አስገራሚው የአለም ክብረ-ወሰን
*********************
እንግሊዛዊው ግብ ጠባቂ ከረጅም ርቀት የተቆጠረች የአለማችን ብቸኛ ጎል ባለቤት በመሆን በአለም የክብረወሰን መዝገብ ውስጥ ስሙን አስፍሯል፡፡ ኒውፖር ካንትሪና ቼልተንሃም ከተማ ባደረጉት የእግር ኳስ ጨዋታ አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
በዚህ ጨዋታ የኒውፖርት ካንትሪው ግብ ጠባቂ ቶም ኪንግ ያስቆጠራት ግብ በአለማችን ከረጅም ርቀት የተቆጠረች በመሆን በክብር መዝገብ ውስጥ ሰፍራለች፡፡ ርቀቱም 96.01 ሜትር ተለክቷል፡፡ ያኛው ግብ ጠባቂ ምን የከበደ ነገር ገጥሞት ይሆን ሳያስብል አይቀርም፡፡
ቶም ኪንግ ኳሷን ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል መስመር ላይ አስቀምጦ እንደለጋት የገለጸው የመረጃ ምንጫችን መረብ ላይ ካረፈች በኋላ ነበር የቼልተንሃሙ ግብ ጠባቂ ኳሷን ማየት የቻለው፡፡
ከዚህ በፊት ለስቶክ ሲቲ ይጫወት የነበረው ቤጎቪክ ሳውዛምተን ላይ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2003 ያስቆጠራት ግብ በ91.9 ሜትር የአለምን ክብረ ወሰን ይዛ ነበር፡፡
ምንጭ Ginuss World Record

አዲሱ የኮሮናቫይረስ አይነት የተገኘባቸው ሀገራት ቁጥር ከ50 በለጠ
====================
መነሻው ከሀገረ እንግሊዝ ያደረገውና ባለው ከፍተኛ የመስፋፋት ፍጥነት ዓለም አቀፋዊ ስጋትን ያጫረው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ አይነት ቢ.1.1.7 እስከ ትናንት ዕለት ድረስ በ55 ሀገራት መገኘቱ ተነግሯል፡፡
የቫይረስ አይነቱ ከቀድሞዎቹ በበለጠ ገዳይ ይሁን አልያም ከአውሮፓና ሰሜን አሜሪካን ውጭ ባለው ዓለም ላይ ውስጥ ለውስጥ እየተሰራጨ ስለመሆኑ ማስረጃ ባይኖርም በተላላፊነቱ ረገድ ግን በ50 በመቶ የላቀ አቅም እንዳለው አሁን እየወጡ ያሉ ጥናቶች እያሳዩ ነው፡፡ ይህ ታድያ የበለጠ ገዳይ ቢሆን እንኳን ከሚያመጣው በላይ ከፍ ያለ ችግርን እንደሚፈጥር ይነገራል፡፡ ለምሳሌ በእንግሊዝ ውሰጥ ባለው መረጃ ተመስርተን ስናይ በአንድ ከተማ ውስጥ 10 ሺህ ሰዎች ቢያዙና እያንዳንዳቸው በአማካኝ ቫይረሱን ለ1.1 ሰዎች ቢያሰራጩ በአንድ ወር ውስጥ በቫይረሱ የሚያዘው ሰው ቁጥር 16 ሺህ ይሆናል፡፡ የሞት መጠኑንም እንዲሁ እንግሊዝ ውስጥ ባለው ላይ ተመስርተን 0.8 በመቶ ነው ብንል የመጀመሪያው የወረርሺኙ ማዕበል ላይ 128 ሰዎች ለህልፈት የሚዳረጉ ይሆናል፡፡ አዲሱ የቫይረሱ አይነት ከመሰራጨት ይልቅ በ50 በመቶ የበለጠ የመግደል አቅም ቢኖረው ኖሮ ከ16 ሺው 192 ሰዎች ይሞታሉ፡፡ ሆኖም በ50 በመቶው የጨመረው የመተላለፍ መጠኑ ከሆነና ገዳይነቱ ላይ ግን ምንም ዓይነት ለውጥ ካልታየ በአንድ ወር ውስጥ በቫይረሱ የሚያዘው ቁጥር 122 ሲሆን ከላይ በተቀመጠው የእንግሊዝ የሞት ምጣኔ መሰረት ስናሰላውም የሟቾቹ ቁጥር 976 ይደርሳል፡፡
አሁን ላይ ቢ.1.1.7 በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራትና የአሜሪካን ግዛቶች ውስጥ ለውስጥ እየተላለፈ መሆኑ አሳሳቢ ሆኗል፡፡ በተቀረው አለም ግን የቫይረስ አይነቱ የተገኘባቸው ሰዎች በዋናነት የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡ ሆኖም ሀገራቱ አዲሱን የቫይረስ አይነት ከተጓዦች ላይ ብቻ የማግኘታቸው ሚምስጢር በውስጣቸው እየተሰራጨ ያለውን ቫይረስ የበራሒ ስንስሉን (genetic sequence) የመለየት ስራ ባለመስራታቸው ሊሆን ይችላል፤ ብዙ ሀገራት ይህን ተግባር ቢ.1.1.7 እስኪከሰት ድረስ ችላ ብለውት ቆይተዋል፡፡
በአንፃሩ የደቡብ አፍሪካው ቢ.1.351 ኮሮና ቫይረስ አይነት ያሳየው ስርጭት የተገደበ ነው፡፡ በአስራዎች የሚቆጠሩ ሀገራት የቫይረስ አይነቱን ማግኘታቸውን ቢያሳውቁም እስካሁን ግን ውስጥ ለውስጥ እየተላለፈ ያለው በቦትስዋና፣ ዛምቢያ እና እንግሊዝ ውስጥ ብቻ ነው፡፡
ምንጭ፡ New Scientist

ለምግብነት የሚውል ስጋን በቤተሙከራ ማበልጸግ
***********************
አዲስ የተገኘው ቀመር የቤተ ሙከራ ስጋ ተፈጥሯዊ ጣዕምና መልክ እንዲኖረው እያስቻለ መሆኑ ተነገረ፡፡ ተመራማሪዎቹ ተፈጥሯዊውን የእንስሳት ስጋ መተካት የሚችልና ጣዕሙ ከሌሎች አማራጮች ለተፈጥሯዊው የእንስሳት ስጋ የቀረበ እንደሆነ ስለ ግኝታቸው አስረድተዋል፡፡
በምርምሩ ሂደት በቤተ ሙከራ የበለጸጉ የጡንቻ ህዋሳትና የስብ ህዋሳት በአንድ ላይ ሆነው የተለያዩ ደረጃዎችን አልፈዋል፡፡ ይህ ስልትም በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት የአካል ንቅለ ተከላ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ህዋሳትን ለማበልጸግ ጥቅም ላይ ከዋለው መንገድ የተቀመረ ነው፡፡
አሁን ላይ በተለያየ መጠን ሰው ሰራሽ ስጋውን እያመረቱ እንደሆነ የተናገሩት ተመራማሪዎቹ ሰዎች ከጤናቸውና ከፍላጎታቸው ጋር የተስማማ የስብ መጠን ያለውን ስጋ መሸመት የሚችሉበት እድል እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፡፡
ወደ ዚህ ስራ እንዴት እንደገቡ ሲናገሩ ተመራማሪዎቹ ምንም እንኳን በአለማችን ላይ ያለው የስጋ ፍላጎት እየጨመረ ቢሄድም አቅርቦቱ የመቀነስ ችግር ውስጥ በመግባቱ ነው ብለዋል፡፡ ከእንስሳት እርባታ ጋር የተያያዘውን የስጋ አቅርቦት ብቻ ተማምኖ መቀመጥ አይገባም ስለዚህ እንደዚህ ያሉ አማራጫቾች መኖር አለባቸው ሲሉ አክለዋል፡፡
ምንጭ SciTechDaily

ኢትዮጵያ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት እንቅስቃሴዎቿን የቃኘው የምክክር መድረክ
===================
ከትናንት አንስቶ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው ሰው ሰራሽ አስተውሎት እንዲሁም ሮቦቲክስ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ በዛሬው መድረክም የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ገለፃዎች የቀረቡ ሲሆን እነርሱን መነሻ በማድረግም ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄና አስተያየቶች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በዕለቱ ከቀረቡት ውስጥ ቀዳሚ የነበረው ከአይኮግ ላብስ የመጡት አቶ ህሩይ ፀጋዬ “Beware of Greeks Baring Gifts: Robotics in Ethiopia” በሚል ርዕስ ያቀረቡት ሮቦቲክስ ላይ ያተኮረ ገለፃ ነው፡፡ በገለፃቸው ስለ ሮቦቶች ምንነት፣ ከቀድሞ ጊዜያት አንስቶ የነበረ አረዳድን እንዲሁም ሀገራዊ እንቅስቃሴ ላይ ያለውን ድክመት እና ዕድል አብራርተዋል፡፡ ሮቦቲክስን በተመለከተ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ዕንቅስቃሴዎች እጅግ ውስን ከመሆናቸውም ባሻገር የተሰሩ አነስተኛ ስራዎችም በኢንዱስትሪው ሊሰጣቸው ከሚገባው ቦታ በላይ ተጋኖ እንደሚወራላቸው የተናገሩት አቶ ህሩይ ዘርፉን ለማሳደግ የትምህርት ተቋማትና እና ባለድርሻዎች ተገቢውን ስራ ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በተቋማቸው አይኮግ ላብ ውስጥ የተኬዱ ርቀቶችን እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችንም ለታዳሚው በምሳሌነት አቅርበዋል፡፡
የዕለቱን ሁለተኛ ገለፃ ያቀረቡት በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ውስጥ በተመራማሪነት እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ቃልኪዳነ ገዛኸኝ ሲሆኑ እርሳቸውም በበኩላቸው በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ኢ-ኮሜርስ ግንኙነት ላይ በማተኮር ዳሰሳቸውን አጋርተዋል፡፡ በገለፃቸው የኢ-ኮሜርስ አይነት ታሪክ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ሊጫወትበት ስለሚችለው ሚና ከመጥቀስም ባሻገር በኢትዮጵያ ደረጃ ተግባራዊ መሆን ይችላሉ ያሏቸው የቴክኖሎጂው ገፅታዎችን አስቃኝተዋል፡፡ በአሁን ሰዓት 14 ያህል ኢ-ኮሜርስ ላይ አተኩረው የሚንቀሳቀሱ ተቋማት በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ያሉት አቶ ቃልኪዳን በሀገራችን በቅርቡ እያቆጠቆጠ ላለው የኢ-ኮሜርስ እንቅስቃሴ የኮቪድ-19 ወረርሺኝን ተከትሎ የመጣውን አካላዊ ግንኙነትን የመቀነስ ፍላጎትን ጨምሮ በጎ ዕድልን ፈጥረዋል ያሏቸውን ነጥቦች አስቀምጠዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ አይሲቲ ፓርክ፣ ሮቦ ሮቦቲክስ፣ መረጃና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣ ኢትዮ-ቴኬኮምን ጨምሮ ከግልና መንግስት መስሪያ ቤቶችና ከፍተኛ የትምሀርት ተቋማት የተወከሉ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡

ጁፒተር መሳይዋ ደመና አልባ ፕላኔት
***********************
ተመራማሪዎች በስነ-ፈለክ ምርምር ውስጥ የመጀመሪያ የሆነ ጁፒተርን የሚመስል ደመና አልባ ፕላኔት ማግኘታቸውን አሳወቁ፡፡ ስለ ፕላኔቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍንጭ የተገኘው በ2012 ቢሆንም ከባቢ አየሩ ግን እስካሁን ድረስ ሳይታወቅ ቆይቷል፡፡ ሞቃቱ ጁፒተር የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው በሳይንሳዊ መጠሪያው WASP-62b የሚባል ሲሆን በስርዓተ ፀሐይ ውስጥ ከሚገኘው ጁፒተር ግማሽ ያክል መጠን ሲኖረው በ575 የብርሃን ዓመት ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ፕላኔቱ ፀሐይን ለመዞር 12 ዓመት ከሚወስድበት ከጁፒተር በተቃራኒው የራሱን ኮከብ ዞሮ ለመጨረስ አራት ቀን ተኩል ብቻ ይፈጅበታል፡፡ ለኮከቡ ባለው ቅርበት የተነሳ ከፍተኛ ሙቀት አለው፡፡ ለዚህም ነው ተመራማሪዎቹ ሞቃቱ ጁፒተር ሲሉ የሰየሙት፡፡
ለምርምሩ ሃብል የተባለው የህዋ ቴሌስኮፕ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን በውስጡ የሚገኙ ንጥረ ነገሮችን ለመለየት ስፔስትሮስኮፒ የተባለ ስልትን እንደተጠቀመች ምርምሩን ያደረገችው ሙንዛ አላም ተናግራለች፡፡ ምንም እንኳን ፖታሺየም መኖርን የሚያመለክት ፍንጭ ባይኖርም ሶዲየም የተባለው ንጥረ ነገር ግን በግልጽ ይታያል ስትል አስረድታለች፡፡
ደመና አልባ ፕላኔቶችን የማግኘት እድል እጅግ ዝቅተኛ እንደሆነ የምትናገረው አላን እስካሁን ባለው ምርምር ግልጽ የሆነ ከባቢ አየር ያለው ኤግዞ ፕላኔት ሞቃቱ ሳተርን የተሰኘውና በ2018 የተገኘው WASP-96b ፕላኔት መሆኑን ገልጻለች፡፡ የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች እንዲህ አይነት ግልጽ የሆነ ከባቢ አየር ያላቸውን ፕላኔቶች ማጥናት በፕላኔቶች አፈጣጠር ዙሪያ ለሚደረገው ምርምር አጋዥ ይሆናል ብለዋል፡፡
ምንጭ PHYS.ORG

10 አስፈላጊና ነፃ የዊንዶውስ 10 መተግበሪያዎች
በ2021 ስራዎችን ይበልጥ ሊቀላጥፉ የሚችሉ እና አዳዲስ የዘመኑ ገፅታዎችን ያካተቱ የኮምፒውተር መተግበሪያዎች ሊያስፈልጉን ይችላሉ፡፡ ታዲያ ከዚህ በታች የምትመለከቷቸው 10 መተግበሪያዎች አዳዲስ ገፅታዎችን በማከል በአዲሱ የፈረንጆቹ አመት ብዙ ተጠቃሚ ያፈራሉ ተብለው የሚጠበቁ ናቸው፡፡ መረጃውን ያስነበበው ቴክራደር እነዚህ ጠቃሚ መተግበሪያዎችን እንደሚከተለው አስቀምጧል፡-
1 TestDisk
ሜካኒካል የሆነው የመረጃ ማከማቻ በተለያዩ ምከንያቶች ብልሽት በሚያጋጥመው ወቅት መረጃችንን ለማዳን የሚያስችሉ መተግበሪያዎች እጅግ ይጠቅሙናል፡፡ TestDisk ይህን መረጃ የማዳን እና የመመለስ ስራ በሚገባ ለመከውን የሚያስችል መተግበሪያ ሲሆን በ2021 በ open-source ከተመዘገቡ ጠቃሚ መተግበሪያዎች አንዱ ነው፡፡
2 Cobian Backup
ይህ መተግበሪያ ፋይሎቻችንን እንደመጠባበቂያ ለማስቀመጥ ከሚረዱ ከፍተኛ አቅም ካላቸው ነፃ የባካፕ ፓኬጅ (free backup packages) ውስጥ በቀዳሚነት የሚቀመጥ ሲሆን በ2021 ብዙ ተጠቃሚዎች ይኖሩታል ተብሎ የሚታሰብ ጠቃሚ መተግበሪያ ነው፡፡
3 Tablacus File managers
ይህ የፋይል ማስተዳደሪያ እንደ ዊንደዎስ ኤክስፕሎረር ባሉ የፋይል ማስተዳደሪያዎች ላይ የልተጨመሩ እንደ tabs ያሉ አዲስ ገፅታዎችን ያካተተ ከመሆኑም ባለፈ የፋይል ማህደሮችን በምንፈልገው መልኩ ስድሮ ለማስቀመጥ እና የማይፈለጉ ፋይሎችን ደግሞ ዲሴብል ለማድረግ የሚረዳ ነው፡፡
4 CCleaner
ኮምፒውተራችንን ሊያጨናንቁ የሚችሉ አላስፈላጊ መረጃዎች ለማፅዳት እና ተመሳሳይ ፋይሎችን ለይቶ ለማጥፋት CCleaner እጅግ ጠቃሚ መተግበሪያ ነው፡፡ ይህ መተግበሪያ ረጅም እና አድካሚ የማጽዳት ሥራዎችን በአንድ ቦታ ሊሰራለን ከመቻሉም ባለፈ በፈጣን የማጣሪያ ሥርዓት ኮምፒውተራችንን በፍጥነት አንዲጓዝ የሚያደርግልን ነው፡፡
5 LibreOffice
በ2010 የተመሰረተው ይህ የመፃፊያ ስርዓት በየጊዜው በሚጨመሩለት አዳዲስ ገፅታዎች ይበልጥ እየተሻሻለ የመጣ እና አሁን ላይ በጣም ፈጣን ለአሳሰራ ምቹ ከሚባሉ የመፃፊያ ስርዓቶች በቀዳሚነት የሚመደብ ነው፡፡ LibreOffice ምንም ከማይከፈልባቸው ጠቃሚ open-source መተግበሪዎች ውስጥ ቀዳሚው ሲሆን በቀጣዮቹ አመታትም ብዙ ተጠቃሚዎች እንደሚኖሩት የሚገመት ነው፡፡
6 Notepad++
የትኛውንም የኮዲንግ ቋንቋዎች ተጠቅመን ኮድ ለመፃፍ እና የተለያዩ ስራዎችን ለማከናወን የሚያግዘን ይህ መተግበሪያ ከማይክሮሶፍት ዊንዶውስ Notepad ጋር እንዳማራጭ ልንጠቀመው እና እጅግ የበዙ ኮንቴክስችዋል ፎርማቶችን (contextual formatting) ያቀፈ ጠቃሚ መተግበሪያ ነው፡፡
ከእነዚህ መተግበሪያዎች በተጨማሪ ለቪዲዮ፣ ለምስል እና ለድምፅ ማቀናበሪ የሚያግዙ እጅግ አስፈላጊ መተግበሪያዎች መረጃውን ባስነበበው ቴክራደር እንዲሁ የተቀመጡ ሲሆን እነሱም ለምስል ማስተካከያ (Polarr)፣ ለድምፅ ማቀናበሪያ (Audacity እና Cakewalk) እንዲሁም ለቪዲዮ መስሪያ (Shotcut) በተከታይነት ተቀምጠዋል፡፡
ምንጭ፡ Techradar

ሳኒታይዘሮች የህፃናት ዓይን ላይ አሳሳቢ ጉዳት እያደረሱ ነው
======================
ከአንድ አመት በፊት የኮቪድ-19 ወረርሺኝ መቀስቀሱን ተከትሎ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘሮችን መጠቀም ዕለታዊ ተግባራችን ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ እነዚህ ሳኒታይዘሮች እጃችንን ሲያደርቁትና ሽታቸውም በዓይናችን እንባ ሲያቀር ቢቆይም ያሳለፍነው ሐሙስ የወጣ ጥናት እንደሚያሳየው ግን እስከ አይነ ስውርነት ሊያደርስ በሚችል ሁኔታ አይናቸው ውስጥ ሳኒታይዘር የሚገኝባቸው ህፃናት ቁጥር እያደገ መጥቷል፡፡
በአውሮፓውያኑ 2019 ሳኒታይዘር ህፃናት ለኬሚካል ካላቸው ተጋላጭነት ውስጥ የ1.3 በመቶውን ድርሻ ብቻ ይወስድ ነበር፡፡ ይህ ቁጥር በፍጥነት አድጎ በ2020 መጨረሻ ላይ 9.9 በመቶ ሆኗል፡፡ ለምሳሌ አንድ ትንሽ ህፃን ብቻ በፈረንሳይ ዓይኑ ውስጥ በተገኘ ሳኒታይዘር ሳብያ በሆስፒታል ቆይቶ ህክምና ለመከታተል ተገዶ የነበረ ቢሆንም በ2020 ቁጥሩ ወደ 16 ከፍ ብሏል፡፡ በሌላ ጥናትም ህንድ ውስጥ በሳኒታይዘር ሳብያ ሁለት ትናንሽ ህፃናት ከፍተኛ የዓይን ጤና ችግር ውስጥ ገብተው ነበር፤ የኋላ ኋላ በተደረገላቸው ርብርብ ሙሉ ለሙሉ ቢያገግሙም፡፡
የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘሮች ከፍተኛ የአልኮል መጠን በተለይም በኢታኖል መልኩ ስለሚይዙ ኮርኒያ ተብሎ በሚታወቀው የአይናችን ክፍል ውስጥ ያሉትን አንዳንድ ሕዋሳት ሊገድሉ ይችላሉ፡፡ ትናንሽ ህፃናት ደግሞ ከቁመታቸው ማጠር የተነሳ ሳኒታይዘሩ ሲረጭ ቀጥታ ወደ አይናቸው ተፈናጥሮ የመግባት ዕድሉ ከፍ ስለሚል ለዚህ በተለየ ተጋላጭ ናቸው፡፡ አንዳንድ ህፃናት ደግሞ ይባስ ብሎ ሳኒታይዘሩ እጃቸው ላይ ከተደረገላቸው በኋላ ወዲያው አይናቸውን ይነካካሉ፡፡ ቀዳሚው ስጋት ግን በህዝብ መሰብሰቢያ አካባቢዎች ብዙን ጊዜ ሳኒታይዘር የሚረጨው የህፃናቱ አይን በሚገኝበት ቁመት ገደማ መሆኑ ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ በወርሀ ግንቦት ፈረንሳይ ውስጥ ሳኒታይዘር በአይናቸው ከገባባቸው ህፃናት መካከል 16.4 በመቶው ብቻ በነዚህ ስፍራዎች ቢሆንም ነሀሴ ላይ ግን መጠኑ ወደ 52.4 ሊያድግ ችሏል፡፡
ታድያ ይህን ችግር ለመከላከል ከሳኒታይዘር ይልቅ በማፅዳት ረገድም የተሻለ የሆነውን እጅን በውሃና ሳሙና መታጠብ ቀዳሚ ምርጫ ሊሆንና ወላጆችም የእነርሱ መጠንቀቅ እንዳለ ሆኖ ልጆቻቸው እንዴት ሳኒታይዘር በትክክል መርጨት እንዳለባቸው ማስተማር እንደሚገባ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡ ሆኖም ሳኒታይዘሩ የህፃናት አይን ውስጥ (ወይም አዋቂ ውስጥም ቢሆን) የሚገባ ከሆነ ተከታዮቹን እርምጃዎች በአስቸኳይ መውሰድ ይገባል፡-
፩. አይናቸውን እንዳያሻሹ ማድረግ (ችግሩን በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚያባብሰው)፤
፪. ሳኒታይዘሩ የተረጨበትን አይን ትንሽ ሞቅ ባለ ውሃ ለአስር ደቂቃ ማጠብ፤
፫. ህመሙና ማቃጠሉ ከቀጠለ ወይም የማየት እክል ከገጠማቸው ግን ህፃናቱን በፍጥነት ወደ አይን ሀኪሞች ወይም ድንገተኛ ክፍል ውስጥ ማስገባት ይገባል፡፡
ምንጭ፡ Live Science

ሁዋዌ ሹፌር አልባ መኪናዎችን የሚያዋራ መንገድ ሰራ
========================
በቻይናዋ ጃንሱ ግዛት ውስጥ ባለቸው የዉሺ ከተማ የተዘረጋው ባለ 4 ኪ.ሜ መንገዱ አሽከርካሪ አልባ አውቶብሶች የሚመላለሱበት ሲሆን የተገጠሙለት የትራፊክ መብራት፣ የመንገድ ዳር ምልክቶች እና ሌሎችም እንደ ራዳር፣ ሴንሰር እና ካሜራ ያሉ ቴክኖሎጂዎቹን ተጠቅሞ ከአውቶብሶቹ በመነጋገር ፍጥነታቸውን እንዲጨምሩ፣ እንዲቀንሱ፣ እንዲቆሙ ብሎም መሰናክሎች ሲያጋጥሙ አቅጣጫን ቀይረው እንዲያልፉ ያስችላቸዋል፡፡ በግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሁዋዌ እና ሌሎች አጋሮች ጥቅም ላይ የሚውለው መንገዱ ተሽከርካሪዎቿን ብልህ እና የተሳሰሩ የማድረጉ የቻይና ሀገራዊ ውጥን አካል ነው፡፡ ታድያ ሀገሪቱም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፎችን ለመምታት አልማለች፤ የመንገድ ትራፊኩ ደህንነት እንዲጠበቅና ሁዋዌን የመሳሰሉ ኩባንያዎቿም በመሰረተ ልማት ግንባታው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል፡፡
ኤክስ-ባስ ተብሎ የዳቦ ስም የወጣላቸው አውቶብሶቹ በመንገዱ ላይ የሚፈጠሩትን ማናቸውንም ነገሮች ከሚመለከትና ውሳኔ ከሚሰጥ የትራፊክ ቁጥጥር ስርዓት ጋራ የተገናኙ ናቸው፡፡ ሆኖም መረጃ ከስርዓቱ ወደ አውቶብሶቹ የሚተላለፍ ብቻ ሳይሆን አውቶብሶቹም በየጊዜው መረጃን ወደ ስርዓቱ የሚልኩና ሰዓታችንን ጠብቀን ወደ ጉዞ መዳረሻችን እንድንደርስ ያስችለናል የሚሉት የትራፊክ መብራትንም ለመምረጥ ጥያቄ የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡ ታድያ አውቶብሶቹ በራሳቸው የሚንቀሳቀሱ ቢሆኑም እንደ አስፈላጊነቱ ሊሾፍራቸው የሚችል አሽከርካሪ አላቸው፡፡
አሜሪካን በሀገር ደህንነት ስጋትነት ከፈረጀችው ጊዜ አንስቶ ዓለም አቀፍ ግፊት ውስጥ የሰነበተው ሁዋዌ አዳዲስ መስኮች ላይ አይኑን ጥሎ እየሰራ ነው፡፡ እዚህም በራሳቸው የሚንቀሳቀሱ ብልህ ተሽከርካሪዎችን ከመስራት ይልቅ የተሽከርካሪዎቹን አብዮትን ዕውን የሚያደርጉ ሶፍትዌሮችን እና የትስስር ግብዓቶችን ለማቅረብ ተነስቷል፡፡
እራስ ገዝ ተሸከርካሪዎች መንገዶችን ለመቆጣጠር ዓመታትን እንደሚፈጅባቸው ቢገመትም የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎችን እያሳዩን ነው፡፡ ለምሳሌ አማዞን እራስ ገዝ ተሸከርካሪዎቹን በህዝብ ጎዳናዎች ላይ እንዲሞክር ፍቃድ ሲሰጠው አፕልም መሰል መኪናዎችን እስከ አውሮፓውያኑ 2024 እንደሚሰራ ይፋ አውጥቷል፡፡ በቻይናም ባይዱ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በቤጂንግ ዙርያ ራስ ገዝ ተሽከርካሪዎችን እየሞከረ ሲሆን የሀገሪቱ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችም መኪናዎችን ያለ አሽከርካሪ ለማንቀሳቀስ የሚየስችሉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፕሮሰሰሮችን እና ቀመሮችን በመስራት ተጠምደዋል፡፡ የሁዋዌ ቴክኖሎጂም ትክክለኛ መረጃን ለተሽከርካሪ፣ እግረኛ እና ሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎች ስለ መንገድ ትራፊኩ፣ አየር ፀባይ እና ሊከሰቱ ስለሚችሉ አደጋዎች ወዲያው ወዲያው መረጃን ይሰጣል፡፡
በየ ስምንት ደቂቃው ልዩነት አንድ ሰው በትራፊክ አደጋ የምታጣው ቻይና በዚህ ቴክኖሎጂ እና አስቻይ መሰረተ ልማቶቹ ላይ በማተኮር አደጋን ለመቀነስ ወጥና እየሰራች ናት፡፡
ምንጭ፡ Bloomberg

በከፍተኛ መጠን እየቀለጠ ያለው የአለማችን በረዶ
********************************
አንድ አዲስ ጥናት በአለማችን ላይ ያለው በረዶ በከፍተኛ መጠን እየቀለጠ መሆኑን ይፋ አደረገ፡፡ በጥናቱም አለማችን ከ1994 እስከ 2017 ድረስ 28 ትሪሊዮን ቶን የበረዶ ግግርን እንዳጣች አሳውቋል፡፡ ይህ በሌላ አገላለጽ መቶ ሜትር ውፍረት ያለው ሙሉ እንግሊዝን ሊሸፍን የሚችል የበረዶ ንጣፍ ማለት ነው፡፡ ጥናቱም የሳተላይት መረጃን በመጠቀም የተሰራ እንደሆነ ተገልጧል፡፡
በሊድስ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት የሚመራው ጥናት ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ውስጥ በአለማችን ያለው የበረዶ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እየቀለጠ እየጠፋ እንደሆነ የሚያሳይ መረጃን ይዞ ወጥቷል፡፡ የቅልጠት መጠኑም በ90ዎቹ በየአመቱ 0.8 ትሪሊዮን ቶን ያክል ሲሆን ከዚያ ወዲህ እስከ 2017 ደግሞ በ1.3 ትሪሊዮን ቶን በየአመቱ የተለካ ነው፡፡ ይህ የበረዶ መቅለጥ በአለማችን ውስጥ የሚገኘውን የባህር ጠለል ልክ ከፍ በማድረግ የጎርፍ አደጋ ስጋትን እየጨመረው ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ የተፈጥሮ ሀብት መጥፋትን እያስከተለ ይገኛል ሲል ጥናቱ አመልክቷል፡፡
በእንግሊዙ የተፈጥሮ ሀብት ምርምር ካውንስል እየተደገፈ የሚሰራው ምርምር ባለፉት 23 ዓመታት በተሰራ ተከታታይ ጥናት የበረዶ ቅልጠት መጠኑ በ65 በመቶ ከፍ ማለቱን አሳይቷል፡፡ በጥናቱ ውስጥ ከፍተኛ የበረዶ ክምችት የሚገኝባቸው የአለማችን ሀገራት የተካተቱ ቢሆንም የቅልጠት መጠኑ ከፍ ብሎ የታየው በአንታርቲካ እና በግሪን ላንድ ነው፡፡ የበረዶ ግግሩ የሚቀልጥባቸው ሁለት ምክንያቶች ሲኖሩ አንደኛው ከከባቢ አየር ጋር የተያያዘው atmospheric melting የሚባለው ሲሆን 68 በመቶ ድርሻ ያለው ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ መሰረቱን በውቅያኖሶች ላይ ያደረገውና የ32 ድርሻ ያለው oceanic melting ነው፡፡
ከላይ በተገለጸው የቁጥር መረጃ እንደምረዳው የከባቢ አየር ሙቀት መጨመር በአለማችን ላለው የበረዶ ግግር መቅለጥ ከፍተኛውን ድርሻ እየወሰደ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በውቅያኖሶች ላይ ያለውን በረዶ እያቀለጠ የውቅያኖስ ውሃ ከፍተኛ የሆነ የፀሐይ ብርሃን እንዲያገኝ ያደርገዋል፡፡ የውቅያኖስ ውሃ መሞቅ ደግሞ የአርክቲክ ሙቀት ከመቸውም ጊዜ በላይ እንዲጨምር አድጎታል፡፡ እስካሁን በተሰራው ጥናት በሰሜን ንፍቀ ክበብ የሚገኘው በረዶ ከጠቅላላው 58 በመቶውን ሲሸፍን ቀሪው 42 በመቶ ደግሞ በደቡብ ንፍቀ ክበብ የሚገኝ ነው፡፡