አዲሱን የኮሮናቫይረስ አይነት ክትባትም ላያስቆመው ይችላል
===================
መነሻውን ከሀገረ እንግሊዝ ያደረገው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ አይነት አሁን ያሉትን ክትባቶች ማምለጥ የሚያስችሉትን ለውጦች ማድረጉን አዲስ ሪፖርት አሳየ፡፡ ቢ.1.1.7 በሚል ስያሜ የሚታወቀውና ከቀድሞው የኮሮና ቫይረስ ዓይነት የላቀ የመተላለፍ አቅም ያለው የቫይረስ ዓይነቱ መስከረም ላይ ለመጀመሪያ ጊዚ እንግሊዝ ውስጥ ከታየበት ጊዜ አንስቶ በመላው ዓለም እየተሰራጨ ይገኛል፡፡
ባሳለፍነው ሰኞ የእንግሊዝ መንግስት ከወሰዳቸውና 214,000 የአዲሱ ቫይረስ ዓይነት ናሙናዎች ውስጥ በ11 ናሙናዎች ላይ ኢ484ኬ (E484K) የተሰኘው ለውጥ (mutation) መገኘቱን አስታውቋል፡፡ ይህኛው ለውጥ ከዚህ ቀደምም ከጥቅምት አንስቶ በደቡብ አፍሪካ በታየው የቢ.1.351 ኮሮና ቫይረስ ዓይነት ላይ ታይቶ ነበር፡፡ የመንግስት ኃላፊዎችን ያስጨነቀው ጉዳይ ይህ የለውጥ ዓይነት የክትባቶችን ውጤታማነት ሊቀንስ መቻሉ ላይ ነው፤ እንደ ኖቭአቫክስ እና ጆንሰንና ጆንሰን ያሉት የመድሃኒት አምራቾች ያመረቷቸው የኮቪድ-19 ክትባቶች በደቡብ አፍሪካ አነስተኛ ውጤታማነትን አሳይተዋልና፡፡ የኢ484ኬ ለውጥ አንዳንድ የበሽታ መከላከያዎችን ቫይረሱ ወደ ሰውነት ከመግባቱ አስቀድሞ አቅም የለሽ እና ከጥቅም ውጪ የማድረግ አቅማቸውን ሊቀንሰው ይችላል፡፡ ሆኖም ይህ ለውጥ በእንግሊዙ የቫይረስ ዓይነት ላይ መታየቱ ቫይረሱን ይበልጥ ተላላፊና ክትባቱንም አቅም አልባ ያደርገዋል ማለት አይደለም፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ኢ484ኬ በደቡብ አፍሪካው የቫይረሱ አይነት ላይ ያሳየውን ተፅዕንዖ በእንግሊዙ ላይም ላይደግመው ስለሚችል ነው፤ የእያንዳንዱ ለውጥ ተፅዕንዖ እንደየበለፀጉበት በራሒ የሚለያይ በመሆኑ፡፡
የኢ484ኬ ለውጡ የተከሰተው ቫይረሱ ሰውነትን ሲያጠቃ ቀድሞ በሚያርፍበት ሪሴፕተር ባይንዲንግ ዶሜን (RBD) በተባለው ክፍል ላይ ነው፡፡ በዚህም ስፍራው ላይ ሆነው ቫረሱ ወደ ህዋሳት ዘልቆ እንዳይገባ የሚጠብቁት የበሽታ መከላከያ ዘቦች ኢ484ኬን እንዳያውቁት በማድረግ ቫይረሱን በመከላከሉ ስራ ላይ አቅም አልባ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህ ለውጥ ያለባቸው የኮሮና ቫይረስ ዓይነቶች በተለይ አብዛኛው ሰው በቫይረሱ በተያዘባቸው አካባቢዎች ላይ በቀላሉ ተሰራጭተው ክትባቶች ውጤታማ እንዳይሆኑ ከማድረግም ባሻገር ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችን ዳግም ሊያጠቁ ይችላሉ፡፡
ኢ484ኬ ብራዚል ውስጥ ባሉት ልዩ ልዩ የኮሮና ቫይረስ አይነቶች ላይም የታየ ሲሆን ለቫይረስ አይነቶቹ የሚሰጠው ጥቅም ገና በመጠናት ላይ ነው፡፡ እስካሁን የኢ484ኬ ለውጥ የታየባቸው የቢ.1.1.7 አይነቶች ቁጥር በጣም አነስተኛ ቢሆንም ወደፊት ሊኖራቸው የሚችለው ስርጭት ግን አሳሳቢ ሆኗል፡፡
ምንጭ፡ Live Science

የኤች.አይ.ቪ ቅድመ መከላከያ መድሃኒቶችን በማዳረስ አፍሪካ እየመራች ነው
====================
በዓለም ዙርያ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በኤች.አይ.ቪ የመያዝ ዕድልን የሚቀንሰውን የፕሪ ኤክስፖዠር ፕሮፊላክሲስ ወይም ፕሬፕ (PrEP) መድሃኒት በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፡፡ ታድያ ቀድሞ በዋናነት የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎች የነበሩት ምዕራባውያን ሀገራት የነበሩ ቢሆንም አሁን ግን ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት ያሉት የመድሃኒቱ ተጠቃሚ አፍሪካዊያን ቁጥር በፍጥነት አድጎ ከአጠቃላይ ተጠቃሚው ቁጥር ከግማሽ የሚልቀውን ድርሻ ሊይዝ ችሏል፡፡
መረጃው ይፋ የሆነው ከሳምንት በፊት የኤች.አይ.ቪ መከላከል ላይ አተኩሮ በተሰናዳ የጥናት ኮንፈረንስ ላይ ነው፡፡ መረጃውን ያቀረበችው መቀመጫውን ኒው ዮርክ አድርጎ በኤች.አይ.ቪ መከላከል ላይ ከሚሰራው የኤድስ ክትባት ተሟጋች ዓለም አቀፍ ትብብር ድርጅት (AVAC) የመጣችው ኬት ሴጋል የፕሬፕ መድሃኒቶች አጠቃቀም ከቀደመው ዓመት ሲነፃፀር በአውሮፓውያኑ 2020 በ300,000 ሰው ማደጉን ተናግራለች፡፡ ከሰሃራ በታች አፍሪካም እ.አ.አ በ2016 4,154 ብቻ የነበረው የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎች ቁጥር በ2020 517,000 ደርሷል፡፡ በመድሃኒቱ ተጠቃሚነት ዓለምን ከሚመሩት 10 ሀገራት ውስጥም 7ቱ በዚሁ የአፍሪካ ክፍል ያሉት ናቸው፡፡ ደቡብ አፍሪካ የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎቿን ቁጥር ከ100 ሺህ ያሻገረች ሲሆን ኬኒያም በ83 ሺህ ትከተላታለች፤ ዛምቢያና ዩጋንዳም በቅርብ ርቀት ተቀምጠዋል፡፡
ለዚህ የተጠቃሚዎች ማሻቀብ በዋና ምክንያትነት የተጠቀሱት በሰሃራ በታች አፍሪካ ቀዳሚው የኤች.አይ.ቪ ስራዎች ድጋፍ ሰጪ በሆነው የአሜሪካን መንግስት መዋለ ነዋይ ፈሰስና የአካባቢው ሀገራት ቁርጠኝነት ነው፡፡ የአካባቢው ሀገራት መድሃኒቶቹን እንደ ሴተኛ አዳሪዎች ላሉ ከፍተኛ የቫይረሱ ተጋላጭነት ላላቸው ወገኖችም ሆነ ለተቀረው ህዝብ በማዳረስ ረገድ ስኬታማ መሆናቸው ተነግሯል፡፡ በተጨማም አሁንም መድሃኒቱን በመድሃኒት ቤቶች እንዲገኝ በማድረግና በህዝቡ ላይም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት የተጠቃሚዎችን ቁጥር ከዚህ በበለጠ ማሳደግ እንደሚቻል ተገልጿል፡፡
በአፍሪካ የበሽታ ቁጥጥር ማዕከል ሚሰራው ጆን ኒኬንጌሶንግ አሁን ላይ ያለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ እነዚህን ጥረቶች ሊጎዳ እንደሚችል ይናራል፡፡ ኮቪድ-19 የኤች.አይ.ቪን ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ የጤና ስራዎች ላይ ተፅዕንዖ ማሳደሩን የሚናገረው ጆን “በዚህኛው ዓመት በፕሬፕ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕንዖ እንደሚኖር እጠረጥራለሁ” ሲል ስጋቱን ገልጿል፡፡ ሆኖም ከዚህ በተቃራኒ በአውሮፓውያኑ 2016 76 ብቻ ከነበረው የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎቿ ቁጥር በ2020 ወደ 32 ሺህ ማሳደግ የቻለችው ናይጄሪያ ለተቀናጀ የኤች.አይ.ቪ መከላከል ጥረቷ ምስጋና ይግባና ቁጥሩን በመጪው ዓመትም መጨመር እንደምትችል በሀገሪቱ የጤና ማማከር ስራ ላይ የተሰማራው ኤፒአፍሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢፌኒ ንሶፎር ይናገራሉ፡፡
ምንጭ፡ New Scientist

የመዘንጋት ችግር በኮቪድ የመሞትን እድል እንደሚያሰፋው በጥናት ተረጋገጠ
*****************************
በአሁኑ ሰዓት አለማችን የኮቭድ ክትባትን ለሁሉም ለማዳረስ በትጋት እየሰራች ትገኛለች፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ተመራማሪዎች በወረርሽኙ እጅግ ተጠቂ የሆኑትን ሰዎች ለመለየት የተለያዩ ጥናቶችን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በዚህም አንድ በኮቪድ የተያዙ 7400 ሰዎች የተሳተፉበትና በኒዮርክ የተካሄደ ጥናት የመዘንጋት ህመም ያለባቸው ሰዎች ይህ ችግር ከሌለባቸው ሰዎች ሶስት እጥፍ ለቫይረሱ ተጋላጭ እንደሆኑ አሳይቷል፡፡
በዚህም ጥናቱ schizophrenia እየተባለ በሚጠራው የመዘንጋት በሽታ ሰዎች በቫይረስ ለሚተላለፉ በሽታዎች ተጋላጭ እንዲሆኑ የሚያደርግ ምክንያት እንደሚኖረው ተገምቷል፡፡ በኒዮርክ ዩኒቨርሲቲ ላንጎን ሜዲካል ሴንተር የስነ አዕምሮ ሀኪም የሆኑት ካትሊን ኔማኒ የጥናቱ ውጤት በመዘንጋት በሽታ የተያዙ ሰዎች ለኮቪድ 19 ውጤቶች እጅግ ተጋላጭ እንደሆኑ አመልክቷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሀኪሟ አክለውም ከዚህ ውጤት በመነሳት የክትባት እደላው የታማሚዎችን የአእምሮ ጤና መሰረት ያደረገ ሊሆን እንደሚገባው ሀሳባቸውን አስቀምጠዋል፡፡
አራት ሆስፒታሎችን የሚያካትት ከኒውዮርክ ላንጎን የጤና ስርዓት የህክምና መዝገቦችን በማረጋገጥ ቡድኑ በመጋቢት እና በግንቦት 2020 መካከል COVID-19 የተያዙ 7,350 ጎልማሳዎችን ለይቷል ፡፡ ከእነዚህም መካከል 75 በመቶ የሚሆኑት በመዘንጋት በሽታ የተጠቁ ናቸው፡፡
ምንም እንኳን ቀደም ሲል የተደረጉ ጥናቶች የአእምሮ ችግር ያላቸው ግለሰቦች በበሽታው የመያዝ ዕድላቸው ሰፊ እንደሆነ ቢታመንም እንደ ጭንቀት ያሉ የስሜት መቃወስ ያሉባቸው ሰዎችም በCOVID-19 የመሞት ዕድላቸው ከፍ ያለ እንዳልነበረ ይታመናል፡፡ ስኪዞፈሪንያ ያለባቸው ሰዎች ከሌለባቸው ሰዎች በኮቭድ 19 በ2.67 እጥፍ የመሞት እድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡
በጥናቱ እንደ እድሜ፣ ጾታ፣ ዘር፣ ስኳርና የልብ በሽታ ያሉ ችግሮች ተካትተው መረጃ የተሰበሰበባቸው ሲሆን ስኪዞፈሪንያ ከእድሜ ቀጥሎ በኮቪድ የመሞት እድልን የሚያፋጥን ምክንያት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ እነዚህ ታካሚዎች ቀድሞውኑ ለአደጋ ተጋላጭ ከሆኑት የህብረተሰብ አባላት መካከል ናቸው እና ምናልባትም በዓለም ዙሪያ በአብዛኛዎቹ የጤና አጠባበቅ ሥርዓቶች ያልተረዱ ናቸው ፡፡
ከኤድንበርግ ዩኒቨርሲቲ ክሊኒክ ሳይካትሪስት ባለሙያ የሆኑት ዴቪድ ኦዌንስ እንደተናገሩት ጥናቱ “እንደ ስኪዞፈሪንያ ያሉ የረጅም ጊዜ የአእምሮ ሕመሞች ያሉባቸው በሽተኞች የተጋለጡበትን የጤና እና ማህበራዊ እኩልነት ችግር በምሳሌነት ሊገልጽ ይችላል” ብለዋል ፡፡
ምንጭ Science Alert

አዲስ የሚወጡ ምርጥ የሳይንስ ልብ ወለድ ፊልም እና ዘጋቢዎች
=====================
ለወትሮው ስሜትን እየጋለቡ ወደማናውቀው ምዕናባዊ አለም የሚወስዱ ፊልሞችን ለተመልካቾች በማድረስ የሚታወቀው ሆሊዉድ የኮቪድ-19 ወረርሺኝን ተከትሎ ያሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት 2020 በመሰናክሎች የተሞላ አድርጎበታል፤ በርካታ ፊልሞችም የመለቀቂያ ቀናቸው እንዲዘዋወር ጭምር ሆነዋል፡፡ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ግን እነዚህ የመለቀቂያ ቀናቸው የተላለፉ ፊልሞችን ጨምሮ ሌሎች አዳዲስ የሳይንሳዊ ልብወለድ እንዲሁም ሳይንስ ተኮር ዘጋቢ ፊልሞች ለተመልካች ይደርሳሉ፡፡
ኤ ኳየት ፕሌስ ክፍል ሁለት፤ ያለንበት የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን ተከትሎ ለሁለት ጊዜያት ያህል የሚለቀቅበት ቀን የተራዘመ ቢሆንም ይህ በኤምሊ ብላንት መሪ ተዋናይነት እና በባለቤቷ ጆን ክራሲንስኪ ተፅፎ ዳይሬክት የተደረገው አስፈሪ ፊልም በመጪው ሚያዝያ ለዕይታ ይፋ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡ ድምፅን ሰምተው በሚያድኑ አውሬዎች በተሞላው የድህረ ውድመት አካባቢ መኖርያውን ያደረገው የአበት ቤተሰብ ስፍራው ላይ በተጨማሪነት ሌሎች አደጋዎች ሲገጥማቸው ፊልሙ ያሳያል፡፡
ባዮስ፤ ሌላኛው የሚታይበት ጊዜ ከ2020 የተላለፈ ሳይንሳዊ ልቦለድ ፊልም ሲሆን በመሪ ተዋናይነት የሚደምቀው ቶም ሄንክስ በአንድ ከፍተኛ የተፈጥሮ አደጋ አማካኝነት ዶጋ አመድ በሆነ የሰሜን ማዕከላዊ የአሜሪካን ክፍል ውስጥ እርሱ ሲሞት ውሻውን ይንከባከብለት ዘንድ ሮቦት የሰራ ግለሰብ ሆኖ ይተውንበታል፡፡
ቶፕ ገን ማቭሪክ፤ በምዕናቡ ዓለም ውስጥ ጠልቀው ከሚገቡ የሳይንሳዊ ልብወለድ ፊልሞች በተጨማሪም በአውሮፓውያኑ 1986 ተሰርቶ የነበረው “ቶፕ ገን” ፊልም ቅጣይ የሆነው ቶፕ ገን፤ ማቭሪክ ከወራት በኋላ ለስክሪን የሚበቃ ይሆናል፡፡ መሪ ተዋናዩ ቶም ክሩዝ የፊዚክስ ህጎችን የሚገዳደርበት ፊልሙ መጪው ሐምሌ ላይ ይሆናል ለተመልካች ዕይታ የሚቀርበው፡፡
ዶንት ሉክ አፕ፤ ፊልሙ ዝነኞቹ ተዋናዮች ሊዮናርዶ ዲካፕሪዮ እና ጄንፈር ላውረንስ ወደ ምድር አቅጣጫ እየገሰገሰ ያለ አንድ አጥፊ ሜትሮይትን አስመልክተው ሰዎችን ለማስጠንቀቅ የሚባዝኑ ሁለት የህዋ ተመራማሪዎችን ገፀ ባህርይ ተከላብሰው ይተውኑበታል፡፡ አሁን ላይ በቦስተን ቀረፃው እየተከናወነለት ያለው ዶንት ሉክ አፕ ከሁለቱ በተጨማሪም ሌሎች የሆሊውድ ዘነኛ ተዋንያንን ይዟል፡፡
ባቢሎን፤ የላላ ላንድ ፊልም ዳይሬክተሩ ዳሚየን ሻዜል ፊልም የሆነው ባቢሎን ከድምፅ አልባዎቹ ዘመን አንስቶ እስከ ባለ ድምፆቹ ድረስ እንዴት በጊዜ ሂደት ውስጥ የፊልም ቴክኖሎጂዎች እንደተለወጡ የሚቃኝ ይሆናል፡፡
ከነዚህ የሲኒማ ፊልሞች በተጨማሪ የተለያዩ ሳይንስና የሳይንስ ስብዕናዎች ላይ ያተኮሩ ዘጋቢ ፊልሞችም በዓመቱ ለህዝብ የደረሱና የሚደርሱ ይሆናል፡፡ ከነዚህ ዘጋቢዎች አንዱ በአየር ንብረት ጠበቃነቷ የምትታወቀው ታዳጊዋ ግሪታ ተንበርግ ላይ የሚያተኩረው “አይ አም ግሪታ” የተሰኘው ዘጋቢ ፊልም ይገኝበታል፡፡ በተጨማሪም ስለ ስመጥሩ የፊዚክስ ተመራማሪ ስቴፈን ሀውኪንግ ከዚህ በፊት ያልታዩ ጉዳዮችን የሚዳስሰው “ሀውኪንክ” የተሰኘው የስካይ ዘጋቢ ፊልመ ተጠቃሽ ነው፡፡

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ የፓርኪንግ (መኪና ማቆሚያ) ስራ
*************************************
በከተሞች አካባቢ የሚስተዋለው የመኪናዎች ቁጥር መጨመር የህዝቡን የእለት ከእለት እንቅስቃሴ እየጎዳው እንደሆነ ይታመናል፡፡ በዚህም ምክንያት አሽከርካሪዎች ክፍት የሆነ የመኪና ማቆያ ስፍራ በመፈለግ ጊዜያቸውን ያጠፋሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በተጣበበና ለሌሎች መኪናችና ለሰዎች እንቅስቃሴ በማይመች መልኩ መኪናቸውን አቁመው ይሔዳሉ፡፡
ለዚህ ችግር እንደ ትልቅ መፍትሔ የሚወሰደው ለመኪኖች ብቻ የተለየ ጥብቅ የፓርኪንግ ስፍራ ማዘጋጀት ነው፡፡ ይህንንም እውን ለማድረግ ከተሞች በቅድሚያ በአጠቃላይ የፓርኪንግ ፍላጎት ዙሪያ ጥናት ማድረግ አለባቸው፡፡ ጥናቱ በብዛት የፓርኪንግ ፍላጎት የሚበዛባቸውን፣ የተቀላጠፈ የንግድ እንቅስቃሴ ያለባቸውንና በመኪና መብዛት ምክንያት ለእንቅስቃሴ ያስቸገሩ ቦታዎችን ለመለየት ያስችላል፡፡ ይህ ደግሞ ጥቂት የማይባል ጊዜና ገንዘብ ያስፈልገዋል፡፡
ችሩን የተመለከተው ፍራውንሆፈር የተባለ የኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ የምርምር ተቋም ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ለፓርኪንግ ክፍት የሆኑ ስፍራዎችን መለየት የሚያስችል ስልት ቀይሷል፡፡ ፕሮጀክቱ በአሁኑ ሰዓት ለስራው የሚያስፈልገውን አጠቃላይ መረጃ ካሜራችንና ድኖችን በመጠቀም ያዘጋጀ ሲሆን ይህም ጊዜ የሚወስደውንና ዋናውን የፕሮጀክቱን ክፍል ማጠናቀቁን ያሳያል፡፡
በተመሳሳይ ጊዜ በመረጃ ጥናት ላይ ማሻሻያ እየተደረገ ሲሆን ፣ መረጃን በእጅ በሚመረምርበት ጊዜ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለዚሁ ዓላማ ተመራማሪዎች ስልተ-ቀመሮችን በማዘጋጀት እና በምስሎቹ ውስጥ የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች በሙሉ ለመለየት እና በትክክል ለማጣራት ሰው ሰራሽ የነርቭ ኔትወርክን በማሰልጠን ላይ ናቸው ፡፡ አልጎሪዝሙ የቆሙ እና የሚንቀሳቀሱ መኪናዎችን ለመለየት እንዲረዳ የሙከራው ቦታ ከመልክዓ ምድር መረጃዎች ጋር በተያያዙ በተወሰኑ የመኪና ማቆሚያ ዞኖች ተከፍሏል ፡፡ ከዚያ አልጎሪዝም የአንድ የተወሰነ ዞን ምስሎችን በመተንተን እዚያ የቆሙትን ተሽከርካሪዎች ሁሉ ምልክት ያደርጋል ፡፡ በዚህ መሠረት ሲስተሙ የቆሙ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር በአንድ ጊዜ ሊወስን ይችላል ፣ በዚህም ክፍት የሆነውን የመኪና ማቆሚያ ቦታ ያሰላል ፡፡
ሰው ሰራሽ አስተውሎትን መጠቀሙ አሁን በስፋት እና በአጠቃላይ በኢንዱስትሪ አካባቢ ተቀባይነት አግኝቷል ፡፡ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ፍላጎትን ለመወሰን መጠቀሙ ለከተሞች ቁልፍ ጥቅሞችን ሊያስገኝ የሚችልበት ጥሩ ምሳሌ ነው ፡፡ ለዚህ ፕሮጀክት የተሠራው ስልተ-ቀመር የመኪና ማቆሚያ ቦታ አጠቃቀምን በራስ-ሰር ያሰላል። ይህ በእጅ መረጃን ለመሰብሰብ የሚያስፈልገውን ጊዜ እና ወጪን በእጅጉ የሚቀንስ ሲሆን በዚህም ምክንያት በከተሞች ውስጥ የመኪና ማቆሚያ ችግሮች በፍጥነት መፍትሄ ሊያገኙ ይችላሉ ፡፡
ምንጭ Tech Xplore

የቴክ-ሳይንስ፤ በዚህ ሳምንት መሰናዶዋችንም
=================
በአብይ ፕሮግራም፤ ስለ ስመ ጥሩ ወ/ሮ ስህን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ያዘጋጀነውን ፕሮግራም ክፍል ሁለት
በተመራማሪዎች ታሪክ፤ ዶ/ር ተስፋዬ ሽምብር ክፍል ሦስት
በብላቴናት፤ የደህንነት ካሜራ የሰራው ታዳጊ
በተቋማት፤ ታክሲዬ የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ እንዴት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ደንበኞቹን እንደሚያስተናግድ የሚያሳይ ዝግጅት
በቴክኖሎጂ ታሪክ፤ የነፋስ ኃይል ማመንጫ
ከነዚህ አባይት ዝግጅቶቻችን ባሻገር የስኮላርሺፕ መረጃንም ጨምረን ነገ በ10 ሰዓት እንዲሁም በዕለተ ማክሰኞ በተመሳሳይ ሰዓት በMOU TV እንጠብቃችኋለን፡፡
የዩትዩብ ቻናላችንንም (https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg) ሰብስክራይብ ማድረጉን እንዳይረሱ፤ ከዓመታት በፊት ከተላለፈው የመጀመሪየው ክፍል አንስቶ ያሉትን ሁሉንም የቴክ-ሳይንስ ፕሮግራሞች አንድ በአንድ መመልከትና ለእርስዎም ሆነ ቤተሰብዎ ዕውቀትን መገብየት ይችሉበታልና፡፡

YouTube
EthioTunes
Share your videos with friends, family, and the world
ኢኖቬተሮችን በክህሎት ለመደገፍ የተሰናዳው የቅድመ ኢንኪዩቤሽን ዝግጅት ተጠናቀቀ
======================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የኢኖቬሽን ባህልን ለማሳደግ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ ኢኖቬተሮችን ለማፍራት ያግዝ ዘንድ ያሰናዳው የቅድመ-ኢንኪዩቤሽን ፕሮግራም የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በትናንትናው ዕለት ፍፃሜውን አድርጓል፡፡ ከረቡህ ጥር 26 አንስቶ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ዝግጅቱ ከተለያየ ዘርፍ የተውጣጡ 26 ኢኖቬተሮችን ያሳተፈ ነበር፡፡
ዝግጅቱ የተሳታፊዎችን ክህሎት ለማዳበር፣ ዕውቀትን ለመጨመር፣ ትስስር ለመፍጠር እንዲሁም ዕውቅና ለመስጠት ያለመ መሆኑን የተናገሩት የስታርትአፕ እና የኢኖቬሽን ፕሮሞሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በረከት አባይነህ ተሳታፊ ኢኖቬተሮቹ ከጠበቁት በላይ ትልልቅ ሀሳብን ያነገቡ ሆነው እንዳገኟቸውና ከእነርሱም ብዙ መማራቸውን ገልፀዋል፡፡ ለኢኖቬሽን ትልቁ አስፈላጊ ጉዳይ ክህሎት እና ትስስር ነው ያሉት አቶ በረከት ተሳታፊዎች የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለመሻገር በይበልጥ ወደ ራሳቸው እንዲመለከቱና ከመደበኛ ትምህርት ባሻገርም በንባብና ሌሎች መንገዶች እራሳቸውን እንዲያበቁ ተናግረዋል፡፡
በትናንቱ መርሃ ግብር ላይ ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የመጡት አቶ በኃይሉ መልከፃዲቅ በአዕምሮ ንብረት እና ተጓዳይ ጉዳዮች ላይ ለተሳታፊ ኢኖቬተሮቹ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ ስልጠናው በምን በምን ጉዳዮች ላይ የአዕምሮ ንብረት ጥበቃ እንደሚደረግ በዝርዝር የተገለፀበት ሲሆን በፓተንት ምዝገባ ረገድም ተሳታፊዎቹ ፈጠራቸውን በፓተንት የማስመዝገባቸው ትልቅ ፋይዳና በምንም መልኩ አስመዝግበው ለፈጠራቸው ጥበቃ ማግኘት እንደሚችሉም የዳሰሰ ነበር፡፡
ያለ አዕምሮ ንብረት ጥበቃ ፈጠራዎች ትልቅ አደጋ ውስጥ እንደሚገቡ አፅዕንዖት የሰጡት አቶ በኃይሉ አስፈላጊውን ነገር ከማሟላትና ፈጠራቸውን ከማስመዝገብ ወደኋላ እንዳይሉ ለፈጠራ ባለሙያዎቹ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡
ዝግጅቱ የተለያዩ ቁም ነገሮችን ማግኘታቸውን የተናገሩት ተሳታፊ ኢኖቬተሮቹ ዝግጅቱ በተለይም በአዕምሮ ንብረት ጥበቃ ረገድ ቀድሞ የነበራቸውን አመለካከት ሙሉ በሙሉ የለወጠና ጉዳዩ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ትምህርት የሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ለሚዘጋጀውና የሦስት ወራት ቆይታ ለሚኖረው የሙሉ ኢንኪዩቤሽን መርሃ ግብር መሰናዶዎች በመደረግ ላይ መሆናቸውን በመድረኩ ላይ ያስታወቁት አቶ በረከት ይህ ዝግጅትም ለዚህ መንደርደሪያ እንደሚሆን ለተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት ሲያበረክቱ ተናግረዋል፡፡

የሐይል መስመሮችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ድሮን ከወደ ዴንማርክ
************************
በደቡባዊ ዴንማርክ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ በሚገኝ የምርምር ተቋም የሚሰሩ ተመራማሪዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ የከፍተኛ ሐይል ተሸካሚ መስመሮችን ደህንነት የሚቆጣጠር ድሮን መስራታቸው ተነገረ፡፡ ድሮኑ የሐይል ማስተላለፊያውን ሽቦ ከዝገትና ከሀይል ማቆራረጥ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፈተሸ የሚያግዝ ነው፡፡ በዴንማርክ ከ7000 ኪሎሜትሮች በላይ የሚሆን ርዝመት ያለው የከፍተኛ ሐይል ማስተላለፊያ መስመር አለ፡፡
እስካሁን ባለው ሁኔታ የመስመር ቁጥጥሩ ስራ ሄሊኮፍተር እና መኪኖችን በመጠቀም በሰው ሀይል የሚሰራ ሲሆን መስመሩ ከመሬት ከፍ ያለ በመሆኑ ለአደጋ የሚያጋልጥና ከዋጋም አንጻር አዋጭ አይደለም፡፡ ለዚህ አላማ የተሰሩት ድሮኖች በመስመሮቹ ዙሪያ በተከታታይ ያለማቋረጥ እየበረሩ ሊኖር የሚችልን ችግር ይከታተላሉ፡፡ በክትትሉ ወቅት ድሮኑ ችግር ካገኘ ሐይል ማስተላለፊያውን ለሚያስተዳድረው አካል መልዕክት ይልካል፡፡
የዚህ ድሮን ሌላው አስገራሚው ነገር ለመብረር የሚያስፈልገውን የባትሪ ጉልበት በሐይል ማስተላለፊያ መስመሩ ተጠግቶ ሲበር በሚያገኘው ወይም ከሀይል አስተላላፊ መስመሩ መግነጢሳዊ ክልል በሚያገኘው ሀይል ይሞላል፡፡ ስለዚህ ክትትሉን ያለማቋረጥ ማድረግ ይችላል፡፡ በዚህ መንገድ ድሮኑ የተበላሸን መስመር ለመፈለግ የሚጠፋውን ጊዜና ጉልበት በመቀነስ ትክክለኛው ችግር የተከሰተበትን ቦታ በማመልከት የጥገና ቡድን ለመላክ ያስችላል፡፡
አዲሱ ድሮን ረጃጅም መስመሮችን ብዙ ሆነው የሚከታተሉ ሲሆን በአስቸጋሪ አከባቢ ውስጥ ይሰራሉ ፡፡ በቤታችን ውስጥ ባሉ ሶኬቶች ውስጥ 230 ቮልት አለ ፣ ግን በላይኛው መስመር ላይ ያለው ቮልቴጅ 400,000 ቮልት ነው፡፡ ይህ በመብረቅ የመመታት እድሉን ከፍ ያደርገዋል፤ እናም ድሮኖቹ በከፍተኛው ሀይል ምክንያት ችግሮች ሊያጋጥሟቸው እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ስለሆነም የሳይንስ ሊቃውንት ወደ ኬብሎች በጣም በሚጠጉበት ጊዜ ድሮኑን የሚከላከል ልዩ ስርዓት አዘጋጅተዋል፡፡
ምንጭ Technology.org

ደቡብ አፍሪካ የአስትራ ዜኒካ ክትባቶች ለህዝቧ እንዳይሰጡ አገደች
========================
ደቡብ አፍሪካ ለኮቪድ-19 ተብለው ከተሰሩ ክትባቶች ከቀዳሚዎቹ አንዱ የሆነውን የኦክስፎርድ-አስትራ ዜኒካ ክትባቶችን ሀገሪቱ ላይ ባለው አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዓይነት (ቢ.1.351) ላይ ከዓለም አቀፉ የክትባት ደረጃ የወረደ የ25 በመቶ ብቻ ውጤታማነት ማሳየታቸውን ተከትሎ ዜጎቿን ክትባቶቹ መከተቡን እንዳገደች ትናንት አስታወቀች፡፡ ደቡብ አፍሪካ ውሳኔውን ያስተላለፈችው ክትባቶቹ 2ሺህ ያህል ተሳታፊዎችን ባካተተ ጥናት ላይ ቀላል እና መካከለኛ ደረጃ ላላቸው የኮቪድ-19 ህመሞች አነስተኛ ጥበቃን ማሳየታቸውን ተከትሎ ነው፤ ምንም እንኳን ጥናቱ በምሁራን ግምገማ ባይደረግበትም፡፡ ተመራማሪዎች የአስትራ ዜኒካ ክትባቶች በኮቪድ-19 የተነሳ የሚመጡ ከፍተኛ ህመሞችን እና ሞትን ያስቀራሉ አያስቀሩም የሚለው ላይም ጥናት የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
መነሻውን ከደቡብ አፍሪካ ያደረገው ኮሮና ቫይረስ አይነት ከቀድሞውም በላቀ ተላላፊና አሁን በሀገሪቱ ካሉ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች መካከልም የ90 በመቶውን ድርሻ የወሰደ ነው፡፡ ታድያ እስካሁን 1.5 ሚሊዮን ነዋሪዎቿ በኮቪድ-19 ተጠቅተውባት 46,000 የሚሆኑትን በሞት ያጣችው ደቡብ አፍሪካ አንድ ሚሊዮን የኦክስፎርድ አስትራ ዜኒካ ክትባት ፍሬዎችን ተረክባ ነበር፡፡ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ማለቂያ ላይም 67 በመቶ ወይም 40 ሚሊዮን ያህል ህዝቧን ለመከተብ ዕቅድ ያላት ሲሆን በግዳጅ ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎቿንም ከያዝነው ወር ጀምሮ ለመከተብ አቅዳ ስትንቀሳቀስ ቆይታለች፡፡
ቢ.1.351 ያሳየውን ተቋቋሚነት ተከትሎ የኦክስፎርድ-አስትራ ዜኒካ ክትባት አበልፃጊዎች እስከ ፈረንጆቹ የበጋ ወራት መባቻ ድረስ ማስተካከያ የተደረገባቸው የክትባት ፍሬዎችን እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ለቢቢሲ ቃለ መጠይቅ የሰጡት በኦክስፎርድ ቡድን ውስጥ መሪ አጥኚ የሆኑት ሳራህ ጊልበርትም ለደቡብ አፍሪካው የኮሮና ቫይረስ ዓይነት የሚሆን ክትባትን እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
አሁን ላይ የሀገሪቱ መንግስት ትኩረቱን በጆንሰንና ጆንስን እንዲሁም ፋይዘር አማካኝነት በሚመረቱት የኮቪድ-19 ክትባቶች ላይ የሚያደርግ ሆናል፡፡ ሆኖም እነዚህ ክትባቶችም ቢሆን በአዲሱ የደቡብ አፍሪካ ኮሮና ቫይረስ ዓይነት ላይ ያሳዩት ውጤታማነት ብዙም አበረታች አይደለም፡፡ በጆንሰንና ጆንሰን የተሰራው ክትባት በዚህኛው የቫይረሱ ዓይነት ላይ ውጤታማ መሆን የቻለው በ57 በመቶ ሲሆን ሌላኛው የኮቪድ-19 ከትባት ኖቫቫክስም ውጤታማነቱ 49 በመቶ ሆኗል፡፡
የአስትራ ዜኒካ ክትባቶች በደቡብ አፍሪካው የኮሮና ቫይረስ ዓይነት ላይ ያሳዩት ውጤት ከደቡብ አፍሪካም የተሻገረ ተፅዕንዖ ሊኖረው ይችላል፡፡ ባለው ረከስ ያለ ዋጋ እና በማንኛውም አይነት ማቀዝቀዣ ውስጥ ለማቆየት የሚቻል በመሆኑ ሳብያ ብዙ አፍሪካውያን ሀገራት የአስትራ ዜኒካ ክትባትን ለመጠቀም ሲያቅዱ ቆይተዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደሃ ሀገራትን የኮቪድ-189 ክትባቶች ተጠቃሚ ያደርግ ዘንድ የተወጠነው የኮቫክስ ጥምረትም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአስትራ ዜኒካ ክትባቶችን ከህንዱ ሴረም ኢንስቲትዩት ገዝቷል፡፡
ምንጭ፡ DW እና science መፅሔት (ድረ-ገፅ)