ማንጎ የፊት ቆዳ መሸብሸብን ለመቀነስ
***********************
እንደሌሎቹ አትክልትና ፍራፍሬዎች ሁሉ የማንጎ ፍሬ የሰውነታችን ህዋሳት በቶሎ እንዳይሞቱ የሚያደርግ ኬሚካል በውስጡ ይዟል፡፡ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የተሰራ አንድ አዲስ ጥናት ማንጎን መብላት አጠቃላይ ፍራፋፍሬን በመብላት ከሚገኝ ጥቅም በተጨማሪ በፊት ላይ የሚከሰትን የቆዳ መሸብሸብ እንደሚያስቀር አረጋግጧል፡፡
የወር አበባ ማየት ያቆሙ ሴቶች በሳምንት አራት ጊዜ ግማሽ የሻይ ብርጭቆ ጣፋጭ ማንጎ ቢበሉ በሁለት ወር ውስጥ 23 በመቶ የፊት ቆዳ መሸብሸብን መቀነስ ሲችሉ ከሌላ ሁለት ወር በኋላ ደግሞ ተጨማሪ 20 በመቶ መቀነስ ይችላሉ ሲሉ አጥኝዎቹ አረጋግጠዋል፡፡ አንዳንድ የማንጎ ዝርያዎች በብዛት የምንመገባቸው ከሆነ የከፋ የፊት ቆዳ መሸብሸብ የሚያስከትሉ እንደሆኑና ይህም ባላቸው ከፍተኛ የሆነ የስኳር መጠን ሊሆን እንደሚችል ግምቶች አሉ፡፡ ኤታውለፎ እየተባለ የሚጠራው የማንጎ ዝርያ ግን ከሌሎቹ ዝርያዎች በተቃራኒው ለፊት ቆዳ መሸብሸብ መድሃኒት ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡
በምርምሩ ወቅት 28 የእርግዝና ጊዜያቸውን የጨረሱ ሴቶች በሁለት ምድብ ተከፍለው ሙከራው የተሰራ ሲሆን ግማሾቹ ግማሽ የሻይ ብርጭቆ ማንጎ በሳምንት አራት ጊዜ ለተከታታይ አራት ወራት እንዲጠቀሙ ሲደረግ ግማሾቹ ደግሞ በተመሳሳይ ጊዜ አንድ ከግማሽ የሻይ ብርጭቆ ማንጎ እንዲጠቀሙ ተደርገዋል፡፡ የፊት ቆዳ መሸብሸብ ውጤቱም ከፍኛ ጥራት ባለው ካሜራ ክትትል ተደርጎበታል፡፡
በዚህም ከአራት ወር በኋላ ግማሽ የሻይ ብርጭቆ ማንጉ ሲጠቀሙ የነበሩ ሴቶች በፊታቸው ቆዳ ላይ ከፍተኛ የሆነ መሻሻል ማሳየት ችለዋል፡፡ ከዚህም በመነሳት በሳምንት ውስጥ የምንመገበውን የማንጎ መጠን በማስተካከል በፊታችን ላይ የሚደርስን የቆዳ መሸብሸብ መቀነስ እንችላለን የሚል ማረጋገጫን አጥኝዎቹ ሰጥተዋል፡፡
ምንጭ SciTechDaily

ዘንዶን መመገብ
በአሜሪካኗ የፍሎሪዳ ግዛት ዘንዶዎችን መመገብ ሊጀመር እንደሚችል ተነግሯል፡፡ የግዛቲቱ አስተዳደር ለአካባቢው መጤ የሆኑት የበርማ ዘንዶዎች ከቁጥጥር ውጪ ሆነው በመስፋፋታቸው ሳብያ ቁጥራቸውን ለመቀነስ ህዝቡ እንዲመገባቸው ሊያበረታታ ይችላል፡፡ አስቀድሞ ግን የዘንዶዎቹ ስጋ በሜርኩሪ አለመጠቃቱን ለማረጋገጥ የዱር ጥበቃ ኮሚሽኑ ከጤና ቢሮው ጋር በመሆን ምርመራን እያደረጉ ነው፡፡ ይህ ግን ለአንዳንዶች የዘገየባቸው ይመስላል፤ በደቡባዊ ፍሎሪዳ የውሃ አስተዳደር ውስጥ በዘንዶ አዳኝነት ተቀጥራ የምትሰራውና ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ቁጥራቸው የበዛ ዘንዶዎችን ማጣጣሟ የተዘገበላት ዶና ካሊል የዘንዶ ስጋ በጣም ጣፋጭ ሆኖ እንዳገኘችው ትናገራለች፡፡
የበርማ ዘንዶዎች ደቡባዊ ፍሎሪዳ ውስጥ በሚገኘው የኤቨርግሌድስ ብሄራዊ ፓርክ መስፋፋት የጀመሩት ከአውሮፓውያኑ 1990ዎቹ ጀምሮ ነበር፡፡ መጀመሪያ ላይ በቤት ውስጥ ከሚንከባከቧቸው አሳዳጊዎች አምልጠው እንደሆነ በሚገመት መልኩ ወደ አካባቢው የተሰራጩ ሲሆን ወደ ኋላ ስነ-ምህዳሩ ላይ ጥፋት ለማድረስ በቅተዋል (ከዚህ ቀደም ዘንዶዎቹን ለመቀነስ ታስቦ በግዛቲቱ የሚደረገውን የአደን ውድድር መዘገባችን ይታወሳል)፡፡ አሁን ላይ ዘንዶዎቹ በግዛቲቱ የሰሜን እና ምዕራባዊ ክፍሎች በመስፋፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ አካባቢው ላይ ኑሮዋቸውነ ያደረጉት የበርማ ዘንዶዎች በአማካኝ ከ1.8 እስከ 2.7 ሜትር ርዝመት ያላቸው ቢሆኑም እስከዛሬ ከተገኙት በርዝመት አቻ የለሽ ሆኖ የተመዘገበው 5.4 ሜትር ነው፡፡ ይህ ግዝፈታቸው በጣም የተወሰነ አዳኝ እንዲኖራቸውና በተቃራኒው ከበፊትም በአካባቢው የሚኖሩትን ከአዕዋፍ እስከ አርጃኖ ያሉ እንስሳትን እንዲመገቡ ያደረጋቸው ሲሆን ከታዳኝ እንስሳቱ ውስጥ የተወሰኑት የመጥት አደጋ የተጋረጠባቸው ብርቅዬ እንስሳት ናቸው፡፡
ይህ አይነት ወራሪ እንስሳትን ለምግብነት እንዲውሉ ማድረጉ በግዛቲቱ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደምም ከርከሮ እና ሌሎች ወራሪ እንሽላሊት እንዲሁም የአሳ ዝርያዎች እንደልብ ተበልተዋል፡፡ ሆኖም ዘንዶዎችን ለየት የሚያደርገው ሰውነታቸው ለሜርኩሪ ብክለት በይበልጥ ተጋላጭ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡ እንደ ማዕድን ማውጣት ያሉ የሰው ልጅ እንቅስቃሴዎች በተፈጥሮ ከሚገኝበት የምድራችን ክፍል ወደ ከባቢ አየር እንዲለቀቅ የሆነው ሜርኩሪ ከዝናብ ጋር ተቀላቅሎ በመዝነብ ወደ ውሃ አካላት ይገባል፤ ኤቨርግሌድ በዚህ ረገድ ከፍተኛ ተጋላጭነት አለው፡፡ ሜርኩሪው ወደ ውሃ አካላት በሚገባበት ወቅት የተለያዩ ደቂቀ አካላት ሜቲልሜርኩሪ ወደተባለ መርዛማ ቅርፅ ይለውጡታል፡፡ ከዚህ በኋላ በዚህ የተበከለ እንስሳ በሌላው እየተበላ ብክለቱ ከፍ ወዳሉት አዳኝ እንስሳት ይደርሳል፡፡
የሚተነፍስ እና ሚንቀሰቀስ ነገርን ሁሉ በመብላት የማይታሙት ዘንዶዎች በሜርኩሪው የተበከሉ እንስሳትን ሁሉ ሲያግበሰብሱ እንደመኖራቸው የስጋቸውን የመበከል እድል ከፍተኛ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው የተያዙ አንዳንድ ዘንዶዎች ለሰው ልጅ ጤናማ ነው ከሚባለው የሜርኩሪ መጠን በእጥፍ የበለጠ ይዘው ተገኝተዋል፡፡ ይህ የሜርኩሪ ይዘት ታድያ በሰው ልጆች ላይ የነርቭ፣ አተነፋፈስ እና ሌሎች የጤና ጉዳቶችን የማድረስ አቅም አለው፡፡ አስተዳደሩም በእባቦቹ ላይ ያለውን የሜርኩሪ መጠን ለመመርመር ማሰቡ ለዚህ ነው፡፡ ታድያ እስከ ዛሬ ዘንዶዎቹን ስመገብ የኖረችው ካሊ ጤና ድንገት ካሳሰብዎት በዘንዶዎቹ ስጋ ውስጥ ያለውን የሜርኩሪ መጠን የሚለካ መሳርያ ስላላት ከጉዳቱ ያመለጠች ይመስላል፡፡
ምንጭ፡ Live Science

የውሃ መልክ ያለው የጸሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፍ እንደ መስኮት
*******************************
በኮሪያ በሚገኝ ኢንኮን ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የተሰራ አንድ ምርምር ብርሃን መሉ ለሙሉ አስተላላፊ የሆነና ለመስኮት መስታወትነት ሊያገለግል የሚችል የጸሐይ ሀይል መሰብሰቢያ ንጣፍ የሚሰራበትን መንገድ ማበልጸጉ ተሰማ፡፡ ይህ ቀለም አልባ አስተላላፊ ንጣፍ በቤት መስኮቶች ላይ ተገጥሞ ኤሌክትሪክ በማመንጨት የወደፊቱን የቤት ውስጥ የሀይል ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡
ፈጠራው ከመደበኛው የጸሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፍ ብርሃን ሰብሳቢውን ክፍል ብቻ በመለየት ታይታኒየም ዳይኦክሳይድና ከፊል አስተላላፊ ከሆነ ኒኬል ኦክሳይድ ጋር በማቀናጀት የተሰራ እንደሆነ ተመራማሪዎቹ አሳውቀዋል፡፡ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነት በኋላ አብዛናዎቹ የአለማችን ሀገራት ከካርቦን ነጻ አለምን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የየበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ እንደሆነ በስፋ እየተነገረ ነው፡፡
በአማራጭ ሀይል ረገድ ተስፋ ሰጭ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በተለይ የጸሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፎች ከዋጋቸው፣ ከመፈጸም ብቃታቸውና ከአካባቢ ጋር ካላቸው ተስማሚነት አንጻር እጅግ ተመራጭ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ የሀይል ፍላጎትን ከማሟላት ጎን ለጎን ከእለት ተእለት መገልገያዎች ጋር ተቀናጅቶ ሲገኝ ደግሞ ተመራጭነቱ የበለጠ ይጨምራል፡፡
ለምሳሌ ያክል የዚህ የጸሐይ ሀይል መሰብሰቢያ እንደ የቤት መስኮት፣ የህንጻ ጣሪያዎች እና የሞባይል ስልክ ስክሪኖች ሆኖ ቢመጣ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት በመያዝ ተመራጭነቱ ከፍያለ ይሆናል፡፡ ብርሃን አስተላላፊ የሆነ የጸሐይ ሐይል በሰብሰቢያ ንጣፍ በሀሳብ ደረጃ የታወቀ ቢሆንም አዲሱ ግኝት ሀሳቡ ወደ ተግባር እንዲለወጥ አድርጎታል፡፡
ምንጭ: SciTechDaily

ሰብአ ሰገልን የመራችው ኮከብ፤ የትኛዋ ናት?
በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ሦስት ጥበበኛ ሰዎች የተወለደውን ንጉስ ፍለጋ አሁን ላይ “የቤተልሄም ኮከብ” ተብላ የምትታወቀው ኮከብን ተከትለው ወደ እየሩሳሌም ማቅናታቸው ተነግሯል፡፡ ሄሮድስን በማማከርም የተወለደውን ህፃን በቤተልሄም ማግኘታቸውን ይህ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ያስነብባል፡፡ ይህ ሁነት በሀይማኖት ውስጥ ካለው ቦታ ባለፈ ግን ለተመራማሪዎች አጓጊ የሆነ ጥያቄን ያጭራል፤ የትኛዋ ናት የቤተልሄም ኮከብ? ጥያቄው ከሃይማኖት እና ታሪክ ውጪም ያሉ ምሁራንን ሲያጠያየይቅ የቆየ ነው፡፡ ይህን ጉዳይ ለማብራራት ያለሙ ልዩ ልዩ የሕዋ ምርምር ሀልዮቶች ሲነገሩ ቢቆዩም አሁን ላይ ግን ወደ መልሱ እየቀረብን መስሏል፡፡
የቤተልሄም ኮከብ ኮሜት ወይም የፈነዳች ኮከብ አልነበረችም
ሀሌይ ተብላ የምትታወቀው ኮሜት በ11 ዓመተ ዓለም ትታይ ነበር፡፡ ግን ደግሞ ምድር በተሽከረከረች ቁጥር ቦታዋም እየተለወወጠ ስለሚመጣ የተጠቀሰችው ኮከብ የሀሌይ ኮሜት አትመስልም፡፡ ከዚህም ባሻገር በጥንት ጊዜ ኮሜቶች እንደ መጥፎና የጥፋት ምልክት ተደርገው ይታዩ ስለነበር ከሁነቱ ጋር ያላት ትስስር እጅጉን አጠራጣሪ ነው፡፡
ተመራማሪዎች በዚህ ወቅት የኮከብ ፍንዳታ ወይም ሱፕርኖቫ ስለመከሰቱ የሚያሳይ ማስረጃ አለማግኘታቸውም የኮከብ ፍንዳታን ከእጩነቱ ያገላል፡፡ በተጨማሪ ሰብአ ሰገል ይህን ተከትለው ቢሆን ኖሮ የተጓዙት በከዋክብቱ ባሕርይ ምክንያት ክብ እየዞሩ በቆዩ ነበር፡፡
ሌሎች ተመራማሪዎች እ.አ.አ 2005 ላይ የወጣን ጥናት ላይ ተመርኩዘው የሚሰጧቸው ሀልዮቶች ደግሞ በአንድሮሜዳ ጋላክሲ ውስጥ የተከሰተ የኮከ ፍንዳታን ለሁነቱ በምክንያትነት ያቀርባሉ፡፡ ሆኖም ምንም እንኳን ጋላክሲውን ያለ መሳርያ እርዳታ በአይናችን ልንመለከተው የምንችል ቢሆንም ኮከቡ ሲፈነዳ ግን በቴሌስኮፕ እርዳታ እንኳን የሚቻል አልነበረም፡፡
ኮከብ ሲባል ሰማዩ በከዋክብት መሞላቱን ለማመላከት ይሆን?
ይህ ወደ ሁለት ግምቶች ይመራናል፡፡ አንደኛው ሰብአ ሰገል ሰማዩን በኮከብ ቆጠራ አማካኝነት ተርጉመውት ነበር የሚለው ነው፡፡ በቦታው ሲደርሱ ሄሮድስን አቅጣጫ መጠየቃቸው ጉዞዋቸው እስከመጨረሻው ድረስ ሙሉ በሙሉ በኮከብ እየተመሩ ስላለማድረጋቸው ጥቁምታን ይሰጠናል፡፡ በጊዜው የኮከብ ቆጠራ በከፍተኛ ደረጃ ጥቅም ላይ ይውል የነበረ በመሆኑ ኮከቡን በምስራቅ አይተው የመጡት ሰብአ ሰገልም ኮከብ ቆጣሪዎች ይሆናሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ በፕላኔቶች እና ከዋክብት መካከል ልዩ ቅንጅት እንደመኖሩ ሰብአ ሰገል በከዋክብቱ መካከል የሰፈረውን ምስጢራዊ መልዕክት አንብበው ከሄሮድስ ዘንድ ሄደው ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ የከዋክብት ቆጠራ ጁፒተርን ከነገስታት ጋራ እንደማስተሳሰሩ እና ጨረቃም በ17 እንዲሁም 6 ዓ.ዓ በኤሪስ ህብረ ኮከብ ውስጥ እንደማለፏ መጠን የጁፒተር ዕይታ በጉዳዩ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ሊኖረውና የክርስቶስን መወለድም አመላክቶ ይችላል፡፡
ኮከቧ የጥምረት ውጤት ብትሆንስ?
ሌላኛው የህዋ ምርምር ማብራርያ በፕላኔት እና ከዋክብት መካከል የተፈጠረ ጥምረትን ተከትሎ የመጣ አብሪ ነገር በሰማይ ታይቶ ነበር የሚለው ነው፡፡ ይህ አይነት ጥምረት ሁለት ወይም ከዚያ የበለጡ የህዋ አካላት በጨለማ ሰማይ ሲገናኙ ከምድራችን ሆኖ ማየት ሲቻል የሚፈጠር ነው፡፡ ይህ ሁነት በተመሳሳይ ቦታ ላይ ተኮኖ ለቀናት ከፍ ሲልም ለሳምንታት በዚህ አኳሀን ሊታዩ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ጥበበኛ ሰዎችም ጥምረቱን እየተከታተሉ የነበር ከሆነ ወደ አንድ ቦታ መርቷቸው ይሆናል፡፡ የህዋ ተመራማሪው ማይክል ሞልናርም “ዘ ስታር ኦፍ ቤተልሄም” በሚለውን መፅሐፉ ትክክለኛው ሀልዮት ይህ ሊሆን እንደሚችል ያስቀምጣል፡፡ 17 እና 6 ዓ.ዓ የተከሰተው የፀሐይ፣ ጁፒተር፣ ሳተርን፣ እና ጨረቃ በኤሪስ ህብረ ኮከብ ላይ ያሳዩት መጣመር በተወሰኑ ምክንያቶች በመፅሐፍ ቅዱስ ከሰፈረው ታሪክ ጋር ይገጥማል፡፡ በመጀመሪያ ይህ ጥምረት የተፈጠረው ወደ ንጋት ላይ መሆኑ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ኮከቧ በንጋት ላይ እንደወጣች ተደርጋ ከመገለጿ ጋር ይገጥማል፡፡ ክርስቶስ ያለበት ቦታ ላይ ዳግም ከማየታቸው በፊትም ኮከቧ ከሰብዓ ሰገል ተሰውራ ነበር፡፡ ይህም ምድር ስትዞር አቅጣጫዋን መቀየሯንና ጁፒተርም የዕይታ አቅጣጫዋን በጨለማ ትታይበት የነበረውን ስፍራ መቀሯን ተከትሎ የመጣ ሊሆን የሚችል ነው፡፡
ሌሎች በተመሳሳይ ጊዜ የተከሰቱ ሁለት ጥምረቶችም ለጉዳዩ ቀረብ ብለው ተገኝተዋል፡፡ አንደኛው በሰኔ 17 2ኛው ዓ.ዓ ላይ የተከሰተው የጁፒተር፣ ቬኑስ እና ሬግዩለስ ኮከብ ግንኙነት ሲሆን ሁለቱ ፕላኔቶች ለየብቻቸው ይታዩ ከነበረው በላይ ደምቀው ያለ ምንም ቴሌስኮፕ እርዳታ በቅንጅት እንደ አንድ ኮከብ ሆነው ታይተው ነበር፡፡ ሌላኛው ጥምረት ስድስተኛው ዓ.ዓ ላይ በጁፒተር፣ ሳተርን እና ማርስ ፓይሲስ ህብረ ኮከብ ላይ የፈጠሩት ጥምረት ነው፡፡ ሆኖም ሁለቱም የተገለፁት ጥምረቶች መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ከተቀመጠው አኳሀን በማይገነኝ መልኩ የተፈጠሩ ናቸው፡፡
የማይፈታው ምስጢር
ተመራማሪዎች የቤተልሄም ኮከብን የሚያብራሩ ልዩ ልዩ ሀልዮቶችን ከስራ ውጪ ያደረጉ ቢሆንም ይህች ኮከብ የትኛዋ እንደነበረች ወይም ስለመፈጠሯ ሳይንስ ምላሽ ሳይሰጥ ሊቀር ይችላል፡፡ ሆኖም ጉዳዩ ዛሬም ሆነ ወደፊት የብዙ ተመራማሪዎችን የማወቅ ፍላጎት እየኮረኮረ እንደሚቀጥል ይጠበቃል፡፡

የሰዎችን የፊት ገጽ ፎቶ ወደ ስዕል የመቀየሪያ ስልት
*********************************
በህንድ በሚገኝ አንድ የሮቦቲክስ የምርምር ማእከል የሚሰሩ ተመራማሪዎች በቅርቡ የሰዎችን የፊት ገጽ ፎቶ ወደ ስእል መቀየር የሚያስችል የሰው ሰራሽ አስተውሎት መንገድ ማበልጸጋቸው ተሰምቷል፡፡ ይህ ስልትም ጆርዳን ከርቭ ከሚባለው የአሳሳል ስልት ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡ ግኝታቸውንም ኪትራካር ሲሉ ሰይመውታል፡፡ የቃሉ አቻ ፍችም ሰዓሊ እንደማለት ነው፡፡
ይህ ጆርዳን ከረፍቭ መነሻውና መድረሻው ተመሳሳይ የሆነ አንድን ስዕል ያለምም መቆራረጥ መሳል የሚያስችል ነጠላ መስመር ነው፡፡ ይህ ኪትራካር የተባለ ስልት የአንድን ፎቶ መሰረታዊና ጥቃቅን ነገሮች በመረዳት እና የተለያዩ ስዕላዊ ቴክኒኮችን በመጠቀም ስዕልን መስራት የሚያስችል ነው፡፡
እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ ይህ አዲሱ ስልት በመሰረታዊነት የሚሰራው ስራ አንድን የፊት ገጽ ፎቶ ወደ ጆርዳን ከርቪንግ አሳሳል ስልት መቀየር ነው፡፡ ሮቦቱ የተለያየ ቀለምና ውፍረት ያላቸውን መሳያ እስክርቢቶዎች የሚጠቀም እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ አንድ ደንበኛ ሰዓሊ ማድረግ ከሚችለው በተሻለ የአንድን ሰው ፊት ጥንቅቅ አድጎ ከ30 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ መሳል እደሚችል ኪትራካር ስለተባለው በሮቦት የታገዘ የአሳሳል ስልት ተነግሮለታል፡፡
ለስራው በተለያዩ ሀገራት የአእምሮ ንብረት ማረጋገጫ እየተሰጠው እደሆነ የገለጹት ተመራማሪዎቹ በቅርቡም በስፋ አገልግሎት ላይ እንደሚውል ተናግረዋል፡፡ ይህንንም መንገድ በማስፋ በሰዎች በቀላሉ የማሰሩ የተለያዩ ሞዴሎችን ለመስራት ማቀዳቸውን ተመራማሪዎቹ አስረድተዋል፡፡
ምንጭ፡ Tech Xplore

መላው ክርስትና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን በሙሉ፤ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!!! ሁላችሁም ባላችሁበት መልካም በዓልን ታሳልፉ ዘንድ ምኞታችን ነው፡፡
ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት
ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት
የቻይና ኳንተም ኮሚኒኬሽን ኔትወርክ
************************
ቻይና በአለማችን የመጀመሪያ የሆነውን ኢንተግሬትድ ኳንተም ኮሚኖኬሽን ኔትወርክ መገንባቷ ተሰማ፡፡ ይህ ኔትወርክ 700 የሚደርሱ የመሬት ውስጥ ገመዶችን ከሁለት የምድርና ሳተላይት መገናኛዎች ጋር የያዘ ሲሆን በሀገሪቱ ውስጥ ለሚገኙ ተጠቃሚዎች እንዲሆን 4,600 ኪሎ ሜትሮች ያክል የተዘረጋ ነው፡፡
አሁን ላይ ያሉ በይነ መረብ ላይ መሰረት ያደረጉ ልዩ ልዩ ተግባራ ለተለያዩ የሀክ ወይም ስርቆት አደጋዎች የተጋለጡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ቻይና የገነባችው ኳንተም ኔተወርክ የወደፊቱን የበይነ መረብ እንቅስቃሴ አደጋ በእጅጉ መቀነስ የሚያስችለውን ብቃት የተላበሰ እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡
ታማኝ በሆኑ የግንኙነት መስመሮች ምድር ውስጥ የተቀበረው መስመርና ሳተላይቱ ከ150 የሚልቁ የተለያዩ ተቋማትን ማገልገል በሚያስችል መንገድ ኢንተግሬትድ ተደርገዋል፡፡ ከእነዚህ ተቋማት መካከል ባንኮች፣ የሀይል ማሰራጫ ጣቢያዎችና የመንግስት ልዩ ልዩ ድረ-ገጾች ይገኙበታል፡፡ ተመራማሪዎቹ ይህ ስራ ከፍተኛ ስኬል ያለው ስራን ለመስራት እንደሚያስችል እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን የቻይናን ተሞክሮ ተከትለው ሌሎች ሀገራት የየራሳቸውን ብሔራዊ የኳንተም ኮሚኒኬሽን ኔትወርክ ቢገነቡ አለማቀፍ የሆነ ኔትወርከ ለመገንባት እንደሚያስችል ያላቸውን ተስፋ ተናግረዋል፡፡
በ2016 ቻይና የአለማችን የመጀመሪያ የሆነውን የኳንተም ኮሚኒኬሽን ሳተላይት ወደ ህዋ ማምጠቋ የሚታወስ ነው፡፡

የሰዎችን እድሜ ያረዝማል የተባለለት ምርምር
*************************
ተመራማሪዎች እርጅናን በማዘግየት የሰዎችን እድሜ ማርዘም የሚያስችል አዲስ የጅን ቴራፒ መንገድ ማበልጸጋቸው ተሰማ፡፡ በቻይና የሳይንስ አካዳሚ አካል በሆነው የዙኦሎጂ የምርምር ተቋም፣ በፔኪነግ ዩኒቨርሲቲ እና በቤጂንግ ጀኖሚክ የምርምር ተቋም የሚሰሩ ተመራማሪዎች የህዋሳትን የእርጅና ጊዜ በመቀነስ ቶሎ ማርጀትንና የእሜ ማጠርን ሊያስቀር የሚችል መንገድ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
በጥናቱም 100 የሚደርሱ ከእደሜ ጋር የተያያዙ የሰው ህዋሳት የተለዩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ለእርጅና የመዳረግ ከፍተኛ አቅም ባላቸው 50 እጩ ጅኖች ላይ ምርምር ተደርጓል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በጥልቀት በተደረገ ጥናት KAT7 የተሰኘ የሰዎችን አካላዊና ሁለንተናዊ እርጅና የሚያፋጥን ክፍል ተለይቷል፡፡
የምርምሩ ውጤትም ነጠላ የሆነ ለእርጅና መሰረት የሆነውን ጅን መሰረት ያደረገ የጅን ቴራፒ ሙከራ የተደረገባቸውን አይጦች እደሜ ማስረዘም ችሏል፡፡ በምርምሩ ሂደት የተገኙ ሌሎች ተስፋ ሰጭ ውጤቶች ይህን ምርምር ከቤተ ሙከራ አውጥቶ ክሊኒካዊ ሙከራን ማድረግ እንደሚያስችል ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

የሲጋራ ሱስን ማስወገድ የሚያስችል ውጤት የተገኘበት ምርምር
*********************
ሰዎች በልዩ ልዩ አጋጣሚዎች በሱሶች ልንጠመድ እንችላለን፡፡ አንዴ በሱስ ከተጠመድን በኋላ ሱሱን ብንወደውም ባንወደውም በቀላሉ ከእኛ ለማላቀቅ እንቸገራለን፡፡ ከተለመዱ በኋላ ለመተው ከሚያስቸግሩ ሱሶች መካከል አንዱ የሲጋራ ሱስ ነው፡፡ በዚህ ከሱስነቱ ባሻገር ከፍተኛ የሆነ የጤና ቀውስ የሚያስከትል መጥፎ ልምድ ብዙዎች ሲቸገሩበት ያታያል፡፡
በ2018 በተሰራ አንድ ጥናት አይጦችን በኒኮቲን ሱሰኛ እንዲሆኑ ከተደረገ በኋላ በቤተሙከራ የበለጸገ NicA2 የተሰኘ ኢንዛይም ሲሰጣቸው የነበረባቸውን ሱስ በሙሉ አስወግዶላቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ኢንዛይም በአይጦቹ ያለውን የኒኮቲን ፍላጎት ዘገምተኛ በሆነ መንገድ ስለሚያጠፋው ከፍተኛ መጠን ያለው NicA2 መጠቀም ነበረባቸው፡፡ መወሰድ ከሚገባው ከፍተኛ መጠን አንጻርም በፍጹም በሰዎች ላይ ሊሞከር የማይችል ሆኗል፡፡ ይህ ኢንዛይም ኒኮቲኑን ለማጥፋት የኤሌክትሮን አገናኝ ያስፈልገው ነበር፡፡ በሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ ተሰርቶ በነበረው ምርምር ሞሎኪዩላዊ ኦክስጅን በስህተት የኢንዛይሙ ኤሌክትሮን አክሴፕተር ተደርጎ ተወስዶ ነበር፡፡
አዲስ የተሰራው ምርምር ከላይ የተገለጸውን ስህተት ማስተካከል የቻለ እንደሆነ አጥኝዎቹ ተናግረዋል፡፡ በውጤቱም ሳይቶክህሮም ፕሮቲን ተፈጥሯዊ ኤሌክትሮን አክሴፕተር እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ግኝቱ በተለይ በሲጋራ ሱስ ለሚሰቃዩ ሰዎች ትልቅ የምስራችን ይዞ የመጣ ነው፡፡
ሲጋራ ማጨስ በቀላሉ መከላከል የምንችላቸው በአለማችን ካሉ ዋነኛ የበሽታ ምንጮች ውስጥ አንዱ ነው ያሉት ተመራማሪዎቹ በዚህ ሱስ የተጠቁ ሰዎች መፍትሄ የሚያገኙበትን የህክምና መንገድ ማዘጋጀት ከተቻለ በሰው ልጅ ጤና ዙሪያ ከፍተኛ መሻሻላ ማምጣት ይቻላል ሲሉ በምርምራቸው ውጤት ያላቸውን ተስፋ አስረድተዋል፡፡
ምንጭ Medical Xpress

አዲስ የተገኙት ድንክዬ ቀጭኔዎች
==============
የቀጭኔዎች ቁመተ ለግላጋነት በረጃጅም ዛፎች ላይ የሚገኙ ቅጠሎችን እንዲመገቡ የሚያስችል የተፈጥሮ ስጦታቸው ነው፡፡ ታድያ ከሰሞኑን ይፋ የተደረገወ በሁለት የተለያዩ የአፍሪካ ክፍሎች ላይ አጫጭር ቀጭነዎች የመገኘታቸው ዜና ለተመራማሪዎቹ አግራሞትን ፈጥሯል፡፡
ብዙውን ጊዜ የቀጭኔዎች ቁመት ከ4.5 እስከ 6 ሜትር የሚለካ ነው፡፡ ለቀጭኔዎች ጥበቃን ከሚያደርግ አንድ ድርጅት ጋር የሚሰሩት ተመራማሪዎች ግን በአውሮፓውያኑ 2018 ላይ 2.6 ሜትር ብቻ የሚረዝም ቀጭኔን በናሚቢያ መመልከት ቻሉ፡፡ ከዚህ ሦስት ዓመታትን ቀደም ብሎም ዩጋንዳ ውስጥ ባለ የዱር ፓርክ ምስሉ ላይ አጥሮ የሚታየውን ቁመቱ 2.8 ሜትር የሆነ ሌላ ቀጭኔ አግኝተውም ነበር፡፡ ተመራማሪዎቹ የሁለቱን አጫጭር ቀጭኔዎች መገኘት አስመልክቶ ባሳለፍነው ወር መቋጫ ላይ የብሪቲሽ ሜዲካል ጆርናል ላይ የጥናት ውጤታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
በጥናቱ ላይ እንደተነገረው ሁለቱም ቀደጭኔዎች ላይ የተለመደው አይነት ረጃጅም አንገት ያላቸው ሆነው ሲገኙ እግሮቻቸው ግን አጠር ብለው ወፋፍራም ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስኬሌታል ዲስፕሌዚያ የተሰኘው ይህ አይነት የቁመት እጥረት መከሰት በሰው ልጆች እና የቤት ውስጥ እንስሳት ላይ መመልከቱ አዲስ ባይሆንም የዱር እንስሳት ላይ ግን ብዙም አልተለመደም፡፡ በድርጅቱ አማካኝነት የዩጋንዳው መርኪሰን ፏፏቴዎች ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ ከተወሰዱት ምስሎች ላይ ቀጭኔዎቹ ያላቸውን በጡንቻ የፈረጠመ እግር መመልክት ይቻላል፡፡
ሆኖም የቀጭኔዎች ቁመት መርዘም ለምክንያት ነውና እነዚህ ድንክዬ ቀጭኔዎች ከረጃጅም ዛፎች ላይ የመመገብን ፀጋ የተነፈጉ መሆናቸውን የሚናገረው የቀጭኔዎች ተንከባካቢ ድርጅቱ መስራች ጁሊያን ፌነሲ አካላዊ ሁኔታቸውም ከሌሎች ቀጭኔዎች ጋር ፆታዊ ግንኙነት የመፈፀሙን ነገር በምኞት ከማለፍ በቀር የማይቻል እንደሚያደርግባቸው አክሎ ይገልፃል፡፡
ምንጭ፡ Reuters

እስካሁን ከተሰሩት የጠፈር ሮኬቶች ከፍተኛ ሃይል የሚኖረው አዲስ ሮኬት
በ322 የጫማ ከፍታ በመገንባት ላይ የሚገኘው አዲሱ የሮኬት ማስወንጨፊያ ወይም የጠፈር ማስጀመሪያ ስርዓት በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ የጠፈር ተመራማሪዎችን ወደ ጨረቃ ካስወነጨፈው ሳተርን ቪ (Saturn V) ከተሰኛው ከባድ የማስወንጨፊያ ስርዓት በእርዝመቱ አነስ ያለ ቢሆንም የግፊት አቅሙ እና የመሸከም ጉልበቱ በአለም ላይ የመጀመሪያው እንደሚያደርገው ተዘግቧል፡፡
ይህ የጠፈር ማስጀመሪያ ስርዓት ወይም (Space Launch System) በእቅዱ መሰረት ስራዎቹ የሚካሄዱ ከሆነ 24 ሺ ኪሎግራም የመሸከም አቅም የሚኖረው ሲሆን ስፔስ ሸትል ከተሰኘው ሮኬት በ2,000 ኪ.ግ በመብለጥም ከፍተኛ የመሸከም አቅም ያለው የማስወንጨፊያ ሮኬት ይሆናል፡፡
ከስፔስ ድረ ገፅ የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው መንኮራኩሮችን ወደጨረቃ ለማሰወንጨፍ ጥቅም ላይ የዋለው ሳተርን ቪ ከአዲሱ የሮኬት ማስወንጨፊያ (SLS) ጋር በዚህ የመሸከም አቅም ተቀራራቢ ቢሆኑም በተለያዩ የሮኬት ማስወንጨፊያ ደረጃዎች እና የነዳጅ አወሳሰድ ላይ SLS እጅግ የተሻለ በመሆኑ ወደጨረቃ የሚደረገውን ጉዞ ጨምሮ ሌሎች ተልዕኮዎችን በተሻለ ሁኔታ እንዲፈፅም ያስችለዋል፡፡
በናሳ የአርተሚስ ፕሮግራም የታቀፈው የዚሁ የሮኬት የሙከራ ሂደት ስምንት ደረጃዎች የነበሩት ሲሆን እስከ ታህሳስ 2020 ሰባቱ የሙከራ ሂደቶች መጠናቀቃቸውን እና በመጪው ጥር 17 የሮኬቱ የማስወንጨፍ ሙከራ እንደሚካሄድም የ SLS ዋና ዳይሬክትር ጁሊ ባስለር ተናግረዋል፡፡ ለሰዎች የጥልቅ ህዋ ምርምር እና ወደ ጨረቃ ለሚደረገው የሰዎች ጉዞ ትልቅ አገልግሎት ይሰጣል የተባለው ይህ ሮኬት እስካሁን ከታዩት ከፍተኛ ሃይል ያላቸው የጠፈር ማስወንጨፊያ ሮኬቶች በቀዳሚነት የሚጠቀስ መሆኑም በዘገባው ተገልጿል፡፡
ምንጭ፡ business insider africa