TechIn2
1.16K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
እድሜያቸው ከ55 በላይ ለሆኑ ሰዎች የ T-Mobile እቅድ
**************************
T-Mobile በመባል የሚታወቀው የስማርት ስልክ አምራች ድርጅት እድሜያቸው 55 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ገደብ አልባ የ5 ጂ የሚጠቀም ተንቀሳቃሽ ስልክ ማቅረቡን አሳወቀ፡፡ ይህ ስልክ የተሻሻለ የሆትስፖት ትስስር ያለውና ያለገደብ ኢንተርኔት መጠቀም የሚያስችል ነው፡፡
ማግኔታ ማክስ የተባለ አዲስ ገደብ አልባ ስልክ ታክስንና ሌሎች ክፍያዎችን ጨምሮ ሁለት መስመሮችን 45 የአሜሪካን ዶላር (ለሁለቱ 90) ያስከፍላል፡፡ ክፍይው ለወራዊ የኢንተርኔት ጥቅል የሚውል ሲሆን መጠቀሚያ ስልኩ ግን ያለ ክፍያ የቀረበ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስልኩ የ5ጂ እና 4ጂ ፕሪሚየም ዳታ፣ 40ጌጋ የሆትስፖት ዳታ፣ 4K የቪዲዮ ጥራትና ነጻ የኔትፍሊክስ አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡
ከ55 ዓመት በላይ ለሆናቸው ሰዎች የቀረበው ስልክ ለአንድ መስመር በወር 35 የአሜሪካን ዶላር የሚያስከፍል ሲሆን የ100 ሜጋ ባይት ፐሪሚየም ዳታ፣ የ5ጂ ሆትስፖት ዳታ እና ኔትፍሊክስን በነጻ መመልከት የሚያስችል ተጨማሪ እድልም አለው፡፡ አምራች ድርጅቱ ከዚህ በተጨማሪም እሜያቸው ከ55 በላይ ለሆኑ ሰዎች ብቻ የሚሆን 4 መስመሮችን የሚያስጠቀወም ተመሳሳይ ስልክ ለማቅረብም አቅዷል፡፡
የምርት ትውውቅ በተደረገበት ወቅት የድርጅቱ የገበያ ጥናት ባለሙያ የሆኑት ማት ስታኔፍ እኛ በእድሜ ከፍ ያሉ ደንበኞቻችን ስልካቸውን በተመጣጣኝ ወጭ መጠቀም የሚችሉበትን የተለያዩ ዘዴዎችን እየቀየስን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ Tech Xplore
Software development progress in Ethiopia፤ የኢንዱስትሪውን ባለድርሻዎች ያሰባሰበው መድረክ
======================
ሁሉንም የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላትን አሳትፎ በኢትዮጵያ የሚከናወኑ የሶፍትዌር ማበልፀግ ስራዎችን አንድ ደረጃ ለማራመድ በማለም የተዘጋጀው የምክክር መድረኩ ትናንት በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተካሄዷል፡፡ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት የተካሄደው የምክክር መድረኩ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉ ዕድልና ተግዳሮቶች፣ ሀገራዊ የሶፍትዌር ስታንዳርድ፣ ብሄራዊ ፖሊሲ እና ድንጋጌዎችን ጨምሮ አምስት አባይት ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያውጠነጠነ ነው፡፡
የዕለቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ የሶፍትዌር ማበልፀግ ከሌሎች ኢንዱስትሪዎች አንፃር ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የማጠይቅና በየትኛውም ትምህርት ዘርፍ ላይ ያለ ሰው በአጭር ጊዜ ስልጠና ሊከውነው የሚችለው ሆኖ ሳለ የቢዝነሶች አሰራር ስርዓትን አዘምኖ ምርታማነትን እንደሚያሻሽል ጠቅሰወዋል፡፡ “ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና ማማ እየተምዘገዘገች እንደምትገኝ ሁላችሁም ታውቃላችሁ” ያሉት አቶ ሙሉቀን ለዚህ ዕድገት እንደ ዋነኛ ምሰሶ ተደርጎ በሚወሰደው የሶፍትዌር ስራ ላይ ብዙ ተግዳሮቶች ቢኖሩም መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ ለተሳታፊዎች ጠቁዋል፡፡ አክለውም ኢትዮጵያውያን በጋራ በቆምንባቸው የታሪክ አጋጣሚዎች ሁሉ አሸናፊዎች እና ባለ ድሎች ስለመሆናችን የአድዋ ድልን ማሳያ አድርገው በዚህ መስክም ሀገራችንን ወደ ተሻለ የዕድገት ደረጃ ይወስዳት ዘንድ ያለንን እናበርክት ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤትን ጨምሮ ከልዩ ልዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮችን ያሳተፈ የፓናል ውይይት ተደርጓል፡፡ በዚህም በደረጃዎች፣ አዕምሮ ንብረት፣ የፖሊሲ እርምጃ እና ሌሎችም ዘርፉ ላይ ተፅዕንዖ የሚያደርጉ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ዘርፉን አስመልክቶ በመንግስት በኩል ብዙ እየተሰራ ስለመሆኑ እንዲሁም የግል ተቋማት እና ኢኖቬተሮችም ከመንግስት በኩል እንዲሻሻሉ በሚፈለጉ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጥያቄ እንዲያቀርቡ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የቴክኖሎጂ አማካሪ የሆኑት አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል ተናግረዋል፡፡ በአዕምሮ ንብረት እና ደረጃዎች ላይ አተኩረው ማብራርያ የሰጡት ሌላኛው በፅ/ቤቱ የቴክኖሎጂ አማካሪ አቶ አብዱራዛቅ ኡመርም የአዕምሮ ንብረትን አስመልክቶ ይጠቅማሉ ያሏቸውን ምክረ ሀሳቦች ያቀረቡ ሲሆን በቅርቡም ከብሔራዊ ባንክ ጋራ በመሆን ኢኖቬተሮች ተመዝግቦ የተጠበቀ የአዕምሮ ንብረታቸውን በማስያዝ ብድር እንዲያገኙ ጭምር እየተሰራ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
በተሳታፊዎች ዘንድ እንደ ሀገር ሊስተካከሉ ይገባሉ በተባሉ የዘርፉ ተግዳሮቶች ላይ ያተኮሩ ጥያቄና አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡፡ ከነዚህም መካከል በኢትዮጵያ የሚከሰተው የበይነ-መረብ መቆራረጥንን ተከትሎ ተቋማቱ ስለሚደርስባቸው ከፍተኛ ችግር፣ የመንግስት ተቋማት በሶፍትዌር ገበያው ላይ አለአግባብ ተወዳዳሪ ሆነው ስለመቅረባቸው፣ የአይሲቲ ፓርክ ለኢንዱስትሪው ባለድርሻዎች ያለው ተደራሽነት፣ የታክስ ድንጋጌዎች እንዲሁም ቪዛ አሰጣጥ ላይ ባለው መጓተት ላይ ያተኮሩት ይገኙበታል፡፡
በምክክር መድረኩ ፍፃሜ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ይረዳ ዘንድ የግል ተቋማቱን በማስተሳሰርና በመንግስትም በኩል ነገሮችን የሚያመቻች ኮሚቴ ከኢንስቲትዩቱ እና ተቋማቱ በተውጣጡ ሰዎች ተመስርቷል፡፡
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከክልል የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራት ከስምምነት ደረሰ
=========================
ኢንስቲትዩቱ ከተለያዩ የክልል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር ለሦስት ዓመታት ያህል ተፈፃሚ ሆነው የሚቆዩ ስምምነቶችን ዛሬ ተፈራርሟል፡፡ ቀድሞ የነበሩ የትብብር ስራዎችን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሳድጉ ተስፋ የተጣለባቸው ስምምነቶቹ ኢንስቲትዩቱን በመረጃ ስርጭት፣ ዕውቀት ሸግግር እንዲሁም ቴክኖሎጂን አሳድጎና አስፋፍቶ ተደራሽ በማድረግ ጨምሮ በ11 አበይት የትብብር ጉዳዮች ላይ ከክልል ቢሮዎቹ ጋር በጋራ እንሰዲሰራ የሚያስችሉት ናቸው፡፡
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት መረጃዎችን ዲጂታል በሆነ መልኩ ከማቅረብ አንስቶ አገልግሎት አቅራቢ ተቋማት ስራቸውን ቀልጣፋ በሆነ መልኩ እንዲያከናውኑ የሚያስችሉ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ተሾመ ሳህለማርያም በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡ ምንም እንኳን ኢንስቲትዩቱ ከተመሰረተ የአጭር ዓመታት ዕድሜ ቢኖረውም ብዙ ልምድ ለማካበት የቻለ መሆኑን የገለፁት ኢ/ር ተሾመ በቴክኖሎጂ እና ዕውቀት ሽግግር ረገድ ለተቋማቱ እገዛ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡
በክልልሎቹ በኩል የስምምነት ፊርማውን ያኖሩት ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊዎች ከኢንስቲትዩቱ ጋር ቀድሞም የጋራ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን በማስታወስ አዲሱ ስምምነትም ከፊርማ ባለፈ ወደ ተግባር ያመራ ዘንድ አፅዕንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ወደ ህብረተሰቡ መውረድ የሚችሉ በተለይም በኤሌክትሮኒክስ አስተዳደር (E-Governance) ላይ ያተኮሩና ለዚህም የሚረዱ የልምድ፣ ስልጠና እና ቁሳቁስ ድጋፎችን እንዲያደርግም ኃላፊዎቹ ጠይቀዋል፡፡
ቴክ-ሳይንስ ሪቪው ፫፤ ነገ በ10 ሰዓት ይጠብቁን
በነገው የሦስተኛ ሳምንት የሪቪው ፕሮግራማችን ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት ለአየር ያበቃናቸው የተቋማት፣ ቴክኖሎጂ ታሪክ እና የተመራማሪዎች የህይወት ታሪክ ዝግጅቶቻችን መልሰው በዳሰሳ መልክ ወደ እናንተው የሚቀርቡ ይሆናል፡፡ በዚህም፤
በተቋማት ፕሮግራማችን ላይ፤ ስለ የኢትዮጰያ ምርት ገቢያ፣ ፋሪስ ሮቦቲክስ ትምህርት ቤት፣ ጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት፣ አክሪዴሽን፣ ሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል፣ የኢትዮጰያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት፣ ሳይንስና ከፍተኛ ት/ሚ፣ ሳይንስ አካዳሚ፣ ወይዘሮ ስህን ፖ/ቴ/ኮ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
ቴክኖሎጂ ታሪክ ፤ ማይክሮስኮፕ፣ ሬድዮ፣ ሰርጓጅ መርከብ፣ ካሜራ፣ ቨርቹዋለ ሪያሊቲ
እንዲሁም በተመራማሪዎች የህይወት ታሪክ፤
ስለ ዶክተር ሃብቴ ጀቤሳ እና ቀሲስ ዶክተር ኃይሉ ተረፈ ላይ ያሰናዳናቸውን አስተማሪ ዝግጅቶች መለስ ብለን ነገ ቅዳሜ በ10 ሰዓት በMOE ቲቪ ይዘንልዎ እንመጣለን፡፡
የዩትዩብ ቻናላችንን (https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg) ሰብስክራይብ ማድረጉን እንዳይረሱ፤ ከዓመታት በፊት ከተላለፈው የመጀመሪየው ክፍል አንስቶ ያሉትን ሁሉንም የቴክ-ሳይንስ ፕሮግራሞች አንድ በአንድ መመልከትና ለእርስዎም ሆነ ቤተሰብዎ ዕውቀትን መገብየት ይችሉበታልና፡፡
የአየር ብክለትን መቆጣጠር የሚያስችል የመንገድ ዳር አጥር
********************************
የሰው ልጆችን አስከፊነቱ እያየለ ከመጠው የአየር ብክለት መታደግ የሚያስችል እንደ ማንኛውም የመንገድ ዳር አጥሮች የመንገድ ጠርዞችንና እጥፋቶችን ተከትሎ ሊተከል የሚችል ልዩ ቴክኖሎጂን ተመራማሪዎች መስራታቸው ተነገረ፡፡ ይህን የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ችግር ለመፍታት ተመራማሪዎች የማያቋርጥ ትግል እያደረጉ ነው፡፡ ከእነዚህ መካከል ችግሩን መፍታት የሚያስችሉ የፈጠራ ስራዎችን ማበልጸግ አንዱ ነው፡፡
በለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ የሚሰሩ ተመራማሪዎች የአየር እንቅስቃሴን ተከትለው በካይ ቅንጣቶች መንገደኞችን እንዳያገኙ የሚያችሉ የመንገድ ዳር አጥሮችን ሰርተው አቅርበዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በገንዘብ ማጣት ወይም በድህነት ምክያት ከሚመጡ የጤና ቀውሶች በላይ በተበከለ አየር ምንያት የሚከሰቱ የጤና መታወኮች እያየሉ መጥተዋል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ህጻናት በቁመታቸው ምክንያት ለምድር እጅግ ቅርብ በመሆናቸው ለተበከለ አየር የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡
በኢምፔሪያል ኢንቫይሮሜንታል ፖሊሲ ማዕከል የምትሰራው ዶክተር ቲሊ ኮሊንስ በለንደን አንድ መንገድ ዳር ያለ ትምህር ቤት ውስጥ የሚማር ልጇ ሜዳ ላይ ሲጫወት ለተበከለ አየር መጋለጡን ከተመለከተች በኋላ ለችግሩ መፍትሔ ለማበጀት ያሰበችው፡፡ ወዲያውም ዶክተሯ በአፋጣኝ መሰራት ስለሚቻለው ነገር ማሰብ ጀመረች፡፡ በዚህም የመንገድ ዳር አጥሮች በካይ ቅንጣቶች በከባቢ አየር ውስጥ እንዳይቆዩ ማድረግ የሚቻልበትን መንገድ ማጥናት ጀመረች፡፡ በጥናቱም እጥፋት ያላቸው የመንገድ ዳር አጥሮች ከመኪኖች የሚወጡ በካይ ጋዞች በቀጥታ ወደ እግረኞችና ሌሎች ተጓዦች እንዳይሔዱ አቅጣጫ ማስቀየር እንደሚችሉ አረጋግጣለች፡፡
አጥኝዎቹ የጥናቱን ውጤት ባሳወቁበት ወቅት እጥፋት ያላቸው የመንገድ ዳር አጥሮች የተለያዩ በካይ ቅንጣቶችን ወደመጡበት አቅጣጫ እንዲመለሱ በማድረግ በመንገድ ግራና ቀኝ ያሉ የእግረኛ መንገዶችና ሌሎች ቦታዎች ከብክለት ነጻ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚያስችሉ አሳውቀዋል፡፡ ምንም እንኳን ከመንገድ ጋር በተያያዙ የተለያዩ ችግሮች ምክንያት የተግባራዊነት ክፍተት ይገጥመዋል ብለው ተመራማሪዎቹ ቢያስቡም ግኝቱ በሰዎች በተለይም በህጻናት ጤና ላይ ከፍተኛና የቅርብ ጊዜ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
ምንጭ፡ Tech Xplore
ያሳደጓትን ቤተሰቦች ስትከላከል ህይወቷ ያለፈው ድመት
=======================
ለወትሮ ውሾች ያሳደጓቸውን ወይም በጣም የለመዷቸውን ሰዎች በመጠበቅ እና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው የአሳደጊዎቻቸውን ህይወት ለማዳን ሲጣጠሩ መመልከት ብዙም አስገራሚ አይደለም፡፡ ነግር ግን ከሰሞኑ ከተሰማው አስደናቂ ዜና በፊት ድመቶች አንዲህ ያለውን ነገር ይፈፅማሉ ብሎ ማሰብ እጅግ ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡
በአውስትራሊያ ብሪስቤን ከተማ የተሰማው አስገራሚ ዜና ድመቶች እንደውሻ ሁሉ ከአሳደጊዎቻቸው ጋር በቃል የማይገለፅ ጥብቅ ቁርኝት ሊኖራቸው እንደሚችል ያመላከተ ነው፡፡ በዚህ ከተማ ውስጥ ኑሯቸውን ያደረጉት የድመቷ አሳደጊዎች በሚኖሩበት አካባቢ ተደጋግሞ በሚስተዋለው አደገኛ የእባብ ጥቃት የልጆቻቸው ህይወት አደጋ ውስጥ ወድቆ የነበረ ቢሆንም፤ ባልተጠበቀ ሁኔታ ያሳደጓት ድመት ህይወታቸውን ልትታደግ ችላለች፡፡ አርተር የተባለቸው ይህች ድመት በቤት ውስጥ በነበሩ ሁለት ህፃናት ላይ እባቡ ሊያደርስ የነበረውን ጥቃት በመከላከል ቤተሰቧን ከሞት የታደገች ቢሆንም እባቡ ባደረሰባት ከፍተኛ ንክሻ ምክንያት ህይወቷ በሁለተኛው ቀን ማለፉን ህክምና ሲያደርግላት የነበረው የእንስሳት ማከሚያ ማዕከል አስታውቋል፡፡
በድመቶች እና በእባቦች መካከል ያለው ደመነፍሳዊ ጥላቻ አዲስ ነገር ባይኖረውም ብዙዎችን ያስገረመው ጉዳይ ግን የድመቷ ተፈጥሮአዊ ምላሾች በዚህ ልክ ሊፈጸሙ የቻሉት ከአሳዳጊዎቿ ጋር ምን አይነት ደመነፍሳዊ ቁርኝት ቢኖራት ነው የሚለው ነው፡፡ መረጀውን በፌስቡክ ገፁ የለቀቀው የእንስሳት ድንገተኛ ህክምና አገልግሎት እንደሚያስቀምጠው ይህ አደገኛ እባብ በአለማችን ላይ እጅግ መርዛማ ከሚባሉት የእባብ ዘርያዎች በሁለተኛነት የሚቀመጥ ሲሆን፤ የእባቡ አንድ ንክሻ የደም ዝውውርን በማቆም በጥቂት ጊዜ ውስጥ ተጠቂውን ሽባ አድርጎ ሊያስምጥ ይችላል፡፡
የእንስሳት ሃኪሞች ከዚህ በፊት ተሰርቶ የነበረ ተያያዥ ምርምር ዋቢ በማድረግ እንደሚያስረዱት ድመቶች ከአሳዳጊዎቻቸው ጋር የሚኖራቸው ደመነፍሳዊ ቁርኝት እድሜያቸው አንድና ሁለት የሆኑ ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር ከሚኖራቸው ግንኙነት ጋር በዙም እንደማይለያይ ይናገራሉ፡፡
ምንጭ፡ Independent
የከሰል ምርትን ለከባቢ ተስማሚ የማድረጉ ጥረት ክሽፈት እና ቀጣይ እርምጃዎች
========================
ከሰሃራ በታች ለሚገኙ ብዙ አፍሪካውያን ዜጎች ከሰል እጅግ አስፈላጊ የኃይል ምንጭ ነው፡፡ አካበባቢው 65 በመቶ የሚሆነውን የምድራችን የከሰል ምርትን ሲሰጥ ከዚህ ውስጥም ናይጄሪያ፣ ኢትዮጵያ እና ጋና ቀዳሚዎቹ አምራቾች ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ በዋናነት በአነስተኛ አምራቾች አጅ የሚገኘው ዘርፉ በአካባቢው ብቻ እስከ 40 ሚሊዮን ሰዎችን ቀጥሮ እያሰራ ይገኛል፡፡ በተጠቃሚነት ረገድም ከሰሃራ በታች የአፍሪካ ክፍል ቀዳሚው ነው፤ በአካባቢው አንድ ሰው በአማካኝ በየዕለቱ 0.69 ኪዩቢክ ሜትር ከሰል የሚጠቀም ሲሆን ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ አንድ ሰው በነፍስ ወከፍ ከሚጠቀመው የእንጨት መጠን በ2.5 እጥፍ የላቀ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ዘርፉ በተለያዩ ችግሮች የተከበበ ነው፡፡
ከሰል አንድን እንጨት በማቃጠል የሚገኝ ምርት ነው፡፡ በቃጠሎው ወቅት ኦክስጅን ሲበዛ እንጨቱን ወደ አመድነት ይለውጠዋል፡፡ ብዙውን ጊዜ በአካባቢው ከሰልን የሚያመርቱ ሰዎች የኦክስጅን አቅርቦቱን በአግባቡ መቆጣጠር አስቸጋሪ ስለሚሆንባቸው ምርቱ እንዲባክን አስገድዶታል፡፡ ይህም ከብዙ እንጨት አነስተኛ ከሰል እንዲገኝ ከማድረጉም ባሻገር ኢንዱስትሪው በአፍሪካ ካሉ ቀዳሚ የደን ጭፍጨፋ መንስኤዎች መካከል እንዲሆን አድርጓል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን አሁንም በአካባቢው የከሰል ፍላጎት በማደግ ላይ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ መንግስታት ኢንዱስትሪውን ለመቆጣጠር ያለሙ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ መካከል ዘርፉን ስርዓታዊ እንዲሆን የማድረጉ ተግባር ተጠቃሽ ነው፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በከባቢ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ በማለምም ሆነ ከኢንዱስትሪው የታክስ ገቢ ለመሰብሰብ ጋና እና ማላዊ ይህን መንገድ ተጉዘውበታል፡፡ የነዚህ ጥረቶች ውጤት ታድያ መልካም ያልሆነ ውጤትን ከስቷል፡፡ ለምሳሌ በጋና ለአካባቢ ተስማሚ የከሰል ማምረትን ለማስፋፋት በሚል መንግስት የውጪ ባለሃብቶች ዘርፉ ላይ እንዲገቡ መፍቀዱ አነስተኛ አምራቾችን ያፈናቀለ ሆኗል፡፡ ታክስን የማስተዋወቁ ሀሳብም ኢንዱስትሪውን እንዴት ለከባቢ የተስማማ አልያም የገጠሩን ልማት የሚደግፍ እንደሚያደርገው ጠርቶ አልተቀመጠም፡፡ ማላዊም በበኩሏ በከሰል ምርቶች ላይ ያሳለፈችው እገዳ ብዙዎችን ወደ ድህነት የገፈተረ ሆኖባታል፡፡
እነዚህ እርምጃዎች በተቋማት ደካማ መሆን እና ሌሎች ምክንያቶች ሳብያ ከስኬት የራቁ ከመሆናቸውም ባሻገር አነስተኛ አምራቾች ከመንግስት የሚመጣባቸውን ክልከላ ለማምለጥ ወደ ጓሮ በር እንዲያማትሩ አስገድዷቸዋል፡፡ በዚህም ለምሳሌ በሕገ ወጥ መልኩ ከሰልን እንዲያዘዋውሩና ለሕግ አስከባሪዎችም ጉቦ እንዲከፍሉ ሆነዋል፡፡ እነዚህ ውድቀቶች ተደማምረው ዘርፉን ለከባቢ ተስማሚ ለማድረግ ቢፈለግም ውጥኑን ፍሬ አልባ ህልም አድርገውታል፡፡ ታድያ ይህን ችግር ለመቅረፍ ተከታዮቹን እርምጃዎች መውሰዱ ተገቢ ተደርጎ ይጠቆማል፡፡
የመጀመሪያው መንግስታት ባህላዊ የማህበረሰብ መሪዎች በገጠራማው ክፍል ለከሰል የሚሆኑ ዛፎችን በመለየት በኩል ያላቸውን ሚና ከፍ እንዲል ማድረግ አለባቸው፡፡ ይህ የራሱ ድክመቶች አሉበት፤ ለምሳሌ ዛፎቹን በመለየት በሚገኘው ገቢ ላይ መሪዎቹ ስርዓታዊ ተጠያቂነት የለባቸውም፡፡ በሌላ መልኩ ግን አደጋ ውስጥ ያሉ የዛፍ ዝርያዎች ተጠብቀው እንዲቆዩ አስችሏል፡፡
ሁለተኛው መንግስታት ግንዛቤን ለመፍጠር እና ከከባቢ የተስማማ የእንጨት ምርትን በማመቻቸት ላይ በገጠሩ አካባቢ በስፋት ሊሰሩ ይገባል፡፡ በነጋዴ እና አምራቹ መካከል ያለውን የትርፍ ክፍፍል መጠንን ከማስተካከል አንስቶ የአነስተኛ አምራቾች ማህበር እስከመመስረት ያሉ እርምጃዎች ለዚህ ስኬት ይረዳሉ፡፡
በሦስተኝነትም ከታች ጀምሮ የሚሰሩ የከሰል ምርትን የማሻሻል ስራዎች መንግስታት በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ እያደገ ከመጣው ከከባቢ በተስማማ መንገድ የሚመረቱ ከሰሎች ፍላጎት ተጠቃሚ እንዲሆኑና በአየር ንብረት ለውጥም ሆነ የሰዎች ስደት ላይ በጎ ሚናን እንዲጫወቱ ያስችላቸዋል፡፡
ምንጭ፡ The Conversation