TechIn2
1.17K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የኢንክሪፕሽን መሰረታዊ ጥቅሞች ምንድን ናቸው
========================
መረጃዎችን ያለምንም ስጋት ከሰርጎ ገቦች ወይም ፍቃድ ከሌላቸው ሰዎች በመጠበቅ በድብቅ ማስቀመጥም ሆነ መላላክ እጅግ በጣም ወሳኝ ነው። ከቅርብ አመታት ወዲህ ኢንክሪፕሽን በብዛት አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ወንጀለኞችን ለመከላከል፣ የሰዎችን መብት ለማስጠበቅ ፋይሎችን፣ ዶክመንቶችን፣ መልዕክቶችን ለመላክና ለመጋራት፣ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚካሄድ ማንኛውንም አይነት የምስልም ሆነ የቪዲዮ ልውውጥ ያለምንም ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ለማስተላለፍ፣ ዲጂታል ሚዲያዎችን በመጠቀም ሙዚቃዎችንና ቪዲዮችን በህገ ወጥ መንገድ እንዳይለወጡ፣ ክፍያ ሳይፈፀም እንዳይቀዱ ወይም ክፍያም ከተፈፀመ በኋላ ለሌላ ሶስተኛ ወገን እንዳይባዙ ለማድረግ ብሎም እንዳይነበቡ በማድረግ ለባለቤቶችና ለባለመብቶች ከፍተኛ የሆነ አገልግሎት ይሰጣል።
በዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ዘመን የግብይት ስርዓትን በኤሌክትሮኒክስ አማካኝነት መጠቀም ተችሏል። በተለይ ደግሞ የባንኪንግ አገልግሎቶች መጀመራቸው እና ዲጂታል የክፍያ ሥርዓት መዘረጋቱ ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም ብዙ የስርቆት ወንጀሎች ይፈፀማሉ። ይህንን የስርቆት ድርጊት ለመከላከል ደግሞ የኢንክሪፕሽን ወይም ክሪፕቶግራፊ ቴክኖሎጂ በጣም አስፈላጊ ነው። ማንኛውም አይነት የግብይት ስርዓት በሚፈፀምበት ወቅት መልዕክቶች የሚላኩበት ዘዴ ሚስጥራዊ እንዲሆን ከማስፈለጉ አንጻር ማንኛውም የኢንክሪፕሽን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እንዲውል ያስፈልጋል።
ኢንክሪፕሽን ከሚሰጣቸው መሰረታዊ ጠቀሜታዎች መካካል
የመረጃዎችን አስተማማኝነት ለማረጋገጥ - ይህም ማለት በመልዕክት የሚላኩ መረጃዎች የሚያገኙት ፍቃዱን ያገኙ አካላት ብቻ መሆናቸው እና ማን የላከው መልዕክት መሆኑን ለማወቅ የሚረዳ ነው።
የመረጃዎችን ተአማኒነት ለማረጋገጥ - መልዕክት ተቀባዩ የደረሰው መልዕክት ምንም ሳይነካ ወይም ማስተካከያ ሳይደረግበት መድረሱን ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው።
የመረጃዎችን ባለቤትነት ለማረጋገጥ - ላኪው የላከውን መልዕክት መካድ እንዳይችል ለማድረግ እና ክህደትን ወይም ከላኪው በኩል የሚታይ እምቢተኝነትን ለማስቀረት ያግዛል።
https://www.genetec.com/.../what-is-encryption-and-how....
ሰዎችን ለኢንተርኔት ጥቃት (ሀክ) እየዳረገ ያለው የመተጫጫ መተግበሪያ
*****************************
በጃፓን የመተጫጫ መተግበሪያን በመጠቀም ውሃ አጣጫቸውን የሚፈልጉ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች ለኢንተርኔት መረብ ጥቃት መጋለጣቸው ተሰምቷል፡፡ በጃፓን የተለያዩ የመተጫጫ መተግበሪያዎች (dating app) ሲኖሩ በእነዚህ መተግበሪያዎች የሚጠቀሙ ከሚሊዮን በላይ የሆኑ ሰዎች የግል መረጃ በኢንተርኒት ጥቃት ፈጻሚዎች እንደተሰረቀ ወይም እንደታወቀ መተግበሪያዎችን የሚቆጣጠሩ አካላት ይፋ አድርገዋል፡፡
ኦሚአይ የተሰኘው መተግበሪያ ተጋሪ የሆነው ኔት ማርኬቲንግ በመተግበሪያው ላይ ፈቃድ ያልተሰጣቸው ሰዎች ካለፈው ሚያዚያ ወር ጀምሮ የተጠቃሚዎችን መረጃ እየበረበሩ ነው ብሏል፡፡ በሀከሮቹ ትኩረት ከተደረገባቸው መረጃዎች መካከል ለእድሜ ማመሳከሪያነት የተጫኑ የመንጃ ፈቃድ ፎቶዎችና ፓስፖርቶች ይገኙበታል፡፡
እስካሁን ከ1.7 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች የተጠቁ ሲሆን አንዳንዶቹ አሁን ላይ መተግበሪያውን እየተጠቀሙት እንዳልሆነ ተገልጧል፡፡ ኦሚአይ የተሰኘው መተግበሪያ በጃፓን እጮኛቸውን በቁምነገር የሚፈልጉ ብዛት ያላቸው ሰዎች ከሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች ውስጥ ዋነኛው ሲሆን እስካሁንም 6.89 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች አሉት፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/.../2021-05-million-affected-hack...
ስለ ኤሎን መስክ የ1952ቱ ትንቢት
********************
በ1952 የተጻፈ አንድ መጽሐፍ ኤሎን አንድ ቀን በማርስ ላይ እንደሚገኝ ተንብዮ እንደነበር መረጃዎች ይፋ ተደረጉ፡፡ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ለጀርመኑ ናዚ የሮኬት ቴክኖሎጂ ተመራማሪ የነበረው ዋርንሄር ቮን ብራውን በጻፈው መጽሐፍ አንድ ቀን ኤሎን የሚባል ብዙዎችን ወደማርስ መርቶ እንደሚወስድ ተንብዮ ነበር፡፡ ይህ ሰው የመጀመሪያው የአለም ጦርነት ከመጀመሩ ከጥቂት ጊዜያት በፊት በጀርመን የተወለደ ነው፡፡
ሰውየው በህዋ በረራ ላይ እጅግ ተማርኮ የነበረ ሲሆን በመጨረሻም በ1932 በፈሳሽ ነዳጅ የሚሰራ ሮኬትን ለጀርመን ጦር ሰርቶ አስረክቧል፡፡ ስራውን የቀጠለው ቮን በራውን በጀርመኑ ናዚ ስር ሆኖ ከጓደኞቹ ጋር ምርምር በማድረግ V-2 የተሰኘ ሮኬትን መፍጠር ችሏል፡፡ ይሁን እንጂ ጦርነቱ ከማለቁ በፊት እጁን ለአሜሪካው ጦር ሰጥቶ ስለነበር በምርኮ ወደ ናሳ ሊመጣ ችሏል፡፡
ሰውየው ከቆይታዎች በኋላ የናሳው የማርስ ሼል በረራ ማእከል ዳይሬክተር መሆን ችሏል፡፡ በዚህም ሰዎችን ወደ ጨረቃ በሚወስዱ ሮኬቶች ዙሪያ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በህዋ ምርምር ዙሪያ በወቅቱ እንደሱ ከፍተኛ ፍላጎትና ጥረት ያለው ሰው እንዳልነበረ የሚነገርለት ብራውን በ1952 ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ የማርስ ፕሮጀክት በሚል ርዕስ መጻፍ ችሏል፡፡ በመጽሐፉም በ1965 ወደማርስ 70 ያክል ሰዎችን መጓጓዝ እንደሚቻል ጽፎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እንዳሰበው አልሆነም፡፡
በሚያስደንቅ ሁኔታ የብዙዎችን ትኩረት የሳበው በመጽሐፉ ሁለተኛ ግማሽ ላይ የተካተተው ሀሳብ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ላይ ኤሎን ወደማርስ የሚያደረገውን እንቅስቃሴ እንደሚመራ የሚናገር አረፍተ ነገር ተካትቷል፡፡ በዚህ ክፍል ላይ ኤሎን የሚለው የአንድ ሰው ስም ሆኖ ሳይሆን የተገለጸው ሰዎችን ወደ ማርስ መውሰድ ሲቻል ወደዚያ የሔዱ ሰዎች የስራቸው ወይም የግዛታቸው መሪ የሚሆነውን የሚገልፅ ቃል ነው፡፡ መጽሐፉም የማርስ መንግስት በ10 ሰዎች የሚመራ እንደሆነና በአለም አቀፍ ደረጃ ተመርጦ ለአምስት አመት የሚያስተዳድርና ስሙም ኤሎን ይባላል ሲል አስነብቧል፡፡
ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/space/a-book-from-1952-predicted-an-elon-would-one-day-rule-over-mars/?fbclid=IwAR3Bvlg5TSdrvNKtXLw2VytvvpFb9-wDAZHJ_rJSR9LXgqNZfQJJ6CoQ2qY
Ethio Locate አዲሱ የጉዞ መመሪያ ፕላትፎርም
========================
ለአገር ውስጥ እና ለዓለም አቀፍ የቢዝነስ እንቅስቃሴዎች ዲጂታል መፍትሄዎችንና አሰራሮችን በማቅረብ የሚሰራው ዋይ-ቴክ (Y-Tech) የተሰኘው አገር በቀል የቴክኖሎጂ ድርጅት Ethio Locate የተባለ አዲስ የጉዞ መመሪያ ፕላትፎርም ማቅረቡን ይፋ አድርጓል፡፡ ኢትዮ ሎኬቴ በቀላል ሂደት ተጠቃሚዎች ቦታዎችን እና መረጃዎችን በኢትዮጵያ ውስጥ በነፃ እንዲያገኙ የሚያግዝ የጉዞ መመሪያ ፕላትፎርም ሲሆን፤ ማንኛውም የንግድ ድርጅቶች እና ተቋማት አገልግሎታቸውን ወይም ምርቶቻቸውን በኦንላይን እንዲያስተዋውቁ እና ዲጂታል ፕሮፋይል እንዲኖራቸውም የሚያስችል ነው፡፡
ኢትዮ ሎኬቴ በአሁኑ ወቅት በአንድሮይድ ስልኮች እና በፕለይ ስቶር መተገበሪያዎች ላይ የሚገኝ ቢሆንም ለአንድ አመት በዌብሳት ፕላተፎርም ግልጋሎት ሲሰጥ የቆየ እና በዚህ ቆይታውም ከተጠቃሚዎች ጥሩ ምላሽ ማግኘቱ ተገልጿል፡፡ በዚህ የጉዞ መመሪያ ፕላትፎርም ተጠቃሚዎች የሆቴሎችን፣ ሙዚየሞችን፣ ፓርኮችን እና በመላ አገሪቱ ያሉ የተለያዩ ቦታዎችን አጠቃላይ አድራሻ በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡
የኢትዮ ሎኬቴ የቡደን አባላት ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ሲጓዙ መረጃዎችንና ቦታዎችን ለማግኘት ያጋጠማቸውን የግል ፈተናዎች መሠረት በማድረግ ፕላትፎርሙን ለመስራት መነሳሳታቸውን የሚያስረዳው የኢትዮ ሎኬቴ ዋና ሥራ አስፈፃሚና መስራች አቶ ይሳቅ አምደሥላሴ ኢትዮ ሎኬቴ አገልግሎት አቅራቢዎች እና ደንበኞቹ የሚፈልጉትን የተደራጀ እና የተጣራ የዲጂታል መረጃ በአንድ ቦታ ለማግኘት የሚስችል ፕላትፎርም መሆኑን ይናገራል፡፡ ይህ የመረጃ እጥረት ከተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ለሚመጡ ቱሪስቶችም ትልቅ ችግር በመሆኑ የአገልግሎት አቅራቢዎች የተሻሻለ መረጃቸውንና አድራሻቸውን በቀላሉ በዲጂታል መንገድ ማቅረብ እንዲችሉ ይህ ፕላትፎርም ትልቅ እድል እንደሚፈጥርም አቶ ይሳቅ ተናግሯል፡፡
በፕላትፎርሙ አማካኝነት የሀገራችንን የቱሪስት መስህቦች፣ መዳረሻዎች እና የታላቋን ሀገራችንን ታሪክ በተፃፈና በተደራጀ ይዘት ማስተዋወቅ እንፈልጋለን የሚለው አቶ ይሳቅ ይህን ለማሳካትም በኢትዮ ሎኬቴ ዙሪያ ሰፋፊ እቅዶች ይዘን በመስራት ላይ እንገኛለን ብሏል፡፡
መተግበሪያውን በተከታዩ የጎግል ፕለይ ሊንክ ማውረድ ይቻላል
https://play.google.com/store/apps/details...
ምንጭ፡ https://www.techinafrica.com/ethiopia-tech-startup-launches-travel-guide-application/
ከፊል እይታን መመለስ የቻለው ኦፕቶጀኔቲክስ ቴክኖሎጂ**********************************
ሁለቱም አይኖቹ ማየት ተስኗቸው የነበሩ አንድ ሰው ኦፕቶጀኔቲክስን በሚጠቀም ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ህክምና አማካኝነት ከፊል ብርሃን ማግኘቱ ተሰማ፡፡ ህክምናው የነርቭ ዘረመሎችን ለብርሃን መልስ እንዲሰጡ በሚያስችል መልኩ የተካሄደ እንደሆነ የመረጃ ምንጫችን ዘግቧል፡፡
ኦፕቶጀኔቲክስ በአሁኑ ወቅት በብዛት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ ቴክኖሎጂ ሲሆን የጭንቅላት ህዋሳትን በትክክል መቆጣጠር የሚያስችልና ህዋሳቱም ለብርሃን መልስ እንዲሰጡ የሚያደርግ ነው፡፡ በእንስሳት ላይ ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ የተለያዩ ግኝቶችን ማሳወቅ የቻለ ሲሆን ባለው የሳይንስ እውቀት ክፍተት ምክንያት በሰዎች ላይ ለመሞከር ብዙ እንቅፋቶች አሉበት፡፡ ለምሳሌ በጭንቅላት ውስጥ ብርሃንን ለማብራት ብርሃን አስተላላፊ ገመዶችን በጭንቅላት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ደግሞ ለጊዜው የማይደፈር ነው፡፡
ብዙዎች የአይን ብርሃን ማጣትን ለመከላከል ወይም ለማከም እንዲውል የተለያዩ ጥረቶችን እያደረጉ ሲሆን እስካሁን በዚህ ዘዴ የአይን ብርሃኑ የተመለሰለት አንድ ፈረንሳዊ የ58 ዓመት ጎልማሳ ነው፡፡ ይህም ሰው በመንገድ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ምስል በነጭና ጥቁር ቀለማት ማየት መቻሉ ተነግሯል፡፡ ይህም እንዲሆን ታካሚው የሚያደርገው ለምስል መከሰት የተለያዩ እገዛዎችን የሚያደርግ መነጸር መልበስ ይኖርበታል፡፡
ምንጭ newscientist
ተጨማሪ ንባብ https://www.newscientist.com/article/2278405-partial-sight-restored-for-man-who-is-blind-thanks-to-optogenetics/?utm_medium=social&utm_campaign=echobox&utm_source=Facebook&fbclid=IwAR2sHL1KWnO7M8MMQGIf5_auP91iwfaQwWrh7nKqtAs5EEcUoIPEK-wjPuU#Echobox=1621874379-1
ለትምህርት ቤቶች “ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ” የተሰኘ መተግበሪያ
******************************
ለትምህርት ቤት አስተዳደር ሠራተኞች እና ለመምህራን የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን መከላከል እና ለቁጥጥር ሥራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት “ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ” መተግበሪያ ይፋ ሆነ።
የግንዛቤ ማስጨበጫ መተግበሪያው ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ርእሰ ጉዳዮችን ማካተቱ ተገልጿል።
የኮሮና ቫይረስ መተግበሪያው በጤና እና ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ የተዘጋጀውን የኮሮና ቫይረስ መከላከል መመሪያን መሠረት ያደረገ ነውም ተብሏል፡፡
መተግበሪያው የበሽታ ቅኝት፣ የተግባቦት እና የማኅበረሰብ ተሳትፎ ሥራዎችን እንዲሁም በሁሉም ደረጃ ስላለው ኃላፊነቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
በመጨረሻም “ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ” መተግበሪያን ሁሉም መምህራን እና የትምህርት ቤት አስተዳደር ሠራተኞች በስልካቸው በመጫን ስልጠናውን እንዲወስዱ እና ለኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ቁጥጥር ሥራ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ምንጭ ጤና ሚኒስቴር
https://www.facebook.com/EthiopiaFMoH/posts/1823445957826199
ኬኒያዊቷ ዶክተር የአለም ጤና ድርጅት አዋርድን አሸነፈች
----------------------------------------
የ28 አመቷ ዶ/ር ጀሚማህ ካሪዩኪ በኩቪድ -19 እገዳ ወቅት ነፍሰ ጡር እናቶች የወሊድ እንክብካቤ እንዲያገኙ በማስቻል ዓለም አቀፍ ጤናን ለማሳደግ ላበረከተችው ትልቅ አስተዋፅዖ የአለም ጤና ድርጅት እውቅና ሰቷታል፡፡ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ለአለም ጤና መጠበቅ ትልቅ አበርክቶት ነበራቸው በሚል በየዓመቱ እውቅና እና ሽልማት የሚሰጥ ሲሆን በዚህኛው የ 2021 ዓመትም ወጣቷ ኬኒያዊት ዶክተር አሸናፊ መሆን ችላለች፡፡
ዶ/ር ካሪዩኪ በአለም ጤና ድርጅት አሸናፊ መሆኗ ከተረጋገጠ በኋላ በቲውተር ገፅዋ ባስተላለፈችው መልክት ይህ ሽልማት በማህበረሰቡ ውስጥ ላሉ ወጣቶች ማድረግ አንደሚችሉ እና የአለም ማህበረሰብ ለሁሉም ነፍሰ ጡር እናቶች ግድ እንደሚለው ያመላከተ ነው ብላለች፡፡ ዶ/ር ካሪዩኪ ኮቪድ ባስከተለው ቀውስ ምክንያት በተለያዩ ጤና ጣቢያዎች አስፈላጊውን የቅድመ ወሊድ እንክብካቤ ያላገኙ ነፍሰ ጡር እናቶች ተገቢውን እገዛ እንዲገኙ በማለም የተለያዩ ፕሮግራሞችን በማቅረብ ተሳታፊ ሆናለች፡፡ በተለይም በኮቪድ -19 እገዳ ወቅት በቲውተር ገፅዋ እንዳስታወቀቸው ነፍሰ ጡር እናቶች የወሊድ እንክብካቤ እንዲያገኙ የበኩሌን አስተዋፅዖ እወጣለሁ በሚል ነጻ የአሙቡላንስ አገልግሎት ለነፍሰ ጡር እናቶች እንዲሰጥ እና በዚህም ከ1ሺ በላይ እናቶችና ህጻነት ተገቢውን ክትትል እንዲያገኙ ትልቅ አስተዋፅዖ አበርክታለች፡፡
ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ በጆንስ ሆፕኪንስ የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው ወረርሽኙ በፈጠረው የጤና ስርዓት መቃወስ ብቻ 1.1 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ 56,700 የሚደርስ የእናቶች ሞት ደግሞ በዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ሊመዘገብ ችሏል፡፡
https://nation.africa/.../kenyan-doctor-wins-who-director...
በሀገራችን የቴሌኮም ፈቃድን በማግኘት የመጀመሪያው የግል ተቋም ስለሆነው ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ጥቂት እንበልዎ
======================
ከወራት በፊት ባለስልጣኑ የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት ጨረታ ማውጣቱን ተከትሎ የደቡብ አፍሪካው ኤምቲኤን እና ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ወደ ጨረታው መግባታቸው ይታወሳል፡፡ ታድያ ባሳለፍነው ቅዳሜ የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን ባለስልጣን በሀገራችን የቴሌኮም ኢንዱስትሪ ውስጥ ከኢትዮ ቴሌኮም በመቀጠል ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ እንዲሆን የሚያስችለውን ፈቃድ ለግሎባል ፓርትነሺፕ ፎር ኢትዮጵያ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
ፈቃድ የማግኘት ውድድሩን በአሸናፊነት የተወጣው ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ለኮምዩኒኬሽን ባለስልጣኑ 850 ሚሊዮን ዶላር የፈቃድ ክፍያን የሚፈፅም ሲሆን የ8.5 ቢሊዮን ዶላር መዋለ ነዋይ ፈሰስ ለማድረግም ቃል ገብቷል፡፡
ግሎባል ፓርትነሺፕ ፎር ኢትዮጵያ አምስት ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ፣ ቴሌኮም እና ፋይናንስ ተቋማትን ያቀፈ ጥምረት ነው፡፡ ከነዚህ ኩባንያዎች መካከል የእንግሊዙ ዓለም አቀፍ የቴሌኮምዩኒኬሽን ኩባንያ ቮዳፎን ሲገኝበት በዚህ ተቋም አብዛኛው የአክሲዮን ድርሻው የተያዘው የደቡብ አፍሪካው ቮዳኮምም የጥምረቱን 6.2 በመቶ ድርሻ ይዟል፡፡ በአንፃሩ የኬኒያው ግዙፍ የቴሌኮምዩኒኬሽን ኩባንያ ቀድሞ የጥምረቱ ዋና ባለቤት ሆኖ የ51 በመቶ ድርሻን እንደሚይዝ ተነግሮ የነበረ ሲሆን ኋላ ላይ ድርጅቱ ድርሻውን በበለጠ ወደ 56 በመቶ አሸጋግሮታል፡፡
በማዕድን ማውጣት፣ መሰረተ ልማት ግንባታ እና ሌሎችም ኢንዱስትሪዎቹ የሚታወቀው የጃፓኑ ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽን ጥምረቱ ላይ የ25 በመቶ ድርሻን ይዞ ይሳተፋል፡፡ ታድያ ሱሚቶሞ ከባለቤትነት ድርሻ ባሻገርም ጥምረቱ በኢትዮጵያ ለሚዘረጋው የቴሌኮም ስራ የቴክኖሎጂ አቅራቢም ነው፡፡ ኩባንያው ከዚህ ቀደም ከጃፓኑ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ኬዲዲአይ እና በማይናማር መንግስት ባለቤትነት ከሚተዳደረው ኤምቲፒ የቴሌኮም ኩባንያ ጋር ሆኖ የማይናማርን ቴሌኮም ገበያ ክፍት የማድረግ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ የእንግሊዙ የፋይናንስ ተቋም ሲዲሲ ግሩፕ በበኩሉ ከጥምረቱ የአስር በመቶ ድርሻን ይዞ እናገኘዋለን፡፡
በፋይናንስ ረገድ የአሜሪካኑ ዴቨሎፕመንት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን የጥምረቱ አካል ለሆነው ቮዳፎን የ500 ሚሊዮን ዶላር ብድር እንደሚያቀርብ ሸጋ ዘግቦታል፡፡
በተጠቃሚዎች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚው የሆነው ኤምቲኤን በውድድሩ ላይ የተሳተፈው ከሲልክ ሮድ ፈንድ እና ሌሎች ለጊዜው ግልፅ ያልወጡ አጋሮችን በመያዝ ነበር፡፡ ግልፅ የወጣው ሲልክ ሮድ ፈንድን ስናይ ተቋሙ በቻይና መንግስት ባለቤትነት የሚተዳደር ሆኖ ሀገሪቱ ከዓለም ጋር ይበልጥ ያስተሳስረኛል ብላ በጀመረችው የቤልት ኤንድ ሮድ እንቅስቃሴ ለሚሳተፉ ሀገራት የገንዘብ አቅርቦትን የሚያደርግ የልማትና መዋለነዋይ ድጋፍ አድራጊ ነው፡፡ ሆኖም ኤሜምቲኤን በውድድሩ ላይ ማቅረብ የቻለው 600 ሚሊዮን ዶላር አነስ ብሎ በመገኘቱ ተቀባይነትን ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ ሆኖም ቀሪውን ፈቃድ ለማግኘት የሚደረገው ውድድር የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ምንጭ፤ Shega
ለተጨማሪ፤ https://shega.co/.../summary-ethiopia-telecommunication.../
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው አፍሪካን ዩኒቲ ፎር ሬነሳንስ ኮንፈረንስ
===========================
በምድረ አፍሪካ ለሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን አስቻይ የሆነ ከባቢ መፍጠርን አልሞ የሚካሄደው ዓመታዊው አፍሪካን ዩኒቲ ፎር ሬነሳንስ ኮንፈረንስ (AURC) ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያን ተካሄደ፡፡ ኮንፈረንሱ በዋናነት በኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት አማካኝነት የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ምሁራን፣ ተመራማሪዎችና ባለድርሻዎችን በማሰባሰብ በራዲሰን ብሉ ሆቴል ሲካሄድ ከወደ ደቡብ አፍሪካም በዙም አማካኝነት ተሳታፊዎችን አካቶ ተደርጓል፡፡
በኮንፈረንሱ ላይ “Africa’s Future Beyond COVID-19” በሚል ርዕስ መቀመጫቸውን ደቡብ አፍሪካ ያደረጉ ምሁራን በዙም አማካኝነት የፓናል ውይይት ያደረጉ ሲሆን እዚሁ ኢትዮጵያ በነበረው ዝግጅትም አራት ያህል የጥናትና ምርምር ስራዎችና ለታዳሚው ቀርበዋል፡፡ በእለቱ ከቀረቡት የምርምር ስራዎች መካከል የጎማ ውስጥ አየር አሞላል በመኪናው የነዳጅ ፍጆታ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕንዖ የሚዳስሰው የአቶ ንጋቱ በላይነህ ጥናት ይገኝበታል፡፡ ብዙውን ጊዜ መኪኖች የጎማቸው አየር ከሚገባው በላይ አልያም በታች ሆኖ እንደሚሞላ የተናገረው አቶ ንጋቱ ይህ የሚያሳድረውን ውጤትም በአንበሳ የከተማ አውቶብሶች ላይ ካደረገው ሙከራ ጋር በማያያዝ ለታዳምያኑ አስቃኝቷል፡፡
ሌላው በዕለቱ የቀረበው ጥናት በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት አማካኝነት በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ተቋማትን በመዳሰስ ተጠንቶ ለህዝብ በቀረበው የብሔራዊ ኢኖቬሽን ሰርቬይ ላይ ነው፡፡ የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪ በሆኑት አቶ በላቸው አለማየው አማካኝነት ለታዳምያን እንዲደርስ በተደረገው በዚህ ዳሰሳ በኢትዮጵያ ያሉ ሀገራዊ የኢኖቬሽን ደረጃዎች ተመላክተውበታል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ተቋማት በተገበሯቸው የኢኖቬሽን ስራዎች አማካኝነት ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የተናገረው አቶ በላቸው ለዚህ ያበቃቸው ዘንድ ተቋማቱ ሲተገብሯቸው የሚስተዋሉ የኢኖቬሽን አይነቶች እንዲሁም ወደ ኢኖቬሽን ለመግባት መነሻ ምክንያቶቻቸው ናቸው ያላቸውን በዝርዝር አሳይቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በኢትዮጵያ ያለውን የኢኖቬሽን እንቅስቃሴ እጅግ ዝቅተኛና በውስን ሁናቴዎች ላይ የተንጠለጠለ በመሆኑ ይህን እንደ ሀገር ያሻሽላሉ የተባለላቸው ጠንካራ የአዕምሮ ንብረት ጥበቃ ስርዓት ግንባታ፣ የገንዘብ ድጋፍ እና የዕውቀት ሽግግርን ጨምሮ ልዩ ልዩ የመፍትሄ እርምጃ ጥቁምታዎች ተሰጥተውበታል፡፡
ከሁለቱ በተጨማሪ “Termal Regulating Leather for Hot Environment” እንዲሁም “Analysis Factors Affecting Firm Level Innovation Activity in Ethiopia” በሚል ርዕስ የምርምር እና ጥናት ስራዎች የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪ በሆነው አቶ ወገኔ ደምሴ እና ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በመጣው አቶ አበባው አቢቦ ቀርበዋል፡፡ በአጠቃላይ የቀረቡት ጥናቶች እና የፓናል ውይይትንም አስመልክቶ በመድረኩ ተገኝተው በነበሩ ምሁራን አማካኝነት ጥያቄና አስተያየት ሲሰጥባቸው ቆይቷል፡፡
አፍሪካን ዩኒቲ ፎር ሬነሳንስ ኮንፈረንስ ላለፉት 10 ዓመታት ሲካሄድ ቢቆይም ከደቡብ አፍሪካ ውጪ ሲደረግ ግን ይህ ለመጀመሪያ ጊዜው ነው፡፡ ኮንፈረንሱ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው ባለፈው ዓመት ቢሆንም በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ምክንያት ወደዚህ ዓመት ሊሸጋገር ችሏል፡፡