TechIn2
1.17K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
በነብሳት (ሶስት አጽቄዎች) ቅርጽ የተሰራ የኮምፒውተር ሲስተም
*****************************
ኢንሴክት ኮምፒውተር የተባለ ወረርሽኞች እና የተለያዩ አደጋዎች ከተከሰቱ በኋላ ለሚደረግ የአሰሳ ስራ ተግባር ላይ የሚውል ሲስተም ይፋ ተደረገ፡፡ ከሲንጋፖር፣ ቻይና፣ ጀርመንና እንግሊዝ የተውጣጡ የተመራማሪዎች ቡድን ይህን ልዩ ቴክኖሎጂ ሰርተው እንዳቀረቡ ተነግሯል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች መጠናቸውና ድግግሞሻቸው እጅግ ከፍ እያለ ይገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት ተመራማሪዎች በአደጋዎች ለሚጠቁ ሰዎች ድጋፍ ለማድረግና የሞትና የአካል ጉዳት መጠንን ለመቀነስ የተለየ ስልት ያስፈልጋል ብለው ያምናሉ፡፡ እንደ ጎርፍ፣ ገሞራ ፍንዳታ፣ ሰደድ እሳት እና ሌሎች አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ሰዎችን በመጠቀም የሚደረገው የድጋፍ እንቅስቃሴ ተጨማሪ አደጋ የሚያመጣ በመሆነ በጣም አነስተኛ መጠን ያላቸው (ልክ እንደ ነብሳት) የቴክኖሎጂ ቁሶችን መጠቀም በጣም አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል፡፡
ተመራማሪዎች በማዳጋስካር የሚገኝን ክንፍ አልባ በረሮ ቅርጽን በሞዴልነት በመውሰድ እና በረሮው ሊሸከመው በሚችለው መልኩ ተዘጋጅቶ አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ በቦታዎቹ በመገኘት ፍለጋዎችንና የተለያዩ መረጃዎችን ማቀበል የሚያስችል ማይክሮ ቴክኖሎጂን ነው ያቀረቡት፡፡ ይህ ቴክኖሎጂም አምስት እርስ በርሳቸው የተገናኙ ሰርኪዩቶች ያሉትና እንደ ካሜራ፣ የግንኙነት ቺፕ፣ የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ መለኪያ፣ ሚሞሪ እና ሌሎች አስፈላጊ ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙለት ነው፡፡
ይህ አነስተኛ መጠን ያለው የኮምፒውተር ሲስተም በበረሮው ጀርባ ላይ በቀላሉ መቀመጥ እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡ በተጨማሪም በረሮው አካባቢውን ለመረዳት የሚጠቀምበትን እንደ አንቴና ያለ ክፍል ላይ ኤሌክትሮድ በማስገባት የበረሮው እንቅስቃሴ በኤሌክርቲክ ሞገድ አማካኝነት በተሸከመው ማይክሮ ቴክኖሎጂ እንዲመራ ማድረግ ተችሏል፡፡
በሙከራ ወቅትም 94 በመቶ የተሳካ የተጎጅዎችን ፍለጋ ማካሄድ ተችሏል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-06-insect-computer-hybrid-disasters.html
መቋጫውን ያገኘው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋማት አቅም ግንባታ ስልጠና
======================
በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ተዘጋጅቶ በአራት የታዳጊ ክልሎች እና የድሬደዋ ከተማ አስተደዳደር ውስጥ ላሉ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተቋማት ሲሰጥ የቆየው የሦስት ቀናት ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል፡፡ በቢሾፍቱ ከተማ ሲሰጥ የቆየው ስልጠናው በስታርታፕ፣ ዲጂታል ተግባራት እንዲሁም የፕሮጀክት አስተዳደርና ሌሎች ጉዳዮችን የዳሰሰ ነበር፡፡
የመሰናዶው መጠናቀቅያ በሆነው የዛሬው ዕለትም በኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች አማካኝነት ገለፃዎች ሲቀርቡ ቆይተዋል፡፡ የዕለቱን የመጀመሪያ ገለፃ ያቀረበችው ወ/ት አለሜ ወ/ገብርኤል የስታርታፕ ስነ ምህዳርን አስመልክታ በሀሳቡ ምንነት፣ የሚያስገኘው ጥቅም እንዲሁም የመንግስትና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ አካላትን ጨምሮ ባለድርሻዎችን የዘረዘረች ሲሆን ከዚህም ባሻገር የህንድ እና ኢስቶኒያን እንቅስቃሴ እንደምሳሌ በማጣቀስ እንዴት ስኬታማ የሆነ የስታርታፕ ስነ ምህዳር መፍጠር እንደሚቻል አስረድታለች፡፡
ሌላኛው የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪ አቶ ሙሉጌታ አንበሴም እንዲሁ በሀገራችን ስታርታፖችን ለማውጣት የራሱን ሚና እንደሚጫወት በሚጠበቀውና ኢንስቲትዩቱ በሚያዘጋጀው የቅድመ ኢንኩቤሽን ፕሮግራም ዙርያ ማብራርያ ሰጥቷል፡፡ በያዝነው ዓመት ብቻ ኢንስቲትዩቱ ሁለት የቅድመ ኢንኩቤሽን ፕሮግራሞችን አዘጋጅቶ እንደነበር ያስረዳው አቶ ሙሉጌታ ፕሮግራሞቹ አንግበው በተነሱባቸው ዓላማዎችና ተጠቃሚ ባደረጓቸው የፈጠራ ባለሙያዎች እንዲሁም በቀጣይነት የኢንኩቤሽን ደረጃ ላይ ሲደረስም በሚኖሩት ሁኔታዎች ላይ ያውጠነጠነ ገለፃን አቅርቧል፡፡ ከዚህም ባለፈ እነዚህን መሰል ፕሮግራሞችን ወደ ክልል ከተሞች ቢስፋፉ ሊኖራቸው ስለሚችለው ጠቀሜታ ተናግሯል፡፡
ሌላኛው የዕለቱ ገለፃ አቅራቢ አቶ ደስታ አበራ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ስር ሆኖ የስልጠና እና ድጋፍ ስራዎችን በሚያከናውነው ዳይሬክቶሬት የስራ ክንውኖች ላይ አተኩረው ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ የስራ ክፍላቸው ከማይክሮሶፍት አፍሪካ፣ ኮይካ፣ ሲስኮ እና ላይት ሃውስ ከተሰኙ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ከስምምነት በመድረስ የጋራ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ያወሱት አቶ ደስታ በተለይም ከማይክሮሶፍት አፍሪካ ጋር በመተባበር 50 ያህል ሰዎች ጠቃሚ ስልጠናን እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ በዳይሬክቶሬቱ አማካኝነት በአጠቃላይ ከ600 በላይ ሰዎች ስልጠና እንዲያኙ መደረጉንና ከዚህም ባሻገር የፈጠራ ስራዎች ወደ ምርት እንዲያሳድጉ ታስበው ስለተከናወኑ የሰመር ካምፕ ዝግጅቶችንም ለታዳምያኑ አብራርተዋል፡፡
ቀና ብለን ስንመለከት ጊዜን ወደኋላ እየቃኘን ነው
-------------------------------------
ጊዜ ከማይክሮ ሴኮንድ ተነስቶ ሴኮንድ፣ ደቂቃ፣ ሰዓት፣ ቀናት፣ ወራት እና አመታት እያለ ይነጉዳል፡፡ ድምፅና ብርሃን በእነዚህ ጊዚያት ውስጥ ከመንጎድ ይልቅ ይበናሉ፡፡ ድምፅ በየሶስት ሴኮንዱ አንድ ኪሎ ሜተር ያክል የሚጓዝ ሲሆን፤ ብርሃን በበኩሉ በየአንድ ሴኮንዱ 300,000 ኪሎ ሜትር አቋርጦ ይሄዳል፡፡ ብርሀን በህዋ አካለት ውስጥ የመለኪያና የመግባቢያ ቋንቋ በመሆኑ ከምድራችን ውጭ ያሉ አለማትንና ከዋክብትን ለመቃኘት ይረዳናል፡፡ ለምሳሌ የኛዋ ፀሃይ ከመሬት ያላት ርቀት 150 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር በመሆኑ ከሷ የሚመነጨው ብርሃን ወደኛ ለመድረስ 8 ደቂቃዎች ብቻ ያስፈልጉታል፡፡ ይህ ማለት ፀሃይን በተመለከትናት ቁጥር በየስምንት ደቂቃው የሚኖራትን ገፅታ ተመለከትን ማለት ነው፡፡
በአንፃሩ ጨረቃ ከመላው ዩኒቨርስ እጅግ የምትቀርበን አካል በመሆኗ ከፀሃይ የምታገኘውንና ከገጿ ተንፀባርቆ የሚመለሰውን ብርሃኗን ለመመልከት ጥቂት ሰከንዶች ብቻ ያስፈልጉናል፡፡ ይህም ማለት ጨረቃ ከምድር የምትርቅበት መጠን 380,000 ኪ.ሜ በመሆኑ ከሷ የሚነሳ ብርሃን ወደኛ ለመድረስ 1.3 ሰኮንዶች ብቻ ያስፈልጉታል ማለት ነው፡፡ ጨረቃን በየ 1.3 ሰኮንድ ልዩነት ስለምንመለከታት ምንም አይነት ለውጥ አናይባትም፡፡ ይሁንና ከስርዓተ ፀሃያችን ውጭ ያሉ ከዋክበት ወይም ሌሎች የህዋ አካለት የሚያመነጩትን ብርሃን ስንመለከት ጊዜን ወደኋላ እየቃኘን ነው፡፡ ድቅድቅ ባለ ጨለማ ውስጥ ቀና ብለን ከምንመለከታቸው ክዋክብት መካከል አንዳንዶቹ በአሁኑ ጊዜ ህልውናቸው ያከተመ ሊሆን ይችላል፡፡
ለምሳሌ ለእኛ ፕላኔት ቅርቡ የሆነው አልፋ ሴንቸሪ የተሰኘው ኮከብ ከኛ አራት የብርሃን አመታት ይርቃል፡፡ ይህ ማለት ብርሃን በሴከንድ ሶስት መቶ ሺህ ኪሎ ሜትር እየተጓዘ አራት አመታት ያህል የሚወስድበት እርቀት ሲሆን ይህ ርቀት በኪሎ ሜትር ሲለካ ከሰላሳ ስድስት ትሪሊዮን ኪሎ ሜትር በላይ ነው፡፡ ይህ ማለት አሁን የምናየው የኮከቡ ገጽታ አሁን ያለውን መልኩን ሳይሆን ከአራት የብርሃን አመታት በፊት የነበረውን ነው፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ከኮከቡ የዛሬ አራት አመት በፊት የተነሳው ብርሃን ከርቀቱ የተነሳ እኛ ጋ የደረሰው አሁን በመሆኑ ነው፡፡
አሁን ያለውን የኮከቡን መልክ ለማየት አራት የብርሀን አመታት መጠበቅ አለብን። ምክንያቱም ብርሃኑ ከኮከቡ ዛሬ ቢነሳ እኛ ጋ የሚደርሰው ከአራት የብርሃን አመታት በኋላ ስለሆነ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ለእኛ ቅርቡ የሆነው ኮከብ ያለው ርቀት ሲሆን በሚሊዮን የብርሃን አመታት ከእኛ የሚርቁ ከዋክብት አሁን የምናየው መልካቸው ከሚሊዮን አመታት በፊት የነበረ ነው፡፡ ምናልባት በአሁኑ ሰዓት በእድሜ ብዛት ሞተው ወይም ፈንድተው ድምጥማጣቸው ጠፍቶ ሊሆን ይችላል፡፡
https://theconversation.com/when-you-look-up-how-far-back-in-time-do-you-see-101176
በ28 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ጉዞ ወደ ጠፈር
************************
ከአማዞኑ መስራች እና እውቁ የአለማችን ሀብታም ጋር ወደ ጠፈር ጉዞ ለማድረግ ጨረታ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ የአለማችን እውቁ ባለሃብት ጄፍ ቤዞስ ከወንድሙ ማርክ ጋር በመሆን የፊታችን ነሐሴ 20 ወደ ጠፈር ለመምጠቅና ለመመለስ አስበው ብዙ ስራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በዚህ በረራም አንድ ተጨማሪ ሰው አብሮ እንዲጓዝ በመታሰቡ ከፍተኛ የሆነ ጨረታ ሲካሄድ ነበር፡፡ በጨረታውም አንድ ማንነቱ ያልታወቀና በሚስጢር ሲወዳደር የነበረ ሰው በ28 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማሸነፍ ችሏል፡፡
የአማዞኑ መስራች ጄፍ ቤዞስ ወደ ህዋ ለመምጠቅ የተነሳው የራሱ ካምፓኒ በሆነው ብሉ ኦሪጅን አማካኝነት በተሰራው ሮኬት ነው፡፡ ጨረታውን ያሸነፈው ተጓዥ በጨረታው 20 የሚደርሱ ተወዳዳሪዎችን ያሸነፈ ሲሆን በአጠቃላይ ሮኬቷ 4 ሰዎችን የምትይዝ ይሆናል፡፡ ሮኬቷ የምትወነጨፍበት ቦታ በበረሃማው የምዕራብ ቴክሳስ ክፍል ሲሆን የምድር ከባቢ አየርና የህዋ መለያ ነው ተብሎ በሚታሰበው ቦታ (የካርማን መስመር) ላይ ለ10 ደቂቃ ያክል አራቱን ተጓዦች ለማቆየት ታስቧል፡፡
በዚህ አመት መጨረሻ ላይ ከአማዞን ሀላፊነቱ ለመልቀቅ እንዳሰበ የተናገረው ጄፍ ቤዞስ በቀጣይ እንደ ብሉ ኦሪጅን ያሉ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት እንዳሰበም ተናግሯል፡፡ አክሎም ወደ ህዋ መጓዝ የህይወት ዘመን ህልሙ እንደነበር ገልጧል፡፡ በብሉ ኦሪጅን አማካኝነት የተሰራው ሮኬት ከቴክሳስ ከ10 በላይ የሆኑ ሰው አላባ የተሳኩ ሙከራዎችን ማካሄድ ችሏል፡፡
ምንጭ phys.org
ተጨማሪ ንባብ https://phys.org/news/2021-06-space-jeff-bezos-mn.html
የባርኮድ ቴክኖሎጂ እንዴት ይሰራል
ባርኮድ የተለያዩ ቋሚ መስመሮችን በመጠቀም እቃዎች ላይ የሚታተም፣ ይህም በቀላሉ ስካን መደረግና በኮምፒውተር መነበብ የሚችል እና አንድን እቃ ለመለያነት የሚያገለግል ቴክኖሎጂ ነው። የባርኮድ መሳሪያ ለአጠቃቀም ቀላል፣ ፈጣን፣ ዋጋውም ከሚሰጠው አገልግሎት አንፃር ውድ የማይባል እና የሰዎችን ድካምና ለስህተት የመጋለጥ ችግሮችን የሚቀንስ ቴክኖሎጂ ሲሆን የአሰራር ሂደቱም እንደሚከተለው ነው። የቴክኖሎጂው አሰራር በባርኮድ መፍጠሪያ ወይም (Barcode Generator) የሚጀምር ሲሆን ይህም ወደ ባርኮድ መቀየር የምንፈልገውን ቁጥር፣ ፊደል፣ ቃል ወይም ምስል ወደ ሲስተሙ በማስገባት፤ ይህም የገባውን ፅሁፍ ወደ ተለያየ መጠን ወዳላቸው ቋሚ መስመሮች መቀየር የሚያስችል ነው። ይህንንም ለማንበብ የባርኮድ ማንበቢያ መሳሪያ ይጠቀማል። ባርኮዱ ላይ የሚገኙትን ዘንጎች ንፅፅራዊ ስፋትና ቦታቸውን በመለካት የዘንግ ሞዴሎቹን ተገቢ ወደሆኑ ፊደሎች በመተርጎም ወደ ኮምፒውተሩ ይልካቸዋል።
በመቀጠል በባርኮድ ማንበቢያ ባርኮድን በምናነብበት ጊዜ የምናገኛቸው ፊደሎች ባርኮዱ ላይ ባሉ ሰፊና ጠባብ ዘንግ መሳይ ሞዴሎች ይገለፃሉ። የባርኮድ ማንበቢያ ባርኮዱን በሚያነብበት ጊዜ ፎቶ ሴንሰር (Photo Sensor) በመጠቀም ባርኮዱን ወደ ኤሌክትሪካዊ ሲግናል (Electric Signal) ይቀይረዋል። በመቀጠልም የባርኮድ ማንበቢያው ባርኮዱ ላይ የሚገኙትን ዘንጎች ንፅፅራዊ ስፋትና ቦታቸውን በመለካት የዘንግ ሞዴሎቹን ተገቢ ወደሆኑ ፊደሎች በመተርጎም ወደ ኮምፒውተሩ ይልካቸዋል።
ማንኛውም ባርኮድ የባርኮዱ መጀመሪያ መሆኑን የሚያሳይ ለየት ያለ ዘንግ የሚኖረው ሲሆን፤ እንዲሁም በባርኮዱ መጨረሻ ላይ የባርኮዱ መጨረሻ መሆኑን የሚያመላክት ለየት ያለ ዘንግ ይይዛል። እነዚህ ኮዶች የባርኮድ ማንበቢያው በሚያነብበት ጊዜ ባርኮዱ እያነበበ ያለው ከመጨረሻ ወደ መጀመሪያ ወይም ከመጀመሪያው የባርኮድ ክፍል ወደ መጨረሻው የባርኮድ ክፍል መሆኑን ለይቶ እንዲያውቅ ይረዱታል።
ምንጭ፡ lightspeedhq
ተጨማሪ https://www.lightspeedhq.com/blog/how-do-barcodes-work/
40 መቀመጫ ያለው ድሮን አውቶቢስ
*********************
መነሻ ሀሳቡ እጅግ ዘመናዊ ከሆነውና ከኒው ጀርሲ ወደ ኒዮርክ ከተዘረጋው ባቡር የሆነ ባለ 40 መቀመጫ ድሮን አውቶቢስ መሰራቱ ተነገረ፡፡ ይህም ሀሳብ በኮቪድ ምክንያት በሰዎች መካከል የሚፈለገውን አካላዊ ርቀት ለመጠበቅ በሚያስችል መልኩ የተጠነሰሰ ነው፡፡ መኪናው በራሪ እንዲሆን ታስቦ የተሰራ ሲሆን ካለበት ቦታ ሁሉ መነሳትና ማረፍ እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡
በራሪ መኪናው በአራቱም አቅጣጫ የተገጠሙ ሁለት ሁለት በአጠቃላይ ስምንት ተሽከርከሪዎች (ፋኖ) ያሉት ሲሆን እነዚህም መኪናው የተሳካ በረራ እንዲያደርግና ወደ መሬት ለመውረድና ከመሬት ለመነሳት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እጅግ ቀላል የሚያደርጉለት ናቸው፡፡ የዚህ ፈጠራ ባለቤት የሆነው ኬሌኮና የተሰኘው የቴክኖሎጂ ድርጅት በራሪ አውቶቢሱ አሁን ላይ ያለውን የህዝብ ትራንስፖርት የሚፎካከርና ሊተካ የሚችል እንደሆነ ይፋ አድርጓል፡፡
ድርጅቱ አክሎም በ2023 አገልግሎት መስጠት ይጀምራል የተባለውን የኡበር የአየር ላይ ታክሲ የሚፎካከር እንደሆነም ገልጧል፡፡ ለዚህም በራሪ አውቶቢሱ በአንድ ጊዜ 40 ሰዎችን መጫን የሚችል መሆኑ እንደመተማመኛ ተወስዷል፡፡ እንደሚታወሰው ኡበር በአየር ላይ ታክሲው ከአብራሪው ሌላ አንድ ሰው ብቻ ለማጓጓዝ ያሰበ ነው፡፡
እንደ ኒዩርክ ባሉ እጅግ በተጨናነቁ ከተሞች በአንዴ ያለምንም
የመንገድ መጨናነቅ 40 ሰዎችን ማጓጓዝ መቻሉ እጅግ ተመራጭ እንደሚያደርገው ይጠበቃል፡፡ በመጀመሪያው ዙር ድርጅቱ ከማንሃታን ወደ ሃምፕቶንስ የ30 ደቂቃ በረራን በ85 ዶላር ለማድረግ ያሰበ ሲሆን በቀጣይም ከቦስተን ወደ ኒዮርክ፣ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ሎስ አንጀለስ እና ሳንፍራንንስኮ በረራውም የተሳካ እንዲሆን በሰዓት 3.6 ሜጋ ዋት ሀይልን የሚያመነጭ ባትሪን በልዩነት እንዳዘጋጀም ድርጅቱ ይፋ አድጓል፡፡ ይህ ሀይል ከፍተኛ ሲሆን በመቶዎች ወይም በሺዎች ለሚቆጠሩ ቤቶች አገልግሎት የሚውልን ሀይል የሚወዳደር ነው፡፡ በድርጅቱ እቅድ መሰረት የእቃ ማጓጓዝ አገልግሎትን በ2022 የሚጀምር ሲሆን ሰዎችን ለማመላለስ 2024ን የቀጠሮ ቀን አስቀምጧል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-06-startup-kelekona-seat-drone-bus.html
መሰረታቸውን ህዋ ላይ ያደረጉ የበይነ-መረብ አውታር-መረቦች
*********************************
ከጥቂት ወራት በፊት ሰዎች የስታር ሊንክ ምልክቶችን በምሽት ሰማይ ላይ እንዳዩ ተናግረው ነበር፡፡ ይህ በምሽት ሰማይ የታየው ከዚህ አለም ውጭ የሆነ ወይም ስነ ፈለካዊ ገጽታ ያለው ሳይሆን በቅርብ ጊዜያት በስፔስ ኤክስ አማካኝነት የተወነጨፉ ሳተላይቶች የፈጠሩት ግንኙነት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ይህም ለወደፊት ከፍተኛ የሆነ የሳተላይቶች ግንኙነትን ወይም ስታር ሊንክን መፍጠር በሚያችል መልኩ በብዙ ሳተላይቶች ግንኙነት እንደሚቀጥልም እየተነገረ ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት ምድራችን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ኢንተርኔት አገልግሎትን እንድታገኝ የሚያደርጋት ግዙፍ ፕሮጀክት አካል ነው፡፡
ስታር ሊንክ አገልግሎት እየሰጡ ካሉ አለማቀፍ የሳተላይት ግንኙነቶች ውስጥ የሆነና በእድገት ላይ ያለ አውታር-መረብ ወይም (ኔትወርክ) ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ የሳተላይቶች ትስስር ቴክኖሎጂ ከምሽት ሰማይ ጋር የተያያዙ አንዳንድ ቅሬታዎች እየቀረቡበት ነው፡፡ ስታር ሊንኮቹ እያንዳንዳቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ሳተላይቶችን ከተለያየ ከፍታ እና አንግል እንዲገናኙ በማድረግ ከቅርብም ሆነ ከሩቅ ያሉ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ግኙነት እንዲፈጥሩ ያስችላሉ፡፡
ሳተላይቶችን በማገናኘት የተለያዩ የበይነ መረብ አገልግሎት ከሚሰጡና በአለማችን ካሉ ግዙፋን ተቋማት ውስጥ አራቱ ስፔስ ኤክስ፣ ቴሌሳት፣ ዋን ዌብና አማዞን ዋነኞች ናቸው፡፡ መኤም አይ ቲ ውስጥ የሚሰሩ ተመራማሪዎች እነዚህን የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢ ተቋማት በማወዳደር መርምር ሰርተዋል፡፡
ተመራማሪዎቹም የእያንዳንዱን ተቋም አለማቀፍ የዳታ አቅም ተቋማቱ ባላቸው ቴክኒካዊ መረጃ መሰረት አስልተዋል፡፡ የእያንዳንዱ ተቋምም ኔትወርክ በሚጠቀሙት የሳተላይት ብዛት፣ የምድር ላይ መቆጣጠሪያዎች እና የግንኙነት አቅም መሰረት ተቋማቱ በሴኮንድ በአስሮች የሚቆጠር ቴራባይት ጥቅል አቅም እንዳላቸው ታውቋል፡፡
እነዚህ መሰረታቸውን ህዋ ላይ ያደረጉ የበይነ መረብ አገልግሎቶች በምድር ላይ ተመስርተው በሴኮንድ በሼዎች የሚቆጠር ቴራባይት የሚሰጠውን አገልግሎት የሚተኩ እንዳልሆኑና ይልቁንም በገመድ አማካኝነት ኢንተርኔትን ተደራሽ ማድረግ በማይቻልባቸው ቦታዎች የበይነ መረብ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ናቸው፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-06-largest-internet-meganetworks.html
የ3D ቴክኖሎጂ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሚኖረው ጠቀሜታ
=====================
የሳይንስና ቴክኖሎጂ አቅም የትምህርት ዘርፉን ለመደገፍና ለማበልፀግ ጥቅም ላይ ከመዋሉ ባለፈ ለብዙ አገራት የተሻለ የኢኮኖሚ ዕድገት ደረጃ ላይ መገኘት የሳይንስና ቴክኖሎጂው ዘርፉ የተጫወተው ሚና እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው። የ3D ፕሪንቲንግ ቴክኖሎጂ በዚህ የልማት ሂደት ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሲሆን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ ጥቅም ላይ መዋሉ ደግሞ ይበልጥ ተመራጭ ያደርገዋል፡ ያደጉ ሀገራት በዚህ ዘርፍ ላይ ብዙ እርምጃ የተራመዱ ሲሆኑ ገና በማደግ ላይ ሀገራትም ዘርፉን በመጠቀም የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ እንደሚችሉ ይጠቀሳል፡፡ ይህ የቴክኖሎጂ አይነት በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ ከሚውልባቸው ዘርፎች መካከል ጥቂቶቹን እንመልከት፡፡
የግብርና ቁሶችን ለማምረት (3D Printed Agricultural Tools) የ3D ፕሪንቲንግ ቴክኖሎጂ የአገራቱ አርሶ አደሮች በራሳቸው የተለያዩ የግብርና ምርቶችን በማምረት እንዲጠቀሙ እና ራሳቸውንም ከተለያዩ ወጪዎች በመታደግ የኢኮኖሚ አቅማቸውን ማሳደግ እንዲችሉ ዕድልን ይከፍታል። አሁን በታዳጊ አገራት አርሶ አደሮች የተለያዩ በእጅ የተሠሩ ቁሳቁሶችን በመጠቀም ላይ ይገኛሉ። በተጨማሪም ጊዜው ደግሞ አምራቹ ኃይል/ወጣቱ ከገጠር ወደ ከተማ በተለያዩ ምክንያቶች እየተመመ ያለበት ሁኔታ ላይ ይገኛል። ይህ ደግሞ የተቀሩት ህዝቦች የማምረት አቅማቸው የደከመ በመሆኑና ሌላ ተጨማሪ አቅም እንደሚያስፈልጋቸው ያመለክታል። የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን ለማከናወን እነዚህ አርሶ አደሮች የተሻሻሉ እና በአይነታቸው አዲስ የሆኑ የዚህ ቴክኖሎጂ ግኝቶችን ይፈልጋሉ። ይህም ለማረስ፣ ለማጨድ፣ ለማረም፣ ለመዝራት፣ ምግባቸውን ለመስራት እንዲሁም ለሌሎች ተግባራት የሚረዷቸው ይሆናል። እነዚህ አገራት የተሻሻሉ እና ተመሳሳይ የሆኑ የፈጠራ ግኝቶችን እንደየዘርፉ አስፈላጊነት በማምረት ለሰፊው ማህበረሰብ ማድረስ ይችላሉ ማለት ነው።
ታዳሽ የኃይል አማራጭን በማምረት ረገድ (Low Energy Solutions) ታዳሽ የኃይል አማራጭን ከማምረት አንፃር ደግሞ በታዳጊ አገራት ውስጥ እንዴት ተጨማሪም ሆነ የአደጋ ግዜ ታዳሽ ኃይሎችን በዚህ ቴክኖሎጂ አማካኝነት መፍጠር እንደሚቻል ያሳያል። ለምሳሌ በ2010 በሀይቲ አገር በመሬት መንቀጥቀጥ አማካኝነት የተፈጠረውን ችግር ለመታደግ የኃይል መቋርጥ ችግሩን ከባድ ሊያደርገው ይችል የነበረ ሲሆን በዚህ አደጋ ግዜም የታደጋት የሀይል አማራጭ የተገኘውም በ3-ማዕዘን የተመረተው ታዳሽ ሀይል ነበር። ይህ ጥናት እስካሁንም በጥናት እና ሙከራ ላይ ያለ ሲሆን ሲጠናቀቅም የኃይል እጥረት በብዛት ለሚታይባቸው ታዳጊ አገራትም ጥሩ መፍትሔን ይዞ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በውሃ እና የግል ንፅህና ላይ (Water and Sanitation) የ3 ዲ ቴክኖሎጂ በታዳጊ አገሮች ውስጥ በተደጋጋሚ የዝናብ ውሃን ለማቆር የሚረዱ ፕላስቲኮችን ለማምረት ያገለግላል። በተጨማሪም የተለያዩ የውሀ ማጣሪያና ማፅጃ ፕላስቲኮችን ለማምረት ይረዳሉ። ይህም ቁሱ ቆሻሻውን ውሀ እስከ 85º C በማሞቅ በእንፋሎቱ አማካኝነት ተጣርቶና ተከማችቶ ንፁህ ውሀን መፍጠር ወደሚችልበት ደረጃ ላይ ይደርሳል። ይህ ሂደት ደግሞ የውሃ ብክለት/ንፅህና ችግርን የመቅረፍ አቅም አለው። በተጨማሪም ይህ የ3D ፕሪንቲንግ ቴክኖሎጂ የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ሳሙናዎችን ማስቀመጫ እና የመፀዳጃ ቤት መገልገያ ቁሶችን በዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ አስተዋፅኦ አላቸው።
https://www.makerbot.com/.../top-5-3d-printing-application/
የዘመነ የመአድን ስራ ለከፍተኛ ሀብት
**********************
ዲጂታላይዜሽን ወይም ስራን ማዘመን በተለይ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ድካምን በመቀነስ ምርታማነትን የሚያሳድግ ከፍተኛ ጥቅም ያለው አሰራር ነው፡፡ እንደ አለም ኢኮኖሚክ ፎረም መረጃ ከሆነ የዘመነ የማእድን ፍለጋ እና አጠቃላይ ስራ በአለማችን ውስጥ በአመት እስከ 321 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያስገኛል፡፡
የተቋማት ዲጂታል ሽግግር በአለማችን ውስጥ ከፍተኛ እድገት እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ድንጋይና ሌሎች ማእድናት ላይ ያለው ዘመናዊ አሰራር አሁንም ተጨማሪ መሻሻሎች የሚፈልገ ነው፡፡ በዘርፉ አንድ በቻይናና በኖሮይ ትብብር የሚሰራ ፕሮጀክት ተስፋ ሰጭ ነገሮችን ይዞ እንደመጣ ተነግሯል፡፡ በተለይም የማእድን (በተለይ ከድንጋይና ከብረት ጋር የተያያዙ) ሙያተኞችንና በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን በጥምረት እንዲሰሩ በማድረግ ከዘርፉ ሊገኝ የሚገባውን ከፍተኛ ጥቅም ሀገራት ማግኘት እንደሚችሉ የመረጃ ምንጫችን ሲንትፍ ኢንደስትሪን እና የምርምር ተቋምን ዋቢ አድርጎ የሰራው ዘገባ ያመለክታል፡፡
እንደሚታወቀው ቻይናና ኖሮይ በከፍተኛ ሁኔታ በማዕድን ቁፋሮ ዙሪያ እየሰሩ እና ውጤትም ያስገኙ ሀገራት ናቸው፡፡ የሁለቱ ሀገራት ጥምረትም በዘርፉ ያለውን የዘመናዊነት ችግር ለመቅረፍ ያለመ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ኖሮይ ለጸሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ፓኔልና ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ምርት ዋነኛ ግብዓት የሆነውን ሲልከንና ለብረት ምርት ከፍተኛ ግብዓት የሆነውን ማንጋኔዝ በማምረት ትታወቃለች፡፡ ቻይና ደግሞ በወርቅ ምርቷ ቀዳሚ ሀገር ናት፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱም ሀገራት ዘርፉን በማዘመን ረገድ ወደኋላ የቀሩ ነበሩ፡፡
የማእድን ዘርፉን ማዘመን ከሚሰጣቸው ጥቅሞች ውስጥ ከፍተኛ የሀይል ብክነት ቅነሳ፣ ውጤታማና ደህንነቱ የተጠበቀ አሰራር፣ የተሸለ የጥሬ እቃ አጠቃቀም፣ ስኬታማ የማእድናት ፍለጋ እና በኢንዱስትሪዎች፣ በመንግስትና በምርምር ተቋማት መካከል የተሸለ ግንኙነት መፍጠር ያስችላል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-06-digitalization-goldmine-real.html
TECHIN seminar
=========
የቴክኢን ሴሚናር መርሃ-ግብራችን ነገ ሐሙስ የሚመለስ ሲሆን በዚህ ሳምንቱ የቴክኢን ሴሚናርም “Robots, Automation and Smart Systems” በሚል ርዕስ በአቶ በኩረፅዮን ፀጋዬ ገለፃ አቅራቢነት የሚመራ ውይይት የሚከናወን ይሆናል፡፡
ስፍራ፡ 4 ኪሎ በሚገኘው የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት መሰብሰቢያ አዳራሽ
ቀን፡ ነገ ሐሙስ ሴኔ 10፤ 2013 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ
TECHIN seminar will be back this week, @TECHINhall. For this session Mr. Bekuretsion Tsegaye will discuss Robots, Automation and Smart Systems.
Starting time: 9:30 AM
You are invited to join us tomorrow @TECHINhall
#TECHIN
#weeklyseminar