አፕል አዲስ የኮምፒውተር ኪቦርድ ሊያቀርብ ነው
********************************
በያዝነው ሳምንት የባለቤትነት ማረጋገጫ ፓተንት በአሜሪካው የፓተንትና የንግድ ምልክት ፈቃድ ሰጭ ተቋም ማረጋገጫ ያገኘው አዲሱ የአፕል የኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ የሚገኙ ቁልፎች ራሳቸውን አስፈላጊውን ተግባር መፈጸም በሚያስችል መልኩ የሚያላምዱ ናቸው ተብሏል፡፡
እያንዳንዱ ቁልፍ አንድን ተግባር ሰርተን እስክንጨርስ ድረስ ለዚያ ተግባር በሚያስፈልግ መልክ የሚላመዱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የድምጽ መቅዳት ተግባርን ለመፈጸም ስናስብ ቁልፎቹ ለድምጽ ቀረጻ ወደሚያስፈልጉ የተለያዩ ተግባራት ወዳላቸው መተግበሪያነት መለወጥ እንዲችሉ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም ደግሞ የፎቶ ኢዲቲንግ ስራን ለመስራት ስንዘጋጅ በኪቦርዱ ላይ የሚገኙ ቁልፎች ጥምር ተግባራትን እንድንፈጽም ያስችሉናል፡፡
አፕል ባቀረበው ኪቦርድ የሚገኙ ልዩ ልዩ ቁልፎች ምስሎችን በመከሰት መሰረታዊውን የጽሁፍ ስራ ሳያቋርጡ የተለያዩ ግብረ መልሶችን መስጠት የሚችሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ቁልፎች ካላቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል የኮምፒውተር ጌሞችን ለመጫወት የሚያስችሉ መሆናቸው አንዱ ነው፡፡ በዚህም ለአንድ የኮምፒውተር ጌም የሚያስፈልጉ ተግባራትን በማላመድ ቁልፎቹ ለማንኛውም አይነት ጌም መጫወቻነት ያገለግላሉ፡፡
በተጨማሪም ተጠቃሚዎች አንድን ጽሁፍ ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ መቀየር በሚፈልጉበት ወቅት የኮምፒውተር ቁልፎቹ ይህን ተግባር ለመፈጸም የሚያስችል ብቃትን ተላብሰዋል፡፡ ቁልፎቹ ከጠርሙስ፣ ሴራሚክ፣ ፖሊመርና ሳፋየር ከተባሉ ግብዓቶች የተሰሩ ናቸው፡፡
ባለቀው የፈረንጆች አመት ካምፓኒው አንድ ሌላ ለተንቀሳቃሽ መገልገያዎች የሚያገለግልና በማግኔት አማካኝነት የሚሰራ ኪቦርድ ፓተንት ማግኘቱ የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ Tech Xplore

ቴክ-ሳይንስ የቲቪ ፕሮግራም፤ በዚህ ሳምንት፡-
--------------------
ዓብይ ፕሮግራም፤ የበቆሎ ገዳይ ቫይረስን የሚከላከል ምርምር
ብላቴናት፤ የደህንነት ካሜራ የሰራው ታዳጊ
ተቋማት፤ የኢትዮጵያ ጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት
የቴክኖሎጂ ታሪክ፤ ካሜራ
የተመራማሪዎች ሕይወት ታሪክ፤ ፕ/ር ዘመደ አስፋው
ከዋናዎቹ ዝግጅቶቻችን በተጨማሪም የስኮላርሺፕ መረጃዎችንም ይዘን የምንመጣ ሲሆን እርስዎም ነገ ቅዳሜ 10 ሰዓት ላይ የቻናል ምርጫዎን MOE ቴሌቪዥን ላይ በማድረግ ይጠብቁን፡፡
በ MOE ቴሌቪዥን ከሚቀርበው በተጨማሪ ወደ ዩትዩብ ቻናላችን (https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg) ጎራ በማለት አዳዲሶቹን እና ከዚህ ቀደም የተሰሩትን ፕሮግራሞች በሙሉ መመልከት ይችላሉ፡፡

YouTube
EthioTunes
Share your videos with friends, family, and the world
የተሳትፎ ጥሪ፤ ለኢኖቬተሮች
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የኢኖቬሽን ባህልን ለማሳደግና ቀጣይነት ባለው መልኩ ኢኖቬተሮችን ለማፍራት ያግዝ ዘንድ የቅድመ-ኢንኩቤተር ፕሮግራም ተቋሙ አዘጋጅቷል፡፡ በዚህም ፕሮግራም የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች፣ ተመራማሪዎችና ሌሎች ማንኛውም መስፈርቱን የሚያሟሉ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች መሳተፍ የሚችሉበት ሲሆን የስራ ፈጠራ ሃሳባቸውን የሚያሳድጉበት እና ቢዝነስን የሚመሩበት ክህሎትን ይቀስሙበታል፡፡ ከአመልካቾች መካከል ሀያ አምስቱ ተመርጠው ከጥር 19 እስከ 21 2013 ዓ.ም ድረስ በሚካሄደው በዚህ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ መስፈርቱን የምታሟሉ ሁሉ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ከዛሬ ታህሳስ 23 አንስቶ እስከ ጥር 7 ድረስ መመዝገብና መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
መመዝገቢያ ሊንክ= https://tinyurl.com/Pre-Incubation-Program-2021
ለበለጠ መረጃ በኢ-ሜይል አድራሻችን startup@techin.gov.et ወይም አራት ኪሎ (ከፓርላማ ወደ ፒያሳ በሚወስደው ጎዳና) በሚገኘው ዋና ቢሮዋችን በአካል በመገኘት ሊጠይቁን ይችላሉ፡፡

Google Docs
Call for Pre-Incubation Program 2021
Program In Brief
The F.D.R.E Technology and Innovation Institute (TECHIN2) is highly delighted to announce that it has launched the “Pre-Incubation Program” for innovators/entrepreneurs to recruit technological innovation startup ideas and provide them a…

ባለ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ካሜራ
******************
ካሜራዎች የሚመለከቱትን ምስል ከማየት ባለፈ የሚረዱ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ምርምር በብሪስቶልና ማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ጥምረት መሰራቱ ተነገረ፡፡ በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች የተሰራው ምርምር ካሜራዎች የሚያዩትን ምስል ምንነት በጥልቀት በመመርመር እንዲረዱት የሚያስችል ነው፡፡ የሮቦቲክስና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ተመራማሪዎች በአሁኑ ወቅት ያሉ ካሜራዎች ምስሎችን ሴንስ የሚያደርጉበት መንገድ ችግር አለበት ብለው ያምናሉ፡፡
እነዚህ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ካሜራዎቹ ምስልን ለመቅዳት ዲዛይን በተደረጉ የካሜራ ሴንሰሮችና የቪዲዮ ጌሞችን ለማጫወት የሚያገለግሉ የኮምፒውቲንግ ቁሶችን በማጣመር የሚሰሩ በመሆናቸው ሰው ሰራሽ ክህሎት ምስሎችን የሚያገኘው የተለያዩ ቅጅዎች ከሴንሰር ወደ ፕሮሰሰር በሚያደርጉት ጉዞ ነው፡፡
ይህ ሂደት በካሜራችን እይታ ውስጥ አላስፈላጊ ምስሎች እንዲገቡ ያደርጋቸዋል፡፡ ለምሳሌ ራስ-ነድ በሆኑ መኪናዎች ከመንገድ ውጭ ያሉ ለጉዞው የማያስፈልጉ ምስሎች ይገባሉ፡፡ ይህ ምርምርም ያስፈለገው ይህን ችግር ለመቅረፍ ነው፡፡ በሂደቱም አንድን ምስል ሴንስ ማድረግና መረዳትን (learn) በአንድ ጊዜ በማጣመር ለሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚያገለግል ልዩ ካሜራን መፍጠር ተችሏል፡፡
ይህንን ፈጠራ በማበልጸግ ሂደት ውስጥ ተፈጥሯዊ የሆነውን የአይንና የአእምሮን ቅንጅት መሰረት አድርገው እንደሰሩ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ በኢንጂነሪንግ እና ፊዚካል ሳይንስ ምርምር ካውንስል በሚደገፈው ምርምር የተሰራው ካሜራ ከማሽን ለርኒንግ አቅሙ በተጨማሪ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው በመሆኑ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት እድገት ከፍተኛ አተዋጽኦ እንደሚኖረው ተነግሯል፡፡
ምንጭ፡ SciTechDaily

አዲሱን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ክለሳን አስመልክቶ የተደረገው ምክክር
=====================
ለአዲሱ ፖሊሲ ክለሳ ግብዓት ይሆን ዘንድ ዛሬ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተካሄደው ምክክሩ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የተውጣጡ ተሳታፊዎችን ተሳታፊ ያደረገ ነበር፡፡ በምክክሩ ላይ በሚኒስቴሩ የፖሊሲና ፊውቸር ፕላኒንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደስታ አበራ ቀድሞ በስራ ላይ ስለነበረው እንዲሁም ክለሳ ተደጎበት በመጣው ፖሊሲ ላይ ዝርዝር ማብራርያ ለታዳሚያኑ አቅርበዋል፡፡ የቀድሞው ፖሊሲ ችግሮች ቢኖሩበትም ምጣኔ-ሐብታዊ ዕድገት ማስመዝቡን የገለፁት አቶ ደስታ አጋጠሙት የተባሉት ተግዳሮቶችን በዝርዝር አስቀምጠዋል፡፡ ለአዲሱ ፖሊሲ ክለሳ መነሻ ሁኔታዎች ሆነው የተቀመጡትን ጉዳዮች እንዲሁም ክለሳው ሲሰራ የተከተላቸው ፍልስፍናዎች በአቶ ደስታ ገለፃ ውስጥ ተካተው ቀርበዋል፡፡
የፖሊሲ ክለሳው ታድያ በዋናነት ተግባር ላይ የቆየውን ፖሊሲ ድክመቶች በማሻሻል ላይ ያተኮረ ነው፡፡ እኛም 2012 እና በያዝነው ዓመት ታትመው ለህዝብ በደረሱት 18 እና 19ኛ እትም የቴክ-ሳይንስ መፅሔቶቻችን ላይ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲውን በስፋት መቃኘታችን ይታወሳል፡፡ በሁለቱ ተከታታይ ፅሁፎች ዳሰሳ ከተደረገባቸው የፖሊሲው አቅጣጫና ስትራቴጂ፣ ትግበራ፣ አፈፃፀም እንዲሁም ሌሎች ወሳኝ ጉዳዮች በተጨማሪ አሉበት የሚባሉ ክፍተቶችም በስፋት ተዳሰውበት ነበር፡፡ እዚህ ላይ ከተጠቀሱት ክፍተቶች ውስጥ በዋናነት ፖሊሲው ቴክኖሎጂን ወደ ሀገር ውስጥ አስገብቶ ከማላመድ ባሻገር ለኢኖቬሽን የሚገባውን ትኩረት አለመስጠቱ፣ ሀገር በቀል ዕውቀት ላይ በተገቢ መልኩ አለመስራቱ እንዲሁም የፖሊሲው ዕቅድ እና አተገባበር እርስ በእርስ መጣጣም አለመቻላቸው ይጠቀሳል፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ይፈታል የተባለለት አዲሱ የፖሊሲ ረቂቅ “በ2040 ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ለኢትዮጵያ ብልጽግና ዋነኛ መሣሪያ ሆኖ ማየት” የሚል ርዕይን አስቀምጦ ሲነሳ የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሰው ሃብት ልማት፣ አካባቢዊ ማህበራዊና ባህላዊ ልማት፣ የኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ልማት እንዲሁም አይ.ሲ.ቲ ልማት እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ጨምሮ በ12 ቁልፍ ናቸው ባላቸው ጉዳዮች ላይ ስትራቴጂዎችን የቀረፀ ነው፡፡
በዛሬው ምክክር ላይ ከገለፃው ባሻገር ከተጠሪ ተቋማት የመጡ ተሳታፊዎች በፖሊሲ ክለሳው ላይ ግብዓት የሚሆኑ አስተያየቶች የተሰጡበት ውይይትን አድርገዋል፡፡

ወደ ማርስ የምታቀናው "ውሻዋ" ሮቦት
-----------------------------
እንደ ኪዩሪሲቲ ያሉ ቀደምት የማርስ ሮቨሮች (rovers) የፕላኔቷን ገፀ ምድር በሚገባ በማሳስ አስገራሚ ግኝቶችን ለተመራማሪዎች ያቀበሉ ቢሆንም በሚታሰበው ልክ በቶሎ የሚላመዱ እና ከፍተኛ ፍጥነት የተላበሱ ባለመሆናቸው ሳይንቲስቶች የሚፈልጉትን ተጨማሪ የምርምር ስራ እንዲያካሂዱ አላስቻላቸውም ነበር፡፡ ታዲያ ሌሎች አማራጮችን ሲፈልጉ የነበሩት ተመራማሪዎች ከአመታት በፊት ቦስተን ዳይናሚክ በተባለ የሮቦት ኩባንያ ስትተዋወቅ የነበረችውን ውሻ መሰል ሮቦት በተመሳሳይ መልኩ በመስራት ለዚህ የአሰሳ ተልዕኮ እንዲያጯት ሆኗል፡፡
በዲሴምበር 14 2020 የአሜሪካን ጂዮፊዚካል ህብረት (AGU) ባዘጋጀው የቪዲዮ ኮንፈረንስ ላይ በተመራማሪዎች የተገለፀው የዚህች ሮቦት የመታጨት ዜና በናሳ የምርምር ተቋም ውስጥ አንድ አካል በሆነው JPL- ላብራቶሪ አስተባባሪነት የተከናወነ ነው፡፡ ተመራማሪዎች እንደሚያስረዱት ቀደም ብለው የተላኩት እንደ ስፕሪት፣ ኦፖርቹዩኒቲ እና ኪዩሪሲቲ ያሉ የማርስ ሮቨሮች አብዛኛውን ጊዜ ለጥ ባለ መሬት እንቅስቅሴያቸውን በማድረግ ልዩ ልዩ መረጃዎችን መሰብሰብ ቢችሉም ተመራማሪዎች የሚፈልጓቸው ወሳኝ መረጃዎች በኮረብታዎች፣ በዋሻዎች እና በሌሎች ከባድ ቦታዎች ላይ የሚገኙ በመሆናቸው ይህን ማድረግ የሚችሉ ሮቦቶች እጅግ ወሳኝ ነበሩ፡፡ ታዲያ ይህች አስገራሚ ሮቦት የመንቀሳቀስ እና የመቋቋም ችሎታዋ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ የተመራማሪዎችን የምርምር ፍላጎት በሚገባ እንደምትመልስ የሚጠበቅ ነው፡፡
Au-Spot የሚል ስያሜ ያላት ይህች ሮቦት አሁን ካሉት ሮቨሮች 12 እጥፍ ቅለት ያላት ስትሆን ይህም በፍጥነት መጓዝ እንድትችል እና ይበልጥ ተጣጣፊነት እንዲኖራት የሚያስችላት ነው፡፡ 32 ኪሎ የምትመዝነው ውሻዋ ሮቦት በሰዓት አምስት ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ የምትንቀሳቀስ ሲሆን፤ ምናልባት ደጋግማ በምትወድቅበት ጊዜ በቶሎ መነሳት እንድትችል የሚያግዝ የማገገሚያ አልጎሪዝምም ተዘጋጅቶላታል፡፡ ሮቦቷ ራስ-ገዝ በሚባል ደረጃ ከሚያጋጥሟት የመንገድ አማራጮች የተሻለውን እንድትመርጥ የሚያስችል አቅም ያላት ሲሆን ከርቀት መጠቆም የሚያስችል ፕሮሰሰር ጨምሮ 3D ካርታ መፍጥር የሚያስችል የምስል፣ የሙቀት እና የእንቅስቃሴ ሴንሰሮችንም አቅፋ ይዛለች፡፡
CoSTAR በተባለ የሮቦት ምርምር ተቋም ውስጥ በሚሰሩ 60 ሳይንቲስቶች የተፈጠረችው ይህች ሮቦት በቅርብ ጊዜ ለምታደርገው የማርስ ጉዞ መሬት ላይ በሚገኙ ዋሻዎች እና ኮረብታማ ስፍራዎች ላይ ከባድ ስልጠናዎችን እያካሄደች ሲሆን፤ ስልጠናዋን አጠናቃ ወደፕላኔቷ በምታመራበት ወቅት እስከዛሬ ያልተሰሙ አስገራሚ የምርምር ውጤቶችን ልታስገኝ እንደምትችልም በጉጉት ይጠበቃል፡፡ ምንጭ፡ Bigthink

ምድር እየሰመጠች ነው
===========
በ20 ዓመታት ውስጥ ብቻ በተለያዩ ቦታዎች የሚከሰተው የመሬት መስመጥ 19 በመቶ የሚሆነውን የምድራችን ነዋሪ ተፅዕኖ ውስጥ እንደሚከተው በዩኔስኮ ድጋፍ ሰጪነት የተደረገ አዲስ ጥናት አስታውቋል፡፡ አንድ ካልተባለ የሰው ልጆች ተግባራት፣ ከድርቅ እና የባህር ውሃ መጨመር ጋር በመተባበር ብዙ የባህር ዳርቻ ከተሞችን በከፍተኛ ጎርፍ እንደሚያጥለቀልቋቸውም ተነግሯል፡፡ ባለፈው አስር ዓመት ውስጥ የኢንዶኔዢያ መዲና የሆነችው ጃካርታ 2.5 ሜትር ወደታች በመስመጧ ሳብያ የሀገሬው መንግስት አዲስ መዲና ፍለጋ ወደ በቦርኔኦ ደሴት ለማምራት አቅዷል፡፡ በአውሮፓም 25 በመቶው የሆላንድ መሬት ከባህር ጠለል በታች መገኘት ምክንያቱ ይኸው የመሬት መስመጥ ነው፡፡
በጥናቱ ላይ በመሪ አጥኚነት የተሳተፉት ጌራርዶ ሄሬራ-ጋሪንቻ እንደሚሉት ዝናብ አጠር የሆኑና ህዝብ እጅጉን ታጭቆ የሚኖርባቸው ወይም የመስኖ እርሻ የተስፋፋባቸው አካባቢዎች የከርሰ ምድር ውሃን በስፋት አውጥተው በሚጠቀሙበት ጊዜ ውሃን በውስጡ የያዘው የድንጋይ ንጣፍ (Aquifer) ከሚያገኘው የሚሰጠው በመብለጡ እየሳሳ ይመጣል፡፡ በዚህም የሰው ብዛትና ውሃ ቅርምቱን በህግ መገደብ አለመቻሉ የመሬት መስመጡን በዋናነት እያስከተለ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ኢራን ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ሕዝቧ በእጥፍ ያደገ ቢሆንም የከርሰ ምድርን ውሃ ማውጣቱ ላይ ግን ተገቢው ቁጥጥር ሳታደርግ ቆይታለች፡፡ ታድያ አሁን ላይ የሀገሪቱ ከተሞች በየዓመቱ 25 ሴ.ሜ በመስመጥ ከዓለማችን ቀዳሚዎቹ ቁልቁል ተጓዦች መካከል ለመሆን በቅተዋል፡፡
ምንም እንኳን የመሬት መስመጥ አዲስ ጉዳይ ባይሆንም በአብዛኛው ግን በአካባቢያዊ ጉዳይነት ተወስኖ ቆይቷል፡፡ በዓለም አቀፍ አጥኚዎች ቡድን የተዘጋጀው አዲሱ ጥናት ግን ቀድሞ የነበሩትን ጥናቶች የሚያጠናክር፤ ግን ደግሞ የትኛዎቹ የምድራችን ክፍሎች በከፍተኛ የመስመጥ አደጋ ውስጥ ይገኛሉ የሚለውን ለመላው ዓለም በሚሰራ መንገድ ያቀረበ ነው፡፡ ችግሩ ዋነኛ መነሻ ከማያዛልቅ ግብርና እና አየር ንብረት ለውጥ ጋር የተሳሰረው ዓለም አቀፍ ጉዳይ መሆኑን ያመላከተው ጥናቱ አሜሪካን፣ ቻይና እና ህንድ የምግብ ፍላጎትን ለማሳካት ሲሉ የሚያደርጉት የከርሰ ምድር ውሃ ብዝበዛ የኋላ ኋላ መላውን ዓለም ተፅዕንዖ ስር እንደሚከትም ማስቀመጡን ሄራርዶ ይናገራል፡፡
ነገሩን የከፋ ሚያደርገው አየር ንብረት ለውጥ ረጃጅም የድርቅ ወቅቶችን እንደሚያመጣ የሚጠበቅ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የከርሰ ምድር ውሃ ይበልጥ እንዲወጣ ዕድል መፍጠሩ ነው፡፡ የባህር ውሃም ቢሆን በቀጣዩ ክፍለ ዘመን ከፍታው እስከ አንድ ሜትር እንደሚጨምር መተንበዩን ተከትሎም ሌሎች የባህር ዳርቻ ከተሞችም የጃካርታ እጣ ፈንታ ሊገጥማቸው መቻሉን መገመት አያዳግትም፡፡ ሆኖም የመሬት መስመጥ ከአየር ንብረት ለውጥ ይልቅ ለመፍታት ቀላል ችግር መሆኑን ጌራርዶ ይናገራል ባለፈው ክፍለ ዘመን ጅማሮ ላይ ቶኪዮ ገጥሟት የነበረውን የመስመጥ አደጋ የከርሰ ምድር ውሃ አወጣጥን የሚቆጣጠሩ ደንቦችን በማውጣት መፍታት መቻሏን በመልካም ምሳሌነት እያስቀመጠ፡፡
ምንጭ፡ The Guardian

የዚንክ ባትሪዎችን ታዳሽ የማድረጊያ መንገድ ተገኘላቸው
********************************
ከቻይና፣ ጀርመንና አሜሪካ የተውጣጣ የተመራማሪዎች ቡድን የዚንክ ባትሪዎችን ታዳሽ ማድረግ የሚያስችልን መንገድ ማበልጸጉ ተሰማ፡፡ ከሶስቱ ሀገራት የተውጣጣው የምርምር ቡድን አልካላይን ያልሆኑ ኤሌክትሮላይቶችን በመጠቀም ከተለመደው ዲዛይን የተለየ የዚንክና የኦክስጅን ኤሌክትሮኖች ጥምረት የሆነ አዲስ ባትሪን ሰርቷል፡፡
በአሆኑ ወቅት በጣም የተለመዱት ባትሪዎች የአልካላን ባትሪዎች ሲሆኑ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ባትሪዎች ዚንክን በዋና ግብዓትነት የሚጠቀሙት ለአጠቃቀም ምቹ በመሆኑና ዋጋውም በጣም ቀላል በመሆኑ ነው፡፡ ሌላኛው ኤሌክትሮድ አየርን በመጠቀም የተሰራ ነው፡፡ ይህ ዲዛይን ዚንክን መሰረት ያደረጉ ባትሪዎች በከፍኛ መጠን እንዲመረቱ ያስችላል፡፡
በአዲሱ ግኝት ተመራማሪዎቹ የዚንክ ባትሪዎችን ታዳሽ የማድረጊያ መንገዶችን አስተዋውቀዋል፡፡ ይህንን አዲስ ባትሪ ለመስራት ተመራማሪዎቹ ትክክለኛውን አልካላይን ያልሆነ ኤሌክትሮላይት የመረጡ ሲሆን ዚንክ-ኦክስጅን-ዚንክ ፕርኦክሳይድ የሆነ የሁለት ኤሌክትሮኖች ጥምረትን የሚጠቀም ባትሪን ሰርተዋል፡፡ ይህም ከተለመደው ባትሪ የበለጠ በድጋሚ ጥቅም ላይ እንዲውል አስችሎታል፡፡ ተመራማሪዎቹ ኤሌክትሮላይቶቹን ውሃ እንዳያገኛቸው በማድረግ ውሃ ወደ ካቶዱ እንዳይጠጋ ማድረግ ችለዋል፡፡ አዲሱ ዲዛይን በተሞከረበት ወቅት በድጋሜ ጥቅም ላይ ሲውል ሀይልን ለ1600 ሰዓታት ያክል መያዝ እንደሚችል መረጋገጡን ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ መረጃውን ከTech Xplore አግኝተነዋል፡፡

ማንጎ የፊት ቆዳ መሸብሸብን ለመቀነስ
***********************
እንደሌሎቹ አትክልትና ፍራፍሬዎች ሁሉ የማንጎ ፍሬ የሰውነታችን ህዋሳት በቶሎ እንዳይሞቱ የሚያደርግ ኬሚካል በውስጡ ይዟል፡፡ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የተሰራ አንድ አዲስ ጥናት ማንጎን መብላት አጠቃላይ ፍራፋፍሬን በመብላት ከሚገኝ ጥቅም በተጨማሪ በፊት ላይ የሚከሰትን የቆዳ መሸብሸብ እንደሚያስቀር አረጋግጧል፡፡
የወር አበባ ማየት ያቆሙ ሴቶች በሳምንት አራት ጊዜ ግማሽ የሻይ ብርጭቆ ጣፋጭ ማንጎ ቢበሉ በሁለት ወር ውስጥ 23 በመቶ የፊት ቆዳ መሸብሸብን መቀነስ ሲችሉ ከሌላ ሁለት ወር በኋላ ደግሞ ተጨማሪ 20 በመቶ መቀነስ ይችላሉ ሲሉ አጥኝዎቹ አረጋግጠዋል፡፡ አንዳንድ የማንጎ ዝርያዎች በብዛት የምንመገባቸው ከሆነ የከፋ የፊት ቆዳ መሸብሸብ የሚያስከትሉ እንደሆኑና ይህም ባላቸው ከፍተኛ የሆነ የስኳር መጠን ሊሆን እንደሚችል ግምቶች አሉ፡፡ ኤታውለፎ እየተባለ የሚጠራው የማንጎ ዝርያ ግን ከሌሎቹ ዝርያዎች በተቃራኒው ለፊት ቆዳ መሸብሸብ መድሃኒት ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡
በምርምሩ ወቅት 28 የእርግዝና ጊዜያቸውን የጨረሱ ሴቶች በሁለት ምድብ ተከፍለው ሙከራው የተሰራ ሲሆን ግማሾቹ ግማሽ የሻይ ብርጭቆ ማንጎ በሳምንት አራት ጊዜ ለተከታታይ አራት ወራት እንዲጠቀሙ ሲደረግ ግማሾቹ ደግሞ በተመሳሳይ ጊዜ አንድ ከግማሽ የሻይ ብርጭቆ ማንጎ እንዲጠቀሙ ተደርገዋል፡፡ የፊት ቆዳ መሸብሸብ ውጤቱም ከፍኛ ጥራት ባለው ካሜራ ክትትል ተደርጎበታል፡፡
በዚህም ከአራት ወር በኋላ ግማሽ የሻይ ብርጭቆ ማንጉ ሲጠቀሙ የነበሩ ሴቶች በፊታቸው ቆዳ ላይ ከፍተኛ የሆነ መሻሻል ማሳየት ችለዋል፡፡ ከዚህም በመነሳት በሳምንት ውስጥ የምንመገበውን የማንጎ መጠን በማስተካከል በፊታችን ላይ የሚደርስን የቆዳ መሸብሸብ መቀነስ እንችላለን የሚል ማረጋገጫን አጥኝዎቹ ሰጥተዋል፡፡
ምንጭ SciTechDaily