TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ፋብላብ አዲስ እና ላይታውስ ስልጠና እና አማካሪ ከኢንስቲትዩቱ ጋር ስምምነት ፈፀሙ
=======================
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማሳቹሴት ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ፋብላብ ማዕከልና ላይታውስ ስልጠና እና አማካሪ ድርጅት ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ጋር ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ዛሬ ፈርመዋል፡፡ ተቋማቶቹ በተለያዩ የፈጠራ ስራ ውጤቶች፣ አቅም ግንባታ፣ ሚዲያን ለማህበረሰባዊ ለውጥ መጠቀም እና ሌሎችም አበይት ጉዳዮች ላይ ነው ከኢንስቲትዩቱ ጋራ ለመስራት የተስማሙት፡፡
ላይታውስ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ቤተሰቦችን በአመራር እና አቅም ግንባታ ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን ለመስጠትና ከኢንስቲትዩቱ ጋርም የገበያ ድጋፍ፣ የሰው ኃይል አቅርቦት እና የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ በአንድላይ ለመስራት የተስማማ ሲሆን ኢንስቲትዩቱም የመረጃ፣ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
ፋብላብ አዲስም እንዲሁ ከኢንስቲትዩቱ ጋር የፈጠራ ስራዎችንና መሰረተ ልማትን በጋራ ለመጠቀም፣ አገራዊ ጥቅምና የስራ ዕድል ፈጠራ ሊያመጡ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን በማልማት ወደ ኢንተርፕራይዝ ለማሳደግ፣ ኤግዚቢሽኖች ላይ በጋራ ለማስተዋወቅ፣ ጥልቅ ምርምርን ለሚፈልጉ ፕሮጀክቶች የማማከር ስራ ለመስራት እና ሀገራዊ ጥሪን ተቀብሎ ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት አካሂዷል፡፡
በፊርማ ስነ ስርዓቶቹ ላይ ለሁለቱም ድርጅቶች ተቋማዊ መዋቅር፣ ተግባራት እና ሌሎች ኢንስቲትዩቱን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙርያ በአቶ ዳውድ መሐመድ አማካኝነት ገለፃ ቀርቧል፡፡
ስምምነቶቹ ተቋማቱ ከኢንስቲትዩቱ ጋራ ባላቸው የዓላማ መመሳሰል ሳብያ የመጡ ናቸው ያሉት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ ኢንስቲትዩቱ የሚጎሉትን ነገሮች ለመሙላት እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡
ተቋማቸውን ወክለው ስምምነቱን የተፈራረሙት የላይታውስ እና ፋብላብ ዋና ኃላፊዎች አቶ እስክንድር በላይ እና አቶ ሀብታሙ አገኘው ከኢንስቲትዩቱ ጋራ ትብብር መፍጠሩ ትልቅ እርምጃ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን በጋራ መስራቱም እንደ ሀገር ስኬታማ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
ስለ ጊዜ ያለንን አመለካከት ይለውጣል የተባለለት የ3 ደቂቃ ቪዲዮ
********************************
እንደ ሳይንስ እሳቤ ምድር እጅግ እድሜ ጠገብ እደሆነች ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ከመላምት ያለፈ በትክክል እድሜዋ ይህን ያክል ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ በተለምዶ የምሰማውን የ4.5 ቢሊዮን አመት አእምሯችን ባለው የዘመን ቆጠራ ልምድ መረዳት የምንችለው አይደለም፡፡ ነገሩን በቀላሉ መረዳት እንድንችል በሚል ቢዝነስ ኢንሳይደር የተባለ ተቋም የጊዜ ርቀቱ ከሎሳንጀለስ እስከ ኒዮርክ ቢሆን የአለማችን ዋናዋና ክስተቶች ሊገለጹ የሚችሉበትን አስገራሚ አኒሜሽን ሰርቶ አቅርቧል፡፡
በቪዲዮውም የምድር እድሜ መነሻ በሎሳንጀለስ የተወከለ ሲሆን ኒዮርክ ደግሞ 21ኛውን መቶ ክፍለ ዘመን ወክላለች፡፡ ከሎሳንጀለስ ወደ አሪዞና ከፍታ የሚደረግ ግማሽ መንገድ የአለማችን ግዙፉ አለት የተፈጠረበትን የዛሬ 3.95 ቢሊዮን አመት ወክሏል፡፡ ከዚያም ጥቂት ማይሎችን መጓዝ ህይወት በምድር ላይ መኖር ጀምሯል የሚባልበትን ከ3.8 ቢሊዮን አመታት የነበረ ጊዜን እንዲያስታውስ ተደርጓል፡፡
በቪዲዮው ውስጥ በምድራችን የተከሰቱ ግዙፋን ክስቶች እንደጥላ ሲያልፉ እንመለከታለን፡፡ በአሁን ዘመን እጅግ የሚያስጨንቁን ነገሮች ማስታወስ በማያስችል ፍጥነት የቅጽበተ አይንን ያክል ጊዜ እንኳን ሳይኖራቸው በቪዲዮው ውስጥ አልፈዋል፡፡
ምንም እንኳን ምስሉ ስለ ጊዜያችን ማጠር እጅግ ብዙ የሚያስብል ቢሆንም ውድ ተከታታዮቻችን እናንተው ተመልክታችሁ ሀሳብ እንድትሰጡበት ትተነዋል፡፡
ምንጭ፡ Science Alert
ማብሰል እና የሰው ልጅ የአዕምሮ ዕድገት
የሰው ልጅን ከሌሎች እንስሳት በተለየ ብልሀ ወይም ስማርት ያደረገው ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የሚሞክሩት አንድ የነርቭ ሳይንስ ባለሙያ የሰው ልጆች ከሌሎች እንስሳት በተለየ ብልሀ ወይም ስማርት ያደረጋቸው ሁነኛ ምክንያት የአዕምሮ መጠናቸው ከፍ ማለቱ ሳይሆን በአዕምሯቸው ወስጥ የያዙት አጠቃላይ የነርቭ ህዋስ ብዛት ወይም (total number of neurons) እጅግ የበዛ በመሆኑ ነው ይላሉ፡፡
በአሜሪካ በሚገኘው የቫንደርቤልት ዩኒቨርስቲ የነርቭ ሳይንስ ተመራማሪ የሆኑት ሱዛና ሁዩዞል ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር ባደረጉት የነርቭ ጥናት ስለአዕምሯችን አስገራሚ እውነታዎች እና ተያየዥ ጉዳዮች የሚከተለውን ይላሉ፡፡ ረዳት ፕሮፌሰር ሱዛና ሁዩዞል እንደሚያስረዱት የሰው ልጅ አዕምሮ አንድ የሚለይበት መሰረታዊ ጉዳይ በአዕምሮው ውስጥ ያሉት የነርቭ ህዋሶች ወይም (cortical neurons) እጅግ የበዛ በመሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ የሰዎች የነርቭ ህዋስ ብዛት ከጉሬላ የነርቭ ህዋስ አንጻር ሲሰላ የሰዎች 16 ቢሊዮን ብዛት ሲኖረው የጉሬላ ደግሞ 9 ቢሊዮን ብቻ ነው፡፡
ይህ አውነታ ሰዎች ከሌሎች እንስሳት በተለየ የአዕምሮ እድገቱን የጨመረለት አንዳች የህይወት ልምምድ እንዳለ የሚያመለክት ነው የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር ሱዛና ይህ የህይወት ልምምድ ደግሞ የሚመገበውን ምግብ በጥሬው ከመብላት ይልቅ በትንንሹ ቆራርጦ ማብሰል በመቻሉ ነው ይላሉ፡፡ ፕሮፌሰሯ ይህን ለማበራራት እንደሚሉት “ለምሳሌ ካሮትን በጥሬው የተመገበ አንድ ሰው ለማኘክ እና ለስርዓተ ልመት 10 እና 15 ደቆቃ ከመፍጀቱም ባለፈ ከካሮቱ የሚያገኘው የካሎሪን መጥን አንድ ሶስተኛ ላይደርስ ይችላል፡፡ ነግር ግን ካሮቱን በትንንሹ ቆራረርጦ ለጥቂት ደቂቃ ማብሰል ከቻለ በፈጣን የስርዓተ ልመት የካሮቱን 100% ካሎሪን በቀላሉ ሊያገኝ ይችላል"፡፡
ረዳት ፕሮፌሰር ሱዛና አንደሚሉት የሰዎች አዕምሮ ከፍተኛ ሃይል የሚወስድ የሰውነት አካል ሲሆን በቀን ውስጥ ቢያንስ 25 በመቶው የሰውነት ሃይል በአዕምሮ ጥቅም ላይ የሚውል ነው፡፡ ታዲያ ይህ የሰዎች የማብሰል ክህሎት ከሚመገቡት ምግብ ላይ አስፈላጊውን የካሎሪን ይዘት በሚገባ እንዲየገኙ በማስቻል የሰዎችን የአእምሮ እድገት በፍጥነት እንዲጨምር እና የማሰብ አቅም ይበልጥ አንዲጎለብት ማገዙን ረዳት ፕሮፌሰር ሱዛና ይናገራሉ፡፡
ምንጭ፡ Bigthink
በወረርሽኝ ጊዜ ጤናንና ኢኮኖሚን እንዴት ማመጣጠን ይቻላል
**********************************
አንድ ወረርሽኝ ሲከሰት እንደሚወሰደው የጥንቃቄ እርምጃ ቢወሰንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎችን ህይወት መቅጠፉ የማይቀር ነው፡፡ በአንድ አካባቢ የሚኖርን የወረርሽኝ መስፋፋት ለመከላከል በተለይ የሚጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች በትክክል መተግበራቸውን መከታተል በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ ባሳለፍነው የሀምሌ ወር በአሜሪካ በጣም ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኝ መስፋፋት ተመልክተናል፡፡ ለዚህም እንደምክንያት የሚጠቀሰው ከተወሰኑ ወራት የእንቅስቃሴ ገደብ በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች ምግብ ቤቶችና መገበያያ ሱቆች በመከፈታቸውና ሰዎችም በሰፊው መንቀሳቀስ በመጀመራቸው ነው፡፡
በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የተሰራ አንድ ሒሳባዊ ሞዴሊንግ እንዲህ አይነት በማህበረሰብ ጤናና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ወረርሽኝ በሚከሰትበት ወቅት የጉዳቱን መጠን ለማስተካከል እንደሚያግዝ ተነግሯል፡፡ ከተለያዩ የሳይንስ የሙያ ዘርፎች የተውጣጣው የምርምር ቡድን ያቀረበው ሴናሪዮ በወረርሽኝ ወቅት ሊወሰዱ የሚገባቸውን በጣም አስፈላጊ እርምጃዎች የሚመለክት ነው፡፡ ይህ ሴናሪዮ በመነሻነት የማህበረሰቡን ኢኮኖሚ በማሳደግ በተለይ እድሜያቸው ከፍ ያለ ጎልማሳ ሰዎች በቤታቸው በመቀመቀመጥ ወጣቶች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረጉ ስራቸውን እንዲሰሩ የሚያስችል ነው፡፡
ይህም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደሚባለው በአንድ በኩል በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኙ የሰዎችን ቁጥር በመቀነስ የወረርሽኙን የመስፋፋት እድል የሚቀንስና በሌላ በኩል ደግሞ ኢኮኖሚያዊው እንቅስቃሴ ፈጽሞ እንዳይቋረጥ በማድረግ ሀገርን ከከፋ ጉዳት መከላከል እንዲቻል የቀረበ ሞዴሊንግ ነው፡፡ በመሰረታዊነት የበሽታውን መስፋፋት የሚገታና ኢኮኖሚው እንደተነቃቃ እንዲቆይ የሚያደርግ የውሸባ ወይም ኳራንታይን ስርአትን የያዘ ነው፡፡
ምንጭ Sciencedaily
የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስነ-ምግባራዊ እሴቶች
****************************
ሳይንስና ቴክኖሎጂ በሰው ልጆች የእድገት ግስጋሴ ውስጥ ያለውን ከፍተኛ ድርሻ አስጠብቆ ለማስቀጠል ብሎም የሰው ልጆች ያልተቋረጠ የእውቀትና የእድገት ፍላጎት ይሳካ ዘንድ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስነምግባራዊ እሴቶች ሊጠበቁ ይገባል። በየትኛውም ሙያና ዘርፎች እንደተቀመጡ የስነምግባር እሴቶች ሁሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የራሱ እሴቶች አሉት። የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስነምግባር ድንጋጌዎችን በአንድ ጥቅል ስነድ ውስጥ ተስድረው ማግኘት የማይቻል ነው። በተመሳሳይም እንደ ሌሎች አለም አቀፍ የህግና የመብት ድንጋጌዎች ይህ ነው የሚባል የሳይስና ቴክኖሎጂ ህግጋት ስነድ ባይኖርም በተለያዩ ማዕቀፎች ውስጥ ማለትም በትምህርት፣ ባህል፣ ንግድ፣ እድገት፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ስምምነቶችና ድንጋጌዎች ላይ ሳይንስ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የሚኖረው ሚናን ከዘርፉ ከሚጠበቀው የስነምግባር እሴት ጋር ተቆራኝቶ ይገኛል።
ከተለያዩ ሰነዶች ላይ የተሰባሰቡ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚናን እንዲሁም ዘርፉ ሊከተለው የሚገባውን ስነምግባራዊ እሴት በተመከተ የተገለጹ ሃሳቦች በሙሉ አንድም የሰው ልጆችን ክቡርነት፣ የሰው ልጆች ህይወት ቀጣይነት ለድርድር የሚቀርብ አለመሆኑን፣ ተፈጥሮና የተፈጥሮ ሚዛን አደጋ ውስጥ የሚከት ማንኛውም ነገር ጎጂ መሆኑን፣ እውነት እና አግባብነትን ያልተከተለ ሂደትና ውጤት የማታማታ ኢጤነኛ የሆነ ተጽእኖንና የማይገባ ኪሳራን የሚያመጣ መሆኑን ማዕከል ያደረጉ ናቸው። በዚህም መሰረት እውነተኛነት (ተአማኒነት)፣ አግባብነት፣ ተፈጥሯዊ ሚዛናዊነት፣ ሰውን አክባሪነት፣ ጉዳት አልባነት፣ እና ትብብርና ቁርኝት የሚሉት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስነምግባራዊ እሴቶች ናቸው።
ለአብነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኒውሮቴክኖሎጂ የምርምር ዘርፍ ዙሪያ እየጨመረ የመጣው አግባብነት የሌለው አጠቃቀም እና ስነ ምግባርን ያልተከተለ የምርምር እንቅስቃሴ የነርቭ ሳይነቲስቶችን ይበልጥ እያሰጋ እንደሚገኝ እና ይህን ከባድ አደጋም በጊዜ መከላከል እንዲቻል የኒውሮ-መብቶች በአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ውስጥ እንዲካተቱ ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ አንደሚገኝ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲገለፅ ቆይቷል፡፡ ይህ ክስተት በሌሎች የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ በተመሳሳይ መልኩ ሊከሰት የሚችል በመሆኑ ይህን የስነ- ምግባር እና የእሴት ማዕቀፍ በሁሉም ዘርፎች ላይ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡
በኢትዮጵያም በተመሳሳይ ሁኔታ የትምህርት፣ የባህል፣ የንግድ፣ የምርትና የሌሎችም ሳይንስና ቴክኖሎጂን በቁሳዊም ሆነ በሌላ መልኩ በግብአትነት የሚጠቀሙ አካላት ከላይ የተዳሰሱትን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስነምግባራዊ እሴት ከግንዛቤ ያስገቡ መሆን መቻል አለባቸው። በተጨማሪም በምርምርና ጥናት ዘርፎች የተሰማሩ ተመራማሪዎች እንዲሁም በምርትና ንግድ ላይ የሚገኙ የኢኖቬሽና ፈጠራ ባለሙያዎች በሚያከናዉኗቸው የምርምር ስራዎችም ሆነ በሚያፈልቋቸው የፈጠራ ሃሳቦች እና ለንግድ በሚያቀርቧቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሳቢያ ሊፈጠር የሚችል ማናቸውንም ጎጂ ተጽእኖ ለመቀነስ ብሎም ለማስቀረት በሚችሉበት መንግድ መንቀሳቀስ ይገባቸዋል። ይህን እንቅስቃሴ የሚመራ፣ ፈር የሚያሲይዝና የሚከታተል መንግስታዊ ማዕቀፍም እንዲሁ በህግጋትና በተቋማት በኩል መጠናከሩ ለነገ የሚባል ስራ አይሆንም።
ምንጭ፡ Big Think እና Tech science
አዲሱ የኮቪድ-19 አይነት እና ስጋቶቹ
*********************
ከሳምንት በፊት የብሪታንያ ባለስልጣናት ከሌሎቹ በ70 በመቶ በበለጠ መሰራጨት የሚችል አዲስ አይነት ሳርስ-ኮቭ-2 (ኮቪድ 19ኝ በሽታን የሚያመጣው ቫይረስ) መታየቱን የሚያሳይ መረጃ መውጣቱን ተከትሎ በለንደን እና ደቡባዊ አንግሊዝ አካባቢ ነዋሪዎች ከቤት እንዳይወጡ ክልከላን አስተላልፈው ነበር፡፡ በአሁኑ ሰዓት አዲሱ የቫይረሱ አይነት ቀድሞ የነበሩትን በሚያሰጋ ፍጥነት እየተካና ቀዳሚ እሆነ መምጣቱን ተከትሎ እስራኤል፣ ካናዳ፣ ቻይና እና ህንድን ጨምሮ ከ40 በላይ የዓለም ሀገራት ከወደ እንግሊዝ የሚነሳ በረራን አግደዋል፡፡
ይህን መሰል በቫይረሱ በራሒ ላይ በሚመጣ ለውጥ (Mutation) አማካኝነት አዲስ የቫይረሱ አይነት መከሰቱ ታድያ ብዙም አስገራሚ አይደለም፤ ተደጋግሞ የሚከሰት ነውና፡፡ ነገር ግን አዲሱ የቫይረሱ አይነት በፍጥነት ተሰራጭቶ ቀዳሚውን ስፍራ መያዙ ነው ለብዙዎች እራስ ምታት የሆነው፡፡ አዲሱ የቫይረስ ዓይነት ቅድሚያ የተገኘው ወርሀ መስከረም ላይ ነበር፡፡ ከሁለት ወራት በኋላ ግን በለንደን እንደ አዲስ ከሚያዙት ኮቪድ-19 ተጠቂዎች መካከል ሩብ ያህሉን፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ደግሞ የሁለት ሶስተኛውን ድርሻ ወስዷል፡፡
አዲሱ የቫይረሱ አይነት ቀድሞ ከነበረው ሲነፃፀር 17 ያህል የበራሒ ለውጦች ታይተውበታል፡፡ ከነኚህ ለውጦች መካከል ቫይረሱ ህዋሳችንን እንዲያጠቃ የሚያስችለው የፕሮቲን እሾሁ ይገኝበታል፡፡ እንደዚህ አይነት ለውጦች ታድያ ቫይረሱ ይበልጥ በፍጥነት እንዲስፋፋ የማድረግ እድል አላቸው፡፡ ለዓብነት ቫይረሱ ቅድሚያ በሰው ልጅ ህዋስ ላይ በሚያርፍበት ስፍራ (Receptor-Binding Domain) ላይ የሚኖረው ለውጥ ቫይረሱ ሕዋሶቹ ላይ በበለጠ መጣበቅ እንዲችል የማድረግ አቅም አለው፡፡
በተመሳሳይ 501.ቪ2 (501.V2) ተብሎ የሚጠራ ሌላ የቫይረሱ አይነት በደቡብ አፍሪካ የተገኘ ሲሆን ይህ በበኩሉ አዳዲስ ከሚያዙት ሰዎች መካከል የ80 እና 90 በመቶውን ድርሻ ይዟል፡፡ 501.ቪ2 ቫይረሱ በመጀመሪያው ማዕበል ሲሰራጭ ከነበረበትም በበለጠ ፍጥነት እተሰራጨ መሆኑን የደቡብ አፍሪካ የጤና ባሙያዎች እና ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡ በየቀኑ የሚያዘው ሰው መጠን ከሳምንታት በፊት ከነበረበት በሁለት እጥፍ ማደጉን ተከትሎ የሟቾች እና በሆስፒታል ቆይተው የሚታከሙ ሰዎችም ቀድሞ ከነበረበት ከፍተኛ ብልጫ እያሳየ ነው፡፡ የሀገሪቱ ተመራማሪዎች የኮቪድ-19 ክትባቶች አዲሱን የቫይረሱ አይነት መከላከል መቻላቸውን ለማረጋገጥ ሙከራዎችን እያደረጉ ሲሆን የእንቅስቃሴ እቀባዎችም ተላልፈዋል፡፡
ሆኖም እነዚህ ለውጦች አሁን እየተሰራጩ ያሉትን ክትባቶች ውጤታማ እንዳይሆኑ የማድረጋቸው እድል ቢያንስ ለአሁኑ ጠባብ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ለዚህ የሚሰጠው ምክንያት ቫይረሱ በአንድ በኩል ክትባቱን ማምለጥ ቢችል እንኳን በሌሎች ብዙ ጎኖቹ ግን ለክትባቱ እጅ ይሰጣል የሚለው ነው፡፡
ምንጭ፡ Associated Press፣ Live Science እና cnn
"የኮሪያ አርቲፍሻል ፀሐይ" አዲስ ክብረ-ወሰን
******************************
የኮሪያ ሰው ሰራሽ ፀሐይ ለ20 ሴኮንዶች ያክል መቆየት የቻለ የ100 ሚሊዮን ዲግሪ ሙቀት በመያዝ የአለማችን አዲስ ክብረ-ወሰን አስመዝግቧል፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ በሚገኝ አንድ የዘርፉ የምርምር ተቋም (KSTAR) የተሰራው ይህ ሰው ሰራሽ ፀሐይ መቶ ሚሊዮን ዲግሪ ሴልሺየስ የደረሰ ከፍተኛ ሙቀት በመያዝ ለተመራማሪዎቹ ትልቅ ስኬትን አስገኝቷል፡፡
የምርምር ተቋሙ ከሴኡል ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲና ከአሜሪካው ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሰራው ይህ ምርምር ለተከታታይ 20 ሴኮንዶች ያክል የቆየ ሲሆን በኒውክሌር ፊውዥን ዙሪያ ለሚሰሩት ጥናት ምቹ ሁኔታ እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡ በ2019 በተደረገ ሙከራ የቆይታ ጊዜው ለ8 ሴኮንዶች ያክል ብቻ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን የአሁኑ ሁለት እጥፍ ስኬትን ያስገኘ ነው፡፡
ተመራማሪዎቹ አርቲፍሻል ፀሐይ ሲሉ የሰየሙት ከፍተኛ አስተላላፊ ቁስ የሀይድሮጅን አይሶቶፖችን የያዘ ሲሆን ይህ አዮኖችና ኤሌክትሮኖች የሚለያዩበትን የፕላዝማ ኩነት (state) እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው፡፡ አዮኖቹ ከፍተኛ መጠን ባለው ሙቀት እንዲግሉ ይደረጋል፡፡
ምንም እንኳን ከ100 ሚሊዮን በላይ ከፍ ያለ ሙቀትን መያዝ የሚችሉ ሌሎች የፊውዥን ቁሶች ቢኖሩም እስካሁን ከ10 ሴኮንዶች በላይ ሙቀቱን ተቋቁመው መቆየት የቻሉ ግን አልነበሩም፡፡ ይህኛው ሙካራ ሊሳካ የቻለውም የምርምር ተቋሙ የውስጣዊ ግድግዳውን አቅም በማሻሻሉ ሲሆን ለዚህ ያበቃውም ባለፈው አመት የተሰራው ከፍተኛ ሙቀትን መቋቋም የሚችል ቁስ (plasma operation mode) መጠቀሙ ነው፡፡
እንደ ተመራማሪዎች ገለጻ ከሆነ የዚህ ምርምር ዋና አላማ እንከ 2025 ድረስ ከመቶ ሚሊዮን ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሙቀትን ለ300 ሴኮንዶች ያክል ማቆየት መቻል ነው፡፡ ፈጠራው ከፍተኛ ሙቀት መቋቋም የሚችል ቁስ በማግኘት የወደፊቱን የኒዩክሌር ማበልጸጊያ መሳሪያ ለማግኘት ያለመ ነው፡፡ መረጃውን ከPHYS.ORG አግኝተነዋል፡፡
ቴክኖፖሊ
****
ቃሉ በዲጂታል አገልግሎቶች ላይ የጠቅላይነት ወይም ሞኖፖሊስቲክ ቁጥጥር ያላቸውን ግዙፎቹ ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ስብስብን የሚያመላክት ነው፡፡ 2020 የቴክኖሎጂ ዓለም ገበያ ላይ ያለው ድርሻ ባልተቋጨ የከፍታ ሂደት ውስጥ የቆበት ነበር፡፡ በእንደ ፌስቡክ፣ ግዙፎቹ ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የአሜሪካንን የአክሲዮን ገበያ ተቆጣጥረውት አሳልፈዋል፡፡ ይህ በተለይም ዓለማችን ያጋጠማት የኮቪድ-19 ወረርሺኝን ተከትሎ ብዙ ነገሮች ወደ ዲጂታል መለወጣቸውን እና በመንግስታት የተወሰዱ የምጣኔ ሐብቱን የማረጋጋት እርምጃዎች (Monetary And Fiscal Stimulus) ዘርፉን በፍጥነት እንዲያድግ እና ተቋማቱ ለአክሲዮን ገበያ ሲቀርቡም የሚገዙበት የገንዘብ መጠን እ.አ.አ 1990ዎቹ መባቻ ላይ ከነበረውና ዶትኮም ቦም ወይም ዶትኮም በብል ተብሎ ከሚጠራው የበይነ-መረብ ተቋማት ዋጋ የናረበት ጊዜ በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ከፍ ያለበት ነበር፡፡
የነዚህ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት ዋጋ ማሻቀብን አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ ዕድገቱ እየተመዘገበ ያለው በዓለም ዙርያ ባሉ መንግስታዊ ተቆጣጣሪዎች ዓይነ ቁራኛ ክትትል ውስጥ በወደቁበት ሰዓት መሆኑ ነው፡፡ በአሜሪካን እንኳን ብናይ የሀገሪቱ ፍትህ ቢሮ እንዲሁም የፌደራሉ ንግድ ኮሚሽን በጉግል እና ፌስቡክ ላይ የክስ ጅራፍ አንስተውባቸዋል፡፡ የአውሮፓ ህብረትም ሆነ እንግሊዝ በቅርቡ እነዚህን ተቋማት የሚቆጣጠር ጠንካራ ሕግ ወደፊት ሲያመጡ ቻይናም እንደ አሊባባ ያሉ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቿ ላይ ጥርስ መንከስ ጀምራለች፡፡
ሆኖም ይህ ሁሉ ጫና ባለበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እንኳን ዘርፉ እድገቱን እንደቀጠለ ነው፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሺኝ እና ተከትሎት የሚፈጠረው ሁኔታ ስራዎች ከቢሮ ርቀው እንዲሰሩ እና ተቋማትም እንደ ሶፍትዌር፣ ፓተንት፣ የጥሬ ሀቅ ወይም ዳታ ትንተና እና ሌሎችም የአዕምሮ ንብረት አይነቶች ላይ ሀብታቸውን ማፍሰሳቸው እየጨመሩ መሆኑን ተከትሎ ሰው ልጆችን ሕይወት ቀድሞ ከነበረበትም በላይ ወደፊት ይበልጥ ዲጂታል እንደሚያደርገው ይጠበቃል፡፡ ይህ ለእነዚህ ግዙፍ ተቋማት መልካም ዜናን ይዞ ቢመጣም እነዚህ የማይዳሰሱ ሀብቶች ላይ የሚደረገው የመዋለ ነዋይ ፈሰስ ግን ከስራ አጥነት ያልተላቀቀ ምጣኔ ሀብት መነቃቃት ጋራ በመያያዙ ለተቀጣሪ ሰራተኛው ቢያንስ ለአሁኑ ነገሮችን ጥሩ የሚያደርገው አይመስልም፡፡ ይህ ዘርፉ አሁንም በሀገራት ምጣኔ ሀብት ላይ ያለውን ቴክኖፖሊ በቀጣዮቹ ወራትና አመታት ውስጥ አስቀጥሎ ይዘልቃል ማለት ነው፡፡
ምንጭ፡ Financial Times
ለካንሰር ህሙማን ተስፋ ሰጭ መድሀኒት
**************************
የካንሰር ሴሎችን እንዲዳብሩ እና እንዲስፋፉ የሚያደርገውን ክፍል በማጥቃት የህመሙን መስፋፋት መቀነስ የሚያስችል መድሀኒት መሰራቱ ተሰማ፡፡ መድሀኒቱ የካንሰር ሴሎችን እንዲዳከሙ የሚያደርገው የሀይል ምንጭ የሚሆናቸውን ማይቶኮነዶሪያ የተባለውን ክፍል በማጥቃት ነው፡፡ በስቶኮልም የሚገኝ አንድ የምርምር ተቋምና የጉተምበርግ ዩኒቨርሲቲ በሰሩት ምርምር መድሀኒቱን ለወደፊቱ የካንሰር ህሙማንን ለማከም ተስፋ ሰጭ ምልቶች መኖራቸውን ይፋ አድገዋል፡፡
ማይቶኮንዶሪያ ለህዋሳት ግንባታ የሚሆን ሀይልና የህዋሳት ክፍሎችን ለማዳበር የሚያገለግል ክፍል ነው፡፡ ለብዙ ጊዜያት ያክል የካንሰር ህዋስ እድገት ከማይቶኮንዶሪያ ተግባር ጋር የማይገናኝ ተደርጎ የሚታሰብ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሚወጡ መረጃዎች ግን እሳቤው ስህተት መሆኑን እያረጋገጡ ናቸው፡፡ በተለይም ለካንሰር ህመም ዋና የሚባሉ ህዋሳት ከማይቶኮንዶሪያ ተግባር ጋር ጥገኞች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ማይቶኮንዶሪያ ለመደበኛ የሰውነት ህዋሳት ባለው ጥቅም ምክንያት እሱን ለማጥቃት የሚሰጡ መድሀኒቶች ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ካንሰርን ለማከም ማይቶኮንዶሪያን ማጥቃት አስቸጋሪ መሆኑ ታውቋል፡፡
ይህ የአሁኑ ምርምር ከላይ የተገለጸውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ውጤት ይዞ እንደመጣ የመረጃ ምንጫችን አስነብቧል፡፡ የምርምሩን ውጤት ካሳወቁት መካከል አንዷ የሆኑት ኒና ቦኔካምፕ በምርምሩ የከፋ ጉዳት የማያደርስና ጤነኛ ህዋሳትን የማያጠቃ መድሀኒት መሰራቱን በጽሁፋቸው አመልክተዋል፡፡
ምንጭ SciTechDaily