የሲጋራ ሱስን ማስወገድ የሚያስችል ውጤት የተገኘበት ምርምር
*********************
ሰዎች በልዩ ልዩ አጋጣሚዎች በሱሶች ልንጠመድ እንችላለን፡፡ አንዴ በሱስ ከተጠመድን በኋላ ሱሱን ብንወደውም ባንወደውም በቀላሉ ከእኛ ለማላቀቅ እንቸገራለን፡፡ ከተለመዱ በኋላ ለመተው ከሚያስቸግሩ ሱሶች መካከል አንዱ የሲጋራ ሱስ ነው፡፡ በዚህ ከሱስነቱ ባሻገር ከፍተኛ የሆነ የጤና ቀውስ የሚያስከትል መጥፎ ልምድ ብዙዎች ሲቸገሩበት ያታያል፡፡
በ2018 በተሰራ አንድ ጥናት አይጦችን በኒኮቲን ሱሰኛ እንዲሆኑ ከተደረገ በኋላ በቤተሙከራ የበለጸገ NicA2 የተሰኘ ኢንዛይም ሲሰጣቸው የነበረባቸውን ሱስ በሙሉ አስወግዶላቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ኢንዛይም በአይጦቹ ያለውን የኒኮቲን ፍላጎት ዘገምተኛ በሆነ መንገድ ስለሚያጠፋው ከፍተኛ መጠን ያለው NicA2 መጠቀም ነበረባቸው፡፡ መወሰድ ከሚገባው ከፍተኛ መጠን አንጻርም በፍጹም በሰዎች ላይ ሊሞከር የማይችል ሆኗል፡፡ ይህ ኢንዛይም ኒኮቲኑን ለማጥፋት የኤሌክትሮን አገናኝ ያስፈልገው ነበር፡፡ በሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ ተሰርቶ በነበረው ምርምር ሞሎኪዩላዊ ኦክስጅን በስህተት የኢንዛይሙ ኤሌክትሮን አክሴፕተር ተደርጎ ተወስዶ ነበር፡፡
አዲስ የተሰራው ምርምር ከላይ የተገለጸውን ስህተት ማስተካከል የቻለ እንደሆነ አጥኝዎቹ ተናግረዋል፡፡ በውጤቱም ሳይቶክህሮም ፕሮቲን ተፈጥሯዊ ኤሌክትሮን አክሴፕተር እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ግኝቱ በተለይ በሲጋራ ሱስ ለሚሰቃዩ ሰዎች ትልቅ የምስራችን ይዞ የመጣ ነው፡፡
ሲጋራ ማጨስ በቀላሉ መከላከል የምንችላቸው በአለማችን ካሉ ዋነኛ የበሽታ ምንጮች ውስጥ አንዱ ነው ያሉት ተመራማሪዎቹ በዚህ ሱስ የተጠቁ ሰዎች መፍትሄ የሚያገኙበትን የህክምና መንገድ ማዘጋጀት ከተቻለ በሰው ልጅ ጤና ዙሪያ ከፍተኛ መሻሻላ ማምጣት ይቻላል ሲሉ በምርምራቸው ውጤት ያላቸውን ተስፋ አስረድተዋል፡፡
ምንጭ Medical Xpress

አዲስ የተገኙት ድንክዬ ቀጭኔዎች
==============
የቀጭኔዎች ቁመተ ለግላጋነት በረጃጅም ዛፎች ላይ የሚገኙ ቅጠሎችን እንዲመገቡ የሚያስችል የተፈጥሮ ስጦታቸው ነው፡፡ ታድያ ከሰሞኑን ይፋ የተደረገወ በሁለት የተለያዩ የአፍሪካ ክፍሎች ላይ አጫጭር ቀጭነዎች የመገኘታቸው ዜና ለተመራማሪዎቹ አግራሞትን ፈጥሯል፡፡
ብዙውን ጊዜ የቀጭኔዎች ቁመት ከ4.5 እስከ 6 ሜትር የሚለካ ነው፡፡ ለቀጭኔዎች ጥበቃን ከሚያደርግ አንድ ድርጅት ጋር የሚሰሩት ተመራማሪዎች ግን በአውሮፓውያኑ 2018 ላይ 2.6 ሜትር ብቻ የሚረዝም ቀጭኔን በናሚቢያ መመልከት ቻሉ፡፡ ከዚህ ሦስት ዓመታትን ቀደም ብሎም ዩጋንዳ ውስጥ ባለ የዱር ፓርክ ምስሉ ላይ አጥሮ የሚታየውን ቁመቱ 2.8 ሜትር የሆነ ሌላ ቀጭኔ አግኝተውም ነበር፡፡ ተመራማሪዎቹ የሁለቱን አጫጭር ቀጭኔዎች መገኘት አስመልክቶ ባሳለፍነው ወር መቋጫ ላይ የብሪቲሽ ሜዲካል ጆርናል ላይ የጥናት ውጤታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
በጥናቱ ላይ እንደተነገረው ሁለቱም ቀደጭኔዎች ላይ የተለመደው አይነት ረጃጅም አንገት ያላቸው ሆነው ሲገኙ እግሮቻቸው ግን አጠር ብለው ወፋፍራም ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስኬሌታል ዲስፕሌዚያ የተሰኘው ይህ አይነት የቁመት እጥረት መከሰት በሰው ልጆች እና የቤት ውስጥ እንስሳት ላይ መመልከቱ አዲስ ባይሆንም የዱር እንስሳት ላይ ግን ብዙም አልተለመደም፡፡ በድርጅቱ አማካኝነት የዩጋንዳው መርኪሰን ፏፏቴዎች ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ ከተወሰዱት ምስሎች ላይ ቀጭኔዎቹ ያላቸውን በጡንቻ የፈረጠመ እግር መመልክት ይቻላል፡፡
ሆኖም የቀጭኔዎች ቁመት መርዘም ለምክንያት ነውና እነዚህ ድንክዬ ቀጭኔዎች ከረጃጅም ዛፎች ላይ የመመገብን ፀጋ የተነፈጉ መሆናቸውን የሚናገረው የቀጭኔዎች ተንከባካቢ ድርጅቱ መስራች ጁሊያን ፌነሲ አካላዊ ሁኔታቸውም ከሌሎች ቀጭኔዎች ጋር ፆታዊ ግንኙነት የመፈፀሙን ነገር በምኞት ከማለፍ በቀር የማይቻል እንደሚያደርግባቸው አክሎ ይገልፃል፡፡
ምንጭ፡ Reuters

እስካሁን ከተሰሩት የጠፈር ሮኬቶች ከፍተኛ ሃይል የሚኖረው አዲስ ሮኬት
በ322 የጫማ ከፍታ በመገንባት ላይ የሚገኘው አዲሱ የሮኬት ማስወንጨፊያ ወይም የጠፈር ማስጀመሪያ ስርዓት በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ የጠፈር ተመራማሪዎችን ወደ ጨረቃ ካስወነጨፈው ሳተርን ቪ (Saturn V) ከተሰኛው ከባድ የማስወንጨፊያ ስርዓት በእርዝመቱ አነስ ያለ ቢሆንም የግፊት አቅሙ እና የመሸከም ጉልበቱ በአለም ላይ የመጀመሪያው እንደሚያደርገው ተዘግቧል፡፡
ይህ የጠፈር ማስጀመሪያ ስርዓት ወይም (Space Launch System) በእቅዱ መሰረት ስራዎቹ የሚካሄዱ ከሆነ 24 ሺ ኪሎግራም የመሸከም አቅም የሚኖረው ሲሆን ስፔስ ሸትል ከተሰኘው ሮኬት በ2,000 ኪ.ግ በመብለጥም ከፍተኛ የመሸከም አቅም ያለው የማስወንጨፊያ ሮኬት ይሆናል፡፡
ከስፔስ ድረ ገፅ የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው መንኮራኩሮችን ወደጨረቃ ለማሰወንጨፍ ጥቅም ላይ የዋለው ሳተርን ቪ ከአዲሱ የሮኬት ማስወንጨፊያ (SLS) ጋር በዚህ የመሸከም አቅም ተቀራራቢ ቢሆኑም በተለያዩ የሮኬት ማስወንጨፊያ ደረጃዎች እና የነዳጅ አወሳሰድ ላይ SLS እጅግ የተሻለ በመሆኑ ወደጨረቃ የሚደረገውን ጉዞ ጨምሮ ሌሎች ተልዕኮዎችን በተሻለ ሁኔታ እንዲፈፅም ያስችለዋል፡፡
በናሳ የአርተሚስ ፕሮግራም የታቀፈው የዚሁ የሮኬት የሙከራ ሂደት ስምንት ደረጃዎች የነበሩት ሲሆን እስከ ታህሳስ 2020 ሰባቱ የሙከራ ሂደቶች መጠናቀቃቸውን እና በመጪው ጥር 17 የሮኬቱ የማስወንጨፍ ሙከራ እንደሚካሄድም የ SLS ዋና ዳይሬክትር ጁሊ ባስለር ተናግረዋል፡፡ ለሰዎች የጥልቅ ህዋ ምርምር እና ወደ ጨረቃ ለሚደረገው የሰዎች ጉዞ ትልቅ አገልግሎት ይሰጣል የተባለው ይህ ሮኬት እስካሁን ከታዩት ከፍተኛ ሃይል ያላቸው የጠፈር ማስወንጨፊያ ሮኬቶች በቀዳሚነት የሚጠቀስ መሆኑም በዘገባው ተገልጿል፡፡
ምንጭ፡ business insider africa

Wi-Fi እንዴት ይሰራል?
************
ምንም እንኳን በአይናችን ባናያቸውም የራዲዮ ሞገዶች ሁሌም መረጃዎችን ተሸክመው በዙሪያችን እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ የሬዲዮ ሞገዶች ጥቂቶቹ የWi-Fi ሲግናሎች ናቸው፡፡ Wi-Fi በሚለው ስም ውስጥ የሚገኙ ሆሄያት እንደ አህጽሮተ ቃል የትኛውንም ነገር የማይወክሉ ሲሆን በመነሻነት አንድ ከፍተኛ መጠን ያለውን መረጃ በአጭር ርቀት ውስጥ የራዲዮ ሞገዶችን በመጠቀም ማስተላለፍ የሚችልን ቁስ በቀላሉ ማስታዎስ እንዲቻል ተብሎ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡
እንደ ብሮድካስት ራዲዮና ተንቀሳቃሽ ስልክ ሲግናሎች ሁሉ የWi-Fi ሲግናልም በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ አካባቢ የተገኘ ሳይንሳዊ ፈጠራ ነው፡፡ ኤሌክትሮኖች በሽቦ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ በየተወሰኑ ጊዜያት አቅጣጫዎችን ይቀይራሉ፡፡ በሌላ ሽቦ ላይ የሚገኙ ኤሌክትሮኖች ከእነዚህ አቅጣጫ ከሚቀያይሩ ኤልክትሮኖች ጋር ቴሌፋቲክ በሆነ መንገድ የተያያዙ ስለሆኑ መንቀሳቀስ ይጀምራሉ፡፡ ይህ ግኝት መጀመሪያ የታወቀው በ1887 በሄንሪክ ሄርትዝ ነው፡፡
የሚታይ ብርሃንን የያዙ ኤሌክትሮመግነጢሳዊ ህብሮች ከራዲዮ ሞገዶች የተሻለ ከፍተኛ ፍሪኩየንሲን ያመነጫሉ፡፡ የተለመዱት የኤ ኤም ወይም ኤፍ ኤም ራዲዮ እና የቴሌቪዥን ስርጭቶች መረጃን በተከታታይ ሲግናሎች ወይም በአናሎግ ያደርሳሉ፡፡ Wi-Fi መረጃን የሚያሰራጨው እንደ ያልተያያዙ ዋጋዎች የባይናሪ መረጃ ዜሮዎችና አንዶች በዲጂታል መንገድ ነው፡፡ ይህም የሞባይል ቁሶች ከፍተኛ መጠን ያላቸውን እንደ ቪዲዮ፣ ምስል፣ ድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶችን በቀላሉ እንዲልኩ ያስችላቸዋል፡፡
አንድን መረጃ በዋይ ፋይ ኦንላይን ላይ ስንፈልግ የዋይ ፋይ ቁሳችን የሬዲዮ ሞገዶችን አልፎ ከዋይ ፋዩ መገኛ ነጥብ ጋር ይናበባል፡፡ ይህም በኢንተርኔት ራውተራችን አንቴና አማካኝነት ነው፡፡ ከዚያም በአካባቢው ባሉ የኢንተርኔት ገመዶች አማካኝነት ጥያቄያችን ወደምንፈልገው የመረጃ ቋት ይተላለፋል፡፡ ሂደቱ ሲያልቅም በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይመጣል፡፡
በተለያዩ ኩባንዎች የተሰሩ የዋይ ፋይ ቁሶች 802.11 የተሰኘ ተመሳሳይ ስታንዳርድን ስለሚከተሉ እርስ በርሳቸው መናበብ ይችላሉ፡፡ ይህ ስታንዳርድ ዜሮዎችና አንዶች ራዲዮ ሞገድን በመጠቀም እንዴት እንደተወከሉና ቁሶቹ ራሳቸውን እንዴት እንደሚለዩ የሚወስን ነው፡፡ እነዲሁም ደግሞ ኬሪየር ሴንስ መልቲፕል አክሰስ (CSMA) የተሰኘ እንዴትና መቼ መግባባት እንዳለባቸው የሚወስን አሊጎሪዝም ይከተላሉ፡፡ ይህ አሊጎሪዝም የዋይ ፋይ ቁሶችን ስማርት ያደርጋቸዋል፡፡
አንዳንድ ጊዜ ከዋይ ፋይ ጋር በተያያዘ ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ወይም ከዋይ ፋዩ መገኛ ነጥብ ጋር ለመገናኘት እንቸገራለን ይህም የሚሆነው የራዲዮ ሲግናሎች በርቀት ምክንያ ሲደክሙ ነው፡፡ ለምሳሌ ወፍራም ግድግዳ፣ የብረት መከለያዎች አንዲሁም አኳሪየም የራዲዮ ሞገዶችን ሊያደክማቸው ይችላል፡፡
Tech Xploreን በምንጭነት ተጠቅመናል፡፡

የአንድ መልክ መንትያዎች ከሚገመተው በላይ የተለያዩ ናቸው
=======================
አንድ አይነት ወይም በሙያው አጠራር ሞኖዛይጎቲክ መንትያዎች በእናት ማህፀን ውስጥ አንድን እንቁላል ለሁለት የተካፈሉ ልጆች ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም እነዚህ መንትያዎች በጣም አነስተኛ የሚባል የበራሒ (ጀነቲክ) ለውጥ አላቸው ተብሎ ስለሚታሰብ በመካከላቸው የሚታይ አካላዊም ሆነ የባህርይ ልዩነት ከከባቢያቸው የሚነሳ ስለመሆኑ ከድምዳሜ ይደረስ ነበር፡፡ ሆኖም ባሳለፍነው ሳምንት የወጣ ጥናት እንደሚያሳው የበራሒ ልዩነቱ ቀድሞ ከሚገመተውም በላይ መሆኑን ነው፡፡
የጥናቱ ተሳታፊ የነበረው ካሪ ስቴፋንሶን እንደሚለው ሁለት አንድ አይነት መንትያዎች በተለያየ አካበቢ ቢያድጉና አንደኛው የአዕምሮ ዕድገት ውስንንት (ኦቲዝም) ቢያጋጥመው የጤና እክሉ የመጣው ካደገበት አካባቢ መነሾነት ነው ተብሎ በራሒን ከጥያቄው ያወጣ አደገኛ ድምዳሜ በህክምና ዓለም ይወሰድ ነበር፡፡
በዘረ-መል ላይ የሚካሄዱ ለውጦች (Mutation) መጥፎም ይሁኑ ጥሩ በአካላዊ ገፅታ ብሎም ለአንድ የጤና እክልም ሆነ በሽታ ያለን ተጋላጭነት የመቀየር አቅም አላቸው፡፡ ካሪ ስቴፋንሶን እና የጥናት ቡድኑ ከመንትያዎች እንዲሁም ወላጅ፣ የትዳር አጋር እና ልጆች የወሰዷቸው 387 በራሂዎችን ተጠቅመው የበራሂ ለውጦችን ለመከታተል ጥረት አድርገዋል፡፡ በዚህም ፅንስ ውስጥ ባሉ ጊዜ የሚከሰተውን ለውጥ በመለካት መንትያዎቹ በመጀመሪያዎቹ እድገታቸው ወቅት በአማካኝ የ5.2 ለውጦችን እንደሚያስተናግዱ ለማወቅ ችለዋል፡፡ በ15 በመቶዎቹ መንትያዎች ላይ የሚታየው ለውጥ ደግሞ ከሌሎቹም ከፍ ያለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በፅንስ እድገት ወቅት የሚኖር መሰል የበራሒ ለውጥ በህዋሳቱም ሆነ ልጁ ላይ ከፍ ያለ ለውጠን እንዲያመጣ ይጠበቃል፡፡ ለምሳሌ ከፅንሱ የመጀመሪያ ወቅቶች አንስቶ የተከሰተ በሚመስል መልኩ በአንደኛው ልጅ ሰውነት ውስጥ ያሉት ሁሉም ሕዋሳት ለውጦችን ያስተናገዱ ሲሆን መንትያው ግን በተቃራኒው ይህ ሳይታይበት ቀርቷል፡፡
ከዚህ ቀደም የተጠኑ ጥናቶች በአንድ አይነት መንትያዎች መካከል የተወሰኑ ልዩነቶች መኖራቸውን አመላክተው ነበር፡፡ አዲሱ ምርምር ግን ከዚህም በመሻገር የመንታዎቹን ወላጅ፣ ትዳር አጋር እና ልጆችን ዲ.ኤን.ኤ አካቶ የተመለከተ ነው፡፡ ይህም በአንዱ ላይ ብቻ የሚታዩት እና በዚያ ሰው ልጆች የሚወረሱትን የተለያዩ አይነት ህዋሳት ላይ የሚከሰተውን የበራሒ ለውጥ ከመቼ ጀምሮ እንደሚከሰት ለማወቅ እስችሏል፡፡
ጥናቱ በተለያዩ ምሁራን ታሪካዊና በህክምናው ዘርፍ ያለ አረዳድንም በከፍተኛ ደረጃ የሚቀይር ስለመሆኑ ምስክርነት ተሰጥቶበታል፡፡
ምንጭ፡ The Guardian

ሲ.አይ.ኤ ስለ ዩፎዎች ያሉትን መረጃዎች ይፋ አደረገ
======================
የሜሪካኑ የስለላ ተቋም ሲ.አይ.ኤ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ሲሰበስብ የቆየውን ያልታወቁ በራሪ አካላት ወይም ዩፎዎችን የሚመለከቱ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ ይፋ ከተደረጉት ሰፊ መረጃዎች መካከል ከ2,700 በላይ ገፅ ያላቸው ከዩፎ ጋራ የተገናኙነ ሰነዶች ይገኙበታል፡፡ መረጃዎቹ ይፋ የሆኑት መሰል ሰነዶችን በሚሰበስበው ዘ ብላክ ቫውት የተሰኘው ጆን ግሪንዋልድ ጁኒየር ያቋቋመው ድረ-ገፅ አማካኝነት ሲሆን እርስዎም መረጃዎቹን ከስር በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለረጅም ጊዜያት ሲቀርቡለት በነበሩት ጥያቄዎች መሰረት ሲ.አይ.ኤ ዘ ዩፎ ኮሌክሽን የተሰኘ ሲዲ ላይ ቀድሞ በሚስጥር ተይዘው የነበሩ መረጃዎቹን አንድ ላይ በሲዲ አማካኝነት ሰብስቦ አስቀምጦ ነበር፡፡ ጆን ሲዲውን ከተቋሙ የገዛው ሲሆን አሁን ላይ መረጃዎቹን ድረ-ገፁ ላይ ጭኖ በመጨረሱ ማንኛውም ሰው ድረ-ገፁን በመጎብኘት መረጃዎቹን በፒዲኤፍ መልኩ ማግኘት ይችላል፡፡ ይፋ ከሆኑት መረጃዎች መካከል በአወውያኑ 1976 እኩለ ሌሊት ላይ በአንድ የሩሲያ ከተማ ውስጥ የደረሰ ምስጢራዊ ፍንዳታን እና በሌላ ጊዜ በአዘርባጃን መዲና ባኩ ሰማይ ላይ የታየ ልዩ በራሪ ነገርን የተመለከቱት ይገኙበታል፡፡
ታድያ ዩፎን የተመለከቱ መረጃዎች ይፋ ሲሆኑ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፤ ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ላይም የአሜሪካን ባህር ኃይል በሦስት የተለያዩ ወቅቶች ቀርፆ ያስቀመጣቸውን ምንነታቸው ያልታወቁ ነገሮች በከፍተኛ ፍጥነት ሲበሩ የሚያሳዩ ምስሎችን ይፋ አድርጎ ነበር፡፡ በቀጣይም ከጥቂት ወራት በኋላ የአሜሪካን መከላከያ እና የስላላ ተቋማት ኃላፊዎች ስለ ዩፎዎች ሚያውቁትን እያንደንዱን ነገር በኮንግረስ ፊት ቀርበው እንደሚናገሩ የሚጠበቅ ሲሆን ባለፈው ወርም መሰል ጉዳዮችን ለሚከታተለው የኮንግረሱ ኮሚቴ ዩፎዎቹን የሚመለከት ሪፖርት በ180 ቀናት ውስጥ እንዲቀርብለት ኮንግረስ ጠይቆ ነበር፡፡
ሲ.አይ.ኤ በዩፎዎች ዙርያ አሉኝ የሚላቸውን መረጃዎች በሙሉ ይፋ አድርጊያለው ቢልም የቀሩ ድብቅ መረጃዎች ስላለመኖራቸው ማረጋገጥ አይቻል ይሆናል የሚለው ጆን ተጨማሪ መረጃዎች ካሉም ለማግኘት እንደሚጥር ድረ ገፁ ላይ ባሰፈረው ፅሁፉ ገልጿል፡፡ አሁን ላይ ድረ-ገፁ ከ2.2 ሚሊዮን በላይ ገፅ ያላቸው ዩፎን የሚመለከት ሰነድ መያዙ ሚነገርለት ሲሆን እነዚህም ጆን የ15 ዓመት ታዳጊ ከነበረበት ከ1996 (እ.አ.አ) አንስቶ ባቀረባቸው ከአስር ሺህ በላይ ጥያቄዎች አማካኝነት ማከማቸት የቻላቸው ናቸው፡፡
የድረ ገፁ ሊንክ https://www.theblackvault.com/documentarchive/ufos-the-central-intelligence-agency-cia-collection/?fbclid=IwAR2_Caclhnjgn6QnHYFKwE7UP7PWF18jAURcpmxQbQLpK1ysAIpZVZyTjgE

The Black Vault - Discover the Truth
UFOs: The Central Intelligence Agency (CIA) Collection - The Black Vault
Background Below you will find a collection of CIA related UFO records. The Black Vault's connection to the CIA in getting some of these UFO documents released goes back to 1996. Originally, the CIA would only release about 1,000 pages that had been previously…
የማሽተትን ስሜት ለኮምፒውተሮች
******************
ተመራማሪዎች ለኮምፒውተሮች የማሽተትን ብቃት እንዲኖራቸው የሚያደርግ የባዮሀይብሪድ ኦልፋክቶሪ ሴንሰር መስራታቸው ተሰማ፡፡ ከስሜት ህዋሳት መካከል የማሽተት ስሜት ለብዙ ህይወት ላላቸው ነገሮች ተፈጥሯዊ ስጦታ ነው፡፡ በሳይንስ ምርምር ውስጥ ከስሜት ህዋሳት ጋር የተያያዘ ከፍኛ ምርምር ተደርጓል፡፡ የኤልክትሮኒክ ቁሶች ድምጽን፣ እይታንና አካዊ ንክኪን (መስማት፣ ማየት፣ መንካት) በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ መፈጽም ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ማሽተት አንዱ ተፈጥሯዊ ስሜት ቢሆንም ለሳይንሱ አለም ግን እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ውጤት ካላገኙ እረፍት የማያቁት የዘርፉ ተመራማሪዎች የስነ-ህይወትና የኢንጅነሪንግ ክህሎቶችን በማቀናጀት ለኤሌክትኒክስ ቁሶች የማሽተት ብቃትን የሚያላብስ ባዮሀይብሪድ ግኝትን አስተዋውቀዋል፡፡ ይህ ግኝትም ሽታንና የጋዝ ውቅርን መለየት እንደሚያስችል ተነግሮለታል፡፡
ልዩ ልዩ ሽታዎችና በአየር ውስጥ የሚርመሰመሱ የተለያዩ ኬሚካሎች ስለ ከባቢ አየር ሁኔታ በጣም ጠቃሚ መረጃዎችን የያዙ ናቸው፡፡ ይሁን እንጄ ብቁ የሆነ ሴንስ ማድረጊያ መሳሪያ ባለመኖሩ ምክንያት ለከባቢ አየር ጥናት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ማሰባሰብ አልተቻለም፡፡ በቶኪዮ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ሾጂ ታኩቺ ስነ-ህይወታዊ ፍጥረታት ሽታን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጠቀሙ ገልጸው አሁን ላይ የሚገኙትን ስነ-ህየህወታዊ ሴንሰሮች ከሰው ሰራሽ ፈጠራዎች ጋር በማጣመር ከፍተኛ የማሽተት ብቃት ያላቸው ቁሶችን ለመስራት ጥረት እንዳደረጉ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ SciTechDaily

እቁብን ዲጂታል የሚያደርገው አዲስ መተግበሪያ
===================
እኛ ኢትዮጵያውያን አሉን ብለን ከምንኮራባቸው ባህላዊ የፋይናንስ ስርዓቶቻችን መመካከል አቁብ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፡፡ አሁን ደግሞ ይህ ባሀላዊ የቁጠባ ስርዓታችንን ዲጂታል በሆነ መልኩ እንዲከወን የሚያደርግ መተግበሪያ ይዞ መምጣቱንና በቅርቡም ለአገልግሎት እንደሚያበቃው መተግበሪያውን የሰራው የእቁብ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ ይናገራል፡፡ መተግበሪው የቁጠባ ስርዓቱን ከኤሌክትሮኒክስ ክፍያ የሚያቀናጅ እንደሆነም ተነግሮለታል፡፡ ድርጅቱ መተግበሪያው ይፋ በሚያደርግባቸው ሦስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ30 ሺህ በላይ ተጠቃሚዎችን የማፍራት ዕቅድን ይዟል፡፡
መተግበሪያው በበይነ መረብ አማካኝነት ሲሰራ እቁብተኞቹ ክፍያዎችን ከመከታተልም ባሻገር መረጃ እንዲለዋወጡ የሚያስችላቸው ይሆናል፡፡ እቁባቸውን በጊዜው ይጥሉ ዘንድ ማስታወሻ የሚልክላቸው መተግበሪያው በጊዜ የሚጥሉትንም ኋላ ላይ ማበረታቻ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ማን እቁቡን እንደጣለና እንዳልጣለ፣ ማን አርፍዶ ገንዘቡን እንደላከ እንደሆ መረጃ እንዲሰጥና በአካባቢያቸው ያሉ ሌሎች እቁቦችንም መፈለግ እንዲችሉ ሆኖ የተሰራ ነው፡፡ ሆኖም መተግበሪያ ተጠቃሚዎቹ ሌሎች እቁቦችን በሚቃኙበት ሰዓት እቁቡ የስንት ብር እንደሆነ ከማስመልከትና ለመቀላቀል ጥያቄ እንዲያቀርቡ ከማመቻቸት በቀር ሌሎች የእቁብ ቡድኑን መረጃዎች በሚስጥር ይጠብቃል፡፡
በመተግበሪያው እቁቦቹ ልክ እንደ ባህላዊ ስርዓቱ ሁሉ ከእቁብተኞች የሚላከውን ገንዘብ የሚቆጣጠር የየራሳቸው ሰብሳቢ ሲኖራቸው የእቁብ አወጣጡም እንዲሁ በእጣ የሚወሰን ይሆናል፡፡ ለአስተማማኝነቱ ሲባል መተግበሪያውን ለመጠቀምና እቁብተኛ ለመሆን ስም፣ አድራሻ እና የመታወቂያ ካርድ ማቅረብ ግን እንደ ግዴታ ተቀምጧል፡፡
መተግበሪያው ባህላዊው የቁጠባ ስርዓታችንን ማህበረሰባዊነቱን በጠበቀ መልኩ ወደ ዘመናዊ አሰራር እንደሚቀይረው የድርጅቱ ኃላፊዎች ይጠቁማሉ፡፡ አሁን ላይ መተግበሪያውን ከባንክ አገልግሎት ጋራ ለማስተሳሰር እና የገንዘብ ልውውጡንም ቀላል ለማድረግ ያስችል ዘንድ ከተለያዩ የባንክ ዘርፉ ባለድርሻዎች ጋራ እየተነጋገሩ መሆኑን የምትናገረው የእቁብ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ መስራች እና ቺፍ ቴክኖሎጂካል ኦፊሰሯ ዮሓና ኤርሚያስ ይህም በኢትዮጵያ ለሚካሄደው የፋይናንስ ቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትልቅ አስተዋፅዖን እንደሚያበረክት ገልፃለች፡፡
ድርጅቱ መተግበሪያውን የሚጠቀሙ እቁብተኞችን ታላሚ አድርገው ከሚሰሩ ማስታወቂያዎች ይሆናል ገቢውን የሚያገኘው፡፡
ምንጭ፡ Addis Fortune እና The Reporter

ዊንዶውስ 10X ወንጀልን ለመከላከል የሚያግዝ የፀረ-ሌብነት ጥበቃ ሊታከልበት ነው
=======================
ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት የተሰረቁ ኮምፒውተሮች እንደገና ተስተካክለው ወይም (resetting) ተደርገው ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የሚያስችል አዲስ የፀረ-ሌብነት ጥበቃ (anti-theft protection) በዊንዶውስ 10X ላይ እያዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ይህ ዊንዶውስ የተጫነባቸው ኮምፒውተሮች የፀረ-ሌብነት ጥበቃ ሞድ ከተጨመረላቸው በኋላ የግድ በተሰጣቸው የማይክሮሶፍት አካውንት የይለፍ ቃል የሚገለገሉ ሲሆን ይህን ኮምፒውተር ዳግም ለማስጀመር የሚፈልግ ሰውም ይህን የይለፍ ቃል የግድ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
ይህ ደግሞ ማንኛውም የተሰረቀ ኮምፒውተር እንደገና ተስተካክሎ ወይም (reset) ተደርጎ ጥቅም ላይ እንዳይውል በማድረግ የሌብነት ወንጀልን ለመቀነስ ሊያግዝ ይችላል፡፡ በዚህ ዊንዶውስ የሚገለጉ ሰዎች ንብረታቸው ቢሰረቅ እንኳን በአዲሱ ጥበቃ አማካኝነት ኮምፒውተራቸውን በማንኛውም ቦታ ሆነው መቆለፍ የሚያስችላቸው ሲሆን፤ ጎግል ባቀረበው ‘Find my device’ በተባለው የመፈለጊያ አማራጭ ደግሞ የኮምፒውተሩን መገኛ ሊረዱ ይችላሉ፡፡
የማይክሮሶፍት ባለሙያዎች እንደጠቀሱት አዲሱ የፀረ-ሌብነት ጥበቃ አሁን ላይ ሊሰራበት የታሰበው የዊንዶውስ አይነት መደበኛው ዊንዶውስ 10 ሳይሆን በሱ ቨርዥን በቀረበው ዊንዶውስ 10X ላይ የሚሰራ ሲሆን ወደፊት በሌሎች የዊንዶውስ አይነቶች ላይ የመተግበር እቅድ እንዳለም አስረድተዋል፡፡
ዊንዶውስ 10X አሁን ላይ ባለሁለት ስክሪን ባላቸው የኮምፒውተር አይነቶች ላይ እየተሞከረ ያለ ቢሆንም ወደፊት በሌሎች መደበኛ የላፕቶፕ አይነቶች እና የኮምፒውተር ዝርያዎች ላይ የመጠቀም እድል ሊኖር ይችላል፡፡
ምንጭ፡ Tech Radar

ቴክ-ሳይንስ መፅሔቶችን ለናንተው
================
ቀድሞ በየ ሦስት ወሩ ትወጣ የነበረው የቴክ ሳይንስ መፅሔት ካለፈው ዓመት አንስቶ እንደ አዲስ ከተዋቀረች በኋላ የወጡት ቅፅ 18 እና 19ኝን መፅሔቶችን እንካችሁ ብለናችኋል፡፡
በተለያዩ ዓምዶች ተዘጋጅተው የቀረቡት መፅሔቶቹ የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ፈጠራ ሰዎችን፣ የሀገራችን የተፈጥሮ ሐብት፣ የፖሊሲ ሁኔታዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን የሚዳስሱ ፅሑፎችን ያካተቱ ናቸው፡፡
በመፅሔቶቹ ከተካተቱት ውስጥ በቅፅ 18፤ በፕላስቲክ አጠቃቀማችን ላይ ከኢንዶኔዢያ የምንማረው ጉዳይ፣ ፕሮፌሰር ተከተል፣ አስደናቂው የሶፍ ኡመር ዋሻ፣ የቴሌፎን ቴክኖሎጂ ታሪካዊ ዳራ፣ የማይቻል ሚመስለውን ሰርቶ ያሳየን የፈጠራ ሰው፣ ግብርና ተኮር ሚቲዎሮሎጂና ኢትዮጵያ እና አነስተኛ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል በኢትዮጵያ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በቅፅ 19 ላይም ባዮስፌር ሪዘርቭ በአለም ያለው አንድምታ፣ ፕሮፌሰር ኢሳያስ፣ ቢግ ዳታ እና የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ፣ ያልታወቁ በራሪ አካላት (ዩፎ)፣ የፈጣሪዎች ስነ-ልቦና፣ አፍሪካና ቴክኖሎጂ፣ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ስርዓት፣ እንዲሁም ከወዳዳቁ ፕላሰቲኮች የጫማ ቀለም የሰራው ኢትዮጵያዊ እና ሌሎች ጉዳዮችን ይዘንልዎ ቀርበናል፡፡
በተጨማሪም በቀድሞ መልክ ከተዘጋጁት መፅሔቶች የመጨረሻው የሆነውን ቅፅ 17ን መመልከት ይችላሉ፡፡
ታድያ እርስዎም መፅሔቱን በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት ወደ ድረ-ገፃችን በማምራት ማውረድ ይችላሉ፡፡
ቴክ-ሳይንስ ቅፅ 17፤ http://techin.gov.et/post/632/
ቴክ-ሳይንስ ቅፅ 18፤ http://techin.gov.et/post/633/
ቴክ-ሳይንስ ቅፅ 19፤ http://techin.gov.et/post/634/
መልካም ንባብ !!!

ቴክ-ሳይንስ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም፤ በዛሬው መሰናዶም
===================
ስለ ፓርኪንሰን የተዘጋጀውን በአብይ ፕሮግራም (ክፍል ሁለት)፤
ኮምፓስን በቴክኖሎጂ ታሪክ፤
አካባቢ እና ደን ምርምር ኢንስቲትዩትን በተቋማት፤
ፕ/ር ዘመደ አስፋውን በተመራማሪዎች ታሪክ (ክፍል አራት)፤
እንዲሁም የቧንቧ ውሃ ሲመጣ የማሳወቂያ መልዕክት የሚሰጥ ፈጠራ ያበረከተልን ታዳጊን በብላቴናት ዝግጅቶቻችን ይዘንላችሁ እንቀርባለን፡፡
እነዚህን ለእርስዎም ሆነ ልጆችዎ የሚጠቅሙ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ተኮር ዝግጅቶች ከስኮላርሺፕ ጥቆማ ጋር በማዳበል ዛሬ ቅዳሜ በ10 ሰዓት በMOE ቲቪ ይዘንልዎ እንመጣለን፡፡ በተጨማሪም እዚሁ ጣብያ ላይ ማክሰኞ 10 ሰዓት ስለሚደገም ያመለጥዎትን መከታተል ይችላሉ፡፡
የዩትዩብ ቻናላችንንም (https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg) ሰብስክራይብ በማድረግ ከዓመታት በፊት ከተላለፈው የመጀመሪየው ክፍል አንስቶ ያሉትን ሁሉንም የቴክ ሳይንስ ፕሮግራሞች አንድ በአንድ መመልከትና ዕውቀትን መገብየት ይችላሉ፡፡