TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ልዩ የዚንክ ባትሪ በአዲስ ቀመር
*****************************
የባትሪ ፍላጎትን ለማሟላት የተዘጋጀ በዘርፉ ተመራማሪዎች የተበረከተ የዚንክ አየር ባትሪ የወደፊቱ ተመራጭ ባትሪ እንደሚሆን ተነገረ፡፡ አለማቀፍ የሆነ የምርምር ጥምረት ከፍተኛ ብቃት ያለው፣ ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ፣ ምቹና በተመጣጣኝ ዋጋ ሊቀርብ የሚችል የወደፊቱ ተመራጭ ባትሪን በዚንክ አየር መስራታቸው ታውቋል፡፡
እስከ ዛሬ ድረስ ያለው የዚንክ አየር ባትሪ ከፍኛ ኬሚካዊ አለመረጋጋት የሚታይበትና የተለያዩ ችግሮች የሚታዩበት የነበረ ነው፡፡ አዲሱ የሀይል ማከማቻ ባትሪ ግን ከአልካላይን የጸዳ በመሆኑ ከዚህ በፊት የነበሩትን ችግሮች በሙሉ የቀረፈ ነው፡፡
ተመራማሪዎቹ የምርምር ውጤታቸውን ባሳወቁበት ወቅት ግኝቱ ከአልካላይን የጸዳ ኤሌክትሮላይት የበፊቱን ዚንክ ፐርኦክሳይድ ወደ ዚንክ አየር ባትሪ መለወጥ ያስቻለ ነው ብለዋል፡፡ የዚንክ አኖድ በከፍተኛ ኬሚካዊ መረጋጋትና ኤሌክትሮ ኬሚካል ሪቨርሴብሊቲ በጥሩ ሁኔታ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ አንዴ የተሞሉ የዚንክ አየር ባትሪዎች ለ320 ዙሮች እና ለ1600 ሰዓታት ያክል ግልጋሎት ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
ይህ ቴክኖሎጂም ከበፊቱ የተሻለ ለአካባቢ ተስማሚ እንዲሁም ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው የሀይል ማከማቻ ባትሪዎች እንዲኖሩ ያስችላል ሲሉ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ ምርምሩም በሙንስተር ዩኒቨርሲቲ ተጨማሪ ጥናቶች እየተካሄዱበት ሲሆን በሻንጋዩ ፉዳን የኒቨርሲቲ፣ የውሃን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና የአሜሪካ ጦር የምርምር ቤተ-ሙከራ ትብብር የተሰራ ነው፡፡
ምንጭ SciTechDaily
ዘርፎ መደራደርን የለመዱት አስገራሚ ጦጣዎች
================
በኢንዶኔዢያው ኡሉዋቱ የሂንዱ ቤተ እምነት የሚገኙ ማፊያ ጦጣዎች ሌብነት ምትክ የለሽ ስራቸው ሆኖላቸዋል፡፡ በጥንታዊው ቤተ-መቅደስ ዙርያ ኑሮዋቸውን ያደረጉት ጦጣዎቹ ያልጠረጠረ ወይም ሚነገረውን ያልሰማ ሀገር ጎብኚ ሲያገኙ በመዝረፍ እና እቃውን በማስያዣነት አስቀምጠው ምግብን በመጠየቅ ዕውቅናን አትርፈዋል፡፡ በቅርብ የተሰራ ጥናት ደግሞ እነዚህ ጦጣዎች በአስገራሚ ሆኔታ ሀገር ጎብኚዎቹ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጧቸው እቃዎችን በመለየት ከዝርፊያቸው የሚያገኙትን ትርፍ ለማሳደግ እንደሚሰሩ አመላክቷል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው ሰዎች ያን ያህል ዋጋ ማይሰጧቸው እንደ ፀጉር ማስያዣና የካሜራ ማስቀመጫ ቦርሳ ያሉትን በመተው መሰረቃቸው ሊያሳብዱ የሚደርሱትን እንደ ዋሌት፣ ሞባይል ስልክ፣ በሀኪም የታዘዙ መነፅሮችን ይዘው ይፈተለካሉ፡፡
የጥኛት ቡድኑ ለዘጠኝ ወራት ያህል የጦጣና ሀገር ጎብኚዎቹን ግንኙነት በምስል ቀርፆ ሲመለከት ከቆዩ በኋላ ነው ጦጣዎቹ የሰረቁት እቃ ዋጋው ከፍ ባለ ቁጥር የሚጠይቁት ምግብ ብዛትንም እንደሚያሳድጉ ማረጋገጥ የቻለው፡፡ ቡድኑ መመልከት እንደቻለው ጦጣዎቹ የሰረቁትን እቃ አስመልክቶ ከቤተ-እምነቱ ሰራተኞች እና ሀገር ጎብኚዎቹ ጋር ሚያደርጉት ድርድር እስከ ግማሽ ሰዓት ሊወስድ ይችላል፡፡ በቆይታቸው ከተመለከቱት ውስጥ አድን እቃ ለማስመለስ የወሰደው ረጅሙ ጊዜ 25 ደቂቃ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 17 ደቂቃው በድርድር የጠፋ ነው፡፡ ሆኖም የሰረቁት ዕቃ ዋጋው አነስተኛ ከሆነ አነስተኛ ምግብን ተቀብለው ድርድሩን በስኬት ለመዝጋት ፍቃደኛ ናቸው፡፡ አዲሱን ጥናት ከሌሎች መሰል ባህርይን ካመላከቱ ጥናቶች ለየት የሚያደርገው ጦጣዎቹ ነገሮች ተመጥነው በሚገኙበት በቤተ-ሙከራ ውስጥ የሚኖሩ ሳይሆን እንደ ፍቃዳቸው የሚንቀሳቀሱ ራስ ገዝ ዱር አዳሪዎች መሆናቸው ነው፡፡
እንደ ጥናቱ ከሆነ ጦጣዎቹ ይህን መሰል ባህርይን የሚያዳብሩት 4 ዓመት ዕድሜ ላይ እስከሚደርሱ ባለው የታዳጊነት ዘመናቸው ውስጥ ነው፡፡ መስረቅ እና የሰረቁትን ለድርድር ማቅረባቸው ደግሞ የብልህነት ባህላቸው መገለጫ መሆኑን የሚናገሩት የጥናቱ መሪና በካናዳው የሌዝብሪጅ ዩኒቨርሲቱ የስነ-ልቦና ረዳት ፕሮፌሰር የሆነው ዦን-ባፕቲስ ሌካ ባህርዩን ላፉት ሦስት አስርት ዓመታት በባህላቸው ውስጥ ሲማሩትና ከትውልድ ትውልድ ሲያስተላልፉት የቆየ መሆኑን ገልጿል፡፡
በኡሉዋቱ ሀገር ጎብኚዎች በቤተ-እምነቱ ዙርያ ካሉት ቀማኛ ጦጣዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት መልካም ለማድረግ የሚሰሩ ሰዎች ያሉ ቢሆንም ሌሎች ቦታዎች ግን ለዚህ ባለመታደላቸው በጦጣዎች እና የሰው ልጆች መካከል ያለው ፍቅር አልባ ግንኙነት እየተካረረ ሄዷል፡፡ ለምሳሌ በህንድ የሚገኙ ራስ ገዝ ጦጣዎች የገበሬዎችን ማሳ በመብላት፣ መንደርና ከተሞችን በመውረር ባስ ሲልም የኮሮና ቫይረስ ተመርማሪዎችን የደም ናሙና የያዙ የጤና ባለሙያዎችን በቡድን ማጥቃት ውስጥ ተሰማርተዋል፡፡ በሌሎች የዓለማችን ስፍራዎችም የኮቪድ-19 ወረርሺኝ ተከትሎ የሚበሉትን በማጣታቸው ሳብያ ከሰው ልጆች ጋር ተጠጋግተው የሚኖሩ ጦጣዎችን ጠብ አጫሪና ከቀን ወደቀንም አብሮ ለመኖር አስቸጋሪ ሆነዋል፡፡
ምንጭ፡ The Guardian
የብረት ነዳጅ ተስፋ ሰጭው የወደፊት አማራጭ
*******************************
ማይክሮ ግራቪቲን በመጠቀም የዘርፉ ተመራማሪዎች ለወደፊት የሀይል አማራጭ ተስፋ የተጣለበትን የብረት ነዳጅ እያዘጋጁ እንደሆነ ተገለጸ፡፡ ማይክሮ ግራቪቲ የብረት ቁርጥራጮችን በበቂ ሁኔታ ማንደድ የሚያስችል ስልት እንዳስገኘላቸው ተመራማሪዎች ተናግረዋል፡፡ ይህም ከፕትሮሊየም ይልቅ የተፈጨ ብረትን ለነዳጅነት መጠቀም የሚያስችል እድልን ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ተነግሯል፡፡
ብዙውን ጊዜ ጠጣር የሆኑ ተቀጣጣይ ነገሮች ክብሪት ለማቀጣጠል ወይም ደግሞ ለበዓላት ማድመቂያ የሚሆኑ ብርሃናማ ተቀጣጣይ ነገሮች( ርችት) ለመስረፋት ያገለግላሉ፡፡ ነገርግን እንደ አይረን ያሉ የብረት አይነቶች በዱቄት መልክ መቀጣጠል የሚችሉና በተመሳሳይ ጊዜ ጭስ አልባና ከካርቦን ነጻ የሆኑ ናቸው፡፡
ብረተቶች በካይ ባልሆኑ እንደ ፀሐይና ነፋስ ያሉ የሀይል አማራጮች ሊመረቱ ይችላሉ፡፡ የሚፈለገው ኤሌክትሪክ ሀይል በኬሚካል ኢነርጂ መልኩ ከፎሲል ነዳጅ እፍግታ ተወዳዳሪ በሆነ መልኩ በብረት ብናኙ ውስጥ ይከማቻል፡፡ ይህም በአለማቀፍ ደረጃ ያለውን የግሪን ሀውስ ጋዝ ልቀት መጠን በከፍተኛ መልኩ ይቀንሰዋል፡፡ በዚህ ዘርፍ እንደ ትልቅ ተግዳሮት ተደርጎ የሚወሰደው ብረቱን ማቃጠል የሚያስችል የቴክኖሎጂ ስልት እጥረት መኖሩ ነው፡፡
ምንጭ SciTechDaily
መላው የክርስትና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን፤ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ እያልን ሁላችሁም ባላችሁበት መልካም በዓልን ታሳልፉ ዘንድ እንመኝላችኋለን!!!
ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በ10 ደቂቃ ውስጥ መሞላት የሚችለው የኤሌክትሪክ መኪናዎች ባትሪ
*******************************
በሳይንስ ሬንጅ እየተባለ የሚታወቅ የፍርሃት አይነት አለ፡፡ ይህ Range anxiety እየተባለ የሚታወቀው የፍሃት አይነት ሰዎች እንደ ስልክ፣ ኮምፒውተርና መኪና ያሉ የተለያዩ መጠቀሚያ ቁሶችን ሀይል ከመሙላታቸው በፊት ሃይላቸውን ይጨርሳሉ ብለው ሲያስቡ የሚሰማቸው የፍርሃት አይነት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሳይንስ ራሱ ይህን ችግር ሊቀርፍ የሚችል በተለይ የኤሌክትሪክ መኪናዎች የሀይል ፍላጎታቸውን በ10 ደቂቃ ውስጥ መሙላት የሚያስችላቸው ቴክኖሎጂ መሰራቱ ተነግሯል፡፡ ይህም ቅንጡ ለሆኑ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ከሊቲየም አይረን ፎስፌት የተሰራ እስከ 250 ማይሎች ድረስ በአንድ ሙሊት ሊያስጉዝ የሚችል ባትሪ ነው፡፡
ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነ አዲሱ ባትሪ በዋጋ ደረጃ በነዳጅ የሚሰሩ መኪናዎች ከሚጠቀሙት ባትሪ ዋጋ ጋር ተቀራራቢ ሲሆን በአጠቃላይም እስከ 2 ሚሊዮን ማይሎች ድረስ ሊያስጉዝ ይችላል ተብሎለታል፡፡ ባትሪው የመጠን፣ ክብደትና ዋጋ ቅናሽ ተደርጎበት የተሰራ ነው፡፡ ባትሪው ራሱን ማሞቅ የሚያስችለው ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ሲሆን ይህም ያለውን ሀይል አሟጦ ሳይጠቀም ሀይሉ እንዲሞላ ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ ነው፡፡
ይህ በመጠኑ ትንሽ የሆነ ባትሪ ከፍተኛ ሀይል መሰብሰብ የሚችል ሲሆን ባትሪውን የሚጠቀሙ የኤሌክትሪክ መኪናዎች በ3 ሴኮንድ ውስጥ ከ0 እስከ 60 ኪሎ ሜት በሰዓት መጓዝ ይችላሉ፡፡ ቴክኖሎጂው ቅንጡ መኪናዎችን ብቻ ታሳቢ ያላደረገና ለአካባቢ ጥበቃም ሰፊ አስተዋጽኦ እንዳለው ተመራማሪዎቹ መናገራቸውን የዘገበው SciTechDaily ነው፡፡
የሳተላይቶች አይነትና ምንነት
ሳተላይቶች በሚሰጡት ሚና እና ሌሎች መመዘኛዎች ተከፋፍለው ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ አነዚህ ሳተላይቶች በቴክኖሎጂ ባህሪያቸው እና በቁሳዊ ይዘታቸው ከፋፍለን ካስቀመጥናቸው በተለያዩ ግዜያት ስርአተ-ፀሀያችን ውስጥ ወዳሉ የህዋ አካላት የተላኩ ሳተላይቶች በዋነኝነት በሶስት ጎራ ሊመደቡ ይችላሉ። አነዚህ ሳተላይቶች ወይም የጠፈር መንኮራኩራኩሮች ኦርቢተር፣ ላንደር እና ሮቨር ሲሆኑ ምንነታቸውም እንደሚከተለው ነው፡፡
ኦርቢተር (orbiter) የምንላቸው ሳተላይቶች ያንን የህዋ አካል (ፕላኔት፣ ኮሜት፣ አስትሮይድ ወዘተ) በመጠጋትና ምህዋሩ ውስጥ በመግባት እና በመዘዋወር መረጃ የሚሰበስቡ ናቸው። እንደ ምሳሌ ምድራችንን ከ 400 ኪ.ሜ ከፍታ ሆኖ የሚዞራትን የአለም አቀፉን የጠፈር ማእከል (International space station) ማንሳት እንችላለን።
ላንደር (Lander) የምንላቸው ሳተላይቶች የኦርቢተሮች ንኡስ-አካል ሲሆኑ ከኦርቢተሮች ተገንጥለው ወደ ህዋ አካሉ ወለል በመውረድ እና ራሳቸውን በመትከል ውስን ቦታ ላይ ሆነው የታቀደላቸውን አላማ ያከናውናሉ። ለአብነት ያህል የሳተርን ግዙፏ ጨረቃ የሆነችው ታይታን (Titan) ፎቶ ያነሳችውን ሀይጅንስ የተባለችውን ላንደር ማንሳት ይቻላል።
ሮቨር (Rover) የምንላቸው የኦርቢተሮች ንኡስ-አካል ሆነው ወደ ህዋ አካሉ ወለል ከወረዱ በሁዋላ በመንቀሳቀስ መረጃን የሚሰበስቡ የሳተላይት አይነቶች ናቸው። ፕላኔት ማርስ ላይ ካሉት 3 ሮቨሮች ውስጥ 'ኪውሪዮሲቲ' የተባለችው ሮቨር በምሳሌነት ልትጠቃስ ትችላለች።
ምንጭ፡ Airtable universe እና E.A
አየርን ከብክለት መጠበቅ መጠነ ሞትን ለመቀነስ
***************************
የአለም ጤና ድርጅት የአየር ብክለትን በመቀነስ በአውሮፓ ብቻ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎችን ከሞት መታደግ እንደሚቻል አሳወቀ፡፡ እንደ ተቋሙ መረጃ ከሆነ በአለማችን በየአመቱ ከ7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በአየር ብክለት ምክንያት እየሞቱ ሲሆን ለሰዎች ጤና መታወክ ምክንያት ከሆኑ ነገሮች ዋነኛውም ይህ የአየር ብክለት ነው፡፡
ከፍተኛ የመንገድ መጨናነቅ ያለባቸውና ከፍተኛ ሀይል የሚጠቀሙ ከተሞች ከአየር ብክለት ጋር ለተያያዙ ችግሮች የመጋለጥ እድላቸው ላቅ ያለ ነው፡፡ የአለም ጤና ድርጅት PM2.5 በመባል የሚታወቁት ብናኞች በከባቢ አየር ውስጥ ያላቸው መጠን በኪዩቢክ ሜትር ከ10 ሚሊ ግራም እንዳይበልጥ የሚመክር ሲሆን ለ NO2 ደግሞ ከ40 mg/m3 እንዳይበልጥ ይመክራል፡፡ በቅርብ የወጣ አንድ ጥናት እነዚህ ሁለት በካይ ነገሮች 1000 በሚሆኑ የአውሮፓ ከተሞች ለሰዎች ህይወት መጥፋት ያላቸውን ተጽእኖ አሳይቷል፡፡ በዚህም የPM2.5 እና NO2 መጠንን መቀነስ በየአመቱ 51,213 ሰዎችን ከሞት መታደግ እንደሚያስችል አመልክቷል፡፡
አንድ የባርሴሎናው አለማቀፍ ጤና ምርምር ተቋም ተመራማሪ ምርምሩ ከተሞች የአየር ብክለትን ለመቀነስ እየሰሩት ያለው ስራ አነስተኛ መሆኑን ያረጋገጠ ነው ሲሉ ተሰምተዋል፡፡ በአየር ብክለት ምክንያት ያለው የሞት ሁኔታ የተለያዩ መገለጫዎች ያሉት ሲሆን ለምሳሌ NO2 ከአጠቃላዩ የሞት መጠን 7 በመቶውን የሚይዝ ነው፡፡ ጥናቱ በከተማ የሚኖሩ ሰዎች 84 በመቶ ያክል የአለም ጤና ድርጅት ካስቀመጠው ልኬት በላይ ለሆነ የPM2.5 ብክለት ተጋላጮች ናቸው፡፡
ምንጭ PHYS.ORG
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትት “artificial intelligence, robotics and its impact on society” በሚል ለሁለት ቀናት የሚቆይ ተጠባቂ ውይይት ሊያደርግ ነው፡፡ የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ፌስቲቫል አካል የሆነው ውይይቱ በኢትዮጵያ ያለውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ሮቦቲክስ ዕድገት፣ አጠቃቀም እና የወደፊት እጣ ጉዳዩ አድርጎ ይካሄዳል፡፡ ከውይይቶች በተጨማሪም ክርክርም የሚከናወንበት ይሆናል፡፡
ዝግጅቱ የሚደረግበት ዕለት፤ ከነገ ጥር 13 ጀምሮ እስከ ጥር 14 ድረስ
የሚጀምርበት ሰዓት፡ ከጠዋቱ 2፡30
ቦታ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ
Technology and innovation institute is holding a highly anticipated two days discussion regarding “artificial intelligence, robotics and its impact on society”. The discussion which is part of the institute’s Tech-Fest program will cover development, utilization, future prospect of AI and robotics Ethiopia. A debate session is also included.
Date January 21 and 22
Starting time 2:30 am LT
Place MINT hall
አየር መንገዶችና የአፍና የአፍንጫ ጭንብል የለበሱ ደንበኞች
**************************
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ በአለማችን የተለያዩ ችግሮች ተስተውለዋል፡፡ አንዳንዶቹ ወረርሽኙ ይዞት ከመጣው የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግር ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ በሽታውን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ጋር የተያያዙ የቴክኖሎጂ እጥረቶች ናቸው፡፡
በቴክኖሎጂ እጥረት ረገድ ለወረርሽኙ ፍቱን ክትባት ለማግኘት የወሰደው ጊዜ እንዳለ ሆኖ ከዚህ በፊት በነበረን ጽሁፍ የአፍና የአፍንጫ ጭንብል ያደረጉ ሰዎችን ማንነት ለመለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ እንዳልዳበረና እንደ መፍትሔም ሰዎች የራሳቸውን የፊት ቅርጽ ተከትለው የተሰሩ ጭንብሎችን እንዲጠቀሙ ለማድረግ ታስቦ እንደነበር ነግረናችኋል፡፡
የሰዎችን ማንነት መለየት በሚያስፈልግባቸው እንደ አየር መንገድ ባሉ ተቋማት ያሉ ካሜራዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ የለበሱ ሰዎችን ማንነት እስከ 96 በመቶ ትክክለኝነት መለየት የሚያስችላቸው መሻሻል እንደተደረገላቸው ተሰምቷል፡፡ ይህም መንገደኞች ካሜራዎች አካባቢ ጭንብላቸውን እንዲያወልቁ በማድረግ የወረርሽኙን መስፋፋት እያባባሰ የነበረውን ሁኔታ በእጅጉ እንደሚለውጠው ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
በሙከራ ወቅትም ቴክኖሎጂው የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የለበሱ ሰዎችን ማንነት በ96 በመቶ መለየት እንደሚያስችል ተረጋግጧል፡፡ በዚህ ውጤትም የሰራተኞቻቸውን መለያ ፎቶ ማረጋገጥ የሚፈልጉ ተቋማት ቴክኖሎጂውን በመጠቀም የወረርሽኙን ስርጭት መቀነስ እንደሚችሉ ታውቋል፡፡
የ S&T ባዮሜትርክ ምርምር ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት አሩን ቬሙሪ ምንም እንኳን መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን ባይቻልም አየር መንገዶች በተጓዦች ስለሚጨናነቁ የአገልግሎት ሰጭ ሰራተኞችንና የደንበኞችን ደህነት መጠበቅ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡
ምንጭ TECHNOLOGY.ORG