በከፍተኛ መጠን እየቀለጠ ያለው የአለማችን በረዶ
********************************
አንድ አዲስ ጥናት በአለማችን ላይ ያለው በረዶ በከፍተኛ መጠን እየቀለጠ መሆኑን ይፋ አደረገ፡፡ በጥናቱም አለማችን ከ1994 እስከ 2017 ድረስ 28 ትሪሊዮን ቶን የበረዶ ግግርን እንዳጣች አሳውቋል፡፡ ይህ በሌላ አገላለጽ መቶ ሜትር ውፍረት ያለው ሙሉ እንግሊዝን ሊሸፍን የሚችል የበረዶ ንጣፍ ማለት ነው፡፡ ጥናቱም የሳተላይት መረጃን በመጠቀም የተሰራ እንደሆነ ተገልጧል፡፡
በሊድስ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት የሚመራው ጥናት ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ውስጥ በአለማችን ያለው የበረዶ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እየቀለጠ እየጠፋ እንደሆነ የሚያሳይ መረጃን ይዞ ወጥቷል፡፡ የቅልጠት መጠኑም በ90ዎቹ በየአመቱ 0.8 ትሪሊዮን ቶን ያክል ሲሆን ከዚያ ወዲህ እስከ 2017 ደግሞ በ1.3 ትሪሊዮን ቶን በየአመቱ የተለካ ነው፡፡ ይህ የበረዶ መቅለጥ በአለማችን ውስጥ የሚገኘውን የባህር ጠለል ልክ ከፍ በማድረግ የጎርፍ አደጋ ስጋትን እየጨመረው ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ የተፈጥሮ ሀብት መጥፋትን እያስከተለ ይገኛል ሲል ጥናቱ አመልክቷል፡፡
በእንግሊዙ የተፈጥሮ ሀብት ምርምር ካውንስል እየተደገፈ የሚሰራው ምርምር ባለፉት 23 ዓመታት በተሰራ ተከታታይ ጥናት የበረዶ ቅልጠት መጠኑ በ65 በመቶ ከፍ ማለቱን አሳይቷል፡፡ በጥናቱ ውስጥ ከፍተኛ የበረዶ ክምችት የሚገኝባቸው የአለማችን ሀገራት የተካተቱ ቢሆንም የቅልጠት መጠኑ ከፍ ብሎ የታየው በአንታርቲካ እና በግሪን ላንድ ነው፡፡ የበረዶ ግግሩ የሚቀልጥባቸው ሁለት ምክንያቶች ሲኖሩ አንደኛው ከከባቢ አየር ጋር የተያያዘው atmospheric melting የሚባለው ሲሆን 68 በመቶ ድርሻ ያለው ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ መሰረቱን በውቅያኖሶች ላይ ያደረገውና የ32 ድርሻ ያለው oceanic melting ነው፡፡
ከላይ በተገለጸው የቁጥር መረጃ እንደምረዳው የከባቢ አየር ሙቀት መጨመር በአለማችን ላለው የበረዶ ግግር መቅለጥ ከፍተኛውን ድርሻ እየወሰደ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በውቅያኖሶች ላይ ያለውን በረዶ እያቀለጠ የውቅያኖስ ውሃ ከፍተኛ የሆነ የፀሐይ ብርሃን እንዲያገኝ ያደርገዋል፡፡ የውቅያኖስ ውሃ መሞቅ ደግሞ የአርክቲክ ሙቀት ከመቸውም ጊዜ በላይ እንዲጨምር አድጎታል፡፡ እስካሁን በተሰራው ጥናት በሰሜን ንፍቀ ክበብ የሚገኘው በረዶ ከጠቅላላው 58 በመቶውን ሲሸፍን ቀሪው 42 በመቶ ደግሞ በደቡብ ንፍቀ ክበብ የሚገኝ ነው፡፡
ምንጭ PHYS.ORG

በምድር ላይ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ኢንተርኔት ከማግኘታቸው በፊት ጨረቃ የ4G ኢንተርኔት ይኖራት ይሆን
----------------------------------------
ከጥቂት ጊዜያት በፊት ኖኪያ የተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ናሳ በጨረቃ ላይ ለሚያካሂደው የአርተሚስ ፕሮግራም (Artemis program) የ 4G LTE የበይነ መረብ ግንኙነት እንዲዘረጋ መታጨቱ ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ በሁለቱ ኩባንያዎች የተደረሰው ስምምነት ለምድር ብቸኛ የተፈጥሮ ሳተላይት በሆነችው ጨረቃ ላይ የ 4G LTE የበይነ መረብ ግንኙነት ለመዘርጋት የሚያስችል የ14.1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ውልም የተካተተበት ነው፡፡
እንደአውሮፓውያኑ በ2022 ይጠናቀቃል የተባለለት የሁለቱ ኩባንያዎች በጨረቃ ላይ የ 4G ግንኙነት የመዘርጋት ስራ በታቀደው መሰረት የሚካሄድ ከሆነ በጨረቃ ላይ ሊገነባ የሚችለው ይህ ፈጣን የአውተር-መረብ ግንኙነት በምድር ላይ የሚኖሩ 4.5 ቢሊዮን ሰዎች ይህን የመሰለ የበይነ መረብ ግንኙነት ከማግኘታቸው በፊት የሚዘረጋ ፈጣን የበይነ መረብ ግንኙነት ይሆናል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ በአይ ቲ እና በሳይበር ደህንነት መፍትሄዎች ላይ ላይ አዳዲስ መረጃዎችን የሚያወጣው Cisco በቅርቡ ይፋ እንዳደረገው ከአለም አጠቃላይ ህዝብ የበይነ መረብ ግንኙነት ሽፋን ያለው ህዝብ 56 በመቶው ወይም 4.1 ቢሊዮን የሚሆነው ህዝብ ሲሆን ይህ አሃዝ እስከ 2020 መጠናቀቂያ ድረስ ያለውን የሚያካትት ነው፡፡ እንደተቀቋሙ ትንበያ በ2023 የበይነ መረብ ግንኙነት ተደራሽ የሚሆንለት የአለም ህዝብ 5.3 ቢሊዮን የሚሆነው ሲሆን ይህም 2/3ኛውን የአለም ህዝብ ይሸፍናል፡፡
Cisco ብትንበያው ያስቀመጠው የበይነ መረብ ተደራሽነት እንደ 4G ያለ ጥራት ያለው የበይነ መረብ ግንኙነት ሳይሆን በ 2G እና 3G መካከል ያለ መደበኛ የበይነ መረብ ግንኙነት ነው፡፡ በአንፃሩ በ2022 ይጠናቀቃል የተባለለት የሁለቱ ተቋማት ተልዕኮ እጅግ ፈጣን ከሚባለው የ5G ስርዓት በአንድ ደረጃ ብቻ ዝቅ ያለውን ፈጣን የ4G ስርዓት የሚስተዋውቅ ሲሆን በጨረቃ ላይ ለሚካሄደው ፈጣን የመረጃ ልውውጥ ትልቅ መሰረት በመጣልም በምድር ላይ የሚኖሩ ብዙ ቢሊዮን ሰዎች ለግንኙነቱ ተደራሽ ከመሆናቸው በፊት ጨረቃን የ4G ባለቤት የሚያደርጋት ልዩ ተልዕኮ ይሆናል ፡፡
ይህ የበይነ መረብ ተደራሽነት ከአጠቃላዩ የአለም ክፍል በአፍሪካ እና በእስያ በዝቅተኛ ደረጃ መገኘቱ የሚታወቅ ሲሆን ዘርፉን ይበልጥ እንዲሰራራ ለማድረግም ከፖሊሲና ከህግ ማዕቀፎች አንስቶ አስፈላጊ የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴዎችን በማስፋፋት እና ሌሎች የማሻሻያ ስራዎችን በማካሄድ ዝርፉን ይበልጥ ማሳደግ እንደሚቻል በብዙዎች ይገለጻል፡፡
ምንጭ፡ Truth theory

የመስኖ ፕሮጀክቶቻችን ተደጋጋሚ ውድቀት
======================
ኢትዮጵያን ጨምሮ በ24 የሰሃራ በታች አፍሪካዊያን ሀገራት ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ የተተገበሩ ትላልቅ የመስኖ ልማት ስራዎች ቃል በተገባላቸው መሰረት ውጤታማ ለመሆን አለመቻላቸውን የኔቸር ጆርናል ላይ የወጣ አዲስ ጥናት አመላከተ፡፡ የእንግሊዙ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ማንቼስተር ምሁራን በአካባቢው ከአውሮፓውያኑ 1948 እስከ 2008 ድረስ ባሉት 60 ዓመታት ውስጥ የተተገበሩ 79 የመስኖ ፕሮጀክቶችን (አምስቱ ከኢትዮጵያ) ቀዳሚ ውጥን የሚያስቀምጥ መረጃ ያሰባሰቡ ሲሆን በመቀጠልም የሳተላይት መረጃን በመጠቀም የመስኖ ልማት ስራዎቹ ምን ያህል መሬትን ማልማት እንደቻሉ አመሳክረዋል፡፡
በውጤቱ ማረጋገጥ እንደቻሉት የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶቹ አስከፊ ሊባል በሚችል መልኩ ቀድሞ ከተቀመጠላቸው ግብ እጅግ ያነሰ ውጤትን አሳይተዋል፡፡ በዚህም ፕሮጀክቶቹ ሲወጠኑ እንሸፍነዋለን ካሉት መሬት ውስጥ በአማካኝ ማልማት የቻሉት 16 በመቶ የሚሆነውን ብቻ ሲሆን ቀድሞ ካቀዱት መሬት ከ80 በመቶ በላዩን መሸፈን የቻሉት ፕሮጀክቶች ቁጥር ደግሞ ከ20 አይበልጥም፡፡ በተጨማሪም ከ79ኙ ፕሮጀክቶች 16ቱ ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጡ ሆኗል፡፡ ነገሩን አሳዛኝ የሚያደርገው በ60 ዓመታቱ ውስጥ ምንም አይነት የውጤት መሻሻል እየታየ አለመሄዱ ነው፡፡
ይህ ውድቀት ከፕሮጀክቶቹ ግዝፈት አልያም ከአካባቢው የአየር ንብረት ለውጥ ጋራ የተያዘ አይደለም፡፡ ከዚህ ይልቅ የሀገራቱ የፖለቲካ አለመረጋጋት ቀዳሚው መንስዔ መሆኑን የጥናት ቡድኑ ያምናል፡፡ የተረጋጋ አስተዳደር ያለባቸው ሀገራት የሚገኙ ፕሮጀክቶችም የውድቀት ዕድላቸው አነስ ያለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በሌላ መልኩ ፕሮጀክቶቹ ሲወጠኑ የምግብ ደህንነትን ከማረጋገጥ በዘለለ ምጣኔ ሀብታዊ ዓላማን ባለማንገባቸው ዝቅተኛ የገበያ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን በመስጠት ተገድበዋል፡፡ በተጨማሪም ፕሮጀክቶቹ ሲታቀዱ በተዛባ አውንታዊ አመለካከት የተሞሉ እና ፖለቲካውም በወረቀት ላይ ትርፍን የሚያሳዩትን በመሻቱ ሳብያ መሬት ላይ ያለውን ዕውነት የሚመለከቱ ካለመሆናቸው በተጨማሪ ስራዎች በዋናነት የሚመሩት ቴክኒካል ዕውቀት፣ ከባቢያዊ ግንዛቤ እና የገንዘብ አቅርቦት በሚያጥራቸው ማዕከላዊያን የመንግስት ሰራተኞች ነው፡፡
ሆኖም በአካባቢው አሁንም ተረጋግተው እንደሀገር መቆም በተሳናቸው ሀገራት ጭምር እነዚህ በሄክታር (የሚለማ መሬት) በአማካኝ 20 ሺህ ዶላር ወጪን የሚያስወጡ መሰል ፕሮጀክቶች በስፋት ተወጥነው እየተሰራባቸው ይገኛሉ፡፡ መንግስታት እና ዓለም አቀፍ ተቋማትም በአካባቢው ትላልቅ የመስኖ ስራዎች ላይ ገንዘብ ፈገሰስ በማድረግ እንደ ውሃ ማስተላለፍያና ግድብ ያሉትንም እየሰሩ ናቸው፡፡ ይህንንም ተከትሎ ግዙፍ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ከፍተኛ የገንዘብ ወጪን የሚያስወጡና በአካባቢው ህዝብ ላይም ቀላል የማይባል ተፅዕንዖን የሚያደርሱ እንደመሆናቸው መጠን ፕሮጀክቶቹን ወጪ ቆጣቢና በዘላቂነት ከአከባቢያቸው የተስማሙ ለማድረግ ከዚህም በላይ ጥልቅ ጥናቶች ያስፈልጋሉ ሲሉ የዚህ ጥናት ባለቤቶች ምክራቸውን መለገሳቸውን ጥናቱን አስመልክተው በኔቸር እና ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ማንቼስተር የወጡት ዘገባዎች ያመላክታሉ፡፡ ሙሉ ጥናቱን በ nature መፅሄት ያገኛሉ

በሰው ሰራሽ ማዳቀል የተወለደው የአንበሳ ደቦል
***********************
በሲንጋፖር ሰው ሰራሽ የማዳቀል ዘዴን በመጠቀም የአንበሳ ደቦል መወለዱ ተነገረ፡፡ ሲንጋፖር ለከተማዋ የመጀመሪያ የተባለለትን ሲምባ የተሰኘ የአንበሳ ደቦል ወደ እንስሳት ማቆያዋ ተቀብላለች፡፡ ከዚህ በፊት በ2018 በደቡብ አፍሪካ ተመሳሳይ የማዳቀል ስራ ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለት የአንበሳ ደቦሎች የተሞከረ ሲሆን ለአንበሳ ዝርያ የማዳቀል ስራ ብዙውን ጊዜ ያልተለመደ ነው፡፡
ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በአለማችን ያለው የአንበሶች ቁጥር በ40 በመቶ ያሽቆለቆለ ሲሆን እንደ አለማቀፍ የተፈጥሮ ጥበቃ ህብረት መረጃ ከሆነ በአሁኑ ወቅት ከ23,000 እስከ 39,000 አንበሶች በምድራችን ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ሲምባ የተሰኘው የሲንጋፖር የአንበሳ ግልገል ከአንድ እድሜ ጠገብ የአፍሪካ አንበሳ በተወሰደ ዘር የተዳቀለ ነው፡፡ የዚህ አንበሳ ስያሜ በዲዝኒ አኒሜሽን ፊልም (ዘ ላዮን ኪንግ) ካለው ዋና ገጸ-ባህሪ የተወሰደ ነው፡፡
በሚያሳዝን ሁኔታ የሲምባ አባት ሙሳፋ እጅግ ተዳክሞ የነበረ በመሆኑ የማዳቀል ስራውን እንዳልተቋቋመው የእንስሳት ጥበቃ ተቋሙ ተናግሯል፡፡ ሙሳፋ በተመሳሳይ ስሙን የወረሰው በእንስሳት ዙሪያ ከተሰራ የአኒሜሽን ፊልም ነው፡፡
ባሳለፍነው ጥቅምት ወር የተወለደው ሲምባ በእናቱ ካይላ እና በእንስሳት ጥበቃ ተቋሙ ሰራተኞች ጥበቃ እና እንክብካቤ እየተደረገለት ነው፡፡

በስልክ ንግግር ወቅት አላስፈላጊ ድምፆችን የሚያስወግደው መተግበሪያ
--------------------------------------
ባለፈው አመት ኮቪድ-19 ይዞት በመጣው መዘዝ ምክንያት ብዙዎች ከቤታቸው ሆነው ስራዎችን እንዲያካሂዱ ተገደው ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ከስራ ጋር የተያያዙ የመረጃ ልውውጦችን ለማካሄድ አንደ መደበኛ ስልክ፣ የቪዲዮ ኮንፈረንስ እና ሌሎች የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ታዲያ በዚህ የግንኙነት ሂደት ውስጥ ብዙዎች ሲቸገሩበት የነበረው ጉዳይ ባሉበት አካባቢ በሚሰሙ አላስፈላጊ ድምፆች ወይም (noises) የስልክ ግንኙነታቸው ተደጋግሞ መቋረጡ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ብዙዎቻችን መደበኛ ስልክ በምንጠቀምበት ወቅትም በተደጋጋሚ የሚያጋጥመን ችግር ሲሆን አዲሱ መተግበሪያም ቀላል መፍትሄን ያበጀ ይመስላል፡፡
the Krisp noise cancelling app በሚል የተሰየመው ይህ መተግበሪያ በመላው አለም ከሚገኙ ቴሌኮሚዩተሮች ጋር በጋራ ለመስራት በመቻሉ በቤታቸው ሆነው የሚሰሩ ሰዎች በመተግበሪያው የጠራ የድምፅ ሲስተም ወይም (crystal-clear audio) አማካኝነት ቤቶቻቸውን ፀጥ ወዳለ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለመቀየር ያስችላቸዋል፡፡ መተግበሪያው ከ800 በላይ በሚሆኑ አንደ ዙም፣ ስካይፒ እና ሚት ባሉ የመገናኛ መተግበሪያዎች ላይ መጠቀም የሚቻል ሲሆን በስልክ ንግግር ወቅት ከሁለቱም አካላት የሚሰሙ አዋኪ ድምፆችን ለይቶ ለማስወገድም የሚያስችል ነው፡፡
ይህ መተግበሪያ አላስፈላጊ ድምፆችን አጣርቶ ለማስወገድ የሚችለው በተገጠመለት ጥልቅ የነርቭ አውታረመረብ ወይም (Deep Neural Network) አማካኝነት ሲሆን ይህም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓት ውስጥ ውስብስብ ከሚባሉት ቴክኖሎጂዎች አንዱ ነው፡፡ መተግበሪያውን የሰሩት ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት አዲሱ መተግበሪያ ከሌሎች ተመሳሳይ ምርቶች የሚለይበት ዋና ምክንያት ከሚጠቀመው ውስብስብ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓት በተጨማሪ 20 ሺህ ድምፆችን እና 50 ሺ ተናጋሪዎችን በአንድ ጊዜ ለመለየት በመቻሉ ነው ይላሉ፡፡ ይህ ደግሞ እስካሁን ከተሰሩት አላስፈላጊ ድምፅ ማስወገጃ (noise cancelling) ስርዓቶች በቀዳሚነት አንዲቀመጥ ያስቸላዋል፡፡
የመተግበሪያው የአሰራር ሂደት ለተጠቃሚዎች ብዙ አማራጮችን እንዲያገኙ የሚስችላቸው ሲሆን ከግላዊ ጥበቃ ጋር በተያያዘም ምንም አይነት ክፍትት እንዳይኖርበት ተደርጎ መሰራቱን ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡
ምንጭ፡ Futurism

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
============
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከዚህ በታች ለተገለፁት የስራ መደቦች ስራ ፈላጊዎችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡
የምዝገባ ቦታ፡- አራት ኪሎ ከፓርላማ ፊትለፊት ከሚገኘው የትራፊክ መብራት ወረድ ብሎ፣ አልያም በ http://recruit.techin.gov.et/ በመግባትና ቅድሚያ ሬጂስተር በማድረግ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
የመመዝገቢያ ቀን፡- ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 28 2013 ድረስ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ
በምዝገባ ወቅት መቅረብ የሚገባቸው ማስረጃዎች፡- ለሁሉም የስራ መደቦች የትምህርትና አግባብ ያለው የስራ ልምድ ማስረጃዎች ዋናውና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ
መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የተሰጡ የስራ ልምዶች ተቀባይነት የሚኖራው ተገቢውን የመንግስት ግብር መከፈሉን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ሲቀርቡ ብቻ ነው፡፡
ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በ0118547758 ይጠቀሙ
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት

10 ሳይንስና ታሪክ ነክ የአለማችን አስደናቂ እውነታዎች
====================
1. ረዘም ያለ የምግብ አብሳዮች ወይም ሼፎች ኮፍያ በጎኑ በኩል 100 እጥፋቶች ያሉት ሲሆን ይህም እንቁላልን ማዘጋጀት የሚቻልባቸውን 100 መንገዶች ያመለክታል፡፡
2. ከአለማችን ቢራ አምራቾች መካከል የሆነው ጊነስ በእንግሊዝ ብቻ 93,000 ሊትር ቢራ ባለ ረጃጅም ጺም ሰዎች በሚጠጡበት ጊዜ ወደ ጺማቸው ገብቶ እንደሚባክን ግምቱን አስቀምጧል፡፡
3. የእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤት ሁለተኛ የተዋጣላት መካኒክ ነበረች
4. በሲውዲን ሃገር የሚገኙ ደም ለጋሾች የለገሱት ደም ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ የምስጋና መልእክት ይደርሳቸዋል፡፡
5. የአለማችን እውቁ ጠፈርተኛ ኒል አርምስትሮንግ የስራ ማመልከቻ ያስገባው ለማመልከት ከተሰጠው ቀን አንድ ሳምንት ዘግይቶ ነበር፡፡
6. ውሻዎች እስከ 250 ቃላትንና ምልክቶችን የመረዳት ብቃት አላቸው፡፡ የውሾች አማካኝ የአእምሮ አቅም ከሁለት ዓመት ህጻን ልጅ ጋር ይወዳደራል፡፡
7. የሳሙና አረፋ የመታጠቢያ ውሃ ለረጅም ጊዜ ሳይቀዘቅዝ እንዲቆይ ማድረግ ያስችላል
8. ረጅም እግር ባላቸው ፍላሚንጎ በሚባሉ የወፍ ዝርያዎች እግር መካከል ያለው እጥፋት ጉልበት ሳይሆን እንደ አልቦ አይነት ጌጥ ነው
9. በ1967 በናይጀሪያ የርስበርስ ጦርነት ወቅት በተዋጊዎቹ መካከል ለሁለት ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርጎ ነበር፡፡ ለዚህም ምክንያቱ እውቁ የእግር ኳስ ኮከብ የሚያደርገውን ጨዋታ ለመመልከት ነበር፡፡
10. የጎግል መስራች በ1999 ድርጅቱን ከ1ሚሊዮን ዶላር በታች በሆነ ዋጋ ለመሸጥ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ገዥ የሆነው ድርጅት አያዋጣኝም ብሎ ትቶታል፡፡
ምንጭ Mental floss

አዲሱ ቲክቶክ?
=======
ከቲክ ቶክ ጋራ በቀጥታ እንዲሚፎካከር የሚጠበቀው አዲሱ የጎግል የቪዲዮ መጋሪያ ድረ ገፅ “ዩትዩብ ሾርትስ” ህንድ ውስጥ እያደረገ ባለው ሙከራ በየዕለቱ 3.5 ቢሊዮን ተመልካቾችን እያስተናገደ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የዩትዩብ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሱዛን በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ምርቱን ወደተለያዩ ገበያዎች ለማዳረስ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
በጉግል ባለቤትነት ስር ያለው ዩትዩብ አዲሱን የአጫጭር ምስሎች መጋሪያ ገፁን ይፋ ያደረገው ከወራት በፊት መስከረም ላይ ነበር፤ በ15 ሴኮንዶች ውስጥ እራስን የመግለጫ መንገድ ነው በሚል፡፡ ገፁ ከዩትዩብ ጋራ በቀጥታ እንዲተሳሰር የተደረገም ሲሆን አሁን ግን የሙከራ አገልግሎቱን እየሰጠ ያለው ህንድ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ዩትዩብ ሾርትስ ጉግልን በዓለም ዙርያ አንድ ቢሊዮን ያህል ተጠቃሚዎችን ካፈራው ቲክ ቶክ ጋራ ተፎካካሪ ለማድረግ ተወጥኖ የተዘጋጀ ነው፡፡
ነገር ግን ከቲክ ቶክ ጋራ የሚፎካከር አማራጭ ይዞ የመጣው ጎግል ብቻ አይደለም፤ ባሳለፍነው ነሀሴ በፌስቡክ ባለቤትነት የሚተዳደረው ኢንስታግራምም ሪልስ የተባለውን የአጭር ቪዲዮ ምስል መመልከቻ ገፅ ይፋ አድርጓል፡፡ ስናፕ ቻትም በበኩሉ ስፖትላይት የተሰኘውን ምርቱን ይፋ አድርጓል፡፡
በቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ባይትዳንስ ስር የሚገኘው ቲክቶክ ከነዚህ አዳዲስ ፉክክሮች በተጨማሪ በተወሰኑ መንግስታት አለመወደድንም አፍርቷል፡፡ ህንድ መተግበሪያውን ከሰኔ አንስቶ ያገደቺው ሲሆን ይህ በቲክቶክ እና ሌሎች የቻይና መተግበሪያዎች ላይ የተላለፈው እገዳዋ ዘላቂ እንደሚሆን አስታውቃለች፡፡ የቀድሞው የአሜሪካን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕም ለቻይና የስለላ ስራን ይሰራል ሲሉ የከሰሱት ሲሆን ለማገድ ዝተው ነበር፡፡
ምንጭ፡ Tech Xplore

የአለማችን የመጀመሪያው የቤት ውስጥ ባለ 5G አንቴና
**************************
በኮሪያ የሚገኙ ተመራማሪዎች የበይነ መረብ ተጠቃሚዎች የአምስተኛ ትውልድ ኔትወርክን በቤት ውስጥ መጠቀም የሚያስችላቸውን ስልት ማበልጸጋቸው ተሰማ፡፡ ይህ ቴክኖሎጂም የአምስተኛ ትውልድ የበይነ መረብ አገልግሎትን መዳረሻ ለማስፋት የሚደረገውን ስራ እጅግ እንደሚያግዘው ተነግሮለታል፡፡
በኮሪያ የሚገኘው የኤሌክትሮኒክስ እና የቴሌኮሚኒኬሽን ምርምር ተቋም ይህን በአለማችን የመጀመሪያ የሆነውን ግኝት በስኬት መስራቱን ሲያስተዋውቅ ከዋና ማሰራጫ 28GHz የ5G ሲግናልን ወደ ተለያዩ ህንጻዎች ማስተላለፍ የሚያስችል የአንቴና ስርዓት መሆኑን ገልጧል፡፡
በዓለማችን ውስጥ አገልግሎት ከሚሰጠው የሞባይል ዳታ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆነው ጥቅም ላይ የሚውለው በቤት ውስጥ እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ አዲሱ ቴክኖሎጂ 20Gbps በሚደርስ ፍጥነት እንደ አየር መንገድ፣ የባቡር ጣቢያዎችና ትልልቅ የንግድ ማእከላት የአምስተኛ ትውልድ በይነ መረብ አገልግሎትን መጠቀም ያስችላል፡፡
ቴክኖሎጂው በተጨማሪም የ5G ገመድ አልባ ሲግናሎችን ወደ ኦፕቲካል ሲግናሎች መለወጥ የሚያስችል ሲሆን ያለምንም መቆራረጥ እስከ 5 ኪሎሜትሮች ድረስ ማስተላለፍ ያስችላል፡፡
በህንጻዎች ጣሪያ ላይ የሚገጠመው መሳሪያው በአካባቢው ካለ የ5G ሲግናልን በመውሰድ በገመድ ወደሚተላለፍ ሲግናል በመቀየር በተገጠሙለት ብዙ አንቴናዎች አማካኝነት ሲግናሉን ወደ ህንፃው የተለያዩ ክፍሎች ያሰራጫል፡፡
ምንጭ Tech Xplore