ገዳይ ከሆኑ የካንሰር ዓይነቶች አንዱ የሆነው የጡት ካንሰር መንስኤ ታወቀ
******************************
የአውስትራሊያ ተመራማሪዎች በዓለማችን ገዳይ ከሆኑ የካንሰር አይነቶች አንዱ ለሆነው የጡት ካንሰር ህመም ምክንያት የሆነውን ጅን ማግኘታቸው ተሰማ፡፡ ይህ የገዳዩ የጡት ካንሰር ህመም ምክንያት የሆነው ጅን ዝቅተኛ የሆነ በህይወት የመቆየት አቅም (survival rates) ያለው እንደሆነ ታውቋል፡፡ በመሆኑም በበሽታው የሚሰቃዩ ሰዎችን ለማከም ያለው ስኬት አልባ ድካም እንደሚሻሻል ተስፋ ማስገኘቱን የሀሪ ፓርኪንስ ሜዲካል የምርምር ተቋሙ ፒላር በላንስፎርት ተናግረዋል፡፡
የጡት ካንሰር በሚል ጥቅል ስም ውስጥ የተለያዩ የካንሰር አይነቶች ያሉ ሲሆን እንደ ኢስትሮጅንና ፕሮጀስትሮን ላሉ ሆርሞኖች ሴንሲቲቭ የካንሰር ዓይነቶች የተለያዩ ህክምናዎች ያሏቸው ሲሆን ሆርሞን ሴንሲቲቭ ካልሆኑ የጡት ካንሰር አይነቶች ይልቅ የተሻለ ምላሽ ይታይባቸዋል፡፡ በ2012 አንድ የተመራማሪዎች ቡድን የጡት ካንሰር አይነቶችን ኢንተግሬቲቭ ክላስተሪንግ በሚል አከፋፈል ከ10 መድቧቸው ነበር፡፡ እነዚህም እያንዳንዳቸው የየራሳቸው የጀኔቲክ ለውጥ እና ክሊኒካዊ ውጤት ያላቸው ናቸው፡፡
ከአስሩ የጡት ካንሰር ንዑስ ምድቦች ውስጥ IntClust2 የሚባለው የጡት ካንሰር ዓይነት ይህ ነው የሚባል ህክምና የሌለው ነው፡፡ በተሰራው ምርምርም AAMDC የተሰኘ በጡት ካንሰር ውስጥ የሚገኝ የጅን አይነት ለጡት ካንሰር መከሰት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ታውቋል፡፡ ይህም የታወቀው በጡት ካንሰር ውስጥ የሚገኝን ይህንን ጅን በመያዝ የሰውነት ህዋሳት እንደገና ራሳቸውን የማደስ ባህሪ ስለተስተዋለባቸው ነው፡፡
ምንጭ Science alert

በቨርጂን ጋላክቲክ ይፋ የተደረገው አዲስ ትውልድ አውሮፕላን
*******************************
በስፔስ ክራፍት ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተለያዩ አስደናቂ ግኝቶችና ፈጠራዎች በየጊዜው ይፋ እየተደረጉ እና ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ፡፡ በዚህኛው ትውልድ አውሮፕላን አዲስ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የአውሮፕላኑ ሙሉ አካል ብራማ በሆነ የብረት ቁስ የተሸፈነ መሆኑ ነው፡፡ ይህም ለአውሮፕላኑ የቆየ የሚመስል ፋሽን እንዲላበስ አድርጎታል፡፡ እንደ ኩባንያው ፕሬዘዳንት ማይክ ሞሰስ መረጃ ከሆነ የዚህ ፈጠራ ሀሳብ የመጣው በኩባንያው መስራች ሪቻርድ ብራንሰን አማካኝነት ነው፡፡
ይህ V.S.S. Imagine የተሰኘው ስፔስ ክራፍት ለማምረት እጅግ ቀላል በመሆኑ ኩባንያው የዚህ ቀጣይ ትውልድ የሆነውንና V.S.S. Unity የተባለው በምርት ሂደት ላይ መሆኑን የኩባንያው ፕሬዘዳንት ተናግረዋል፡፡ በፍጥነት መመረት ከመቻሉ በተጨማሪም ይህ አዲሱ ዲዛይን የጥገና ወጭን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ የተነገረ ሲሆን በብዛት ተመርቶ ለአገልግሎት ለማሰማራትም ታቅዷል፡፡
በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ የሙከራ በረራ እንደሚካሄድና በቀጣዮቹ የበጋ ወራት በመደበኛ በረራዎችን ያደርጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ካምፓኒው V.S.S. Unity የተሰኘውን የኤሌክትሮ መግነጢስ ጣልቃገብነት ያጋጠመውን ሞዴል በመጪው ግንቦት ወር ለመሞከር ያሰበ በመሆኑ ለኩባንያው መጭው ጊዜ የተጨናነቁ ሙከራዎች የሚካሄዱበት ይሆናል፡፡
ምንጭ Forbs

አረንጓዴ ሀይድሮጅንን ለማበልጸግ የሚደረግ አለማቀፍ ፉክክር
*************************
አለማችን የገጠማትን ከአየር ብክለት ጋር የተያያዘ ችግር ለመቅረፍ እንዲያስችላት ከካርቦን ልቀት ነጻ በሆኑ ነገሮች ላይ ማተኮር ከጀመረች ቆይታለች፡፡ የኢንዱስትሪ አብዮት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ ድህረ ስልጣኔ (post modernism) እስከሚባለው እስካሁኑ ዘመን ድረስ ከተለያዩ ምንጮች የሚለቀቀው ካርቦን በአለማችን ላይ ከፍተኛ ችግሮችን አስከትሏል አሁንም በማስከተል ላይ ይገኛል፡፡ ሀገራት ከዚህ ችግር ለመላቀቅ የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ የሚያስችሉ የተለያዩ የፖሊሲ አማራጮችን በመቅረጽ ተግባራትን እየፈጸሙ ይገኛሉ፡፡
የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ ቀጥተኛ አስተዋጽኦ ካላቸው እርምጃዎች መካከል ከነዳጅ ሀይል ነጻ የሆኑ የቴክኖሎጂ አማራጮችን መጠቀም ዋነኛው ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሀገራችን እየታወቀችበት ያለው የደን ልማት ሌላው አለማችን ከካርቦን ነጻ ለመሆን የምታደርገውን አስተዋጽኦ በእጅጉ የሚያግዝ ተግባር ነው፡፡ በአንዳንድ ሀገራት የኤልክትሪክ መኪኖችን በብዛት መጠቀም ትልቅ መፍትሔ ተደርጎ እየተሰራበት ሲሆን ሞተር አልባ እና በፀሐይ ሐይል የሚሰሩ መንቀሳቀሻዎችን መጠቀም ደግሞ ወደር አልባ መፍትሔ እየሆነ መጥቷል፡፡
ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዘውን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ አማራጮችን መጠቀም በጣም ጠቃሚ መሆኑን የተረዱ አንዳንድ የአለማችን ሀገራት አሁን ላይ ከኤሌክትሪክ፣ ከፀሐይ ሐይልና ከነፋስ ከካርቦን ነጻ የሐይል አማራጮች አልፈው ግሪን ሐይድሮጅን ወደተባለ ሌላ የሐይል አማራጭ ፊታቸውን አዙረዋል፡፡ ይህም ምንም አይነት ነዳጅን ሳይጠቀሙ ሐይል የሚገኝበት አማራጭ እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡
ከካርቦን ነጻ የሆነ ተቀጣጣይ ሐይድሮጅን በካይ የሆኑ ኢንዱስትሪዎች የብክለት መጠናቸውን በእጅጉ እንዲቀንሱ ያስችላቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በባትሪ የሚሰሩ የኤሌክትሪክ መኪኖች የሚያጋጥማቸውን ከሰዓት ጋር የተያያዘ ችግር መቅረፍ ያስችላ ተብሎለታል ፡፡ ለዚህም የሐይድሮጅን የሐይል አማራጭን ለመሙላት የሚወስደው ጊዜ ነዳጅ ከመሙላት ጋር ሲነጻጸር ተቀራራቢ ጊዜ የሚወስድ መሆኑ በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡
ይሁን እንጂ በዘርፉ የተሰማሩ እና ለመሰማራት ያቀዱ ሀገራት ከምህንድስና ጋር ከተያያዘው ችግር በተጨማሪ የሐይድሮጅን አቅርቦት፣ የመሰረተ ልማትና የማጓጓዣ ችግሮች ትልቅ እንቅፋት ሳይሆኑባቸው አልቀረም፡፡ የአለማችን ሀብታም ሀገራት ችግሩን ለመቅረፍ የተለያዩ አማራጮችን እየተከተሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ከፀሐይ እና ከነፋስ የሚገኝን የኤሌክትሪክ ሐይል መጠቀም አንደኛው ሲሆን ሌላኛው አማራጭ ደግሞ ከኒውክሌር የሚገኝን የኤሌክትሪክ ሐይል መጠቀም ነው፡፡ አንዳንድ ሀገራት ደግሞ ይህንኑ ምርት በተፈጥሮ ጋዝ ተረፈ ምርት መልክ ለማምረት እንዳቀዱ ተነግሯል፡፡
ባሳለፍነው የፈረንጆች አመት 76 ጌጋ ግሪን ሐይድሮጅንን ለማምረት ከታቀዱ ፕሮጀክቶች መካከል 40 ያክሉ ይፋ ተደርገዋል፡፡ ዘርፉን በእጅ ለማድረግ የተቀጣጠለውን ጦርነት ልብ ያሉ መንግስታት ግሪን ሐይድሮጅንን ለሐገር ውስጥና ለኤክስፖርት በሚያመች መልኩና በቢሊዮን ዶላርች የሚገመቱ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ ለምሳሌ አሜሪካ የሀይድሮጅን ፍኖተ ካርታ ቀርጻ እየሰራች ሲሆን ጀርመን ለዘርፉ 10.6 ቢሊዮን ዶላር በጅታለች፡፡ እንዲሁም ፈረንሳይና ፖርቱጋል እያንዳንዳቸው 7 ቢሊዮን ዩሮ፣ እንግሊዝ 16.6 ቢሊዮን ዶላር፣ ጃፓን 3 ቢሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም ቻይና 16 ቢሊዮን ዶላር በ2020 ብቻ መድበው እየተፎካከሩ ይገኛሉ፡፡
ምንጭ Tech Xplore

በአሜሪካ ለበረራ የተዘጋጀው የጀርመን የአየር ታክሲ
***********************
ለሊየም የተሰኘው የጀርመን በአየር ላይ ታክሲ የተሰማራ የቴክኖሎጂ ድርጅት በአሜሪካ የአየር ላይ ታክሲ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችለውን ስምምነት ኩዌለወ ከተባለ የቼክ አቅራቢ ድርጅት ጋር በ3.3 ቢሊዮን ዶላር ተፈራረመ፡፡ ይህ ማሽንን መሰረት ያደረገው ሊሊየም የተባለው የቴክኖሎጂ ድርጅት ከሌሎች በአቪየሽን ዘርፍ ላይ ከተሰማሩ ተቋማት ጋር በመሆን በባትሪ የሚሰሩ እና ያለማኮብኮብ መብረር የሚችሉ የአየር ላይ ታክሲዎችን ለማቅረብ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህም ከትራፊክ መጨናነቅ ጋር በተያያዘ እየተገታ ያለውን የከተሞች እድገት ችግር እንደሚቀርፍ ታምኖበታል፡፡
እንደሊሊየም መረጃ ከሆነ ከኩዌል ጋር የተደረገው ስምምነት በአሜሪካ ሰማይ ስር ለመንገደኞች ምቹ የሆኑ የአየር ላይ ታክሲዎችን በ2024 ለማቅረብ ያስችለዋል፡፡ ከዚህ በፊት የቴክኖሎጂ ድጅቱ ባለ አምስት መቀመጫ የሆነ ወጥ ክንፎች ያሉት ፕሮቶታይፕ አቅርቦ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ አሁን ላይ ረዘም ላሉ በረራዎች ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጥቅም ያለው ባለ ሰባት መቀመጫ አዲስ ሞዴልን አስተዋውቋል፡፡
ባለ ሰባት መቀመጫው ጄት ታክሲ በተሳካ ሁኔታ ወደ ምርት ከገቡት ውስጥ የመጀመሪያው ሲሆን በሰዓት 280 ኪሎሜትሮችን መብረር የሚችል ነው፡፡ ባሳለፍነው አመት ይህ ባለ ሰባት መቀመጫ በራሪ ታክሲ ከአውሮፓ የበረራ ደህንነት ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤት CRI-A01 የተባለ የደህንነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማግኘት ችሏል፡፡ ድርጅቱ አሁን ላይ ተመሳሳይ የሆነ ፈቃድ ከአሜሪካው የፌዴራል የበረራ አስተዳደር ተቋም እየጠበቀ ይገኛል፡፡
ሌላኛው የጀርመን በዘርፉ የተሰማራው ኩባንያ ቮሎኮፕተር ቮሎሲቲና ቮሎድሮን የተሰኙ ለሰውና ለእቃ ማጓጓዣነት የሚውሉ በራሪ ታክሲዎችን እንዳቀረበ መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ Autonomous Europe

ዋና ዋናዎቹ የሳይበር ጥቃት መፈፀመያ መንገዶች
=======================
1. ቫይረስ (VIRUS) ቫይረሶች የኮምፒውተር ፕሮግራም ሲሆኑ ጥቃት ለማድረስ ራሳቸውን ከሶፍትዌር ወይም ከፋይል ጋር በማጣበቅ ወደ ተጠቃሚው ኮምፒውተር ይገባሉ። ቫይረሶች የተጣበቁበት ሶፍትዌር አልያም አፕሊኬሽን በሰው አማካኝነት ካልተነሳ ራሳቸውን ማባዛት አልያም የታለመላቸውን ስራ መከወን አይችሉም። ቫይረሶች ሶፍትዌሮችን፣ ሀርድዌሮችን ወይም ፋይሎችን ሊያጠቁ ይችላሉ። ቫይረሶች በመረጃ ልውውጥ ጊዜ በፍላሽ፣ በሲዲ፣ በሀርድ ዲስክ ወይም በኢሜል አማካኝነት ከአንድ ኮምፒውተር ወደ ሌላ ሊሰራጩ ይችላሉ።
2. ስፓይዌር (SPYWARE) ስፓይዌር የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ኮምፒውተርን ከባለቤቱ እውቅና ውጪ መረጃዎችን እንዲልክ የሚያደርጉ ናቸው:: እነዚህ ሶፍትዌሮች የተጠቂውን ኮምፒውተር ካሜራና ስፒከር በመጠቀም ጭምር የባለቤቱን እንቅስቃሴ መቆጣጠር የሚችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ይህ ሶፍትዌር በስፋት ለስለላ ተግባር የሚውል ሲሆን መንግስታት ጭምር ህዝባቸውን ለመሰለል የሚጠቀሙበት ቴክኒክ ነው።
3. መረጃ ማስገር (FISHING) ታዋቂ የሆኑ ድረ-ገፆችን አስመስሎ በመስራት ተጠቃሚዎችን የማታለል ዘዴ ፊሺንግ ይባላል። ለምሳሌ የአንድ ባንክ ድረ-ገፅን አስመስሎ በመስራት የባንኩን ተጠቃሚዎች መረጃቸውን እንዲያስገቡ በመጋበዝ በቀላሉ የተጠቃሚዎችን የክሬዲት ካርድ አካውንትና የይለፍ ቃል የመስረቅ ዘዴ “ፊሺንግ” ተብሎ ይጠራል።
4. ፓኬት ስኒፊንግ (PACKET SNIFFING): መረጃዎችን ከአንድ ኮምፒውተር ወደ ሌላ ኮምፒውተር ወይም ከአንድ ኔትወርክ ወደ ሌላ ኔትወርክ ገመድ አልባ በሆነ መንገድ(WIRELESS) ወይም የኔትወርክ ገመድ ተጠቅመው በሚተላለፉበት ወቅት መረጃዎችን የምስጠራ ዘዴ (ENCODING) በመጠቀም ወደ ማይታወቅ መልኩ ይቀይራሉ፤ ከዚያም ወደ ፓኬት(ጥቃቅን መረጃዎች) ተቆራርጠው ይላካሉ፤ እነዚህን ፓኬቶች በሚተላለፉበት ወቅት የመጥለፍና ምስጠራውን የመፍታት (DECODING) ሂደት “ኔትወርክ/ፓኬት ስኒፊንግ” በመባል ይታወቃል።
ምንጭ፡ Tech Radar

የቀን ብርሃንን የሚሰበስበው አዲስ ቴክኖሎጂ
************************
ተመራማሪዎች የቀን ብርሃንን መሰብሰብ የሚችል ስማርት ቴክኖሎጂ መስራታቸው ተሰማ፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ የቀን ብርሃንን በመሰብሰብ ከመሬት በታች ለሚሰሩ ስራዎች ብርሃንን ማስተላለፍ የሚችል እንደሆነና በባህላዊ መንገድ ጥቅም ላይ የሚውልን የብርሃን ምንጭ ማስቀረት እንደሚችል ቴክኖሎጂውን ያበለጸጉት የሲንጋፖሩ ናንያንግ ቴክኖሎጂካል ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ተናግረዋል፡፡
በሲንጋፖር ባለስልጣናት ለተለያዩ መሰረተ ልማቶች የሚሆኑ የተለያዩ ቁፋሮዎች እየተደረ በመሆኑ ለነዚህ ስራዎች 24 ሰዓት ለመሬት ውስጥ ስራ ምቹ የሆነ ብርሃን ያስፈልጋል፡፡ ይህንን ፍላጎት ለማሟላት ቴክኖሎጂካል ዩኒቨርሲቲው የፀሐይ ብርሃንን ወደ አንድ ነጥብ መሰብሰብ የሚያስችል ምስሪታዊ ጠርሙስን (magnifying glass) ተጠቅመዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተመራማሪዎቹ ብርሃን ተሸካሚ ገመዶችንና በኮምፒውተር ቺፕ የታገዙ ሞተሮችንም ተጠቅመዋል፡፡
ኳስ መሰል ቅርጽያለው ይህ ጠርሙስ ከመሬት በላይ በመሆን ብርሃን ከሰበሰበ በኋላ በሁለት ትይዩ መስመሮች አማካኝነት ጠንካራ ብርሃኖችን ይፈነጥቃል፡፡ እነዚህን በሁለት መስመር የተፈነጠቁ የብርሃን ጨረሮች በብርሃን ተሸካሚው ገመድ (fiber cable) አማካኝነት ወደሚፈለገው የመሬት ውስጥ ክፍል ብርሃንን ማስተላለፍ ይቻላል፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት የብርሃን ማስተላለፊያ ገመድ በተገጠመለት በኮምፒውተር ቺፕ በታገዙ ሞተሮች አማካኝነት የፀሐይ ብርሃን አቅጣጫን በመከተል አቀማመጡን ያስተካክላል፡፡
ፈጠራው አሁን ላይ ባሉ የፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፎች የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡ አሁን ላይ ባለው የፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጠፍ ላይ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል ተፈጥሯዊ እርጥበትና ከፍተኛ ጥገና ይጠቀሳሉ፡፡

አስትራዜንካ እና የደም መርጋት
*******************
እንግሊዝ አስትራዜንካ በተሰኘው የኮቪድ 19 ክትባት ምክንያት ተከስተዋል ያለቻቸውን 25 የደም መርጋት ክስተቶችን ይፋ አደረገች፡፡ ባለፈው የፈረንጆች መጋቢት 24 ከደም መርጋት ጋር በተያያዘ የተከሰተው ችግር 30 የደረሰ ሲሆን ሁሉም ከአስትራዜንካ ጋር የተያያዙ ናቸው ተብሏል፡፡ ሌላኛው የክትባት አይነት ፋይዘር በዚህ ጉዳይ ስሙ እየተነሳ አይደለም፡፡
በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ይህ ክትባት በአውሮፓ እያሽቆለቆለ የመጣ ተቀባይነት ቢኖረውም ሀገራት ከወረርሽኙ ነጻ ለመውጣት ካላቸው ጉጉት በሚመስል ሁኔታ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ክትባቶችን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ የእንግሊዙ የክትባት ኤጀንሲ እንዳሳወቀው 30ው ከደም መርጋት ጋር የተያያዘው ችግር የተስተዋለው ከ18.1 ሚሊዮን ክትባቶች ውስጥ ነው፡፡
ከመጋቢት 24 ቀደም ብሎ ባለው ቀን አምስት የደም መርጋት ችግሮች የተስተዋሉ ሲሆን ይህም ከተሰጠው 11 ሚሊዮን ክትባት ውስጥ ነው፡፡ ይህ የሚያመላክተው ክትባቱ ወረርሽኙን ለማስወገድ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ በጣም ከፍኛ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም ሰዎች ያለ ስጋት ክትባቱን መውሰድ ይገባቸዋል ተብሏል፡፡
በተያያዘ ሮይተርስ ባወጣው መረጃ በኮቪድ 19 በጠቅላላው 29 ሺህ 300 ሰዎች ተይዘውባት ከነዚይም መካከል 909 ሰዎች የሞቱባት እና በቫይረሱ ቁጥጥር ከፍተኛ ስኬት ያስመዘገበችው አውስትራሊያ በስፋ የኦክስፎርዱን አስትራዜንካ እንደተጠቀመች ይናገራል፡፡ ይሁንና ባለፈው አርብ የተስተዋለውን አንድ የደም መርጋት ሁኔታ ከክትባቱ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዳጠናች አሳውቋል፤ ዘገባው፡፡
ይህ በ44 ዓመት ጎልማሳው ላይ የተስተዋለው የደም መርጋት የደም ህዋሳት እጥረትም የተስተዋለበት ነበር፡፡ ችሩም ከክትባቱ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ የሀገሪቱ ተመራማሪዎች ይህ እንደ ትልቅ ችግር ሊወሰድ አይገባውም የሚል አቋም አላቸው፡፡ አውስትራሊያ በየካቲት ወር ብቻ 25 ሚሊዮን የአስትራዜንካ ክትባቶችን ማሰራጨቷ ይነገራል፡፡
ምንጭ Bloomberg እና Reuters

ድምጽን ብቻ በመጠቀም የኮቪድ 19 ተጠቂዎችን የሚለየው መተግበሪያ
*******************************
የሰዎችን ድምጽ ብቻ በመጠቀም የኮቪድ ተጠቂዎችን ለመለየት የሚያስችል በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ መተግበሪያ መሰራቱ ተሰማ፡፡ ይህ መተግበሪያም 80 በመቶ የደረሰ ትክክለኝነት እንዳለውም ተሰምቷል፡፡ እንደሚታወቀው ኮቪድ 19 የሚያሳየው ምልክት ከሰዎች ሰዎች የተለያየ በመሆኑ ተጠቂዎችን መለየት እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ አንድ ሰው የጉሮሮ መከርከር፣ ሙቀት፣ ሳል ወይም የማሽተትና የመቅመስ ችግር ሲስተዋልበት የኮቪድ ምርመራ ማድረግ እንዳለበት ይመከራል፡፡
ይህንን ችግር የተመለከተው ቮካሊስ የተሰኘ ኩባንያ የኮቪድ ተጠቂዎችን ለመለየት የሚያስችል ድምጽንና የሞባይል መተግበሪያን የሚጠቀም ቴክኖሎጂን አበልጽጓል፡፡ ይህን ቴክኖሎጂ የተለየ የሚያደርገው ነገር በአንድ በቫይረስ የተጠቃም አካባቢ የሚገኙ ሰዎችን ለመለየት ሁሉንም ሰዎች ወደ ጤና ተቋም ማምጣት አስፈላጊ ቢሆንም ቴክኖሎጂው ልየታውን ለማድረግ ሰዎች ባሉበት ሆነው በድምጻቸው ብቻ ቫይረሱ በውስጣቸው መኖሩንና አለመኖሩን መለየት የሚያስችል መሆኑ ነው፡፡ ቴክኖሎጂው ይህን ለማድረግ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ይጠቀማል፡፡
ቮቻሊስ የተሰኘው ድርጅት ከሰዎች ድምጽ ጋር የተያያዙ ሰፊ መረጃዎችን የሰበሰበ ሲሆን የቴክኖሎጂ ተቋሙ የህመም ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች የሚኖራቸውን ድምጽ ሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የተሰበሰበውን የድምጽ መረጃ በመጠቀም የሚለይ ቴክኖሎጂን አበልጽጓል፡፡ ካምፓኒው ያበለጸገው ስልተ ቀመር 512 የሚደርሱ የተለያዩ የድምጽ ባህሪያትን የለየ ሲሆን ተገማች ህመሞችን መተንበይ የሚያስችለውን ምስል spectrogram ይሰራል፡፡
በሙከራ ወቅትም ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ከ50 እስከ 70 የሚደርሱ ቁጥሮችን እንዲቆጥሩ በማድረግ ቴክኖሎጂውን የማለማመድ ስራ ተሰርቷል፡፡ በዚህም 275 ሺህ የሚደርሱ የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ይህ ቴከኖሎጂ በአሜሪካ፣ቺሊ፣ኢንዶኖዢያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሉክሰምበርግ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ቮካሊስ የተሰኘው መሰረቱን እስራኤል ያደረገው ተቋም በ2019 የተመሰረተ ሲሆን በያዝነው አመት በህንድ ሙባይ 2000 ታካሚዎችን በመመርመር ነው ስራውን የጀመረው፡፡
ምንጭ The next web

በዓለማችን 50 በሚሆኑ ሰዎች ላይ ብቻ የሚገኘው አደገኛ የደም አይነት
===========================
ስለደም አይነቶች ስናወራ ወደሃሳባችን የሚመጡት A, B O የተባሉት ዋነኞቹ የደም አይነቶቸ ወይም ስርዓቶች ናቸው፡፡ እንደአውሮፓውያኑ በ1901 ለመጀመሪያ ጊዜ የተለዩት እነዚህ የሰዎች የደም ስርዓቶች በውስጣቸው 8 የደም አይነቶች እንደሚገኙባቸውም ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ የደም አይነቶች ውስጥ A, B, AB እና O ዋናዎቹ የሰዎች የደም አይነቶች ሲሆኑ ከዚህ በተጨማሪ አልፎ አልፎ በሰዎች ላይ የሚታዩ እጅግ ብዛት ያላቸው የደም አይነቶች እንዳሉም ይነገራል፡፡
እንደተመራማሪዎች ከሆነ በሰዎች የደም ስርዓት ውስጥ 342 አንቲጅንስ (antigens) የያዙ ቀይ የደም ሴሎች አሉ፡፡ በእነዚህ ሴሎች ውስት ያሉት አንቲጅኖች በሽታ የመከላከል አቅማችንን ለመፍጠር የሚስቸሉንን antibodies የሚያመርቱ ሲሆኑ የማናችንም የደም አይነት ዝርያም በእነዚህ የአንቲጅኖች መኖር እና አለመኖር ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ከ 342 የደም ቡድን አንቲጂኖች (blood group antigens) ውስጥ 160 የሚሆኑት በቀይ የደም ሴሎች ውስጥ የመሰራጨት እድል አላቸው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ማናችንም ከ160 ያላነሱ አንቲጂኖች በደማችን ውስጥ ከተገኘ ከላይ የጠቀስናቸው መደበኛ የደም አይነቶች ሊኖሩን ይችላል ማለት ነው፡፡
ይሁንና ከላይ ካነሳነው በተለየ ሁኔታ 99 በመቶ የሆኑት ሰዎች ያላቸውን ወይም positive የሆኑበትን አንቲጅን ያልያዙ ሰዎች አልፎ አልፎ የሚታይ የደም አይነት (rare blood type) አላቸው እንዲባል ያስችላል፡፡ ከዚህ በባሰ ሁኔታ ደግሞ 99.99 በመቶ የሆኑት ሰዎች ያላቸውን ወይም positive የሆኑበትን አንቲጅን በተፈጥሮ ያላገኙ ሰዎች የመከሰት እድሉ በጣም አናሳ የሆነ (extremely rare) የደም አይነት አላቸው እንዲባል ያስችላል፡፡ ታዲያ በአለማችን ከ50 ያነሱ ሰዎች ላይ ብቻ ይገኛል የሚባለው Rhnull የተሰኘው የደም አይነት መሰረታዊውን የ Rh አንቲጅን ወይም ፕሮቲን በቀይ የደም ሴላቸው ያልያዙ በመሆናቸው የመከሰት እድሉ በጣም አናሳ የሆነ (extremely rare) የደም አይነት ያላቸው ሰዎች እንዲባሉ ሆኗል፡፡
እንደአውሮፓውኑ በ1961 ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው ይህ የደም አይነት በደም ግሩፕ ስርዓት ውስጥ እጅግ ውስብስበ ከሚባሉት ቀዳሚው ሲሆን፤ ከዚህ ጊዜ አንስቶም በአለም ላይ ከ40 እስከ 50 በሚሆኑ ሰዎች ላይ ብቻ እንደሚገኝ ይነገራል፡፡ የመከሰት እድሉ በጣም አናሳ የሆነው ይህ የደም ዝርያ በአለማችን በጥቂት ሰዎች ላይ ብቻ የሚታይ በመሆኑ ደሙን ለማግኘት እጅግ ከባድ ደርገዋል፡፡ በዚህ የተነሳም ይህ የደም አይነት ያለቸው ሰዎች ለተለያዩ አደጋ ቢጋለጡ አንኳን የደም ባንክ እንደሌላቸው በማንሳት አደገኛ ስጋት ያለባቸው ሰዎች መሆናቸውን ብዙዎች ሲገልፁ ይሰማል፡፡
ደሙን ለማግኘት እጅግ ከባድ ከመሆኑ አንፃር አንዳንዶች ወርቃመው ደም ብለው የሚጠሩት ይህ የደም ዝርያ በአለማችን 8 የሚሆኑ ሰዎች ብቻ መለገስ እንደሚችሉ ይነገራል፡፡ ይሁንና እንደየሃገራቱ ህግጋት እና በሰዎቹ ላይ ሊፈጠሩ ከሚችሉ ያልታሰቡ ችግሮች አንጻር ደሙን የማግኘት እድሉ እጅግ የጠበበ ነው፡፡ ይህ የደም አይነት ያላቸው ሰዎች አንደአብዛኞቻቸን የነፃነት ህይወት ላይኖሩ ይችላሉ፣ አንቅስቃሴያቸውም ጥንቃቄ የተሞላበት ሊሆን ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም በተለያየ ችግር የደም እጥረት ቢያጋጥማቸው እንኳን ደሙን የማግኘት እድላቸው እጅግ የጠበበ ነው፡፡
ምንጭ፡ Medicinenet እና bigthink

ከገበያ እየወጣ ያለው LG ስልክ
******************
ከአመታት የቁልቁለት ጉዞ በኋላ እውቁ የደቡብ ኮሪያ ኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩባንያ LG ከስማርት ስልክ ገበያ ሊወጣ እንደሆነ ተሰማ፡፡ ይህም ኩባንያውን በዘርፉ ከተሰማሩና ሰፊ እውቅና ካላቸው የሞባይል ስልክ አምራች ኩባንያዎች ውስጥ የመጀመሪያው እንደሚያደርገው ተነግሯል፡፡ ምንም እንኳን ዘርፉ እጅግ አትራፊ እና ስልኩ በአሜሪካ ገበያ ውስጥ ከአፕልና ከሳምሰንግ ቀጥሎ ተመራጭ ስማር ስልክ ቢሆንም ኩባንያው በገጠመው የትኩረት ማጣት ችግር ምክንያት ራሱን ከገበያው ለማግለል እንዳሰበ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ባወጣው መረጃ አሳውቋል፡፡
የካምፓኒው ከዘርፉ መውጣት በድርጅቱ ቦርድ የጸደቀ ሲሆን የሚመጣው ሐምሌ መጨረሻ ላይ ሙሉ በሙሉ ከዘርፉ ገበያ እንደሚወጣም ተሰምቷል፡፡ አንድ ካውንተር ፖይንት የተባለ የምርምር ተቋም እንዳወጣው መረጃ ከሆነ ባለፈው የፈረንጆች አመት በአሜሪካ ብቻ ከተሸጡ ስማርት ስልኮች ውስጥ 11 በመቶውን በመሸፈን LG በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ኩባንያ ነበር፡፡ ተቋሙ ባወጣው መረጃ መሰረት ከስማርት ስልክ ገበያው መውጣት እንደ የኤሌክትሪክ መኪኖችና መለዋወጫዎች፣ የተለያዩ የኤሌክትኒክስ እቃዎች፣ ስማርት ቤቶችና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ትኩረቱን እንዲያደርግ ያስችለዋል፡፡
የኩባንያውን ከገበያው የመውጣት መረጃ ተከትሎ ድርጅቱ ያለው የሼር ዋጋ በ2.52 ቀንሷል፡፡ በስማርት ስልክ ዘርፍ ተቋሙ ላለፉት ስድስት ዓመታት ሲንከባለል የመጣ የ4.5 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በዓለም ገበያ ውስጥ ካሉ ስማርት ስልኮች ውስጥ LG የሚሸፍነው 2 በመቶውን ብቻ ነው፡፡