የሰሜን ኮሪያ ሀከሮች ስርቆት
+*+*+*+*+*+*+*+*+*+*+*+*+
ባለፉት አምስት ዓመታት ከተደረጉት ትላልቅ የሳይበር ጥቃቶች ውስጥ በመንግስት እንደሚደገፉ የሚታመኑት የሰሜን ኮሪያ ድረ-ገፅ በርባሪ ወይም ሃከሮች የከወኗቸው ከፊት ተሰላፊዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የጥቃት ቡድኖች በተግባሩ እጅግ የተካኑ ሲሆኑ ጥቃቶቹም ይህን ይመሰክራሉ፡፡ በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ፀጥታ ምክር ቤት ባወጣው ሪፖርት መሰረት እነዚህ ቡድኖች 670 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ እና ክሪፕቶከረንሲ በህገ-ወጥ መንገድ አግኝተዋል፡፡
በ2015 የባንግላዲሽ ማዕከላዊ ባንክ ላይ ባደረሱት የሳይበር ጥቃት ብቻ እነዚህ የሰሜን ኮሪያ ድረ-ገፅ በርባሪዎች 81 ሚሊዮን ዶላር እንዳገኙ ይታመናል፡፡ ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመትም የህንድ ኮስሞስ ባንክን በማጥቃት 13.5፤ ከርሱ አስቀድሞም የቺሊን ባንክ ኤቲኤም ማሽኖች ትስስር መረብን በማጥቃት 10 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ችለዋል፡፡
እነዚህ የሰሜን ኮሪያ ሃከሮች የክሪፕቶከረንሲ ዝውውሮችንም በተሳካሁኔታ ማጥቃት ችለዋል፡፡ በግሩፕ አይቢ የሚገኙ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች እንዳስቀመጡት ከሆነ በዓለማችን ከሚፈፀሙት አጠቃላይ የክሪፕቶከረንሲ ጥቃቶች ውስጥ 65 በመቶዎቹ በነኚህ ሰሜን ኮሪያዊያን አማካኝነት እንደሚከወኑ ገልፀዋል፡፡ ከጥር 2017 እስከ መስከረም 2018 በፈፀሙት ጥቃት እንኳን የ570 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራን በሰለባዎቻቸው ላይ አድርሰዋል፡፡
ሰሜን ኮሪያ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተጣለባት ማዕቀብ ገንዘብን በህጋዊ መንገድ እንዳታገኝ አድርጓታል፡፡ ሆኖም የኪም ጆንግ ኡን ሃገር ይህን በመሰሉ ጥቃቶች የምታጋብሰው ትርፍ የማይነጥፍ የገቢ ምንጭ ሆኖላታል፡፡ ለዚህም ይመስላል የሃገሪቱ መጠነ ሰፊ የክሪፕቶከረንሲ አጠቃቀም መሰል ጥቅምን ሊያመጣላት የቻለበት አንዱ ምክንያት መሆኑ፡፡ ክሪፕቶከረንሲዎች በአብዛኛው ሃገራት ህግ በሚያውቃቸው ተቋማት አማካኝነት ስለማይከወኑ ማዕቀቦችን ተፅዕኖ ከመፍጠር ያግዷቸዋል፡፡ ሌላኛው ምክንያት የክሪፕቶከረንሲ ዝውውሮች ለመከታተል አስቸጋሪ መሆናቸው ነው፡፡ ምንም እንኳን ተከታትሎ ማግኘት የሚቻል ቢሆንም ሰፊ ጊዜን የሚወስድ እና ውስብስብ ነው፡፡
ምንጭ፡- Forbes

ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ
$**$**$**$**$**$**$**$**$**$
ተቋማችን የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በሥሩ በሚገኙት ሦስት ማዕከላት ላሉ የምርምር ዳይሬክቶሬቶች ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘሩት የስራ መስኮች ላይ ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ባለሙያዎች እንዲያመለክቱ ይጋብዛል፡፡
በOnline ለመመዝገብ ሊንኩ ይኸውልዎ http://www.techin.gov.et/am/web/sticsite/techin12 /
http://www.techin.gov.et/am/web/sticsite/announcement

የጊዜ ማሽን ተሰራ?
*+*+*+*+*+*+*+*+*+*
ሴኮንዶች፣ ደቂቃ፣ ሰዓታት፣ ቀናት፣ ዓመታትን ወዘተ…. አሻግረው ወደ ኋላ የሚመልሱ የጊዜ ማሽኖች ለብዙ ጊዜያት ተመልክተናል፣ አድንቀንም አልፈናል፤ በሆሊዉድ ፊልሞች ላይ !!! ታድያ ዕልፍ የሳይንስ ጠበብቶች ይህን የሰው ልጆች ጊዜን ወደኋላ የመመለስ ህልም ለማሳካት ምዕተ ዓመታትን በጥረት አሳልፈዋል፡፡ ሰሞኑን ከወደ ሩሲያ የተሰማው ግን ይህ ህልም ወደ ተግባር መለወጥ መጀመሩን ነው፡፡ በዋናነት ከሞስኮ የፊዚክስ እና ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት (MIPT) የተውጣጡ ተመራማሪዎች የኳንተም ኮምፒውተርን በመጠቀም ጊዜን ወደ ኋላ እንዳስጓዙ ዕወቁልን ብለዋል፡፡ የጥናቱ ውጤት ታድያ የፊዚክስን ሕግ የተፃረረና ህዋን የምንረዳበት መንገድንም የሚለውጥ ሊሆን እንደሚችል ተነግሮለታል፡፡ በኳንተም ኮምፒውተሮች ላይ ያለንን መረዳት ጭምር ባሳደገው በዚህ ግኝት ላይ ተመራማሪዎቹ ባከናወኑት ሙከራ የተበታተኑ የፑል መጫወቻ ኳሶችን መልሰው ወደነበሩበነት መመለስን በሚመስል መልኩ ጊዜን ወደኋላ እንዳንቀሳቀሱ ተናግረዋል፡፡
ፈጠራው ተብራርቶ በወጣበት ጆርናል ላይ እንደተገለፀው የጊዜ ማሽኑ ከኤሌክትሮን ኪዩቢቶች (መረጃን በአንድ እና ዜሮ ወይም ሁለቱንም በአንድ ላይ ባነባበረ ርብርብር የሚገለፅበት መንገድ) የተዋቀረ ኮምፒውተርን የያዘ ነው፡፡ ሙከራው በተጀመረበት ወቅት ኪዩቢቶቹ ውስብስብና በዜሮና አንድ መልኩም መቀያየር ጀመሩ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የነበረው ስርዓት የጠፋ ሲሆን ሌላ ፕሮግራም ግን ይህን በመለወጥ ስርዓቱ ወደነበረበት እንዲመለስ አድርጎታል፡፡ ይህን በፑል መጫወቻ ኳሶች መስለበን ብንወስደው ኳሶቹ ልክ እንደ ኪዩቢቶቹ ሁሉ የተበተኑ ሲሆኑ በዚህ ግኝት ዓማካኝነት ግን የተበተኑበነትን መንገድ ተከትለው ወደነበሩበት ስፍራ እንደመመለስ ነው፡፡
ሆኖም ይህ ወደኋላ የመመለስ ስኬቱ ኪዩቢቶቹ ከሁለት ወደ ሶስት በጨመሩ ጊዜ በ50 በመቶ ሊወርድ ችሏል፡፡ ተመራማሪዎቹ ታድያ ግኝቱ ከዚህ በላቀ እንደሚሻሻልና ይበልጡን አስተማማኝ እንዲሁም ትክክለኛ እንደሚሆን ያላቸውን ዕምነት አንፀባርቀዋል፡፡
ምንጭ፡ Independent

ለመሆኑ ብዙ ተስፋ የተጣለባት ብላክ ቦክስ ምንድን ናት?
*********************************************************
ከሰሞኑ የብዙዎችን ልብ ከሰበረው አውሮፕላን አደጋ በኋላ በኢትዮጵያም ይሁን በመላው ዓለም የሚገኙ የተጎጂ ቤተሶቦች እና መላው ህዝብ አደጋው የተፈጠረበትን ትክክለኛ ምክንያት ለማውቅ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይም ደግሞ አደጋው ከተከሰተ ጥቂት ቀናት በኋላ በብዙ ፍለጋ የተገኘቸው ብላክ ቦክስ ወደ ፈረንሳይ ተልካ በአደጋው ወቅት የነበረውን አጠቃላይ ሁነት ለማሳየት የሚያስችሉ መረጃዎችን ልትሰጥ በምትችልበት ሁኔታ ላይ ናት የሚል መረጃ ከወጣ ጀምሮ የሁሉም ዓይን በመረጃ ሳጥኗ ላይ ያነጣጠረ ሆኗል፡፡ የትኛውንም አደጋ መቋቋም የሚያስችል አቅም አላት የምትባለው ይህች ብላክ ቦክስ አጠቃላይ መረጃዋ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ስለቴክኖሎጂዋ አፈጣጠር
እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1934 የዶክተር ዴቪድ ዋረን አባት በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸው ሲያልፍ ዴቪድ ገና የዘጠኝ አመት ልጅ ነበር፡፡ አባቱን ይዞ እንደወጣ ያልተመለሰው አውሮፕላን የተከሰከሰበት ምክንያት እንኳን ሳይታወቅ የዴቪድን ልብ እንደሰበረ ቀረ፡፡ ይህ ሁነት ሁሌም ቁጭት የሚፈጠጥርበት ዴቪድ በ1950 በበረራ ወቅት መረጃዎችን የምትመዘግብና የድምፅ ምልልሶችን የምትቀዳ መሳሪያ ለመፍጠር መነሻ ሆነው፡፡ የአዎስትራሊያ ዜጋ የሆነው ዴቪድ የዚችን መሳሪያ ፕሮቶታይፕ በ1956 ሲሰራ በመጀመሪያ "ARL Flight Memory Unit" የሚል መጠሪያ የሰጣት ቢሆንም ከአምስት አመት በኋላ በአሜሪካ እና እንግሊዝ አማካኝነት ወደ ሙሉ ምርት እንድትገባና እና አሁን የያዘችውን ስያሜም እንድታገኝ ሆኗል፡፡
የብላክ ቦክስ ገፅታ
የመረጃ ሳጥን ወይም ብላክ ቦክስ ሁለት አይነት ገፅታ ሲኖራት እነሱም flight data recorder (FDR) እና cockpit voice recorder (CVR) ይሰኛሉ፡፡ FDR የሚባለው በቋሚነት በየቦታው በተገጠሙለት ሴንሰሮች አማካኘነት ከኤሌክትሪክ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን እያንዳንዳቸውን ነገሮች ለምሳሌ የሞተር ኃይል እና ፍጥነትን ሲመዘግብ፤ CVR የተባለው ደግሞ በበረራው ወቅት የተሰሙ የፓይለቶችን እና የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ አካላትን አጠቃላይ ግንኙነቶችን የሚመዘግብ ነው፡፡ ብላክ ቦከስ ብዙዎች እንደሚያስቡት ጥቁር ቀለም ያላት ሳጥን ሳትሆን በአለም አቀፉ የኤሮስፔስ የቀለም አጠቃቀም መሰረት ከተፈጥሮአዊ ገፅታዎች ለመለየት የብርቱካናማ ቀለም እንዲኖራት ተደርጓል፡፡
የብላክ ቦክስ መሳሪያ ይዘት
የብላክ ቦክስ መሳሪያ አብዛኛውን ጊዜ በቲታንየም ወይም በማይዝግ ብረት የሚሸፈን ሲሆን 227 ኪ.ግ ክብደትም ይመዝናል፡፡ የትኛውንም አደጋ መቋቋም ይችላል የሚባለው የብላክ ቦክስ መሳሪያ ለአንድ ሰዓት የሚቆይ የ100 ዲግሪ ሴሊሺየስ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ መቋቋም ከመቻሉም በላይ ከፍተኛ እርጥበት እና በግፊት የተሞላ ጨዋማ ውሃ ውስጥ ሆኖ እንኳን የያዘውን መረጃ ሳያጣ ለ2 ዓመት መቆየት ይችላል።
መረጃ የማከማቸት አቅም
ብላክ ቦክስ በቀላሉ የማይጎዳ ከመሆኑም ባለፈ 3400 Gs የመረጃ ቋትም አለው። ይህም ማለት ከአዲስ አበባ ሳኦ ፖሎ ብራዚል የሚበር አውሮፕላን፤ ደርሶ አስኪመለስ ያለውን አጠቃላይ መረጃ ማለትም የአብራሪውን እንቅስቃሴ፣ የአውሮፕላኑን ፍጥነት፣ ከፍታውን፣ የነዳጅ ሁኔታ እና ሌሎች አንቅስቃሴዎቹን ይመዘግብለታል ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ CVR የተባለው የብላክ ቦክስ ገፅታ ለ25 ሰዓታት የሚቆይ የበረራ መረጃን ለማከማቸት ዲጂታል መቅጃዎችን የሚጠቀም ቢሆንም በራሱ ለመቅዳት ሲፈልግ ግን የሁለት ሰዓት የበረራ መረጃን ብቻ ይይዛል፡፡
ምንጭ፡ ABC News እና wired.com

ውሃ የሰው ልጆች ፀጋ!!!
*********************
ዛሬ ለሰው ልጅ ከማናቸውም ነገሮች በላይ አስፈላጊ የሆነው “ውሃ” ታስቦ እየዋለ ይገኛል፡፡ ይህ የተፈጥሮ ፀጋ ምናልባት ከኦክስጂን ቀጥሎ ለሰው ልጅ ህልውና እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው ቢባል የሚያከራክር አይደለም፡፡ ሰውነታችን ያለ አንዳች ሳንካ በተስተካከለ ሁኔታ ይሰራ ዘንድ ውሃ በጣም ያስፈልገዋል፡፡ በቀላል አነጋገር በበቂ ሁኔታ ንፁህ ውሃ በጠጣን ቁጥር ይበልጥ ጤናችንን አስተማማኝ እናደርጋለን፡፡ በቂ ውሃ መጠጣትን ችላ ማለት ወይም መዘንጋት ለህይወታችን እጅግ አስፈላጊ የሆነውን ኦክስጂንን የመርሳት ያህል ሊቆጠር ይችላል፡፡ ውሃ ጤንነታችንን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ረጅም ዕድሜና ደስተኛ ህይወት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ይህንን በተጨባጭ ለማረጋገጥ ስለውሃ አንዳንድ ዕውነታዎችን አብረን እንቃኝ ፡፡
ውሃን የሚተካው ውሃ ብቻ ነው
ማናቸውም የውሃ ይዘት ያላቸው እንደ ጭማቂ፣ ሶዳ፣ ሻይ ቡና ወዘተ-- አይነት ፈሳሾች ከውሃ የምናገኘውን ከፍተኛ ጥቅም ተክተው እንደ ውሃ በመሆን ፈፅሞ አያገለግሉም፡፡ ይልቁንም አንዳንዶቹ ውሃ በውሃነቱ የሚሰጠን ጥቅም ከማሳጣት አልፈው በጤናችን ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራሉ፡፡ ለምሳሌ በውስጣቸው የካፊን ንጥረ ነገር የያዙ ፈሳሾች ከሰውነት ውስጥ በመቀነስና በማድረቅ ለሰውነታችን አስፈላጊ የሁኑ ቫይታሚኖችንና ሚኒራሎች በማስወገድ ጉዳት ያስከትላሉ ፡፡ በውስጣቸው ስኳር የያዙ መጠጦችንም እንዲሁ ጣፍያችንን በማነቃቃትና የኢንሱሊን መጠን እንዲጨምር በማድረግ ሰውነታችን በተለመደው መንገድ ስብ የማቃጠል ስራውን እንዲያካሂድ በማወክ ለችግር ያጋልጣሉ፡፡
ውኃና ክብደት፡- ውሃ ክብደትን በመቀነስ ረገድ አስገራሚ ውጤትን ያስገኛል፡፡ ልብ ይበሉ ውሃ በውስጡ ምንም አይነት ካሎሪ፣ ስብ ወይም ለኮሌስትሮል የሚያጋልጥ ንጥረ ነገር የለውም ፡፡ የሶዲየም ይዘቱም እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ የክብደት መጨመር ችግር ላለባቸው በቂና ንፁህ ውሃ መጠጣት ከፍተኛ የምግብ ፍላጎታቸውን በመቀነስ ተጨማሪ የስብ ክምችት ወደ ሰውነታችን እንዳይገባ በማድረግ የስብ ክምችትን በማቃጠል ክብደታቸውን እንዲቀንሱ ያግዛቸዋል፡፡ የቅርብ ግዜ ጥናቶች እንዳሳዩትም በቂ ውሃ የማይወስዱ ሰዎች ለከፍተኛ የስብ ክምችት የተጋለጡ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡
ውሃና ኩላሊት፡- ኩላሊታችን ከሰውነታችን መወገድ የሚገባቸውን ነገሮች በማጣራት የማስወገድ ተግባርን ያከናውናል፡፡ ሰውነታችን በቂ ውሃ ካለገኘ በቀላሉ በውሃ የሚሟሙ እንደ ዩሪክ አሲድ፣ ዩሪያ ላክቲክ አሲድና ሌሎች መሰል ከሰውነታችን መወገድ የሚገባቸውን ንጥረ ነገሮች ማስወገድ ስለሚሳነው ኩላሊታችን በመጉዳት ለአደጋ ያጋልጠናል፡፡
ውሃና አንጎላችን፡- የአንጎላችን ቲሹ /Brain tissue/ 85 በመቶ ውሃ ነው፡፡ አንጎላችን ከጠቅላላ የሰውነት ክብደት 1/50ኛ ያክል የሚመዝን ሲሆን ከጠቅላላ የሰውታችን የደም ዝውውር ደግሞ 20 ከመቶውን ይወስዳል፡፡ በመሆኑም በቂ ውሃ አለመውሰድ ወደ አንጎላችን መድረስ የሚገባውን የደም ዝውውር መጠን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በማሳደር የመጫጫን ስሜትና ቋሚ የድካም ስሜትን እንደሚፈጥር ጥናቶች ይጠቁማሉ ፡፡
ውሃና እርግዝና፡- የማለዳ ህመም /Morning sickness/ በመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ወራት የታወቀና የተለመደ ነው፡፡ ለዚህ ህመም ምክንያት ናቸው ከሚባሉት አንዱ የሰውነታችን ውሃ ይዘት አነስተኛ መሆን ወይም በቂ አለመሆን ነው፡፡ ይህም በእርግዝና ወቅት እናት ከራሷ በተጨማሪ ሽሉን የምትመግብ በመሆኗ ሰውነት ከወትሮው በተለየ ተጨማሪ ውሃን ሲፈልግ ማግኘት ባለመቻሉ የሚፈጠር የህመም ስሜት ነው፡፡ በእርግዝና ወራት በቂና ንፁህ ውሃ አለመውሰድ ከእናትዮዋ አልፎ ለሽሉም አይበጅምነና እናቶች ልብ በሉ፡፡
ለጤንነታችን ካሰብን ውሃ እስኪጠማን አንጠብቅ
ውሃ ጥም /Thirst Refle/ ውሃ ከሰውነታችን እየተሟጠጠ መሆኑን የሚያመለክት ከባድ መልዕክት ነው፡፡ ውሃ እስኪጠማን በፍጹም መጠበቅ አይኖርብንም ፡፡ የውሃ ጥም ተሰማን ማለት ሰውነታችን በወቅቱ ማግኘት የሚገባውን የውሃ መጠን ባለማግኘቱ የሚፈጠረው ጉዳት ደርሷል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አስኪጠማን ሳንጠብቅ የመጠጣት ልማድን ልናዳብር ይገባናል፡፡ እዚህ ላይ አንድ ሰው በአማካይ በቀን ምን ያህል ውሃ መጠጣት አለበት? የሚል ተገቢ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ በመሆኑም መውሰድ የሚገባን የውሃ መጠን እንደ የስራ ባህሪያችን፣ እንደምንኖርበት የአየር ፀባይ፣ እንደ ሰውነት ክብደታችንና እንደ አመጋገብ ልማዳችን እንዲሁም እንደ አካላዊ እንቅስቃሴያችን ሊለያይ ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ 45 ኪ.ግ የሚመዝን ሰው በቀን 1.486 ሊትር ውሃ እንዲጠጣሁኔታ ይመከራል ፡፡ ስለሆነም ውሃ ለሰው ለጅ ከማናቸውም መደኃኒት በላቀ ፈውስን የሚይገኝ ሰለሆነ ንፁህና በቂ ውሃ በመጠጣት ጤንነታችንን እንጠብቅ መልዕክታችን ነው፡፡
ምንጭ፡ BG WIEB

የስራ ማስታወቂያ
ተቋማችን የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በምስሉ ላይ በተገለፁት የሥራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጥር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ሰባት (7) ተከታታይ የሥራ ቀናት በኢንስቲትዩታችን ድህረ-ገፅ ላይ (http://www.techin.gov.et/am/web/sticsite/techin11) ሄዳችው መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የዓለም ምርጥነት ክብርን ስለተቀናጀው ሲንጋፖራዊ ህንፃ
===================================
ዓለማችን አሁን ከደረሰችበት የብክለትም ሆነ የግንዛቤ ደረጃ ጋር በተገናኘ አረንጓዴ ልማት ወደ ቀዳሚ አጀንዳነት ተሸጋግል፡፡ ከዚህ ባህረ ሃሳብ ውስጥ ደግሞ የአረንጓዴ ህንፃዎች ግንባታ አንዱ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በፊት በተከናወነው የዓለም ኪነ ህንፃ ፌስቲቫል (WAF) ላይ የዓመቱ ምርጥ ህንፃ በመሰኘት የሲንጋፖሩ ካምፑንግ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ ይህ ህንፃ ሽልማቱን እንዲያገኝ ያስቻለው ታድያ ይህን የአረንጓዴነት ባህርይ ከሌሎች ማህበራዊ እሳቤዎች አስተሳስሮ በመሰራቱም ነው፡፡
በሰሜናዊው የከተማይቱ ክፍል የታነፀው ይህ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ሰጪ ህንፃ ከአንድ ሄክታር ባነሰ መሬት ላይ የቆመ ነው፡፡ በውስጡም ክፍት የህዝብ ቦታ፣ የህዝብ ፓርክ እና የህክምና ዓገልግሎት መስጫን ከመኖሪያ ቤቶች አዋህዶ ይዟል፡፡ የህንፃው ዲዛይን በኪነ-ህንፃው አርቃቂዎች ዘንድ “club sandwich” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የተለያዩ አገልግሎቶችን በተለያዩ ወለሎች ላይ ይሰጣል፡፡ ህንፃው በዓጠቃላይ የታች፣ መካከለኛ እና የላይኛው በተባሉ ሶስት ክፍሎች የተከፋፈለ ሲሆን ባለ አስራ አንድ ወለል እና 104 አፓርታማዎችንም አቅፎ ያዘ ነው፡፡ የታችኛው ክፍል ለህዝብ ክፍት የተደረጉ መናፈሻ፣ ቴራሶችን እንዲሁም የመመገቢያ ስፍራዎችን ይዟል፡፡
የካምፑንግ ህንፃ በሃገሪቱን ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰውን የእርጅና ጉዳይ ከግምት ውስጥ ማስገባቱ በታላላቅ የኪነ-ህንፃ ባለሙያዎች ዘንድ አድናቆትን ገዝቶለታል፡፡ ዕድሜው እየገፋ የመጣውን የሃገሪቱን ነዋሪ አካታች በሆነ መልኩ መገንባት እንደሚቻል ለማሳየት የታነፀ ሰርቶ ማሳያ መሆኑ ደግሞ ገና የአግራሞች መጀመሪያ እንጂ መቋጫ እንዳይሆን ያደርገዋል፡፡ መሰል ዘጠኝ የቤት ግንባታዎችን ለመስራትም የሃገሪቱ መንግስት እየተንቀሳቀሰ ነውና፡፡
ሐገርም ከተማም የሆነችው ሲንጋፖር በእርግጥ በግንባታ ጥበብ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ህንፃዎችን ገንብታ ለአድናቆት እና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ስታበቃ ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም፡፡ ከዚህ አስቀድሞ ለሁለት ጊዜ ያህል ህንፃዎቿ በተመሳሳይ ሁኔታ ለሽልማት በቅተውላታል፡፡ ሆኖም እዛው ሃገሪቱ ላይ መሰረቱን ባደረገ ተቋም ዲዛይን ተደርጎ ለዚህ ክብር ሲበቃ ግን የመጀመሪያው ያደርገዋል፡፡
ምንጭ፡ CNN style