TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ሁለቱ የምርምር ተቋማት በጋራ ለመስራት ከስምምነት ደረሱ
=====================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ጋራ በተቋማዊ የመረጃ አያያዝ ሲስተም ዝርጋታ፣ ዲታ-ቤዝ ወይም በመረጃ አያያዝ ስርአት ግንባታ ብሎም በፖሊሲ ትንተና እና ምርምር ዘዴን ጨምሮ በ12 አባይት ጉዳዮች ላይ በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከ6 እስከ 7 ቢሊዮን ዶላር በሚደርስ ወጪ ወረዳ ድረስ የዘለቀ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ብታከናውንም ስራ ላይ አለመዋሉን ያወሱት የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ሁለቱ ተቋማትም ኢንፎርሜሽን እና ኮምዩኒኬሽን ላይ ማዕከል አድርገው በሰው ኃይል ማብቃት ላይ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በጥቂት ወራት ውስጥ የትግበራ እቅድ ተዘጋጅቶ በቀጥታ ወደ ስራ መገባት እናዳለበት የተናገሩት ዶ/ር መኩሪያ ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና ለምታደርገው ጉዞም የበኩላችንን ጥረት እንደምናደርግ ተስፋ አለኝ ብለዋል፡፡
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከእኛ ጋር ለመስራት በመፍቀዱ ደስተኛ ነን ያሉት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ ተቋማቸውን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ማብራርያ የሰጡ ሲሆን ወደፊትም በጋራ የተሰሩ ስራዎችን ይዘው ተለቅ ባለ መድረክ እንደሚገናኙ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡
ዛሬ ጠዋት በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የተፈረመው ይህ ስምምነት ለሦስት ዓመታት እንዲቆይ የታቀደለት ሲሆን አተገባበሩም በሁለቱ ተቋማት ዋና ዳይሬክተሮች የሚመራ ዓብይ ኮሚቴ አማካኝነት ክትትል ሚደረግበት ይሆናል፡፡
በጀርመኑ ናዚ ተወስዶ የነበረው የፖላንድ ቤተ-ክርስቲያን ጥንታዊ ደወል
***********************************
1555 ዓመታትን ያስቆጠረው የፖላንድ ቤተ-ክርስቲያን ጥንታዊ ደወል በጀርመኖች በሁለተኛው የአለም ጦርነት ከተወሰደ ከ77 ዓመታት በኋላ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ተወሰነ፡፡ የቤተ-ክርስቲያኗ ተከታዮች የደወሉን ፍለጋ ከሁለት አመታት በፊት የጀመሩት ሲሆን ደወሉ በመገኘቱ እጅግ እድለኞች ሆነዋል፡፡ ምክያቱም በወቅቱ ናዚ ከ80 ሺህ በላይ ደወሎችን ለመሳሪያ ማምረቻ ግብኣትነት በእሳት እንዳቀለጠ መታወቁ ነው፡፡
ከጦርነቱ በኋላ በብረት ይዞታቸው ምክንያት ያልቀለጡ ደወሎች ወደ ተዘረፉበት ቦታ የመመለስ እድል ቢገጥማቸውም ይህ 400 ኪሎ የሚመዝን ደወል ግን ከሌሎች 1300 ከሚጠጉ ደወሎች ጋር በሀምቡርግ ተቀምጦ ነበር፡፡
አንድ ቅርስ ቅርስ ሊባል የሚችለው ታሪኩ ከቅርሱ ባለቤት ጋር አብሮ የሚነገር ሲሆን ነው፡፡ ለምሳሌ ጀርመናውያን ከላይ የተገለጸውን ደወል ቅርሳችን ነው ለማለት የሚያስችል ምንም አይነት መነሻ የላቸውም፡፡ የታሪካቸው አንድ አካል ሊያደርጉት ቢፈልጉ እንኳን የዘረፋ ታሪክ ምንም የሚያኮራ ነገር ስለሌለው ወደ ቦታው እንዲመለስ መወሰናቸው ትክክለኛ ውሳኔ ነው፡፡
በዚህ ረገድ የጥንታዊው የአክሱም ስልጣኔ መገለጫ የሆነውን የአክሱም ሀውልትን ማየት መልካም ነው፡፡ ወደ ኢጣሊያ በዘረፋ ሄዶ በሮም አደባባይ ተተክሎ የነበረው ይህ ሀውልት ከኢጣሊያ ስልጣኔ፣ ባህል፣ የኪነ ህንጻ ጥበብ ከሌላም ከየትኛውም አይነት ሁኔታ ጋር የማይስማማ በመሆኑ በወቅቱ በተደረገ ጥረት ሊመለስ ችሏል፡፡
ሌሎች በተለያዩ ጊዜያት በተለይ ወደ አውሮፓ ሀገራት በተለያዩ ሁኔታዎች የተወሰዱ የሀገራችን ቅርሶች እንዳሉ እሙን ነው፡፡ አንዳንዶቹ በሚደረጉ ጥቂት ጥረቶች እየተመለሱ ቢሆንም ለምሳሌ እንግሊዞች በየሙዚየሞቻቸው በድብቅም በግልጽም ያስቀመቷቸው ልዩ ልዩ የሀገራችን ቅርሶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡
ምንም እንኳን ሙዚየሞቹ እጅግ ዘመናዊ ቢሆኑም በውስጣቸው የራስ ያልሆነ ነገርን ሰብስቦ ሙዚየም አለኝ ማለት ፍትሀዊነቱ አጠራጣሪ ነው፡፡ ይህን እንደማሳያ እና የመረጃ ምንጫችን ለሆነው BBC እናንተም ቤት እሳት አለ ለማለት አቀረብነው እንጂ በብዙዎቹ የአውሮፓ ሀገራት የሚገኙ ቅርሶቻችን ስፍ ቁጥር የላቸውም፡፡
ምንጭ BBC
የእንጨት ሳተላይት ሊሰራ ነው?
********************
የጃፓኑ ሱሚቶሞ ፎረስተሪ ከኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ ጋራ በመሆን እንጨትን በሳተላይት ግንባታ ለመጠቀም የሚያስችል ሙከራ እንደሚያደርግ ይፋ አድርጓል፡፡ ፕሮጀክቱ ላይ ባለሙያዎች የተለያዩ የእንጨት ዓይነቶችን ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እንደሚፈትኑም ተነግሯል፡፡
አሁን ላይ ሳተላይቶች በዋናነት የሚገነቡት አስቸጋሪ የአየር ንብረት እና ከፍተኛ ጨረርን መቋቋም በሚችሉት አልሙኒየም፣ ኬቭላር እና ድብልቅ አልሙኒየሞች ነው፡፡ ጠንካራ ጎናቸው ታድያ በራሱ ጉዳትም አለው፤ አገልግሎታቸው ካበቃ በኋላ እንኳን ለረጀም ጊዜ በምህዋራቸው እየተንቀዋለሉ እንዲቆዩና የጠፈር ላይ ቆሻሻ ሆነው እንዲቀሩ ያደርጋቸዋልና፡፡ እንደ ዓለም የምጣኔ ሐብት ጉባኤ (World Economic Forum) ከሆነ በዚህ ሰዓት 6ሺህ ያህል ሳተላይቶች ምድራችንን እየዞሯት ቢሆንም ከእነርሱ ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ ያሉት ከ60 በመቶ አይበልጡም፡፡ እንደ ዘርፉ ተዋናዮች ትንበያ በቀጣዩ አስር ዓመት ውስጥ አንድ ሺህ አዳዲስ ሳተላይቶች በየዓመቱ ወደ ጠፈር እነዲመጠቁ ይደረጋል፡፡ አንድ ሳተላይት አገልግሎት ውስጥ የሚቆይበትን እድሜ ከግንዛቤ ስናስገባ ይህ ሁኔታ በሺዎች የሚቆጠሩ አገልግሎታቸውን ጨርሰው የሚዞሩ ስራ-ፈት ሳተላይቶችን በቅርቡ ይፈጥርልናል ማለት ይሆናል፡፡ ታድያ ሳተላይቶቹ በህዋ ላይ ሲንቀሳቀሱ በሰዓት በሺዎች ኪሎሜትሮች ፍጥነት እንደመጓዛቸው መጠን ሰውን የጫኑትም ሆነ ያልጫኑት ሳተላይቶችን አደጋ ውስጥ ሊከቷቸው ይችላል፡፡ አሁን ላይ የጠፈር ላይ ቆሻሻ ጠንከር ያለ ችግር እየሆነ መምጣቱ ብዙዎችን ያሳምናል፡፡ ነገሩን የከፋ በሚያደርግ መልኩ ለሳተላይቶች ግንባታ ጥቅም ላይ ሚውለው አልሙኒየም ሳተላይቱ ዳግም ወደ ምድር እንዲመለስ በሚደረግበት ጊዜ የመፈረካከስ ባህርይ ያለው መሆኑ ተደርሶበታል፡፡ ይህም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ጥቃቅን የአልሚኒየም ስባሪዎች ለረጅም ዓመታት ምድራችንን ከበው በጠፈር ላይ እንዲቆዩ በማድረግ ምናልባትም ከባቢ አየር ላይ ጭምር ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ችግሮች ተደማምረው ነው ጃፓናዊያን ተመራማሪዎቹ ባህላዊ ሳተላይት መስሪያ ቁሶችን በእንጨት ለመቀየር እንዲንቀሳቀሱ ያደረጋቸው፡፡
በእንጨት ላይ ተመስርቶ የሚሰራ ሳተላይት በዋናነት የሚሰጠው ጥቅም ወደ ምድር ሲመለስ ሙሉ ለሙሉ መቃጠል መቻሉ ነው፡፡ በተጨማሪነትም የሳተላይቱን ውጪያዊ ሽፋን በእንጨት መስራት ኤሌክትሮማግኔቲካዊ ሞገዶች በውስጡ ሰርገው እንዲያልፉ በማድረግ አንቴናዎች ሳተላይቱ ውስጥ በሚቀመጡ መሳርያዎች እንዲተኩ ያስችላል፤ ይህም ሳተላይቶቹ ንድፋቸውም ሆነ ወደ ጠፈር የሚመነጠቁበትን ሂደት ቀላል እንደሚያደርገው ይታመናል፡፡ ተመራማሪዎቹ ለስራው ተገቢ የሆነውን የእንጨት አይነት መርጠው ከባዱን የጠፈር ላይ ሁኔታ እንዲቋቋም ማድረግ ይችሉ እንደሆን የሚያረጋግጡ ሙከራዎችን ለመከወን አቅደዋል፡፡ እ.አ.አ በ2023 ምርቱን አዘጋጅተው ይፋ እንደሚያደርጉም ትንበያቸው ያሳያል፡፡
ምንጭ፡ Tech Xplore
በአነስተኛ ዋጋ ከፍተኛ ብቃት ያለው መተንፈሻ መሳሪያ
************************
የእንግሊዝ ተመራማሪዎቹ አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት የሚገኙ በኮቪድ ምክንያት ከፍተኛ የአተነፋፈስ ችግር ላጋጠማቸው ህሙማን የሚውሉና በአነስተኛ ዋጋ ተመርተው ከፍተኛ ግልጋሎት የሚሰጡ የመተንፈሻ መሳሪያወችን እንዲያመርቱ የበጀት ድጋፍ ተደረገላቸው፡፡ መካኒካል ቬንትሌሽን ከመተንፈሻ ጋር ለተያያዙ ችግሮች እጅግ ከፍተኛ የሆነ የህይወት አድን ስራ መስራት የሚያስችል መሳሪያ ነው፡፡
በገበያ ላይ ያሉት መተንፈሻ መሳሪያዎች ዋጋቸው ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር ጥቅም ላይ ለማዋል የአጠቃቀም ስልጠና ወይም ክህሎት የሚጠይቁ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የመተንፈሻ መሳሪያወቹ በብዙ ሀገራት የማይገኙ የጤና መሰረተ ልማቶችን የሚጠይቁ በመሆናቸው ተደራሽነታቸው ከሀገራቱ የኢኮኖሚ አቅም ጋር እጅግ የተቆራኘ ነው፡፡
በእንግሊዝ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ግብዓቶች ካውንስል የተደራጀው የምርምር ቡድን በቀላል ዋጋ የሚቀርቡ፣ ብቁና ለአጠቃቀም ምቹ የሆኑ እንዲሁም የተለየ መሰረተ ልማት የማይፈልጉ የመተንፈሻ መሳሪያዎችን በሙከራ ደረጃ ለማምረት ተግባራትን ጀምሯል፡፡ በተጨማሪም የምርምር ቡድኑ የምርት ስራውን የጥገናና የማጓጓዣ ወጭን ከግምት ውስጥ በማስገባት በሁሉም የአለማችን ክፍሎች ለማከናወን አቅድ እንዳለው አሳውቋል፡፡
ምንጭ SciTechDialy
የትኛው ይበጀናል፤ የኤሌክትሪክ መስመርን መዘርጋት ወይስ የፀሐይ ኃይል ቁሳቁሶችን ማቅረብ
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ጨምሮ ከግማሽ ቢሊዮን በላይ የሚሆነው አፍሪካዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ አይደለም፡፡ ይህ በምድራችን ካለው ኤሌክትሪክን ከማይጠቀም ሰው መካከል 72 በመቶው በአፍሪካ ውስጥ ይኖራል ማለት ነው፡፡ የተባበሩት መንግስታት ያስቀመጣቸው የዘላቂ ልማት ግቦችን የተመለከትን እንደሆነ በአውሮፓውያኑ 2030 ሁሉንም የምድራችን ዜጎች በተመጣኝ ዋጋ ዘላቂ፣ አስተማማኝ እና የዘመነ የኃይል አቅርቦት ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚገባቸው ያስቀምጣል፡፡ ታድያ ይህን ለእናት አህጉራችን እንዴት ማሳካት ይቻላል? የትኛውን መንገድ ብንጠቀምስ በአነስተኛ ወጪ ከስኬት እንደርሳለን? ጥናቶች መልሱን ይዘው መጥተዋል፡፡
ባለፈው አስር ዓመት ውስጥ ከተለምዶአዊው የኤሌክትሪክ መስመሮች የተነጠሉ እንደ ፀሐይ ኃይል ተጠቃሚ ቁሶች ያሉ አዳዲስ የኃይል ምንጮችን መስፋፋት አስመልክቶናል፡፡ እነዚህ አማራጮች ማሽኖችን ለማንቀሳቀስ ባይችሉም መብራትን ያበራሉ፣ ስልኮችን ቻርጅ ያደርጋሉ፣ ለራዲዮን እና ቴሌቪዥንም ኃይል ይሰጣሉ፡፡ በዋጋ ረገድም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚከናወነው የኃይል መስመር ዝርጋታ በአንፃራዊነት ዋጋቸው የተሻለ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ሀገር አቀፍ የኤሌክትሪካ ኃይል መስመሮች ለኢንዱስትሪ ማንቀሳቀስ እና ሌሎች መሰል አገልግሎቶች የሚበቃ ኃይልን በመስጠታቸው ምክንያት ለረጅም ጊዜ እድገት ተቀዳሚ ምርጫ ሊሆኑ እንደሚገባ ይነገራል፡፡ ሆኖም በእሲያና ደቡባዊ አሜሪካን በተሰራው መልኩአፍሪካ ላይ መስራቱ በዙም እንደማያዋጣ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በተለያዩ አፍሪካ ገጠራማ ክፍሎች መታዘብ እንደተቻለው እነዚህ ስፍራዎች ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል በዋናነት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ለመብራት እና መሰል አነስተኛ እንቅስቃሴዎች ነው፡፡
ሁለት በቅርብ ቡርኪና ፋሶ፣ ሩዋንዳ እና ሴኔጋልን ማዕከል አድርገው የተሰሩ ….ጥናቶች እንደሚያሳዩት ብዙ አፍሪካውያን አባወራዎች ከወርሀዊ ገቢያቸው ውስጥ ከፍ ያለ ድርሸ ኤሌክትሪክ ለማግኘት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ነው፡፡ ጥናቶቹ ማሳየት እንደቻሉት እነዚህ ቤተሰቦች ከ16 እስከ 23 በመቶ የሚሆነውን ወርሀዊ ገቢያቸውን በመስመር ለሚመጣላቸውየኤሌክትሪካ ኃይል አገልግሎት ለማዋል ፈቃደኛ ሲሆኑ ከመስመር ጋር ላልተያያዙት ደግሞ ከ6 እስከ 15 በመቶ ለመክፈል ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ርዋንዳ ላይ ብቻ የተደረገው ሁለተኛው ጥናት እንደሚያሳየው ደግሞ አባወራዎች 20 በመቶ የሚሆነውን ገቢያቸውን ለአነስተኛ በፀሐይ ኃይል ለምትሰራ አምፖል ግዢ ለማዋልበ ፍቃደኛ ሲሆኑ የፀሐይ ኃይል ቁሱ ስክን ቻርጅ ማድረግ ካስቻለ ወጪው እስከ 70 በመቶ ለማሳደግ ያላቸውን ፈቃደኝነት አሳይቷል፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን 20 ኪሎ ዋት ማቅረብ እና ከመብራትም ባለፈ ስልክ ቻርጅ ማድረግ ብሎም እንደ ተቪና ራዲዮን ያሉ የመዝናኛ መሳርያዎቸን ኃይል መስጠት በሚችል የፀሐይ ኃይል መሳርያ ላይ ግን ሶስት ወር ገቢያቸውን አውጥተው ለመግዛት ፈቃደኛ ናቸው፡፡
ይህ ከፍተኛ ወጪን ለማውጣት ያለ ፍቃደኝነት ግን እነዚህ የገጠር ቤተሰቦች ገቢያቸው አነስተኛ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የፀሐይ ኃይል መሳርያዎቹን ለመግዛትና ለማስገጠም ከሚያስፈልገው ገንዘብ አንፃር እጅግ ዝቅተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ለምሳሌ በረሩዋንዳ አባወራ ቤተሰቦቹ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆኑት እነዚህ ፀሐይ ኃይል ቁሳቁሶች ገበያ ላይ ከሚያወጡት ዋጋ 30 እና 40 በመቶውን ብቻ ነው፡፡
በሌላ መልኩ ለኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እንደየሁኔታው የሚያይ ቢሆንም በሺዎች የሚቆተር ዶላሮችን ያስወጣል፡፡ እያንዳንዱን ሰው ለበኤሌክትሪክ መስመሮች አማካኝነት ተጠቃሚ ለማድረግ በነፍስ ወከፍ 1,100 ዶላር ያስፈልጋል ቢባል እንኳን እነዚህ ቤተሰቦች መክፈል በሚችሉት ተመጣጣኝ በሆነ ወርሀዊ ክፍያ ዋጋ ብናሰላውበዚህ መስመር ዝርጋታ ላይ የሚወጣውን ወጪ ለመመለስ ከ5 እስከ 18 ዓመታት ይፈጃል፡፡
ጥናቱ በገጠራማይቱ የአፍሪካ ክፍል ከፍተኛ ሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት መኖሩን ማረጋገጥ የቻለ ሲሆን ፍጆጆታን የተመለከትን እንደሆነም በመስመር የሚቀርብን ኃይልንም ሆነ ከዚህ ውጪ የሚመጣውን ኃይል ላይ ያለው ፍጆታ መጠን ተመሳሳይ መሆኑን ማወቅ ተችሏል፡፡
በአጠቃላይ ከዚህ እና ቀድሞ ከተጠቀሱት ውጤቶች በመነሳት ቢያን ለአሁን ከመስመር ውጪ ያሉ አማራጮችን መጠቀሙ ከአጠቃላይ ዋጋ አንፃር አዋጪ ሆኖ ይገኛል፡፡ ሆነም ሁለቱንም አማራጮች ተጠቅሞ የኤሌክትሪካ ኃይልን ለነዋሪዎች ማድረሱ በእቅድ ላይ በተቀመተውጊዜ ውስጥ መሳካት የሚችል አይመስልም፡፡ ጥናቱ መንግስታት የኤሌክትሪካ ኃይልን ለመላው ህዝባቸው ለማድረስ የትኛው የፖሊሲ አማራጭ እንደሚያዋጣቸው ዕይታን የሚሰጥ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህን ለማሳካት መንግስታት ሁለቱንም አማራጮች ቢጠቀሙም እንኳን ዜጎች ድጋፍ ካልተደረገላቸው የኤሌክትሪክ ኃይልን ለመተቀም እጅ እንደሚያጥራቸው ነው፡፡
ምንጭ፡ the conversation
አየር ንብረት ለውጥ እና ጦርነት
==================
በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራው ታዋቂው የፎሬን ፖሊሲ መፅሔት አዲስ በገባው የአውሮፓውያን ዓመት 2020 ላይ ከፊት ተሰላፊ ይሆናሉ ብሎ ካስቀመጣቸው 10 ግጭቶች መካከል በአየር ንብረት ለውጥ ሳብያ ይከሰታሉ ያላቸው ተካታች ሆነዋል፡፡ በመፅሔቱ ትንታኔ መሰረት በጦርነት እና የአየር ንብረት ለውጥ መካከል ያለው ግንኙነት ቀላል ወይም በቀጥተኛነት የሚገለፅ አይደለም፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ አየር ንብረቱ ሲቀየር በዚያው ልክ ግጭቱም የሚቀጣጠል ሲሆን በሌላው ላይ ግን ድምፅ ሳይሰማ ሊያልፍ ይችላል፡፡ አንዳንድ ሀገራትም በአየር ንብረት ምክንያት የሚመጣን ፉክክር በአግባቡ መቆጣጠር ሲቻላቸው ሌሎች ግን ጉዳዩ ከቁጥጥራቸው ውጪ ሲሆንባቸው ይስተዋላል፡፡ ዋናው ጉዳይ ሀገራት አካታች በሆነ መልኩ ይመራሉ? በተፈጥሮ ሀብቶች አማካኝነት የሚነሱ ግጭቶችን ለመቆጣጠር ዝግጁ ናቸው? ወይም ወይም የዜጎቻቸው ሕይወት እና ኑሮ ሲቃወስ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት አቅም አላቸው ወይ? የሚለው እንደሆነ ትንታኔው ያሳያል፡፡ በመጪው የፈረንጆች ዓመት ከአየር ንብረት ጋራ ተያይዞ ምን ያህል ግጭት ይመጣል የሚለውን ለመገመት አስቸጋሪ ቢሆንም አንድ ነገር ግን ግልፅ ነው፤ አፋጣኝ አርምጃ ካልተወሰደ ከዚህ ጋር የተያያዙ ግጭቶች የመምጣታቸው አደጋ እንደሚያሻቅብ፡፡
በሰሜናዊ ናይጄሪያ በአካባቢው የተከሰተው ድርቅ በአርብቶ እና አርሶ አደሮች መካከል ያለውን ግጭት ያባባሰው ሲሆን ይህም በሀገሪቱ ከቦኮ ሀራም ጋር ካለው ግጭት በሁለት እጥፍ ለበለጠ የሰው ሕይወት ማለፍ ምክንያት ሆኗል፡፡ ምንም እንኳን አዲስ ባይሆንም በአባይ ጉዳይ የተነሳም በተመሳሳይ በተፋሰሱ ሀገራት መካከል የጦርነት ዛቻ እንዲነሳ አድርጓል፡፡ አከራካሪ ሆኖ አሁን ላይ በአየር ንብረት ሳብያ የሚመጡት ግጭቶች በዋናነት አፍሪካ ውስጥ ይሆናል የሚል ግምት ቢወሰድም ተመሳሳይ አደጋዎች በእሲያ፣ ደቡብ አሜሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ አንዣበዋል፡፡
የተፍረከረኩ ሀገራት ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆር ህዝብ ታይቶ የማይታወቅ ሙቀት፣ በጣም የበዛ ወይም እጅጉን ያነሰ የዝናብ መጠን እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ የባህር ውሃ ከፍታ እያጋጠመው ይገኛል፡፡ ይህ ሁሉ ታድያ አለመረጋጋትን ሊያባብስ ይችላል፤ ለምሳሌ እየተባባሰ የሚመጣ የምግብ ደህንነት ማጣት፣ የውሀ እጥረት በተፈጥሮ ሐብት ላይ የሚደረግ ፉክክር እነዚህ ሁሉ ዜጎች ቤታቸውን ጥለው እንዲሄዱ ሊመሯቸው ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የአየር ሙቀት በግማሽ ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሚጨምር ከሆነ የደም አፋሳሽ ግጭቶች መጠንም በአማካኝ ከ10 እስከ 20 በመቶ ያድጋል፡፡ ይህ ትንበያ ትክክል ሆኖ ከተገኘና የተባበሩተ መንግስታት ተመራማሪዎችም የምድራችን ሙቀት ከአስር ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በግማሽ ዲ.ሴ ይጨምራል ማለታቸውን ከግምት ስናስገባ ቀድሞውንም መረጋጋት የራቃቸው የምድራችን አካባቢዎች ግጭቶች በፍጥነት እየተባባሱ እንደሚመጡ ግምት መውሰድ ይቻላል፡፡
እነዚህን ግጭቶች ለማስቀረት መንግስታት በሀገራቸው ውስጥ አልያም ከሌሎች ሀገራት ጋራ የሚጋሯቸውን የተፈጥሮ ሀብቶችን በሰላም ለማስተዳደር ሊሰሩ ይገባል ሲል ፎሬን ፖሊሲ አሳስቧል፡፡
መልካም ዜናዎችም ግን አልታጡም፡፡ አሁን ላይ ሀገራት ለኤር ንብረት ለውጥይበልጥ ትኩረት እየሰጡ መጡ ሲሆን ለዚህ ችግር ዋና ተጠያቂ ሆነው የሚቀርቡት ምዕራባዊያን ሀገራት እና ድርጅቻቸውም ካለፈው ዓመት አንስቶ በየዓመቱ የ100 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸው ተገልጿል፡፡
አፕል አዲስ የኮምፒውተር ኪቦርድ ሊያቀርብ ነው
********************************
በያዝነው ሳምንት የባለቤትነት ማረጋገጫ ፓተንት በአሜሪካው የፓተንትና የንግድ ምልክት ፈቃድ ሰጭ ተቋም ማረጋገጫ ያገኘው አዲሱ የአፕል የኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ የሚገኙ ቁልፎች ራሳቸውን አስፈላጊውን ተግባር መፈጸም በሚያስችል መልኩ የሚያላምዱ ናቸው ተብሏል፡፡
እያንዳንዱ ቁልፍ አንድን ተግባር ሰርተን እስክንጨርስ ድረስ ለዚያ ተግባር በሚያስፈልግ መልክ የሚላመዱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የድምጽ መቅዳት ተግባርን ለመፈጸም ስናስብ ቁልፎቹ ለድምጽ ቀረጻ ወደሚያስፈልጉ የተለያዩ ተግባራት ወዳላቸው መተግበሪያነት መለወጥ እንዲችሉ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም ደግሞ የፎቶ ኢዲቲንግ ስራን ለመስራት ስንዘጋጅ በኪቦርዱ ላይ የሚገኙ ቁልፎች ጥምር ተግባራትን እንድንፈጽም ያስችሉናል፡፡
አፕል ባቀረበው ኪቦርድ የሚገኙ ልዩ ልዩ ቁልፎች ምስሎችን በመከሰት መሰረታዊውን የጽሁፍ ስራ ሳያቋርጡ የተለያዩ ግብረ መልሶችን መስጠት የሚችሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ቁልፎች ካላቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል የኮምፒውተር ጌሞችን ለመጫወት የሚያስችሉ መሆናቸው አንዱ ነው፡፡ በዚህም ለአንድ የኮምፒውተር ጌም የሚያስፈልጉ ተግባራትን በማላመድ ቁልፎቹ ለማንኛውም አይነት ጌም መጫወቻነት ያገለግላሉ፡፡
በተጨማሪም ተጠቃሚዎች አንድን ጽሁፍ ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ መቀየር በሚፈልጉበት ወቅት የኮምፒውተር ቁልፎቹ ይህን ተግባር ለመፈጸም የሚያስችል ብቃትን ተላብሰዋል፡፡ ቁልፎቹ ከጠርሙስ፣ ሴራሚክ፣ ፖሊመርና ሳፋየር ከተባሉ ግብዓቶች የተሰሩ ናቸው፡፡
ባለቀው የፈረንጆች አመት ካምፓኒው አንድ ሌላ ለተንቀሳቃሽ መገልገያዎች የሚያገለግልና በማግኔት አማካኝነት የሚሰራ ኪቦርድ ፓተንት ማግኘቱ የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ Tech Xplore
ቴክ-ሳይንስ የቲቪ ፕሮግራም፤ በዚህ ሳምንት፡-
--------------------
ዓብይ ፕሮግራም፤ የበቆሎ ገዳይ ቫይረስን የሚከላከል ምርምር
ብላቴናት፤ የደህንነት ካሜራ የሰራው ታዳጊ
ተቋማት፤ የኢትዮጵያ ጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት
የቴክኖሎጂ ታሪክ፤ ካሜራ
የተመራማሪዎች ሕይወት ታሪክ፤ ፕ/ር ዘመደ አስፋው
ከዋናዎቹ ዝግጅቶቻችን በተጨማሪም የስኮላርሺፕ መረጃዎችንም ይዘን የምንመጣ ሲሆን እርስዎም ነገ ቅዳሜ 10 ሰዓት ላይ የቻናል ምርጫዎን MOE ቴሌቪዥን ላይ በማድረግ ይጠብቁን፡፡
በ MOE ቴሌቪዥን ከሚቀርበው በተጨማሪ ወደ ዩትዩብ ቻናላችን (https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg) ጎራ በማለት አዳዲሶቹን እና ከዚህ ቀደም የተሰሩትን ፕሮግራሞች በሙሉ መመልከት ይችላሉ፡፡
የተሳትፎ ጥሪ፤ ለኢኖቬተሮች
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የኢኖቬሽን ባህልን ለማሳደግና ቀጣይነት ባለው መልኩ ኢኖቬተሮችን ለማፍራት ያግዝ ዘንድ የቅድመ-ኢንኩቤተር ፕሮግራም ተቋሙ አዘጋጅቷል፡፡ በዚህም ፕሮግራም የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች፣ ተመራማሪዎችና ሌሎች ማንኛውም መስፈርቱን የሚያሟሉ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች መሳተፍ የሚችሉበት ሲሆን የስራ ፈጠራ ሃሳባቸውን የሚያሳድጉበት እና ቢዝነስን የሚመሩበት ክህሎትን ይቀስሙበታል፡፡ ከአመልካቾች መካከል ሀያ አምስቱ ተመርጠው ከጥር 19 እስከ 21 2013 ዓ.ም ድረስ በሚካሄደው በዚህ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ መስፈርቱን የምታሟሉ ሁሉ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ከዛሬ ታህሳስ 23 አንስቶ እስከ ጥር 7 ድረስ መመዝገብና መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
መመዝገቢያ ሊንክ= https://tinyurl.com/Pre-Incubation-Program-2021
ለበለጠ መረጃ በኢ-ሜይል አድራሻችን startup@techin.gov.et ወይም አራት ኪሎ (ከፓርላማ ወደ ፒያሳ በሚወስደው ጎዳና) በሚገኘው ዋና ቢሮዋችን በአካል በመገኘት ሊጠይቁን ይችላሉ፡፡
ባለ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ካሜራ
******************
ካሜራዎች የሚመለከቱትን ምስል ከማየት ባለፈ የሚረዱ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ምርምር በብሪስቶልና ማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ጥምረት መሰራቱ ተነገረ፡፡ በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች የተሰራው ምርምር ካሜራዎች የሚያዩትን ምስል ምንነት በጥልቀት በመመርመር እንዲረዱት የሚያስችል ነው፡፡ የሮቦቲክስና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ተመራማሪዎች በአሁኑ ወቅት ያሉ ካሜራዎች ምስሎችን ሴንስ የሚያደርጉበት መንገድ ችግር አለበት ብለው ያምናሉ፡፡
እነዚህ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ካሜራዎቹ ምስልን ለመቅዳት ዲዛይን በተደረጉ የካሜራ ሴንሰሮችና የቪዲዮ ጌሞችን ለማጫወት የሚያገለግሉ የኮምፒውቲንግ ቁሶችን በማጣመር የሚሰሩ በመሆናቸው ሰው ሰራሽ ክህሎት ምስሎችን የሚያገኘው የተለያዩ ቅጅዎች ከሴንሰር ወደ ፕሮሰሰር በሚያደርጉት ጉዞ ነው፡፡
ይህ ሂደት በካሜራችን እይታ ውስጥ አላስፈላጊ ምስሎች እንዲገቡ ያደርጋቸዋል፡፡ ለምሳሌ ራስ-ነድ በሆኑ መኪናዎች ከመንገድ ውጭ ያሉ ለጉዞው የማያስፈልጉ ምስሎች ይገባሉ፡፡ ይህ ምርምርም ያስፈለገው ይህን ችግር ለመቅረፍ ነው፡፡ በሂደቱም አንድን ምስል ሴንስ ማድረግና መረዳትን (learn) በአንድ ጊዜ በማጣመር ለሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚያገለግል ልዩ ካሜራን መፍጠር ተችሏል፡፡
ይህንን ፈጠራ በማበልጸግ ሂደት ውስጥ ተፈጥሯዊ የሆነውን የአይንና የአእምሮን ቅንጅት መሰረት አድርገው እንደሰሩ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ በኢንጂነሪንግ እና ፊዚካል ሳይንስ ምርምር ካውንስል በሚደገፈው ምርምር የተሰራው ካሜራ ከማሽን ለርኒንግ አቅሙ በተጨማሪ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው በመሆኑ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት እድገት ከፍተኛ አተዋጽኦ እንደሚኖረው ተነግሯል፡፡
ምንጭ፡ SciTechDaily