TechIn2
1.16K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የአትክልት ዘርፉን የሚያበረታታ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ
=========================
የዓለም አቀፉ የአትክልት ምርምር እና ዕድገት ማዕከል (WorldVeg) በኔዘርላንድ መቀመጫቸውን ካደረጉ ሁለት አለምአቀፍ ተቋማት ጋር እና ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር አትክልቶች ለፕላኔቶች እና ለሰዎች (V4P&P) የሚል አዲስ የመነሻ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡ በትናትናው እለት በተካሄደው በዚህ የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት በኬኒያ የዓለም አቀፉ የአትክልት ምርምር እና ዕድገት ማዕከል ዋና ዳይሬክትር ዶ/ር ራልፍ ሩትሃርት በኢትዮጵያ እና ኬኒያ ሊካሄድ የታሰበው ይህ የፕሮጀክት እንቅስቃሴ የሁለቱን ሀገራት ሴቶችና ወጣቶች በአትክልት ምርት ላይ ዋና ተሳታፊ በማድረግ የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር ያለመ ፕሮግራም መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በፕሮግራሙ ማስጀመሪ ላይ በባለሙያዎች እንደተብራራው በዚህ የፕሮጅት ማዕቀፍ ውስጥ ለሁለቱም ሀገራት በጥቅሉ 200 (80 ኢትዮጵያ፣ 120 ኬኒያ) የአትክልት ቢዝነስ አውታር-መረቦችን በመመስረት 1,600 የስራ እድሎችን ለኢትዮጵውያን፤ 2,400 ደግሞ ለኬኒያውያን በጥቅሉ 4,000 ሴቶችና ወጣቶች በፕሮጀክቱ ኢንዲሳተፉ የታቀደ ሲሆን በቀጣዩ ምዕራፍም የአትክልት ቢዝነስ አውታር-መረቦችን ይበልጥ በማሳደግ የአትክልት ምርት እሴት ሰንሰለትን ለማበልፀግ የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት አንደታቀደ አስረድተዋል፡፡
በፕሮጀክቱ ላይ የሚሳተፉ ሴቶች እና ወጣቶች ለራሳቸው ከሚፈጠርላቸው የስር እድል ባለፈ በቀሰሙት እውቀትና ልምድ አማካኝነት ዘርፉን ይበልጥ ለማሻሻል እድል እንደሚኖራቸው ያስረዱት ዶ/ር ራልፍ ይህ ፕሮጀክቱ በታሳካ ሁኔታ እንዲካሄድም ከፖሊሲ አውጪዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካለት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ራዲሰን ብሉ ሆቴል በተካሄደው በዚህ የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ የግብርና ሚኒስቴርን ወክለው የተናገሩት የግብርና ግብዓት እና የገበያ ዘርፍ አማካሪ አቶ ደረጄ አሳምነው የአትክልት ምርቱን በሁሉም ዘርፍ ማሳደግ ለአፍሪካ ሀገራት የሚኖረው ትልቅ በረከት በማንሳት ይህ ፕሮጀክት በገጠራማ አከባቢዎች ለሚኖሩ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እና ብሎም የአካባቢያቸውን የምግብ ስርዓት ለማሻሻል እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡
በፕሮጀክቱ እንደዋና እቅድ የተያዘው የአትክልት ቢዝነስ አውታር-መረቦችን ወይም (Vegetable Business Networks) የመፍጠር እና የማሳደግ አለማ ሴቶች እና ወጣቶች በአትክልት ምርት እና የግብይት ሰንሰለት ውስጥ እንደአስተሳሳሪ በመሆን በአካባቢያቸው ያለውን አጠቃላይ የአትክልት ምርት እንዲሳድጉ እና የአመጋገብ ስርዓታቸውንም በዚያው እንዲያሻሽሉ የተነደፈ አለምአቀፍ ፕሮግራማ ነው፡፡
ምንጭ፡ Ethiopian herald እና SNV Netherlands Development Organisation
The workshop on “Software Development Progress in Ethiopia” aims at bringing together software developers, startups, public sector institutions, end-users and academia in order to discuss the progress made in software development and to set a way forward.

During the workshop, there will be group discussions in which participants who are invited from private sector and responsible public institutions take part. Discussion points include the opportunities and challenges in Software development business and the challenges of outsourcing public sector software development tasks. A panel discussion with panelists of software developers and public officials will be held, to reflect on the matters raised in group discussion and recommend for the way forward sought.

The main objective of this workshop is to engage all the relevant stakeholders to work towards the next step on the issues that arise and come up with an action plan to facilitate collaborated effort that could advance Software development practices in Ethiopia.
የፕላኔታችን ዲጂታል መንትያ እህት
*******************************
ተመራማሪዎች ከፕላኔታችን ስርዓት ጋር በእጅጉ የምትመሳሰል ዲጂታል ፕላኔትን እየሰሩ እንደሆነ ተነገረ፡፡ ይህም የምድራችንን የወደፊት እጣ ፋንታ ለመተንበይ የሚያስችል እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ በተጨማሪም የፖሊሲ አውጭዎች ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮችን ታሳቢ አድርገው እንዲዘጋጁ የሚያስችላቸውም ነው፡፡ በጉዳዩም ላይ አዲስ ስልት በአውሮፓ ተመራማሪዎችና በዙሪክ የኮምፒውተር ተመራማሪዎች አማካኝነት ተዘጋጅቷል፡፡
በ2050 ከብክለት ነጻ የሆነ ቀጠናን ለመመስረት የአውሮፓ ህብረት ግሪን ዲል እና ዲጂታል ስትራቴጂ የተሰኙ ሁለት ፕሮግራሞችን አዘጋጅቶ እየሰራ ነው፡፡ ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ በኮምፒውተር ሳይንስ እና በአየር ንብረት ላይ የሚሰሩ ተመራማሪዎች ደስቲኔሽን አርዝ የተሰኘ ከተያዘው የፈረንጆች 2021 አጋማሽ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ዓመታት የሚተገበር ፕሮግራምን አስተዋውቀዋል፡፡ በዚህም ወቅት ሊሰሩ ከታቀዱት መካከል አንዱ ወደፊት ሊከሰት የሚችልን ከአየር ጠባይ ለውጥ ጋር የተያያዘ ችግርን ከጊዜና ከቦታ አንጻር በትክክል የሚያመላክት ዲጂታል ፕላኔት ወይም ለምድራችን እህት አንዱ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የተለያዩ የምልከታ መረጃዎች በተከታታይ ወደ ዲጂታል ፕላኔቷ እንዲገባ በማድረግ ዲጂታል የመሬት ሞዴሉ በመረጃው መሰረት የወደፊቱን በተሸለ ትክክለኛነት መተንበይ ያስችላል፡፡ ተከታታይ ከሆነው የአየር ንብረት መረጃዎች በተጨማሪ ተመራማሪዎቹ በሰዎች የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ላይ ያተኮሩ አዳዲስ መረጃዎችንም ለመጠቀም አቅደዋል፡፡ ይህ ዲጂታል ሞዴል በምድራችን ላይ የሚከናወንን ሁሉንም እንቅስቃሴ የሚወክል ሲሆን በተጨማሪም ሰዎች በውሃ፣ በምግብና በሀይል አጠቃቀም ላይ የሚያደርሱትን ተጽእኖ ለመገምገም ያስችላል፡፡
እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ ከሆነ ዲጂታል የመሬት ሞዴሉ የተለያዩ መላ ምቶችንና ተጠባቂ ሁኔታዎችን መስራት የሚያስችል የመረጃ ስርአት በመሆን ለፖሊሲ አውጭዎች እንደሚያገለግል ተገልጧል፡፡ የምድር ዲጂታል መንትያ የበለጠ ዘላቂ ልማት የሚያሳዩ ሁኔታዎችን የሚያዳብር እና የሚፈትሽ የመረጃ ስርዓት እንዲሆን የታሰበ ሲሆን ፖሊሲዎችን በተሻለ ሁኔታም ለማሳወቅ የሚያገለግል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለንጹህ ውሃ እና ለምግብ አቅርቦት ወይም ለንፋስ፣ እርሻዎች፣ ለፀሐይ ኃይል እና እጽዋት ስትራቴጂካዊ እቅድ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ለዚህም ተግባር በአውሮፓ የሚገኙ የተለያዩ በአየር ንብረትና በህዋ ምርምር ላይ የሚሰሩ ድጅቶች ተሳትፈዋል፡፡
ምንጭ፡ PHYS.ORG
እድሜያቸው ከ55 በላይ ለሆኑ ሰዎች የ T-Mobile እቅድ
**************************
T-Mobile በመባል የሚታወቀው የስማርት ስልክ አምራች ድርጅት እድሜያቸው 55 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ገደብ አልባ የ5 ጂ የሚጠቀም ተንቀሳቃሽ ስልክ ማቅረቡን አሳወቀ፡፡ ይህ ስልክ የተሻሻለ የሆትስፖት ትስስር ያለውና ያለገደብ ኢንተርኔት መጠቀም የሚያስችል ነው፡፡
ማግኔታ ማክስ የተባለ አዲስ ገደብ አልባ ስልክ ታክስንና ሌሎች ክፍያዎችን ጨምሮ ሁለት መስመሮችን 45 የአሜሪካን ዶላር (ለሁለቱ 90) ያስከፍላል፡፡ ክፍይው ለወራዊ የኢንተርኔት ጥቅል የሚውል ሲሆን መጠቀሚያ ስልኩ ግን ያለ ክፍያ የቀረበ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስልኩ የ5ጂ እና 4ጂ ፕሪሚየም ዳታ፣ 40ጌጋ የሆትስፖት ዳታ፣ 4K የቪዲዮ ጥራትና ነጻ የኔትፍሊክስ አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡
ከ55 ዓመት በላይ ለሆናቸው ሰዎች የቀረበው ስልክ ለአንድ መስመር በወር 35 የአሜሪካን ዶላር የሚያስከፍል ሲሆን የ100 ሜጋ ባይት ፐሪሚየም ዳታ፣ የ5ጂ ሆትስፖት ዳታ እና ኔትፍሊክስን በነጻ መመልከት የሚያስችል ተጨማሪ እድልም አለው፡፡ አምራች ድርጅቱ ከዚህ በተጨማሪም እሜያቸው ከ55 በላይ ለሆኑ ሰዎች ብቻ የሚሆን 4 መስመሮችን የሚያስጠቀወም ተመሳሳይ ስልክ ለማቅረብም አቅዷል፡፡
የምርት ትውውቅ በተደረገበት ወቅት የድርጅቱ የገበያ ጥናት ባለሙያ የሆኑት ማት ስታኔፍ እኛ በእድሜ ከፍ ያሉ ደንበኞቻችን ስልካቸውን በተመጣጣኝ ወጭ መጠቀም የሚችሉበትን የተለያዩ ዘዴዎችን እየቀየስን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ Tech Xplore
Software development progress in Ethiopia፤ የኢንዱስትሪውን ባለድርሻዎች ያሰባሰበው መድረክ
======================
ሁሉንም የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላትን አሳትፎ በኢትዮጵያ የሚከናወኑ የሶፍትዌር ማበልፀግ ስራዎችን አንድ ደረጃ ለማራመድ በማለም የተዘጋጀው የምክክር መድረኩ ትናንት በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተካሄዷል፡፡ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት የተካሄደው የምክክር መድረኩ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉ ዕድልና ተግዳሮቶች፣ ሀገራዊ የሶፍትዌር ስታንዳርድ፣ ብሄራዊ ፖሊሲ እና ድንጋጌዎችን ጨምሮ አምስት አባይት ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያውጠነጠነ ነው፡፡
የዕለቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ የሶፍትዌር ማበልፀግ ከሌሎች ኢንዱስትሪዎች አንፃር ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የማጠይቅና በየትኛውም ትምህርት ዘርፍ ላይ ያለ ሰው በአጭር ጊዜ ስልጠና ሊከውነው የሚችለው ሆኖ ሳለ የቢዝነሶች አሰራር ስርዓትን አዘምኖ ምርታማነትን እንደሚያሻሽል ጠቅሰወዋል፡፡ “ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና ማማ እየተምዘገዘገች እንደምትገኝ ሁላችሁም ታውቃላችሁ” ያሉት አቶ ሙሉቀን ለዚህ ዕድገት እንደ ዋነኛ ምሰሶ ተደርጎ በሚወሰደው የሶፍትዌር ስራ ላይ ብዙ ተግዳሮቶች ቢኖሩም መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ ለተሳታፊዎች ጠቁዋል፡፡ አክለውም ኢትዮጵያውያን በጋራ በቆምንባቸው የታሪክ አጋጣሚዎች ሁሉ አሸናፊዎች እና ባለ ድሎች ስለመሆናችን የአድዋ ድልን ማሳያ አድርገው በዚህ መስክም ሀገራችንን ወደ ተሻለ የዕድገት ደረጃ ይወስዳት ዘንድ ያለንን እናበርክት ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤትን ጨምሮ ከልዩ ልዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮችን ያሳተፈ የፓናል ውይይት ተደርጓል፡፡ በዚህም በደረጃዎች፣ አዕምሮ ንብረት፣ የፖሊሲ እርምጃ እና ሌሎችም ዘርፉ ላይ ተፅዕንዖ የሚያደርጉ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ዘርፉን አስመልክቶ በመንግስት በኩል ብዙ እየተሰራ ስለመሆኑ እንዲሁም የግል ተቋማት እና ኢኖቬተሮችም ከመንግስት በኩል እንዲሻሻሉ በሚፈለጉ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጥያቄ እንዲያቀርቡ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የቴክኖሎጂ አማካሪ የሆኑት አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል ተናግረዋል፡፡ በአዕምሮ ንብረት እና ደረጃዎች ላይ አተኩረው ማብራርያ የሰጡት ሌላኛው በፅ/ቤቱ የቴክኖሎጂ አማካሪ አቶ አብዱራዛቅ ኡመርም የአዕምሮ ንብረትን አስመልክቶ ይጠቅማሉ ያሏቸውን ምክረ ሀሳቦች ያቀረቡ ሲሆን በቅርቡም ከብሔራዊ ባንክ ጋራ በመሆን ኢኖቬተሮች ተመዝግቦ የተጠበቀ የአዕምሮ ንብረታቸውን በማስያዝ ብድር እንዲያገኙ ጭምር እየተሰራ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
በተሳታፊዎች ዘንድ እንደ ሀገር ሊስተካከሉ ይገባሉ በተባሉ የዘርፉ ተግዳሮቶች ላይ ያተኮሩ ጥያቄና አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡፡ ከነዚህም መካከል በኢትዮጵያ የሚከሰተው የበይነ-መረብ መቆራረጥንን ተከትሎ ተቋማቱ ስለሚደርስባቸው ከፍተኛ ችግር፣ የመንግስት ተቋማት በሶፍትዌር ገበያው ላይ አለአግባብ ተወዳዳሪ ሆነው ስለመቅረባቸው፣ የአይሲቲ ፓርክ ለኢንዱስትሪው ባለድርሻዎች ያለው ተደራሽነት፣ የታክስ ድንጋጌዎች እንዲሁም ቪዛ አሰጣጥ ላይ ባለው መጓተት ላይ ያተኮሩት ይገኙበታል፡፡
በምክክር መድረኩ ፍፃሜ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ይረዳ ዘንድ የግል ተቋማቱን በማስተሳሰርና በመንግስትም በኩል ነገሮችን የሚያመቻች ኮሚቴ ከኢንስቲትዩቱ እና ተቋማቱ በተውጣጡ ሰዎች ተመስርቷል፡፡
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከክልል የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራት ከስምምነት ደረሰ
=========================
ኢንስቲትዩቱ ከተለያዩ የክልል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር ለሦስት ዓመታት ያህል ተፈፃሚ ሆነው የሚቆዩ ስምምነቶችን ዛሬ ተፈራርሟል፡፡ ቀድሞ የነበሩ የትብብር ስራዎችን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሳድጉ ተስፋ የተጣለባቸው ስምምነቶቹ ኢንስቲትዩቱን በመረጃ ስርጭት፣ ዕውቀት ሸግግር እንዲሁም ቴክኖሎጂን አሳድጎና አስፋፍቶ ተደራሽ በማድረግ ጨምሮ በ11 አበይት የትብብር ጉዳዮች ላይ ከክልል ቢሮዎቹ ጋር በጋራ እንሰዲሰራ የሚያስችሉት ናቸው፡፡
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት መረጃዎችን ዲጂታል በሆነ መልኩ ከማቅረብ አንስቶ አገልግሎት አቅራቢ ተቋማት ስራቸውን ቀልጣፋ በሆነ መልኩ እንዲያከናውኑ የሚያስችሉ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ተሾመ ሳህለማርያም በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡ ምንም እንኳን ኢንስቲትዩቱ ከተመሰረተ የአጭር ዓመታት ዕድሜ ቢኖረውም ብዙ ልምድ ለማካበት የቻለ መሆኑን የገለፁት ኢ/ር ተሾመ በቴክኖሎጂ እና ዕውቀት ሽግግር ረገድ ለተቋማቱ እገዛ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡
በክልልሎቹ በኩል የስምምነት ፊርማውን ያኖሩት ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊዎች ከኢንስቲትዩቱ ጋር ቀድሞም የጋራ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን በማስታወስ አዲሱ ስምምነትም ከፊርማ ባለፈ ወደ ተግባር ያመራ ዘንድ አፅዕንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ወደ ህብረተሰቡ መውረድ የሚችሉ በተለይም በኤሌክትሮኒክስ አስተዳደር (E-Governance) ላይ ያተኮሩና ለዚህም የሚረዱ የልምድ፣ ስልጠና እና ቁሳቁስ ድጋፎችን እንዲያደርግም ኃላፊዎቹ ጠይቀዋል፡፡