TechIn2
1.16K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሰው ልጆች ታሪክ እጅግ የከፋው ዘመን የትኛው ነው
========================
ባሰላፍነው የፈረንጆች አመት የብዙ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈና ሁለንተናዊ ቀውስ ያስከተሉ ክስተቶች በብዙ የአለማችን ክፍሎች ተከስተዋል፡፡ አደገኛ አለም አቀፍ ወረርሽኝ፣ በየሀገራቱ የተስተዋሉ የፖለቲከላ አለማረጋጋቶችና ግጭቶች፣ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም ከኮቪድ ጋር ተያይዘው የመጡ የማህበረሰብ የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች 2020ን ከባድ ጊዜ አድርገውት ነበር፡፡
ይህ በሚነሳበት ጊዜ በአለም ደረጃ የ 100 ሚሊዮን ሰዎች ህይወት የነጠቀው እና የመጀመሪያው የአለም ጦርነት የተጠናቀቀበት የ1918 አመት እጅግ የከፋው ዘመን ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ከዚህ ባለፈም ግማሽ አውሮፓን ጠራርጎ ያጠፋው እና በትንሹ 20 ሚሊዮን የአለም ህዝቦች ያለቁበት የ 1349 የብላክ ዴዝ መቅሰፍት በሰው ልጆች ታሪክ አንዲሁ የከፋው ዘመን ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ይሁንና እንደታሪክ ተመራማሪዎች ብያኔ 536 ዓ.ም ከየትኛውም ዘመን በላይ በሰው ልጆች ታሪክ እጅግ አስጨናቂውና አስከፊው ዘመን ነው፡፡
በ 536 ምንድን ነው ተከሰተው
በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ የመካከለኛው ዘመን ታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ማኮርሚክ እንደሚሉት በ 536 የተከሰተው እጅግ የከበደ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ በሰዎች ልጆች ታሪክ ውስጥ እስካሁን ያልታየ ሁለንተናዊ ቀውስ እና የሰዎች እልቂት የፈጠረ ክስተት መሆኑን ይናገራሉ፡፡ በ 536 የመጀመሪያ ወራት ላይ በአይስላንድ የተነሳው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ከፍተኛ መጠን ያለው አመድ በከባቢ አየር ላይ በመልቀቅ አብዛኛው የአለም ክፍል በጭጋግ እንዲሸፈን ምክንያት ሆኖ ነበር፡፡ ይህ ጭጋግ የአሁኗን አውሮፓ ጨምሮ የመካካለኛው ምስራቅ እና የእስያን አብዛኛውን ክፍል ለ18 ወራት የቀን ጨለማ ውስጥ እንዲሆኑ አስገድዷቸዋል፡፡ በጊዜው የነበሩ የታሪክ ፀሃፍት እንዳስቀመጡት በእሳተ ገሞራ ፍንዳታው ምክንያት ፀሃይ ሰማያዊ ቀለም ይዛ የነበረች ሲሆን እኩለ ቀን ላይም የሰውነት ጥላዎችን መመልከት እጅግ ከባድ ነበር፡፡
በ 536 የነበሩት የጨለማ ወራት የቅዝቃዜ ወቅትን በማስከተል የበጋው ሙቀት በ2.5 ዲግሪ ሴልሼየስ እንዲወርድ ያስገደደ ሲሆን ይህም በ2300 አመታት ውስጥ እጅግ አደገኛው የቅዝቃዜ ውቅት እንዲሆን አስችሏል፡፡ ይህ የዘመን ክስተት ምድር ከፀሃይ የምታገኘውን ብርሃንና ሙቀት በማሳጣት መጠን የለሽ የሰብል ውድመት እንዲከተል እና ሰዎች ሊቋቋሙት ወዳማይችሉት አለምአቀፍ ረሃብ እንዲያመሩ አስገድዷቸዋል፡፡
ይህ የብዙዎችን ህይወት የቀጠፈ አስከፊ አደጋ በአለማችን እስካሁን ከታዩት ሰቆቃዎች የሚተካከለው እንደሌለ የሚናገሩት ፕሮፌሰር ማኮርሚክ 536ም ከየትኛውም ዘመን በላይ ለሰው ልጆች በህይወት ለመኖር እጅግ አስቸጋሪ ከነበሩ ዘመናት ውስጥ በቀዳሚነት የምትቀመጥ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
ምንጭ፡ Bigthink
https://bigthink.com/politics.../worst-year-in-human-history
በዓለም ላይ ያሉ 195 ሀገራትን መጎብኘት የቻለችው ሴት
********************************
ጀሲካ ናቦንጎ ትባላለች፡፡ በአለም ላይ የሚገኙ ሆሉንም ሀገራት መጎብኘት የቻለች ብቸኛ ጥቁር ሴት ስትሆን ለዚህ ያበቃትም ምክንያት እንዲህ ትናገራለች፡፡ ነገሩ የተጀመረው በ2017 ነው፡፡ በኢንዶኖዢያዋ ባሊ ባደረገችው የሁለት ሳምንት የእረፍት ጊዜ ነው፡፡ በወቅቱ ጀሲካ በድርጅት ወስጥ ተቀጥራ ከምትሰራበት ለቅቃ ስራ ፈጣሪ መሆን የቻለች ሲሆን በመዝናናት ላይ እያለች አንድ ጽሁፍን ማንበብ ችላለች፡፡ ጽሁፉ ሁሉንም የአለማችን ሀገራት በፍጠነት በመጎብኘት በአለም ክብረወሰን ስሙን ስላስመዘገበው ካሴይ ዴ ፔኮል የሚናገር ነበር፡፡
ይህንን ጽሁፍ ካነበበች በኋላ ጀሲካ በዚህ ረገድ በሁሉም የአለም ሀገራ እግሯን ማሳረፍ የቻለች የመጀመሪያዋ ጥቁት ሴት ለመሆን ተነሳሳች፡፡ እንስቷ ጉዞን ከሚወዱ ቤተሰቦች የተወለደች በመሆኗ የጎዞ ማስታወሻ ይዛ መጓዝ ከመጀመሯ በፊት 65 ሀገራትን ማዳረስ ችላለች፡፡ ጀሲካ ናቦንጎ በአጠቃላይ 193 የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገራትንና ተጨማሪ አባል ያልሆኑ ቅዱሱ ውሃ እና ፍሊስጤምን መጎብኘት ችላለች፡፡ ጉዞዋንም ጥቅምት ስድስት 2019 Seychelles በተባለው የምስራቅ አፍሪካ ደሴት አጠናቅቃለች፡፡
በጉዞ ውስጥ መጓዝ ብቻውን ወይም የሀገራቱ ቁጥር ብቻውን ትልቅ ጉዳይ እንዳልሆነ የተረዳችው ጀሲካ በጉዞዋ ጸሐፊ፣ የፎቶ ባለሙያ፣ በቱሪዝም ላይ ልዩ ፍላጎት ያላት ሴት መሆን ችላለች፡፡ አሁን ላይ ከናሽናል ጆግራፊክ ጋር በመሆን ስለተመረጦ 100 ሀገራት የሚተርክ መጽሀፍን በማዘጋጀት ላይ ስትሆን መጽሀፉም በ2022 ይታተማል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
ተጓዧ እንስት ለናሽናል ጆግራፊክ ባደረገችው ቃለ ምልልስ በአለም ላይ የሚኖሩ ህዝቦችን የተለያየ የአኗኗር ዘይቤ መመልከት እጅግ ቀልቧን ገዝቶት እንደነበር ተናግራለች፡፡
ምንጭ National geographic
ተጨማሪ ንባብ https://www.nationalgeographic.com/travel/article/she-visited-every-country-on-earth-heres-what-she-learned?cmpid=org=ngp::mc=social::src=facebook::cmp=editorial::add=fb20210421travel-jessicanabongotravels&sf245134823=1&fbclid=IwAR3y1CS5BGI6F97Xl-h2TjaEWxNM7tUVyEqhTY0jb22NUgXSi6TxUJnqC80
ዘመን ባንክ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የቅድመ ክፍያ የጉዞ ካርድ አስተዋወቀ
=========================
ዘመን ባንክ ከማስተር ካርድ ጋራ በመተባበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ያለ ጥሬ ገንዘብ ለበረራና ሆቴል ለማስያዝ ግልጋሎት የሚውል የቅድመ ክፍያ የጉዞ ካርድ ይፋ አድርጓል፡፡ ባንኩ በተጨማሪም የኤቲኤም ማሽኖቹን ከካሽ አልባ ክፍያዎች ጋራ እንዲቆራኝ ማድረግ መቻሉ ተነግሯል፡፡ የካርዱ ተጠቃሚዎች ዩሮ ወይም ዶላርን መጠቀም የሚችሉ ሲሆን ወደፊት ግን እንደየ አካባቢው ፍላጎት ከማስተር ካርድ ጋራ በመሆን ሌሎች የገንዘብ አይነቶቸንም በዚህ አገልግሎት ውስጥ ተካታች ለማድረግ እንደሚሰራ የባንኩን ኃላፊዎች ጠቅሶ ፎርቹን ዘግቧል፡፡
ሌላኛው ይህ ካርድ ይሰጠዋል የተባው ጥቅም ደንበኞች በዓለም ዙርያ ባሉት ከማስተር ካርድ ጋራ የተሳሰሩ ኤቲኤም ማሽኖች እና የገንዘብ ዝውውር ስርዓቶችን መጠቀም እንዲችሉ ማድረጉ ነው፡፡ በተጨማሪም የአገልግሎቱ ደንበኞች እንደ ጉዞው ዓላማ እስከ አስር ሺህ ዶላር ድረስ በካርዱ እንዲያንቀሳቅሱ ያስችላቸዋል፡፡
የዘመን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ዘበነ ባንኮች እንዲህ ዓይነት አገልግሎቶችን መስጠት እንዲችሉ ብሔራዊ ባንክ መፍቀዱን አድንቀው በአገልግሎቱ አማካኝነት በተለያዩ ሀገራት የሚጓዙ ደንበኞቻቸውን ጥሬ ገንዘብ ሳይዙ እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ መቻሉ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡ ዘመን ባንክ በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ የባንክ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ ረገድ ቀዳሚ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህ አዲስ አገልግሎትም ለሀገራችን የኢ-ኮሜርስ እድገት መንገድ ጠራጊ መሆኑን እንደሚያምኑ አክለዋል፡፡
የማስተርካርድ ከሰሀራ በታች አፍሪካ ኃላፊ ራንጋቭ ፕራሳድ በበኩላቸው ያለ ጥሬ ገንዘብ የሚንቀሳቀስ ማህበረሰብን በኢትዮጵያ ለመፍጠር ኢኖቬሽን ቁልፍ ሚናን እንደሚጫወት ጠቅሰው ኩባንያቸውም ጠቃሚ የዲጂታል ክፍያ ስርዓቶችን ለደንበኞች ለማቅረብ ቁርጠኛ መሆኑንና ከዘመን ባንክ ጋር የመሰረቱት ትብብርም የዚህ ማሳያ መሆኑን ተናግሯል፡፡
ባንኩ ከዚህ በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የሶፍትዌር አቅራቢ ኩባንያ ከሆነው ሲአርቱ ጋር በመተባበር የሞባይል እና በይነ-መረብ ባንኪንግ ስርዓትን መዘርጋቱ ተነግሯል፡፡ ይህ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የተለያዩ ጠቀሜታዎች ያሉት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ዜድ-ካሽ የተባለውና ደንበኞች በተንቀሳቃሽ ስልካቸው አማካኝነት ቮቸር በማቅረብ ብቻ ከኤቲኤም ማሽኖች ገንዘብ ማውጣት የሚችሉበት እነዲሁም ዜድ-ዋሌት የተሰኘው ደንበኞች የዘመን ባንክ አካውንት ለሌላቸው ሰዎች የሞባይል ዋሌት በመፍጠር ገንዘብ መላክ የሚችሉበት አገልግሎት ይጠቀሳሉ፡፡
ምንጭ፤ Fortune እና africa.com
ለተጨማሪ ንባብ https://addisfortune.news/zemen-bank-rolls-out.../...
https://africa.com/zemen-bank-and-mastercard-partner-to.../
መንታ እህቷን በውስጧ ይዛ የተወለደችው ህጻን
*****************************
በኮሎምቢያ አንዲት እናት በአስገራሚ መልኩ ሁለት ሴት ልጆችን ወልዳለች፡፡ አስገራሚው ነገር የቁጥሩ እንዳልሆነ አምስትና ስድስት አንዳንዴም ከፍያለ ቁጥር ያላቸው መንትዮች መወለዳቸው ስለሚሰማ መረዳት ይቻላል፡፡ የዚህችን ሴት ውልደት አስገራሚ ያደረገው አንዷ ህጻን የተወለደችው በእህቷ ውስጥ ሆና መወለዷ ነው፡፡ ሁለተኛዋ ህጻን በእህቷ ሆድ ውስጥ ሆና መወለዷ በጣም ያልተለመደ ቢሆንም ፈጽሞ ያልተከሰተ ግን አይደለም፡፡ እስካሁን በሳይንስ ታሪክ ውስጥ መቶ የሚደርሱ ተመሳሳይ ክስተቶች ተመዝግበዋል፡፡
ጉዳዩ የታወቀው በ35ኛው የእርግዝና ሳምንት ሲሆን በህጻኗ ሆድ ውስጥ ያለው ሽል እንደሆነ በተደረገ የአልትራሳውንድ ምርመራ ተረጋግጧል፡፡ እናትየዋ በ37ኛው ሳምንት የተገላገለች ሲሆን 3.2 በሆነ የጤነኛ ህጻን ክብደት ያላት ልጅንም ታቅፋለች፡፡ ሁኔታው fetus-in-fetu ነው ብለው ያመኑት ዶክተሮች ከአንድ ቀን በኋላ በህጻኗ ውስጥ ያለውን ሽል ለማስወጣት በማሰብ ምርመራ የጀመሩት ሀኪሞች በዚህ ወቅት ያስተዋሉት ነገን እጅግ ሳያስገርማቸው አልቀረም፡፡
በህጻኗ ውስጥ ያለውን ሽል ለማውጣት በተዘጋጁበት ወቅት ሀኪሞቹ ያስተዋሉት ይህ ሽል አሁንም እያደገ ያለና በህይወት ያለ መሆኑን ነው፡፡ መንትያው ሽል 14 ሚሊሜትር የሚረዝም ሲሆን የራሱ የሆነ ልብና ጭንቅላት የሌለው ነው፡፡ ሁኔታውን ለእናትየዋ የተናገሩት ሀኪሞች እናትየዋ ሁኔታውን አስተውላው እንደማታውቅ ተናግራለች፡፡ ሀኪሞቹም ሁለቱን ህጻናት ያገናኘውን የእንግዴ ልጅ መስመር (umbilical cord) ሲቆርጡት ሽሉ ሞቷል፡፡ ቀሪዋ ህጻንም አሁን ላይ በሙሉ ጤንነት ላይ እንዳለች ሀኪሞቹ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡ iflscience
ተጨማሪ ንባብ፡ https://www.iflscience.com/health-and-medicine/baby-girl-born-with-her-twin-living-inside-her/?fbclid=IwAR2bsIvwNQk_rlGOtV2-V_2qFJeKYX4WnsEA37JCQRfcr57Tyh9IE96W780
የመጀመሪያው ኦክስጅን ከማርስ
*********************
ማርስ ላይ ያለውን እምቅ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ወደ ኦክስጅን በመለወጥ ለወደፊት በማርስ ላይ ለታሰበው ህይወትና ሌሎች ተግባራት መሳካት የመጀመሪያ የሚባሉ ሙከራዎች እየተደረጉ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በተሰሙ መረጃዎች የማርስን ከባቢ አየር መሰረት ያደረጉ ህንጻዎች የሚገነቡበት ዲዛይን እንዲሁም በሚሰሩት ከተሞች መንቀሳቀስ የሚያስችሉ የትራስፖርት አማራጮች በንድፍ ደረጃ እየተሰሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ማርስ ላይ ከዚህ በተጨማሪ የኦክስጅን ጉዳይ ሌላው ከፍተኛ ምርምር እየተደረገበት ያለ ዘርፍ ነው፡፡
ከየካቲት ወር ጀምሮ ላለፉት 60 ቀናት ከማርስ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ኦክስጅንን መስራት የሚያስችሉ የተለያዩ ሙከራዎች ሲሰሩ እንደነበር የመረጃ ምንጫችን ናሳን ዋቢ አድርጎ የሰራው ዘገባ ያመለክታል፡፡ ይህ ጥናት ወደ ውጤት የሚያመራ ከሆነ የሳይንስ ልቦለድ ታሪኮችን እውነት የመሆን እድል እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ አሁን ላይ የመጀመሪያ በሚባል ሙከራ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የመጀመሪያ የሆነውን ኦክስጅን ከማርስ ማግኘት ተችሏል፡፡ ይህ ሙከራ ማደግ ከቻለ ተመራማሪዎች ከማርስ ወደ ምድር ለመመለስ የሚያስፈልጋቸውን የሮኬት ሀይል ከዚያው ከማርስ እንዲያገኙ ሲያደርጋቸው ከፍ ሲልም ሊተነፍሱት የሚችሉትን አየር ማግኘት ያስችላቸዋል የሚል ተስፋን ሰንቋል፡፡
እንደሚታወቀው የማርስ ከባቢ አየር በ96 በመቶ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ የተሸፈነ ነው፡፡ ይህ MOXIE የተሰኘ የናሳ ቴክኖሎጂ ከካርቦን ዳይ ኦክሳይድ በከፍተኛ ሙቀት አማካኝነት የኦክስጅንና የካርቦን ቅንጣቶችን የመለያየት ተግባር በመስራት ከዚህ የሚገኘውን የካርቦን ሞኖ ኦክሳይድ ተረፈ ምርት ወደ ማርስ ከባቢ አየር ይለቃል፡፡ በመጀመሪየው ሙከራ ለ10 ደቂቃ መተንፈስ የሚያስችል 5 ግራም ኦክስጅንን ማምረት ተችሏል፡፡
ምንጭ technology.org
ተጨማሪ ንባብ https://www.technology.org/2021/04/22/nasas-perseverance-mars-rover-extracts-first-oxygen-from-red-planet/?fbclid=IwAR3zlI199iEN2zYImmyQqDk5abPEwfQV4Efpzj8dAd9oNRwt8HUhqmJV4O8
በኢንስቲትዩቱ አዘጋጅነት የተካሄደው የኢትዮጵያ የምርምር ተቋማት የምክክር መድረክ
=========================
በኢትዮጵያ ያሉ የምርምር መሰረተ ልማቶች ትብብር ላይ ያተኮረ ሀገር ዓቀፍ የምክክር መድረክ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ተካሂዷል፡፡ Research infrastructure for national competitiveness በሚል ርዕስ ትናንት ሲካሄድ የዋለው የምክክር መድረኩ በሀገራዊ የምርምር መሰረተ ልማቶች እና ተያያዥ አስቻይ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት እና ሌሎች መሰናዶዎችን ያካተተ ነበር፡፡
በፓናል ውይይቱ በዋናነት እንደ ሀገር ከምርምር ጋር ተያያዘው የሚነሱ የሰው ሀብት አያያዝ፣ የፖሊሲና ግብዓት አቅርቦት ችግር፣ የምርምሮች ሀገራዊ እርባና፣ ማበረታቻ እና የተቋማት ስፔሻላይዜሽን ላይ ያውጠነጠኑ ሀሳቦች ተነስተውበታል፡፡
ውይይቱን በጋራ የመሩት የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት እንዲሁም የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ሙሉቀን ቀሬና ዶ/ር ካሳሁን ተስፋዬ በተነሱት ጉዳዮች ላይ ምላሽ ሰጥተውባቸዋል፡፡ የተነሱት ጥያቄዎች አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን ያወሱት አቶ ሙሉቀን ቀሬ የሚመሩት ኢንስቲትዩት ከባዩ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር መመስረት የቻለውን ጥምረት በምሳሌነት በመጥቀስ ተቋማቱ በጋራ በሚሰሩበት መንገድ ላይ ብሎም የፕሮኪውርመንት ፖሊሲ ዝግጅት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን አንፀባርቀዋል፡፡ በተጨማሪም በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦች ከቃል ባለፈ ወደ ተግባር ይለወጡ ዘንድ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ካሳሁን በበኩላቸው መንግስታዊ የግዢ ሕጉ የምርምር ተቋማትን እንዲያሰራ ሆኖ እየተዘጋጀ መሆኑን ለታዳሚው ተናግረዋል፡፡ በስፔሻላይዜሽን ረገድም በመሰረቱ የተቋማት በየቦታው መገንባት ስህተት ባይሆንም ሁሉንም የልህቀት ማዕከል ለማድረግ መሞከሩ ግን የተሳሳተ መሆኑን ዶ/ር ካሳሁን ተናግረዋል፡፡ ለተመራማሪዎች በሚሰጡ የድጋፍ እና ማበረታቻ ስራዎችም ማሻሻያ ተደርጎባቸው በስራ ላይ መዋላቸው እንደሚቀጥል አስቀምጠዋል፡፡
ከፓናል ውይይቱ ባሻገር መንደርደርያ የሆኑ ማብራርያዎች በተጋባዥ ምሁራን እና የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች ቀርበዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሳይንስ እና ኦኖቬሽን ፖሊሲ አላማ እንዲሁም አቅጣጫና ስትራቴጂዎች ላይ ያተኮረ ማብራርያ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ተሾመ ሳህለማርያም ቀርቧል፡፡ በኢንስቲትዩቲ ማንነት፣ ስልጣንና ተግባራት እንዲሁም ስኬቶች ላይ ደግሞ ወ/ሮ ህልውና ማሜ የተወሰነ ገለፃ አድርገዋል፡፡
በሌላ መልኩ በኢትዮጵያ የምርምር መሰረተ ልማት ስነ-ምህዳር እና የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ላይ ያተኮረ ማብራርያ በዶ/ር አብረሀም ደበበ፣ በምርምር ማዕከላት የኢኖቬሽን ስራዎች፣ የተመረጡ የአስተዳደር ተግባራትና የህግ ማሻሻያዎች እንዲሁም ህብረቶች ላይ ዶ/ር መላኩ ደረጀ በመጨረሻም አቶ ወገኔ ደምሴ የኢትዮጵያ የምርምር ማዕከላትን በሚለይ እና በሚያስተሳስር ፕሮጀክት ዙርያ ገለፃቸውን አቅርበዋል፡፡
የምክክር መድረኩን አስመልክቶ ያነጋገርናቸው የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬተር ኢ/ር ተሾመ ሳህለማርያም መድረኩ የምርምር መሰረተ ልማቶችን ማስተሳሰር እና ማን ምን እየሰራ መሆኑን ማወቅን በዓላማነት ያነገበ መሆኑን ገልፀውልናል፡፡ አያይዘውም መንግስት በኢኖቬሽን ዙርያ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ስለመሆኑና የተቀመጡ ተግዳሮቶችም በጊዜ ሂደት እየተፈቱ እንደሚሄዱ ተናግረዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ከሀገራችን ልዩ ልዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የምርምር ማዕከላት እና የሚመለከታቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ምሁራን ተሳታፊ ሆነውበት አልፏል፡፡
ሩስያ የራሷን የጠፈር ላይ ጣብያ ልትገነባ ነው
========================
በአሜሪካኑ የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ እና በሩስያ አቻው ሮስኮዝሞስ ትብብር እ.አ.አ በ1998 ወደ ጠፈር የተላከው ዓለም አቀፉ የጠፈር ጣብያ እስከዛሬ ድረስ ግምባር ቀደም ሆኖ በግልጋሎት ላይ ይገኛል፡፡ ታድያ ይህ ለ23 ዓመታት በሩስያ እና አሜሪካን ትብብር ማሳያ ሆኖ የቆመ ጣብያ ጉዞ በቅርቡ ሊቋጭ እንደሚችል የሩስያ ባለስልጣናት ጠቁመዋል፡፡ የሩስያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዩሪ ቦሪሶቭ ሩሲያ በአውሮፓውያኑ 2025 ከዓለም አቀፉ የጠፈር ምርምር ጣብያ እንደምትለቅ መናገራቸው በሀገሪቱ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡
እንደ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሆነ በዓለም አቀፉ ጠፈር ጣብያ ላይ ከእርጅና ጋር ተያይዞ እየታዩ ያሉት ጉዳቶች ለውሳኔው በዋና ምክንያትነት አስቀምጠዋል፡፡ የጣብያው መዋቅር እና ብረቶች ማርጀታቸውን የተናገሩት ዩሪ ቦሪሶቭ ነገሮች ወደ አደገኛ ሁኔታ ሊያመሩ እንደሚችሉና እነርሱም የጠፈር ተመራማሪዎቻቸውን ህይወት አደጋ ላይ መጣል እንደማይፍልጉ ተናግረዋል፡፡
ከሮስኮዝሞስ ኃላፊዎች ዘንድ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩትም አሁን ላይ የሀገሪቱ ብሄራዊ ጠፈር ጣብያ ግንባታ የተጀመረ ሲሆን ከዚህ ቀደም በአውሮፓውያኑ 1970 እና 80ዎቹ ወደ ጠፈር ተልከው የነበሩት ሳሊዉት እና ሚር ጣብያዎችን እንደሚተካ ታውቋል፡፡ የተቋሙ ዋና መሪ ዲሚትሪ ራጎዚያንም በተመሳሳይ የጣብያው ስራ በአውሮፓውያኑ 2025 ሊጠናቀቅ ስለመቻሉ ተናግረዋለ፡፡ ሆኖም ሩሲያ የዚህ ጣብያ ስራ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከዓለም አቀፉ የጠፈር ምርምር ጣብያ ለቃ እንደማትወጣ አስታውቀዋል፡፡
ይህ ውሳኔ በዓለም አቀፉ የጠፈር ጣብያ ላይ ጥገኛ ለሆኑት አሜሪካን እና ሌሎች ሀገራት የስራ ጫናን እንደሚፈጥርባቸው ተነግሯል፡፡ ባለ አነስተኛ ወጪ ሳተላይቶችን በማምረት የሚታወቀው ዳውሪያ ኩባንያ የቀድሞ ቃል አቀባይ ቪታሊ ኢጎሮቭ እንደሚሉት ያለ ሩሲያ አጋዥነት ሌሎቹ ሀገራት የጠፈር ጣብያውን መቆጣጠሩ ከባድ ቢሆንባቸውም በስፔስ-ኤክስ የሚቀርቡት የሰውና እቃ ማጓጓዝ አገልግሎቶች ይህን ክፍተት ሊሞሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፤ Live Science
ለተጨማሪ https://www.livescience.com/russia-leaving-international-space-station.html
ሀገራትን የሚያገናኙ 5 የመዋሰኛ ድልድዮች
=======================
የመሸጋገሪያ ድልድይ ስራዎች ከሰው ልጆች እድገት ጋር በፍጥነት እየተለዋወጡ የመጡ ግኝቶች ናቸው:: ትልልቅ ዛፎችን አግድም በመጣል መሸጋሪያ ከመፍጠር ጀምሮ የገመድ ድልድዮች እና የደረጃ ድንጋዮች እስከ ዘመናዊ የእግረኛ መንገዶች ድረስ የመሸጋገሪያ ድልድይ ስራዎች ረዥም የምህንድስና እድገት የታየባቸው ወሳኝ ግኝቶች ናቸው፡፡ አንድን የየብስ ክፍል ከሌላ የየብስ ክፍል ጋር ለማገኛኘት ጥቅም ላይ የሚውሉት የድልድይ ስራዎች በዘመናዊው የሰው ልጅ ታሪክ የሀገራትን የንግድ እንቅስቃሴ ለማፋጠን እና የማህበራዊ መስተጋብርን ለማሳደግ ትልቅ ጥቅም ሰተው አልፈዋል፡፡
አሁን ላይ በአለማችን ሀገራትን ከሀገራት የሚያገናኙ ትልልቅ የመሸጋገሪያ ድልድዮች በብዛት የሚገኙ ሲሆን ለሚጋሯቸው ሀገራትም ትልቅ የኢኮኖሚ ጥቅም ከማስገኘት አልፎ የህዝቦችን የእርስ በእርስ ግንኙነት ለማጠናከርና ለማሳደግም ትልቅ እድል ይፈጥራል፡፡ በውብ የስነ-ሕንፃ ምህንድስናቸው ለቱሪስት መስህብነት ሳይቀር ጥቅም ላይ ከሚውሉት የተለያዩ የድንበር መሸጋገሪያዎች መካከል 5 አስገራሚ አለም አቀፍ ድልድዮችን በጥቂቱ ልናስቃኛችሁ ወደድን፡፡
1. አምባሳደር ብሪጅ የአሜሪካና የካናዳ ድንበር
በሚቺጋን ግዛት የምተገኘውን ዲትሮይት ከተማ ከካናዳዋ ኦንታሪዮ ግዛት የሚያዋስነውና የሚያገናኘው አምባሳደር በሪጅ በሰሜን አሜሪካ ውስጥ በብዛት ከሚገኙ ድልድዮች ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድበት መሸጋገሪያ ድልድይ ነው፡፡ ሁለቱ ሀገራት ካላቸው የንግድ አንቅስቃሴ 27 በመቶው በዚህ ድልድይ ላይ የሚካሄድ ሲሆን ሁለቱ ሀገራት ከላቸው ተመሳሳይ የድንበር መሸጋገሪያዎች ውስጥም በቀዳሚነት የሚጠራ ነው፡፡ እንደአውሮፓውያኑ በ1927 ስራው ተጀምሮ ከ1929 አንስቶ ግልጋሎት መስጠት የጀመረው ይህ ድልድይ በጥቅሉ 7,545 ጫማ ወይም 2,300 ሜትር ርዝመት እንዳለው ይነገራል፡፡
2. ስሪ ካንትሪስ ብሪጅ የፈንሳይ ጀርመንና ስዊዘርላንድ ድንበር
የሶስቱ ሀገራት የድንበር መዋሰኛ በሆነው ራይን ወንዝ ላይ የተዘረጋው ይህ አስገራሚ የመሸጋገሪያ ድልድይ በዋናነት በፈረንሳይ እና ጀርመን መካካል የተዘረጋ ደልድይ ቢሆንም በተወሰነ ክፍል የስዊዘርላንድ ከተማ የሆነቸውን ባዜል ያገናኛል፡፡ ሲንግል ስፓን ተብለው ከሚጠሩት የድልድይ አይነቶች በርዝመቱ በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ስሪ ካንትሪስ ብሪጅ ከተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ በዋናነት ለእግረኞች እና ለብስክሌተኞች መጓጓዣ የሚያገለግል ነው፡፡ እንደአውሮፓውያኑ በ2007 ስራ የጀመረው ይህ ደልድይ አጠቃላይ ርዝመቱም 248 ሜትር ይደርሳል፡፡
3. ቪክቶሮያ ፎልስ ብሪጅ የዚምባብዌ እና ዛምቢያ ድንበር
በአፍሪካ በርዝመቱ በአራተኝነት በሚቀመጠው የዛምቤዚ ወንዝ ላይ የሚገኘው የቪክቶሪያ ፏፏቴ የሁለቱ ሀገራት መዋሰኛ ድንበር ሲሆን ቪክቶሮያ ፎልስ ብሪጅ ደግሞ ሀገራቱን ለማገናኘት የተዘረጋ ውብ የመገናኛ ድልድይ ነው፡፡ ከዚምባብዌ ቪክቶሮያ ፎልስን ከዛምቢያ ደግሞ የሊቪንግስተን ከተማን የሚያገናኘው ይህ ድልድይ የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች በኢኮኖሚና በንግድ ያስተሳሰረ ሲሆን በዋናነት ለመንገድ፣ ባቡርና እግረኞች መጓጓዣነት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ እንደአውሮፓውያኑ በ1904 የግንባታ ስራው ተጀምሮ ከ1905 አንስቶ ማገልገል የጀመረው ይህ የመሸጋገሪያ ድልድይ 429 ጫማ ወይም 198 ሜትር እንደሚረዝምም ይነገራል፡፡
4. የታጃክና አፍጋን ፍሬንድሺፕ ብሪጅ
በሁለቱ ሀገራት የድንበር መዋሰኛ በሆነው የፓንጅ ወንዝ ላይ የተዘረጋው ይህ የታጃኪስታን እና የአፍጋኒስታን የመሸጋገሪያ ድልድይ እንደአውሮፓውያኑ በ2007 ስራውን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለሃገራቱ የንድግ እንቅስቃሴ እና የህዝቦች ትስስር ትልቅ ሚና የተወጣ ድልድይ ነው፡፡ በአሰራር ይዘቱ ቀላል ወይም ገርደር ብሪጅ ከሚባሉት የሚመደበው ይህ የመሸጋገሪያ ድልድይ በጥቅሉ 672 ሜትር እንደሚረዝምም ይነገራል፡፡
5. ጓዲያና ኢንተርናሽናል ብሪጅ የስፔን እና ፖርቹጋል ድንበር
በሁለቱ ሀገራት የድንበር መዋሰኛ በሆነው ጓዲያና ወንዝ ላይ የተዘረጋው ይህ የመሸጋገሪያ ድልድይ ከስፔን ኣያሞንቴ የተባለችውን ደቡባዊ ከተማ ከፖርቹጋል ደግሞ ካስትሮ ማሪም የተባለችውን ትንሽዬ ከተማ የሚዋስንና የሚያገናኝ ድልድይ ነው፡፡ ከሁለቱ ሀገራት የሚመጡ መንገደኞችንና ተጓዦችን የሚያገናኘው ይህ ድልድይ ለንግድ እንቅስቃሴዎችና ለቱሪስት መስህብነት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ በአሰራር ይዘቱ ኬብል ስቴይድ ብሬጅ የሚባለው ይህ የመሸጋገሪያ ድልድይ እንደአውሮፓውያኑ በ1991 ስራውን የጀመረ ሲሆን፤ በጥቅሉም 666 ሜትር እንደሚረዝም ይነገራል፡፡
https://interestingengineering.com/-coolest-bridges-cross...
አስገራሚ ውጤት ያስገኘው የእጅ ንቅለ ተከላ
**************************************
በህንድ ሀኪሞች በቅርብ ጊዜ ለአንዲት ታካሚ የእጅ ንቅለ ተከላ አድርገውላት ነበር፡፡ ሸሪያ ሲዳናጎውዳ የተባለች የ19 ዓመት ወጣት በ2017 ለሁለት እጆቿ ንቅለ ተከላ አሰርታ ነበር፡፡ ጉዳቱ የገጠማት በደረሰባት የመኪና አደጋ ምክንያት ሲሆን በወቅቱ ሁለት እጆቿን አጥታ ነበር፡፡ ጉዳቱ ክርን እስከሚባለው መካከለኛ የእጅ ክፍል የገጠማት ሲሆን ጉዳቱ በደረሰባት ሰሞን ከሞተ አንድ ወጣት እጅ እንድታገኝ ተደረገ፡፡ የእጅ ንቅለ ተከላው በታካሚዋ የሰውነት ቆዳ እና አዲስ ባገኘችው እጅ ቆዳ ቀለም መካከል የተወሰነ መለያየት ከመኖሩ ውጭ በስኬት የተጠናቀቀ እንደነበር ሀኪሞቿ ተናግረዋል፡፡
አስገራሚው ነገር መታወቅ የጀመረው በያዝነው 2021 ነው፡፡ ይኸውም ታጊዋ የተሰጣት እጅ ከጊዜ ወደ ጊዜ የመንጣት ባህሪ እያሳየና ከቀሪው የሰውነት ክፍሏጋር እየተመሳሰለ መምጣቱ ነው፡፡ ሀኪሞቹ ይህ እንዴት ሊከሰት እንደቻለ ማስረዳት ሳይቸገሩ አልቀረም፡፡ ለዚህም በምክንያትነት የተጠቀሰው ተመሳሳይ ክስተቶች ተስተውለው አለማወቃቸው ነው፡፡
ዶክተሮቹ ጉዳዩን በጥብቅ እየተከታተሉት ሲሆን አሁን ላይ ያላቸው ግምት ለሰውነት ቆዳ እና ለፀጉር ቀለም ምክንያት የሆነው ሜላኒን የተሰኘ ተፈጥሯዊ ውህድ በሰውነቷ መመረቱ ነው የሚል ነው፡፡ በሌላም በኩል የተቀየረው እጅ በተፈጥሮ ቀለሙን እየለወጠ ሊሆን ይችላል የሚል መላምት አስቀምጠዋል፡፡
ከዚህ በፊትም በዚሁ ሆስፒታል የእጅ ንቅለ ተከላ የተደረገለት አንድ የአፍጋኒስታን ወታደር ተመሳሳይ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደተስተዋለበት የህንዱ አምሪታ ሆስፒታል ዶክተሮች ተናግረዋል፡፡ በዘርፉ ስራ የተጀመረው በ1998 ዓም ሲሆን ላለፉት 25 ዓመታት ከ100 ያነሱ የእጅ ንቅለ ተከላዎች በተለያየ ደረጃ ተደርገዋል፡፡
ምንጭ iflscience
ተጨማሪ ንባብ https://www.iflscience.com/health-and-medicine/doctors-baffled-by-transplant-patients-new-hands-changing-color/?fbclid=IwAR0Xy2CxQyczNs-nAj1P1EKfrVHMzGkxcDrhFU8aqCs05DvnsbCXO1zSVAk