የተለያዩ ሐገር በቀል ቋንቋዎችን ማወቅ የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ
************************************
ጎግል የተባለው የቴክኖሎጂ ኩባንያ በተለያዩ ሐገራት የሚገኙ ሀገር በቀል ቋንቋዎችን መማርና መረዳት የሚያስችል Woolaroo የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ አደረገ፡፡ የሐሳቡ ጥንስስ መሰረቱን ያደረገው በአውስትራሊያ ደቡብ ምስራቅ ግዛት በሆነችው ኩዊንስላንድ የሚነገርን Yugambeh የተሰኘ ቋንቋ ነው፡፡
ጥንታውያንና በአንድ በተወሰነ አካባቢ የሚነገሩ ቋንቋዎችን የቃላት ስብስብና የተለያዩ ፍችዎች ለመረዳት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ቋንቋ ከማህረሰባዊ እሳቤና የእድገት ደረጃ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ነው፡፡ በአውስትራሊያ ኩዊንስላንድም ያጋጠመው ችግርም እንዲሁ ነው፡፡ በቋንቋው ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ቃላትን ምንነት ለመረዳት ተማሪዎች በእጅጉ ሲቸገሩ ተስተውለዋል፡፡ ይህ ችግር በብዙ ሀገራ ሀገር በቀል ቋንቋዎችና ጥንታውያን ቋንቋዎች የተለመደ ነው፡፡
በዚህ የአውስትራሊያ ቋንቋ በተለይ ከቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ቃላት ትክ የሚሆን ቃል ማግኘት አስቸጋፈሪ ነው፡፡ ጎግልም ይህን ችግር ለመፍታት ይህንን የአውስትራሊያ ሀገር በቀል ቋንቋ የባህልና የስነጥበብ ጥናት ላይ የተመሰረተ Woolaroo ላይ የመጀመጀመሪያ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ አላማውም በ30 ዓመት ውስጥ ቋንቋው የነበረውን ይዘት ለመጠበቅና ከዘመናዊውና እያደገ ካለው አለም ጋር የተቀራረበ አቋም እንዲኖረው ለማድረግ ነው፡፡
በአውስትራሊያ የዩጋምብህ ቋንቋ ማእከል ተጠሪየሆኑት አልን ሌና መተግበሪያው የተለያዩ ጥቅሞች እንዳሉትና ከእነዚህም ጥቅሞች መካከል ቋንቋዎች ተጠብቀው እንዲቆዩ፣ ጨርሰው እንዳይጠፉ እና ከተለያዩ ባህሎችና ቋንቋዎች የሚመጡ ሰዎች ማጥናት የሚፈልጉትን ቋንቋ በቀላሉ እንዲረዱት በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የቋንቋና የባህል ውርርስ እንዲኖር ያስችላል ብለዋል፡፡
መተግበሪያው በየጊዜው ተጨማሪ ቃላትን መጨመር እንዲቻል ተደርጎ የተሰራ ሲሆን የእያንዳንዱን ቃል ትክክለኛ አነባበብ ማወቅ እንዲቻል የድምጽ ቅጅም ተካትቶበታል፡፡ በአሁኑ ሰዓት መተግበሪያው 10 የአለማችን ቋንቋዎችን ያካተተ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ Calabrian Greek, Louisiana Creole, Māori, Nawat, Tamazight, Rapa Nui, Sicilian, Yang Zhuang, Yiddish and Yugambeh የተባ የቋንቋ አይነቶች ይገኙበታል፡፡ የሀገራችንንም ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ቋንቋዎች በዚህ መተግበሪያ የሚካተቱበትና ተጠብቀው የሚቆዩበት እንዲሁም ለሌሎች ተደራሽ የሚሆኑበት መንገድ ቢኖር የሚለው የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ነው፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-05-google-woolaroo-tool-indigenous-languages.html?fbclid=IwAR1M7fQJ70sZ3BqgwEQC9SXw2JQQt1Ns9Au5CbKyQOjLJhUqzgyuvv_3AVg

Tech Xplore
Google introduces Woolaroo, a tool for learning indigenous languages
With many indigenous languages worldwide becoming endangered due to a dwindling number of native speakers, Google has introduced the app Woolaroo which focuses on learning these languages. The idea for ...
አፍጥርን ከእኛ ጋር
=========
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ቅዱሱን የረመዳን ወር በማስመልከት በዛሬው ዕለት የአፍጥር ፕሮግራምን አከናውኗል፡፡ ላምባዲና በተሰኘው የኢንስቲትዩቱ ሶሻል ኮሚቴ አማካኝነት የተዘጋጀው ይህ የአፍጥር ፕሮግራም በአዝናኝ መሰናዶዎች ታጅቦና መላው የተቋሙ ሰራተኞችን አሳትፎ ተከናውኗል፡፡
ከአፍጥር ስነ-ስርዓቱ ባሻገርም ተቋሙን ለሚሰናበቱ እንዲሁም በቅርቡ ጎጆ ለቀለሱ የኢንስቲትዩቱ ቤተሰቦች የሽኝት እና ስጦታ የማበርከት መርሀ ግብርም ነበረው፡፡
እኛም ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት የቀሩት ይህ ቅዱስ ወር መልካም ሆኖ ያልፍ ዘንድ ምኞታችንን እንገልፃለን፤ ረመዳን ከሪም!!!

እናቶች የሚወልዱበትን ቀን በደም ምርመራ ብቻ ማወቅ እንደሚቻል ተገለፀ
===========================
ብዙ ነፍሰጡር ሴቶች ልጃቸውን የሚወልዱበትን ቀን በጉጉት ይጠባበቃሉ፡፡ ምንም እንኳን በህክምናው ዓለም የአንድ እርግዝና ርዝማኔ ፅንሱ ከተቀፀነሰበት እለት አንስቶ ለ40 ተከታታይ ሳምንታት መሆኑ የተቀመጠ ቢሆንም አንዳንድ እናቶች ግን ከዚህ ባጠሩ ሳምንታት ሌሎቹ ደግሞ ረዘም አድርገው በእርግዝና ሲቆዩ ይታያል፡፡ ታድያ ሳይንሱ አንድ ቀን ነፍሰ ጡር ሴት ልጇን የምገላገልበትን ትክክለኛ ቀን በደም ምርመራ ብቻ ሊያሳውቃት እንደሚችል አዲስ ጥናት አመላክቷል፡፡
በአሜሪካኑ ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የምትሰራው ኢና ስቴልዘር ከሙያ አጋሮቿ ጋር ሆና የሰውነት አካላችን እንዴት ከፅንሱ ለሚመጡ ምልክቶች ምላሽ እንደሚሰጥና እራሱን ለውልጃ እንደሚያዘጋጅ በሚከታተል አዲስ ዘዴ ላይ ምርምር እየሰራች ትገኛለች፡፡ እንደኢና አነጋገር ከሆነ የመውለጃ ቀን የደረሰ ስለመሆኑ ደም ያመላክታል፡፡
የጥናት ቡድኑ ከ53 ነፍሰ ጡር ሴቶች ናሙና በመውሰድ በመጨረሻዎቹ 100 የእርግዝና ቀናቶች ውስጥ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ለሦስት ጊዜያት ያህል መርምረዋቸዋል፡፡ አጥኚዎቹ 5 ሺህ ያህል ባዮኬሚካሎችን የተመለከቱና 2 ሺህ ያህል ምርመራዎችንም በደም ውስጥ ባሉ የበሽታ መከላከያ ሕዋሳት ላይ ያደረጉ ሲሆን መጨረሻ ላይ ባገኙት ውጤት መሰረት ልጁ ከመወለዱ ከ2 እስከ 4 ሳምንታትን ቀደም ብሎ በደም ላይ ለውጦች መታየታቸውን ማስተዋል ችለዋል፡፡ ይህም ሲባል የነፍሰ-ጡሮቹ የሆርሞን ቅርፅ ተለውጧል፤ በበሽታ ተከላካይ ህዋሶች ዘንድ ያለው የማቃጠል እንቅስቃሴም ቀንሷል፡፡
አጥኚዎቹ 45 የውስጠ ሰውነት ማመላከቻዎችን (Biomarkers) ተጠቅመው ያበለፀጉትን የትንበያ መንገድ በ10 ሴቶች ላይ ሞክረውታል፡፡ መንገዱ በበኩሉ ነፍሰ ጡር ሴቶቹ በሚወልዱባቸው በ17 ቀናት ውስጥ ልጃቸው ይገላገሉበታል ያለውን ግምታዊ ጊዜ አስቀምጧል፡፡ ሆኖም አጥኚዎቹ አዲሱ መንገድ በተለያዩ እርግዝናዎች ላይ መስራቱን እስካሁን በሙከራ አላረጋገጡም፡፡
አዲሱ መንገድ ስኬታማ የሚሆን ከሆነ ስለ ፅንሱ ሁኔታ ስጋት የገባቸው ሀኪሞችን ሊረዳ ይችላል ተብሎለታል፡፡
ምንጭ፤ New Scientist
ለተጨማሪ፤ https://www.newscientist.com/article/2276534-blood-test-could-predict-when-pregnant-women-will-give-birth/?utm_medium=social&utm_campaign=echobox&utm_source=Twitter#Echobox=1620400060

New Scientist
Blood test could predict when pregnant women will give birth | New Scientist
Current due date predictions are made by counting 40 weeks from a woman's last period, but a blood test looking at 45 biomarkers could predict when labour will actually begin
ከጨዋማ ውሃ የኤሌክትሪክ ሃይል የሚያመርተው ፈጠራ
==================
ሶላርን መሰረት አድርገው ከሚሰሩ የቴክኖሎጂ አማራጮች አስተማማኝነቱ ይበልጥ ያይላል የሚባለው አዲሱ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ኢ ዲና በተሰኘ የኮሎምቢያ ስታርታፕ የበለጸገ ነው፡፡ ከጨዋማ ውሃ በተጨማሪ እጅግ አስፈላጊ በሚሆንበት ሰዓት እንደ ሽንት ባሉ የኢነርጂ ግብዓቶች ሊሰራ የሚችለው ይህ ተንቀሳቃሽ መሳሪያ በአዮናይዜሽን ሂደት (Ionization process) አማካኝነት የኤሌክትሪክ ሃይል ለመፍጠር የሚያስችል ግኝት ነው፡፡
ዋተር ላይት በሚል የተሰየመው አዲሱ ቴክኖሎጂ 500 ሚሊ ሌትር ጨዋማ ውሃ ከተደረገበት በኋላ በመሳሪያው ውስጥ ያሉት የማግኒዢየም እና ኮፐር ንጥረነገሮች ከጨዋማ ውሃው ጋር በሚኖራቸው የአዮናይዜሽን ፕሮሰስ የኤሌክትሪክ ሃይል እነዲፈጠር ያስችላሉ፡፡ መሳሪያው በአንድ የውሃ ሙሌት ለ45 ቀናት ብርሃን ማውጣት የሚችል ሲሆን በተገጠመለት የዩኤስቢ ማራዘሚያም ለስልክና ሌሎች ቀላል የኤሌክትሪክ እቃዎች ቻርጅ ለማድረግ ያስችላል፡፡
የዚህ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ዋና አለማ በኮሎምቢያ ገጠራማ ስፍራዎች የሚኖሩ አነስተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸው ዜጎችን ለመጥቀም የተሰራ መሆኑን የሚናገሩት የድርጅቱ ባለሙያዎች በተለይም በአካባቢው ለሚኖሩ የአሳ አጥማጆች እና ሸክላ ሰሪዎች በማታ ስራቸውን መከወን እንዲያስችላቸው እና ተማሪዎችም ጥናታቸውን በትክክል እንዲያካሂዱ በማለም መሳሪያው እንደተሰራ ይናገራሉ፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ ሶላርን መሰረት አድርገው ከሚሰሩ የቴክኖሎጂ አማራጮች ለየት የሚያደርገው ውሃውን ወደኤሌክትሪክ የሚቀይርበት ጊዜ አጨር መሆኑ እና በአንድ የውሃ ሙሌት ለረዥም ግዜ መስራቱ መሆኑን የሚናገሩት ባለሙያዎች ይህም በሶላር ሃይል ከሚሰሩ ቴክኖሎጂዎች አንፃር የተሻለ እንደሚያደርገው ይገልጻሉ፡፡
በአለማችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ላልተስፋፋባቸው ገጠራማ ስፍራዎች ጥቅም ይሰጣሉ ተብለው ከተለዩ የቴክኖሎጂ አማራጮች አንዱ የሆነው ዋተር ላይት በትንሽ ግብዓት 5,600 ለሚሆን ሰዓት ወይም በጥቅሉ ለሰሶት አመታት ብርሀን መስጠት የሚችል ቀላል ነግር ግን እጅግ ጠቃሚ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ነው፡፡
https://www.dezeen.com/.../waterlight-edina-wunderman.../....

Dezeen
WaterLight is a portable lantern that can be charged with salt water or urine
Colombian renewable energy start-up E-Dina has developed a cordless light that converts salt water into electricity to power off-grid communities.
ለዘጠኝ ወራት ያለማቋረጥ እየነደደ የተገኘው ዛፍ
=====================
በአሜሪካኗ የካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ ባለው የስኮያ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኝ አንድ የስኮያ ዛፍ አካባቢው ከወራት በፊት በሰደድ እሳት ተጠቅቶ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ውስጡ ፍም ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ተመራማሪዎች ዛፉን ያገኙት ከዘጠኝ ወራት በፊት በፈረንጆቹ የበጋ ወራት በአካባቢው የተከሰተው ሰደድ እሳት ብሔራዊ ፓርኩ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ለመመርመር ወደ ስፍራው ባቀኑበት ወቅት ነበር፡፡ ምንም አይነት መንገድ በአካባቢው ያልተገኘበት ዛፉ ያለማቋረጥ ሲጨስ ተመልክተውት ነው ተመራማሪዎቹ ሊያገኙት የቻሉት፡፡
የዛፉን ነገር አስገራሚ ያደረገው በእነዚህ ወራት ውስጥ አካባቢው ላይ ዝናብ እና በረዶ ሲፈራረቅበት ቆይቶ እንኳን በውስጡ ፍም ሆኖ መቆየቱ ነው፡፡
የዛፎች እሳት ሳይጠፋ መቆየት አዲስ ጉዳይ አይደለም፤ አንዳንድ ዛፎች በከባድ የሰደድ እሳት ከተቃጠሉ በኋላ በውስጣቸው ያለው እሳት በቂ ኦክስጅን እና ጥበቃ እያገኘ ስለሚቆይ ውስጥ ውስጡን በዝግት እየነደደ ሊከርም ይችላል፡፡ ሆኖም ይህ አይነት ሁናቴ ሰደድ እሳትን በደምብ በተላመዱትና የእሳት መከላከያ ቅርፊትን ተላብሰው በቆሙት የስኮያ ዛፎች ላይ መከሰቱ ነገሩን ለየት አድርጎታል፡፡
በመብረቅ አማካኝነት ባሳለፍነው ነሀሴ ላይ ተነስቶ በቁጥጥር ስር እስከዋለበት ወርሀ ታህሳስ ድረስ የቆየው ሰደድ እሳቱ 60,700 ሄክታር የሚሆን ስፋት ያለው አካባቢን አቃጥሎ አልፏል፡፡
ምንጭ፤ Live Science
ለተጨማሪ፤ https://www.livescience.com/giant-sequoia-tree-still...

የኒያ ፋውንዴሽን እና የጆይ ኦቲዝም ማዕከል መሥራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ ዘሚ የኑስ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
በኒያ ፋውንዴሽን ስር ጆይ የኦቲዝም ማዕከል የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት አቋቁመው ለበርካታ ወገኖች ደራሽ መሆን የቻሉት የጆይ ኦቲዝም ማዕከል መስራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ ዘሚ የኑስ የብዙ እናቶችን እንባ የተመለከቱ፣ ድምፅ አልባውን የልጆችን ስቃይ ያደመጡ፣ ኦቲዝም ምንም በማይታወቅበት ጊዜ ችግሩን ተረድተው የበኩላቸውን አስተዋፆኦ ለመወጣት የጣሩ እና የኦቲዝም የጤና እክል ያለባቸውን ልጆች በሚችሉት አቅም መርዳት የቻሉ እናት ነበሩ፡፡
በርካታ የኦቲዝም እክል ያለባቸውን ልጆች ይዞና ወላጆቻቸውንም እያገዘ የነበረው የኒያ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1994 ሲቋቋም ዋና ትኩረቱን በችግሩ ዙሪያ ማህበራዊ ግንዛቤ መፍጠር፣ የምክር አገልግሎት ማቅረብ አና ለወሳኔ ሰጪ አካላት የሎቢ ስራ ማከናወን ቢሆንም በጥቂት አመታት ውስጥ ፅህፈት ቤት በመክፈት ቀላል ቁጥር የሌላቸውን የኦቲዝም ተጠቂዎችን ለማቀፍ ችሏል፡፡ በሂደት በተሰሩ የማስፋፊያ ስራዎችም ማእከሉ ሌሎች ተጠቂዎችን በመጨመር መሰረታዊ የሚባሉትን የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና፣ ለንግግር መጎልበት የሚሰጥ ህክምና እና የመገንዘብ ባህሪን የሚያሳድግ ህክምና በመስጠት ብዙ ችግረኞችን ለመርዳት ችሏል፡፡
ማዕከሉ ከዚህ እንቅስቃሴው በኋላ በሂደት እየተፈጠረ በመጣው ንቅናቄና የግንዛቤ መስፋፋት ሰዎች ስለበሽታው እንዲያውቁ ከማድረጉም በተጨማሪ ሌሎች የሱን ፈለግ የተከተሉ ማዕከሎች እንዲመሰረቱ እና ስለጉዳዩ ያለው ትኩረትም እንዲጨምር ምክንያት ሆናል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የዚህን ፋውንዴሽን መንገድ ተከትለው ከተቋቋሙ ማዕከሎች ውሰጥ ነህምያ እና ብራይት ዋነኞቹ ሲሆኑ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ራሱ የኒያ ፋውንዴሽን የሚያሰራው ጆይ የኦቲዝም የልህቀት ማዕከል በመጪዎቹ ጊዚያት ብዙ ተጠቂዎችን ያግዛል ተብሎ የሚጠበቅ ነው፡፡ በዚህ ከባድና ውጣ ውረድ በተሞላበት መንገድ ላይ ትልቅ ህልም ይዘው ትልልቅ ስራዎችን መስራት የቻሉት ወ/ሮ ዘሚ የኑስ የብዙ ወላጆችን እንባ ያበሱና ስለኦቲዝም የነበረውን የተዛባ አመለካከት በራሳቸው ጥረት መቀየር የቻሉ እናት ናቸው፡፡
የኦቲዝም ታማሚ ልጃቸውን ለማሳደግ የተጋፈጡትን ከባድ ሕይወት በአደባባይ በመናገርና ለዘመናት ከህመሙ ጋር ተያይዞ የነበረውን አጉል እምነትና ዝምታ በመስበር ለብዙ ወገኖች ደራሽ የነበሩት ወ/ሮ ዘሚ የኑስ፣ በሚሊኒየም ኮቪድ-19 በፅኑ ህክምና ማዕከል ውስጥ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ለወ/ሮ ዘሚ የኑስ ቤተሰብና ወዳጆች መፅናናትን ይመኛል

አዲሶቹ የዴል ኩባንያ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች
***************************
ዴል የተሰኘው የኮምፒውተር አምራች ኩባንያ አላይንዌር የተሰኘውን የኮምፒውተር አይነት X-Series የተሰኘ ልዩ በሆኑ ቁሶች የተሰራና የተሸለ ብቃት ያለው ላፕቶፕ ኮምፒውተር አስተዋወቀ፡፡ ካምፓኒው በተጨማሪም 11ኛ ትውልድ የሆነውን m15 R6 የተሰኘ የአላይንዌር የላፕቶፕ አይነት አስተዋውቋል፡፡ ኮምፒውተሩም የኢንቴል ሲፒዩ እና RTX 3080 የሞባይል ግራፊክስ ያለው ነው፡፡
ድርጅቱ በ X-Series ኮምፒውተሩ ዙሪያ ተጨማሪ ሀሳቦችን ይፋ ያላደረገ ሲሆን የላፕቶፑን ዲዛይን በአጭር ቪዲዮ አቅርቧል፡፡ ኮምፒውተሩ በጋሊየም ሲልከን የተሰራ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከነበሩት ላፕቶፖች ብዙ መሻሻሎች የተደረጉበት ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል በላፕቶፑ ውስጥ የተገጠመው የንፋስ እንቅስቃሴ ኮምፒውተሩ በጥሩ ብቃት እንዲሰራ ያስችለዋል ተብሏል፡፡ በኮምፒውተሩ ዋጋ እና ለገበያ የሚቀርብበትን መረጃ የተመለከተ መረጃ ግን እስካሁን ይፋ አልተደረገም፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ዴል m15 R6 የተሰኘው ላፕቶፑን የተለያዩ መገለጫዎች ይፋ አድርጓል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የኢንቴል 11ኛ ትውልድ ሲፒዩ፣ 6-core i5-11400H፣ 6-core i5-11400H እና 8-core i9-11900H ሲፒዩ ያላቸውና ከ RTX 3050 እስከ RTX 3080 GPUs ያላቸው እንደሆኑ ይፋ ተደርጓል፡፡ ላፕቶፑ 32 ጂቢ ራም (በተጠቃሚው ከፍ ሊል የሚችልና) 4 ቴራ ባይት መረጃ የማከማቸት አቅም ያለው ነው፡፡
m15 የተሰኘው አላይንዌር ላፕቶፕ በ1300 ዶላር በቅርብ ለገበያ ይቀርባል ተብሏል፡፡ እንዲሁም ደግሞ ዴል G15 የተሰኘ ለተለያዩ ጌሞች የሚያገለግል ላፕቶፕን ይፋ አድርጓል፡፡ ይህም ሞዴል የራሱ መገለጫዎች ያሉት ሲሆን ከ950 ዶላር ጀምሮ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡
ምንጭ engadget
ተጨማሪ ንባብ https://www.engadget.com/dell-alienware-x-series-laptops-exotic-cooling-110043070.html?fbclid=IwAR1Vy7SmR8gLCWPXt-4-FhPBi8lvWosTA5nZu7DJnt9AFJ72QKhx7xJ9XiU
Engadget
Alienware teases new X-Series laptops with exotic cooling solution | Engadget
Dell has teased an upcoming Alienware laptop lineup called the X-Series offering improved thermal performance using new materials..
የስራ ብቃት በኢንዱስትሪ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን
********************************
በአሜሪካ በፋብሪካዎች የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክንያት እስከ 2030 ድረስ 2.1 ሚሊዮን የሚሆኑ የስራ ቦታዎች ክፍት እንደሚሆኑ ተነገረ፡፡ ባለፈው የኮቪድ አንድ አመት ውስጥ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ 578 ሺህ የሚሆኑ የስራ ዘርፎች ተቋርጠዋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ አምስት መቶ ሺህ የሚሆኑ የማኑፋክቸሪንግ የስራ ዘርፎች ያለ ሰራተኛ ክፍት ሆነው ቆያተዋል፡፡
በዘርፉ የተሰራ አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው በአሜሪካ የሚገኙ ከ800 በላይ በማኑፋክቸሪንግ ላያ የተሰማሩ አሰሪዎች በስራቸው ያለውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ወይም በኢዱስትሪዎች እያደገ የመጣውን ሽግግር መላመድና መቋቋም የሚችሉ ክህሎት ያላቸው ሰዎችን ማግኘት እየተቸገሩ ነው፡፡ በተለይ ከ2018 ጀምሮ 36 በመቶ የሚሆኑ የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ብቃት ያላቸው ሙያተኞችን እያገኙ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ ብቃት ያላቸውን ሰዎች ወደ ድርጅታቸው ለመሳብ በሚደረግ ጦርነት (ውድድር) ውስጥ መግባታቸውን ከ77 በመቶ በላይ የሚሆኑ የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ያናገራሉ፡፡ እነዚህ ድርጅቶች ሙያተኞቻቸውን በተለያዩ ስልጠናዎች ከማብቃት ጎን ለጎን ተፈጥሯዊ ብቃት ያላቸውን ሰዎች እያሰሱ እንደሆነ ያነገራል፡፡
በኢንዱስትሪዎችና በተለያዩ አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያለው መረጃ እንደሚያሳየው በአሜሪካ በተለያም 44 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛ ተቋማት በተለያዩ ደረጃዎች ክፍት የስራ መደቦች እንዳላቸው እየተናገሩ ነው፡፡ ይህም ባፉት 48 ዓመታት ውስጥ ያልታየ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የአሜሪካ የሰራተኞች መረጃ ቢሮ በያዝነው ሳምንት ባወጣው መረጃ መሰረት 266 ሺህ በመጋቢት ወር ብቻ የተጨመሩ ናቸው ተብሏል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በኢንዱስትሪዎች ውስጥ ሲተገበር ለዚህ የሚመጥን ብቃት ያላቸው ሙያተኞችም በዚያው ልክ ቁጣራቸው መጨመር እንዳለበት ነው፡፡ የአሜሪካው የስራ ክፍተት ከዚህ በተጨማሪ ከእናቶችና እድሜያቸው ለትምህርት ካልደረሱ ህጻናት ጋር የተያያዘ መገለጫ እንዳለውም የመረጃ ምንጫችን ጠቁሟል፡፡
ምንጭ fortune
ተጨማሪ ንባብ https://fortune.com/.../the-war-for-talent-hits.../...

የድሬደዋ አሜሪካን ኮርነር ክላውድ ሲዲንግን አስመልክቶ በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ባሰናዳው የዙም ውይይቱ ላይ ተሳተፉልኝ ሲል ሁላችሁንም ጋብዟችኋል፡፡ በክላውድ ሲዲንግ ቴክኖሎጂ ምንነትና አሰራር ላይ አተኩሮ በሚካሄደው በዚህ ክፍለ አህጉራዊ ውይይት ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት፣ ግብርና ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ የሚቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ እና ሌሎችም የመንግስት ተቋማት የተወከሉ ኃላፊዎች እንደሚገኙበት ይጠበቃል፡፡ ውይይቱ አርብ ግንቦት 6 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 03፡00 አንስቶ የሚደረግ ሲሆን እርስዎም ከታች በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡
Dire Dawa American Corner is inviting you to a scheduled Zoom Program.
Topic: Cloud Seeding technology and how it works
Time: May 14, 2021 09:00 AM Addis Ababa Time
Join here
https://statedept.zoomgov.com/j/1610459433?pwd=bmg4cEZPQXVud2hCL3I1UTFVZ3M2dz09
Dire Dawa American Corner!
Meeting ID: 161 045 9433
Passcode: 635837

Zoom Video
Join our Cloud HD Video Meeting
Zoom is the leader in modern enterprise video communications, with an easy, reliable cloud platform for video and audio conferencing, chat, and webinars across mobile, desktop, and room systems. Zoom Rooms is the original software-based conference room solution…