ኮካ ኮላ የመጀመሪያውን የወረቀት ማሸጊያ ሊሞክር ነው
====================
በአለማችን ላይ የተፈጥሮን ሚዛን በማዛባት ትልቅ ችግር ከሚፈጥሩ ምክንያቶች መካከል የፕላስቲክ ብክለት አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ በዚህ አለም አቀፍ ችግር ከፍተኛ የፕላስቲክ ገብዓት ጥቅም ላይ በማዋል የፕላስቲክ ብክለቱ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨመር ከሚያደርጉ ግዙፍ ተቋማት ውስጥ ደግሞ የኮካ ኮላ ኩባንያ በቀዳሚነት የሚቀመጥ ነው፡፡ በቅርቡ Break Free From Plastic የተሰኘው አለም አቀፍ ንቅናቄ ባዘጋጀው አመታዊ የደሰሳ ጥናት ላይ የኮካ ኮላ ኩባንያ ከየትኛውም አለም አቀፍ ተቋም በላይ ለፕላስቲክ ብክለት የመጀመሪያውን ደረጃ እንደሚወስድ አስታውቆ ነበር፡፡
በተፈጥሮ ላይ ከፍተኛ አደጋን በሚጠራው በዚህ አለም አቀፍ ችግር ላይ ትልቅ ድርሻን የሚወስደው የኮካ ኮላ ኩባንያ ይህን አደጋ በሚቀንስ መልኩ ወደፊት ለሚኖረው የምርት ግብዓት የመጀመሪያውን የወረቀት ማሸጊያ ጠርሙስ ለመሞከር በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ከሰሞኑ በኩባንያው ድረ-ገፅ ላይ እንደተገለፀው ድርጅቱ በተያዘው የፈረንጆች አመት 2,000 የሚጠጉ የወረቀት ማሸጊያ ጠርሙሶችን በፕሮቶታይፕ ደረጃ በማዘጋጀት የንድፋቸውን ውጤታማነት ለመገምገም እንደሚሞክር ተጠቅሷል፡፡ ኩባንያው ይህን የፕሮቶታይብ ሙከራ በዴንማርክ መቀመጫውን ካደረገ ፓባኮ ከተባለ የምርምር ተቋም ጋር የሚካሂድ ሲሆን፤ በሚኖራቸው የሙከራ ሂደትም አዴዝ በተባለ የአትክልት ጭማቂ ላይ በሚሰራ ተቋም ጋር በጋራ በመሆን የተጠቃሚዎችን እርካታ የሚገመግምሙ ይሆናል፡፡
የወረቀት ማሸጊያ ጠርሙስ ለአለማችን አዲስ የማሸጊያ (packaging) አመራጭ ነው የሚሉት በአውሮፓ የኮካ ኮላ ኢኖቬሽን ማናጀር ስቴን ፍራንሰን ይህን ለመተግበር የምናደርገው ጥረትም ለወደፊቱ የአለማችን የአከባቢ ጥበቃ መልካም ተፅዕኖ እንደሚኖረው እናምናለን ይላሉ፡፡ አሁን በሙከራ ላይ የሚገኘው የወረቀት ጠርሙስ በተወሰነ መልኩ የፕላስቲክ ግብዓት ቢኖረውም በዘላቂነት ግን እንደማንኛውም የወረቀት አይነት መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል የወረቀት ማሸጊያ ሊሰራ እንደታሰበ የኩባንያው ማናጀር ስቴን ፍራንሰን ይናገራሉ፡፡
ባለሙያዎች እንደሚገለፁት ይህ የወረቀት ማሸጊያ ጠርሙስ የመጠቀም እንቅሰቃሴ ለአለማችን የአካባቢ ጥበቃ መልካም ነግር ይዞ በሚጣም በቶሎ ለመተግበር ከባድ ከሚያደርጉት ምክንያቶች መካከል በካርቦን የተሞሉ ማንኛውም መጠቶች (carbonated beverage) በከፍተኛ ግፊት እንዲታሸጉ ከማስፈለጋቸው አንጻር በወረቀት ጠርሙስ የሚከናወነው ይህ የማሸግ ስራ ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች የተነሳ በተጠቃሚዎች ጤና ላይ መጠነኛ ተፅዕኖ ሊኖረው ስለሚችልም በዘርፉ የሚደረገው ረዥም የምርምር ሂደት እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ ኩባንያው ይህን የሙከራ እንቅሰቃሴ ሲጀምር ረዥም ጊዜ የሚወስድ የምርምር ሂደት እንደሚያከናውን ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡ ምንጭ፡ CTV NEWS

ፌስቡክ በአውስትራሊያ የጣለው የዜና ተደራሽነት እገዳ
****************************
ፌስቡክ አውስትራሊያውያን በፕላት ፎርሙ ዜናዎችን እንዳያገኙ ማገዱን አሳወቀ፡፡ እንደ ማህበራዊ ሚዲያው መረጃ ከሆነ እገዳው የተጣለው በሃገሪቱ ዲጂታል ማሰራጫዎች ለሚያሰራጩት መረጃ እንዲከፍሉ የሚጠይቅ ረቂቅ ህግ መውጣቱን ተከትሎ ነው፡፡ ድርጅቱ አክሎም በአውስትራሊያ የሚገኙ መረጃ አሰራጮች መረጃ ማውጣታቸው ያልተቋረጠ ሲሆን መረጃዎቻቸውና ሊንኮቻቸው በፌስቡክ አማካኝነት ለአውስትራሊያውያን ተደራሽ አይሆኑም ብሏል፡፡
በዚህ እገዳ ምክንያት በአውስትራሊያ የሚገኙ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የሀገር ውስጥ ወይም አለማቀፍ መረጃዎችን የማያገኙ ሲሆን ከአውስትራሊያ ውጭ ያሉ ተጠቃሚዎች ደግሞ ምንጫቸውን በአውስትራሊያ ያደረጉ መረጃዎችን ማግኘት አይችሉም፡፡ የፌስቡክ አካባቢያዊ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ዊሊያም ኢስቶን ረቂቅ ህጉ በፌስቡክ እና ፕላትፎርሙን በሚጠቀሙ የዜና ማሰራጫዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ያልተረዳ ነው ሲሉ ትችታቸውን አቅርበዋል፡፡ ዳይሩክተሩ አክለውም በዚህ ሁኔታውን ባልተረዳ ህግ ምክንያት አጣብቂኝ ውስጥ እንደገቡና የዜና ይዘት ያላቸውን መረጃዎች ላማገድ እንደተገደዱ ተናግረዋል፡፡
ይህ መረጃም የወጣው ፌስቡክና ጎግል ከአውስትራሊያ የሚዲያ ተቋማት ጋር ተስፋ ሰጭ ስምምነት ላይ እንደደረሱ ከተነገረ በኋላ ነው፡፡ ፌስቡክ አሁን አንዳንድ ሙከራዎችን እያደረገ እንደሆነ ቢገልጽም የአውስትራሊያው ኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር ፓውል ፍሌቸር ግን ከህግ ማስከበር ጋር በተያያዙ ጉዳዩች መንግስታቸው ወደኋላ እንደማይመለስ ተናግረዋል፡፡ ሚንስትሩ አክለውም ፌስቡክ ስራውን መልሶ ማግኘት ከፈለገ በፕላትፎርሙ ላይ በሚያወጣቸው ዜናዎች ዙሪያ ታማኝነቱን ማሳየት አለበት ብለዋል፡፡
በረቂቅ ህጉ ዙሪያ የአውስትራሊያ ፓርላማ እየመከረበት ሲሆን ሴኔቱም እንደሚመለከተው እየተጠበቀ ነው፡፡ በዚህ ረቂቅ ህግ አብሮ እየተከራከረ ያለው ጎግልም የመረጃ መፈለጊያ ፕላትፎርሙን ከአውስትራሊያ ሊያነሳ ይችላል ተብሏል፡፡
ምንጭ: Tech Xplore

የትንፋሻችን ድምፅ ስንተኛ ለምን ይጨምራል?
====================
አንዳንድ ሰዎች በእንቅልፍ ሰዓት የሌሎችን እንቅልፍ በሚነሳ መልኩ ያንኮራፋሉ፡፡ ሆኖም ሰዎች ባያንኮራፉም እንኳን ከፍ ባለ ድምፅ ሲተነፍሱ ይታያል፡፡ ይህ ለምን ይሆናል?
ተኝተንም ሆነ ሳንተኛ በትንፋሽ ወቅት የምናወጣው ድምፅ በአየር መዘዋወርያ ትቦዋችን ውስጥ በሚፈጠር መርገብገብ ሳብያ የሚከሰት መሆኑን ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ ወደ ውስጥ በምንተነፍስበት ጊዜ ከአፍ እስከ ማንቁርት ድረስ ተዘርግቶ ያለው የላይኛው የአተነፋፈስ ስርዓት ክፍላችን ውስጥ የሚፈጠረው ፈጣን የአየር እንቅስቃሴ በመላው የአተነፋፈስ ስርዓችን ውስጥ ያለውን ግፊት ይቀንሰዋል፡፡ ግፊቱ ይህን የላይኛውን ክፍል ስለሚያኮማትረው ትንፋሽን ሊገድበው ይችላል፡፡
ባልተኛንበት ሰዓት በዚህ ክፍል የሚኖረው እንቅስቃሴ ቱቦውንም ክፍት አሰድርጎ አየር በነፃነት እንደዚዘዋወር አድርጎ የሚያቆይ ይሆናል፡፡ ሆኖም ስንተኛ እንቅስቃሴው በቀድሞ ጥንካሬው ስለማይሆ ክፍሉ የሚኮማተርና የትንፋሻችን ድምፅም እያየለ የሚመጣ ይሆናል፡፡
በእንቅልፍ ሰዓት በትንፋሽ ቱቦው ዙርያ ያሉትን ጡንቻዎች ይላላሉ፡፡ ቱቦው እንዲፍታታ የሚያደርጉት የእነዚህ ጡንቻዎች መላላት ደግሞ ቱቦው እንዲጠብ ያደርገዋል፡፡ የአየር መተላለፊያው ሲጠብ በውስጡ የሚተላለፈው አየር ፍጥነቱ ይጨምራል፡፡ በዚህ ምክንያት አየሩ ይበልጥ ሲርገበገብ ደግሞ የበለጠ ድምፅ የሚፈጥር ይሆናል፡፡ ቱቦው ከዚህም የበለጠ እየጠበበ የሚሄድና ከስትሮ ትንሽ ሰፋ ባለ ጥበት ላይ ሲገኝ ደግሞ ማንኮራፋት ይጀምራል፡፡
በእንቅልፍ ሰዓታችን የትንፋሽ ቱቦው ከማንኮራፋቱ በላይም የሚጠብ ከሆነ መተንፈስን የማይቻል ስለሚያደርገው አየር ፍለጋ እንባንናለን፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ ዋናው መፍትሄ የሰውነት ክብደትን ቀንሶ በአየር መተላለፊያ ቱቦው ዙርያ ያሉትን ስቦች ማስወገድ ነው፡፡ በሌላ መልኩ አልኮልም ቱቦው ላይ ያሉትን ጡንቻዎች ስለሚያላላቸው ከዕንቅልፍ ሰዓት በፊት አልኮልን መውሰድ ማቆም ይገባል፡፡ ይህ ሁሉ መፍትሄን ካላመጣ ግን በእንቅልፍ ሰዓት የአየር ቱቦዎችን ክፍት የሚያደርግ መሳርያ መጠቀም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡
የአየር ቱቦው በሚጠብበት ሰዓት ትንፋሻችንም ቶለ ቶሎ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በአማካኝ በየደቂቃው ለ14 ጊዜያት የሚተነፍስ ሲሆን በሚተኛበት ሰዓት ይህ ቁጥር ወደ 15 እና 16 ያድጋል፡፡
ምንጭ፡ Live Science

ቪዲዮ አይቶ መፅሐፍ የሚፅፈው አዲሱ ቴክኖሎጂ
======================
ቴክኖሎጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቀድሞ በሰዎች ይሰሩ የነበሩ ተግባራትን ወስዶ ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ አሁን ደግሞ ይህ የእንጀራ ነጠቃው ወደ ጥበብ ባለሙያዎችም ፊቱን ማዞር ጀምሯል፡፡ ከቻይናዎቹ የዳሊየን ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቴክኖሎጂ እና ሆንግ ኮንግ ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ አጥኚዎች ቀድሞ ከፍተኛ ክህሎት ባላቸው የጥበብ ባለሙያዎች ዲዛይን ይደረጉ የነበሩ በምስል የተቀነባበሩ ወይም የኮሚክ መፅሐፍትን መስራት ችሏል፡፡ ቴክኖሎጂው መፅሐፍቱን የሚሰራው ፊልም፣ የቴሌቪዥን ድራማ፣ አኒሜሽን እና ሌሎች ቪዲዮዎችንም በመመልከት ነው፡፡
ተመራማሪዎቹ የሰሩት ስልት የቪዲዮ ፍሬሞችን ወስዶ ለኮሚክ መፅሐፍት በሚመች መልኩ ካስተካከላቸው በኋላ አነዱ ገፅ ላይ ያለው ምስል ከሌላኛው የተከተለ እንዲሆን አድርጎ በተለያየ ገፅ ያስቀምጣቸዋል፡፡ በተጨማሪም ምስሎቹ ላይ ያሉት ሰዎች የሚናገሯቸውን ቃላት ማስቀመጫ የሆነው የፅሁፍ ሳጥን ብዙዎቹ የኮሚክ መፅሐፍት ላይ እንደሚደረገው በተመሳሳይ ቅርፅ ከማስቀመጥ ይልቅ የተናጋሪውን ስሜት በሚገልፁ የተለያየ ቅርፅ ባላቸው ሳጥኖች ውስጥ የሚያስቀምጣቸው ይሆናል፡፡ ይህንንም ለማድረግ የቪዲዮውን ድምፅ እና በፅሁፍ የሚቀርበውን ንግግር (ሰብታይትል) ተመልክቶ በተለያዩ ንግግሮች ውስጥ ያለውን የስሜት መንፀባረቅ በመረዳት ነው፡፡
ስልቱ የኮሚክ መፅሐፍቱን ለመስራት ከታይታኒክ፣ ዘ ሜሴጅ፣ ፍሬንድስ እና አፕ ኢን ዘ ኤር ከተሰኙት ፊልምና የቴሌቪዥን ድራማዎች የወሰዳቸው 16 የቪዲዮ ክሊፖችን ተጠቅሟል፡፡ ቪዲዮዎቹ ከሁለት እስከ ስድስት ደቂቃ ርዝማኔ ያላቸው ነበሩ፡፡
ተመራማሪዎቹ አዲሱ ስልታቸውን በተለያዩ ሙከራዎች ላይ የፈተኑት ሲሆን በተጨማሪም በባለሙያዎች አማካኝነት ከፊልም ወደ ኮሚክ መፅሐፍትነት ከሚቀየሩት ጋራ አነፃፅረዋቸዋል፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ ሰዎችን ሰብስበው በአዲሱ ስልታቸው አማካኝነት የሰሯቸውን ኮሚክ መፅሐፍት ጥራት በጥበብ ባለሙያዎች ከሚሰራው ጋራ እንዲያነፃፅሩ አደረጉ፡፡ በውጤቱም አብዛኛዎቹ ተሳታፊዎች ከባለሙያዎች ይልቅ በአዲሱ ስርዓት የተሰራውን መርጠዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ አዲሱን ስልት በበቂ ሁኔታ ካሻሻሉት እና ከዚህም በበለጠ የስራውን ጥራት የሚጨምሩ ጥናቶችን ካከናወኑበት በኋላ ከተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ወይም ሌሎች ቪዲዮዎች ወስዶ ኮሚክ መፅሐፍትን ለመስራት ማገልገል እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡ Tech Xplore

ኤሌክትሪክን ለጦር መሳሪያነት በአሜሪካ
***************************
የአሜሪካ ጦር ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ ውሎ የማያውቅ ጨረር አመንጪ የጦር መሳሪያ እየሰራ መሆኑ ተነገረ፡፡ መሳሪያው ለመምታት ባለመው ነገር ላይ ተከታታይ ጨረሮችን የሚለቅ ነው፡፡ ይህ ተጋክቲካል አልትራሾርት ፐልስድ የተባለ መሳሪያ በሳይንስ ፊክሽን ፊልሞች ላይ እንደሚታዩ መሳሪያዎች አይነት እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡
ይህም ከ250 እስከ 300 ኪሎዋት ተተኳሽ ያለው ሲሆን የአሜሪካ ባህር ሃይል ከታጠቀው መሳሪያ አስር እጥፍ ሀይል ያለውና የተተኮሰ ሚሳኤልን መደምሰስ የሚያስችል እንደሆነም ታውቋል፡፡ ከዚህ በፊት በምድር፣ በባህርና በአየር ሃይሉ የተለያየ ብቃት ያላቸውን የጦር መሳሪያዎች የታጠቀው ጦሩ ይህኛውን ለየት የሚያደርገው በኤሌክትሪክ ሃይል ላይ የተመሰረተ መሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም የኤሌክትሪክ ሃይል እስካልተቋረጠ ድረስ ሃይሉ የማይነጥፍ እንደሆነ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
አዲሱ መሳሪያም በተሸከርካሪ የሚጓጓዝ ሲሆን ተንቀሳቃሽ ጀኔሬተርና ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ ያስፈልገዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ አራት ተሸከርካሪዎች ከነሙሉ መሳሪያቸው ለ2024 እንደሚደርሱ ተነግሯል፡፡
ምንጭ New scientist

በ1 ዓመት የታጣው የ20 ሚሊዮን ዓመታት ህይወት ዘመን
========================
በኮሮና ቫይረስ ሳብያ በ81 ሀገራት ብቻ ከ20.5 ሚሊዮን ዓመታት የሚልቅ ቀሪ ዕድሜ መታጣቱን አዲስ ጥናት አመላከተ፡፡ ጥናቱ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ባይሆንም እንኳን በቅርቡ መሞታቸው አይቀርም ነበር የሚለውን አስተሳሰብ አየር ላይ የሚዋልል መሰረተ ቢስ እንደሚያደርገውም ተነግሮለታል፡፡
የታጣው የመኖርያ ዘመን ሲባል ሟቾች በሞቱበት ጊዜ ባላቸው ዕድሜ እና ይኖሩበታል ተብሎ በሚታመነው የዕድሜ ጣርያ መካከል ያለው ልዩነት ነው፡፡ ጥናቱ የተሰራውም በ81 ሀገራት የተከሰቱ ከ1,279,866 በላይ የኮቪድ-19 ሞቶችን ብሎም የየሀገራቱን የተቀመጠ ዓማካኝ የህይወት ጣርያ ላይ በመመርኮዝ ነው፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት በነዚህ 81 ሀገራት የነበሩ የሚሊዮኖች ህይወት ውስጥ ገና ወደፊት ሊኖር ይቻል የነበረ የ20,507,518 ወይም በእያንዳንዱ ሟች በአማካኝ የ16 ዓመታት ዕድሜ ታጥቷል ማለት ነው፡፡ ከነዚህ የታጡ ዓመታት ውስጥ 44.9 በመቶው ዕድሜያቸው ከ55 እስከ 75 ዓመት ባለው ውስጥ ይገኙ ከነበሩ ሰዎች ላይ፣ 30.2 በመቶው ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በታች ከሆኑት ላይ እንዲሁም 25 በመቶው ዕድሜያቸው ከ75 ዓመት በላይ ከሆኑት ላይ ነው፡፡
ሀገራትን በምሳሌነት ወስደን ካየነው በእንግሊዝ ውስጥ የ833,874 ዓመታት ህይወት የታጣ ሲሆን ይህም በአማካኝ የ11.4 ዓመት ህይወት ነው፡፡ በስፔን ደግሞ አጠቃላይ 572,567 ወይም በአማካኝ 11.24 ዓመት ሲታጣ ነገሩ የከፋባት ፔሩ በአጠቃላይ 764,856 ዓመት በአማካኝ ደግሞ የ20.2 ዓመት ዕድሜን ሟች ዜጎቿ አጥተዋል፡፡ ምንም እንኳን በተለይ በሀብታሞቹ ሀገራት ውስጥ የመሞት ዕድላቸው ከፍ የሚለው በእርጅና ዘመን ውስጥ ባሉት ዜጎች ላይ ቢሆንም አብዛኛው ሞት የተከሰተው ግን ዕድሜያቸው ከ55 እስከ 75 ባለው ክልል ውስጥ ያሉት ላይ ነው፡፡
እንዲህም ሆኖ ግን በሀብታም ሀገራት ውስጥ የታጡት ዓመታት በዋናነት ከነዚህ ዕድሜያቸው በአንፃራዊነት ከፍ ካሉት ላይ ቢሆንም መካከለኛና አነስተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ዘንድ ግን ብዙው ዓመት ዕድሜያቸው 55 እና ከዚያ በታች ከሆኑት ላይ የተቀነሰ ነው፡፡ በፆታም ወንዶች ከሴቶች በ44 በመቶ የበለጠ ዕድሜን አጥተዋል፡፡
ምንጭ፡ The Guardian

ቴክ-ሳይንስ ሪቪው ፪፤ ነገ 10 ሰዓት ይጠብቁን
=================
በነገው የቴክ ሳይንስ መሰናዶዋችን ላለፉት ተከታታይ ሳምንታት ወደ እናንተው ያደረስናቸው የአብይ ፕሮግራም እና ብላቴናት ዝግጅቶቻችንን በሪቪው መልሰን የምንቃኛቸው ይሆናል፡፡ በዚህም፤
በአብይ ፕሮግራማችን ላይ፤ ስለ ሚጥል በሽታ፣ ስለ ዲጂታል ላይብረሪ፣ የግብርና ምርምር ስራዎች መቼ ተጀመረ፣ ቀርከሀ፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ አፍሪካ እና ቴክኖሎጂ እና መድሐኒታማና መዓዛማነት ያላቸው እጽዋቶች
ብላቴናት ደግሞ፤ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዊልቸር፣ የድሮን ፈጠራ፣ የሴኩሪቲ ካሜራ፣ ዘመናዊ የሻይ ቡና ማፊያ፣ ሻማን በድጋሚ መጠቀም፣ ተሸከርካሪ የሰራው ተማሪ፣ የእንጀራ መጋገሪያ ማሽን ላይ የሰራናቸውን ዝግጅቶች መለስ ብለን እናስቃኛችኋለን፡፡
የዩትዩብ ቻናላችንን (https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg) ሰብስክራይብ ማድረጉን እንዳይረሱ፤ ከዓመታት በፊት ከተላለፈው የመጀመሪየው ክፍል አንስቶ ያሉትን ሁሉንም የቴክ-ሳይንስ ፕሮግራሞች አንድ በአንድ መመልከትና ለእርስዎም ሆነ ቤተሰብዎ ዕውቀትን መገብየት ይችሉበታልና፡፡

ያለንበትን ቦታ በመከታተል ብቻ ወደ ገመናችን የሚመለከቱት የስልክ መተግበሪያዎቻችን ነገር
=========================
በየቦታው ከእጃችን የማንለያቸው ስልኮቻችን ላይ ያሉት መተግበሪያዎች በሌላ አካል እንዲታወቁብን የማንፈልጋቸው መረጃዎችን አሳልፈው እንደሚሰጡብን በተለያየ ጊዜ ሲነገር ቆይቷል፡፡ በቅርቡም እነዚህ በስልካችን ላይ ጭነን ያስቀመጥናቸው መተግበሪያዎች ያለንበትን ቦታ በመከታተል ብቻ ስለ እኛ ምን ያህል መረጃን እንደሚሰበስቡ ለማወቅ በማለም ከጣያልያኑ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቦሎኛ የመጣው ሚሮኮ ሙሴሌይሲ እና ከእንግሊዙ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለንደን የመጣው ቤንጃሚን ባሮን ጥናትን አድርገዋል፤ ለዚህ እንዲረዳ ብለው ያዘጋጁትን መተግበሪያ በመጠቀም፡፡ በዚህም አጥኚዎቹ መተግበሪያው ምን አይነት የግል መረጃዎችን እንደሚወስድና በጥናቱ ተሳታፊዎች ዘንድ ያለውን ስሜታዊነትም (Sensitivity) መረዳት ችለዋል፡፡
ተጠቃሚዎች ስልካቸው ላይ ለሚጭኗቸው መተግበሪያዎች ፍቃድ ሲሰጧቸው ምን እንደሚያስከትልባቸው በብዛት እንደማያጤኑ የሚናገረው ሚሮኮ ሙሴሌይሲ መረጃዎቹ ተጠቃሚዎች የሚኖሩበትን፣ ልማዳቸውን፣ ፍላጎታቸውን፣ ስነ-ህዝባዊ ሁኔታቸውን (Demographics) እና ስብዕናቸው የሚያሳዩ እንደሆኑ ጠቅሷል፡፡
ይህ ጥናት አድራሻን ከመከታተል የሚገኘው ሰፊ ግላዊ መረጃ ላይ ምልከታን በመስጠት የመጀመሪያው ነው፡፡ በተለይም እነዚህ መረጃዎች የተጠቃሚዎችን የግለኝነት መብት የሚጥሱ ስለመሆናቸውም አሳይቷል፡፡ ይህን ለማስቆም ታድያ አጥኚዎቹ “ትራኪንግአድቫይዘር” የተሰኘ ያለማቋረጥ ከተጠቃሚዎች ያሉበትን ቦታ የሚከታተል መተግበሪያን ሰርተው መረጃዎችን እየሰበሰቡ መልሰው ወደ ተጠቃሚዎቹ በመውሰድ ስለ መረጃዎቹ ስሜታዊነት ያላቸውን እይታ ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡
በጥናቱ ላይ 69 ተጠቃሚዎች መተግበሪያውን ለሁለት ሳምንታት ስልካቸው ላይ አድርገው ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡ በዚህም ትራክአድቫይዘር የተሰኘ መተግበሪያው ከ200 ሺህ በላይ ቦታዎችን ተከታትሎ 2,500 ስፍራዎችን በመለየት ወደ 5ሺህ የሚጠጉ ስነ-ህዝብ እና ስብዕናን የተመለከቱ የግል መረጃዎችን መሰብሰብ ችሏል፡፡ ከተሰበሰቡት መረጃዎች ውስጥ ስለ ጤና፣ ማህበራዊ-ምጣኔ ሀብታዊ ሁናቴ፣ ዘር እና ኃይማኖት የሆኑትን ተጠቃሚዎቹ ስሜታዊ የግል መረጃዎቻችን ናቸው ሲሉ ለይተዋቸዋል፡፡
እንደ አጥኚዎቹ ከሆነ አሁን የተሰራውን አይነት ትንተናዎች ተጠቃሚውን ታላሚ ያደረጉና በተለይም ስሜታዊ የግል መረጃዎቻቸውን የሚጠብቁ የማስታወቂያ ስርዓቶችን በማምጣት ረገድ መንገድ ጠራጊ ናቸው፡፡ ለእንደዚህ አይነት ስርዓቶች ምስጋና ይግባና ተጠቃሚዎች ወደ ክሊኒክ እና ሆስፒታል ባመሩ ቁጥር ጤናቸውን የተመለከቱ መረጃዎችን እንዲጠብቁ የሚያደርግ ማሳሰቢያዎችን መላክ ይቻላል ሲል ሚሮኮ ሙሴሌይሲ ይናገራል፡፡ አክሎም ቀድሞ በተቀመጡ የግለኝነት ማስተካከያዎች አማካኝነት አስፈላጊ መረጃዎች በሦስተኛ አካል እንዳይሰበሰቡ ወደሚያደርጉ ስርዓች መበልፀግ ሊያመራን ይችላል ብሏል፡፡

የቅዳሜውን አደጋ ተከትሎ ቦይንግ 777 አውሮፕላኖች ከበረራ እየታገዱ ናቸው
=======================
ቅዳሜ የተከሰተውንና የአውሮፕላኑ ስብርባሪዎች ከሰማይ እንዲወድቁ ያደረገው የሞተር ቃጠሎን ተከትሎ በአሜሪካን እና ጃፓን የሚገኙ ቁጥራቸው የበዛ ቦይንግ 777 አውሮፕላኖች ከበረራ እዲታገዱ ተደርጓል፡፡ አውሮፕላኑ በረራውን በማቋረጥ እንዲያርፍ ያስገደደውን ይህን አደጋ ተከትሎ ትናንት የአሜሪካን አቪዬሽን ቁጥጥር ባለስልጣን የፕራት እና ዊትኒ ፒደብልዩ4000 ሞተር የተገጠመላቸው የቦይንግ 777 አውሮፕላኖች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡
የበረራ ቁጥሩ 328 የሆነውና በዩናይትድ አየር መንገድ ንብረትነት የተመዘገበው አውሮፕላኑ ከትናንት ወድያ በረራውን ከጀመረ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ነበር የሞተር ሽፋኖቹ በአቅራብያ በሚገኘው መኖርያ ሰፈር ላይ ቁልቁል መውደቅ እንደጀመሩ ወደ ዴንቨር ኤርፖርት በፍጥነት እንዲመለስ የተገደደው፡፡ አየር መንገዱ በራሱ ተነሳሽነት አሁን እየተገለገለባቸው የሚገኙትን 24 የቦይንግ 777 አውሮፕላኖች (የተጠቀሰው ሞተር የተገጠመላቸውን) ከበረራ እንዳገደና ከአቪዬሽን ተቆጣጣሪዎች ጋርም በትብብር እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡ አሁን አገልግሎት እየሰጡ ካሉት በተጨማሪም 28 ተመሳሳይ አውሮፕላኖች በአየር መንገዱ ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡
ቦይንግ በበኩሉ ነገሮችን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን እና ከአሜሪካንም ሆነ ጃፓን አቪዬሽን ተቆጣጣሪዎች ጋራ አንድ ላይ ሆኖ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል፡፡ እስካሁንም የ346 ሰዎችን ህይወት ከቀጠፉት ሁለቱ የ737 ማክስ አውሮፕላኖች አደጋ አመጣሽ ቀውስ ሙሉ በሙሉ ያልወጣው ቦይንግ የፕራት እና ዊትኒ ሞተር የተገጠመላቸው 777 ሞዴል አውሮፕላኖች ሙሉ በሙሉ ከበረራ እንዲታገዱ ምክሩን ለግሷል፡፡ የአሜሪካን አቪዬሽን ቁጥጥር ባለስልጣን ውስጥ በተቆጣጣሪነት የሚያገለግሉት ስቲቭ ዲኪንሰን እንደሚሉትም ተቋማቸው ከቦይንግም ሆነ ፕራት እና ዊትኒ ጋራ ስብሰባ ተቀምጦ የነበረ ሲሆን የቀረቡ መረጃዎች ላይ በመመስረት ይህን ሞተር የሚጠቀሙ ቦይንግ 777 አውሮፕላኖች በረራቸውን እንዲያቆሙ በጋራ ወስነዋል፡፡
የጃፓን ትራንስፖርት ሚኒስቴር በወርሃ ታህሳስ የበረራ ቁጥሩ 904 የሆነው የጃፓን አየር መንገዱ ቦይንግ 777 አውሮፕላን ኦኪናዋ ካለው የናሃ ኤርፖርት ለቆ በረራ ከጀመረ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ባጋጠመው የሞተር ችግር ሳብያ ተመልሶ ወደ ኤርፖርቱ እንዲያርፍ መገደዱን ተከትሎ የሞተር ማሻሻያዎች እንዲደረጉለት ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር ተናግሯል፡፡ በጃፓን የፒደብልዩ4000 ሞተር የተገጠመላቸው 32 ቦይንግ 777 አውሮፕላኖች ተመዝግበው እንዳሉና 13 በጃፓን አየር መንገድ፤ 19ኙ ደግሞ በኦል ኒፖን አየር መንገድ እጅ ያሉ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
ምንጭ፡ Financial Times

በተለያዩ መተግበሪያዎች የሚሰራጩ የጤና መረጃዎችን ፌስቡክ አገደ
************************************
ፌስቡክ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በፕላትፎርሙ ላይ ጥብቅ ክትትል እያደረገ መሆኑን አመላካች ነገሮች እየታዩ ነው፡፡ ከእነዚህም ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት በተካሄደው አወዛጋቢው የአሜሪካውያን ምርጫ ወቅት የተወሰዱ እርምጃዎች አንድ ማሳያ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ፌስቡክ ፕላተግፎርሙን ተጠቅመው የተለያዩ ጤና ነክ መረጃዎችን የሚያስተላልፉ ሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎችን ማገዱን አሳውቋል፡፡ ጉዳዩን የተከታተሉት የኒዮርክ ባለስልጣናት እንዳሉት ከሆነ ፌስቡክ እርምጃውን የወሰደው የድረ-ገጹን ህጎች በመጣስ መረጃዎችን በሚያሰራጩ መተግበሪያዎች ላይ ነው፡፡
ከዚህ በፊት መተግበሪያ የሚያበለጽጉ ተቋማትን ጤና፣ ቢዝነስና ግላዊ መረጃዎች ላይ መሰረት ያደረጉ ሶስተኛ ወገን መረጃዎችን እንዳያበለጽጉ ማሳሰቢያ ሰጥቶ የነበረው ፌስቡክ እስካሁን ድረስ ነገሩን ይፋ ሳያደርገው ቆይቷል፡፡ እንደ ተቋሙ ሰዎች ገለጻ ከሆነ እርምጃው የደንበኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ታስቦ የተወሰደ ነው፡፡
ፌስቡክ በፕላትፎርሙ የታገዱ የቃላት ዝርዝርን በመፍጠርና በመተንተን እንዲሁም መተግበሪያው ውስጥ ተቀባይነት የሌላቸውን ሚስጥራዊ መረጃዎችን በተሻለ ሁኔታ ለማጣራት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም በማጣራት ላይ ይገኛል ፡፡ ፖሊሲያችን የደንበኞቻችንን ደህንነት ሊጎዱ የሚችሉ ሴንሲቲቭ መረጃዎችን በፕላትፎርሙ እንዲንቀሳቀሱ አይፈቅድም ያሉት የፌስቡክ ቃል አቀባይ በአሁኑ ወቅት እንዲህ አይነት መረጃዎችን የመለየትና የማገድ ስራችንን አጠናክረን ቀጥለናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ Tech Xplore