የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ሰራተኞች የደም ልገሳ አከናወኑ
የደም ልገሳ ለተቀባዩ ህይወት፤ ለለጋሹም የህሊና ሐሴት ብሎም ሰብዓዊ ሃላፊነት ነው፡፡ ይህን የተረዱት የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ሰራተኞችም በትናንትናው ዕለት በኢኒስቲትዩቱ ቅጥር ውስጥ የደም ልገሳን በማከናወን ሰብዓዊ ሃላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡ የደም ልግሳው “ላማባዲና” በተሰኘው የተቋሙ ሰራተኞች ሶሻል ኮሚቴ አዘጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን በየሶስት ወራት ልዩነት ይደረጋል፡፡ የተቋሙ ሰራተኞች ይህን መሰል በጎ ተግባራትን በተለያዩ ወቅቶች ከውነው አልፈዋል፡፡ በደም ልገሳ ረገድም የአሁኑን ጨምሮ ለስምንት ጊዜያት ደም የመለገስ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡
በበጎ ፍቃድ የሚለገስ ደም በአደጋና ሌሎች ሁናቴዎች ምክንያት ደም ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ብቸኛው የደም ምንጭ እና ህይወትን ማስቀጠያ መንገድ ነው፡፡ በዓለም ላይ በዓመት እስከ 80 ሚሊዮን ዩኒት የሚሆን ደም ከበጎ ፍቃደኞች የሚሰበሰብ ቢሆንም የደም ልገሳ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ውስጥ በዝቅተኛ ደረጃ ይከወነል፡፡ ለአብነት እንኳን ብናይ ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት ያለው የደም ፍላጎት 18 ሚሊዮን ዩኒት ቢሆንም ከዚህ ውስጥ የሚሰበሰበው 15 በመቶ ያህሉ ብቻ ነው፡፡ በኢትዮጵያም ያለው የደም ፍላጎት ከ80 እስከ 120 ሺህ ዩኒት ሲሆን በዓመት የሚሰበሰበው ግን ከ43 በመቶ አይበልጥም፡፡
ታድያ ይህን መሰል በበጎ ፍቃደኝነት ደምን የመለገስ ተግባራት በተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት፣ ማህበራት እንዲሁም ሌሎች ማህበረሰቡን በሚያስተሳስሩ አደረጃጀቶች በዘላቂነት ቢከወኑ የሚሊዮን ወገኖችን ህይወት ማዳን ይቻላል፡፡
እርስዎስ ለስንት ጊዜ ደም ለግሰዋል?

የልብ በሽታ ከመከሰቱ ጥቂት ወራት በፊት ሰውነታችን የሚያሳየን 5 ምልክቶች
*******************************************
በዓለማችን ከ30 በመቶ በላይ ለሚሆነው የሰዎች ሞት የልብ በሽታ ዋነኛው መንስኤ ነው፡፡ ከዚህ የልብ በሽታ መንስኤ ውስጥ ደግሞ አብዛኛውን ሰው ለሞት የሚዳርገው ventricular fibrillation የተባለው የልብ ችግር ሲሆን ይህም ተጠቂው በበሽታው መያዙን ሳያውቅ ህይወቱን የሚያጣበት ሁኔታ ሲፈጠር ነው፡፡ ይህ በሽታ ምንም አንኳን ምልክቶቹን አይተን ጥሩ ህክምና የምናገኝበት ሁኔታ ሲፈጠር ከ90 በመቶ በላይ የመዳን እድል ቢሰጠንም ብዙ ሰዎች ግን ምልክቶቹን ባለማወቃቸው ምክንያት የህክምና እርዳታ ሳያገኙ ህይወታቸውን እንዲያጡ ይሆናል፡፡ በመሆኑም የልብ በሽታ ከመከሰቱ ጥቂት ወራት በፊት ሰውነታችን የሚሳየንን የማስጠንቀቂያ ምልክት ችላ ሳንል ተገቢውን የህክመና ሂደት መጀመር ያስፈልጋል፡፡
እጅግ በጣም ከፍተኛ የድካም ስሜት
ለቀናት፣ ለሳምንታትና ለወራት የቆየ ከፍተኛ የድካም ስሜት የሚሰማን ከሆነ የልብ በሽታ ሊከሰት መሆኑን የሚያሳየን የመጀመሪያው መንገድ ነው፡፡ ይህ የድካም ስሜት ምናልባት ከእንቅልፍ ማጣትና ከሌሎች በሽታዎች ጋር የተያያዘ የድካም ስሜት ሳይሆን ለብዙ ጊዜያት የሚቆይ እና በመጠኑም እጅግ በጣም ከፍተኛ ሊባል የሚችል የድካም ስሜት በመሆኑ በጥንቃቄ ማየት ያስፈልጋል፡፡
የትንፋሽ ማጠር
አንዳንድ ጊዜ ቀላል ሊባል የማይችል የአተነፋፈስ ችግር ሲያጋጥም ከሳምባ ጋር ማገናኘት የተለመደ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከልብ ጋር ተያይዞ በሚዘዋወረው ደማችን ውስጥ ያለው የኦክስጅን ማነስ ለትንፋሽ መቆራረጥና ማጠር ምክንያት ሊሆን ስለሚችል በጥንቃቄ ማየት ይበጃል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በአንድ ጥናት እንደተገለፀው በልብ በሽታ ከሚያዙ ሰዎች መካከል 40 በመቶ የሚሆኑት እስከ ስድስት ወር የሚዘልቅ የትንፋሽ ማጠር እንደሚታባቸው አስቀምጧል፡፡
ከፍተኛ መጠን ያለው ላብ እና የደረት ህመም
አብዛኛውን ጊዜ ሞቃታማ አየር ሲኖርና አድካሚ ስራ ስንሰራ ጤናማ የሆነ ላብ ሊያልበን ይችላል፡፡ ነገር ግን ምንም አይነት የሚያደክም ስራ ሳንሰራ ባልተለመደ ሁኔታ በደረታችን፣ በእጃችን፣ በአንገታችን እና በመንጋጋችን ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ላብ ካየን እና በተለይም በደረታችን ላይ የህመም ስሜትና ምቾት ያለመሰማት ነገር ከተመለከትን የልብ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላልና የህክምና ሂደት መጀመሩ ጥሩ ነው፡፡
የእንቅልፍ ማጣት፣ ድብርትና የፀጉር መመለጥ
ከጭንቀትና ድብርት በመነጨ የሚመጣ የእንቅልፍ ማጣት በተለያየ መልኩ የኦክስጅን መጠንን በማውረድ ለልብ በሽታ የመጋለጥ እድልን እንደሚጨምር በተደጋገሚ የተሰራ ጥናት ያሳየል፡፡ ከዚህ ባለፈ የፀጉር መመለጥ በግልፅ የሚታይ በልብ በሽታ የመጋለጥ ምልክት ሲሆን በተለይም 50 ዓመት በሞላቸው ወንዶች ላይ እና አንዳንድ ሴቶች ላይ በግልፅ የመታየት እድሉ ሰፊ ነው፡፡
ያልተለመደ የልብ ምት
ብዙውን ጊዜ ለአንድና ለሁለት ደቂቃ የሚቆይ ያልተለመደ የልብ ምት ለመፍዘዝ እና ለድካም የሚዳርግ ሲሆን ፍጥነቱን ሳይቀንስ የሚቀጥልበት ሁኔታ ደግሞ በአጠቃላይ ላልተስተካከለ የልብ ምት (arrhythmia) እና ለከፍተኛ የልብ ምት (tachycardia) ይዳርጋል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ምልክቶች ስንመለከት አዘውትረን የምናከናውነውን የአኗኗር ዘይቤ ከመፈተሽ ባለፈ የሃኪም ምርመራ የምናደርግበትን ሁኔታ መጀመር እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
ምንጭ፡ My Science Academy እና Bright Side

ተመራማሪዎች የብሬል ላፕቶፕ ሰሩ
*************************
በህንድ ደልሂ መቀመጫውን ባረገው የህንድ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት የሚገኙ ተመራማሪዎች ለአይነ ስውራን የሚሆን የብሬል ላፕቶፕ መስራታቸውን አስታውቀዋል። ረዘም ያለ ጊዜ በወሰደው በዚህ አዲስ ፈጠራ ተመራማሪዎቹ እንደገለፁት ከሆነ የተሰራው የብሬል ላፕቶፕ መሰረታዊ የሆኑትን የኢሜል እና የዌብ ብሮውዘር አገልግሎቶች ከመስጠት ባለፈ የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ሊጫኑበት እንደሚችል ገልፀዋል፡፡
DotBook የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የብሬል ላፕቶፕ ሁለት አይነት መልክ ኖሮት የተሰራ ሲሆን እነሱም 40Q እና 20P የሚል ስያሜ ተሰቷቸዋል፡፡ 40Q የተባለው የብሬል ላፕቶፕ አርባ ፊደሎችን ወይም (characters) በየመስመሩ የያዘ የብሬል ኪቦርድ ሲሆን 20P የተሰኘው ደግሞ ሃያ ፊደሎችን በየመስመሩ የሚይዝ ነው፡፡
እስካሁን ዋጋቸው እጅግ ውድ የሆኑ 40 የሚደርሱ የብሬል መሳሪያዎች መሰራታቸውን የገለፁት ተመራማሪዎቹ ይህ ችግርም አዲሱን የብሬል ላፕቶፕ ለመስራት እንዳነሳሳቸው ገልፀዋል፡፡ ላፕቶፑ ከህንድ የቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት በተጨማሪ ኖኢዳ እና ክሪቲካል ሶሊዩሽን ከተባሉ የግል ድርጅቶች ጋር በትብብር የተሰራ ሲሆን በመጋቢት ወር መጨረሻም ለተጠቃሚዎች እንደሚቀርብ ተገልጿል፡፡
ምንጭ፡ Tech Explorist

ዓለምን የለወጡ ሴት ሳይንቲስቶች
************************
ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴቶች ቀን በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ ይህ በዓል የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ እና ሊኖራቸው የሚገባውን የውሳኔ አቅም ለማጉላት ከመዋሉም ባለፈ በመላው ዓለም የሚገኙ ሴቶች ስለመብታቸው እንዲያውቁና እንዲያሳውቁም ትልቅ በር ይከፍታል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ዓለማችንን በመለወጥ በኩል እና ሴትነት በራሱ ይዞት የሚመጣውን ጫና ተቋቁመው ልይነት መፍጠር የቻሉ ብዙ ሴቶች ያሉ ሲሆን ከዚህ በታች የምትመለከቷቸውም ይህን ጀበድ የፈፀሙና ለመጪዎቹም መንገድ የጠረጉ ናቸው፡፡
1. ቫላንታይን ትረሽኮቫ
በህዋ ጥናት እና ምርምር እ.አ.አ በ1963 የሩሲያ “ቮስቶክ” የተባለች መንኮራኩርን ይዛ ወደ ህዋ በመብረር ያረፈች የመጀመሪያዋ ሴት ስነህዋ ተመራማሪ ለመሆን የበቃች ሲሆን ለዚህም ተግባር የወሰደባት ጊዜ ሶስት ቀናቶች ብቻ ነበሩ። የሷን ፈለግ በመከተል ከ20 አመት በሆላ ሴሊ ራይድ ወደ ህዋ በመጎዝ በአለም ሁለተኛዋ እና በአሜሪካ የመጀመሪያዎ ሴት የስነ-ህዋ ሳይንስ ተመራማሪ ለመሆን ችላለች።
2. ሜሪ ኩሪ
እ.አ.አ በ1903 “በራዴሽን” ዙሪያ ባደረገችው ጥናት እና ምርምር የመጀመሪያዋ ሴት የኖቭል ፕራይዝ ተሸላሚ ለመሆን ስትበቃ ፤ እ.አ.አ በ1911 በኬሚስትሪ ዘርፍ ባደረገችው ጥናት እና ምርምር “ራዲየም” እና “ፖሎኒየም” የተባሉ ሁለት ንጥረ-ነገሮችን በማግኘት የመጀመሪያዋ ሴት ባለሁለት ኖቭል ፕራይዝ ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች። በሁለት የተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ሁለት የኖቭል ሽልማቶችን በማሸነፍ በአለማችን የመጀመሪያዋ ለመሆን ችላለች።
3. ኢኒጂነር ዳና አሊሪያ
እ.አ.አ 1961 የመጀመሪያዋ ሴት የናሳ ኢኒጂነር ዳና አሊሪያ ትምህርቷን የተከታተለችው በኮምፒውተር ሳይንስ ኢኒጂነሪንግ ነው። ስራዋን የጀመረችው በካርኒፎርኒያ “ጄት ፕሮፑሊሽን ላብራቶሪ” ቢሆንም በሆላላይ ግን የመጀመሪያዋ ሴት የናሳ ኢኒጂነር ለመሆን በቅታለች። ዳና አሊሪያ በናሳ ቆይታዋ የጠፈር ተመራማሪዎች ከጠፈር ወደ ምድር መረጃዎችን እና መልእክቶችን የሚያስተላልፉበት በየነ-መረብ ለመዘርጋት በቅታለች። በዚህም ስራዋ በአሜሪካን የወታደሮች ጥናት እና ምርምር ላብራቶሪ ውስጥ የመጀመሪያዋ ሴት ስራ አስኪያጅ ሆናለች።
4. አሚሊያ ኢርህርት
እንደ እ.አ.አ ከ1930 በፊት አንድ ሰው ለብቻው የአትላንቲክ ውቅያኖስን በኢሊኮፍተር ለማቋረጥ ብዙ ሙከራዎች ተደርገው ነበር። ነገር ግን ይህን ማሳካት የቻለው አንድ ሰው ብቻ ነው ። እንደ እ.አ.አ በ1932 አሚሊያ ኢርህርት የአትላንቲክ ውቅያኖስን በማቋረጥ በአለማችን ሁለተኛዋ እና የመጀመሪያዋ ሴት ለመሆን በቅታለች። ይሄንን ጉዞ ለማጠናቀቅ የፈጀባት 15 ሰዓት ብቻ ሲሆን ሰአቱም በወቅቱ ሪከርድ ሆኖ ተይዟል። እ.አ.አ በ1937 አለምን ለመዞር ባደረገችው በረራ ሙከራ እስካሁንም የደረሰችበት ሳይታወቅ ልትጠፋ ችላለች። እንደ እ.አ.አ በ1953 ጃኬሊን ኮችራን የሷን ፈለግ በመከተል የንፋስ እንቅፋችነትን በመቀነስ የጄት ፍጥነትን ከአስራአንድ አመት በኃላ በእጥፍ መጨመር ችላለች።
ምንጭ፡ ቴክ ሳይንስ

ጊዜው ለምን ይሮጣል?
*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*
በምድራችን የሚገኙ ለፍፁምነት የቀረቡ ሰዓቶች በሶስት መቶ ዓመታት ውስጥ አንድ ሴኮንድን ብቻ የሚያጎሉ የጊዜ መለኪያዎች ናቸው፡፡ ሆኖም አዕምሮዓችን እነዚህን ውስን የጊዜ ልኬቶች ወስዶ የራሱን ዕይታ ያክልባቸዋል፡፡ ታድያ ለምን አዕምሮዓችን በትክክለኛው የጊዜ ልኬት መሰረት አይሄድም?፤ በደስታችን ወቅት ሰዓቱ ለምን ይሮጣል፤ በድብርትስ ለምን ይንቀራፈፋል?
አዕምሮ ሰዓትን የሚወስደው ግምቶቹን ተንተርሶ ነው፡፡ አዕምሮ ነገሮች ከመከሰታቸው አስቀድሞ ምን ሊመስሉ እንደሚችሉ የራሱን ግምት ይወስዳል፡፡ እያንዳንዱ ሃሳብ የራሱ የሆኑ ጥጎች (Horizons) አሉት፡፡ ለምሳሌ አንድን መፅሃፍ በምናነብበት ወቅት የሃሳብ ጥጋችን የመፅሃፉ ሽፋን፣ ቃላት፣ ቀጣዩ ዓረፍተ ነገር ወዘተ…. መቋጫ ላይ ይሆናል፡፡ ጊዜው የሚሄድልንም ለእነዚህ መቋጫዎች ባስቀመጥነው ግምት ላይ ተመስርቶ ነው፡፡ አንድን ነገር ለመገንዘብ በምንጥርበት ሰዓት አዕምሮዓችን ሰፊ ምስል በመስራት የቅርብ እና የሩቅ መቋጫዎችን ያስቀምጣል፡፡ በድብርት ሰዓታት ውስጥ የቅርቡን መቋጫ ማማተር እንጀምራለን፡፡ ለምሳሌ ከታሪኩ ይልቅ የአረፍተ ነገሩ ፍፃሜ ላይ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ መቋጫዎቹ አንድ ላይ ሳይጣመሩ ሲቀሩ ሰዓቱም መጓተት ይጀምራል፡፡ ለዚህ አዕምሮአዊ የጊዜ አመለካከት ተጠያቂ የሆነ የአዕምሮአችን አካል ባይኖርም ስለ አንድ ጉዳይ ማሰብ እና ማሰላሰል ከተጀመረ ግን ይህ የጊዜ እይታ ሊከሰት ይችላል፡፡
አዕምሮአችን በጊዜ ላይ ያለው ግንዛቤ በዚህ መልኩ ለምን እንደሆነ ግልፅ ማብራሪያ መስጠት ባይቻልም ዝግመተ ለውጥ አመጣሽ ሊሆን እንደሚችል ግን በቻምፓላሞድ ፋውንዴሽን የኒሮን ተመራማሪ የሆኑት ጆ ፓቶን ያስረዳሉ፡፡ ጨምረውም ህይወት ብቆይ ወይስ ብሄድ ይሻለኛል መሰል ውሳኔዎችን በተከታታይ የምንሰጥባት እንደሆነችና ይህ ውስጣዊ የጊዜ እይታ በአንድ ቦታ ላይ እስከመቼ መቆየት እንዳለብን እንድንወስን እንደሚያደርገን ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ነገሮችን የመረመርን እንደሆነ ሁናቴዎችን አስቀድሞ መገመት አዕምሮአችን ለማስታወስ እንደሚጠቅሙት እንረዳለን፡፡
አዳዲስ ትውስታዎችን የሚያስቀምጡት ኔሮኖች ትስስር እውነታን ከሚያስቀምጡት አንፃር ጥቅጥቅ ያሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ጥቅጥቅ ትስስሮች ትውስታውን እንዲቆይ ያደርጉታል፡፡ ለምሳሌ ረዘም ላለ ሰዓት የአውሮፕላን በረራ የምናከናውን ከሆነና ረዘም ያሉ በረራዎችን በተደጋጋሚ ማከናወን ከለመድን አሁን የምናደርገውን በረራ አዕምሮአችን ብዙ ትውስታዎችን ባለማስቀመጡ ሳቢያ በረራውን አጠር ባለ ቆይታ ያጠናቀቅን ሊመስለን ይችላል፡፡
የሆነው ሆኖ ወደ እርጅና በቀረብን ቁጥር የጊዜ ፍጥነት እየጨመረብን ይመጣል፡፡ ሁሉም ነገር ልብ ወለድ የሚመስልባቸው የልጅነት ጊዜያት አዕምሮአችን ጥቅጥቅ ትስስሮችን ስለሚፈጥር ብዝሃውን ለማስታወስ ይቻለናል፡፡ ባደግን ቁጥር ግን ነገሮችን የማስታወስ ችሎታችን እየመነመነ በወጣትነት አሊያም ተከትለውት በሚመጡት ዘመናት ምን እየሰራን እንዳሳለፍን ግራ እስከሚገባን ድረስ ልንረሳቸው እንችላለን፡፡
ምንጭ፡ Live Science

አረንጓዴ ቦታዎች የአዕምሮን ጤና ከፍ ያደርጋሉ
*********************************
የከተሜነት ማየል እና የኢንዱስትሪዎች መስፋፈት ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የዓለም ህዝብ በከተሞች ብቻ ተወስኖ እንዲኖር እያደረገው ይገኛል፡፡ ሰዎች ከተፈጥሮ እጅግ እየራቁ በመምጣቸው የተነሳም ተፈጥሮ የምትለግሰውን የበዙ ጥቅሞች እንዳያገኙ እና አለፍ ሲልም ለተለያዩ የጤና እክሎች እንዲጋለጡ ምክንያት ይሆናል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ የዓለም ጤና ድርጅት በቅርቡ ያዋጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው በዓለማችን የአዕምሮ መዛበት ችግር ከሚከሰትባቸው 450 ሚሊዮን ሰዎች መካከል ጥቂት የማይባሉት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አረንጓዴ ቦታዎችን ማዘውተር ካለመቻላቸው ጋር የተያያዘ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ከዚህ ሲያልፍም ለህይወት መጥፋት መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ይጠቅሳል፡፡
ድርጅቱ በተለይም እንደሚለው አካላዊ እንቅስቃሴ በሌለበትና የእግር ጉዞ በማይዘወተርበት ሁኔታ በአረንጓዴ ቦታዎች ራስን ያለማዝናናት ተሞክሮ ሲለመድ በሰዎች የአዕምሮ ጤና ላይ ትልቅ ተፅእኖ የሚኖረው ሲሆን፤ በዚህ ላይ ደግሞ የቴክኖሎጂ ቁሶች በሚደመርበት ጊዜ ውጤቱን የበለጠ ሊያካፋው እንደሚችል ይጠቅሳል፡፡ በዚህም የተነሳ ድርጅቱ እንደሚለው 3.3% የሚሆነው የዓለም ህዝብ በዚህና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ለሞት እንደሚዳረግ ይገልፃል፡፡
ታዲያ ከዚሁ ጋር በተገናኘ ሰሞኑን በዴንማርክ አርሁዝ ዩኒቨርስቲ የተደረገ አንድ ጥናት እንዳመለከተው ሰዎች የልጅነት ጊዜያቸውን አረንጓዴ በሆኑ ቦታዎች የሚያሳልፉ ከሆነና እድገታቸውንም በዛ መመስረት ከቻሉ 55 በመቶ ያህል የአዕምሮ ጤናቸውን መጠበቅ አንደሚችሉ ገልጿል፡፡ በተለይም ተፈጥሮአዊ እይታዎች ያሉበትና ልምላሜን በተላበሰ ሰፍራ ህይወትን መመስረትና ስራዎችን መከወን የመልካም ስሜት ባለቤት እንሚያደርግና ደህንነት በተሞላ መንፈስ ስራን በቅልጥፍና ለመስራት እንደሚረዳ ገልጿል፡፡
ምንጭ፡ tribune.com.pk

የሰሜን ኮሪያ ሀከሮች ስርቆት
+*+*+*+*+*+*+*+*+*+*+*+*+
ባለፉት አምስት ዓመታት ከተደረጉት ትላልቅ የሳይበር ጥቃቶች ውስጥ በመንግስት እንደሚደገፉ የሚታመኑት የሰሜን ኮሪያ ድረ-ገፅ በርባሪ ወይም ሃከሮች የከወኗቸው ከፊት ተሰላፊዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የጥቃት ቡድኖች በተግባሩ እጅግ የተካኑ ሲሆኑ ጥቃቶቹም ይህን ይመሰክራሉ፡፡ በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ፀጥታ ምክር ቤት ባወጣው ሪፖርት መሰረት እነዚህ ቡድኖች 670 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ እና ክሪፕቶከረንሲ በህገ-ወጥ መንገድ አግኝተዋል፡፡
በ2015 የባንግላዲሽ ማዕከላዊ ባንክ ላይ ባደረሱት የሳይበር ጥቃት ብቻ እነዚህ የሰሜን ኮሪያ ድረ-ገፅ በርባሪዎች 81 ሚሊዮን ዶላር እንዳገኙ ይታመናል፡፡ ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመትም የህንድ ኮስሞስ ባንክን በማጥቃት 13.5፤ ከርሱ አስቀድሞም የቺሊን ባንክ ኤቲኤም ማሽኖች ትስስር መረብን በማጥቃት 10 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ችለዋል፡፡
እነዚህ የሰሜን ኮሪያ ሃከሮች የክሪፕቶከረንሲ ዝውውሮችንም በተሳካሁኔታ ማጥቃት ችለዋል፡፡ በግሩፕ አይቢ የሚገኙ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች እንዳስቀመጡት ከሆነ በዓለማችን ከሚፈፀሙት አጠቃላይ የክሪፕቶከረንሲ ጥቃቶች ውስጥ 65 በመቶዎቹ በነኚህ ሰሜን ኮሪያዊያን አማካኝነት እንደሚከወኑ ገልፀዋል፡፡ ከጥር 2017 እስከ መስከረም 2018 በፈፀሙት ጥቃት እንኳን የ570 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራን በሰለባዎቻቸው ላይ አድርሰዋል፡፡
ሰሜን ኮሪያ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተጣለባት ማዕቀብ ገንዘብን በህጋዊ መንገድ እንዳታገኝ አድርጓታል፡፡ ሆኖም የኪም ጆንግ ኡን ሃገር ይህን በመሰሉ ጥቃቶች የምታጋብሰው ትርፍ የማይነጥፍ የገቢ ምንጭ ሆኖላታል፡፡ ለዚህም ይመስላል የሃገሪቱ መጠነ ሰፊ የክሪፕቶከረንሲ አጠቃቀም መሰል ጥቅምን ሊያመጣላት የቻለበት አንዱ ምክንያት መሆኑ፡፡ ክሪፕቶከረንሲዎች በአብዛኛው ሃገራት ህግ በሚያውቃቸው ተቋማት አማካኝነት ስለማይከወኑ ማዕቀቦችን ተፅዕኖ ከመፍጠር ያግዷቸዋል፡፡ ሌላኛው ምክንያት የክሪፕቶከረንሲ ዝውውሮች ለመከታተል አስቸጋሪ መሆናቸው ነው፡፡ ምንም እንኳን ተከታትሎ ማግኘት የሚቻል ቢሆንም ሰፊ ጊዜን የሚወስድ እና ውስብስብ ነው፡፡
ምንጭ፡- Forbes

ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ
$**$**$**$**$**$**$**$**$**$
ተቋማችን የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በሥሩ በሚገኙት ሦስት ማዕከላት ላሉ የምርምር ዳይሬክቶሬቶች ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘሩት የስራ መስኮች ላይ ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ባለሙያዎች እንዲያመለክቱ ይጋብዛል፡፡
በOnline ለመመዝገብ ሊንኩ ይኸውልዎ http://www.techin.gov.et/am/web/sticsite/techin12 /
http://www.techin.gov.et/am/web/sticsite/announcement