በተለያዩ መተግበሪያዎች የሚሰራጩ የጤና መረጃዎችን ፌስቡክ አገደ
************************************
ፌስቡክ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በፕላትፎርሙ ላይ ጥብቅ ክትትል እያደረገ መሆኑን አመላካች ነገሮች እየታዩ ነው፡፡ ከእነዚህም ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት በተካሄደው አወዛጋቢው የአሜሪካውያን ምርጫ ወቅት የተወሰዱ እርምጃዎች አንድ ማሳያ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ፌስቡክ ፕላተግፎርሙን ተጠቅመው የተለያዩ ጤና ነክ መረጃዎችን የሚያስተላልፉ ሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎችን ማገዱን አሳውቋል፡፡ ጉዳዩን የተከታተሉት የኒዮርክ ባለስልጣናት እንዳሉት ከሆነ ፌስቡክ እርምጃውን የወሰደው የድረ-ገጹን ህጎች በመጣስ መረጃዎችን በሚያሰራጩ መተግበሪያዎች ላይ ነው፡፡
ከዚህ በፊት መተግበሪያ የሚያበለጽጉ ተቋማትን ጤና፣ ቢዝነስና ግላዊ መረጃዎች ላይ መሰረት ያደረጉ ሶስተኛ ወገን መረጃዎችን እንዳያበለጽጉ ማሳሰቢያ ሰጥቶ የነበረው ፌስቡክ እስካሁን ድረስ ነገሩን ይፋ ሳያደርገው ቆይቷል፡፡ እንደ ተቋሙ ሰዎች ገለጻ ከሆነ እርምጃው የደንበኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ታስቦ የተወሰደ ነው፡፡
ፌስቡክ በፕላትፎርሙ የታገዱ የቃላት ዝርዝርን በመፍጠርና በመተንተን እንዲሁም መተግበሪያው ውስጥ ተቀባይነት የሌላቸውን ሚስጥራዊ መረጃዎችን በተሻለ ሁኔታ ለማጣራት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም በማጣራት ላይ ይገኛል ፡፡ ፖሊሲያችን የደንበኞቻችንን ደህንነት ሊጎዱ የሚችሉ ሴንሲቲቭ መረጃዎችን በፕላትፎርሙ እንዲንቀሳቀሱ አይፈቅድም ያሉት የፌስቡክ ቃል አቀባይ በአሁኑ ወቅት እንዲህ አይነት መረጃዎችን የመለየትና የማገድ ስራችንን አጠናክረን ቀጥለናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ Tech Xplore

ዲ ኤን ኤ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲንቀሳቀስ የሚያሳይ ምስል በተመራማሪዎች ይፋ ተደርጓል
======================
ዲ ኤን ኤ ወይም ዘረመል የምንለው የሞሎኪውል ስብስብ በህዋሶቻችን ውስጥ የሚያደርገውን የመተጣጠፍ ወይም ዳንስ መሰል እንቅስቃሴ የሚያሳይ የመጀመሪያ ምስል ከሰሞኑ በተመራማሪዎች ይፋ ተደርጓል፡፡ እንግሊዝ ውስጥ በሚገኙ ሶስት ዩኒቨርስቲዎች በጥምረት የተሰራው አዲሱ ምርምር ተመራማሪዎች ጥቅም ላይ ባዋሉት እጅግ የላቀ የአቶሚክ ኃይል ማይክሮስኮፕ እና ምስል ለመከሰት በሚያስችል የሱፐር ኮምፒውተር ሲሚዩሌሽን አማካኝነት የተሰራ ነው፡፡
ከፀጉር ቀለማችን አንስቶ እስከ እግር ጥፍራችን ድረስ በምን ልክ ሰውነታችን እንደሚያድግ የሚወስነው እና ትእዛዝ የሚሰጠው ይህ የሰው ልጅ የዘረመል ኮድ (DNA) አጠቃላይ ለመኖራችን ምከንያት የሆነውን ፕሮቲን በማበልፀግና በማምረትም ሰውነታችን በትክክል ስራውን እንዲሰራ የሚያደርግ ረቂቅ የተፈጥሮ ስራ ነው፡፡ እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር በ1953 ጀምስ ዋትሰን እና ፍራንሲስ ክሪክ በተባሉ የስነ ህይወት ተመራማሪዎች የመጀመሪው የዲ ኤን ኤ ድርብ-ሄሊክስ መዋቅር (double-helix structure) ይፋ ከተደረገ በኋላ፤ እነዚህ ዘረመሎች በህዋሶቻችን ውስጥ የሚደርጉት የመተጣጠፍ እንቅስቃሴን ምን እንደሚመስል የሚያሳየው አዲሱ የተመራማሪዎች ምስል ከ70 አመታት በኋላ በዲ ኤን ኤ ዘሪያ የተገኝ ትልቅ የምርምር ውጤት ይሆናል፡፡
ተመራመሪዎች የማይታመነውን ባለነጠላ የዲ ኤን ኤ ሞለኪውል የምስል እንቅስቃሴ ለማበልፀግ በማይክሮስኮፑ የወሰዱት እጅግ ከፍተኛ ጥራት ያለው የምስል ቀረፃ በእጅጉ የረዳቸው ሲሆን ከዚህ በፊት በነበረው የቴክኖሎጂ አቅም የዲ ኤን ኤ ምስል መውሰድ ቢቻልም እንደአሁኑ ሲንቀሳቀስ የሚያሳይ ምስል ግን ማግኘት አልተቻለም ነበር፡፡
ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል የዲ ኤን ኤ ድርብ-ሄሊክስ መዋቅር ውስጥ ያሉ እያንዳንዱን የአቶም አቀማመጥ በማሳየት ሁሉም ሞለኪውሎች በህዋሶቻችን ውስጥ የሚኖራቸውን የመዟዟር እና የመጠማዘዝ እንቅስቃሴ ለማብራራት ያግዛል፡፡ የዘረመሉን ተንቀሳቃሽ ምስል በማበልፀግ ሂደት ውስጥ ዋና ተሳታፊ የነበሩት ዶ/ር አሊስ ፓይን ይህ የምርምር ውጤት አጠቃላይ በዲ ኤን ኤ ዘሪያ የሚኖረንን የእውቀት አድማስ ለማስፋትና ሌሎች አደዲስ ግኝቶችን ለመጨምር ከማገዙም ባላይ አሁን ባለው ህክምና ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለማከል እንደሚረዳም ይናገራሉ፡፡
ምንጭ፡ Express እና Bigthink

የወጣቱ ፈጠራ በመንገድ ላይ ለሚሸጡ ሰዎች መልካም ነገር ይዞ መቷል
========================
በቶሎ የሚደርሱ ምግቦችን እና የተለያዩ መጠጦችን ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች በመዟዟር የሚሸጡ እና በዚህም ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ ብዙ አፍሪካውያን ዜጎች አሉ፡፡ ይህ እንቅስቃሴ በብዛት ከሚስተዋሉባት የአፍሪካ ሀገራት መካከል ናይጄሪያ አንዷ ስትሆን በሃገሪቱ ሰሜናዊ ግዛት ይህ አንቅስቃሴ ይበልጥ ጎልቶ ይታያል፡፡ በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ የሀገሪቱ ዜጎች በመንገድ ላይ ለሚያካሂዱት የምግብ ማቀነባበሪያ እና የሽያጭ ስራ መጠናቸው አነስ ያሉ ጄኔሪተሮች እጅግ አስፈላጊ ሲሆኑ ይህን ማሟላት ያልቻሉ ሰዎች ግን ስራውን በጊዜ ለማቆም ይገደዳሉ፡፡
ታዲያ ይህን ችግር የተመለከተው ወጣቱ የፈጠራ ባለሙያ ኡስማን በፀሃይ ኃይል የሚሰራ ግሩም ቴክኖሎጂን (kiosk) በማቅረብ ለወትሮ ያለጄኔረተር ንክች የማይደረገውን ይህን የማቀነባበር እና የሽያጭ ስራ ባቀረበው ቀላል መሳሪያ አማካኝነት ማንም ሰው እንዲሰራው አስችሏል፡፡ ወጣቱ የፈጠራ ባለሙያ በሚኖርበት የናይጀሪያ ሰሜን ግዛት ልዩ ስሟ ማኢ ሻዪ በተባለች አካባቢ ለሚኖሩ የሰፈሩ ሰዎች ያቀረበው ይህ የቴክኖሎጂ ውጤት ለማብሰል የሚያስችል ስቶቭ፣ ኢንቨርተር ባትሪ፣ ተንቀሳቃሽ ዴስክ እና ደንበኞች ያዘዙት ምግብ እስኪደርስ እንዲያዝናናቸው የተዘጋጀ ቴሌቪዥን ጭምር የተካተተበት ግሩም የቴክኖሎጀ ፈጠራ ነው፡፡ ወጣቱ ከእነዚህ ግብዓቶች በተጨማሪ ለምግብ ማስቀመጫ የሚያገለግል የፈጠራ አይነት በአዲሱ ቴክኖሎጂ ላይ ያካተተ ሲሆን፤ እነዚህ ሁሉ ግብዓቶች ከሶላር ፓኔል በሚያገኙት ሃይል መስራት የሚችሉ ናቸው፡፡
ወጣቱ የፈጠራ ባለሙያ iCart Solution ብሎ የሰየመው ይህ የቴክኖሎጂ ውጤት በቀላሉ መንቀሳቀስ የሚችል እና በቶሎ የሚደርሱ ምግቦችንና የተለያዩ መጠጦችን ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች በመዟዟር ለመሸጥ የሚያስችል ግሩም ቴክኖሎጂ ሲሆን ከዲዛይን ስራው ጀምሮ እስከ ምርት መጠናቀቂያው ድረስ ወጣቱ በሚያስተዳድረው ዳልስማን ቴክ በተባለ የቴክኖሎጂ ድርጅት የተከናወነ ነው፡፡ ይህን የቴክኖሎጂ ፈጠራ በፕሮቶታይፕ ደረጃ ሰርቶ ለማጠናቀቅ አምስት ቀን ብቻ እንደሚወስድበት የሚናገረው ወጣቱ የፈጠራ ባለሙያ ኡስማን በቀጣይ ጊዜያት ቴክኖሎጂውን በብዛት በማምረት ከሀገሩ አልፎ በሌሎች አፍሪካ ሀገራትም ምረቱን በስፋት ማቅረብ እንደሚፈልግ ይናገራል፡፡
ምንጭ፡ growingworld24

ከ87 ሺህ በላይ ከፍ ያለው የኮቪድ 19 ምርምር
*****************************
በአለም ዙሪያ ያሉ ተመራማሪዎች ኮቪድ 19 ከተከሰተ ጀምሮ በወረርሽኙ ዙሪያ ከ87 ሺህ በላይ የሚሆኑ በወረርሽኙ ዙሪያ የተሰሩ ጥናታዊ ጽሁፎችን እንዳሳተሙ ተነገረ፡፡ ይህ መረጃም እስካለፈው የፈረንጆቹ አመት ጥቅምት ወር ድረስ ያለው ነው፡፡ በዚህም ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩ ተመራማሪዎች በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ይህን ያክል የምርምር ውጤት በመታተሙ እጅግ እንደተገረሙ ተናግረዋል፡፡
በኦሃዩ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ጆን ግሌን ቁጥሩ በጣም አስገራሚ እንደሆነና በሳይንስ ታሪክ ውስጥ ተደርጎ ያማያውቅ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ሁሉም በሚባል ደረጃ በአለማችን የሚገኙ የሳይንስ ማህበረሰብ አባላትና ተመራማሪዎች ትኩረታቸውን ወደ ወረርሽኙ ማዞራቸውን ነው፡፡
ተመራማሪዎቹ በጉዳዩ ላይ መረጃ በሰበሰቡበት ወቅት ከተለያዩ ሳይንሳዊ የመረጃ ቋቶች ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የተሰሩ ጥናቶችን ለይተዋል፡፡ በዚህም ከጥር ግማሽ እስከ ሚያዚያ 2020 ድረስ 4875 የጥናት ውጤቶች ወይም አርቲክሎች የታተሙ ሲሆን ይህ ቁጥር እስከ ሀምሌ ግማሽ 2020 ድረስ ወደ 44 ሺህ 13 ከፍ ማለት ችሏል፡፡ በሚያስገርም መልኩ በአለም አቀፍ ደረጃ ተጠናክሮ የቀጠለው ይህ የምርምር ስራ በ2020ው የጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ 87 ሺህ 515 መድረሱን የተሰበሰበው መረጃ ያመለክታል፡፡
አጥኘዎቹ የኮሮና ወረርሽኝ ጥናትን በ1990ዎቹ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ ከነበረው የናኖ ስኬል ሳይንስ ጋር አወዳድረውታል፡፡ በናኖ ስኬል ዙሪያ የተሰሩ ጥናቶች ከ4000 ወደ 90 ሺህ ለማደግ 19 ዓመታት አስፈልጓል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ምርምሮች ግን እዚህ ቁጥር ላይ ለመድረስ አምስት ወራት ብቻ ፈጅቶባቸዋል፡፡ በዚህም ቁጥር ላይ የአሜሪካንና የቻይና አስተዋጽኦ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ከአጠቃላዩ ቁጥር ቻይና 43 በመቶውን የሸፈነች ሲሆን የወረርሽኙ ስርጭት በቻይና እየቀነሰ ከመጣ ወዲህ የሚሰሩ ምርምሮችም ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል፡፡ አሜሪካም ይህ ጥናት እስከተሰራበት ጊዜ ድረስ የ33 በመቶ ድርሻ ነበራት፡፡
ምንጭ: SciTechDaily

ህልም ላይ ሆኖም የሒሳብ ጥያቄዎችን መፍታት እንደሚቻል ታወቀ
=========================
ሰዎችን በተኙበት ሰዓት ማዋራቱ ህልማቸው ላይ ተፅዕንዖ ያደርሳል፤ አንዳንዴም የተኛው ሰው ከእንቅልፉ ሳይነቃ ምላሾችን መስጠት ይችላል፡፡ ከአሜሪካኑ ኖርዝ ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ የሆኑት ኬን ፖለር እና ባልደረባዎቹ ሰዎች ህልም እያለሙ ባሉበት ሰዓት የሂሳብ ጥያቄዎችን ጭምር መፍታት እንደሚችሉ አረጋግጠዋል፡፡ ይህ የሚሆነው ያንቀላፋው ሰው ህልም ላይ መሆኑንና አንዳንዴም ሊቆጣጠረው በሚችለው ፈጣን የአይን እንቅስቃሴ (REM) ተብሎ በሚጠራ የእንቅልፋችን የመባቻ ደረጃ ላይ ነው፡፡
ከህልም አላሚው ጋራ ጥሩ ግንኙነት እያደረጉ መሆናቸውንና መልሱም በትክክል እንደተመለሰላቸው ለማረጋገጥ አጥኚዎቹ ትክክለኛው መልሶቻቸውን የሚያውቋቸውን ጥያቄዎች ለጥናቱ ተሳታፊዎች ሲጠይቁ እንደነበር ኬን ፓለር ተናግሯል፡፡ የጥናት ቡድኑ ተሳታፊዎቹን አዎ ወይም አይደለም የሚል ምላሽ የያዙ ጥያቄዎች ብሎም ቀላል የሂሳብ ስሌቶችን ሲጠይቋቸው የቆዩ ሲሆን መላሾቹ ወደ እንቅልፍ ከማምራታቸው በፊት ስለሚጠየቋቸው ጥያቄዎች መረጃ አልተሰጣቸውም፡፡ ህልም ውስጥ ያሉት የጥናቱ ተሳታፊዎች ታድያ ለተጠየቋቸው ጥያቄዎች 29 ጊዜ ትክክለኛ፣ አምስት ጊዜ የተሳሳተ እንዲሁም 28 ጊዜ የፊት ጡንቻቸውን ወይም አይናቸውን በማንቀሳቀስ አሻሚ የሆኑ ምላሾችን የሰጡ ሲሆን ለ96 ጊዜያት ደግሞ ምንም ምላሽ ሳይሰጡ አልፈዋል፡፡
ከእንቅልፋቸው ከነቁ በኋላ አንዳንድ ተሳታፊዎች እያለሙ ሳለ ከህልሙ ውጪ ጥያቄዎች ሲጠየቁ መስማታቸውን ሲናገሩ ሌሎቹ ደግሞ ጥያቄዎቹን ያዩት ህልም አካል አድርገው ገልፀዋቸዋል፡፡ አንድ መኪና እየነዳ እንደነበር ሆኖ ሲያልም የነበረ ተሳታፊ በበኩሉ መኪናውን በማሽከርከር ላይ ሳለ የሂሳብ ጥያቁዎች በራዲዮን ሲጠየቁ እንደነበር አድርጎ አድርጎ ጥያቄዎቹን ከህልሙ አስተሳስሯቸዋል፡፡
ጥናቱ አንድ ሰው ህልም እያየ ሳለ የህልሙ ይዘት ላይ ተፅዕንዖ ማድረስ እንደምንችል ያሳየ መሆኑን የገለፁት የእንግሊዙ ስዋንዚ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ማርክ ብላግሮቭ “ቀጣዩ ጥያቄ አረፍተ ነገሮቹ በከፍተኛ ደረጃ ግላዊ ህይወት ላይ ያተኮሩና ስሜታዊ ቢሆኑ ምን ሊፈጠር ይችላል?” የሚለው እንደሆነ ይገልፃል፡፡ የሚያሰጋን ነገር ካለ ማለማችን እየታወቀን ባለው ህልም ላይ ነገሩን ብንሞክረው ከስጋታችን ልንላቀቅ እንደምንችልም ግምቱን ያስቀምጣል፡፡ በዚህም መሰረት ህልም ላይ ካለ ሰው ጋራ የሚደረግ ውይይት እንደ ጭንቀት፣ ስጋት እና መሰል የጤና ችግሮች ያሉበት ሰው የተሻለ እንቅልፍ እንዲተኛ ሊረዳው እንደሚችል ተስፋ አድርጓል፡፡
ምንጭ፡ New Scientist
ውድ የፔጃችን ቤተሰቦች አዳዲስ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ነክ መረጃዎችን በየቀኑ ለማግኝት የፔጃችን ተከታይ ይሁኑ፤
በሌሎች አማራጪች ሊያገኙን ከፈለጉም እነዚህን ይጠቀሙ
ድረ-ገፅ http://www.techin.gov.et/
ዩትዩብ youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg
ትዊተር twitter.com/TechinEthiopia

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከብሪጅ ኢትዮጵያ ጋራ በአብሮነት ለመስራት ከስምምነት ደረሰ
========================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ለአምስት ዓመታት የሚቆይ የትብብር ስምምነትን ከብሪጅ ኢትዮጵያ ጋራ ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በዲጂታል ላይብረሪ፣ ኃብት አጠቃቀም እንዲሁም ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ኮንፈረንስ፣ ወርክሾፕ፣ ሴምፖዚየም እና የህትመት ተግባራትን ማሰናዳትን ጨምሮ በ11 ዓበይት ጉዳዮች ላይ በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችላቸው ነው፡፡ ኢንስቲትዩቱን በመወከል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሙሉቀን ቀሬ በስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩ ሲሆን በብሪጅ ኢትዮጵያ በኩልም ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ሙሉጌታ አሰፋ ፈርመዋል፡፡
በትምህርት ዘርፍ ያለውን ክፍተት መሙላት የሚቻለው ተቋማት በጋራ ሆነው ሲሰሩና እነዚህን ክፍተቶች ለይተው የየግል ኃላፊነታቸውን በመወጣት በሀገሪቷ ውስጥ ያሉትን ከስልጠና ወይም ግብዓት ጋራ የተያያዙ ክፍተቶች መድፈን ሲችሉ መሆኑን የብሪጅ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶ/ር ብርሃኑ በየነ ጠቅሰዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ብሪጅ ኢትዮጵያ ላለፉት 17 ዓመታት በትምህርት ተቋማት ላይ እየሰራ ያለና መማርያ ክፍሎችን ከተለመደው አሰራር አሻግሮ ዲጂታል ወደ ማድረግ ስራ ውስጥ እየገባ ያለ መሆኑነም ጠቅሰው ያህንን ለማከናወን ያስችለው ዘንድ ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ጋር ለመስራት አቅደው መምጣታቸውን ተቅሰዋል፡፡
የኢትዮጵያን የትምህርት ስርዓት በመንቀፍ ሳይሆን በመደገፍ ማስተካከል ይቻላል ብላችሁ አምናችሁ ስለመጣችሁ አመሰግናለሁ ያሉት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ ኢንስቲትዩቱ በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ ያሉበትን ክፍተቶች ለመድፈን ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በአብሮነት እየሰራ እንደሆነ በስነ ስርዓቱ ላይ ለተገኙት የብሪጅ ኢትዮጵያ ኃላፊዎች አብራርተዋል፡፡ በቀጣይ ፕሮጀክቶችን ነድፎ በአስቸኳይ ወደ ስራ መገባት እንዳለበት ያወሱት አቶ ሙሉቀን ስራዎችን ውጤታማ በማድረግ ሀገራችን ያሉባትን የትምህርት ተደራሽነት ክፍተቶች ለመሸፈን እንደሚገባ አክለው ተናግረዋል፡፡

የአትክልት ዘርፉን የሚያበረታታ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ
=========================
የዓለም አቀፉ የአትክልት ምርምር እና ዕድገት ማዕከል (WorldVeg) በኔዘርላንድ መቀመጫቸውን ካደረጉ ሁለት አለምአቀፍ ተቋማት ጋር እና ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር አትክልቶች ለፕላኔቶች እና ለሰዎች (V4P&P) የሚል አዲስ የመነሻ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡ በትናትናው እለት በተካሄደው በዚህ የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት በኬኒያ የዓለም አቀፉ የአትክልት ምርምር እና ዕድገት ማዕከል ዋና ዳይሬክትር ዶ/ር ራልፍ ሩትሃርት በኢትዮጵያ እና ኬኒያ ሊካሄድ የታሰበው ይህ የፕሮጀክት እንቅስቃሴ የሁለቱን ሀገራት ሴቶችና ወጣቶች በአትክልት ምርት ላይ ዋና ተሳታፊ በማድረግ የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር ያለመ ፕሮግራም መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በፕሮግራሙ ማስጀመሪ ላይ በባለሙያዎች እንደተብራራው በዚህ የፕሮጅት ማዕቀፍ ውስጥ ለሁለቱም ሀገራት በጥቅሉ 200 (80 ኢትዮጵያ፣ 120 ኬኒያ) የአትክልት ቢዝነስ አውታር-መረቦችን በመመስረት 1,600 የስራ እድሎችን ለኢትዮጵውያን፤ 2,400 ደግሞ ለኬኒያውያን በጥቅሉ 4,000 ሴቶችና ወጣቶች በፕሮጀክቱ ኢንዲሳተፉ የታቀደ ሲሆን በቀጣዩ ምዕራፍም የአትክልት ቢዝነስ አውታር-መረቦችን ይበልጥ በማሳደግ የአትክልት ምርት እሴት ሰንሰለትን ለማበልፀግ የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት አንደታቀደ አስረድተዋል፡፡
በፕሮጀክቱ ላይ የሚሳተፉ ሴቶች እና ወጣቶች ለራሳቸው ከሚፈጠርላቸው የስር እድል ባለፈ በቀሰሙት እውቀትና ልምድ አማካኝነት ዘርፉን ይበልጥ ለማሻሻል እድል እንደሚኖራቸው ያስረዱት ዶ/ር ራልፍ ይህ ፕሮጀክቱ በታሳካ ሁኔታ እንዲካሄድም ከፖሊሲ አውጪዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካለት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ራዲሰን ብሉ ሆቴል በተካሄደው በዚህ የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ የግብርና ሚኒስቴርን ወክለው የተናገሩት የግብርና ግብዓት እና የገበያ ዘርፍ አማካሪ አቶ ደረጄ አሳምነው የአትክልት ምርቱን በሁሉም ዘርፍ ማሳደግ ለአፍሪካ ሀገራት የሚኖረው ትልቅ በረከት በማንሳት ይህ ፕሮጀክት በገጠራማ አከባቢዎች ለሚኖሩ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እና ብሎም የአካባቢያቸውን የምግብ ስርዓት ለማሻሻል እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡
በፕሮጀክቱ እንደዋና እቅድ የተያዘው የአትክልት ቢዝነስ አውታር-መረቦችን ወይም (Vegetable Business Networks) የመፍጠር እና የማሳደግ አለማ ሴቶች እና ወጣቶች በአትክልት ምርት እና የግብይት ሰንሰለት ውስጥ እንደአስተሳሳሪ በመሆን በአካባቢያቸው ያለውን አጠቃላይ የአትክልት ምርት እንዲሳድጉ እና የአመጋገብ ስርዓታቸውንም በዚያው እንዲያሻሽሉ የተነደፈ አለምአቀፍ ፕሮግራማ ነው፡፡
ምንጭ፡ Ethiopian herald እና SNV Netherlands Development Organisation

The workshop on “Software Development Progress in Ethiopia” aims at bringing together software developers, startups, public sector institutions, end-users and academia in order to discuss the progress made in software development and to set a way forward.
During the workshop, there will be group discussions in which participants who are invited from private sector and responsible public institutions take part. Discussion points include the opportunities and challenges in Software development business and the challenges of outsourcing public sector software development tasks. A panel discussion with panelists of software developers and public officials will be held, to reflect on the matters raised in group discussion and recommend for the way forward sought.
The main objective of this workshop is to engage all the relevant stakeholders to work towards the next step on the issues that arise and come up with an action plan to facilitate collaborated effort that could advance Software development practices in Ethiopia.

የፕላኔታችን ዲጂታል መንትያ እህት
*******************************
ተመራማሪዎች ከፕላኔታችን ስርዓት ጋር በእጅጉ የምትመሳሰል ዲጂታል ፕላኔትን እየሰሩ እንደሆነ ተነገረ፡፡ ይህም የምድራችንን የወደፊት እጣ ፋንታ ለመተንበይ የሚያስችል እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ በተጨማሪም የፖሊሲ አውጭዎች ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮችን ታሳቢ አድርገው እንዲዘጋጁ የሚያስችላቸውም ነው፡፡ በጉዳዩም ላይ አዲስ ስልት በአውሮፓ ተመራማሪዎችና በዙሪክ የኮምፒውተር ተመራማሪዎች አማካኝነት ተዘጋጅቷል፡፡
በ2050 ከብክለት ነጻ የሆነ ቀጠናን ለመመስረት የአውሮፓ ህብረት ግሪን ዲል እና ዲጂታል ስትራቴጂ የተሰኙ ሁለት ፕሮግራሞችን አዘጋጅቶ እየሰራ ነው፡፡ ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ በኮምፒውተር ሳይንስ እና በአየር ንብረት ላይ የሚሰሩ ተመራማሪዎች ደስቲኔሽን አርዝ የተሰኘ ከተያዘው የፈረንጆች 2021 አጋማሽ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ዓመታት የሚተገበር ፕሮግራምን አስተዋውቀዋል፡፡ በዚህም ወቅት ሊሰሩ ከታቀዱት መካከል አንዱ ወደፊት ሊከሰት የሚችልን ከአየር ጠባይ ለውጥ ጋር የተያያዘ ችግርን ከጊዜና ከቦታ አንጻር በትክክል የሚያመላክት ዲጂታል ፕላኔት ወይም ለምድራችን እህት አንዱ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የተለያዩ የምልከታ መረጃዎች በተከታታይ ወደ ዲጂታል ፕላኔቷ እንዲገባ በማድረግ ዲጂታል የመሬት ሞዴሉ በመረጃው መሰረት የወደፊቱን በተሸለ ትክክለኛነት መተንበይ ያስችላል፡፡ ተከታታይ ከሆነው የአየር ንብረት መረጃዎች በተጨማሪ ተመራማሪዎቹ በሰዎች የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ላይ ያተኮሩ አዳዲስ መረጃዎችንም ለመጠቀም አቅደዋል፡፡ ይህ ዲጂታል ሞዴል በምድራችን ላይ የሚከናወንን ሁሉንም እንቅስቃሴ የሚወክል ሲሆን በተጨማሪም ሰዎች በውሃ፣ በምግብና በሀይል አጠቃቀም ላይ የሚያደርሱትን ተጽእኖ ለመገምገም ያስችላል፡፡
እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ ከሆነ ዲጂታል የመሬት ሞዴሉ የተለያዩ መላ ምቶችንና ተጠባቂ ሁኔታዎችን መስራት የሚያስችል የመረጃ ስርአት በመሆን ለፖሊሲ አውጭዎች እንደሚያገለግል ተገልጧል፡፡ የምድር ዲጂታል መንትያ የበለጠ ዘላቂ ልማት የሚያሳዩ ሁኔታዎችን የሚያዳብር እና የሚፈትሽ የመረጃ ስርዓት እንዲሆን የታሰበ ሲሆን ፖሊሲዎችን በተሻለ ሁኔታም ለማሳወቅ የሚያገለግል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለንጹህ ውሃ እና ለምግብ አቅርቦት ወይም ለንፋስ፣ እርሻዎች፣ ለፀሐይ ኃይል እና እጽዋት ስትራቴጂካዊ እቅድ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ለዚህም ተግባር በአውሮፓ የሚገኙ የተለያዩ በአየር ንብረትና በህዋ ምርምር ላይ የሚሰሩ ድጅቶች ተሳትፈዋል፡፡
ምንጭ፡ PHYS.ORG