በሃውልት ላይ የተቀረፁ ጥንታዊ የሮም ነገስታትን ምስል ወደ እውነተኛ ምስል የቀየረው የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ስልት
======================
የማሽን ለርኒንግ ቴክኖሎጂ የጥንት ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን እንደ አዲስ ለማውጣት እና አሁን ባለው ገፅታ ለመከሰት ጥቅም ላይ መዋል ከጀመረ ትንሽ ሰነባብቷል፡፡ ይህ አስደናቂ ቴክኖሎጂ በዚህም ብቻ ሳያበቃ በሃውልቶች ላይ የተቀረፁ ጥንታዊ የነገስታት ምስሎችን ወደ እውነተኛው መልካቸው ወይም (photorealistic images) በመቀየርም የሰዎችን በምናብ የመጓዝ ፍላጎት በእጅጉ እያራቀቀው ይገኛል፡፡
የቨርቿል ሪያሊቲ ዲዛየነር የሆነው ዳንኤል ቫሸርት በሃውልት ላይ የተቀረፁ 54 ጥንታዊ የሮም ነገስታትን ምስል ወደ እውነተኛ መልካቸው ለመቀየር የተጠቀመበት የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ በማሽን ለርኒንግ ዘርፍ ውስጥ አንድ የሰራር ዘዴ ሲሆን ቆየት ያሉ ስእሎችን እና የመሬት አቀማመጦችን በምንፈልገው መልኩ ለመላዋወጥና ለመከሰት የሚስችለን የማሽን ለርኒንግ ዘዴ ነው፡፡ Generative Adversarial Network (GAN) የሚል ስያሜ ያለው ይህ የማሽን ለርኒንግ ስልት በተለያዩ የኦን ላይን ፕላትፎርሞች እና መተግበሪያዎች የሚገኝ ሲሆን ይህን ምርምር ያከሄደው ዳንኤል ቫሸርትም ArtBreeder የተባለውን የኦን ላይን ፕላትፎርም ለምርምሩ ተጠቅሟል፡፡
ይህን የማሽን ለርኒንግ ስልት የተገበረው ተመራማሪው የ54ቱን ነገስታት ምስሎች ከሃውልቶች፣ ከሳንቲሞች እና የጥንት ስእሎች ከውሰደ በኋላ በጥቅሉ 800 የሚጠጉ የነገስታቱን ምስለ ቅርፅ ArtBreeder በተባለው የኦን ላን ፕላትፎርም በማስገባት ትንተና እንዲደረግባቸው አድርጓል፡፡ በዚህ የትንተና ሂደትም የነገስታቱን እውነተኛ የፊት ቅርፅ፣ ገጽታ፣ የቆዳ አይነት በቀላሉ ሊያመለክት የሚችል እውነተኛ ምስል ከፕላትፎርሙ ሊገኝ ችሏል፡፡ ተመራማሪው ዳንኤል ቫሸርትም ይህን አውነተኛ ምስል ከነገስታቱ ግላዊ የታሪክ ጽሁፎች እና ከሌሎች የስነ ጥበብ መዘግብቶች ጋር ካነፃፀረ በኋላ በፎቶሾፕ መተግበሪያ ይበልጥ ሊቀራረብ የሚችል የነገስታቱን እውነተኛው መልክ ወይም (photorealistic images) ከምርምሩ ማውጣት ችሏል፡፡
54ቱ የነገስታት ምስሎች የሰዎች አዕምሮ እና የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ አንድ ላይ ምን ሊፈጥሩ እንደሚችሉ የሚያሳይ ስራ ነው የሚለው ዳንኤል ቫሸርት በዚህ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ሰዎች እጅግ አስገራሚ ስራዎችን ከዚህ በኋላም እንደሚሰሩ ይናገራል፡፡ ምንጭ፡ Big Think

የዶሮን ፆታ በእንቁላል ሳለ መቀየር ይቻላል?
===================
በዘመናዊ የዶሮ እንቁላል ኢንዱስትሪ ውስጥ ጫጩቶች ሲፈለፈሉ ወንድ እንዳይሆኑ ስለሚፈለግ በየዓመቱ ከ7 ቢሊዮን በላይ ወንድ ሆነው የሚፈለፈሉ ጫጩቶች ይሰዋሉ፡፡ ይህንንም ለማስቀረት እ.አ.አ በ2017 የተመሰረተው የእስራኤሉ ሱስ ቴክኖሎጂ ጫጩቶች ገና በእንቁላላቸው ውስጥ ከተፀነሱበት ጊዜ አንስቶ ባለው ዕድገታቸው ውስጥ ፆታቸውን በመቀየር የእንቁላል ማስጣል ስራን ወጪ ቆጣቢ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡ ለዚህ ስራ ጥቅም ላይ የሚውለው ቴክኖሎጂ እንቁላሎቹን ለድምፅ ንዝረት በማጋለጥ የዲ.ኤን.ኤ ትዕዛዞች ወደ ተግባር የሚለወጡበትን ሂደት (Gene Expression) ላይ ባሉት አዳዲስ የተፀነሱ ጫጩቶች ላይ ለውጦችን በማምጣት ነው ፆታቸውን ከወንድ ወደ ሴት እንዲቀየር የሚያደርግ ነው፡፡ እንደ ድርጅቱ ከሆነ አሁን ላይ ባለው የሙከራ ምርቱ ቢያንስ 60 በመቶው እንቁላሎቹ በእርግጠኝነት ሴት ሆነው እንዲፈለፈሉ እያደረገ ነው፤ ወደፊትም ድርሻው ከዚህም በላቀ እንደሚያድግ ይናገራል፡፡ አሁን ላይ ቴክኖሎጂውን እዛው እስራኤል ውስጥ ባለ የእንቁላል ማስጣያ እርሻ ጋራ በመስራት ላይ ሲገኝ በቀጣይም ከጣልያን እና አሜሪካን እንቁላል አምራቾች ጋራ የሚሰራ ይሆናል፡፡
ድምፅን ተተቅሞ የጫጩቶችን ፆታ የመለወጡ ነገር እንዲሁ ስናስበው የሚሆን መስሎ ላይታየን ይችል ይሆናል፡፡ ሆኖም ሌላ ውጫዊ ተፅዕንዖ የሆነው ሙቀት በተለያዩ የዓሳ እንዲሁም እንደ እንቁራሪት፣ አዞ እና መሰል ፍጥረቶች የፆታ ለውጥን ሲያመጣ ይታያል፤ ምንም እንኳን ይህ ለወፍ ዝርያዎች የሚሰራ ባይሆንም፡፡ በሌላ መልኩ ጥናቶች የሚያሳዩት የዲ.ኤን.ኤ ትዕዛዞች ወደ ተግባር የሚለወጡበት ሂደቶች ለድምፅ ሲጋለጡ በተፅዕንዖ ስር እንደሚወድቁ ነው፡፡
የሱስ ቴክኖሎጂ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ያኤል አልተር እንደምትለው ከሆነ ድርጅቱ እንቁላሎቹን ስፒከር በተገጠመላቸው የጫጩት ማስፈልፈያ ማሽኖች ውስጥ የመጀመሪያዎቹን 13 ቀናት ለሰው ጆሮ ሊሰማ በሚችል መጠን የጩኸት ድምፅ (beeping) ይለቀቅባቸዋል፡፡ ድምፁ በቀን ውስጥ ያለማቋረጥ ለረጅም ሰዓታት እንቁላሎቹ ላይ እየጮኸ ይውላል፡፡ እዚህ ላይ ዋናው ነገር የድምፁ ከፍታ እና ፍሪኩዌንሲ ላይ ነው፤ ሙቀት እና ወበቁም ቁጥጥር ይደረግባቸዋል፡፡ በዚህም ሳብያ በድምፅ ፆታን ወደ ሴት እንዲያደላ የማድረግ ስልቱን በተደጋጋሚ በሺዎች እንቁላሎች ላይ ሞክረው በውጤቶቹ ከ60 በመቶ በላይ ሴት ጫጩቶች መፈልፈል እና በአንዳንድ አካባቢዎችም ድርሻው እስከ 70 በመቶ የደረሰ መሆኑን ያኤል አልተር ትናገራለች፡፡
እንደ ያኤል ግምት ከሆነ ለውጡ ሊመጣ የቻለው በዶሮዎች ፆታዊ አፈጣጠር ላይ ትልቅ ሚናን የሚጫወተው ዲኤምአርቲ1 (DMRT1) በራሒን በድምፁ አማካኝነት ማስቆም በመቻሉ ነው፡፡ ሆኖም በተቃራኒው ስለ ዶሮዎች በማጥናት ላይ ያሉትና በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኤደንብራ እና በሞናሽ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያገለግሉት ማይክ ክሊንተን እና ግሬግ ስሚዝ ዲኤምአርቲ1 ሊቆም የሚችል ነገር እንዳልሆነ ይገልፃሉ፡፡ እንደነርሱ ከሆነ በመጀመሪያ ዲኤምአርቲ1ን በመቀነስ ፆታቸው ወደ ሴትነት የተለወጡ የዶሮ ጫጩቶች ወንድነታቸው የማይለቃቸውና በአካልም ወንድ መስለው የሚፈለፈሉ ናቸው፡፡ ይህም አዕዋፍ በጎኔዳል ሆርሞኖች የተነሳ የሚመጣባቸው ተፅዕንዖ አነስተኛ በመሆኑ ነው፡፡ ሁለተኛው፤ ተፀንሰው ሳለ ዲኤምአርቲ1ን በመቀነስ ፆታቸው ከወንድ ወደ ሴትነት የተቀየሩ ዶሮዎች እንቁላሎችን እንደማይጥሉ ገና ታትሞ ያልወጣው ጥናታቸው አሳይቷል፡፡
ክሪስተን ናቫራ የተባለች ሌላ ተመራማሪም በበኩሏ ድርጅቱ አገኘው የሚለውን ውጤት በሳይንሳዊ መንገድ የመጣ ስለመሆኑ በምሁራን የተፈተኑ ጥናቶችን ማቅረብ እንዳለበት ታስረዳለች፡፡ በዚህ ረገድ ሱስ ቴክኖሎጂም የጥናቱን አስፈላጊነት ዕውቅና በመስጠት የሰራቸው ምርምሮቹን ለማሳተም እየሰራ መሆኑንም የሳይንቲፊክ ዳይሬክተሯ ሮተም ካዲር ተናግራለች፡፡
በዘመናዊ የዶሮ እንቁላል ኢንዱስትሪ ውስጥ እንቁላሎች እንዲጣሉ የወንድ አውራ ዶሮዎች ድርሻ ቢያስፈልግም ለእንቁላል ጣይነት የሚፈለጉ ጫጩቶች ሲፈለፈሉ ግን እነርሱም እንቁላልን ይሰጡ ዘንድ ሴት ሆነው እንዲወጡ ይፈለጋል፡፡ ሆኖም ግማሾቹ እንቁላሎች ወንድ ሆነው በመፈልፈላቸውና እነርሱን አደል በየዓመቱ ከ7 ቢሊዮን በላይ ወንድ ጫጩቶች እንቁላል ለማግኘት ሲባል በቄራ ይሰዋሉ፡፡ ከሱስ ቴክኖሎጂስ በተጨማሪ ሌላ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ኩባንያም በተለየ አኳሀን ገና እንቁላሎቹ ወደ ማስፈልፈያ ማሽኑ ከመግባታቸው አስቀድሞ ፆታቸውን በመለየት እና እንዳይገቡ በማድረግ ላይ አተኩሮ እየሰራ ነው፡፡ ለዚህም የእንቁላሉን ፈሳሽ በናሙናነት ወስዶ የመመረምርና ሌሎች ስልቶችን የሚጠቀም ይሆናል፡፡
ምንጭ፡ The Guardian

ታዳሽ ኃይል እና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ
-------------------------------
ኢትዮጵያ የሃይድሮ ሀይልን ጨምሮ የነፋስ፣ ጂኦተርማል፣ ሶላር ባዮማስን እና ሌሎች በርካታ የታዳሽ ሀይል ሀብቶች ያሏት ሃገር ናት፡፡ አነዚህ ብዛት ያላቸው የታዳሽ ሃይል ሀብቶች ሀገሪቱ ከ 60,000 ሜጋዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዲኖራት የሚስችሉ ቢሆንም አሁን ላይ ጥቅም ላይ የዋሉት የታዳሽ ሃይል ሀብቶች በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ አብዛኛው የሀገሪቱ ህዝብ በገጠራማ አካባቢ ከመኖሩ ጋር ተያይዞ ዘመናዊ የሃይል አማራጮችን የማግኘት እድሉ እጅግ የጠበበ ሲሆን፤ ከእነዚህ የሃይል ምንጮች በላይ በኤሌክትሩክ ሃይል የማይመደቡ እንደ ባዮማስ ያሉ የሃይል አማራጮች ይበልጥ ጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙ ናቸው፡፡
መረጃዎች እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያ የተትረፈረፈ የታዳሽ ኃይል ሀብቶች ባለቤት ብትሆንም በአፍሪካ በነፍስ ወከፍ ደረጃ ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ከሚጠቀሙ ሀገራት አንዷ ነች፡፡ በአሁኑ ሰዓት የሀገሪቱ ሀይል የማምረት አቅም 4,200 ሜጋዋት የደረሰ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ከ12 በላይ የሀይል ማመንጫ ጣቢያዎች የሚካተቱበት የሃይድሮ ሀይል 94 በመቶውን የሀገሪቱን የሃይል አቅርቦት ይሸፍናል፡፡ በቅርቡ የተሰሩ የኢትዮጵያ የሀይል ፍላጎት ዳሰሳ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት የአገሪቱ የሀይል ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን በአገሪቱ ያሉ ሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም የኢንዱስትሪ፣ የግብርና፣ የንግድ እና የመሳሰሉት ዘርፎች የሀይል ፍላጎታቸው ይበልጥ እየጨመረ መምጣቱ በግልጽ የሚታይ ነው፡፡
ሃገሪቱ አሁን በያዘችው የሀይል አቅርቦት እንቅስቃሴ እንደአውሮፓውያኑ በ2025 ለሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች የኤሌክትሪክ ሃይልን ለማዳረስ ወጥና እየሰራች ቢሆንም በዘርፉ ከሚያግጡ መሰናክሎች አንጻር እቅዱ በተባለለት ግዜ ማሳካት እንዲቻል የሁሉም ባለድርሻ አካለት ሁለንተናዊ ተሳትፎ እጅጉን ወሳኝ ነው፡፡ በዚህ የሃገሪቱ የሀይል አቅርቦት እንቅስቃሴ ውስጥ በእቅድ ደረጃ የተያዘው 35 በመቶ የሚሆነው የኤሌክትሪክ ሃይል ከማእከላዊ ስርጭት ውጭ በሆነ የ (off-grid) አማራጮችን ለማልማት የታሰበ ሲሆን፤ ቀሪውን ደግሞ በመደበኛው የመንግስት የሃይል ስርጭት ውስጥ የተካተተ ነው፡፡
ታዲያ በዚህ የሀይል አቅርቦት እንቅስቃሴ ውስጥ ቢያንስ ከ35 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ ከታዳሽ ሃይል ከሚገኙ ዘመናዊ የሃይል አማራጮች ኤሌክትሪክን እንዲያገኝ የታቀደ ሲሆን በዚህ ማዕቀፍ ውስጥም 8,370 የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ሂደት ሀገራችን አትዮጵያን በአሁኑ ወቅት ለአለማችን ስጋት የሆነውን የአካባቢ ብክለትን ከግምት ውስጥ በማስገባት አረንጓዴ አብዮትን በማራመድ ላይ ከሚገኙ ጥቂት ሀገሮች መካከል አንዷ የሚያደርጋት ከመሆኑም ባለፈ እዚህም እዚያም የተጀመሩት የአማራጭ ሀይል ምንጮች፣ የሀገሪቱ አረንጓዴ ፖሊሲ እና በፕሮጀክቶች ላይ ለአካባቢ ጥበቃ እየተሰጠ ያለው ትኩረት ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ መጎልበት ተጨማሪ ማሳያ ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡
በጠቅላላው በዚህ ዘርፍ እየታየ ያለው እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪ መሆኑ እንዳለ ሆኖ የአለም የእድገት ሩጫ ተወዳዳሪ በበዛበት በዚህ ወቅት ያለውን አማራጭ ሁሉ በመጠቀም ትንፋሽ መሰብሰብ አስፈላጊነቱ አጠያያቂ አይሆንም፡፡ እንደዚህ ያለው የሀይል ፍላጎት ወደ ተደራጀና ዘመናዊ የሀይል አቅርቦት የተሸጋገረ ማህበረሰብ፣ መሰረተ-ልማት በአጠቃላይ ስርአት ይፈልጋል፡፡ ይህም የሚረጋገጠው ከፍተኛ ሀይል ማመንጨት ሲቻል ብቻ ሳይሆን የመነጨውም ሀይል የሚሰራጭበት ስርዓት የዳበረ ሲሆን፣ የተለያዩ የሀይል አማራጮችን በአንድ ጊዜ ማቅረብ ሲቻል፣ የአገሪቱ ዋና ዕቅድ ፕሮጀክቶች ውጤታማና እርስ በርሳቸው የተሰናሰሉ ሲሆኑ እንዲሁም የግል ኢንቨስትመንቱን የሚያበረታታ አካባቢ መፍጠር ሲቻልም ጭምር ነው፡፡
ምንጭ፡ Ethiopian Herald እና IEA

ህመም አልባ የደም ናሙና መውሰጃ መርፌ
************************
የሰው ልጅ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለተለያዩ የጤና መታወኮች ይጋለጣል፡፡ ታዲያ ይህ የጤና መታወክ በቀላሉ የማይመለስ ከሆነ መፍትሔ ፍለጋ ወደ ሀኪም ጎራ ማለት አስፈላጊ ነው፡፡ በዛሬ ይተወኛል፤ ሲውል ሲያድር ቀለል ይለኛል በሚል ተስፋ በበሽታው በተዳከመ ሰውነት ወደ ሀኪም ቤት ከተሄደ በኋላ ያ የደከመ ሰውነት ከማይቋቋማቸውና የግድ ከሆኑ የህክምና መንገዶች አንዱ በመርፌ የሚወሰድ የደም ናሙና ነው፡፡ በዚህ ናሙና አማካኝነት ሀኪሞቻችን የያዘን ህመም በቫይረስ ወይም በባክቴሪያ ምክንያት መምጣቱን ይመረምራሉ፡፡
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የተለያዩ በሽታዎችን የሚያመለክቱ ስነ-ህይወታዊ ፍንጮች በደም ህዋሳት ላይገኙ ይችላሉ፡፡ በቀላሉ ሊገኙ በማይችሉ የህዋሳት ክፍሎቻችን ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ማክልቬይ የኢንጅነሪንግ ትምህር ቤት የሚገኙ ኢንጅነሮች ያለምንም የህመም ስሜት በሰውነት ቆዳ ላይ ተደርጎ በደም ውስጥና በህዋሳት ሌሎች ፈሳሽ ክፍሎች የሚገኝን የበሽታ ምልክት መመርመሪያ microneedle ማበልጸጋቸው ተሰምቷል፡፡
ይህ ግኝት በአነስተኛ ዋጋ ሊቀርብ የሚችልና የተለያዩ አነስተኛ ክሊኒኮች እንዲሁም ታማሚዎቹ ራሳቸው በቀላሉ ሊጠቀሙት የሚችሉና አስፈላጊውን ከደም ናሙና የሚጠበቅን መረጃ ለሀኪሞች ማቅረብ የሚያስችል ነው፡፡ በቆዳ ላይ እንደ ፕላስተር የሚለጠፈው ፈጠራ በዋጋና ለአጠቃቀም ምቹ ከመሆኑ በተጨማሪ ህመም አልባ መሆኑ ተመራጭ እንደሚያደርገው ተገምቷል፡፡
ግኝቱ በደም ውስጥ ያለን መረጃ ያለምንም ተጨማሪ ነገር በቆዳችን ስር ያሉ ህዋሳትን የከበበውን ፈሳሽ በመጠቀም መለየት ያስችላል፡፡ ፈሳሹ በሳይንሳዊ አጠራሩ dermal interstitial fluid (ISF) የሚባለው ነው፡፡ ምንም እንኳን ይህ ፈሳሽ ስለ አጠቃላይ ሰውነታችን ሰፊ መረጃን የያዘ እና የስነ-ህይወታዊ ሞለኪዩሎች ምንጭ ቢሆንም መረጃ ለማግኘት ከቆዳችን ውጭ ማውጣት ያስፈልግ ነበር፡፡
አዲሱ መንገድ ፈሳሹን ከሰውነት ማውጣት ሳያስፈልግ በከፍተኛ ብርሃን በማንጸባረቅ አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ያስችላል፡፡
ምንጭ SciTechDaily

ኢንስቲትዩቱ ያሰናዳው የቅድመ ኢንኪዩቤሽን ፕሮግራም ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጀመረ
======================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የኢኖቬሽን ባህልን ለማሳደግ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ ኢኖቬተሮችን ለማፍራት ያግዝ ዘንድ ያሰናዳው የቅድመ-ኢንኪዩቤሽን ፕሮግራም የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡ ለሶስት ቀን በሚቆየው በዚህ የስልጠና መርሃግብር የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች፣ ተመራማሪዎች እና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የሚሳተፉ ሲሆን፤ የፈጠራ ሃሳባቸውን የሚያሳድጉበት እና ቢዝነስን መምራት የሚችሉበትን ሁለንተናዊ ክህሎት ከስልጠናው ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በመርሃግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የመክፈቺያ ንግግር ያደረጉት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ ኢንስቲትዩቱ በስልጠና፣ በምርምር እና በቢዝነስ መካከል ያሉትን ሁለንተናዊ የግንኙነት ክፍተቶች ለመሙላት እና የሀገሪቱን የቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን አንስተው ይህ የቅድመ ኢንኪዩቤሽን ፕሮግራምም በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ጠቃሚ ሃሳብ ያላቸው የፈጠራ ባለሙያዎች ሃሳባቸውን ወደ ቢዝነስ ማሰደግ እንዲችሉ የሚያግዝ የመማሪያ መድረክ እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ በተለይም እንዳነሱት ኢኖቬተሮች የፈጠራ ሃሳባቸውን መጎልበት እንዲችሉ ሃሳባቸውን ለሌሎች ማጋራት እንደሚገባቸው እና እንደዚህ አይነት መድረኮች ሲገኙም ጠንካራ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው አሳስበዋል፡፡
የስታርት አፕ እና የኢኖቬሽን ፕሮሞሽን ዳይሬክተር የሚያዘጋጀው ይህ ስልጠና ለተሳታፊዎች የፈጠራ አቅምን ለማሳደግ በሚያስችሉ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ስልጠና፣ የቢዝነስ ፕላን አቀራረፅ፣ እና ሌሎች መሰረታዊ የክህሎት ስልጠናዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ለሶስት ቀን የሚቆይ ሲሆን ከተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት የሚጋበዙ የዘርፉ ባለሙያዎችም ልምድ እና ተሞክሯቸውን ለሰልጣኞች የሚያካፍሉ ይሆናል፡፡ በዛሬው የስልጣና መርሃ ግብርም የቢብሎኪ የቴክኖሎጂ ተቋም ዋና መስራች አቶ ናታን ዳምጠው ስለኢኖቬሽን የመጀመሪያ ሂደቶች እና ስለዘላቂ ቢዝነስ አካሄድ ጠቃሚ ሃሳቦችን ለሰልጣኞች አካፍለዋል፡፡
ይህ የመጀመሪያ ዙር የቅድም ኢንኪዩቤሽን ፕሮግራም ኢንስቲትዩቱ ቀድሞ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት የፕሮጀክት ሃሳባቸውን አቅርበው ለተመረጡ 25 አመልካቾች የሚሰጥ እና ለተሳትፎዋቸውም ሰርተፍኬት እንዲያገኙ የሚያስችል ስልጠና ሲሆን በቀጣይ ጊዜያትም በተለያዩ መንገዶች መርሃ ግብሩ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ጄፍ ቤዞስ ከኃላፊነቱ ሊነሳ ነው
============
የግዙፉ ቴክኖሎጂ ኩባንያ አማዞን ዋና ስራ አስፈፃሚው ጄፍ ቤዞስ ከኃላፊነቱ እንደሚለቅ ተናገረ፡፡ የዋና ስራ አስፈፃሚነቱን ቦታ አሁን ላይ የአማዞን ዌብ ሰርቪስ ዋና ኃላፊ የሆነው አንዲ ጃሲ የሚይዝ ሲሆን ጄፍ ቤዞስ የኩባንያው ቦርድ ሊቀ መንበር ሆኖ ይቀጥላል፡፡ የልተጠበቀው ዜና የተሰማው ኩባንያው በተለይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን ተከትሎ ከፍተኛ ትርፍን እና በዓመቱ የመጨረሻ ሦስት ወራት ብቻም የ100 ቢሊዮን ዶላር ሽያጭ ማስመዝገቡን ባሳወቀበት ወቅት ነው፡፡
የ57 ዓመት ጉልምስናው ላይ የሚገኘው ጄፍ ቤዞስ አማዞንን በአውሮፓውያኑ 1994 ከመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በመምራት በምድራችን ካሉ ግዙፍ ኩባንያዎች አንዱ ሊያደርገው በቅቷል፡፡ ያኔ የበይነ-መረብ መፃህፍት መሸጫ ሆኖ ብቅ ያለው ኩባንያው አሁን ላይ በክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ፍጆታ ምርቶች አቅርቦት፣ ኤሌክትሮኒክስ እና መዝናኛ ላይ ከቀዳሚ ተዋናዮች አንዱና በስሩም ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ቀጥሮ የሚያሰራ ተቋም ነው፡፡ ጄፍ ቤዞስም በዚህ ሰዓት ከሌላኛው የቴክኖሎጂ ሰው ኢለን መስክ ቀጥሎ በ185 ቢሊዮን ዶላር የዓለማችን ቁጥር ሁለት ሀብታም ሰው ሆኗል፡፡ “አማዞን አሁን የሆነውን የሆነው በፈጠራው ምክንያት ነው” የሚለው ጄፍ ቤዞስ ፈጠራዎች በስኬት ከተመሩ ከአንድ ወቅት አስገራሚ ፈጠራነት በተወሰኑ ዓመታት ውስጥ በሰዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ የሚገቡና ለአምጪዎቻቸውም ዘላቂ ጥቅምን የሚያስገኙ እንደሆነ ይናገራል፡፡
ጄፍ ቤዞስ ከቅርብ አመታት ወዲህ ከአማዞን የዕለት ተዕለት ተግባራት እራሱን እያወጣና እንድ ህዋ አሰሳ እና ባለቤት በሆነበት ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ላይ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ አንዲ ጃሲም የቤዞስ ተተኪ ተደርጎ መታየት ከጀመረ ቆየት ብሏል፡፡ እርሱ የሚመራው አማዞን ዌብ ስርቪስስ ለተለያዩ መንግስታት እና እንደ ኔትፍሌክስ ላሉ ትላልቅ ኩባንያዎችም የኮምፒውቲንግና መረጃ ማከማቸት አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ከአማዞን አጠቃላይ ሽያጭ የ10 በመቶ ከትርፉም የ52 በመቶውን ድርሻ ይወስዳል፡፡

፭ቱ አስገራሚ ውሃን የማግኛ ቴክኖሎጂዎች
=================
የሰው ልጆች ለመኖር ያስፈልጓቸዋል ከሚባሉ መሰረታዊ ነገሮች መካከል አንዱ ንፁህ ውሃ ነው፡፡ ታድያ ይህ ከተፈጥሮ የምናገኘው ፀጋችን እንደ አየር ንብረት ለውት ባሉ ችግሮች ሳብያ ጉዳት እየደረሰበትና መጠኑም እያሽቆለቆለ ይገኛል፡፡ ይህን የውሃ እጥረት ሊቀርፉ ይችላሉ ተብለው ከሚገመቱ ቴክኖሎጂያዊ መፍትሄዎች ውስጥ ተከታዮቹን አንመልከት፤
ጉምን መሰብሰብ
በጭጋግ ወይም ጉም ውስጥ የሚገኝ ውሃ ጉሙ ጠንከር ብሎ በተደጋጋሚ ሚፈጠርባቸው አካባቢዎች ላይ እንደ አንድ የመጠጥ ውሃ ምንጭ መታየት ጀምሯል፡፡ የደመና ጭጋግ የቁም መረብን በመጠቀም መሰብሰብና ለተጠቃሚ ማሰራጨት ይቻላል፡፡ ለመረቡ ስራ እንደ አልሙኒየም፣ ፕላስቲክ፣ ፕሌክሲግላስ ያሉትን ግብዓቶች ጥቅም ላይ ማዋል ይቻላል፡፡ የቴክኖሎጂው ውጤታማነት አካባቢው ላይ ባለው መልከአ ምድራዊ አቀማመጥ የሚወሰን ቢሆንም በተራራማና መልከአ ምድሩ አስቸጋሪ በሆነባቸው ስፍራዎችም ሊሰራ ይችላል፡፡ ቴክኖሎጂው እስከ አሁን ድረስ በቺሊ፣ ኤርትራ እስራኤል እና ኦማን ተግባራዊ እየሆነ ነው፡፡
ከደመና መሰብሰብ
በትክክለኛው ሁኔታ ላይ ከተገኘ ስልቱ ከአየር ላይ የሚወርደውን ውሃ የመጨመር አቅም አለው፡፡ ቴክኖሎጂው ጥቃቅን አካላትን ወደ ደመናው እና ዙርያ አካባቢው በማሰራጨት የሚሰራ ነው፡፡ እነዚህ አካላት የዝናብ ጠብታ እና በረዶዎች እዲፈጠሩ በመገፋፋት ዝናብ የመዝነቡን እድል ይጨምሩታል፡፡ እንደ አካባቢው የደመና ሽፋን፣ አይነት፣ የውሃ ይዘት እና ሙቀት ቢለያይም ቴክኖሎጂው በተለያዩ ሀገራት ሲሰራበት አመታዊ የዝናብ መጠኑን እስከ 20 በመቶ ማሳደግ ችሏል፡፡ በሰማይ ካለው ደመና ወደ መሬት ወርዶ ውሃ የሚሆነው 10 በመቶው ብቻ መሆኑን ከግንዛቤ ስናስገባ ደግሞ ቴክኖሎጂው ያለውን ከፍተኛ እምቅ አቅም እንረዳለን፡፡
ትነትን መቀነስ
አነስተኛ ዝናብን በሚያገኙ ደረቃማ አካባቢዎች ሊተን ይችል የነበረውን የመሬት ውሃ ይዞ ማስቀረቱ የውሃ ችግሩን በመቀነሱ ረገድ ሊረዳ ይችላል፡፡ ሁለት አይነት የውሃ መሰብሰብያ ስርዓቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው በጣርያ ላይ የሚፈሰውን የዝናብ ውሃ ሰብስቦ ማጠራቀም ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ከዚህ ውጪ ባለው መሬት ላይ የሚፈሰውን ውሃ በሰፋፊ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ውሃ ማጠራቀሚያዎች ማከማቸት ነው፡፡ በሁለተኛው አማራጭ ላይ የውሃ ማከማቻው አፈሩ በተለይም አሸዋማ በሆነ አካባቢ ውሃውን ከመምጠጥ የሚያስጥለው ሆኖ መገኘት አለበት፡፡
የባህር ውሃን ከጨው አፅድቶ መጠቀም
ይህ ስልት ከባህር አልያም ሌሎች የከርሰ ምድር ምንጮች የሚገኘውን ውሃ ከጨው በማፅዳት ለመጠጥ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ ከጨው የማፅዳት ስልቱ የሰው ልጆች ከመደበኛው የዝናብ ዑደት ከምናገኘውም በተጨማሪ ሌላ ውሃን የሚሰጠንና ጥራት ያለው ውሃ አቅርቦቱን ከመጨመርም ባሻገርም ከአየር ንብረት ጥገኝነት የሚያላቅቀን ነው፡፡ ስልቱ በተለይም ከጊዜ ወደጊዜ በሜምብሬን ቴክኖሎጂ እና ማቴሪያል ሳይንስ ልህቀቶች እተመዘገቡ ከመምጣታቸው ጋራ በተያያዘ እያደገ ሲሆን የምርት ዋጋውም በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንስ ይጠበቃል፡፡ አሁን ላይ በባህር ዳርቻ የሚገኙ ከተሞች ስልቱን ተጠቅመው የሚያገኙት ውሃ ከአጠቃላይ አቅርቦታቸው የ10 በመቶ ድርሻን ሲወስድ ይህ ቁጥር እንደ አውሮፓውያኑ 2030 25 በመቶ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የበረዶ ግግሮች
ባለንበት ዘመን ግዙፍ የበረዶ ግግሮችን ጎትቶ ወደ አንድ ቦታ በመውሰድ አክስሞ የውሃ ችግርን ለመፍታት ማሰቡ ስሜት የሚሰጥ ነገር ባይመስልም የተለያዩ ተመራማሪዎች፣ ፖለቲከኞች እና ምሁራን ግን እያሰቡበት ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ሀሳቡን እያውጠነጠኑ ካሉት ሀገራት መካከል የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች እና ደቡብ አፍሪካ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ይህ ስልት ስኬታማ ሆኖ እንዲገኝ ታድያ አመቺ የበረዶ ማግኛን መለየት፣ ለመጎተት የሚያስፈልገውን የጉልበት መጠን ማወቅ፣ በጉዞ ሂደት የሚቀልጠውን በረዶ መጠን መተንብይ እና ምጣኔ ሐብታዊ አዋጭነቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
ምንጭ፡ The Conversation

አዲሱን የኮሮናቫይረስ አይነት ክትባትም ላያስቆመው ይችላል
===================
መነሻውን ከሀገረ እንግሊዝ ያደረገው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ አይነት አሁን ያሉትን ክትባቶች ማምለጥ የሚያስችሉትን ለውጦች ማድረጉን አዲስ ሪፖርት አሳየ፡፡ ቢ.1.1.7 በሚል ስያሜ የሚታወቀውና ከቀድሞው የኮሮና ቫይረስ ዓይነት የላቀ የመተላለፍ አቅም ያለው የቫይረስ ዓይነቱ መስከረም ላይ ለመጀመሪያ ጊዚ እንግሊዝ ውስጥ ከታየበት ጊዜ አንስቶ በመላው ዓለም እየተሰራጨ ይገኛል፡፡
ባሳለፍነው ሰኞ የእንግሊዝ መንግስት ከወሰዳቸውና 214,000 የአዲሱ ቫይረስ ዓይነት ናሙናዎች ውስጥ በ11 ናሙናዎች ላይ ኢ484ኬ (E484K) የተሰኘው ለውጥ (mutation) መገኘቱን አስታውቋል፡፡ ይህኛው ለውጥ ከዚህ ቀደምም ከጥቅምት አንስቶ በደቡብ አፍሪካ በታየው የቢ.1.351 ኮሮና ቫይረስ ዓይነት ላይ ታይቶ ነበር፡፡ የመንግስት ኃላፊዎችን ያስጨነቀው ጉዳይ ይህ የለውጥ ዓይነት የክትባቶችን ውጤታማነት ሊቀንስ መቻሉ ላይ ነው፤ እንደ ኖቭአቫክስ እና ጆንሰንና ጆንሰን ያሉት የመድሃኒት አምራቾች ያመረቷቸው የኮቪድ-19 ክትባቶች በደቡብ አፍሪካ አነስተኛ ውጤታማነትን አሳይተዋልና፡፡ የኢ484ኬ ለውጥ አንዳንድ የበሽታ መከላከያዎችን ቫይረሱ ወደ ሰውነት ከመግባቱ አስቀድሞ አቅም የለሽ እና ከጥቅም ውጪ የማድረግ አቅማቸውን ሊቀንሰው ይችላል፡፡ ሆኖም ይህ ለውጥ በእንግሊዙ የቫይረስ ዓይነት ላይ መታየቱ ቫይረሱን ይበልጥ ተላላፊና ክትባቱንም አቅም አልባ ያደርገዋል ማለት አይደለም፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ኢ484ኬ በደቡብ አፍሪካው የቫይረሱ አይነት ላይ ያሳየውን ተፅዕንዖ በእንግሊዙ ላይም ላይደግመው ስለሚችል ነው፤ የእያንዳንዱ ለውጥ ተፅዕንዖ እንደየበለፀጉበት በራሒ የሚለያይ በመሆኑ፡፡
የኢ484ኬ ለውጡ የተከሰተው ቫይረሱ ሰውነትን ሲያጠቃ ቀድሞ በሚያርፍበት ሪሴፕተር ባይንዲንግ ዶሜን (RBD) በተባለው ክፍል ላይ ነው፡፡ በዚህም ስፍራው ላይ ሆነው ቫረሱ ወደ ህዋሳት ዘልቆ እንዳይገባ የሚጠብቁት የበሽታ መከላከያ ዘቦች ኢ484ኬን እንዳያውቁት በማድረግ ቫይረሱን በመከላከሉ ስራ ላይ አቅም አልባ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህ ለውጥ ያለባቸው የኮሮና ቫይረስ ዓይነቶች በተለይ አብዛኛው ሰው በቫይረሱ በተያዘባቸው አካባቢዎች ላይ በቀላሉ ተሰራጭተው ክትባቶች ውጤታማ እንዳይሆኑ ከማድረግም ባሻገር ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችን ዳግም ሊያጠቁ ይችላሉ፡፡
ኢ484ኬ ብራዚል ውስጥ ባሉት ልዩ ልዩ የኮሮና ቫይረስ አይነቶች ላይም የታየ ሲሆን ለቫይረስ አይነቶቹ የሚሰጠው ጥቅም ገና በመጠናት ላይ ነው፡፡ እስካሁን የኢ484ኬ ለውጥ የታየባቸው የቢ.1.1.7 አይነቶች ቁጥር በጣም አነስተኛ ቢሆንም ወደፊት ሊኖራቸው የሚችለው ስርጭት ግን አሳሳቢ ሆኗል፡፡
ምንጭ፡ Live Science

የኤች.አይ.ቪ ቅድመ መከላከያ መድሃኒቶችን በማዳረስ አፍሪካ እየመራች ነው
====================
በዓለም ዙርያ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በኤች.አይ.ቪ የመያዝ ዕድልን የሚቀንሰውን የፕሪ ኤክስፖዠር ፕሮፊላክሲስ ወይም ፕሬፕ (PrEP) መድሃኒት በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፡፡ ታድያ ቀድሞ በዋናነት የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎች የነበሩት ምዕራባውያን ሀገራት የነበሩ ቢሆንም አሁን ግን ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት ያሉት የመድሃኒቱ ተጠቃሚ አፍሪካዊያን ቁጥር በፍጥነት አድጎ ከአጠቃላይ ተጠቃሚው ቁጥር ከግማሽ የሚልቀውን ድርሻ ሊይዝ ችሏል፡፡
መረጃው ይፋ የሆነው ከሳምንት በፊት የኤች.አይ.ቪ መከላከል ላይ አተኩሮ በተሰናዳ የጥናት ኮንፈረንስ ላይ ነው፡፡ መረጃውን ያቀረበችው መቀመጫውን ኒው ዮርክ አድርጎ በኤች.አይ.ቪ መከላከል ላይ ከሚሰራው የኤድስ ክትባት ተሟጋች ዓለም አቀፍ ትብብር ድርጅት (AVAC) የመጣችው ኬት ሴጋል የፕሬፕ መድሃኒቶች አጠቃቀም ከቀደመው ዓመት ሲነፃፀር በአውሮፓውያኑ 2020 በ300,000 ሰው ማደጉን ተናግራለች፡፡ ከሰሃራ በታች አፍሪካም እ.አ.አ በ2016 4,154 ብቻ የነበረው የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎች ቁጥር በ2020 517,000 ደርሷል፡፡ በመድሃኒቱ ተጠቃሚነት ዓለምን ከሚመሩት 10 ሀገራት ውስጥም 7ቱ በዚሁ የአፍሪካ ክፍል ያሉት ናቸው፡፡ ደቡብ አፍሪካ የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎቿን ቁጥር ከ100 ሺህ ያሻገረች ሲሆን ኬኒያም በ83 ሺህ ትከተላታለች፤ ዛምቢያና ዩጋንዳም በቅርብ ርቀት ተቀምጠዋል፡፡
ለዚህ የተጠቃሚዎች ማሻቀብ በዋና ምክንያትነት የተጠቀሱት በሰሃራ በታች አፍሪካ ቀዳሚው የኤች.አይ.ቪ ስራዎች ድጋፍ ሰጪ በሆነው የአሜሪካን መንግስት መዋለ ነዋይ ፈሰስና የአካባቢው ሀገራት ቁርጠኝነት ነው፡፡ የአካባቢው ሀገራት መድሃኒቶቹን እንደ ሴተኛ አዳሪዎች ላሉ ከፍተኛ የቫይረሱ ተጋላጭነት ላላቸው ወገኖችም ሆነ ለተቀረው ህዝብ በማዳረስ ረገድ ስኬታማ መሆናቸው ተነግሯል፡፡ በተጨማም አሁንም መድሃኒቱን በመድሃኒት ቤቶች እንዲገኝ በማድረግና በህዝቡ ላይም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት የተጠቃሚዎችን ቁጥር ከዚህ በበለጠ ማሳደግ እንደሚቻል ተገልጿል፡፡
በአፍሪካ የበሽታ ቁጥጥር ማዕከል ሚሰራው ጆን ኒኬንጌሶንግ አሁን ላይ ያለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ እነዚህን ጥረቶች ሊጎዳ እንደሚችል ይናራል፡፡ ኮቪድ-19 የኤች.አይ.ቪን ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ የጤና ስራዎች ላይ ተፅዕንዖ ማሳደሩን የሚናገረው ጆን “በዚህኛው ዓመት በፕሬፕ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕንዖ እንደሚኖር እጠረጥራለሁ” ሲል ስጋቱን ገልጿል፡፡ ሆኖም ከዚህ በተቃራኒ በአውሮፓውያኑ 2016 76 ብቻ ከነበረው የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎቿ ቁጥር በ2020 ወደ 32 ሺህ ማሳደግ የቻለችው ናይጄሪያ ለተቀናጀ የኤች.አይ.ቪ መከላከል ጥረቷ ምስጋና ይግባና ቁጥሩን በመጪው ዓመትም መጨመር እንደምትችል በሀገሪቱ የጤና ማማከር ስራ ላይ የተሰማራው ኤፒአፍሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢፌኒ ንሶፎር ይናገራሉ፡፡
ምንጭ፡ New Scientist

የመዘንጋት ችግር በኮቪድ የመሞትን እድል እንደሚያሰፋው በጥናት ተረጋገጠ
*****************************
በአሁኑ ሰዓት አለማችን የኮቭድ ክትባትን ለሁሉም ለማዳረስ በትጋት እየሰራች ትገኛለች፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ተመራማሪዎች በወረርሽኙ እጅግ ተጠቂ የሆኑትን ሰዎች ለመለየት የተለያዩ ጥናቶችን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በዚህም አንድ በኮቪድ የተያዙ 7400 ሰዎች የተሳተፉበትና በኒዮርክ የተካሄደ ጥናት የመዘንጋት ህመም ያለባቸው ሰዎች ይህ ችግር ከሌለባቸው ሰዎች ሶስት እጥፍ ለቫይረሱ ተጋላጭ እንደሆኑ አሳይቷል፡፡
በዚህም ጥናቱ schizophrenia እየተባለ በሚጠራው የመዘንጋት በሽታ ሰዎች በቫይረስ ለሚተላለፉ በሽታዎች ተጋላጭ እንዲሆኑ የሚያደርግ ምክንያት እንደሚኖረው ተገምቷል፡፡ በኒዮርክ ዩኒቨርሲቲ ላንጎን ሜዲካል ሴንተር የስነ አዕምሮ ሀኪም የሆኑት ካትሊን ኔማኒ የጥናቱ ውጤት በመዘንጋት በሽታ የተያዙ ሰዎች ለኮቪድ 19 ውጤቶች እጅግ ተጋላጭ እንደሆኑ አመልክቷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሀኪሟ አክለውም ከዚህ ውጤት በመነሳት የክትባት እደላው የታማሚዎችን የአእምሮ ጤና መሰረት ያደረገ ሊሆን እንደሚገባው ሀሳባቸውን አስቀምጠዋል፡፡
አራት ሆስፒታሎችን የሚያካትት ከኒውዮርክ ላንጎን የጤና ስርዓት የህክምና መዝገቦችን በማረጋገጥ ቡድኑ በመጋቢት እና በግንቦት 2020 መካከል COVID-19 የተያዙ 7,350 ጎልማሳዎችን ለይቷል ፡፡ ከእነዚህም መካከል 75 በመቶ የሚሆኑት በመዘንጋት በሽታ የተጠቁ ናቸው፡፡
ምንም እንኳን ቀደም ሲል የተደረጉ ጥናቶች የአእምሮ ችግር ያላቸው ግለሰቦች በበሽታው የመያዝ ዕድላቸው ሰፊ እንደሆነ ቢታመንም እንደ ጭንቀት ያሉ የስሜት መቃወስ ያሉባቸው ሰዎችም በCOVID-19 የመሞት ዕድላቸው ከፍ ያለ እንዳልነበረ ይታመናል፡፡ ስኪዞፈሪንያ ያለባቸው ሰዎች ከሌለባቸው ሰዎች በኮቭድ 19 በ2.67 እጥፍ የመሞት እድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡
በጥናቱ እንደ እድሜ፣ ጾታ፣ ዘር፣ ስኳርና የልብ በሽታ ያሉ ችግሮች ተካትተው መረጃ የተሰበሰበባቸው ሲሆን ስኪዞፈሪንያ ከእድሜ ቀጥሎ በኮቪድ የመሞት እድልን የሚያፋጥን ምክንያት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ እነዚህ ታካሚዎች ቀድሞውኑ ለአደጋ ተጋላጭ ከሆኑት የህብረተሰብ አባላት መካከል ናቸው እና ምናልባትም በዓለም ዙሪያ በአብዛኛዎቹ የጤና አጠባበቅ ሥርዓቶች ያልተረዱ ናቸው ፡፡
ከኤድንበርግ ዩኒቨርሲቲ ክሊኒክ ሳይካትሪስት ባለሙያ የሆኑት ዴቪድ ኦዌንስ እንደተናገሩት ጥናቱ “እንደ ስኪዞፈሪንያ ያሉ የረጅም ጊዜ የአእምሮ ሕመሞች ያሉባቸው በሽተኞች የተጋለጡበትን የጤና እና ማህበራዊ እኩልነት ችግር በምሳሌነት ሊገልጽ ይችላል” ብለዋል ፡፡
ምንጭ Science Alert