TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ቴክ-ሳይንስ ሪቪው፤ ነገ ይጠብቁን
በነገው የቴክ ሳይንስ መሰናዶዋችን ላለፉት ፭ ተከታታይ ሳምንታት ወደ እናንተው ያደረስናቸው ዝግጅቶቻችንን በሪቪው መልሰን የምንቃኛቸው ይሆናል፡፡
በዚህም በዓብይ፤ ፕሮግራም ስለ ግብርናና ባዮ ቴክኖሎጂ፣ የማጃንግ ባዮስፌር ሪዘርቭ እና አዳማ የግብርና መሳርያዎች ኢንዱስትሪ ላይ የተሰሩት ፕሮግራሞች
በተመራማሪዎች ታሪክ፤ ፕ/ር ማስረሻ ፈጠነ እና ፕ/ር ሽብሩ ተድላ
በተቋማት፤ የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን
በተጨማሪም የብላቴናት እና የቴክኖሎጂ ታሪክ ዝግቶቻችን ሰዓታቸው እንደተጠበቀ ወደ እናንተው ይደርሳሉ
የዩትዩብ ቻናላችንን (https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg) ሰብስክራይብ ማድረጉን እንዳይረሱ፤ ከዓመታት በፊት ከተላለፈው የመጀመሪየው ክፍል አንስቶ ያሉትን ሁሉንም የቴክ-ሳይንስ ፕሮግራሞች አንድ በአንድ መመልከትና ለእርስዎም ሆነ ቤተሰብዎ ዕውቀትን መገብየት ይችሉበታልና፡፡
የኢትዮጵያን ኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት የሚያሻሽል ሀሳብ አልዎት? እነሆ የውድድር ጥሪ
=========================
የኢትዮ-ጀርመን የኃይል ትብብር ባልተማከለ የኃይል አቅርቦት መፍትሄዎች ላይ እየሰሩ ያሉና ይህ ሀሳባቸውን ወደ ቢዝነስ መለወጥ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን የፈጠራ ባለሙያ፣ ስታርታፕ፣ ተማሪ እና አጥኚዎችን ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡ “Decentralised Energy Solutions in Ethiopia” በሚል ርዕስ የሚከናወነው ዝግጅቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ዘላቂ በሆነ መልኩ መፍታት የሚችሉ እንዲሁም በስፋትና ተመጣጣኝ ዋጋ ወደ ህብረተሰቡ የሚሰራጩ ያልተማከሉ መፍትሄዎችን የሚጠይቅ ነው፡፡ ፕሮፖዛሎቹ በነዚህ ላይ ብቻ የተገደቡ ባይሆንም በቴክኖሎጂያዊ ፈጠራዎች፣ አዳዲስ የቢዝበነስ እና ፋይናንስ መንገዶች፣ የማህበረሰብ አቀፍ ተሳትፎ ስትራቴጂ፣ ዲጂታላይዜሽን፣ እንዲሁም በዳታ እና ኃይል አስተዳደር ላይ ያተኮሩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለውድድሩ የሚቀርቡት ፕሮፖዛሎች በ4 መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ማለትም፤ በከባቢና አየር ንብረት ለውጥ፣ ኢኖቬሽን፣ ምጣኔ-ሐብታዊ የስኬት አቅም፣ እንዲሁም ፆታና ማሕበራዊ ተፅዕንዖ ላይ በመመርኮዝ ዳኝነት ይሰጥባቸዋል፡፡ ለ10ሩ ተመራጭ ተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት ብሎም የስልጠና፣ ትስስር እና ቢቢዝነስ ነክ ድጋፍ የሚበረከትላቸው ሲሆን ከ1-3ኛ ደረጃ ይዘው ለሚያጠናቅቁ ተሳታፊዎች የገንዘብ ሽልማት ያገኛሉ፡፡
በውድድሩ ለመሳተፍ የሚያስፍልጉ ነገሮች፤
• አመልካቾች በኢትዮጵያ ተግባራዊ ሊሆን በሚችል መፍትሄ ላይ እየሰሩ ያሉ ኢትዮጵያውያን መሆን አለባቸው
• ፕሮፐዛሎቹ በኢትዮጵያ ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል ችግር በመቅረፍ እና የብሄራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል የማዳረስ ስትራቴጂን በማሳካት ደረጃ ግልፅ ጠቀሜታ ያላቸው መሆን አለባቸው
• ተሳታፊዎች ከጀርመንም ሆነ አውሮፓ ህብረት ከመጡ አጋሮች ጋራ በጋራ መስራት ይችላሉ
• ኮቪድ-19ኝን አስመልክቶ የመፍትሄ ሀሳቦችን የሚያካትቱ እንዲሁም በሴት አመልካቾች የሚቀርቡ ፕሮፖዛሎች ይበረታታሉ
የምዝገባ ቀን፤ ተሳታፊዎች ከየካቲት 21 (February 28) በፊት በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት መመዝገብ አለባቸው
የመመዝገቢያ ሊንክ፤ https://www.energy-cooperation.et/newsroom/competition/
በአንታርክቲካ በረዶ ስር ልዩ ፍጥረታት ተገኛተዋል
******************************
ለፍጥረታት ህይወት የማይስማሙ አካባቢዎች ከሚባሉት ውስጥ በበረዶ የተሸፈነው የአለማችን አንዱ አህጉር አንታርክቲካ ነው፡፡ ለብዙ ጊዜያት ካለው ቅዝቃዜ የተነሳ በዚህ አህጉር ብዙ ፍጥረታት ይኖራሉ ተብሎ አይገመትም ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አሁን የወጣ አዲስ መረጃ እንደሚያመለክተው በቀዝቃዛማው አህጉር ያልተጠበቀ ልዩ ፍጥረት በበረዶ ንጣፎች ውስጥ እንደተገኘ አመልክቷል፡፡ መረጃውም ሌሎች እስካሁን ያልታወቁ ፍጥረታት በአካባቢው እንዳሉ የሚያመላክት መሆኑን የመረጃ ምንጫችን ያመለክታል፡፡
በጥናቱ ወቅት ተመራማሪዎቹ የበረዶ ግግሩን 900 ሜትር ጠልቀው የቆፈሩ ሲሆን ክፍት ከሆነው ውቅያኖስ 260 ኪሎሜትር ያክል ርቀት ባለው አካባቢ ከዜሮ በታች 2.2 ዲግሪ ሙቀት ውስጥ ፍጥረታት ተገኝተዋል፡፡ የብሪትሽ አንታርክቲክ ጥናት መሪ ዶክተር ሁው ግሪፍዝ ግኝቱ ያልተጠበቀና በቀዝቃዛው አለም ውስጥ የተለያዩና ያልታወቁ ፍጥረታ እንዳሉ የሚያሳይና ስለ አካባቢው እስካሁን ያለውን እሳቤ የሚቀይር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ ስለ ግኝቱ ሲናገሩ ከመልስ ይልቅ ብዙ ጥያቄዎችን ይዞ የመጣ እንደሆነ ሲናገሩ በማሳያነትም ፍጥረታቱ በዚህ ጥልቀት ውስጥ እንዴት ሊገቡ ቻሉ፣ ምን ይመገባሉ፣ ለምን ያክል ጊዜ በዚህ ቦታ ቆዩ የሚሉና የመሳሰሉ ከፍጥረታቱ ህልውና ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡
በአሁን ጊዜ ያለው መረጃ እንደሚያመለክተው በቀዝቃዛ ቦታዎች ከፀሐይና ከውቅያኖስ አካባቢ እየራቅን በሄድን ቁጥር የህይወት ዋስትናም በዚያው ልክ እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ ከዚህ በፊት የተደረጉ ጥናቶች እንደ አሳዎች፣ ትላ ትሎች፣ ጀልፊሽ እና ከሪል ያሉ ዝርያዎች በእነዚህ አካባቢዎች መኖራቸውን አሳውቀዋል፡፡
ምንጭ SciTechDaily
የአይንን ብርሃን ማጣትና የአየር ብክለት
*************************
በአየር ብክለት ምክንያት የሚመጣ የአይን በሽታ የአይናችንን ብርሃን ላይመለስ እንደሚያሳጣን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ ጥናቱ የአየር ብክለት በብዙ መንገዶች የሰው ልጆችን አኗኗር እየጎዳ እንደሆነ ያረጋገጠ ነው፡፡ የአየር ብክለት በዓለማችን ውስጥ የሚኖሩ የሁሉም ፍጥረታት ችግር እየሆነ መምጣቱ የማይካድ ነው፡፡ እንደ አለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ 90 በመቶ የሚሆነው የአለማችን ህዝብ የሚኖረው ጤናማ ባልሆነ የአየር ንብረት ውስጥ ነው፡፡
ለአየር ንብረት መበከል መንስኤ ናቸው ተብለው የሚታመንባቸው እንደ ጥቃቅን ብናኞች፣ ናይትሮጅን ዳይ ኦክሳይድ፣ ሳልፈር ዳይ ኦክሳይድ እና ሌሎች ከመኪናዎች፣ ከግዙፍ ኢንዱስትሪዎቻና ከማገዶ እንጨት የሚወጡ ጭሶች ናቸው፡፡ PM2.5 እየተባሉ የሚጠሩት ጥቃቅን ብናኞች ዋናውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ እነዚህ መጠናቸው ከ2.5 ማይክሮ ሜትር የሆኑ ጥቃቅን የፕላስቲክ ብናኞች በሰውነታችን ሰርገው ወደ ሳንባና የደም ቧንቧዎች የመግባት አቅም አላቸው፡፡ ይህም ሰውነታችን የተለያዩ በሽታዎችን እንዲያዳብር እንደሚያደርገው ይታመናል፡፡
ጥቃቅን ብናኞቹ የሰዎችን የማየት አቅም የሚያዳክሙና የአተነፋፈስ ስርዓት የሚያዛቡ እንደሆኑ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ ጥናቱ (AMD) እየተባለ የሚጠራውን ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የአይን ብርሃን ማጣትን ለማጥናት ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ በሽታው ከአይናችን ጀርባ አካባቢ ካሉ የደም ስሮች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ነው፡፡ የበሽታው ዋነኛ መንስኤዎች በመባል የሚታወቁት ዘርና ማጨስ ናቸው፡፡
በጥናቱም በእንግሊዝ የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን በቤታቸው አካባቢ ያለው የአየር ሁኔታ መረጃ በጥናቱ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ከ2006 ጀምሮ 116 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች መረጃዎችን የሰጡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 52 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የአይን ምርመራ አድርገዋል፡፡ የጥናቱ ውጤትም በአካባቢያቸው ከፍያለ መጠን ላለው ብናኝ የተጋለጡ ሰዎች ለአይን መድከም ብሎም ለአይን ብርሃን ማጣት የመጋለጥ እድላቸውደ ከፍተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
ምንጭ Science Alert
ምድራችን ከተሞችን መሸከም እያቃታት ነው
**********************
የአለማችን ከተሞች ከእድገታቸው ጋር ተያይዞ እየጨመረ የመጣው ግዝፈታቸው የምድራችንን የመሸከም አቅም እየተፈታተነው እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ ለወትሮው በአለማቀፍ የሙቀት መጠን መጨመር ምክንያት እየጨመረ የመጣው የባህር ጠለል ከፍታ ለአንዳንድ የአለማችን ከተሞች በውሃ የመዋጥ ምክንያት ነበር፡፡ የአሜሪካ ጊኦሎጂካል ጥናት ኤጀንሲ የስነ-ምድር ተመራማሪ የሆነው ቶም ፓርሰንስ የሳንፍራንሲስኮን ሁኔታ ያጠና ሲሆን በውጤቱም የግዙፋን ከተሞች መስፋፋት ገፀ-ምድርን እየተጫነው እንደሆነ አሳይቷል፡፡
ከጥናቱ ውጤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ሳንፍራንሲስኮ እድገቷ በጨመረ ቁጥር እስከ 80 ሚሊ ሜትር ድረስ ወደታች እየሰመጠች ትገኛለች፡፡ አካባቢው በባህር ጠለል ከፍታ መጨመር ምክንያት እስከ 2050 ድረስ 300 ሚሊ ሜትር የመስመጥ አደጋ እንደተጋረጠበት ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ 7.75 የሚደርስ የህዝብ ቁጥር ያላት ሳንፍራንሲስኮ ያሏት ህንጻዎች ክብደት ተሰልቶ 1.6 ትሪሊዮን ኪሎግራም እንደምትመዝን ጥናቱ አመልክቷል፡፡
ይህ ክብደት ከተማዋ የተገነባችበትን ተፈጥሯዊ ቅርፀ ምድር እንዲታጠፍ እንደሚያደርገው ተገምቷል፡፡ ከላይ የተገለጸው ክብደት ከህንጻ ውጭ ያሉ ሌሎች መሰረተ ልማቶችንና መገልገያዎችን እንዲሁም ህዝቡን የማይጨምር በመሆኑ የስጥመት መጠኑ ከ80 ሚሊ ሜትር ከፍ ሊል እንደሚችል በጥናቱ ተካትቶ ቀርቧል፡፡ ከከተሞች ክብደት በተጨማሪ የከርሰ ምድር ውሃ አጠቃቀምና የቴክቶኒክ አለታማ ንጣፎች መንሸራተትና ቦታቸውን መልቀቅ ሌሎች ለምድር መስመጥ ስጋቶች እንደሆኑ ተመራማሪዎቹ አክለው አሳውቀዋል፡፡
ምንጭ፡ Science Alert
ተቋማዊ የዕውቀት አስተዳደር ላይ ያኮተረ ወርክሾፕና የልምድ ልውውጥ መድረክ በመከናወን ላይ ነው
በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት አማካኝነት የተዘጋጀው ወርክሾፑ በእውቀት አስተዳደር ስርዓት ዙርያ ግንዛቤ የመፍጠር፣ የልምድ ልውውጦችን ማድረግና በጉዳዩ ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ፅሁፎችን በማቅረብ ግንዛቤን የማስጨበጥ ስራን ለማከናወን ታልሞ የተዘጋጀ ነው፡፡ ከ30 ተቋማት የተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች በተሳተፉበት በዚህ መድረክ የዕውቀት አስተዳደርን የተመለከቱ ውይይቶች ብሎም ልዩ ልዩ ጥናታዊ ፅሁፎች በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ እና ዕውቀትን ባካበቱ ምሁራን አማካኝነት ቀርበውበታል፡፡
በዓለም ሀገራት መካከል ላለው ሰፊ የማህበራዊ እና ምጣኔ-ሐብታዊ እድገት ልዩነት አንዱ ምክንያት “መረጃን እና ዕውቀትን ለልማት የመጠቀም ልዩነት ነው” ያሉት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ተሾመ ሳህለማርያም ሀገራት ጠንካራ የዕውቀት እና ቴክኖሎጂ አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋታቸውና ስራዎቻቸውንም በዚህ እንዲታገዙ በማድረጋቸው ፈጣን ምጣኔ-ሐብታዊ ዕድገት ማስመዝገባቸውን በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ አመላክተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ቀደምት ስልጣኔ እና በዕውቀት አስተዳደር ውስጥም የራሷ ድርሻ እንደነበራት ያወሱት ኢ/ር ተሾመ አሁን ላይ ተቋማዊ የዕውቀት አስተዳደርን ለዕድገት በማዋል ረገድ በተለይም መረጃን በአግባቡ ያለመያዝ፣ ያለማደራጀት፣ ያለመተንተን፣ ያለማሰራጨት እንዲሁም መልሶ ጥቅም ላይ ያለማዋል ችግሮች መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱም የዕውቀት አስተዳደር ፋይዳን በመረዳት ተቋማዊ እና ሀገራዊ የዕውቀት አስተዳደር ስርዓት ለመገንባት ያከናወናቸውን የተለያዩ ተግባራት ጠቅሰው አስረድተዋል፡፡
በኢንስቲትዩቱ የመረጃ አደረጃጀት እና ዕውቀት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቃልኪዳን ተሾመ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ያለውን አደረጃጀት እንዲሁም በሕግ የተሰጡትን ተግባራት ለታዳሚው አብራረተዋል፡፡ አቶ ቃልኪዳን በኢንስቲትዩቱም ሆነ በእርሳቸው ዳይሬክቶሬት የተከናወኑትን እንደ ብሄራዊ የልማት አመላካች ዳሽቦርድ እና ኮቪድ-19 ተኮር የመፍትሄ ስራዎች ያሉ ዋና ዋና ክንውኖችን አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም ስራቸው እየተከናወነ ያሉትንና በቅርብ ተጠናቀው ይፋ የሚሆኑትን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ጆርናል እንዲሁም ተደጋጋሚ ግዢዎች ከመፈፀም የሚያድነው በኢትዮጵያ የሚገኙ የቤተ-ሙከራ ግብዓቶችን የመመዝገብና ለተጠቃሚ የማሳወቅ ስራዎች ተጠቅሰዋል፡፡
በጠዋቱ መርሃ ግብር ሁለት ምሁራዊ ጥናቶች ሲቀርቡ ቀዳሚ የነበረው “knowledge management practices in commercial bank of Ethiopia” በሚል ርዕስ በዶ/ር ተምትም አሰፋ የቀረበው ነው፡፡ ጥናቱ በዕውቀት አስተዳደር ረገድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ያለውን ሂደት አንዲሁም ክፍተቶችን እና ከሌሎች ተቋማት በተለየ በዕውቀት አስተዳደር ላይ ስኬታማ እንዲሆን ያስቻሉትን አብይ ጉዳዮች የዳሰሰ ነው፡፡ ሁለተኛውን ያቀረቡት ዶ/ር ጌታቸው ኃይለማርያም በበኩላቸው “frugal knowledge sharing for frugal innovation diffusion in Africa” በሚል ርዕስ በዝቅተኛ ምጣኔ ሐብታዊ ደረጃ ላይ ላለው ማህበረሰብ ግልጋሎት ሊሰጡ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ አዘጋጅቶ ወደ ታች እንዲወርዱ የማድረግ ስራን እንዴት ማከናወን ይቻላል በሚለው ላይ ገለፃ አቅርበዋል፡፡