማጓጓዝ ስራዋ በሌላኛው የጄፍ ቤዞስ ኩባንያ ብሉ ኦሪጅን አማካኝነት የሚከወን ይሆናል፡፡ ብሉ ኦሪጅን ከዚህ በተጓዳኝ ቴሳት ከተባለ ተመሳሳይ የበይነ መረብ አገልግሎትን ለማቅረብ ከሚሰራ ተቋም ጋር ሳተላይቶችን የማምጠቅ ውል አስሯል፡፡
ምንጭ፡ Tech Crunch

የአዎሮፓ ፓተንት ጽ/ቤት ልዕካን የቴክኖሎጂና ኢኖቬስን ኢንስቲትውትን ጎበኙ
በአውሮፓ ፓተንት ጽ/ቤት የዓለም አቀፍ ግንኝነት ኃላፊ ፈራንሳ ሃነርት ሚያዝያ 1/2011 ዓ.ም የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትውትን ጎበኙ፡፡ በጉብኝታቸውም ወቅት የኢኒስቲትውቱ ዋና ዳሬክተር አቶ ሳንዱካን ደበበ ስለተቋሙ ሁለተናዊ አቋም ገለፃ ያደረጉላቻው ሲሆን ልኡካን ቡድኑም በሚስተር ኒኮላስ ኮርኒዠ አማካኝነት ስለ አውሮፓ ፓተንት ጽ/ቤት ገለፃ አድርጓል፡፡
በውይይቱ ወቅት ሁለቱም ተቋማት በትብብር ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸውን መስኮች የለዩ ሲሆን፡- በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የኢኖቬሽንና ክሬቲቪቲን ለማህበረሰብ በማስተዋወቅ፣ በስልጠናና ሰው ሀይል ልማት እንዲሁም በፓተንት መረጃዎች ላይ በትብብር ለመስራት ዕቅድ ተቀምጧል፡፡
በማጠቃለያውም የልዑካን ቡድኑ መሪ ሚስተር ፈራንሳ ሃነርት ከኢንስቲትውቱ ጋር በቀጣይ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዙሪያ ድጋፍ በማድረግ ግንኙነታቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልፀዋል፡፡

የመጀመሪያው ብላክ ሆል ምስል እንዲገኝ ያስቻለችው ዕንስት
ከሰሞኑን በሳይንሱ ዓለም ከናኙት ወሬዎች መካከል ብላክ ሆልን ለመጀመሪያ ጊዜ በምስል ማየት መቻሉ ቀዳሚው ነው፡፡ ይህ ግኝት ከምዕተ ዓመቱ ምርጥ የሳይንስ ግኝቶች የተደመረውን ስራ ህልው እንዲሆን ያስቻለው የ29 አመቷ ዕንስት ተመራማሪ ዶ.ር ካቲ ቦውማን ባስቀመጠችው ቀመር አማካኝነት ነው፡፡ ካለእርሷ ስራ ቢሆን ኖሮማ አንድን ብላክ ሆል ለማየት አስር ሺህ ኪ.ሜ የሚሰፋ ቴሌስኮፕ ባስፈለገን ነበር፡፡ በተግባር ደረጃ ካየነው ይህ የማይቻል ተግባር ሆኖ ነወ፡፡ ከዚህ ይልቅ በኬቲ ቀመር መሰረት በምድር ላይ የሚገኙትን ቴሌስኮፖች አንድ ላይ በማጣመር 55 ሚሊዮን የብርሃን አመታት ርቆ የሚገኝ ብላክ ሆልን ምስል ማግኘት ተችሏል፡፡
ዶ.ር ካቲ CHIRP (Continuous High-resolution Image Reconstruction using Patch priors) ብላ የሰየመችው ይህ ቀመር በዓለም ዙሪያ በሚገኙት ስምንት ቴሌስኮፖች አማካኝነት በተነሱት ምስሎች መካከል የሚፈጠረውን ክፍተት መሙላት የሚያስችል ነው፡፡ ለስራውም በጠቅላላው ግማሽ ቶን የሚመዝኑ ሃርድ ድራይቮች ጥቅም ላይ ሲውሉ በእነርሱ አማካኝነትም 5 ፔታ ባይት የሚለካ ጥሬ ሃቅን ማሰባሰብ ተችሏል (ለአምስት ሺህ አመት ሳያቋርጥ የሚዘፍን ሙዚቃን የሚስተካከል መረጃ መሆኑን ልብ ይሏል)፡፡
ምንጭ፡ Daily Mail

እጅግ ጠቃሚ የድረ-ገፅ ጥቆማ
****************************
ማናቸውንም ከትምህርት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች ሲሹና ከዚያም አለፍ ሲል ለህይወቶ አዲስ መንገድና ክህሎት ለመማር ሲፈልጉ ልዩ ልዩ የኢንተርኔት ድረ-ገፆችን መጎብኘት እየተለመደ መጥቷል፡፡ በመሆኑም በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ላይ መሰልጠን ካስፈለጎት እና በተለይም አሁን ካለው የቴክኖሎጂ ዓለም ጋር ራሶን ይበልጥ ማጎዳኘት ከፈለጉ ከዚህ በታች የምትመለከቷቸው ልዩ ልዩ ድረ-ገፆች በእጅጉ ሊረዷችሁ ይችላሉና ይጎብኟቸው፡፡
ለሌሎች እንዲደርሳቸው ሼር ያድርጉ!!!
ነጻ የኦንላይን ትምህርቶችን ማግኛ (FREE ONLINE COURSES & CERTIFICATE)
• COURSERA
• MIT OPEB WARE
• UDACITY
• UDEMY
• EDX
ነፃ የስኮላርሺፕ እድሎች የሚሞክሩበት (FREE SCHOOLARSHIP FOR ETHIOPIAN STUDENT)
• ERASMUS MUNDUS (EUROPEAN COMMISSION)
• NUFFIC (HOLAND)
• EIFFEL (FRANCE)
• NEWZELAND DEVELOPMENT SCHOLARSHIP
• VLIROUS (BELGIUM)
• ITALIAN GOVERNMENT SCHOLARSHIP
የኮዲንግ ትምህርቶችን የሚያገኙበት (CODING SITES)
• THE ODIN PROJECT
• UPSKILL
• FREECODECAMP
• W3SCHOOLS
• TUTORIALSPOINT
• kHAN ACADEMY
• GA DASH
• SOLOLEARN
• CODE ACADEMY
• C4LEARNER
የሂሳብ ትምህርቶችን ማግኛ (MATHEMATHS
• https://amser.org
• https://www.brightstorm.com/math/
• https://www.doubledivision.org/
• http://www.mathtv.com
• http://mathforum.org
• http://www.aaamath.com/
ክራክ የተደረጉ መተግበሪያዎች የሚያገኙበት (Cracked software’s downloading sites)
• www.piratecity.net
• Igetintopc.com
• https://securityxploded.com/
• www.p30download.com
• www.downloadha.com

የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓትን ለማፋጠን በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ተካሄደ
*************************
የኢትዮጵያን የንግድ ስርዓት፣ የታክስ አከፋፈል እና አጠቃላይ የክፍያ ስርዓት ወደ ኤሌክትሮኒክስ ለማሸጋገር በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ የህግ ማዕቀፍ የሚያበጅ ረቂቅ አዋጅ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ወይይት ተካሄደበት፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ የውይይት መድረክ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ጨምሮ ጥሪ ተደረገላቸው የተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት ሃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይም ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይቱ መነሻ ላይ የመግቢያ ንግግር ያደረጉት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ዓለማችን በዲጂታል ኢኮኖሚ ከሄደችበት ርቀት አኳያ ሃገራችን ወደ ኋላ የቀረች ቢሆንም፤ ባለው ሰፊ የሰው ሃይል በመጠቀም እና ከኋላ የመነሳት እድልን (late comer adventage) አንደመደላድል በመውሰድ ፈጣን ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡
በተለይም ሚኒስተሩ እንደጠቀሱት በዓለማችን ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሚደረግበት የአገልግሎት ዘርፍ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ እና አውቀትን በመቀመር ወደ ዲጂታል ስርዓት መግባት ካልተቻለ ከሚያመጣው ጉዳት አንፃር፤ በኤሌክትሮኒክስ ትራንዛክሽን ላይ ያተኮረ አዋጅ መዘጋጀቱ ትልቅ መነሻ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡
በመድረኩ ላይ እንደተገለፀው ረቂቅ አዋጁን ለማዘጋጀት የተለያዩ ሃገሮች ተሞክሮ እንደመነሻ ተወስዶ የተሰራ ሲሆን በተለይም የዓለም ባንክ ልዩ ቡድን ያቀረበው ሰፊ ግብዓት የረቂቅ አዋጁ ጠንካራ ጎን እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ እንደ ውይይት መነሻ ዶክተር ማንደፍሮ የረቂቅ አዋጁን ይዘት በስድስት ምዕራፎች ከፋፍለው አቅርበዋል።

ናና ቅጠል
======
ወደ ገጠራማው የሀገራችን ክፍል ወጣ ስንል በየተራራው እና በየመንገዱ ዳር የሚበቅል እጅግ የሚማርክ መአዛ ያለው ተክል ነው፡፡ ይህ የቅመም ዘር ደርቆና በርጥብነቱ ልንጠቀመው እንችላለን፡፡ የሚንት ዘይት ለጥርስ ሳሙና፣ ለመስቲካ፣ ለከረሜላ እና የውበት መጠበቂያ ምርቶችን ለማምረት በግብአትነት ያገለግላል፡፡ እስከ 20 የሚደርሱ የተለያዩ የሚንት ዝርያወች አሉ፡፡ የናና ቅጠል በቀላሉ መብቀል ሲችል በምግብ እና ሻይ ውስጥ በመጨመር የተሻለ ጣእም እንዲሰጠን ያደርጋል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የአንቲ ኦክሲደንት ይዘት ያለው እጽዋትም ነው፡፡
ይዘት፡ 100 ግራም የጦስኝ ቅጠል
• ሀይል----------44ኪሎ ካሎሪ
• ካርቦ ሀይድሬት----8.41 ግራም
• ስብ--------------0.73 ግራም
• ፕሮቲን----------3.29 ግራም
• አይረን------11.87ሚሊ ግራም
• ኮፐር-------0.240 ሚሊ ግራም
• ፖታሺየም---458 ሚሊ ግራም
• ቫይታሚን ሲ--13.3ሚሊ ግራም እና ሌሎችም
ይህ ቅጠል በራካታ ጠቀሜታወች ቢኖሩትም የተወሰኑት ለማየት ያክል፡-
• ለቆዳ መቆጣት (ለአለርጂ)፡- የሚንት ቅጠል በውስጡ የሚይዘው ሮዝማርኒክ አሲድ ወቅታዊ የሆነ የቆዳ መቆጣትን (አለርጂክን ) ተፈጥሮአዊ በሆነ መልኩ ለማከም ያስችላል፡፡
• ጡት ለማጥባት፡- የሚንት ቅጠል ጡት ለምታጠባ እናት እና ለጨቅላው ጠቃሚ ነው፡፤በውስጡ የሚይዘው ንጥረ ነገር የጡት ጫፍ ህመሞችንና መሰንጠቅን ይከላከላል፡፡
• ጉንፋንን ለማከም ፡- የጦስኝ ሻይ በተለይ በጉንፍን ምክንያት የተዘጋን ጉሮሮ በመክፈት ያለው ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡
• ለሆድ ህመም፡- የናና ቅጠል ለረዥም ዘመን የሆድ ህመም እና የምግብ አለመፈጨትን እንደ መፍትሄ ሆኖ ሲያገለግል ኖሯል፡፡ የሆድ ህመም የሚያስቸግራቸው ሰዎች ከሱፐር ሚንት የሚዘጋጅ መድሃኒት ለአራት ሳምንት በቀን ሁለት ግዜ በመውሰድ ህመማቸውን ከ50 በመቶ በላይ መቀነስ ይችላል፡፡
• የህመም ማስታገሻ፡- የቡሽሜን ማህበረሰብ የብራዚል ሜንትን ልክ እንደ አስፕሪንኪኒን በመጠቀም ከህመማቸው ማረፍ(ማስታገስ) እንደሚችሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
• ለቆዳ፡- ብዙን ግዜ ቆዳችን በትንኝ ንክሻ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ሊጎዳ ይችላል፡፡ከናና የሚዘጋጅ የውበት መጠበቂያ ሎሽኖች ፍቱን መፍትሆ መሆናቸው ተደርሶበታል፡፡
• ለአፍ ውስጥ ጤንነት፡- የናና ቅጠል ተፈጥሮአዊ ጸረ-ተህዋሲያን ንጥረ ነገር በውስጡ በመያዙ ለአፍ ውስጥ ጤንነት እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ በተጨማሪም መልካም የአፍ ጠረን እንዲኖር ያደርጋለል፡፡
የናና ቅጠል የጎንዮሽ ጉዳት ሊኖረው ስለሚችል ስንጠቀም በጥንቃቄ መሆን ይኖርብናል
• እጅግ መጠኑ የበዛ ጦስኝ መጠቀም አይመከርም
• ለህጻናትና ለጨቅላዎች የሚንት ዘይት መቀባት አደገኛ ነው
• የሀሞት ጠጠር ያለበት ሰው ናና(ሚንት) መጠቀም አይኖርበትም
• ነፍሰጡር ለሆኑ ሴቶች እንዲጠቀሙ አይመከርም፡፡
ምንጭ፡ Medical News Today

የSpaceX ካፕሱል በፍሎሪዳ በሚያደርገው ሙከራ ላይ ችግር እንዳጋጠመው ተገለጸ ግዙፉ የአሜሪካ ኩባንያ SpaceX ፍሎሪዳ በሚገኘው ኬፕ ካናቫራል የአየር ሃይል ጣቢያ ሲያደርገው የነበረው የጠፈርተኞች ካፕሱል ሙከራ አንዳች አደጋ እንዳጋጠመው የአሜሪካ አየር ሃይል ቃል አቀባይ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
አየር ሃይሉ እንዳስታወቀው በመንኮራኩሯ ዙሪያ ሲደረግ የነበረው የመጀመሪያ ሙከራ በስኬት የተጠናቀቀ ቢሆንም በመጨረሻው የጠፈርተኞች ካፕሱል ክፋይ ላይ በተደረገ የሞተር ሙከራ ግን የመለያየት (anomaly) አደጋ መከሰቱን ጠቁሟል፡ https://www.facebook.com/TechinEthiopia/photos/a.565568780217878/2153208101453930/?type=3&theater

Facebook
Technology and Innovation Institute, Ethiopia
የSpaceX ካፕሱል በፍሎሪዳ በሚያደርገው ሙከራ ላይ ችግር እንዳጋጠመው ተገለጸ ******************************************************************* ግዙፉ የአሜሪካ ኩባንያ SpaceX ፍሎሪዳ በሚገኘው ኬፕ ካናቫራል የአየር ሃይል ጣቢያ ሲያደርገው የነበረው የጠፈርተኞች ካፕሱል...
አነስተኛ የውልደት እና ጋብቻ ምጣኔን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሳቢያ በአንድ ቤት ውስጥ ለብቻቸው የሚኖሩ ግለሰቦች ቁጥር በመጨመር ላይ ይገኛል፡፡ ይህ የብቸኝነት ኑሮ ከአዕምሮ ጤና መቃወስ ጋር ያለውን ዝምድና የሚገመግሙ ጥናቶች ከዚህ ቀደም ተከናውነው ቢያልፉም ዕድሜያቸው በገፋው ላይ ብቻ አተኩረው ነበር የሰሩት፡፡
አዲስ በተሰራው በዚህ ጥናት ታድያ አጥኚ ቡድኑ ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 64 በሆኑ 20,500 የሐገረ እንግሊዝ ነዋሪዎች ላይ በተለያዩ ዓመታት ከተደረጉ ዳሰሳዎች የተወሰደ ጥሬ ሃቅን በግብዓትነት አካቷል፡፡ ግለሰቦቹ የአዕምሮዓዊ ጤና መቃወስ ተጠቂ መሆን አለመሆናቸውን እንዲያመላክት የሚያስችል ፅሁፋዊ የህክምና መጠይቅ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን በግለሰቦቹ የሰውነት ክብደት፣ ቁመት፣ የመጠጥ አወሳሰድ፣ አደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም፣ ማህበራዊ ድጋፍ እና ብቸኝነት ላይም መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡
እ.አ.አ በ1993፣ 2000 እና 2007 ለብቻቸው ይኖሩ የነበሩት ግለሰቦች ምጣኔ 8.8፣ 9.8 እና 10.7 በመቶ የነበር ሲሆን በነዚህ ወቅቶች የነበረው የጋራ አዕምሮዓዊ ጤና መቃወስ (Common Mental Disorder) ምጣኔ 14.1፣ 16.3 እና 16.4 በመቶ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በነዚህ ዓመታት ውስጥ በማንኛውም ፆታም ሆነ እድሜ ውስጥ ያሉ ላጤዎች ከአዕምሮዓዊ ጤና መቃወስ ጋራ የላቀ ቁርኝትን ፈጥረዋል (በሁለቱ መሀል ያለው ምጣኔ ወይም Odds Ratio በ1993-1.69፣ 2000-1.63 እንዲሁም 2007-1.88 ነው)፡፡ በጠቅላላው ለብቻቸው የሚኖሩ ሰዎች ለአዕምሮ ጤና መቃወስ ያላቸው ተጋላጭነት ከ1.39 እስከ 2.43 እጥፍ የላቀ እንደሆነ ለማረጋገጥ ሲቻል ከነዚህ ውስጥ 84 በመቶዎቹ የአዕምሮ ጤና መቃወስ ተጋላጮችም ብቸኝነት እንደሚገልፃቸው የጥናት ቡድኑ አስረድቷል፡፡
ምንጭ፡ Science Daily