TechIn2
1.17K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ጉዞ ወደ ቬነስ
******
በስርዓተ ፀሐይ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ቬነስ ስያሜዋን በጥንታውያን የሮም የፍቅርና የውበት አምላክ ከሆነችው እንዳገኘች ይነገራል፡፡ ቬነስ በስርዓተ ፀሐይ ከጨረቃ ቀጥላ ብሩህ የሆነች ፕላኔት እንደሆነች ይነገራል፡፡ ታዲያ የአለማችን ግዙፉ የህዋ ምርምር ተቋን በመጪው 2030 ሁለት ጉዞዎችን ወደ ቬነስ ላማድረግ ማቀዱን ይፋ አድርጓል፡፡ የጉዞውም አላማ ገጸ ቬነስ (ገፀ-ምድር እንደሚባለው) እንዴት በአለታማ ከፈረታዎች እንደተሞላ ለማጥናት ነው፡፡
መልክዓ ቬነስ በቀላጭ ሊድ የተሞላ ሲሆን እነዚህ በናሳ ሊደረጉ የታሰቡ ጉዎች የቬነስ ቅልጥ ሊድ ምንጩ ምን እንደሆነና ተያያዥ ጥናቶችን ለማድረግ ያለመ ነው፡፡ ይህ ጥናትም ለ30 ዓመታት ያክል ምንም አይነት ጥናትም ሆነ ጉዞ ስላልተደረገባት ብሩኋ ፕላኔት ለተመራማሪዎች ትልቅ የምርምር እድል የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡ ተልእኮው በናሳ የ500 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በጀት የተያዘለት ሲሆን ጉዞውም ከ2028 እስከ 2030 ባሉት ጊዜያት እንደሚደረግ ተነግሯል፡፡
በቬነስም DAVINCI+ የተባለ በቬነስ ከባቢ አየር ውስጥ የሚገኝን የኖብል ጋዝ፣ ኬሚስትሪ እና ምሰላ በተመለከተ እንዲሁም ከፍተኛ መጠን ያለውን የቬነስ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ክምችት እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ ለማጥናት ያለመ ስራ ለመስራትም ታስቧል፡፡
በአጠቃላይ በተልእኮዎቹ በቬነስ ውስጥ ያሉ የተለያዩ የጋዝ ክምችቶችን፣ አሀን ላይ ለሚስተዋለው የግሪን ሀውስ ጋዝ ክምችን መንስኤውን፣ ከእስካሁኑ የተሸለ የቬነስን ምስል እንዲሁም በፕላኔቷውስጥ ከዚህ በፊት ውቅያኖስ ወይም የውሃ አካል መኖርና አለመኖሩን ለመመርመር የታለመ እንደሆነ ከመረጃ ምንጫችን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ምንጭ sciencealert
ተጨማሪ ንባብ https://www.sciencealert.com/we-re-going-back-to-venus-nasa-announces-two-new-missions-by-2030?utm_term=Autofeed&utm_medium=Social&utm_source=Facebook&fbclid=IwAR2VzcuJrFB9g83WtyIoLX653tCpcYyvXCtEiESuZF7WVxp_BRhzLKag-DU#Echobox=1622695106
የአለማችን የመጀመሪያው ከመሬት ጋር ያልተገናኘው ሰማይ ጠቀስ ህንጻ
በወትሮው ልማድ ጠራነው እንጂ ለነገሩ መባል ያለበት ምድር ጠቀስ ህንጻ ነበር መባል የነበረበት፡፡ እስካሁን የአየር ላይ ጓሮ በቻይና፣ ተንሳፋፊ ከተማ በፓስፊክ ተሰርተው አይተን አድንቀናል፡፡ ይህ የስነ-ህንጻ ጥበብ አሁን ደግሞ ከፍ ወዳለ ደረጃ ደርሷል፡፡ መቀመጫቸውን በኒዮርክ ያደረጉ የስነ ህንጻ ጠበብቶች ከአስትሮይድ ላይ ተንጠልጥሎ ቁልቁን ወደ ምድር 50 ሺህ ኪሎሜትር ያክል የሚርቅ ምድር ጠቀስ ህንፃን ለመገንባት ዲዛይን አቅርበዋል፡፡
ይህ ክላውድስ አርኪቴክቸር በተሰኘው ኩባንያ ዲዛይን የተደረገው ህንጻ በአለማችን ረጅሙ ከመሆኑ በተጨማሪ ብቸኛው መሰረቱ ከላይ የሆነ የተንጠለጠለ ህንጻም ነው፡፡ ኩባንያው ከዚህ በፊት የማርስ ላይ የበረዶ ቤቶችን ዲዛይን ሰርቶ ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡ እንደ ኩባንያው መረጃ ከሆነ ዩኒቨርሳል ኦርቢታል ሰስፔንስ ሲስተም ሲሉ በጠሩት ዘዴ (UOSS) አማካኝነት ህንጻውን ለማንጠልጠል አስበዋል፡፡
የህንጻው ዲዛይን እቅድ እንደሚያሳየው ከሆነ ህንጻው ግዙፍ ብቻ ሳይሆን በብዙ የተከፋፈሉ ግን የተቀጣጠሉ ሰፋፊ ከተሞችም እንደሚወጣው ታውቋል፡፡ የኦርቢታዊ ጉዞው በ24 ሰዓታት የየማያቋርጥ እንቅስቃሴ የሚያልፍ ሲሆን ሰሜንና ደቡብ ንፍቀ ክበብን በመከተል እንደ ሃቫና፣ ፓናማ እና ኒዮርክ አይነት ግዙፋን ከተሞችን ቁልቁል እየተመለከተ ይንቀሳቀሳል፡፡
ለሀይል አቅርቦትም የፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፎችን የሚጠቀም ሲሆን ለውሀ አቅርቦትም የዝናብ ውሃን መሰብሰብ በሚያስችል መልኩ እንደሚገነባ ተሰምቷል፡፡ መጠሪያው አናሌማ ታወር የተሰኘው ይህ ልዩ ኪነ- ህንጻ ብዙ መልስe የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች ቢኖሩበትም የአለማችንን ብዙ ሪከርዶች የሚሰብር ልዩ ህንጻ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ምንጭ iflscience.
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/technology/worlds-first-skyscraper-designed-to-hang-suspended-from-an-asteroid/?fbclid=IwAR3w4RPf05sDmoG4xEZnUOQpGvA5E-ejIMrskM7ILXHt-kxWCGw-sO_DH2o
ሁዋዌይ በ2.1 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የአይሲቲ ማዕከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስገነባ
==========================
ግዙፉ የቻይና ቴክኖሎጂ ኩባንያ ሁዋዌይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን የአይሲቲ ልምምድ ማዕከልን በዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የፋርማሲ ካምፓስ ውስጥ አስገንብቶ አስመርቋል፡፡ ተማሪዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች የተግባር ልምድ እንዲያገኙበት ታልሞ የተገነባው ማዕከሉ በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ ከ2000 በላይ ተማሪና መምህራን መሀንዲሶችን በማሰልጠን የተሰጥዖ ስነ-ምህዳሩ እንዲያብብ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡ በነዚህ ሦስት ዓመታት ውስጥ ታድያ የዕውቀት ሽግግር ከተደረገ በኋላ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማዕከሉ መቶ በመቶ ባለቤት እንደሚሆን ሸጋ ዘግቦታል፡፡
አዲሱ ማዕከል የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ሙሉ ነጋ፣ የሁዋዌይ ሰሜን አፍሪካ ምክትል ዋና ፕሬዘዳንት ፊሊፔ ዋንግ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ፕ/ር ጣሰው በተገኙበት ተመርቆ ተከፍቷል፡፡ በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይም ሁዋዌይ ለ10 ተማሪዎች ድህረ ምረቃ ትምህርት ዕድል ይውል ዘንድ የ30 ሺህ ዶላር ድጋፍ ለዩኒቨርሲቲው አበርክቷል፡፡
በፋርማሲ ካምፓሱ ውስጥ ለትምህርት እንዲውል ዘመናዊ የቴሌኮም መሳርያዎች የስራው አካል ሆኖ የተገጠመ ሲሆን 1.9 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የቁሳቁስ፣ ስልጠና የተግባር ማሳያዎች ለአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራን የሚሰጥም ይሆናል፡፡
በዓለማችን ቀዳሚ የቴሌኮም ግብዓት አቅራቢ የሆነው ሁዋዌይ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪና ባለሙያዎችን የአይሲቲ አቅም የሚገነቡ ተግባራትን ሲከውን ቆይቷል፡፡ አሁን ላይ ከ36 የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከስራ ፈጠራ ኮሚሽን ጋር በትምህርትና ተሰጥዖን ማብቃት ላይ በትብብር እየሰራ ይገኛል፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን የውድድር መርሀ ግብሮችን በማዘጋጀት ታዳጊዎችን የማብቃት ስራ እየሰራ ሲሆን በቅርቡም አንድ ሺህ ያህል ተማሪዎችን እንደሚያሳትፍ የሚጠበቀው 6ኛው የሁዋዌይ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ውድድን እዚሁ ኢትዮጵያ የሚያዘጋጅ ይሆናል፤ ለውድድሩ የመመዝገቢያ ሊንክ (https://e.huawei.com/en/talent/#/ict-academy/ict-competition/regional-competition?zoneCode=&zoneId=98269503&compId=85131961&divisionName=Huawei%20ICT%20Competition%20Ethiopia%202021)፡፡
ምንጭ፤ Shega
ለተጨማሪ፤ https://shega.co/post/huawei-launches-a-2-1m-ict-practice-center-in-addis-abeba-university/
አፈትልከው የወጡት የአሜሪካን ምስጢራዊ ኒውክለር ጦር መሳርያ መረጃዎች
===============================
በአውሮፓ ምድር የአሜሪካን ኒውክለር ጦር መሳርያዎች ተከማችተው በሚገኙባቸው ጦር ሰፈሮች ውስጥ የሚያገለግሉ የአሜሪካን ወታደሮች ረጅምና ውስብስብ የሆኑትን የኒውክለር ኮዶችን ለማስታወስ ይረዳቸው ዘንድ ለህዝብ ክፍት በሆኑ የፍላሽካርድ መተግበሪያዎች ላይ እንደሚያስቀምጧቸው ቤሊንግካት የተሰኘው በድረ-ገፆች ላይ የምርመራ ጋዜጠኝነት ስራን የሚሰራ ገፅ አስታወቀ፡፡ ወታደሮቹ በድረ ገፆቹ ላይ ለማስታወስ አስቀምጠዋቸው ከተገኙት ምስጢራዊ መረጃዎች መካከል ኮዶች፣ ስውር መግባብያ ቃላት እንዲሁም የኒውክለር ማከማቻዎቹን መገኛ ይፋ የሚያደርጉት ይገኙበታል፡፡
ከዚህ ቀደም የአውሮፓ መንግስታት የአሜሪካን ኒውክለር ጦር መሳርያዎች በሀገራቸው መኖራቸውን ወይም አለመኖራቸውን ለመናገር ፈቃደኛ ሳይሆኑና ሲያስተባብሉ ቢቆዩም አፈትልከው የሚወጡ ሰነድ፣ ፎቶዎችና ጡረታ የወጡ ኃላፊዎች አስተያየቶች መሳርያዎቹ እዚያ ስለመኖራቸው በተደጋጋሚ ጥቁምታን ሲሰጡ ነበር፡፡ ሆኖም አዲስ የወጣው ምስጢራዊ መረጃ ከዚህም አንድ ደረጃ ተሸግሮ በጦር ሰፈሮቹ ውስጥ ያሉት የኒውክለር መሳርያዎች ብዛት፣ የቱ የቱ ጋር እንዳሉ እንዲሁም መሳርያዎቹ የተከማቹበት ክፍል ሙቅ አልያም ቀዝቃዛ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
ምስጢራዊ መረጃውን መርምሮ ዘገባውን የፃፈው ፎካ ፖስትማ እንደሚለው አጥኚዎቹ የወታደሮቹን ፍላሽካርድ ማግኘት የቻሉት ከኒውክለር የጦር ሰፈር ጋር ሊገናኙ የሚችሉ አንዳንድ ነሮችን አስገብተው በይነ-መረብ ላይ በማፈላለግ (ሰርች በማድረግ) ነው፡፡ በዚህም ጀርመን፣ ኔዘርላንድ እና ቱርክን ጨምሮ በመላው አውሮፓ የሚገኙትን የጦር ሰፈሮችን መረጃ የያዙ ፍላሽካርዶችን ማግኘት ችለዋል፡፡ አጥኚዎቹ ካገኟቸው 70 ፍላሽካርዶች መካከል "Study!" በሚል ርዕስ የተቀመጠው አንደኛው ካርድ በኔዘርላንዱ የፎልኮል አየር ኃይል ሰፈር ውስጥ ዝግጁ ሆነውና ሳይሆኑ በማከማቻዎች ውስጥ የተቀመጡትን የኒውክለር ጦር መሳርያዎችን ብዛት ያሳየ ሆኗል፡፡ ይህ ታድያ በኔዘርላንድ መንግስት ዘንድ በሚስጥርነት ተይዞ የቆየ መረጃ ነው፡፡ ሌሎች ያፈተለኩት መረጃዎችም ወታደሮቹ ምን ሲፈጠር እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው፣ የደህንነት ካሜራዎቹ የት የት ቦታ ላይ እንደሚገኙ እንዲሁም አንድ አደጋ ሲፈጠር ወታደሮቹ በምን አየይነት ስውር መግባብያ ቃላት እንደሚነጋገሩ ያመላክታሉ፡፡
ቤሊንግካት ያገኛቸው መረጃዎች እድሜያቸው ከአውሮፓውያኑ 2013 እስከ ያዝነው ዓመት ሚያዝያ 2021 ድረስ የዘለቁ ናቸው፡፡ ገፁ ያገኛቸውን ውጤቶች ይፋ ከማድረጉ አስቀድሞ ኔቶ እና የአሜሪካን ጦር ኃይልን አስተያየት የጠየቀ ሲሆን ምስጥራዊ ሰነዶቹን የያዙት ካርዶችም ኋላ ላይ እንዲነሱ ተደርገዋል፡፡
ምንጭ፤ DW
ለተጨማሪ፤ https://www.dw.com/en/us-soldiers-accidentally-leak-nuclear-secrets-via-study-apps-report/a-57710899
ብዙ ሳተላይቶች ከግንኙነት ውጭ እንዳይሆኑ የሚያደርገው ስቴሽን
************************************
ለተለያዩ የምርምር አገልግሎቶች ህዋ ላይ የሚገኙ ሳተላይቶች ከምድር ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዳይቋረጥ የሚያደርገው መቆጣጠሪያ አክቲክ ስቴሽን ይባላል፡፡ ይህ በአለማችን ሰሜናዊ ጫፍ የሚገኝ መቆጣጠሪያ በኖርዌያን ደሴት የሚገኝ ሲሆን በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የሚሰሩ ምርምሮችን በእጅጉ ያግዛል፡፡
በኖርዌይ መለስተኛ ከፍታ ባለው የአርክቲክ ደሴት ላይ የሚገኘው ይህ የሳተላይት መቆጣጠሪያ ዙሪያው 100 በሚሆኑ የ geodesic ሽፋኖች የተለበጠ ነው፡፡ እያንዳንዱ ልባሶች የዲሽ አንቴና ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ እነዚህም በህዋ ላይ ያሉ ሳተላይቶች ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆኑ ያለማቋረጥ የሚሰሩ ናቸው፡፡
አንድ ሳተላይት ወደ ምድር ከመመለሱ በፊት በሶፍትዌር የታገዘ ትእዛዝን በመቀበልና በመላክ መረጃ ከህዋ ወደ ምድር እንዲመጣ ያደረጋል፡፡ በሌላ ስሙ ስቫልሳት (SvalSat) የተሰኘው ይህ የሳተላይት መቆጣጠሪያ ከመጋረጃ ጀርባ እንደሚባለው ለብዙ ጥናትና ምርምሮች ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ነው፡፡ መቆጣጠሪያ ጣቢያው ከሰሜን ዋልታ 800 ማይሎች ርቆ የሚገኝ በመሆኑ የአለማችን ሰሜናዊ ጫፍ ላይ የሚገኝ ብቸኛው መቆጣጠሪያ ነው፡፡
በመቆጣጠሪያው ያሉት 100 አንቴናዎች አንዳንዶቹ 42 ጫማ መጠነ ዙሪያ ያላቸው ሲሆን በየቀኑ 3500 የሚደርሱ የሳተላይት መረጃዎችን ይቆጣጠራሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ለአየር ንብረት ቁጥጥር የሚያግዙ የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች ይገኙበታል፡፡
ምንጭ New York Times
ተጨማሪ ንባብ https://www.nytimes.com/2021/05/31/climate/arctic-station-satellites.html?smtyp=cur&smid=fb-nytscience&fbclid=IwAR1Z3jd7mR4j188HWyurCJPwStpEI69Ad4llAA690VCyM61HqKzoFT03FtM
የዜግነት ሳይንስ
=========
በ18 እና 19ነኛው ክፍለ ዘመን አማተር ወይም መደበኛ ስራቸው ተመራማሪ ያልሆኑ የሳይንስ አፍቃሪያን ለዘመናዊው የሳይንስ እድገት ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በ20 ኛው ክፍለ ዘመን ሳይንስ ተቋማዊ ወይም በሙያው የተካነ ግለሰብ የሚያከናውነው ድርጊት እየሆነ ሲመጣ በግላቸው የሚንቀሳቀሱ ተመራማሪዎች አስቸጋሪ እየሆነባቸው ሄዷል፡፡ በቅርብ ጊዜያት በተለይም ባለፉት ሁለት አስርት አመታት በሳይንስ አቀራረብ ዙሪያ አዲስ መንገድ ተፈልስፏል የዜግነት ሳይንስ፡፡
ይህ የሳይንስ አቀራረብ እጅግ ብዛት ያላቸው መደበኛ ሰዎችን የሚያሳትፍ በመሆኑ በምሁራን ወይም በባለሙያዎች በቀላሉ ሊሰበሰብ የማይችል እጅግ ብዛት ያለው መረጃን በቀላሉ ለማሰባሰብ ያስችላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ከፍተኛ ጥቅም ሊሰጥ የሚችል ምርምርን ለማድረግ በመቶዎች፣ በሺዎች እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ማሳተፍ በ10 እና በ15 ሰዎች በፍፁም ሊሰራ የማይችልን ግዙፍ ምርምር በቀላሉ መከወን ያስችላል፡፡ በትልልቅ የምርምር ስራዎች ላይ ሰፊና ጥልቅ የመረጃ ሃብቶች ጥቅም ላይ ከዋሉ ዘመን ተሻጋሪ ጥናቶች ለማካሄድ እና በሁሉም መልኩ ይዘታቸው የላቀ መርምሮችን ለማካሄድ ያግዛል፡፡
የዜግነት ሳይንስ ሲነሳ በ1900 የተመሰረተውና እስካሁን ድረስ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ንቁ ተሳትፎ የሚደርገው ብሔራዊ የኦዱቦን ማህበር ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ይህ ሳይንስ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚንቀሳቀስ የግለሰቦች ስብስብ ከ121 ዓመት በፊት በ27 ሰዎች የጀመረው የወፍ ዝርያዎችን የመለየትና የመቁጠር ስራ አሁን ላይ በዓለም ዙሪያ 30 ሺ በላይ ሰዎችን በማሳተፍ በየዓመቱ 2,400 የወፍ ዝርያዎችን የመለየት እና 70 ሚሊዮን ወፎችን የመቁጠር አቅም ላይ ደርሷል፡፡ ይህ እንደቀላል የተጀመረ የሰዎች እንቅስቃሴ አሁን ላይ ለበዙ የምርምር ተቋማት እና የእንስሳት አጥኝዎች ሰፊ መረጃ እና ምልከታ የሚሰጥ ሆነ ይገኛል፡፡
የዜግነት ሳይንስን የሚያካሂድ ማህበረሰብ በጊዜ፣ በጂኦግራፊ ወይም በሃብት እጥረቶች ምክንያት ለማግኘት አስቸጋሪ የሚሆነውን ሰፊ መረጃ የመሰብሰብ አቅምን በማጎልበት የምርምር ስራን ከማሳደጉም ባለፈ በዜጎች እና በተመራማሪዎች መካከል ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ግዙፍ ችግሮችን በቀላሉ ለምፍታት ትልቅ በር ይከፍታል፡፡ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ግኝቶችን በቀላሉ የሚረዳና ለለውጥ የተዘጋጀ ማህበረሰብን ለመፍጠር የሚያግዘው የዜግነት ሳይንስ በዘርፉ የሚታዩ ስንኩል አመለካከቶችን ለመቅረፅ እና ግልፅነት የተሞላበት ነፃነት ለመፍጠርም ይረዳል፡፡ አሁን ካለው መረጃን በቀላሉ ለማግኘትና ለማከማቸት ከሚቻልበት የቴክኖሎጂ አቅም ጋር ተያይዞም የዜግነት ሳይንስ ይበልጥ እንደሚዳበር ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡ theconversation
https://theconversation.com/tracking-science-a-way-to...
https://magazines.rivm.nl/.../10-benefits-citizen-science
ቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም፤ ዛሬም እንደተለመደው፡-
===================
• በአብይ ፕሮግራም፤ ባዮ ዲዝልን አስመልክቶ በወንዶ ገነት ግብርና ምርምር ስለተሰራው ጥናት
• የተመራማሪዎች ታሪክ፤ ዶ/ር ፍቃዱ ላይ ያተኮረውን ዝግጅት ክፍል ፪
• ተቋማት፤ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ያስገነባውን የዲጂታል ሜዲካል ላይብረሪ
• እንዲሁም በቴክኖሎጂ ታሪክ፤ ስለ ግዙፍ መረጃ ወይም (Big Data) መሰናዶን ያጠናቀርን ሲሆን ብላቴናትም ሰዓቱን ጠብቆ ይቀርባል፡
እርስዎም ዛሬ 10 ሰዓት ላይ የቻናል ምርጫዎን MOE ቴሌቪዥን ላይ በማድረግ ለእራስዎም ሆነ መላው ቤተሰብዎ የሚሆን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዕውቀትን እንዲሸምቱ ስንጋብዝዎ በደስታ ነው፡፡
በየሳምንቱ ቅዳሜ በ10 ሰዓት እንዲሁም በድጋሚ ማክሰኞ 10 ሰዓት በMOE ቴሌቪዥን ከሚቀርበው በተጨማሪ ወደ ዩትዩብ ቻናላችንም በማቅናት አዳዲስና እስከዛሬ ለተመልካች የደረሱ የቴክ ሳይንስ ፕሮግራሞች አንድም ሳይጎል ማግኘት ይችላሉ (https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg)፡፡
ኒው ዮርክ አቅራብያ ሲዘፍኑ የተገኙት አሳ ነባሪዎች
=======================
ተመራማሪዎች የውሃ ውስጥ መቀረፀ ድምፅ መሳርያዎችን በመጠቀም በተለምዶው የሀምፕባክ ዓሳ ነባሪዎች መራብያ ቦታ ከሆነው የካሪቢያን አካባቢ ርቀው ከበስተ ሰሜን በኒው ዮርክ የባህር ዳርቻዎች አካባቢ ሲያዜሙ የሚያሳይ የመጀመሪያውን ማስረጃ አግኝተዋል፡፡ ምንም እንኳን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሀምፕባክ ዓሳ ነባሪዎችን በአካባቢው መመልከቱ እየተደጋገመ ቢመጣም የእንስሳቱን ድምፅ በማሳየት ረገድ ግን ይህ በማሪን ማማል ሳይንስ ጆርናል ላይ ታትሞ የወጣው ጥናት የመጀመሪያው የተሟላ ጥናት ሆኗል፡፡
ተመራማሪዎቹ ጥናቱን ለማጥናት ከኒው ዮርኳ የሎንግ ደሴት በደቡብ አቅጣጫ 113 ኪ.ሜ ርቆ በሚገኝ የባህር ወለል ላይ በተቀመጡ የውሀ ውስጥ መቀረፀ ድምፆች አማካኝነት የተሰበሰቡና የ6,305 ሰዓታት ርዝማኔ ያላቸው የሀምፕባክ አሳ ነባሪ ድምፆችን በማዳመጥ ተንትነዋል፡፡ ድምፆቹ የተቀዱት ከአስር ዓመታት በፊት በአውሮፓውያኑ 2009 እና 2010 ቢሆንም የሀምፕባክ ዓሳ ነባሪዎችን እንቅስቃሴ ለመመልከት ተብሎ ትንታኔ የተደረባቸው ግን ገና በቅርቡ ነው፡፡
ከዚህ ቀደም የተከናወኑ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት የሀምፕባክ ዓሳ ነባሪዎች የመራብያ ወቅታቸው መድረሱን እንዲያመላክትላቸው ዜማ ያዜማሉ፡፡ ሆኖም ከወንድም ሆነ ሴት ታዳጊ እንዲሁም ህፃናት የሚነሱ አንዳንድ ድምፆች እንስሳቱ በጋራ በሚሰበሰቡባቸው ጊዜያት የተለያዩ ማህበራዊ ሁናቴዎችን ለማመላከት የሚደረጉም ናቸው፡፡ ታድያ እንደ ተመራማሪዎቹ ሆነ እነዚህ ሀምፕባክ ዓሳ ነባሪዎችን ከመራብያ ወቅታቸውም ሆነ መራብያ አካባብያቸው ርቀው ከወደ ሰሜን ሆነው ሲያዜሙ መገኘታቸው ያልተለመደ ክስተት ነው፡፡ ይህም በተለይ በዓለማችን ካሉ በመርከብ ጉዞ እጅጉን ከሚጨናነቁ ስፍራዎች መካከል በሆነው በዚህ አካባቢ ለሚገኙት ዓሳ ነባሪዎች የበለጠ ጥበቃና እንክብካቤን ለማድረግ ዕድሉን እንደሚሰጥ ተነግሮለታል፡፡
ምንጭ፤ Independent
ለተጨማሪ፤ https://www.independent.co.uk/.../new-york-humpback...
በክብደት መጨመር ለተቸገሩ ሰዎች ከFDA አዲስ መድሃኒት
*********************************
የአሜሪካው የምግብና መድሃኒት አስተዳደር የሆነው FDA ለመጀመሪያ ጊዜ ክብደትን ለመቀነስ የሚያስችል መድሃኒትን ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ ሰጠ፡፡ ይህ ከፍኛ ለውጥ ያመጣል የተባለለት መድሃኒት ዌጎቪ የተሰኘ ሲሆን የደኒሽ መድሀኒት ማምረቻ ኩባንያ የሆነው ኖቮ ኖርዲስ ምርት ነው፡፡ ይህም ከ2014 በኋላ በፌዳ እውቅና የተሰጠው ብቸኛው መድሃኒት ሆኗል፡፡
ስማግልቲዩድ የተሰኘ ተመሳሳይ መድሃኒት በአሜሪካ ለዘመናት ጸረ ዲያቤቲክ ህክምና ላይ አገልግሎት እየተጠ የነበረ ቢሆንም ይኸው መድሃኒት ከፍ ባለ መጠን ሲወሰድ ከምግብ ፍላጎት ጋር ለተያያዘ ችግር መፍትሔ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ዌጎቪ ስለ ተሰኘው መድሃኒት የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው 2000 የሚደርሱ ከፍተኛ ውፍረት ያላቸው ሰዎች እንዲወስዱት ተደርጎ ከ15 በመቶ በላይ ክብደታቸውን መቀነስ መቻላቸውን አሳውቋል፡፡
ይህ መድሃኒትም ሰዎች ክብደታቸውን ለመቀነስ የሚያደርጉትን ቀዶ ህክምና በማስቀረት በመድሃኒት ብቻ መፍትሔ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡ ኖቮ ኖርዲስክ እስካሁን የመድሃኒቱን ዋጋ ይፋ ባያደርግም በወር 1300 የአሜሪካን ዶላር ሊያስከፍል ይችላል የሚሉ መረጃዎች እየተሰሙ ናቸው፡፡
ምንጭ sciencealert
ተጨማሪ ንባብ https://www.sciencealert.com/game-changer-treatment-is-first-new-weight-loss-drug-approved-by-the-fda-in-years?utm_medium=Social&utm_source=Facebook&fbclid=IwAR3rc6NU9Rs-xGK706QGwS7DyrOsCX72tBXiuHegad_PM42tiQKRPANycNk#Echobox=1623035219
በዓለማችን የውሃ አካላት የሚገኘው ኦክስጅን እያሽቆለቆለ ነው
=======================
የዓለማችን ሀይቅ እና ውቅያኖሶች በሟሟ ኦክስጅን (O2) የተሞሉ መሆናቸውና የውሀ ውስጥ እንስሳትም ይህን ተጠቅመው እንደሚተነፍሱ ይታወቃል፡፡ ሆኖም በኔቸር ጆርናል ላይ የወጣ አዲስ ጥናት እንደሚያመላክተው የሙቀት መጠኑ እንደየወቅቱ በሚቀያየርባቸው ሀይቆች (temperate lakes) ውስጥ የሚገኘው የኦክስጅን መጠን በፍጥነት እያሽቆለቆለ መሆኑን ነው፡፡
የተመራማሪዎች ቡድኑ በመላው ዓለም ባሉ 393 መሰል ሀይቆች ውስጥ ከአውሮፓውያኑ 1941 እስከ 2017 ያለውን ከ45 ሺህ በላይ የሟሙ ኦክስጅኖች ሁኔታን መርምሯል፡፡ በውጤቱም ከአውሮፓውያኑ 1980 በኋላ ብቻ በገፀ-ምድር የውሀ አካላት ውስጥ የሚገኘው የሟሟ ኦክስጅን በ5.5 በመቶ የወረደ ሲሆን ጠለቅ ባሉ የውሀ አካላት የሚገኘው ደግሞ በ18.6 በመቶ አሽቆልቁሏል፡፡
ከውቅያኖሶች ጋር ሲነፃፀር ሀይቆች ከ2.75 እስከ 9.3 እጥፍ በላቀ ፍጥነት ኦክስጅናቸውን እያጡ ነው ያሉት የጥናቱ ዋና ፀሀፊ ፕ/ር ኬቨን ሮስ ይህ የኦክስጅን ማሽቆልቆልም የባህር ውስጥ እንስሳት ዝርያዎችን ለመመናመን ስነ-ምህዳሩንም ለመዛባት የሚዳርግ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡
ለዚህ የኦክስጅን ማጣት ምክንያት ተደርጎ የተቀመጠው የገፀ-ምድር የውሀ አካላት ሙቀት በ0.38 ዲ.ሴ መጨመሩ ነው፡፡ ውሃ ሙቀት በውስጡ ሲበዛበት መያዝ የሚችለው የኦክስጅን መጠን የሚቀንስ መሆኑ ለዚህ ጥፋት መንስኤ ሆኗል፡፡ ሆኖም ጥልቅ የውሃ አካላት ያላቸው ሙቀት ባለፉት አራት አስርት ዓመታት ውስጥ ብዙም ለውጥን ያስተናገደ አልነበረም፡፡ ታድያ በነዚህ የውሃ አካላት ላይ የታየው የኦክስጅን መጠን መሳሳት በገፀ ምድር ውሃው ገፅ ላይ ያለው ሙቀት እየጨመረ መምጣቱ አነስተኛ እና ከፍተኛ ጥልቀት ባላቸው የውሀ አካላት መካከል ያለውን የእፍጋት መጠን ልዩነት በመጨመር ኦክስጅንን እንዳይቀላቀሉና ወደ ጥልቅ ውሃ መድረስ የሚችለው ኦክስጅንም እያነሰ እንዲመጣ አደርጎታል፡፡ ይህ አይነት የእፍጋት ልዩነት ከከባቢ አየር የሚገኘውን ኦክስጅን በጥልቅ ውሀ አካላት ላይ ማቀላቀልን አስቸጋሪ ስለሚያደርገው በዚያ ያለው የሟሟ ውሃ እንዲቀንስ ማድረጉን ኬቨን ሮስ ይናገራሉ፡፡
ሆኖም ይህ የኦክስጅን መጠን ማሽቆልቆል በሁሉም የዓለማችን ሃይቆች ላይ የሚስተዋል አይደለም፡፡ እንደውም በአንዳንድ አካባቢዎች የሙቀት መጠኑ እየጨመረ ሳለ እንኳን የኦክስጅ መጠኑ ከማሽቆልቆል ይልቅ ሲጨምር ተስተውሏል፡፡ ይህም ምናልባት በንጥረ ነገሮች ብክለት ሳብያ የመጣ ኦክስጅን አምራች ባክቴሪያ የሆኑት ሳያኖባክቴሪያዎች እንዲያብቡ ከማድረግ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል በተመራማሪዎቹ ተነግሯል፡፡
የዚህ ጥናት ውጤት በዓለማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ለመጣው የዓለም ሙቀት መጨመር አንድ ማሳያ ሆኖ ቀርቧል፡፡
ምንጭ፤ Cosmos
ለተጨማሪ፤ https://cosmosmagazine.com/earth/water/oxygen-declining-in-the-worlds-lakes/?utm_content=buffere3bdf&utm_medium=social&utm_source=twitter.com&utm_campaign=buffer