የወንዝ ዳር መዝናኛዎች መጨናነቅን የሚቆጣጠረው መተግበሪያ
***************************
እንግሊዝ ባሳለፍነው ዓመት ለኮቪድ 19 ስርጭት ዋነኛ ምክንያት የሆነውን የአካላዊ ቅርርብን ለመቆጣጠር በሚል የተሰራን አንድ መተግበሪያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የወንዝ ዳር መዝናኛዎችን መጨናነቅ ለመቆጣጠር እንዲውል እያደረገች እንደሆነ ተሰማ፡፡ በአንድ BCP በተባለ ድርጅት የተሰራው ይህ መተግበሪያ ባሳለፍነው የፈረንጆች አመት ሰዎች በብዛት ወደ ወንዝ ዳር መዝናኛዎች መጉረፍ መጀመራቸውን ተከትሎ የተሰራ ሲሆን አሁን ላይ አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ ባለው አስተዋጽኦ ምክንያት በሁሉም የእንግሊዝ ከተሞች ጥቅም ላይ እንዲውል በመመሪያ የተደገፈ የበጀት ድጋፍ ተደርጎለታል፡፡
መተግበሪያውን የሰራው ድርጅት 55 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ የተደረገለት ሲሆን ድጋፉም መተግበሪያውን ለማሻሻልና ወደ ስራ ለማስገባት ያለመ ነው፡፡ መተግበሪያው ከሰዎች በተጨማሪ ሌሎች እንደ መኪና ማቆሚያና መንገዶች ያሉ መጨናነቆችን መቆጣጠር የሚያስችል እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡ መተግበሪያው በአንድ የሐይቅ ዳር መዝናኛ ያለውን የሰዎች እንቅስቃሴ እና ብዛት ለተጠቃሚዎች የሚያሳውቅ ሲሆን ለተቋማትም ልዩ ልዩ የአስተዳደርና የመስተንግዶ ስራዎችን በቀላሉ እንዲሰሩ ያስችላቸዋል፡፡
መተግበሪያው እንደ አካባቢው ሁኔታ ለተጠቃሚዎች ሶስት አይነት ቀለማትን የሚያመላክት ሲሆን በጣም የተጨነናነቀ ቦታ ሲሆን ቀይ በተቃራኒው ለእንቅስቃሴ ምቹ ሲሆን ደግሞ አረንጓዴ ምልክቶችን ያሳያል፡፡ መተግበሪያው በአሁኑ ሰዓት በሙሉ የእንግሊዝ ግዛቶች በነጻ የቀረበ ሲሆን ለቀጣይ አንድ አመታት አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል አበልጻጊው ድርጅት ከእንግሊዝ መንግስት 110 ሺህ ይሮ ለመጠየቅ እንዳሰበም ይፋ አድርጓል፡፡
ምንጭ cities-today

በቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያ የተሰሩት ሮቦት ውሾች
******************************
በጣም ፈጣን የሆነና ትእዛዝ አክባሪ የሮቦት ውሻ በቻይና መሰራቱ ተሰምቷል፡፡ ይህ አልፋ ዶግ የተሰኘው ሮቦት ውሻ የቻይናን በቤት እንስሳትና በቴክኖሎጂ ላይ ያላትን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነው ተብሎለታል፡፡ ውሻው ከፍተኛ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ አካባቢውን ማየትና መስማት የሚያችል ብቃት ያለው ሲሆን ውደ ውጭ ይዘውት ወጥተው አብረውት ሊንቀሳቀሱ የሚችሉት ነው፡፡
ሮቦቱን ያመረተው ድርጅት ዌይላን የቴክኖሎጂ ሙያተኛ የሆኑት ማ ጄይ ሮቦቶ ከተፈጥሯዊው ውሻ ጋር ብዙ የሚያመሳስለው ነገር እንዳለ ተናግረዋል፡፡ የፈጠራ ባለቤቶቹ የሰሩት ሮቦት በሰዓት 15 ኪሎሜትሮች ያክል መጓዝ የሚችል እንደሆነና በዘርፉ ገበያ ላይ ካሉት በጣም ፈጣኑ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከብረት የተሰሩት አራቱ እግሮቹ ከተፈጥሯዊው ውሻ የተሸለ የተረጋጋ አካሄድ እንዲኖረው አድርጎታል ብለው እንደሚያስቡ የመረጃ ምንጫችን አስነብቧል፡፡
ሮቦቱ በራሱ መንቀሳቀስ እንዲችል ፈጣን የሆነ የአምስተኛ ትውልድ ኔትወርክን የፈጠራ ባለቤቶቹ የተጠቀሙ ሲሆን የ5G ቴክኖሎጂን መጠቀማቸው ችግር በሚገጥመው ጊዜ አፋጣኝ መልስ መስጠት እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡ በመጀመሪያው የሽያጭ ወር 1800 ሮቦቶች የተሸጡ ሲሆን ዋጋቸውም 2400 የአሜሪካን ዶላር ወይም 16 ሺህ የቻይና ገንዘብ ነው፡፡ እንደ ሽያጭ ድርጅቱ መረጃ ከሆነ አብዛኛው ትእዛዝ የሚመጣው ከኮምፒውተር አበልጻጊዎች፣ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ከሚሰሩና ምርቱን ይወዱታል ተብለው ከተጠበቁት ከህጻናት ነው፡፡
ምንጭ Tech xplore

የጂ.አይ.ኤስ ቴክኖሎጂ ዋና ዋና ክፍሎች
=====================
ጂ.አይ.ኤስ ወይም ጂዮግራፊካል ኢንፎርሜሽን ሲስተም የኮምፒዉተር አፕሊኬሽን ሶፍትዌር ሲሆን ከጠፈር ላይ የሚወሰዱ መረጃዎችን የምናስቀምጥበት እንዲሁም የተሰበሰበዉን (አውዳዊ) መረጃ በሚፈለገው ሁኔታ ከምስሎች ጋር በማያያዝ ለማሳይት የሚያስችል ነው። ይህ ሲሰተም የተለያዩ ቦታዎችን እርስ በርሳቸው በምን አይነት መንገድ እንደሚገናገኙ የሚያሳይ ሲሆን አፕሊኬሽን ሲስተሙም ከቦታ ጋር የተገናኘን ዳታ በቀላሉ ለማየት ያስችላል። የጂ.አይ.ኤስ ቴክኖሎጂ ዋና ዋና ክፍሎች፡
ሃርድዌር (Hardware) - በጂ.አይ.ኤስ (GIS) ሲስተም ውስጥ ሀርድዌር የምንለው የጂኦግራፊካል ኢንፎርሜሽን ሲስተም ሶፍትዌር የሚጫንበት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የተለያዩ አይነት ሀርድዌሮች ይገኛሉ። ከትልልቆቹ ሰርቨሮች ጀምሮ እስከ ዴስክቶፕና ታብሌቶች ድረስ በተለያዩ አውታር ዝርጋታዎች ላይ መጠቀም የሚቻል ሲሆን በመጠን፣ በአሰራር፣ በሚይዙት የማስታወሻ ቦታ (memory capacity) እንዲሁም በዋጋ የተለያዩ ናቸው።
ሶፍትዌር (Software) የጂዮግራፊካል ኢንፎርሜሽን ሲስተም ሶፍትዌር ኮምፒውተር ላይ ከተጫነ በኋላ መረጃዎች የሚቀመጡበት፣ እንዲሁም በተሰበሰቡበት መረጃዎች ላይ ትንተና በማካሄድ ወደ ስነ መልክዓ ምድር መረጃነት የሚቀየርበት የቴክኖሎጂው ክፍል ነው።
መረጃ - ካሉት የጂ.አይ.ኤስ ክፍሎች መካከል በጣም ከፍተኛውን ስፍራ የሚይዝ ሲሆን ጂ.አይ. ኤስ ከጠፈር ላይ ሆኖ አውዳዊ መረጃዎችን በመሰብሰብና ሌሎች ጥሬ መረጃዎችን በአንድ ዳታ ቤዝ የሚያስተዳድር ሲስተም ላይ የሚቀመጥበት ስልት ነው። የጂ.አይ.ኤስ ሲስተም ብቻውን ያለ ሰው እርዳታ አገልግሎት ሊሰጥ አይችልም። ስለሆነም ይህንን ሲስተም እንዲሰራና ተግበራዊ እንዲሆን እንዲሁም የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን የሚቆጣጠሩት፣ የሚያስተዳድሩትና የጥገና እና የድጋፍ አገልግሎት የሚያገኙት በሰዎች አማካኝነት በመሆኑ ሰዎችም የዚህ ሲስተም አንዱ ክፍል ናቸው።
ዘዴዎች - ሃርድዌር እና ሶፍትዌር በምን ዘዴ መዋሀድ እንዳለባቸው፣ ምን ቴክኖሎጂና መሳሪያ ቢጠቀሙ ውጤታማ ይሆናሉ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሚስፈልግ ሲሆን በሳይንሳዊ ዘዴ አካሄድ የአሰራር ንድፎችንና ሕጎችን ከመከተል አንፃር በአጠቃላይ ስለሲስተሙ አስተማማኝ የአሰራር ሂደትን የሚከታተል ነው።
ምንጭ Frontierinternet

ለአይናችን እረፍት የሚሰጥ መተግበሪያ
***********************************
መቼም የአይን ነገር ሲነሳ በተለይ የኮምፒውተርና የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች ምን ተባለ ይሆን ማለት አለባቸው ብለን እናስባለን፡፡ ምክንያቱም ከኮምፒውተርና ከስልካችን ስክሪኖች የሚፈነጥቀው ሰማያዊ ብርሃን በከፍተኛ ሁኔታ አይናችንን እየጎዳው በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ችግር ከቴክኖሎጂና ከአጠቃቀም ጉድለት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ቢሆንም መፍትሔውንም ቴክኖሎጂ ይዞልን ቀርቧል፡፡ ይኸውም ጽሁፍን ወደ ድምጽ የሚቀይር መተግበሪያ ነው፡፡
ቴክኖሎጂን መጠቀም ማቆም የሚመከር ጉዳይ ባይሆንም አማራጭ መፍትሔዎችን መጠቀም ግን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም ነው የፈጠራ ባለሙያዎች Elocance የተሰኘ ጽሁፍን በንባብ የሚያሰማ መተግበሪያን ሰርተው ያቀረቡት፡፡ ይህም መተግበሪያ አንዴ በስልካችን ከጫንነው በኋላ ለሁል ጊዜ መስራት የሚችል ነው፡፡ በተጨማሪም መተግበሪያው በስልካችን ያሉ ጽሁፎችን (PDFs) የተለያዩ ህትመቶችንና የስብሰባ ማጠቃለያዎችን ወደድምጽ በመቀየር እንድንሰማቸው ያስችለናል፡፡ በመሆኑም መተግበሪያው እያንዳንዱን ጽሁፍ የሚያነብልን ረዳትና አደጋ ካለው ሰማያዊ ብርሃን የሚጠብቀን ትልቅ መፍትሔ ሆኖ ቀርቧል፡፡
በጣም ተፈላጊ የሆነው ይህ መተግበሪያ በመተግበሪያ መደብር (App Store) ውስጥ የ4.4 ኮኮብ ደረጃ ተሰጥቶታል፡፡ መተግበሪያው ግልጽ የሆነ አነጋገርን የሚከተል ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የድምጽ ጥራትም እንዳለው ተነግሮለታል፡፡ የሆነው ሆኖ የዋጋውስ ነገር ያላችሁ እንደሆን 34.99 የአሜሪካን ዶላር ከፍለን ለሁልጊዜ መጠቀም እንድንችል የቀረበ ነው፡፡
ምንጭ iflscience

የአኳፖኒክስ (AQUAPONICS) አሰራር
===================
የአኳፖኒክስ የሽቅብ እርሻ አሰራር የሃይድሮፖኒክስ ስርዓትን አንድ ደረጃ በመጨመር እፅዋትንና ዓሳዎችን በአንድ ስርዓተ ምህዳር (Ecosystem) የማሳደግ ሂደት ነው። እንደሚታወቀው አለማችን 75 በመቶ በውሃ በመሸፈኗ አብዛኛው እፅዋት የሚገኘው በውሃ ውስጥ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ እጽዋትና ዓሳ በአንድ ስርዓተ ምህዳር መኖራቸው የታመነ ነው፡፡ በተመሳሳይ አኳፖኒክስም ይህን ስርዓተ ምህዳር በመፍጠር እፅዋትንና ዓሳን በአንድ ላይ እንዲመገቡ ያደርጋል።
አኳፖኒክስ ሁለት ስርዓቶችን አጣምሮ የያዘ ሲሆን እነሱም አኳካልቸር (Aquaculture) እና ሃይድሮፖኒክ ናቸው። ይህም ማለት እፅዋትን ያለ አፈር ለማሳደግ እና ዓሳን በአንድ ላይ ለማርባት ትክክለኛው ስርዓት ነው ማለት ነው። የአኳፖኒክስ አሰራርን አስገራሚ የሚያደርገው የዓሳው ውጋጅ (Waste) በንጥረ ነገር የበለፀገ በመሆኑ ለእጽዋት እንደምግብነት ማገልገሉ ነው። በተመሳሳይ እፅዋቱ ውጋጁን ከውሃው በመለየት መልሶ ወደ ዓሳ ማቆሪያ ይልካል ይህም ባለማቋረጥ በአኳፖኒክ ይከናወናል ፡፡
ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው የዓሳውን ውጋጅ ለተክሉ እንደምግብ እንዲጠቀመው የሚያደርገው ማይክሮብስ (Microbes) የተሰኘ ባክቴሪያ ነው። ይህም ባክቴሪያ አሞኒያ (Amonia) የተባለውን ጎጂ የዓሳ ውጋጅ በመመገብ ናይትሬት (Nitrate) ያመነጫል። ይህም የመነጨው ናይትሬት የናይትሮጅን ይዘት ስላለው ለተክሎች ፈጣን እድገት እጅጉን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ በአንፃሩ ተክሎች ናይትሬቱን ከወሰዱ በኋላ ከሚዘዋወረው ውሃ ውስጥ አሞኒያ እና ናይትሬትን በማጥፋት ውሃው መልሶ ወደ ዓሳ ማቆሪያ በመሄድ ለዓሳዎቹ እንደአዲስ እንዲያገለግል ያደርጉታል። ይህንም ሂደት የአኳፖኒክስ ናይትሮጅን ስርዓተ ኡደት ብለን እንጠራዋለን፡፡
አኳፖኒክስ እንደሌሎች የሽቅብ እርሻ አይነቶች የእድገት ማከናወኛ ንጥረነገሮች የሚጠቀም ሲሆን ይህውም የተክሉ እድገት እንዲያፋጥን ይረዳል፡፡ ይህን የእርሻ ዘዴ ከሌሎች የሚለዩት በአንድ የእርሻ ስርዓት የእፅዋትንም ሆነ የዓሳን ምርት በአንድ ላይ ማስገኘት መቻሉ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከሌሎች ሽቅብ እርሻ ስርዓቶች በመለየት ኬሚካላዊ ንጥረ ነገሮችን አለመጠቀሙ አኳፖኒክስን ልዩ ያደርገዋል፡፡
ምንጭ፡ Sciencedirect እና tech science

የኮቪድ 19 ምርመራ ናሙና መስጫ ፈጠራ
***************************
ለኮቪድ 19 ምርመራ ናሙናን ከአፍንጫ ለመውሰድ የሚያስችል ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ ከዋሉት የተሻለ ነው የተባለ ፈጠራ ይፋ ተደረገ፡፡ ናሙና የሰጠ ሰው እንደሚያስታውሰው ከአፍም ሆነ ከአፍንጫ ናሙና በሚወሰድበት ጊዜ ምቾት የማይሰጡ ሁኔታዎች አሉ፡፡ ወደ ሁለቱም የአካል ክፍሎቻችን ባዕድ ነገር ሲገባ የምናሳየው ግብረ መልስ ናሙናው በትክክል እንዳይወሰድ ያደርገዋል፡፡
ከአፍንጫ ናሙና መውሰጃው ስስና ፀጉር መሰል ቅርጽ ያላቸው ርጥበት ሰብሳቢ ቁሶች ያሉት ነው፡፡ ከሰባት አመት በፊት የተለያዩ በ3ዲ ህትመት የሚሰሩ መገልገያዎችን ለማምረት ጥረቶችን ሲያደርግ የነበረ OPT የተባለ ኩባንያ ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ ለተለያዩ የጤና ተቋማት ለኮቪድ 19 ምርመራ ናሙና መውሰጃ የሚያገለግሉ ምርቶችን እያቀረበ ይገኛል፡፡
እስካሁን ባለው መረጃ 800 ሺህ ናሙና መውሰጃዎችን አምርቶ የቤት ለቤት የምርመራ አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማት በማቅረብ በሆስፒታሎች አካባቢ የሚስተዋልን እጥረት በእጅጉ አግዟል፡፡
ምንጭ techxplore

5,200 ቶን የሚደርስ ብናኝ አቧራ ከህዋ ወደ ምድር በየአመቱ ይወርዳል
***********************
ከህዋ ወደ ምድር ከፍ ያለ አቧራ ብናኝ እንደሚወርድ የታወቀ ቢሆንም ምን ያክል መጠን እንዳለው ማወቅ ግን እጅግ አስቸጋሪ ነበር፡፡ እነዚህ ከህዋ ወደ ምድር የሚወርዱ ብናኞች በጣም አነስተኛ መጠን ያላቸውና በማይክሮስኮፕ የሚለዩ ናቸው፡፡
በአንታርክቲካ ለተከታታይ ሁለት አመታት መረጃን በመሰብሰብ አንድ አለማቀፍ የተመራማሪዎች ቡድን በመጨረሻ 5200 ቶን ብናኝ በየአመቱ እንደሚወርድ መረጃ አውጥቷል፡፡ ይህም ማይክሮሜቶሪትስ ከህዋ ወደ ገጸ መሬት ከወረዱ ቁሶች ውስጥ ትልቁ እንደሆነ አጥኝዎቹ ተናግረዋል፡፡ የምድራችን ከባቢ አየር 17 ሜተሪክ ቶን በሚመዝን ብናኝ አቧራ የተሞላ እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡
በጥናቱ ውስጥ ተገኝቷል የተባለው ብናኝ 1280 ያልቀለጡ ሜቴሮይቶች፣ 808 የቀለጠ የህዋ አለት አካቶ በተሰበሰበ መረጃ መሰረት የተሰላ ነው፡፡ በዚህም ስሌት መሰረት ከ5200 ውስጥ 1600 የሚሆነውን የያዙት ማይክሮሜቴሮይቶች ሲሆኑ ቀሪው 3600 ደግሞ በቀለጡ የህዋ አለቶች የተሸፈነ ነው፡፡
ጥናቱ አክሎም ከህዋ ወደ ምድር ከሚወርደው ብናኝ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆነውን የሚሸፍነው ኮሜቶች ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚለቀቅ እንደሆነ መረጃ ሰጥቷል፡፡ ይሁን እንጂ ከህዋ ወደ ምድር የሚወርደው ብናኝ ከህዋ ሲነሳ 15000 ቶን የሚመዝን ቢሆንም አብዛኛው መጠን ወደ ምድር ከባቢ አየር ሳይገባ በህዋ ይቆያል፡፡
ምንጭ sciencealert

በዲጂታል የክትትልና ሪፖርት አቀራረብ ሥርዓት (D~MRS) ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ
-----------------------------------------
የፕላንና ልማት ኮሚሽን ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስትቲዩት ጋር በመተባበር በዲጂታል የክትትልና ሪፖርት አቀራርብ ሥርዓት(D~MRS) ላይ በተግባር የታገዘ ሥልጠና ከመጋቢት 28 ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ተሰቷል፡፡
ይህ አሰራር አዲስና በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ የሚደረግ ሆኖ የክትትልና ግምገማ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ በማገዝ በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን በግልፅ፣ በተቀናጀና ሃላፊነትና ተጠያቂነት በተሞላበት አግባብ ተፈፃሚ እንዲሆኑ የሚያግዝ ነው፡፡
በስልጠናው ላይ በፕላንና ልማት ኮሚሽን የክትትልና ግምገማ ቢሮ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰለሞን ተስፋስላሴ በክትትልና ግምገማ ፅንሰ ሃሳብ፣ አስፈላጊነቱና ጠቀሜታው እንዲሁም ስለ አስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ የክትትልና ግምገማ ስርዓት ይህን ተከትሎ በፕላንና ልማት ኮሚሽን በኩል የተዘጋጁ መመሪያዎችና አሰራሮች ዙሪያ ማብራሪያ ሠጥተዋል፡፡ በተጨማሪም የዲጂታል ክትትልና ሪፖርት አቀራረብ ሥርዓት (D~MRS) አስፈላጊነትና አላማ ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስትቲዩት የተወከሉት አቶ ዘሪሁን ከበደ ስለ አሰራሩ አላማዎች፣ ዋና ዋና ገፅታዎችና አሰራሩ ምን ያህል አሁን ያለውን አሰራር እንደሚያቃልል ገለፃ ካደረጉ በኋላ ወደ ተግባር ሥልጠና የተገባ ሲሆን፣ ሰልጣኞችም ጊዜ ወስደው በተግባር እንዲለማመዱ፣ እንዲሞክሩና በተግባር እንዲያዩት ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም የልማት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና ዋና ዋና ቁልፍ የአፈፃፀም አመልካቾች እንዴት ሪፖርት እንደሚደረጉ ስልጠና ከተሰጠ በኋላ ሁሉም ተቋማት የሚጠቀሙበትን መለያ ኮድ እንዲያገኙ በማድረግ በራሳቸው መረጃና ሪፖርት የተግባር ሥልጠናውን እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡
በዚህ የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና ላይ የተሳተፉት 7 የሚንስቴር መ/ቤቶች ማለትም ከውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከጤና ሚኒስቴር እና ሰላም ሚኒስቴር የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶቻቸውን በዚሁ ሥርዓት እንዲልኩ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
በዚህ መድረክ የተገኙ ግብዓቶቸን በማካተት በቀጣይ ለሌሎች ተቋማት ስልጠናው የሚሰጥ መሆኑንና ለሙከራ በተመረጡ ተቋማት ላይ ክትትል እንደሚደረግ በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል፡፡
የኢፌድሪ ፕላንና ልማት ኮሚሽን

አስለቃሽ ጋዝ (ጭስ) ምንድን ነው?
********************
አለማችን በተለያዩ ጊዜያት እና በተለያዩ ምክንያቶች የተለያዩ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን አስተናግዳለች፡፡ ከእነዚህም መካከል በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የታዩትን እንደ ዘረኝነት፣ የጸጥታ አካላትን ተገቢ ያልሆነ የሀይል አጠቃቀምና የጆርጅ ፍሎይድን ሞት ምክንያት በመቃዎም በአሜሪካ የተካሄዱትን ማንሳት ይቻላል፡፡ በእነዚህ ተቃውሞዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተሳተፈ ሲሆን ተቃውሞውን ለመቆጣጠር ከጸጥታ አካላት በኩል አስለቃሽ ጋዝ መልቀቅ የተለመደ ነው፡፡ ለመሆኑ አስለቃሽ ጋዝ ምንድን ነው? እንዴትስ አደገኛ ሊሆን ቻለ?
አስለቃሽ ጋዝ ለመጀመሪያ ጥቅም ላይ የዋለው በአንደኛው የአለም ጦርነት (1914-1918) ወቅት ሲሆን ጥቅም ላይ ያዋሉትም የፈረንሳይ ወታደሮች ናቸው፡፡ በወቅቱ የፈረንሳይ ጦር በተለያዩ ቦዮች የሚርመሰመሰውን የተቃራኒ ጦር ለመመለስ ተጠቅመውበታል፡፡ ይሁን እንጂ በ1997 በተደረገ አንድ ስምምነት መሰረት ይህን ጋዝ አለማቀፍ በሆኑ ግጭቶችና ጦርነቶች መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ይህ በአለማቀፍ የኬሚካል የጦር መሳሪያ ስምምነት እነዚህ አይነት መሳሪያዎችን በተለያዩ የሐገር ውስጥ አመጾችና የተለያዩ ተቃውሞዎች መጠቀምን አይከለክልም፡፡
እንደ CDC መረጃ ከሆነ አስለቃሽ ጋዝ ወይም ጭስ በሰዎች አይን፣አፍ፣ ጎሮሮ፣ ሳንባ እና ቆዳ ላይ ጉዳት ለሚያደርስ ኬሚካል የተሰጠ ለጀሮ የተመቸ ስም ነው፡፡ ጋዙን ለማዘጋጀት በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉት CS gas የሚባለው (chlorobenzylidenemalononitrile) እና CN የሚባለው (chloroacetophenone) የጋዝ አይነቶች ናቸው፡፡ ሌላው በአስለቃሽ ጋዝ ውስጥ የማይጠፋው የበርበሬ ብናኝ ነው፡፡
CS የተባለው ጋዝ በስርዓተ ነርቫችን ህመምን እንድናስተውል የሚያስችለንን TRPA1 የተባለ ህዋስ በማጥቃት ምቾት እንዳይሰማን ያደርጋል፡፡ የዚህን ባእድ ነገር ወደ ሰውነታችን መግባት በሽታ ተከላካይ ህዋሶቻችን በተረዱበት ቅጽበት እንደ ላብና እንባና የአፍንጫ ፈሳሽ ያሉ ማጣሪያዎችን በመጠቀም ጋዙን ከሰውነታችን ለማስወጣት ይጥራሉ፡፡ እነዚህ ፈሳሾች ደግሞ በተፈጥሮ ሳልና የአይን ብዥታ በመፍጠር ለሰውነታችን ምቾት አይሰጡም፡፡
በንድፈ ሀሳብ ደረጃ አስለቃሽ ጭስ ለ30 ደቂቃ የሚቆይ እንባ፣ የአፍንጫ ፈሳሽና ንጥሻ ያስከትላል፡፡ ነገር ግን የጭስ መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ ከፍ ላለ አደጋም ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ በ2016 በወጣ አንድ የጤና መረጃ እንደተመለከተው ጭሱ ከቅርብ ርቀት የተለቀቀ ከሆነ እንደ የቆዳ ማቃጠል፣ ሽፍታ፣ መታፈን፣ ማስመለስ እንዲሆም መድማት ሊያከትል ይችላል፡፡ ምንም እንኳን ለሞት የማጋለጥ እድሉ አነስተኛ ቢሆንም በዚህ ምንክንያት የሞቱ ሰዎች እንዳሉ ይታመናል፡፡ በሚያገርም መልኩ በቅርብ ጊዜ በአሜሪካ በጸጥታ ሀይሎች ጥቅም ላይ የዋለ አስለቃሽ ጋዝ ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ መስፋፋት ምክንያት እንደነበረም ተረጋግጧል፡፡
የጤና ሙያተኞች አንድ ሰው አስለቃሽ ጭስ የተለቀቀበት አካባቢ ላይ ማድረግ ይገባዋል ያሉትን ጥንቃቄ ተናግረዋል፡፡ የመጀመሪያው ነገር ጋዙ ከተለቀቀበት አካባቢ በፍጥነት መልቀቅ ሲሆን በተቻለ ፍጥነት ፊታችንንና ለጋዙ ተጋላጭ የሆነ የሰውነት ክፍላችን በሳሙናና በንጹህ ውሃ መታጠብ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ጭሱ በነበረበት ወቅት የለበስነውን ልብስም በቶሎ ማውለቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ሰውነታችንን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ያክል ወይም የጋዙ ሽታ እስከሚጠፋ ድረስ መታጠብ ይኖርብናል፡፡

አነስተኛ እርሻዎችና ትልቁ ጥቅማቸው
=====================
በአነስተኛ መሬት ላይ የሚሰሩ እርሻዎች ከትልልቆቹ አንፃር ይበልጥ ምርታማ፣ አትራፊና ለአካባቢው ስነ-ምህዳርም ይበልጥ ተስማሚ ናቸው ተባለ፡፡ በዓለማችን አብዛኛው የምግብ ምርት ከሰፋፊ እርሻዎች የሚሰበሰበው ቢሆንም አነስተኛ እርሻዎችም ብዙ ያልተባለለት ትርፋማነትን እንደሚያጎናፅፉ ተነግሯል፡፡
በዓለማችን ካሉ አርሶ አደሮች ውስጥ 84 በመቶ የሚሆኑት ከሁለት ሄክታር ባነሰ መሬት ላይ እያረሱ ይገኛሉ፡፡ ታድያ ብዙ የፖሊሲ አውጪዎች እና የሳይንሱ ተመራማሪዎች እነዚህ በአነስተኛ መሬት ላይ የሚከወኑ እርሻዎች የዓለማችንን አብዛኛውን ሰብል ከሚሰጡት ሰፋፊ እርሻዎች በላቀ ውጤታማ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ ቪንሰንት ሪቺያርዲ እና በካናዳው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ የሚገኙ የሙያ አጋሮቹ ከ50 ዓመታት በተሻገረ ጊዜ ውስጥ በ51 ሀገራት ላይ የተሰሩ 118 ጥናቶችን በመተንተን የአንድ እርሻ መሬት ስፋት ከምርት ዕድገት ባሻገር ስለሚያመጣው ልዩነት ምልከታን አድርገዋል፡፡
በዚህም ቡድኑ ምናልባትም በቤተሰብ የሰው ጉልበት ምክንያትም ሊሆን ይችላል ባለው መልኩ አነስተኛ ማሳዎች ከትላልቆቹ የተሻለ ምርትን እንደሚሰጡ መመልከት ችሏል፡፡ በተጨማሪም እነዚ አነስተኛ እርሻዎች ከትላልቆቹ እርሻዎች በበለጠ የአዝእርት ብዝሀነት እና ከሰብል ውጭ ያለ ስነ-ምህዳርንም ይዘው ተገኝተዋል፡፡ ለዚህም ከትላልቆቹ የእርሻ ኢንዱስትሪዎች ጋር ሲነፃፀሩ አነስተኛ ፀረ-ተባይን መጠቀማቸው፣ በተለያየ አይነት የመሬት አቀማመጦች ላይ መገኘታቸው እንዲሁም ሰፋ ያለ ከማይታረሰው መሬት ጋር የሚለይ ነፃ መሬትን መያዛቸው በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡
አጥኚዎቹ ባቀረቡት ምክረ ሀሳብ መሰረት አነስተኛ እርሻዎችን መደገፉ በአንድ እጅ የምግብ ምርትን በከፍተኛ ደረጃ ሲያሳድግ በሌላ እጅ ደግሞ እጅግ ጠቃሚ ሰብአዊና ስነ-ምህዳራዊ ጥቅሞችን ያመጣል፡፡
ምንጭ፤ Nature