TechIn2
1.17K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
በቀዳሚው የኒውክለር ፍንዳታ አማካኝነት የተፈጠረው አዲስ ቁስ
===========================
የተለየና የማይደገም መዋቅር ያለው ኮዌሰክሪስታልን ሲፈልጉ የቆዩ ሳይንቲስቶች በመጀመሪያው የኒውክለር ቦምብ ሙከራ ወቅት የተፈጠረውን ኢምፖሲብል የተሰኘ አንድ ኮዌሰክሪስታል መለየት ችለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም አይታወቅ የነበረው ይህ ኮዌሰክሪስታል ከአይረን፣ ሲልከን፣ መዳብ እና ካልሺየም የተዋቀረና ምናልባትም በተነኑ የበረሃ አሸዋ እና ኮፐር ገመዶች ጥምረት የተፈጠረ እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ የሆኑ ቁሶች በቤተ-ሙከራ ሴንተሳይዝ የተደረጉና በሜትሮይቶች ውስጥም የተገኙ ቢሆንም በንጥረ-ነገሮች ጥምረት ለመመስረት ግን ይህ የመጀመሪያው ኮዌሰክሪስታል ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ኮዌሰክሪስታሎች ከተለምዶአዊዎቹ ክሪስታሎች በተለየ የአተሞች አወቃቀር የተገነቡ ናቸው፤ ተለምዶአዊዎቹ ክሪስታሎች ሲደጋገሙም ተመሳሳይ ሆነው ሲቀጥሉ ኮዌሰክሪስታሎች ግን የማይቻል ተብለው ይታሰቡ የነበሩ ሲሜትሪዎች አሏቸው፡፡ በአውሮፓውያኑ 1982 ይህን አይነት የማይቻል ሲንተቲክ አሎይን በማግኘት የመጀመሪያው ሰው የሆነው ዳንኤል ሼትማን ስራው በሂሳብ ስሌት የማይሆን ነው ባሉት አጥኚዎች ዘንድ ከጥርጣሬ ወድቆ ነበር፤ ምንም እንኳን የኋላ ኋላ እ.አ.አ 2011 ላይ የኖቤል ሽልማትን በኬሚስትሪ ዘንድ ለማሸነፍ ቢያበቃውም፡፡ በተመሳሳይ ወቅት ፖል ስቴንሀርዲት እና የሙያ አጋሮቹ የማይደገሙ የባለ ሦስት እይታ (3D) መዋቅሮችን በሀልዮት ማስቀመጥ ጀምረው ነበር፤ ይህም እንዴት ሒሳብ ላያገኛቸው ሊቀር እንደቻለ የሚያብራራ ነበር፡፡
በአውሮፓውያኑ ሀምሌ 16 1945 በጆርዳና ዴል ሙኤርቶ በረሃ ከተደረገው ትሪኒቲ የኒውክለር ቦምብ ሙከራ ፍንዳታ በኋላ አጥኚዎች ከበረሃ አሸዋ የተሰሩ አረንጓዴያማ መስታውት መሰል ቁሶችን በስፋት አግኝተው ነበር፡፡
ምንጭ፤ Nature
ለተጨማሪ፤ https://www.nature.com/articles/d41586-021-01332-0...
ከአገልግሎት ውጭ የሆነው የኢንተርኔት ማፈላለጊያ
********************************
ማይክሮሶፍት ኩባንያ የኢንተርኔት ማፈላለጊያ ፕላት ፎርሙ ከአገልግሎት ውጭ መሆኑን አሳወቀ፡፡ ይህ Internet Explorer የተሰኘው ማፈላለጊያ ለ25 ዓመታት ግልጋሎት የሰጠ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ተጠቃሚዎች እንደ ጎግል ክህሮምና የአፕሉ ሳፋሪ እየተጠቀሙበት ባለመሆኑ ከአገልግሎት ውጭ መደረጉ ተነግሯል፡፡ መረጃው ይፋ በሆነበት ወቅት ድርጅቱ ፕላትፎርሙ በተለይ በዊንዶው 10 በ Microsoft Edge መተካቱን አሳውቋል፡፡
ተቋሙ አክሎም ማይክሮሶፍት ኤጅ ከኢንተርኔት ኤክስፕሎረር የተሻለ ፈጣንና ደህንነቱ የተረጋገጠ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ቀስ በቀስ ከአገልግሎት ውጭ እየሆነ የመጣው ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር በቀጣዩ የፈረንጆች አመት ሰኔ 15 2022 ሙሉ ለሙሉ አገልግሎቱ ተቋርጦ ከተቋሙ እንደሚሰረዝ ተነግሯል፡፡
ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር ከተቋረጠ በኋላ በዚህ ማፈላለጊያ አማካኝነት ይሰሩ የነበሩ መተግበሪያዎችና ድረ-ገጾች እስከ 2029 ድረስ አገልግሎታቸውን በማይክሮሶፍት ኤጅ አማካኝነት እንደሚቀጥሉም ታውቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የጎግሉ ክሮም የገበያውን 65 በመቶ የተቆጣጠረ ሲሆን በአፕል ካምፓኒ ተበልጽጎ ድርጅቱ ባመረታቸው ቁሶች የሚሰራው ሳፋሪ ደግሞ 19 በመቶ ገደማ ሽፋን ይዟል፡፡ ፋየር ፎክስ በ3.59 በመቶ ሽፋን ሲከተል ኤጅ ደግሞ 3.39 በመቶ የገበያውን ሽፋን ይዟል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-05-microsoft-internet-explorer.html?fbclid=IwAR24t8M9vNpCTRtQnX6k8Wl32mPtoDXxQO1f6bTNTHdlcDU7AzfoxZVM1-A
ለፈጠራ ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ቅድመ ኢንኩቤሽን ፕሮግራም ፍፃሜውን አገኘ
============
በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቅድመ ኢንኩቤሽን ፕሮግራም ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ ፕሮግራሙ ልዩ ልዩ የፈጠራ ባለሙያዎችን ከተለያዩ ቦታዎች እንዲውም ከኢንስቲትዩቱ በማሰባሰብ የተካሄደ ሲሆን ተሳታፊዎቹን በማንኛውም የኢንኩቤሽን ፕሮግራም ውስጥ ተሳታፊ ለመሆን ብቁ እንዲሆኑና የፈጠራ ሀሳቦቻቸውንም ወደ ቢዝነስ እንዲለውጡ የሚያደርግ ነው ተብሎለታል፡፡
የፕሮግራሙ መጠናቀቅያ በሆነው የዛሬው መርሀ ግብር ፕሮጀክቶችን በማስተዳደር፣ ሀሳብን ለሌሎች እንዴት ማቅረብ እንደሚቻል እና በሌሎችም አባይት ጉዳዮች ላይ ለተሳታፊዎች ገለፃ ቀርቧል፡፡ ተሳታፊዎቹ ሀሳባቸውን ለሌሎች በማስረዳት ረገድ ማድረግ ስለሚገባቸው ተግባራት የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪ በሆኑት አቶ በላቸው አለማየሁ አማካኝነት የክህሎት ስልጠና ሲሰጣቸው ይህን ክህሎት ማዳበር ይችሉ ዘንድም በተለይ በሀሳባቸው ላይ መዋለ-ነዋያቸውን በሚያፈሱ ባለሀብቶች ዘንድ በምን መልኩ መቅረብ እንዳለባቸው ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የተግባር ልምምድንም ማድረግ ችለዋል፡፡
ፕሮግራሙን ላለፉት አራት ቀናት ሲከታተሉ ከነበሩት ተሳታፊዎች መካከል ቃለ መጠይቅ ያደረግንለት ዮሃንስ ቢምረው የተሰኘ የ12ተኛ ክፍል ተማሪ ፕሮግራሙ ከዚህ ቀደም በተገቢው መልኩ አይመለከታቸው የነበሩት እንደ አዕምሮ ንብረት ጥበቃ ባሉ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ ዕውቀትን የሰጠው መሆኑን ገልፆልናል፡፡ በአነስተኛ የኃይል ማመንጫዎች ግንባታ አማካኝነት ታዳሽ ኃይልን ለገጠሩ ማህበረሰብ የማዳረስ ፕሮጀክትን ይዞ በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፈው ዮሃንስ በቆይታው በተለይም ሀሳብን ለሌሎች በመግለፅ ረገድ የተሰጡትን አስተያየቶች ለወደፊት በአግባቡ እንደሚጠቀምባቸው ተናግሯል፡፡
የዕለቱን መዝግያ ንግግር ያሰሙት በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የስታርታፕና ኢኖቨቬሽን ፕሮሞሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ በረከት አባይነህ የክህሎት ጠቀሜታ በመደበኛ ትምህርት ከሚገኘው ዕውቀትም የላቀ መሆኑን በመጥቀስ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎችም በተለይ ሀሳባቸውን ለሌሎች የማስረዳትና ትስስር የመፍጠር ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የፈጠራ ባለሙያዎቹ የሚገጥሟቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ወደ ዕድል እንዲለውጡ የተለያዩ ታዳጊ ሀገራት ምሳሌዎችን ለአብነት በማንሳት ተናግረዋል፡፡
ፕሮግራሙ ለተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት በማበርከት መቋጫውን አግኝቷል፡፡
ቴክ ሳይንስን ዛሬ በ10 ሰዓት ይጠብቋት
==========
በዚህ ሳምንትም ከባዮፎውል እስከ ብረት ቴክኖሎጂ እንዲሁም የአቅጣጫ ማሳወቂያ ስርዓትን ከሰሩት ሁለት ታዳጊዎች በሙያቸው ላቅ ያለ ደረጃ እስከደረሱት ዶ/ር ፈቃዱ ማሴቦ ድረስ ዳሰሳ የሚያደርጉት የአብይ ፕሮግራም፣ ቴክኖሎጂ ታሪክ፣ ብላቴናት እና የተመራማሪዎች የህይወት ታሪክ መሰናዶዎቻችንን ይዘንልዎ እንመጣለን፡፡
ሁሉም ሙሉ ሁሉም ዝግጁ ሆኖ እርሰዎን እየጠበቀ ነውና ዛሬ ቅዳሜ በ10 ሰዓት ላይ ቻናሉን ወደ MOE TV በማዞር ለእርስዎም ሆነ መላው ቤተሰብዎ የሚሆን ልምድ እና ዕውቀትን ይሸምቱ፡፡
በየሳምንቱ ቅዳሜ እንዲሁም በድጋሚ ማክሰኞ 10 ሰዓት በMOE ቴሌቪዥን ከሚቀርበው በተጨማሪ ወደ ዩትዩብ ቻናላችንም ጎራ በማለት አዳዲሶቹን ጨምሮ እስከዛሬ የተሰሩትን ፕሮግራሞች በሙሉ መመልከት ይችላሉ (https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc
5Annfwvg)፡፡
በተለያዩ አማራጮችም ይከታተሉን:-
ቴሌግራም t.me/TechIn2
ትዊተር twitter.com/TechinEthiopia
ለአፍሪካ ተስፋ የሰጠው የኢትዮጵያ የብሎክ ቼን እንቅስቃሴ
*******************************
ኢትዮጵያ በብሎክቼን ቴክኖሎጂ ላይ ያሳየችው ጅማሮ ለዘርፉም ሆነ ለአፍሪካውያን ትልቅ ተምሳሌት እንደሚሆን ተነገረ፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ ቢትኮይን ይፋ ከተደገ በ2009 የብሎክቼን ቴክኖሎጂ እምብዛም ተቀባይነት አላገኘም ነበር፡፡ ይህም የሆነው ቴክሎጂው የሰዎችንና የተለያዩ የንግድ ስራዎች ላይ የሚኖረው ጥቅም በብዙዎች ዘንድ ስላልታወቀ ነበር፡፡
ብሎክቼን ክፍት የሆነ የመረጃ ምንጭ ሶፍትዌር ሲሆን ይህ ባህሪው አዲስ ምርትና አገልግሎት ይዘው ለሚቀርቡ ሰዎች ህጋዊና ያለዋጋ የቀረበ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ያልተማከለ የመረጃ አስተዳደር ስርዓትንም ጥቅም ላይ እንዲውል ያስችላል፡፡ በብሎክቼን አማካኝነት የሚሰጠው አገልግሎች በየትያውም አካል ቁጥጥር የማይደረግበት ሲሆን በኔትወርኩ ውስጥ የተካተቱትት ሁሉ በዚህ ስራ ላይ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ እንዲሁም ደግሞ ብሎክቼን የተለያየለየዩ አካላት ያለሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ግንኙነቶችን እንዲያደርጉ ምቹ ሆኔታን ይፈጥራል፡፡
የመረጃ ምንጫችን በሚያዚያ ወር የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣውን መረጃ ተከትሎ በሰራው ዘገባ ኢትዮጵያ በ3500 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ አምስት ሚሊዮን ተማሪዎችንና መምህራንን ዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ማስተዳደር የሚያችል ሀገራዊ የመረጃ ቋት ለመገንባት መፈራረሟን ገልጧል፡፡ ስምምነቱም የተማሪዎችን የትምህርት መረጃ ለማከማቸት የሚያስችል ነው፡፡ ይህም በመንግስት ደረጃ ከተፈረሙ ተመሳሳይ ስምምነቶች ውስጥ ትልቁ ስምምነት እንደሆነ የመረጃ ምንጫችን አሳውቋል፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-05-ethiopia-blockchain-watershed-moment-technology.html
የኢንክሪፕሽን መሰረታዊ ጥቅሞች ምንድን ናቸው
========================
መረጃዎችን ያለምንም ስጋት ከሰርጎ ገቦች ወይም ፍቃድ ከሌላቸው ሰዎች በመጠበቅ በድብቅ ማስቀመጥም ሆነ መላላክ እጅግ በጣም ወሳኝ ነው። ከቅርብ አመታት ወዲህ ኢንክሪፕሽን በብዛት አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ወንጀለኞችን ለመከላከል፣ የሰዎችን መብት ለማስጠበቅ ፋይሎችን፣ ዶክመንቶችን፣ መልዕክቶችን ለመላክና ለመጋራት፣ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚካሄድ ማንኛውንም አይነት የምስልም ሆነ የቪዲዮ ልውውጥ ያለምንም ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ለማስተላለፍ፣ ዲጂታል ሚዲያዎችን በመጠቀም ሙዚቃዎችንና ቪዲዮችን በህገ ወጥ መንገድ እንዳይለወጡ፣ ክፍያ ሳይፈፀም እንዳይቀዱ ወይም ክፍያም ከተፈፀመ በኋላ ለሌላ ሶስተኛ ወገን እንዳይባዙ ለማድረግ ብሎም እንዳይነበቡ በማድረግ ለባለቤቶችና ለባለመብቶች ከፍተኛ የሆነ አገልግሎት ይሰጣል።
በዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ዘመን የግብይት ስርዓትን በኤሌክትሮኒክስ አማካኝነት መጠቀም ተችሏል። በተለይ ደግሞ የባንኪንግ አገልግሎቶች መጀመራቸው እና ዲጂታል የክፍያ ሥርዓት መዘረጋቱ ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም ብዙ የስርቆት ወንጀሎች ይፈፀማሉ። ይህንን የስርቆት ድርጊት ለመከላከል ደግሞ የኢንክሪፕሽን ወይም ክሪፕቶግራፊ ቴክኖሎጂ በጣም አስፈላጊ ነው። ማንኛውም አይነት የግብይት ስርዓት በሚፈፀምበት ወቅት መልዕክቶች የሚላኩበት ዘዴ ሚስጥራዊ እንዲሆን ከማስፈለጉ አንጻር ማንኛውም የኢንክሪፕሽን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እንዲውል ያስፈልጋል።
ኢንክሪፕሽን ከሚሰጣቸው መሰረታዊ ጠቀሜታዎች መካካል
የመረጃዎችን አስተማማኝነት ለማረጋገጥ - ይህም ማለት በመልዕክት የሚላኩ መረጃዎች የሚያገኙት ፍቃዱን ያገኙ አካላት ብቻ መሆናቸው እና ማን የላከው መልዕክት መሆኑን ለማወቅ የሚረዳ ነው።
የመረጃዎችን ተአማኒነት ለማረጋገጥ - መልዕክት ተቀባዩ የደረሰው መልዕክት ምንም ሳይነካ ወይም ማስተካከያ ሳይደረግበት መድረሱን ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው።
የመረጃዎችን ባለቤትነት ለማረጋገጥ - ላኪው የላከውን መልዕክት መካድ እንዳይችል ለማድረግ እና ክህደትን ወይም ከላኪው በኩል የሚታይ እምቢተኝነትን ለማስቀረት ያግዛል።
https://www.genetec.com/.../what-is-encryption-and-how....
ሰዎችን ለኢንተርኔት ጥቃት (ሀክ) እየዳረገ ያለው የመተጫጫ መተግበሪያ
*****************************
በጃፓን የመተጫጫ መተግበሪያን በመጠቀም ውሃ አጣጫቸውን የሚፈልጉ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች ለኢንተርኔት መረብ ጥቃት መጋለጣቸው ተሰምቷል፡፡ በጃፓን የተለያዩ የመተጫጫ መተግበሪያዎች (dating app) ሲኖሩ በእነዚህ መተግበሪያዎች የሚጠቀሙ ከሚሊዮን በላይ የሆኑ ሰዎች የግል መረጃ በኢንተርኒት ጥቃት ፈጻሚዎች እንደተሰረቀ ወይም እንደታወቀ መተግበሪያዎችን የሚቆጣጠሩ አካላት ይፋ አድርገዋል፡፡
ኦሚአይ የተሰኘው መተግበሪያ ተጋሪ የሆነው ኔት ማርኬቲንግ በመተግበሪያው ላይ ፈቃድ ያልተሰጣቸው ሰዎች ካለፈው ሚያዚያ ወር ጀምሮ የተጠቃሚዎችን መረጃ እየበረበሩ ነው ብሏል፡፡ በሀከሮቹ ትኩረት ከተደረገባቸው መረጃዎች መካከል ለእድሜ ማመሳከሪያነት የተጫኑ የመንጃ ፈቃድ ፎቶዎችና ፓስፖርቶች ይገኙበታል፡፡
እስካሁን ከ1.7 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች የተጠቁ ሲሆን አንዳንዶቹ አሁን ላይ መተግበሪያውን እየተጠቀሙት እንዳልሆነ ተገልጧል፡፡ ኦሚአይ የተሰኘው መተግበሪያ በጃፓን እጮኛቸውን በቁምነገር የሚፈልጉ ብዛት ያላቸው ሰዎች ከሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች ውስጥ ዋነኛው ሲሆን እስካሁንም 6.89 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች አሉት፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/.../2021-05-million-affected-hack...
ስለ ኤሎን መስክ የ1952ቱ ትንቢት
********************
በ1952 የተጻፈ አንድ መጽሐፍ ኤሎን አንድ ቀን በማርስ ላይ እንደሚገኝ ተንብዮ እንደነበር መረጃዎች ይፋ ተደረጉ፡፡ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ለጀርመኑ ናዚ የሮኬት ቴክኖሎጂ ተመራማሪ የነበረው ዋርንሄር ቮን ብራውን በጻፈው መጽሐፍ አንድ ቀን ኤሎን የሚባል ብዙዎችን ወደማርስ መርቶ እንደሚወስድ ተንብዮ ነበር፡፡ ይህ ሰው የመጀመሪያው የአለም ጦርነት ከመጀመሩ ከጥቂት ጊዜያት በፊት በጀርመን የተወለደ ነው፡፡
ሰውየው በህዋ በረራ ላይ እጅግ ተማርኮ የነበረ ሲሆን በመጨረሻም በ1932 በፈሳሽ ነዳጅ የሚሰራ ሮኬትን ለጀርመን ጦር ሰርቶ አስረክቧል፡፡ ስራውን የቀጠለው ቮን በራውን በጀርመኑ ናዚ ስር ሆኖ ከጓደኞቹ ጋር ምርምር በማድረግ V-2 የተሰኘ ሮኬትን መፍጠር ችሏል፡፡ ይሁን እንጂ ጦርነቱ ከማለቁ በፊት እጁን ለአሜሪካው ጦር ሰጥቶ ስለነበር በምርኮ ወደ ናሳ ሊመጣ ችሏል፡፡
ሰውየው ከቆይታዎች በኋላ የናሳው የማርስ ሼል በረራ ማእከል ዳይሬክተር መሆን ችሏል፡፡ በዚህም ሰዎችን ወደ ጨረቃ በሚወስዱ ሮኬቶች ዙሪያ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በህዋ ምርምር ዙሪያ በወቅቱ እንደሱ ከፍተኛ ፍላጎትና ጥረት ያለው ሰው እንዳልነበረ የሚነገርለት ብራውን በ1952 ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ የማርስ ፕሮጀክት በሚል ርዕስ መጻፍ ችሏል፡፡ በመጽሐፉም በ1965 ወደማርስ 70 ያክል ሰዎችን መጓጓዝ እንደሚቻል ጽፎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እንዳሰበው አልሆነም፡፡
በሚያስደንቅ ሁኔታ የብዙዎችን ትኩረት የሳበው በመጽሐፉ ሁለተኛ ግማሽ ላይ የተካተተው ሀሳብ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ላይ ኤሎን ወደማርስ የሚያደረገውን እንቅስቃሴ እንደሚመራ የሚናገር አረፍተ ነገር ተካትቷል፡፡ በዚህ ክፍል ላይ ኤሎን የሚለው የአንድ ሰው ስም ሆኖ ሳይሆን የተገለጸው ሰዎችን ወደ ማርስ መውሰድ ሲቻል ወደዚያ የሔዱ ሰዎች የስራቸው ወይም የግዛታቸው መሪ የሚሆነውን የሚገልፅ ቃል ነው፡፡ መጽሐፉም የማርስ መንግስት በ10 ሰዎች የሚመራ እንደሆነና በአለም አቀፍ ደረጃ ተመርጦ ለአምስት አመት የሚያስተዳድርና ስሙም ኤሎን ይባላል ሲል አስነብቧል፡፡
ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/space/a-book-from-1952-predicted-an-elon-would-one-day-rule-over-mars/?fbclid=IwAR3Bvlg5TSdrvNKtXLw2VytvvpFb9-wDAZHJ_rJSR9LXgqNZfQJJ6CoQ2qY
Ethio Locate አዲሱ የጉዞ መመሪያ ፕላትፎርም
========================
ለአገር ውስጥ እና ለዓለም አቀፍ የቢዝነስ እንቅስቃሴዎች ዲጂታል መፍትሄዎችንና አሰራሮችን በማቅረብ የሚሰራው ዋይ-ቴክ (Y-Tech) የተሰኘው አገር በቀል የቴክኖሎጂ ድርጅት Ethio Locate የተባለ አዲስ የጉዞ መመሪያ ፕላትፎርም ማቅረቡን ይፋ አድርጓል፡፡ ኢትዮ ሎኬቴ በቀላል ሂደት ተጠቃሚዎች ቦታዎችን እና መረጃዎችን በኢትዮጵያ ውስጥ በነፃ እንዲያገኙ የሚያግዝ የጉዞ መመሪያ ፕላትፎርም ሲሆን፤ ማንኛውም የንግድ ድርጅቶች እና ተቋማት አገልግሎታቸውን ወይም ምርቶቻቸውን በኦንላይን እንዲያስተዋውቁ እና ዲጂታል ፕሮፋይል እንዲኖራቸውም የሚያስችል ነው፡፡
ኢትዮ ሎኬቴ በአሁኑ ወቅት በአንድሮይድ ስልኮች እና በፕለይ ስቶር መተገበሪያዎች ላይ የሚገኝ ቢሆንም ለአንድ አመት በዌብሳት ፕላተፎርም ግልጋሎት ሲሰጥ የቆየ እና በዚህ ቆይታውም ከተጠቃሚዎች ጥሩ ምላሽ ማግኘቱ ተገልጿል፡፡ በዚህ የጉዞ መመሪያ ፕላትፎርም ተጠቃሚዎች የሆቴሎችን፣ ሙዚየሞችን፣ ፓርኮችን እና በመላ አገሪቱ ያሉ የተለያዩ ቦታዎችን አጠቃላይ አድራሻ በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡
የኢትዮ ሎኬቴ የቡደን አባላት ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ሲጓዙ መረጃዎችንና ቦታዎችን ለማግኘት ያጋጠማቸውን የግል ፈተናዎች መሠረት በማድረግ ፕላትፎርሙን ለመስራት መነሳሳታቸውን የሚያስረዳው የኢትዮ ሎኬቴ ዋና ሥራ አስፈፃሚና መስራች አቶ ይሳቅ አምደሥላሴ ኢትዮ ሎኬቴ አገልግሎት አቅራቢዎች እና ደንበኞቹ የሚፈልጉትን የተደራጀ እና የተጣራ የዲጂታል መረጃ በአንድ ቦታ ለማግኘት የሚስችል ፕላትፎርም መሆኑን ይናገራል፡፡ ይህ የመረጃ እጥረት ከተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ለሚመጡ ቱሪስቶችም ትልቅ ችግር በመሆኑ የአገልግሎት አቅራቢዎች የተሻሻለ መረጃቸውንና አድራሻቸውን በቀላሉ በዲጂታል መንገድ ማቅረብ እንዲችሉ ይህ ፕላትፎርም ትልቅ እድል እንደሚፈጥርም አቶ ይሳቅ ተናግሯል፡፡
በፕላትፎርሙ አማካኝነት የሀገራችንን የቱሪስት መስህቦች፣ መዳረሻዎች እና የታላቋን ሀገራችንን ታሪክ በተፃፈና በተደራጀ ይዘት ማስተዋወቅ እንፈልጋለን የሚለው አቶ ይሳቅ ይህን ለማሳካትም በኢትዮ ሎኬቴ ዙሪያ ሰፋፊ እቅዶች ይዘን በመስራት ላይ እንገኛለን ብሏል፡፡
መተግበሪያውን በተከታዩ የጎግል ፕለይ ሊንክ ማውረድ ይቻላል
https://play.google.com/store/apps/details...
ምንጭ፡ https://www.techinafrica.com/ethiopia-tech-startup-launches-travel-guide-application/
ከፊል እይታን መመለስ የቻለው ኦፕቶጀኔቲክስ ቴክኖሎጂ**********************************
ሁለቱም አይኖቹ ማየት ተስኗቸው የነበሩ አንድ ሰው ኦፕቶጀኔቲክስን በሚጠቀም ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ህክምና አማካኝነት ከፊል ብርሃን ማግኘቱ ተሰማ፡፡ ህክምናው የነርቭ ዘረመሎችን ለብርሃን መልስ እንዲሰጡ በሚያስችል መልኩ የተካሄደ እንደሆነ የመረጃ ምንጫችን ዘግቧል፡፡
ኦፕቶጀኔቲክስ በአሁኑ ወቅት በብዛት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ ቴክኖሎጂ ሲሆን የጭንቅላት ህዋሳትን በትክክል መቆጣጠር የሚያስችልና ህዋሳቱም ለብርሃን መልስ እንዲሰጡ የሚያደርግ ነው፡፡ በእንስሳት ላይ ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ የተለያዩ ግኝቶችን ማሳወቅ የቻለ ሲሆን ባለው የሳይንስ እውቀት ክፍተት ምክንያት በሰዎች ላይ ለመሞከር ብዙ እንቅፋቶች አሉበት፡፡ ለምሳሌ በጭንቅላት ውስጥ ብርሃንን ለማብራት ብርሃን አስተላላፊ ገመዶችን በጭንቅላት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ደግሞ ለጊዜው የማይደፈር ነው፡፡
ብዙዎች የአይን ብርሃን ማጣትን ለመከላከል ወይም ለማከም እንዲውል የተለያዩ ጥረቶችን እያደረጉ ሲሆን እስካሁን በዚህ ዘዴ የአይን ብርሃኑ የተመለሰለት አንድ ፈረንሳዊ የ58 ዓመት ጎልማሳ ነው፡፡ ይህም ሰው በመንገድ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ምስል በነጭና ጥቁር ቀለማት ማየት መቻሉ ተነግሯል፡፡ ይህም እንዲሆን ታካሚው የሚያደርገው ለምስል መከሰት የተለያዩ እገዛዎችን የሚያደርግ መነጸር መልበስ ይኖርበታል፡፡
ምንጭ newscientist
ተጨማሪ ንባብ https://www.newscientist.com/article/2278405-partial-sight-restored-for-man-who-is-blind-thanks-to-optogenetics/?utm_medium=social&utm_campaign=echobox&utm_source=Facebook&fbclid=IwAR2sHL1KWnO7M8MMQGIf5_auP91iwfaQwWrh7nKqtAs5EEcUoIPEK-wjPuU#Echobox=1621874379-1