TechIn2
1.17K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የዳውሮን ቱሪዝም መስህቦች የሚያሳይ ቱር አፕሊኬሽን ተመረቀ
===========
በዳውሮ ዞን የሚገኙ ልዩ የቱሪስት መስህቦችን በቨርቹዋል ሪያሊቲ አማካኝነት የሚያስጎበኝ ቱር አፕሊኬሽን በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት እንዲሁም በባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ትብብር ተሰርቶ ትናንት ተመረቀ፡፡ ቨርቹዋል ዳውሮ 360 የተሰኘው ቱር አፕሊኬሽኑ በቦታው ተገኝተው አካባቢውን መጎብኘት የማይችሉ ሰዎች በቨርቹዋል ሪያሊቲ መመልከቻ አማካኝነት እዚያው ሆነው እየጎበኙ እንዲመስላቸው ከማድረግም ባሻገር ቦታውን የማስተዋወቅና ታዳጊዎችንም በ3ዲ ቴክኖሎጂ አማካኝነት በማነሳሳት በቀጣይ ወደ ስፍራው እዲሄዱ ማድረግን ያለመ ነው፡፡
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ተሾመ ሳህለማርያም ኢንስቲትዩቱ ባለው መዋቅራዊ አደረጃጀት እና በሚሰራቸው ተግባራት ዙርያ በዕለቱ ለተገኙት የክብር እንግዶች ገለፃ አቅርበዋል፡፡ አያይዘውም በሁለቱ ኢንስቲትዩቶች ትብብር የተሰራው ይህ የቱር አፕሊኬሽን ሀገራችን በደምብ ከሰራችበት የተሻለ ገቢ እንደምታገኝበት የገለፁት የቱሪዝም መስኩን በማስቷወቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ካሳሁን ተስፋዬ በበኩላቸው መጋቢት 2012 ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የዳውሮን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት በጎበኙበት ወቅት በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት ተቋማቸው ወደ ስራ የገባ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ይህን ተከትሎም በስፍራው ጥናትና ምርምር ከማድረግ ባሻገር ተቋማቸው ከቀረፃቸው ስምንት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ይህ የዞኑን የተፈጥሮ መስህቦች የሚያስቃኝ የቨርቹዋል ቱሪዝም ስራ መሆኑን ጠቅሰው ቨርቹዋል ዳውሮ 360 ወደፊትም እየተሻሻለ በመሄድ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ጎብኚዎች የሚያዘወትሩት የተዋጣለት የመረጃ መረብ እና የዲጂታል ቱር እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ተናግረዋል፡፡
በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው ቱር አፕሊኬሽኑ ተጠናቆ በማየታቸው ደስ መሰኘታቸውን ገልጸው ይህን ስራ በአጭር ጊዜ ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ ላደረጉት ጥረት ለቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት እንዲሁም የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ዳውሮ በአስደናቂ የተፈጥሮ ውበት እና ብዝሀ ሕይወት የታደለች አካባቢ መሆኗን ያወሱስ ዶ/ር ሂሩት ቨርቹዋል ዳውሮ 360 ይህን ሙሉ ለሙሉ ለመመልከት ባያስችልም እንደሚያስተዋውቀው ተናግረዋል፡፡
የምሽቱን መዝጊያ ንግግር ያሰሙት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱም እንዲሁ በተሰራው የቱር አፕሊኬሽን ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያን የሚያሻግር ኃብት በአካባቢው እንዳለና ሰፊ ጥናት ሊደረግበት እንደሚገባ የገለፁትት ፕ/ር አፈወርቅ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዳውሮን በጎበኙበት ወቅት በሰጡት መመርያ መሰረት ስራው ሳይጓተት ለዚህ በመብቃቱ ምስጋናቸውን ቸረዋል፡፡
በምረቃ ዝግጅቱ ላይ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የዳውሮ ዞን አስተዳደር፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም ከሁለቱ ኢንስቲትዩቶች የተውጣጡ ኃላፊዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል የሚገኘው የዳውሮ ዞን ልዩ ልዩ የእንስሳት እና ዕፅዋት ሐብትን በውስጡ የያዘው የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክን ጨምሮ የተለያዩ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ መስህቦችን የያዘ የሀገራችን ክፍል ነው፡፡
ፋይዘር የመጀመሪያውን በታብሌት መልክ የሚወሰድ የኮቪድ 19 መድሃኒት እየሞከረ ነው
************
ፋይዘር የተሰኘው የመድሃኒት አምራች ተቋም በታብሌት መልክ የሚወሰድ የኮቪድ 19 መድሃኒት ለመስራት ሙከራዎችን እያደረገ እንደሆነ ተነገረ፡፡ በህክምና ዘርፍ ከማከም ይልቅ መከላከል የሚባለው መንገድ እጅግ ተመራጭ ነው፡፡ በተለይ እንደ ኮቪድ 19 ላሉ ተላላፊ ወረርሽኞች ከማከም ይልቅ መከላከል መድሃኒት ከመፈለግ ይልቅ በሽታው እንዳይሰራጭ ስራ መስራት በጣም አዋጭ ነው፡፡ እንደሌሎቹ በቫይረስ እንደሚተላለፉ በሽታዎች ሁሉ በኮቪድ የተጠቁ ሰዎችን ለማከም የሚያስችል መድሃኒት አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል
አንድ አመት ከተቃረበ ጥረት በኋላ በሽታውን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የተለያዩ ክትባቶች መገኘታቸውን ብዙዎችም ክትባቶቹን እየወሰደ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ክትባቶቹ የቫይረሱን ስርጭት የሚከላከሉ እንጂ ታማሚዎችን የሚያግዙ ባለመሆናቸው ብዙዎች አሁንም በከፍተኛ ስወቃይ ውስጥ ሆነው እየሞቱ ነው፡፡ ፋይዘር የተሰኘው የመድሃኒት አምራች ድርጅትም ይህን የህሙማንን ስቃይ ሊያቀልና ከበሽታቸው እንዲያገግሙ የሚያግዛቸውን መድሃኒት ነው እየሞከረ ያለው፡፡
አሁን ባለው ህክምና በጽኑ ህሙምነት ላሉ ሰዎች የሚደረገው የህክምና እርዳታ ኦክስጅን እንዲያገኙ በማድረግ ሰውነታቸው በራሱ የበሽታ መከላከል ብቃቱን በማሳደግ እስኪያገግሙ መጠበቅ ነው፡፡ ይህ ግን ሁል ጊዜ አዋጭ አይሆንም ለዚህም ነው ብዙዎች ኦክስጅን እንኳን እያገኙ እንደ ቅጠል እየረገፉ ያሉት፡፡ ይህን ያስተዋሉ ተመራማሪዎች ያለ እረፍት ለህሙማን ድጋፍ የሚሆን መድሃኒትን በመፈለግ ላይ ናቸው፡፡ በዘርፉ ፋይዘር የተሸለ እንቅስቃሴ እያደረገ ይመስላል፡፡ ለዚህም በታብሌት መልክ የሚወሰድ መድሃኒትን እየሞከረ መሆኑ ማሳያ ነው፡፡
መድሃኒቱ አሁን ላይ በቤልጀም ብራሰልስ የመጀመሪያ ደረጃ ክሊኒካዊ ሙከራ እየተደረገበት ሲሆን መድሃኒቱም ቫይረሱ በሰውነታችን ውስጥ ለመራባት የሚጠቀምበትን ኢንዛይም በመለየት የሚያጠቃ ነው፡፡ እንደ ፋይዘር መረጃ ከሆነ ይህ PF-07321332 የተሰኘ ክኒን (ታብሌት) በሽታው በሰውነታችን እንደገባ ወይም እንደያዘን ወዲያው የሚወሰድ ነው፡፡
ታማሚዎች የመጀመሪያው የህመም ስሜት እንደተሰማቸው ወደ ተጨማሪ ህክምና ሳይሔዱ መድሃኒቱን ሊወስዱት እንዲችሉ ታስቦም የተሰራ መሆኑን ድርጅቱ ተናግሯል፡፡
ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/health-and-medicine/pfizer-is-trialling-the-first-pill-to-treat-covid19/?fbclid=IwAR0aYBp8BEQ10UFgADMaGKmXx9ld7TrQ3fD_XqLKYKeQeaqZyPSnYi9ryNk
አፖሎ 11ን ወደ ጨረቃ ያበረረው ዝነኛ የጠፈር ተመራማሪ አረፈ
==============
አፖሎ 11ድን በማብረር የሰው ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃ ላይ እንዲያርፍ ያደረገውና የጨረቃን ምስጥራዊ የጀርባ ክፍል በመዞር የመጀመሪያው ሰው የሆነው ማይክል ኮሊንስ በ91 ዓመቱ በካንሰር ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
የጠፈር ተመራማሪው ከ50 ዓታት በፊት በተከናወነው ዝነኛ የጨረቃ ተልዕኮ ላይ ብቻውን ለ21.5 ሰዓታት ሰርቶ ነበር፡፡ ሌሎቹ የጠፈር ተመራማሪዎች ጨረቃ ላይ ባረፉበት ሰዓት እርሱ መንኮራኩሩ ላይ ሆኖ ብቻውን ጨረቃን እየዞረ ሳለ ለተወሰነ ጊዜ ግንኙነቱ ተቋርጦ የነበር በመሆኑም ኋላ ላይ “በታሪክ ብቸኛው ሰው” ወይም “the loneliest man in history” የሚል ቅፅል ስም ወጥቶለት ነበር፡፡ በተጨማም የተልእኮ አጋሮቹ ኒል አርምስትሮንግ እና በዝ አልድሪን ጨረቃን ሲረግጡ እርሱ ለዚህ ዕድል ባለመብቃቱ “የተዘነጋው የጠፈር ተመራማሪ” (forgotten astronaut) የሚል ስምንም አግኝቷል፡፡
ታድያ ማይክል ኋላ ላይ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ከጨረቃ ጀርባ ሲዞር ብቸኝነት ተስምቶት እንዳልነበር ተናግሯል፡፡ “ከጨረቃ ጀርባ እጅጉን ሰላም ነበር፤ ማንም እየነዘነዘኝና ይህን፣ ያሀንና ሌላኛውን አድርግ እያለኝ አልነበረም” ሲል ሁኔታውን መለስ ብሎ ገልፆታል፡፡ ሆኖም በተልእኮው ይዘዋቸው የሄዷቸው አይጦች ነገር አሳስቦት እንደነበር ግን አልደበቀም፡፡ ታድያ ሚካኤልም ሆነ መላው የጠፈር ተመራማሪዎች ቡድን ወደ ምድር ሲመለሱ አይጦቹ በጉዞው የተለየ ህመም ታይቶባቸው እንደሆን ለመገምገም ለይቶ ማቆያ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡
ሚካኤል አፖሎ 11ን እያበረረ ወደ ጨረቃ ከማምራቱ አስቀድሞ 16 ሰዎችን በያዘው የጂሚኒ 10 መንኮራኩር ምድርን ዞሮ ነበር፡፡ በተጨማሪም በአፖሎ 8 ላይ ከነበሩት የጠፈር ተመራማሪዎች ጋር ይደረግ በነበረውን ግንኙነት ውስጥም ትልቅ ሚናን መጫወቱ ይነገርለታል፡፡
ምንጭ፤ Live Science
ለተጨማሪ፤ https://www.livescience.com/michael-collins-obituary.html
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን በሙሉ መልካም የትንሳኤ በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛል፡፡
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሠላም አደረሳችሁ !!!
ቴክኢን ወግ
======
የዚህ ሳምንቱ ቴክኢን ወግ ዝግጅታችን “physical activities and sedentary behavior” በሚል ርዕስ 4 ኪሎ በሚገኘው የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዋና ፅ/ቤት ይቀርባል፡፡ በአቶ ናኦል ከበደ መሪነት በሚቀርበው በዚህ መሰናዶ ላይ የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች እና ተጋባዥ እንግዶች እንደሚገኙበት የሚጠበቀቅ ሲሆን የተሳታፊነት ዕድሉ ለእርሰዎም ክፍት መሆኑን አውቀው እንዲቀላቀሉን ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ቀን፤ ሐሙስ ሚያዝያ 28 2013
ሰዓት፤ 03፡00 እስከ 4፡30
This week's techin seminar will be hosted in our office (located around 4 killo) with a title of “physical activities and sedentary behavior”. The event, led by Mr. Naol Kebede, is expected to be attended by our researchers invited guests, and knowing that the opportunity is open to you as well we invite you to join us for it.
Date: Thursday, May 6, 2021
Time: 09:00-10:30 AM
ጅግጅጋ በሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር ቀዳሚ ሆናለች
==========================
የጅግጅጋ ከተማ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ከሚገኙ ሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች አንጻር ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ያለበት ከተማ መሆኗ ተገልጿል፡፡ የጅግጅጋ ከተማና ነዋሪዎቿ እንደ ሄሎ ካሽ፣ ሳሂ እና ኢ-ብር የሞባይል ባንኪንግና ክፍያ ስርዓቶችን በመጠቀም በሀገሪቱ ካሉ የተለያየ ከተማ ነዋሪች የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ በብዛት በቀዳሚነት መሰለፏን የኢትዮጵያን ሄራልድ ያወጣው ዘገባ ያሳያል፡፡
የሶማሌ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው ጅግጅጋ ዋና ዋና መንደሮች እና አደባባዮች በተለያዩ በሞባይል ባንኪንግ ማስታወቂያዎች የተሸፈኑ መሆናቸውን ያወሳው ዘገባው አብዛኞቹ የኤሌክትሮኒክስ መሸጫ ሱቆች፣ የጅምላ ሻጮች፣ ነጋዴዎች እና ሌሎችም የንግዱ አካላት በከተማው ውስጥ የሞባይል ባንኪንግን በመጠቀም የንግድ ግብይትና የቁሳቁስ ልውውጥ እያካሄዱ እንደሚገኝ አስቀምጧል፡፡
በጅግጅጋ ከተማ ለሚኖሩ ዜጎች የሞባይል ባንኪንግና ክፍያ ስርዓቶችን በማቅረብ ፈር ቀዳጅ የሆኑትና የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት ሄሎ ካሽ እና ሳሂ ሲሆኑ ከዚህ በተጨማሪም ኢ-ብር በተከታይነት ይገኛል፡፡ እነዚህ የሞባይል ባንኪንግና ዲጂታል የክፍያ ስርዓት አቅራቢዎች በከተማዋ አብዛኛዎቹ ቦታዎች የአገልግሎት ማዕከል በመክፈት ሰፊ እንቅስቃሴ የሚደርጉ ሲሆን፤ በወናነትም የአየር በረራ ትኬቶችን ለመቁረጥ፣ የሞባይል ካርድ ለመሙላት፣ የኤሌክትሪክ ቢል ፍጆታዎችን ለመክፈል እና ሌሎች የዕለት ተዕለት እንቅስቀቃሴዎችን ለማሳለጥ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጡ ይገለፃል፡፡
ለአብነት በዚህ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ውስጥ ከፍተኛ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች እንዲኖሩ በዋናነት እየሰሩ ከሚገኙ ድርጅቶች መካከል ቀዳሚ የሆነው ሳሂ ከጅግጅጋ ከተማ በተጨማሪ ተጎራባች በሆኑ እንደ ድሬዳዋ፣ ሃረር እና ምስራቅ ሀረርጌ አከባቢዎች የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን በቀጣይም በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች አገልግሎቱን ለማስፋት እቅድ እንዳለው ጥያቄ የቀረበላቸው አንድ የድርጀቱ ባለሙያ ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፡ The Ethiopian Herald
https://www.press.et/english/?p=34172#
ያለዲፕሎማ ሄሊኮፕተር፣ መኪና እና ድሮን መስራት የቻለው አፍሪካዊ
============================
የአፍሪካ ምድር አስደናቂ ተሰጥዖ ያላቸው ነገር ግን ወተው መታየት ያልቻሉ ብዙ የፈጠራ ሰዎችን ይዛለች፡፡ አንዳንዶች ተሰጥዖ የታከለበትን ፈጠራቸውን ለፍሬ ሳያበቁ በተለያዩ እክሎች ምክንያት ተሰናክለው ሲቀሩ ሌሎች ጥቂቶች ደግሞ ይህን ልዩ አቅምና ችሎታ ወደውጤት በመቀየር አስገራሚ ታሪክ ይፅፋሉ፡፡ ይህ እውነታ ከታየባቸው ጥቂት ሰዎች መካከል የዚምቧብዌ ተወላጁ ማክስዌል ሳንጉላኒ ቺኩምቡስቶ እንደምሳሌ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
ይህ ግለሰብ ከልጅነቱ አንስቶ ከቴክኖሎጂው ዓለም ጋር በፍቅር አንዲወድቅ የአባቱ የመካኒክ ባለሙያነት አስተዋፅዖ ቢኖረውም በተፈጥሮ ያገኘው ልዩ የፈጠራ ችሎታና በዚህ ላይ ደግሞ ደጋግሞ የመሞከር ዝንባሌው አሁን ለደረሰበት ትልቅ ደረጃ ዋና ምክንያቶች ናቸው፡፡ በሃራሬ ከተማ ኩድዝዋና በተባለች መንደር ያደገው ይህ የፈጠራ ሰው እንደሌሎች የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች አሁን በሚሰራበት ዘርፍ በዲግሪ ወይም በዲፕሎማ መመረቅ ሳያስፈልገው በተሰጠው ልዩ ችሎታ እና ደጋግሞ የመሞከር ብቃት ብቻ ለማመን የሚከብዱ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ማበልፀግ የቻለ ኢኖቬተር ነው፡፡
ማክስዌል ሳንጉላኒ ቺኩምቡስቶ በህጻንነቱ ሲሞክራቸው ከነበሩ ቀላል ፈጠራዎች ተነስቶ ራሱን ወደቴክኖሎጂው አለም ይበልጥ የሚያቀርብበትን የኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ትምህርቶች ገና በልጅነቱ መለማመድ ቻለ፡፡ ከዚህ በኋላ ከአመታት ሙከራ እና ራስ ላይ የመስራት ጊዜያት በኋላ Saith Technologies የተባለ የግል ድርጅት በማቋቋም በኢነርጂና የኮምፒውተር ግንኙነት ቴክኖሎጂዎች ላይ በጥልቀት መስራት ጀመረ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በቅጡ መጨረስ እንኳን ያልቻለው ማክስዌል እንደ ሄሊኮፕተር እና መኪና ያሉ ውስብስብ ቴክኖሎጂዎችን ባቋቋመው ኩባንያ አማካኝነት መስራት ችሏል፡፡ የሰራት ሄሊኮፕተር ሁለት መቀመጫ ያላት ስትሆን ስድት የዘይት አይነቶችን መቀበል የምትችል እና ሃይብሪድ ኢንጂን የተገጠመላት ሄሊኮፕተር ናት፡፡
ይህ የፈጠራ ባለሙያ ለእይታ ያበቃት መኪና እና ራስ-ገዝ የሆነቸው የመከታተያ ድሮን በ Saith Technologies ዲዛይን በተደረገና በበለፀገ ግሪነር ፓወር ማሽን በተባለ የታደሽ ሃይል አማራጭ የተከናወኑ አስገራሚ ፈጠራዎች ናቸው፡፡ ትልቅ ህልም ይዞ ትልልቅ ፈጠራዎችን ለሀገሩና ለአፍሪካ ህዝቦች ማቅረብ የሚፈልገው ማክስዌል ከዚምቧብዌ መንግስት ፍቃድ ካገኘ በኋላ የቴክኖሎጂ ስራዎቹን በበሰፊ ስኬል በማምረት ከሌሎች የአውሮፓ፣ አሜሪካና እስያ ኩባንያዎች ጋር መወዳደር እንደሚፈልግም ይናገራል፡፡
https://zambiareports.com/.../without-diploma-african.../
የወደፊቱ ሞተር አልባ የአየር ትራንስፖርት
***************************
ተመራማሪዎች የአዮን ድራይቭን ብቻ በመጠቀም የለምንም ተንቀሳቃሽ ክፍልና ያለ ነዳጅ በረራ ሊያደርግ የሚችል አውሮፕላን መስራታቸው ተሰማ፡፡ በማሳቹሴት የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የሚገኝ በሰቴቨን ባሬት የሚመራ አንድ የምርምር ቡድን በኤሌክትሮኤሮዳይናሚክስ የሚንቀሳቀስ ምንም አይነት የአውፕላን ሞተር ወይም ነዳጅ የማይጠቀም አውሮፕላን መስራታቸውን ተናግረዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ የወደፊቱ የአየር ትራንስፖርት ከባድ ሞተሮችን፣ ተርባይኖችንና ነዳጅን የማይጠቀም እጅግ ዘመናዊ ልክ እንደ ባለጅራት ኮከቦች የሚንቀሳቀስ መሆን አለበት ብለው እንደሚያምኑ የጥናታቸውን ውጤት ይፋ ባደረጉበት ወቅት ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊት በ1921 ተመራማሪዎች የልተሳካ ሙከራን በዘርፉ ያካሄዱ ሲሆን በወቅቱ የነበረው የቴክኖሎጂ አለመዘመን ለሙከራው አለመሳካት ከፍኛ ድርሻ ነበረው፡፡ አሁን ላይ ያለው የቴክኖሎጂ ልህቀት ለዘርፉ ምርምር መፍትሔ ይዞ መጥቷል፡፡
ከ2016 እስከ 2018 በተደረገ ሙከራ የክንፍ ርዝማኔው አምስት ሜትር ወይም 16 ጫማ የሆነና አጠቃላይ ክብደቱ 2.45 ኪሎግራም የሆነ አውሮፕላን ሰርተው ነበር፡፡ ይህ አውሮፕላን በፊት ለፊቱ በኩል በ20,000 ቮልት ፖዘቲቭ ቻርጅ የተደረጉ ቀጫጭን ገመዶች ሲኖሩት በኋለኛው በኩል ደግሞ በኔጌቲቭ 20,000 ቻርጅ የተደረገ በመደበኛው አውሮፕላን እንዳለው አይነት ኤሮፎይል አለው፡፡ ይህም ጠንካራ የሆነ ኤሌክትሪካዊ ከባቢ (electric field) እንዲኖር ያደርጋል፡፡
በፊት ለፊት በኩል በከባቢ አየሩውስጥ ከሚገኙ የናይትሮጅን ሞሎኪዮሎች ኤልክትሮኖች በመውጣት አዮኖችን ይፈጥራሉ፡፡ እነዚህም በፍጥነት ወደ ኋላ በመሄድ አውሮፕላኑ እንዲንቀሳቀስ የሚያስችለውን አዮናዊ ንፋስ ይፈጥራሉ፡፡ ሀሳቡም የመነጨው ከአየር ውስጥ ኤሌክትሮንን በማውጣት አየሩን በአዮኖች መሙላት በኤሌክትክ ቻርጅ አማካኝነት አየሩን ማንቀሳቀስ ይቻላል ከሚለው እሳቤ ነው፡፡
ከ10 ጊዜ በላይ በተደረገ ሙከራም አውሮፕላኑ በ12 ሴኮንዶች 60 ሜትር መብረር መቻሉን ተመራማሪዎቹ አስረድተዋል፡፡ በሀሳብ ደረጃ ከመደበኛው የመንገደኞች አውሮፕላን የፈጠነና በሰዓት 1080 ኪሎሜትሮችን መጓዝ ይችላል የሚል ግምት እንዳላቸው ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/technology/scientists-have-created-a-star-treklike-plane-that-flies-using-ion-thrusters-and-no-fuel/page-2/
በስራ ቦታ በቂ እንቅስቃሴ አለማድረግ፤ መዘዙና መፍትሄው
=======================
ዛሬ በተከናወነው የሳምንቱ ቴክኢን-ወግ መሰናዶ የሰራተኞች በስራ ቦታ ላይ የአካከል ብቃት እንቅስቃን ሳያደርጉ መቅረት በጤና ላይ ያለውን ጠንቅ እና ይህንንም መቅረፍ በሚቻልበት መንገድ ላይ አተኩሮ ቀርቧል፡፡ “physical activities and sedentary behavior” በሚል ርዕስ በአቶ ናኦል ከበደ ገለፃ አቅራቢነት የተከናወነው ይህ መሰናዶ የኢንስትዩቱ ኃላፊ እና ተመራማሪዎችን ተሳታፊ አድርጎ ተከናውኗል፡፡
አቶ ናኦል በገለፃው በስራ ቦታ ላይ ያለ በቂ እንቅስቃሴ የምንቆይበት የህይወት ዘይቤያችን ተፅዕኖውን ወድያው የምናየው ሳይሆን በጊዜ ሂደት የሚመጣና ጉዳቱም ምናልባት ኋላ ላይ በአካል ብቃት እንቅስቃሴም ጭምር ሊመለስ የማይችል መሆኑን ተናግሯል፡፡ በዚህም የሰራ ቦታ ላይ ያለ በቂ እንቅስቃሴ ለረጅም ጊዜ መቀመጡ በእግር እና የጀርባ አጥንት እንዲሁም ጡንቻዎች ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባሻገር እንደ ስኳር፣ ውፍረት፣ ደም ግፊት እና ጭንቀት ያሉ በሽታዎችን እንደሚያስከትል ተናግሯል፡፡ ይህም በየዓመቱ በዓለማችን 2 ሚሊዮን ሰው ህይወቱን እንዲያጣ ምክንያት ስለ መሆኑ አቶ ናኦል ተናግሯል፡፡
አቶ ናኦል ለነዚህ ሁሉ ችግሮች መፍትሄ ይሆናሉ ያላቸውን የቢሮ ውስጥ እንቅስቃሴ ምክረ ኃሳቦችን የለገሰ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘም ቀላል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነቶች ለታዳሚው በእንቅስቃሴ መልክ በማሰራት አሳይቷል፡፡ በቀጣይም እንደ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሊደረጉ ይገባቸዋል ያላቸው የመፍትሄ ሐሳቦችን አስቀምጧል፡፡
በዛሬው የቴክኢን ወግ በቀረበው ገለፃ ዙርያ ሐሳባቸውን ለታዳሚው ያካፈሉት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ተሾመ ሳህለማርያም አነስተኛ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ባለው አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ አመራር በመድረኩ የቀረቡ የመፍትሄ ሐሳቦችን ተቀብሎ እንደሚሰራባቸው የተናገሩት ኢ/ር ተሾመ ወደፊትም ለሰራተኞች የሚሆን ጂም የመገንባት እንቅስቃሴ መኖሩን አስታውቀዋል፡፡