ቴክኢን ወግ
======
የዚህ ሳምንቱ ቴክኢን ወግ ዝግጅታችን “physical activities and sedentary behavior” በሚል ርዕስ 4 ኪሎ በሚገኘው የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዋና ፅ/ቤት ይቀርባል፡፡ በአቶ ናኦል ከበደ መሪነት በሚቀርበው በዚህ መሰናዶ ላይ የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች እና ተጋባዥ እንግዶች እንደሚገኙበት የሚጠበቀቅ ሲሆን የተሳታፊነት ዕድሉ ለእርሰዎም ክፍት መሆኑን አውቀው እንዲቀላቀሉን ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ቀን፤ ሐሙስ ሚያዝያ 28 2013
ሰዓት፤ 03፡00 እስከ 4፡30
This week's techin seminar will be hosted in our office (located around 4 killo) with a title of “physical activities and sedentary behavior”. The event, led by Mr. Naol Kebede, is expected to be attended by our researchers invited guests, and knowing that the opportunity is open to you as well we invite you to join us for it.
Date: Thursday, May 6, 2021
Time: 09:00-10:30 AM

ጅግጅጋ በሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር ቀዳሚ ሆናለች
==========================
የጅግጅጋ ከተማ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ከሚገኙ ሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች አንጻር ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ያለበት ከተማ መሆኗ ተገልጿል፡፡ የጅግጅጋ ከተማና ነዋሪዎቿ እንደ ሄሎ ካሽ፣ ሳሂ እና ኢ-ብር የሞባይል ባንኪንግና ክፍያ ስርዓቶችን በመጠቀም በሀገሪቱ ካሉ የተለያየ ከተማ ነዋሪች የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ በብዛት በቀዳሚነት መሰለፏን የኢትዮጵያን ሄራልድ ያወጣው ዘገባ ያሳያል፡፡
የሶማሌ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው ጅግጅጋ ዋና ዋና መንደሮች እና አደባባዮች በተለያዩ በሞባይል ባንኪንግ ማስታወቂያዎች የተሸፈኑ መሆናቸውን ያወሳው ዘገባው አብዛኞቹ የኤሌክትሮኒክስ መሸጫ ሱቆች፣ የጅምላ ሻጮች፣ ነጋዴዎች እና ሌሎችም የንግዱ አካላት በከተማው ውስጥ የሞባይል ባንኪንግን በመጠቀም የንግድ ግብይትና የቁሳቁስ ልውውጥ እያካሄዱ እንደሚገኝ አስቀምጧል፡፡
በጅግጅጋ ከተማ ለሚኖሩ ዜጎች የሞባይል ባንኪንግና ክፍያ ስርዓቶችን በማቅረብ ፈር ቀዳጅ የሆኑትና የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት ሄሎ ካሽ እና ሳሂ ሲሆኑ ከዚህ በተጨማሪም ኢ-ብር በተከታይነት ይገኛል፡፡ እነዚህ የሞባይል ባንኪንግና ዲጂታል የክፍያ ስርዓት አቅራቢዎች በከተማዋ አብዛኛዎቹ ቦታዎች የአገልግሎት ማዕከል በመክፈት ሰፊ እንቅስቃሴ የሚደርጉ ሲሆን፤ በወናነትም የአየር በረራ ትኬቶችን ለመቁረጥ፣ የሞባይል ካርድ ለመሙላት፣ የኤሌክትሪክ ቢል ፍጆታዎችን ለመክፈል እና ሌሎች የዕለት ተዕለት እንቅስቀቃሴዎችን ለማሳለጥ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጡ ይገለፃል፡፡
ለአብነት በዚህ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ውስጥ ከፍተኛ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች እንዲኖሩ በዋናነት እየሰሩ ከሚገኙ ድርጅቶች መካከል ቀዳሚ የሆነው ሳሂ ከጅግጅጋ ከተማ በተጨማሪ ተጎራባች በሆኑ እንደ ድሬዳዋ፣ ሃረር እና ምስራቅ ሀረርጌ አከባቢዎች የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን በቀጣይም በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች አገልግሎቱን ለማስፋት እቅድ እንዳለው ጥያቄ የቀረበላቸው አንድ የድርጀቱ ባለሙያ ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፡ The Ethiopian Herald
https://www.press.et/english/?p=34172#

ያለዲፕሎማ ሄሊኮፕተር፣ መኪና እና ድሮን መስራት የቻለው አፍሪካዊ
============================
የአፍሪካ ምድር አስደናቂ ተሰጥዖ ያላቸው ነገር ግን ወተው መታየት ያልቻሉ ብዙ የፈጠራ ሰዎችን ይዛለች፡፡ አንዳንዶች ተሰጥዖ የታከለበትን ፈጠራቸውን ለፍሬ ሳያበቁ በተለያዩ እክሎች ምክንያት ተሰናክለው ሲቀሩ ሌሎች ጥቂቶች ደግሞ ይህን ልዩ አቅምና ችሎታ ወደውጤት በመቀየር አስገራሚ ታሪክ ይፅፋሉ፡፡ ይህ እውነታ ከታየባቸው ጥቂት ሰዎች መካከል የዚምቧብዌ ተወላጁ ማክስዌል ሳንጉላኒ ቺኩምቡስቶ እንደምሳሌ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
ይህ ግለሰብ ከልጅነቱ አንስቶ ከቴክኖሎጂው ዓለም ጋር በፍቅር አንዲወድቅ የአባቱ የመካኒክ ባለሙያነት አስተዋፅዖ ቢኖረውም በተፈጥሮ ያገኘው ልዩ የፈጠራ ችሎታና በዚህ ላይ ደግሞ ደጋግሞ የመሞከር ዝንባሌው አሁን ለደረሰበት ትልቅ ደረጃ ዋና ምክንያቶች ናቸው፡፡ በሃራሬ ከተማ ኩድዝዋና በተባለች መንደር ያደገው ይህ የፈጠራ ሰው እንደሌሎች የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች አሁን በሚሰራበት ዘርፍ በዲግሪ ወይም በዲፕሎማ መመረቅ ሳያስፈልገው በተሰጠው ልዩ ችሎታ እና ደጋግሞ የመሞከር ብቃት ብቻ ለማመን የሚከብዱ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ማበልፀግ የቻለ ኢኖቬተር ነው፡፡
ማክስዌል ሳንጉላኒ ቺኩምቡስቶ በህጻንነቱ ሲሞክራቸው ከነበሩ ቀላል ፈጠራዎች ተነስቶ ራሱን ወደቴክኖሎጂው አለም ይበልጥ የሚያቀርብበትን የኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ትምህርቶች ገና በልጅነቱ መለማመድ ቻለ፡፡ ከዚህ በኋላ ከአመታት ሙከራ እና ራስ ላይ የመስራት ጊዜያት በኋላ Saith Technologies የተባለ የግል ድርጅት በማቋቋም በኢነርጂና የኮምፒውተር ግንኙነት ቴክኖሎጂዎች ላይ በጥልቀት መስራት ጀመረ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በቅጡ መጨረስ እንኳን ያልቻለው ማክስዌል እንደ ሄሊኮፕተር እና መኪና ያሉ ውስብስብ ቴክኖሎጂዎችን ባቋቋመው ኩባንያ አማካኝነት መስራት ችሏል፡፡ የሰራት ሄሊኮፕተር ሁለት መቀመጫ ያላት ስትሆን ስድት የዘይት አይነቶችን መቀበል የምትችል እና ሃይብሪድ ኢንጂን የተገጠመላት ሄሊኮፕተር ናት፡፡
ይህ የፈጠራ ባለሙያ ለእይታ ያበቃት መኪና እና ራስ-ገዝ የሆነቸው የመከታተያ ድሮን በ Saith Technologies ዲዛይን በተደረገና በበለፀገ ግሪነር ፓወር ማሽን በተባለ የታደሽ ሃይል አማራጭ የተከናወኑ አስገራሚ ፈጠራዎች ናቸው፡፡ ትልቅ ህልም ይዞ ትልልቅ ፈጠራዎችን ለሀገሩና ለአፍሪካ ህዝቦች ማቅረብ የሚፈልገው ማክስዌል ከዚምቧብዌ መንግስት ፍቃድ ካገኘ በኋላ የቴክኖሎጂ ስራዎቹን በበሰፊ ስኬል በማምረት ከሌሎች የአውሮፓ፣ አሜሪካና እስያ ኩባንያዎች ጋር መወዳደር እንደሚፈልግም ይናገራል፡፡
https://zambiareports.com/.../without-diploma-african.../

Zambia Reports
WITHOUT A DIPLOMA, AN AFRICAN BUILDS A HELICOPTER, A CAR AND A DRONE | Zambia Reports
The latest news, politics, business, and opinion from Zambia
የወደፊቱ ሞተር አልባ የአየር ትራንስፖርት
***************************
ተመራማሪዎች የአዮን ድራይቭን ብቻ በመጠቀም የለምንም ተንቀሳቃሽ ክፍልና ያለ ነዳጅ በረራ ሊያደርግ የሚችል አውሮፕላን መስራታቸው ተሰማ፡፡ በማሳቹሴት የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የሚገኝ በሰቴቨን ባሬት የሚመራ አንድ የምርምር ቡድን በኤሌክትሮኤሮዳይናሚክስ የሚንቀሳቀስ ምንም አይነት የአውፕላን ሞተር ወይም ነዳጅ የማይጠቀም አውሮፕላን መስራታቸውን ተናግረዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ የወደፊቱ የአየር ትራንስፖርት ከባድ ሞተሮችን፣ ተርባይኖችንና ነዳጅን የማይጠቀም እጅግ ዘመናዊ ልክ እንደ ባለጅራት ኮከቦች የሚንቀሳቀስ መሆን አለበት ብለው እንደሚያምኑ የጥናታቸውን ውጤት ይፋ ባደረጉበት ወቅት ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊት በ1921 ተመራማሪዎች የልተሳካ ሙከራን በዘርፉ ያካሄዱ ሲሆን በወቅቱ የነበረው የቴክኖሎጂ አለመዘመን ለሙከራው አለመሳካት ከፍኛ ድርሻ ነበረው፡፡ አሁን ላይ ያለው የቴክኖሎጂ ልህቀት ለዘርፉ ምርምር መፍትሔ ይዞ መጥቷል፡፡
ከ2016 እስከ 2018 በተደረገ ሙከራ የክንፍ ርዝማኔው አምስት ሜትር ወይም 16 ጫማ የሆነና አጠቃላይ ክብደቱ 2.45 ኪሎግራም የሆነ አውሮፕላን ሰርተው ነበር፡፡ ይህ አውሮፕላን በፊት ለፊቱ በኩል በ20,000 ቮልት ፖዘቲቭ ቻርጅ የተደረጉ ቀጫጭን ገመዶች ሲኖሩት በኋለኛው በኩል ደግሞ በኔጌቲቭ 20,000 ቻርጅ የተደረገ በመደበኛው አውሮፕላን እንዳለው አይነት ኤሮፎይል አለው፡፡ ይህም ጠንካራ የሆነ ኤሌክትሪካዊ ከባቢ (electric field) እንዲኖር ያደርጋል፡፡
በፊት ለፊት በኩል በከባቢ አየሩውስጥ ከሚገኙ የናይትሮጅን ሞሎኪዮሎች ኤልክትሮኖች በመውጣት አዮኖችን ይፈጥራሉ፡፡ እነዚህም በፍጥነት ወደ ኋላ በመሄድ አውሮፕላኑ እንዲንቀሳቀስ የሚያስችለውን አዮናዊ ንፋስ ይፈጥራሉ፡፡ ሀሳቡም የመነጨው ከአየር ውስጥ ኤሌክትሮንን በማውጣት አየሩን በአዮኖች መሙላት በኤሌክትክ ቻርጅ አማካኝነት አየሩን ማንቀሳቀስ ይቻላል ከሚለው እሳቤ ነው፡፡
ከ10 ጊዜ በላይ በተደረገ ሙከራም አውሮፕላኑ በ12 ሴኮንዶች 60 ሜትር መብረር መቻሉን ተመራማሪዎቹ አስረድተዋል፡፡ በሀሳብ ደረጃ ከመደበኛው የመንገደኞች አውሮፕላን የፈጠነና በሰዓት 1080 ኪሎሜትሮችን መጓዝ ይችላል የሚል ግምት እንዳላቸው ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/technology/scientists-have-created-a-star-treklike-plane-that-flies-using-ion-thrusters-and-no-fuel/page-2/

IFLScience
Scientists Have Created A Star Trek-Like Plane That Flies Using "Ion Thrusters" And No Fuel
Scientists have taken a major step towards creating an aircraft of the future, one powered by an ion drive rather than using moving parts and fuel like con
በስራ ቦታ በቂ እንቅስቃሴ አለማድረግ፤ መዘዙና መፍትሄው
=======================
ዛሬ በተከናወነው የሳምንቱ ቴክኢን-ወግ መሰናዶ የሰራተኞች በስራ ቦታ ላይ የአካከል ብቃት እንቅስቃን ሳያደርጉ መቅረት በጤና ላይ ያለውን ጠንቅ እና ይህንንም መቅረፍ በሚቻልበት መንገድ ላይ አተኩሮ ቀርቧል፡፡ “physical activities and sedentary behavior” በሚል ርዕስ በአቶ ናኦል ከበደ ገለፃ አቅራቢነት የተከናወነው ይህ መሰናዶ የኢንስትዩቱ ኃላፊ እና ተመራማሪዎችን ተሳታፊ አድርጎ ተከናውኗል፡፡
አቶ ናኦል በገለፃው በስራ ቦታ ላይ ያለ በቂ እንቅስቃሴ የምንቆይበት የህይወት ዘይቤያችን ተፅዕኖውን ወድያው የምናየው ሳይሆን በጊዜ ሂደት የሚመጣና ጉዳቱም ምናልባት ኋላ ላይ በአካል ብቃት እንቅስቃሴም ጭምር ሊመለስ የማይችል መሆኑን ተናግሯል፡፡ በዚህም የሰራ ቦታ ላይ ያለ በቂ እንቅስቃሴ ለረጅም ጊዜ መቀመጡ በእግር እና የጀርባ አጥንት እንዲሁም ጡንቻዎች ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባሻገር እንደ ስኳር፣ ውፍረት፣ ደም ግፊት እና ጭንቀት ያሉ በሽታዎችን እንደሚያስከትል ተናግሯል፡፡ ይህም በየዓመቱ በዓለማችን 2 ሚሊዮን ሰው ህይወቱን እንዲያጣ ምክንያት ስለ መሆኑ አቶ ናኦል ተናግሯል፡፡
አቶ ናኦል ለነዚህ ሁሉ ችግሮች መፍትሄ ይሆናሉ ያላቸውን የቢሮ ውስጥ እንቅስቃሴ ምክረ ኃሳቦችን የለገሰ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘም ቀላል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነቶች ለታዳሚው በእንቅስቃሴ መልክ በማሰራት አሳይቷል፡፡ በቀጣይም እንደ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሊደረጉ ይገባቸዋል ያላቸው የመፍትሄ ሐሳቦችን አስቀምጧል፡፡
በዛሬው የቴክኢን ወግ በቀረበው ገለፃ ዙርያ ሐሳባቸውን ለታዳሚው ያካፈሉት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ተሾመ ሳህለማርያም አነስተኛ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ባለው አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ አመራር በመድረኩ የቀረቡ የመፍትሄ ሐሳቦችን ተቀብሎ እንደሚሰራባቸው የተናገሩት ኢ/ር ተሾመ ወደፊትም ለሰራተኞች የሚሆን ጂም የመገንባት እንቅስቃሴ መኖሩን አስታውቀዋል፡፡

ብዙ ጨው መመገብ የሰውነት የበሽታ መከላከል አቅምን እንደሚያዳክም አዲስ ጥናት አመላከተ
========================
ከዚህ ቀደም ከበቂ በላይ ሶዲየምን መመገብ እንደ ደም ግፊት፣ ስትሮክ፣ ልብ ድካም፣ የሆድ ካንሰር እና የኩላሊት በሽታ ካሉት ጋር ሲገናኝ ቆይቷል፡፡ ታድያ አዲሱ ጥናት እንደሚለው የበዛ ጨውን መመገቡ የበሽታ መከልከል ስርዓታችን ሕዋሳት ማምረት የሚችሉትን የኃይል መጠን በመቀነስ ተግባራቸውን በተለምዶው መልኩ ለማከናወን እንዳይችሉ ያግዳቸዋል፡፡
ከጥቂት ዓመታት በፊት የጀርመን አጥኚዎች የጨው በደም ውስጥ መከማቸት ሞኖሳይት በተባሉት የበሽታ መከላከያ ስርዓታችን ሕዋሳት ቡድን ላይ በቀጥታ ተፅዕንዖን እንደሚያሳድር ማወቅ ችለው ነበር፡፡ በአዲሱ ጥናት ታድያ ይህ እንዴት እንደሆነ የሚያጤኑ ምርምሮች ተከናውዋል፡፡ በመጀመሪያ ተመራማሪዎቹ በቤተ-ሙከራ ውስጥ የአይጥ እና የሰው ልጆች ሞኖሳይቶች ላይ ምልከታን ያደረጉ ሲሆን በዚያም ከሦስት ሰዓታት ከፍተኛ የጨው ክምችት ተጋላጭነት በኋላ የበሽታ ተከላካይ ሕዋሳቱ ያነሰ ኃይልን ወይም አዴኖሲን ትራይፎስፌት (ATP) ማምረት መጀመራቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የኃይል ምንጭ የሆነው ማይቶኮንድሪያ የተለያዩ የኬሚካል አፀግብሮቶችን በመጠቀም ከሚያገኘው ምግብ ውስጥ አድሬኖሲን ትሪዮስፌትን ያመርታል፡፡ አድሬኖሲን ትሪዮስፌት በበኩሉ ለጡንቻዎች ኃይል እንደማቅረብ ያሉ ተግባራትን ይከውናል ሲል ጥናቱ ያትታል፡፡
አጥኚዎቹ የሰው ልጆች ላይ ባደረጉት ሙከራ ጤናማ ሰዎችን በመሰብሰብ ለሁለት ሳምንታት የህክምናው ዓለም ከሚመክረው በሦስጥ እጥፍ በላቀ መልኩ በየዕለቱ 600 ሚሊ ግራም ጨው እንዲወስዱ ሲያደርጓቸው ቆይተዋል፡፡ በሌላ ሙከራም ሌሎች ተሳታፊዎች ከጣልያን ምግብ ቤት የመጣላቸውን ሙሉ ፒዛ እንዲመገቡ ሆነ፡፡
በውጤቱ መሰረት በውስጡ 10 ሺህ ሚ.ግ ጨው የሚይዘውን ሙሉ ፒዛ ከተመገቡ በኋላ የጥናቱ ተሳታፊዎች የሚያመነጩት ኃይል አሽቆልቁሎ ተገኘ፡፡ ሆኖም ተፅዕንዖው ለብዙ ጊዜ የቆየ አልሆነም፤ ፒዛውን ከበሉ ከስምንት ሰዓታት በኋላ ማይቶኮንድሪያቸው ስራውን እንደቀድሞው ወደማከናን መግባት ችሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን አንድ ሰው ከፍተኛ የጨው መጠን ያለው ምግብን በተከታታይ እየተመገበ መቆየቱ ማይቶኮንድሪያን በዘላቂነት ሊጎዳው መቻሉ አልተረጋገጠም፡፡ ታድያ አጥኚዎቹም ማይቶኮንድሪያ በሁሉም ለማለት በሚያስችል ደረጃ የሰውነታችን ሕዋሳቶቻችን ውስጥ እንደመገኘታቸው ጨው ሌሎች ሕዋሳቶቻችን ላይም ተፅዕኖውን ማሳረፍ ይችል ይሆን የሚለውን ለማወቅ ያልማሉ፡፡
ምንጭ፤ Live Science
ለተጨማሪ፤ https://www.livescience.com/salt-disrupts-immune-cell...

ቴክ-ሳይንስ
======
በዚህ ሳምንቱ የቴክ-ሳይንስ ቴሌቪዥን ፕሮግራማችን እንደተለመደው ለእርስዎና ቤተሰብዎ ይመጠጥናሉ ያልናቸውን መልከ ብዙ የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መሰናዶዎች በሚከተለው መልኩ አዘጋጅተን እየጠበቅንዎ እንገኛለን፤
በአብይ ፕሮግራም፡ የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ከፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ወደ ዩኒቨርሲቲ ማደጉን አስመልክቶ ስለተዘጋጀ ሲምፖዚየም፤
በብላቴናት፡ የኮምፒውተር ሲስተም የሰራ ታዳጊ፤
በቴክኖሎጂ ታሪክ፡ ስለ ሮኬት፤
በተመራማሪዎች የህይወት ታሪክ፡ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ውስጥ የአፈር ተመራማሪ ስለሆኑት ፕሮፌሰር ሸለመ በየነ፡፡
ታድያ ከነገ ቅዳሜ 10 ሰዓት አንስቶ የቻናል ምርጫዎን MOE ቴሌቪዥን ላይ በማድረግ እነዚህ ለእርስዎና መላው ቤተሰብዎ የተስማሙ ዝግጅቶችን መከታተል ይችላሉ፡፡ ቀንና ሰዓቱ አልመች ያልዎት እንደሆነም በዕለተ ማክሰኞ ከቀኑ 10 ሰዓት በድጋሚ ስለሚተላለፍ ሳይቸገሩ ያገኙናል፡፡
ከነዚህ የቴሌቪዥን ስርጭቶች በተጨማሪ ወደ ዩትዩብ ቻናላችንም በማቅናት አዳዲሶቹን ጨምሮ ላለፉት ዓመታት የተሰሩትን ፕሮግራሞች በሙሉ መመልከት ይችላሉ (https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg)፡፡

YouTube
EthioTunes
Share your videos with friends, family, and the world
የተለያዩ ሐገር በቀል ቋንቋዎችን ማወቅ የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ
************************************
ጎግል የተባለው የቴክኖሎጂ ኩባንያ በተለያዩ ሐገራት የሚገኙ ሀገር በቀል ቋንቋዎችን መማርና መረዳት የሚያስችል Woolaroo የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ አደረገ፡፡ የሐሳቡ ጥንስስ መሰረቱን ያደረገው በአውስትራሊያ ደቡብ ምስራቅ ግዛት በሆነችው ኩዊንስላንድ የሚነገርን Yugambeh የተሰኘ ቋንቋ ነው፡፡
ጥንታውያንና በአንድ በተወሰነ አካባቢ የሚነገሩ ቋንቋዎችን የቃላት ስብስብና የተለያዩ ፍችዎች ለመረዳት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ቋንቋ ከማህረሰባዊ እሳቤና የእድገት ደረጃ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ነው፡፡ በአውስትራሊያ ኩዊንስላንድም ያጋጠመው ችግርም እንዲሁ ነው፡፡ በቋንቋው ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ቃላትን ምንነት ለመረዳት ተማሪዎች በእጅጉ ሲቸገሩ ተስተውለዋል፡፡ ይህ ችግር በብዙ ሀገራ ሀገር በቀል ቋንቋዎችና ጥንታውያን ቋንቋዎች የተለመደ ነው፡፡
በዚህ የአውስትራሊያ ቋንቋ በተለይ ከቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ቃላት ትክ የሚሆን ቃል ማግኘት አስቸጋፈሪ ነው፡፡ ጎግልም ይህን ችግር ለመፍታት ይህንን የአውስትራሊያ ሀገር በቀል ቋንቋ የባህልና የስነጥበብ ጥናት ላይ የተመሰረተ Woolaroo ላይ የመጀመጀመሪያ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ አላማውም በ30 ዓመት ውስጥ ቋንቋው የነበረውን ይዘት ለመጠበቅና ከዘመናዊውና እያደገ ካለው አለም ጋር የተቀራረበ አቋም እንዲኖረው ለማድረግ ነው፡፡
በአውስትራሊያ የዩጋምብህ ቋንቋ ማእከል ተጠሪየሆኑት አልን ሌና መተግበሪያው የተለያዩ ጥቅሞች እንዳሉትና ከእነዚህም ጥቅሞች መካከል ቋንቋዎች ተጠብቀው እንዲቆዩ፣ ጨርሰው እንዳይጠፉ እና ከተለያዩ ባህሎችና ቋንቋዎች የሚመጡ ሰዎች ማጥናት የሚፈልጉትን ቋንቋ በቀላሉ እንዲረዱት በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የቋንቋና የባህል ውርርስ እንዲኖር ያስችላል ብለዋል፡፡
መተግበሪያው በየጊዜው ተጨማሪ ቃላትን መጨመር እንዲቻል ተደርጎ የተሰራ ሲሆን የእያንዳንዱን ቃል ትክክለኛ አነባበብ ማወቅ እንዲቻል የድምጽ ቅጅም ተካትቶበታል፡፡ በአሁኑ ሰዓት መተግበሪያው 10 የአለማችን ቋንቋዎችን ያካተተ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ Calabrian Greek, Louisiana Creole, Māori, Nawat, Tamazight, Rapa Nui, Sicilian, Yang Zhuang, Yiddish and Yugambeh የተባ የቋንቋ አይነቶች ይገኙበታል፡፡ የሀገራችንንም ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ቋንቋዎች በዚህ መተግበሪያ የሚካተቱበትና ተጠብቀው የሚቆዩበት እንዲሁም ለሌሎች ተደራሽ የሚሆኑበት መንገድ ቢኖር የሚለው የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ነው፡፡
ምንጭ techxplore
ተጨማሪ ንባብ https://techxplore.com/news/2021-05-google-woolaroo-tool-indigenous-languages.html?fbclid=IwAR1M7fQJ70sZ3BqgwEQC9SXw2JQQt1Ns9Au5CbKyQOjLJhUqzgyuvv_3AVg

Tech Xplore
Google introduces Woolaroo, a tool for learning indigenous languages
With many indigenous languages worldwide becoming endangered due to a dwindling number of native speakers, Google has introduced the app Woolaroo which focuses on learning these languages. The idea for ...