ለዘጠኝ ወራት ያለማቋረጥ እየነደደ የተገኘው ዛፍ
=====================
በአሜሪካኗ የካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ ባለው የስኮያ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኝ አንድ የስኮያ ዛፍ አካባቢው ከወራት በፊት በሰደድ እሳት ተጠቅቶ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ውስጡ ፍም ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ተመራማሪዎች ዛፉን ያገኙት ከዘጠኝ ወራት በፊት በፈረንጆቹ የበጋ ወራት በአካባቢው የተከሰተው ሰደድ እሳት ብሔራዊ ፓርኩ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ለመመርመር ወደ ስፍራው ባቀኑበት ወቅት ነበር፡፡ ምንም አይነት መንገድ በአካባቢው ያልተገኘበት ዛፉ ያለማቋረጥ ሲጨስ ተመልክተውት ነው ተመራማሪዎቹ ሊያገኙት የቻሉት፡፡
የዛፉን ነገር አስገራሚ ያደረገው በእነዚህ ወራት ውስጥ አካባቢው ላይ ዝናብ እና በረዶ ሲፈራረቅበት ቆይቶ እንኳን በውስጡ ፍም ሆኖ መቆየቱ ነው፡፡
የዛፎች እሳት ሳይጠፋ መቆየት አዲስ ጉዳይ አይደለም፤ አንዳንድ ዛፎች በከባድ የሰደድ እሳት ከተቃጠሉ በኋላ በውስጣቸው ያለው እሳት በቂ ኦክስጅን እና ጥበቃ እያገኘ ስለሚቆይ ውስጥ ውስጡን በዝግት እየነደደ ሊከርም ይችላል፡፡ ሆኖም ይህ አይነት ሁናቴ ሰደድ እሳትን በደምብ በተላመዱትና የእሳት መከላከያ ቅርፊትን ተላብሰው በቆሙት የስኮያ ዛፎች ላይ መከሰቱ ነገሩን ለየት አድርጎታል፡፡
በመብረቅ አማካኝነት ባሳለፍነው ነሀሴ ላይ ተነስቶ በቁጥጥር ስር እስከዋለበት ወርሀ ታህሳስ ድረስ የቆየው ሰደድ እሳቱ 60,700 ሄክታር የሚሆን ስፋት ያለው አካባቢን አቃጥሎ አልፏል፡፡
ምንጭ፤ Live Science
ለተጨማሪ፤ https://www.livescience.com/giant-sequoia-tree-still...

የኒያ ፋውንዴሽን እና የጆይ ኦቲዝም ማዕከል መሥራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ ዘሚ የኑስ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
በኒያ ፋውንዴሽን ስር ጆይ የኦቲዝም ማዕከል የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት አቋቁመው ለበርካታ ወገኖች ደራሽ መሆን የቻሉት የጆይ ኦቲዝም ማዕከል መስራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ ዘሚ የኑስ የብዙ እናቶችን እንባ የተመለከቱ፣ ድምፅ አልባውን የልጆችን ስቃይ ያደመጡ፣ ኦቲዝም ምንም በማይታወቅበት ጊዜ ችግሩን ተረድተው የበኩላቸውን አስተዋፆኦ ለመወጣት የጣሩ እና የኦቲዝም የጤና እክል ያለባቸውን ልጆች በሚችሉት አቅም መርዳት የቻሉ እናት ነበሩ፡፡
በርካታ የኦቲዝም እክል ያለባቸውን ልጆች ይዞና ወላጆቻቸውንም እያገዘ የነበረው የኒያ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1994 ሲቋቋም ዋና ትኩረቱን በችግሩ ዙሪያ ማህበራዊ ግንዛቤ መፍጠር፣ የምክር አገልግሎት ማቅረብ አና ለወሳኔ ሰጪ አካላት የሎቢ ስራ ማከናወን ቢሆንም በጥቂት አመታት ውስጥ ፅህፈት ቤት በመክፈት ቀላል ቁጥር የሌላቸውን የኦቲዝም ተጠቂዎችን ለማቀፍ ችሏል፡፡ በሂደት በተሰሩ የማስፋፊያ ስራዎችም ማእከሉ ሌሎች ተጠቂዎችን በመጨመር መሰረታዊ የሚባሉትን የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና፣ ለንግግር መጎልበት የሚሰጥ ህክምና እና የመገንዘብ ባህሪን የሚያሳድግ ህክምና በመስጠት ብዙ ችግረኞችን ለመርዳት ችሏል፡፡
ማዕከሉ ከዚህ እንቅስቃሴው በኋላ በሂደት እየተፈጠረ በመጣው ንቅናቄና የግንዛቤ መስፋፋት ሰዎች ስለበሽታው እንዲያውቁ ከማድረጉም በተጨማሪ ሌሎች የሱን ፈለግ የተከተሉ ማዕከሎች እንዲመሰረቱ እና ስለጉዳዩ ያለው ትኩረትም እንዲጨምር ምክንያት ሆናል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የዚህን ፋውንዴሽን መንገድ ተከትለው ከተቋቋሙ ማዕከሎች ውሰጥ ነህምያ እና ብራይት ዋነኞቹ ሲሆኑ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ራሱ የኒያ ፋውንዴሽን የሚያሰራው ጆይ የኦቲዝም የልህቀት ማዕከል በመጪዎቹ ጊዚያት ብዙ ተጠቂዎችን ያግዛል ተብሎ የሚጠበቅ ነው፡፡ በዚህ ከባድና ውጣ ውረድ በተሞላበት መንገድ ላይ ትልቅ ህልም ይዘው ትልልቅ ስራዎችን መስራት የቻሉት ወ/ሮ ዘሚ የኑስ የብዙ ወላጆችን እንባ ያበሱና ስለኦቲዝም የነበረውን የተዛባ አመለካከት በራሳቸው ጥረት መቀየር የቻሉ እናት ናቸው፡፡
የኦቲዝም ታማሚ ልጃቸውን ለማሳደግ የተጋፈጡትን ከባድ ሕይወት በአደባባይ በመናገርና ለዘመናት ከህመሙ ጋር ተያይዞ የነበረውን አጉል እምነትና ዝምታ በመስበር ለብዙ ወገኖች ደራሽ የነበሩት ወ/ሮ ዘሚ የኑስ፣ በሚሊኒየም ኮቪድ-19 በፅኑ ህክምና ማዕከል ውስጥ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ለወ/ሮ ዘሚ የኑስ ቤተሰብና ወዳጆች መፅናናትን ይመኛል

አዲሶቹ የዴል ኩባንያ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች
***************************
ዴል የተሰኘው የኮምፒውተር አምራች ኩባንያ አላይንዌር የተሰኘውን የኮምፒውተር አይነት X-Series የተሰኘ ልዩ በሆኑ ቁሶች የተሰራና የተሸለ ብቃት ያለው ላፕቶፕ ኮምፒውተር አስተዋወቀ፡፡ ካምፓኒው በተጨማሪም 11ኛ ትውልድ የሆነውን m15 R6 የተሰኘ የአላይንዌር የላፕቶፕ አይነት አስተዋውቋል፡፡ ኮምፒውተሩም የኢንቴል ሲፒዩ እና RTX 3080 የሞባይል ግራፊክስ ያለው ነው፡፡
ድርጅቱ በ X-Series ኮምፒውተሩ ዙሪያ ተጨማሪ ሀሳቦችን ይፋ ያላደረገ ሲሆን የላፕቶፑን ዲዛይን በአጭር ቪዲዮ አቅርቧል፡፡ ኮምፒውተሩ በጋሊየም ሲልከን የተሰራ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከነበሩት ላፕቶፖች ብዙ መሻሻሎች የተደረጉበት ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል በላፕቶፑ ውስጥ የተገጠመው የንፋስ እንቅስቃሴ ኮምፒውተሩ በጥሩ ብቃት እንዲሰራ ያስችለዋል ተብሏል፡፡ በኮምፒውተሩ ዋጋ እና ለገበያ የሚቀርብበትን መረጃ የተመለከተ መረጃ ግን እስካሁን ይፋ አልተደረገም፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ዴል m15 R6 የተሰኘው ላፕቶፑን የተለያዩ መገለጫዎች ይፋ አድርጓል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የኢንቴል 11ኛ ትውልድ ሲፒዩ፣ 6-core i5-11400H፣ 6-core i5-11400H እና 8-core i9-11900H ሲፒዩ ያላቸውና ከ RTX 3050 እስከ RTX 3080 GPUs ያላቸው እንደሆኑ ይፋ ተደርጓል፡፡ ላፕቶፑ 32 ጂቢ ራም (በተጠቃሚው ከፍ ሊል የሚችልና) 4 ቴራ ባይት መረጃ የማከማቸት አቅም ያለው ነው፡፡
m15 የተሰኘው አላይንዌር ላፕቶፕ በ1300 ዶላር በቅርብ ለገበያ ይቀርባል ተብሏል፡፡ እንዲሁም ደግሞ ዴል G15 የተሰኘ ለተለያዩ ጌሞች የሚያገለግል ላፕቶፕን ይፋ አድርጓል፡፡ ይህም ሞዴል የራሱ መገለጫዎች ያሉት ሲሆን ከ950 ዶላር ጀምሮ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡
ምንጭ engadget
ተጨማሪ ንባብ https://www.engadget.com/dell-alienware-x-series-laptops-exotic-cooling-110043070.html?fbclid=IwAR1Vy7SmR8gLCWPXt-4-FhPBi8lvWosTA5nZu7DJnt9AFJ72QKhx7xJ9XiU
Engadget
Alienware teases new X-Series laptops with exotic cooling solution | Engadget
Dell has teased an upcoming Alienware laptop lineup called the X-Series offering improved thermal performance using new materials..
የስራ ብቃት በኢንዱስትሪ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን
********************************
በአሜሪካ በፋብሪካዎች የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክንያት እስከ 2030 ድረስ 2.1 ሚሊዮን የሚሆኑ የስራ ቦታዎች ክፍት እንደሚሆኑ ተነገረ፡፡ ባለፈው የኮቪድ አንድ አመት ውስጥ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ 578 ሺህ የሚሆኑ የስራ ዘርፎች ተቋርጠዋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ አምስት መቶ ሺህ የሚሆኑ የማኑፋክቸሪንግ የስራ ዘርፎች ያለ ሰራተኛ ክፍት ሆነው ቆያተዋል፡፡
በዘርፉ የተሰራ አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው በአሜሪካ የሚገኙ ከ800 በላይ በማኑፋክቸሪንግ ላያ የተሰማሩ አሰሪዎች በስራቸው ያለውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ወይም በኢዱስትሪዎች እያደገ የመጣውን ሽግግር መላመድና መቋቋም የሚችሉ ክህሎት ያላቸው ሰዎችን ማግኘት እየተቸገሩ ነው፡፡ በተለይ ከ2018 ጀምሮ 36 በመቶ የሚሆኑ የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ብቃት ያላቸው ሙያተኞችን እያገኙ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ ብቃት ያላቸውን ሰዎች ወደ ድርጅታቸው ለመሳብ በሚደረግ ጦርነት (ውድድር) ውስጥ መግባታቸውን ከ77 በመቶ በላይ የሚሆኑ የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ያናገራሉ፡፡ እነዚህ ድርጅቶች ሙያተኞቻቸውን በተለያዩ ስልጠናዎች ከማብቃት ጎን ለጎን ተፈጥሯዊ ብቃት ያላቸውን ሰዎች እያሰሱ እንደሆነ ያነገራል፡፡
በኢንዱስትሪዎችና በተለያዩ አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያለው መረጃ እንደሚያሳየው በአሜሪካ በተለያም 44 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛ ተቋማት በተለያዩ ደረጃዎች ክፍት የስራ መደቦች እንዳላቸው እየተናገሩ ነው፡፡ ይህም ባፉት 48 ዓመታት ውስጥ ያልታየ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የአሜሪካ የሰራተኞች መረጃ ቢሮ በያዝነው ሳምንት ባወጣው መረጃ መሰረት 266 ሺህ በመጋቢት ወር ብቻ የተጨመሩ ናቸው ተብሏል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በኢንዱስትሪዎች ውስጥ ሲተገበር ለዚህ የሚመጥን ብቃት ያላቸው ሙያተኞችም በዚያው ልክ ቁጣራቸው መጨመር እንዳለበት ነው፡፡ የአሜሪካው የስራ ክፍተት ከዚህ በተጨማሪ ከእናቶችና እድሜያቸው ለትምህርት ካልደረሱ ህጻናት ጋር የተያያዘ መገለጫ እንዳለውም የመረጃ ምንጫችን ጠቁሟል፡፡
ምንጭ fortune
ተጨማሪ ንባብ https://fortune.com/.../the-war-for-talent-hits.../...

የድሬደዋ አሜሪካን ኮርነር ክላውድ ሲዲንግን አስመልክቶ በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ባሰናዳው የዙም ውይይቱ ላይ ተሳተፉልኝ ሲል ሁላችሁንም ጋብዟችኋል፡፡ በክላውድ ሲዲንግ ቴክኖሎጂ ምንነትና አሰራር ላይ አተኩሮ በሚካሄደው በዚህ ክፍለ አህጉራዊ ውይይት ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት፣ ግብርና ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ የሚቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ እና ሌሎችም የመንግስት ተቋማት የተወከሉ ኃላፊዎች እንደሚገኙበት ይጠበቃል፡፡ ውይይቱ አርብ ግንቦት 6 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 03፡00 አንስቶ የሚደረግ ሲሆን እርስዎም ከታች በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡
Dire Dawa American Corner is inviting you to a scheduled Zoom Program.
Topic: Cloud Seeding technology and how it works
Time: May 14, 2021 09:00 AM Addis Ababa Time
Join here
https://statedept.zoomgov.com/j/1610459433?pwd=bmg4cEZPQXVud2hCL3I1UTFVZ3M2dz09
Dire Dawa American Corner!
Meeting ID: 161 045 9433
Passcode: 635837

Zoom Video
Join our Cloud HD Video Meeting
Zoom is the leader in modern enterprise video communications, with an easy, reliable cloud platform for video and audio conferencing, chat, and webinars across mobile, desktop, and room systems. Zoom Rooms is the original software-based conference room solution…
ከምድር ወደ ህዋ በፈጣን አውሮፕላን
***********************
በበረራ ታሪክ ውስጥ ከራይት ወንድማማቾች ጀምሮ የተለያዩ እድገቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ፡፡ የእድገት ደረጃዎቹም ከመጠን፣ ከፍጥነት፣ ከከፍታ፣ ከድምጽና አየር ብክለት እና ከመሳሰሉት ጋር የተለያዩ መሻሻሎችን እያሳዩ አሁን ላለንበት ዘመን ደርሰናል፡፡ አሁን ላይ በአለማችን ትኩረት ተሰጥቷቸው በአቪየሽን ዘርፍ እየተሰሩ ካሉ ስራዎች ውስጥ ፍጥነትን አሁን ካለው መሻሻል፣ የጄቶች ድምጽ መቀነስ፣ ለማኮብኮብ የሚያስፈልግን ቦታ በመቀነስ በረራዎችን ካሉበት መጀመር እና የአየር ላይ ታክሲዎችን መጠቀም በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ከከባቢ አየር እንክብካቤ አንጻር ከካርቦን ነጻ የሆኑ የሃይል አማራጮችን ለመጠቀም እየተደረገ ያለው ጥረት ሌላው ተጠቃሽ ነገር ሲሆን በአየርም በህዋም ውስጥ መብረር የሚችል ጄት ለመስራት እየተደረገ ያለው ሙከራ ግን እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ይህም ዲቶኔሽን የተሰኘ የከፍተኛ ፍንዳታ አይነትና ከድምጽ የሚፈጥን ሀይል ነው፡፡ የዚህን ሀይል ምንነት ለመረዳት ባሳለፍነው ነሃሴ ወር በሊባኖስ ቤሩት በተፈጠረው ፍንዳታ የፈራረሱትን ህንጻዎች ማስታዎስ በቂ ነው፡፡ ተመራማሪዎችም ከብዙ ጊዜያት ጀምሮ ይህንን ሀይል መጠቀም የሚችል ሞተር ያላቸው በራሪዎችን ለመስራት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ይህም በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ ከኒው ዮርክ ወደ ለንደን ከአንድ ሰአት በታች መድረስ የሚያስችል ነው፡፡
ይሁን እንጂ ዲቶኔሽን የሚባለው ለመቆጣጠር የሚያስቸግርና ለመከሰት ከአንድ ማይክሮ ሴኮንድ በታች የሚወስድ ከፍተኛ ፍንዳታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በማእከላዊ ፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ ይህንን በቅጽበት የሚጠናቀቅ ክስተት ባለበት ደረጃ በዛ ላሉ ሴኮንዶች እንዲቆይ ማድረግ መቻላቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ይህም ማለት በሊባኖስ ፍንዳታው የተከሰተው አንድ ቤት ውስጥ ሲሆን በአካባቢው የሚገኙትን ህንጻዎች ሁሉ ያፈረሰውን ሀይል ህንጻዎችን ከማፍረሱ በፊት መያዝ መቻል ነው፡፡ መሰረታዊ ሀሳቡም አየርንና ነዳጅን ሱፐር ሶኒክ ወይም ከድምጽ ፍጥነት አምስት እጥፍ በሆነ ፍጥነት በመተላለፊያ ውስጥ እንዲያልፍ ማድረግ ሲሆን ይህም ከፍተኛ ንዝረት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ ንዝረትም የአየርና የነዳጅ ውህዱ እንዲግልና ፍንዳታ እንዲፈጠር ያደርገዋል፡፡ በፍንዳታው ወቅት ከድምጽ ፍጥነት በበለጠ ፍጥነት ጋዝ ይወጣል፡፡ ይህን ጋዝ ከጄቶች ሞተር እንዲወጣ ማድረግ ነው ዋናው ሃሳብ እንደ ተመራማሪዎቹ መረጃ፡፡ እንዲህ ማድረግ ከተቻለ በከፍተኛ ፍጥነት የሚጓዙ ጄቶችን መስራት ይቻላል፡፡
በዚህ ጽንሰ ሀሳብ መሰረት የሚሰራው ጄት ከድምጽ ፍጥነት 17 እጥፍ በሚሆን ፍጥነት መጓዝ እንዲችል ያደርገዋል ሲሉ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ ይህ ፍጥነት ጄቱን በቀላሉ ያለምንም ሮኬት ወይም ማስወንጨፊያ ከምድር ከባቢ አየር ወደ ህዋ እንዲጓዝ ማድረግ ያስችላል፡፡
ምንጭ sciencealert
ተጨማሪ ንባብ https://www.sciencealert.com/move-over-thrusters-never...

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለ1 ሺህ 442ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን መልካም በዓልን እንመኝላችኋለን፡፡
ኢድ ሙባረክ!!!
ኢድ ሙባረክ!!!
ከቁጥጥር ውጪ ሆና እየሰመጠች ያለችው ሜክሲኮ ከተማ
=========================
የሀገረ ሜክሲኮ መዲና የሆነችው የሜክሲኮ ከተማ በፍጥነት እየሰመጠች ሲሆን አንዳንድ የከተማው ክፍሎችም ባሳለፍነው አስር ዓመታት ውስጥ በዓመት እስከ ግማሽ ሜትር ወደታች እየወረዱ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ታትሞ የወጣ አዲስ ጥናት እንደሚያመላክተው ለክፍለ ዘመናት ከዚህች ከተማ እንዲወጣ የተደረገው የከርሰ ምድር ውሃ የከተማዋ መሰረት በአሳሳቢ ፍጥነት እንዲኮማተር እያደረገው መሆኑን አስቀምጧል፡፡
የሜክሲኮ ከተማ የተገነባችው ቀድሞ ቴክስኮኮ ተብሎ ይጠራ በነበረ ሀይቅ ላይ ነው፡፡ ሆኖም ከተማዋ የቆመችበት የሀይቁ ወለል እጅጉን ከመድረቁ የተነሳ እየተሰነጣጠቀና እየተኮማተረ በመምጣቱም ከተማዋም በየጊዜው ወደታች እየሰመጠች እንድትመጣ አድርጓታል፡፡
የሜክሲኮ ከተማ ከ21 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን በመያዝ የሰሜን አሜሪካን በህዝብ ብዛት ትልቋ ከተማ ናት፡፡ ባለሙያዎች ከተማዋ እየሰመጠች መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋሉት እ.አ.አ በ1900 ነበር፡፡ ያኔ ከተማዋ በየዓመቱ ዘጠኝ ሴ.ሜ ትሰምጥ ነበር፡፡ ሆኖም የከርሰ ምድር ውሃን እስከቀነሰበት እስከ 1950ዎቹ ድረስ በ29 ሴ.ሜ እየሰመጠች ነበር፡፡ ኋላ ላይ ከርሰ ምድሯ የሚወጣው ውሃ እንዲቀንስ መደረጉ የምትሰምጥበትን ፍጥነት ዳግም ወደ 9 ሴ.ሜ ቢያወርደውም ችግሩን ግን አላቆመውም፡፡ እንዲያውም የከተማዋ ህዝብ ቁጥር እያደገ መምጣትና የልማት ስራዎች መስፋፋት ነገሩን ይበልጥ ተባብሶ እንዲቀጠውል አድርጎታል፡፡
አዲሱ ጥናት እንዳመላከተው ታድያ ታሪካዊ ክፍሏን ጨምሮ ከተማዋ በየዓመቱ በ40 ሴ.ሜ እየሰመጠች መሆኑን ነው፡፡ ሰሜን ምስራቃዊው የከተማዋ ክፍል ደግሞ ከዚህ በባሰ መልኩ በ50 እየሰመጠ ነው ሲል ይህ ጥናት አመላክቷል፡፡ ጥናቱን ያጠኑት የሜክሲኮና አሜሪካን ተመራማሪዎች የከተማዋ መስመጥ ከዚህ ወዲህ ከከርሰ ምድር እየወጣ ባለው ውሃ መጠን መብዛትና ማነስ የማይወሰን መሆኑን ለሁኔታው ከቁጥጥር ውጪ መውጣት በማሳያነት አስቀምጠውታል፡፡
ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ በውሃ እጦቱ ሳብያ የመጣው የመሬት ድርቀት እስካሁን ወለሉን በ17 በመቶ እንዲኮማተር ያደረገው ሲሆን ከዚህ በኋላም የከርሰ ምድር ውሃ መጠኑ እንዲያድግ የማይደረግ ከሆነ በተጨማሪ 30 በመቶ የሚኮማተር ይሆናል፡፡ ይህም ከተማዋ በሚቀጥሉት 150 ዓመታት ውስጥ ከፍታዋ በ30 ሜትር እንዲያሽቆለቁል ያደርጋል፡፡
ምንጭ፤ Daily Mail
ለተጨማሪ፤ https://www.dailymail.co.uk/.../Mexico-City-SINKING-Land...

የሰሞኑ ዝናብ እና የክላውድ ሲዲንግ ሙከራዎች ውጤታማነት
==========================
ከሰሞኑን በሀገራችን መነጋገርያ ሆኖ በሰነበተው የደመናን ማዝነብ ወይም ክላውድ ሲዲንግ ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ የበይነ መረብ ውይይት ዛሬ ተካሄደ፡፡ በውይይቱ ላይ በሰሞናዊው የደመናን ማዝነብ ሙከራ ከዚህ ቀደም በበልግ ወቅት ተመዝግቦ ከነበው የተሻለ ዝናብ ማግኘት ችለናል ያሉት አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል (በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የቴክኖሎጂ አማካሪ) በሙከራው ወቅቶች እስከ 2 ቶን ሀይድሮስኮፒክ ቁሶች ጥቅም ላይ መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡ በመንግስት በኩል ይህ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ሲውል የግብርናውን ዘርፍ መርዳትና የኃይል ማመንጫ ግድቦችን መሙላት በዋና ዓላማነት ተይዞ መሆኑን ያወሱት አቶ ዮዳሄ ለዚህም ይረዳ ዘንድ በየዕለቱ ሰሜናዊ አዲስ አበባ እና መላው የአባይ ተፋሰስን ጨምሮ በየዕለቱ ከ30 እስከ 40 ቦታዎች ላይ ደመናን የማዝነብ ስራው ሲከናወን ቆይቷል ብለዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ከሰሞኑን ሙከራዎች ባሻገርም ስለ ክላውድ ሲዲንግ ቴክኖሎጂ ምንነት፣ ለኢትዮጵያ ስለሚሰጠው ጥቅም፣ የዋጋው ጉዳይና ለህብረተስብ ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ ስለሚከናወኑ ስራዎች ዳሰሳ ተደርጓል፡፡ በክላውድ ሲዲንግ ምንነት እንዲሁም ስለ ደመና አፈጣጠር፣ ባህርያት እና ዓይነቶች ዙርያ በብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ውስጥ በሚቲዎሮሎጂስትነት የሚያገለግሉት አቶ ለታ በቀለ ገለፃ የሰጡ ሲሆን በቴክኖሎጂው ሀገራዊ አስፈላጊነት ረገድም የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ኃ/ማርያም፣ በተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን የሃይድሮሎጂና ውሃ ጥራት ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሰሙነሽ ጎላ እንዲሁም በግብርና ሚኒስቴር ውስጥ በአማካሪ ሚኒስትር ደኤታነት እያገለገሉ ያሉት አቶ ኢፋ ሙለታ ማብራርያ አቅርበዋል፡፡ ቴክኖሎጂው በተለይም ሀገራችን በተደጋጋሚ ድርቅ የምትመታ ከመሆኗና ምስራቃዊው የሀገራችን ክፍልም ዝናብ አጠር ከመሆኑ አንፃር በተለይም በግብርና ዘርፍ ከፍተኛ ጥቅምን እንደሚያጎናፅፍ በኃላፊዎቹ ተነግሯል፡፡ ከዚህም ባሻገር ግን ከዝናብ ተቀላቅሎ የሚመጣ በረዶን ለመከላከል፣ ጭጋግን ለመበተን እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች ላይ ጠቀሜታ አለው ተብሏል፡፡
ከቴክኖሎጂው ውድነት እና ተቋማቸውም ለዚህ መፍትሄ በማበጀት ረገድ ምን እየሰራ እንዳለ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ተወክለው የተገኙት አቶ ዋሲሁን በቀለ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ አቶ ዋሲሁን ቴክኖሎጂው ውድ ሊባል የሚችል ቢሆንም ከሚያስገኘው ጠቀሜታ አንፃር በአንፃራዊነት የተሻለ እንደሆነ አስቀምጠዋል፡፡ አያይዘውም ተቋማቸው የቴክኖሎጂውን ከፍተኛ ወጪ በመቀነስ ረገድ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ስለመሆኑ ተቋማቸው አንዳንድ የቴክኖሎጂው ግብዓቶችን እዚሁ በሀገራችን ለመስራት የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎችን ለአብነት ጠቅሰው ተናግረዋል፡፡
ውይይቱን ያስተባበሩትና በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ውስጥ በሳይንስ ጋዜጠኝነት እያገለገሉ ያሉት ወ/ት ፍሬህይወት ረታ ቴክኖሎጂውን ለማህበረሰቡ በማስተዋወቅ ረገድ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አብራርተዋል፡፡ እንደ ኢንስቲትዩት መሰል ውይይቶችን የማዘጋጀት እንዲሁም በቅርቡ ወደ ህብረተሰብ የሚደርሱ ቴክኖሎጂውን የተመለከቱ አስተማሪ ዘጋቢ ፊልሞችን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ጋር በመተባበር መዘጋጀታቸውንም ወ/ት ፍሬህይወት ተናግረዋል፡፡