TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ናኖ ቴክኖሎጂ ለዘመናዊ ግብርና
የግብርና ቴክኖሎጂ መሠረታዊ መለኪያው የምርት መጠንን መጨመር፣ የጥራት ደረጃ ማሻሻል፣ የሥራ ቅልጥፍና መፍጠርና ማቀነባበርን ያካትታል፡፡ እ.ኤ.አ በ1990ዎቹ መጨረሻ አካባቢ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ሀገራት የናኖ ቴክኖሎጂን የሚደግፉ ተቋማትን በመመስረት ምርምር በሰፊው ከማካሄድ ባለፈ ወደ ምርት ተግባር መግባታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከቅርብ ዓመታት በኋላ ታዳጊ ሀገራትም ናኖ ቴክኖሎጂን በኢንዱስትሪዎቻቸው ውስጥ እየተጠቀሙባቸው ይገኛል፡፡
ናኖ ቴክኖሎጂ የምርት ጥራትና ብዛት ማሳደግ የሚያስችል በመሆኑ በግብርና ምርት ላይ መጠቀም የሚፈለገዉን ለዉጥ ለማምጣት ያግዛል፡፡ ከዚህም በተጓዳኝ ናኖ ቴክኖሎጂ በግብርና ኬሚካል ቅመም በመጠቀም የአፈር፣ የውሃና የአየር ብክለትን በመቀነስ ግብርናው የበለጠ አስተማማኝ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በድረ-ገጹ ባወጣው የግብርና ፖሊሲ መግለጫ በ2050 የዓለም ህዝብ ብዛት 9 ቢሊዮን እንደሚደርስና እየጨመረ ያለውን የህዝብ ቁጥር ለመመገብ ግብርናውን ማዘመን የግድ እንደሚል አስቀምጧል፡፡ ለዚህ ደግሞ ናኖ ቴክኖሎጂ መፍትሄ ያመጣል ተብሎ ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎበታ፡፡ ናኖ ቴክኖሎጂ የምርትን ጥራትና ብዛት ከመጨመር ባሻገር ለዘላቂ የውሃ አጠቃቀም፣ ለንፁህ ዘር አቅርቦት፣ ተባይ እና በሽታን ለመለየት፣ አልሚ የምግብ አቅርቦትን ለመጨመር ፋይዳው የጎላ ነው፡፡ የእፅዋት ጥበቃና ተፈጥሮ ሃብት ከብክለት ነፃ ለማድረግ ወይም ለመቀነስ የሚረዳ መድሃኒት ማቅረብ ትኩረት ሊደረግበት የሚገባ ነው፡፡
ናኖ ቴክኖሎጂ በተፈጥሮ ላይ የጎንዮሽ ጉዳት ሳይደርስ ሚዛኑን ጠብቆ አረንጓዴና የተመቻቸ ስነ-ምህዳራዊ አካባቢን በመፍጠር የግብርና ምርትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡ ይሁን እንጅ በበለፀጉትና በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የናኖ ቅንጣቶች በረዥም ጊዜ አደጋ ያስከትላሉ ብሎ በመጠራጠር ለመቀበል መቸገር እንደሚስተዋል መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ማንኛውም የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች እንደሚሰጡት ትሩፋት ሁሉ መጠነኛ ጉዳት ሊኖራቸው ስለሚችል የአጠቃቀም ሁኔታን ይበልጥ በማሻሻል እና ተሞክሮዎችን በመቀመር የቴክኖሎጂውን ፍሬ በበልሃት መጠቀም ግድ ይላል፡፡ የናኖ ቴክኖሎጂ ወጭ ቆጣ፤ ምርታማነትን ይበልጥ የሚያሳድግ እና ወቅቱን የዋጀ ቴክኖሎጂ መሆኑን ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር በአጠቃቀም ሂደቱ ላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡
ምንጭ፡ Frontiersin
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከልሳን ቴክኖሎጂ ጋራ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከልሳን ቴክኖሎጂ ጋራ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡ የቴክኖሎጂ ሽግግርን በዋና አላማነት አንግቦ የተካሄደው የመግባብያ ስምምነቱ በሁለቱም ተቋማት ያሉ ተመራማሪዎችን በማስተባበር የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ውጤት እንደሚያስገኝም ታምኖበታል፡፡ ስምምነቱን በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በኩል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሙሉቀን ቀሬ ሲፈርሙ ልሳን ቴክኖሎጂን በመወከል ደግሞ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ አዳም ቦዶዊን ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡
ስምምነቱ ሁለቱ አካላት በማሽን ትራንስሌሽን እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ እንዲሁም በሁለቱም ተቋማት የሚገኙ ተመራማሪዎች፣ ሶፍትዌር መሀንዲሶች እና ሌሎች ባለሙያዎች በጋራ እንዲሰሩ የሚያደርግ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ልሳን የስልጠና እንዲሁም የማሽን ትራንስሌሽን እና ኦፕቲካል ካራክተር ሪኮግኒሽን (OCR) ሲስተሞች ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን ኢንስቲትዩቱም ለጋራ ምርምር የሚያስፈልግ መሰረተልማት፣ ቁሳቁስ እና አስተዳደራዊ አቅርቦቶችን የሚያከናውን ይሆናል፡፡
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በስልጠና፣ ጥናት እና ቢዝነስ መካከል ድልድይ መሆኑንና በሀገሪቱ ስትራቴጂዎች ውስጥም ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አውስተው ስምምነቱ በፍጥነት ወደ ተግባር እንዲለወጥ ያላቸውን ፍላጎት አንፀባርቀዋል፡፡ አቶ አዳም በበኩላቸው ተቋማቸው በዋናነት መቀመጫውን ጀርመን ሀገር አድርጎ እንደሚሰራ ገልፀው ሀገራዊ ቋንቋዎችን ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እና በኢትዮጵያ እየሰሩ ያሏቸውን ቴክኖሎጂያዊ ስራዎች አስተዋውቀዋል፡፡
ካርቦንዳይ ኦክሳይድን በመጠቀም የአውሮፕላን ነዳጅን ማምረት ተቻለ
******************************
በእንግሊዝ የሚገኝ አንድ የምርምር ቡድን ሳውዲ አረቢያ ከሚገኝ አንድ ተቋምና ከሌሎች የምርምር ተቋማት ጋር በመሆን በዋናነት ካርቦንዳይ ኦክሳይድን በግብአትነት ተጠቅመው የአውሮፕላን ነዳጅ ማምረት የሚስችላቸው ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተነገረ፡፡ ተመራማሪዎች በከባቢ አየር ላይ ያለውን የካርቦንዳይ ኦክሳይድ መጠን ለመቀነስ በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ይህንን የተቃጠለ አየር ጥቅም ላይ ማዋል የሚቻልበትን መንገድ መፈለግ እንደ አንድ አማራጭ እየተጠቀሙት ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም መንገዶች አንዱ በተበከለ አየር ልቀት 12 በመቶ ድርሻ ያለው የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ መሆኑ ታውቋል፡፡
በአቪየሽን ኢንዱስትሪው የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ የሚደረገው ሙከራ ክብደት ያላቸውን ባትሪዎች በአውሮፕላኖች ላይ መግጠም ለአደጋ ሊያጋልጥ የሚችል በመሆኑ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ በዚህኛው ምርምር ግን ተመራማሪዎች ካርቦን አልባ የሆነ ነዳጅን ማምረት የሚያስችል ኬሚካዊ ሂደት ማበልጸጋቸው ተሰምቷል፡፡
በሂደቱም ተመራማሪዎቹ በአየር ላይ ያለን ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ወደ አውሮፕላን ነዳጅና ሌሎች ምርቶች ለመቀየር የሚያስችል ኦርጋኒክ ኮምባስሽን የሚባል መንገድን ተጠቅመዋል፡፡ እንደ መረጃ ምንጫችን ከሆነ ፖታሺየምና ማንጋኔዝ ያሉበት የብረት ውህድ፣ ሀይድሮጅን፣ ሲትሪክ አሲድ እና ካርቦንዳይ ኦክሳይድን በ350 ዲግሪ ሙቀት በማንደድ በ CO2 ውስጥ የሚገኝ ካርቦን ተለይቶ ከሀይድሮጅን ጋር እንዲጣመር ማድረግ ተችሏል፡፡ በዚህም ፈሳሽ የአውሮፕላን ነዳጅ የያዘ ሀይድሮ ካርቦን ሞሎኪዩል ማግኘት ችለዋል፡፡ በተጨማሪም ውሃና ሌሎች ምርቶች ተገኝተዋል፡፡
በሙከራው ወቅት ጥቅም ላይ ከዋለው ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ውስጥ 38 በመቶው ወደ አውሮፕላን ነዳጅነትና ወደ ሌሎች ምርቶች የተለወጠ ሲሆን ከአጠቃላይ ምርቱም የአውሮፕላን ነዳጁ 48 በመቶውን የሚይዝ ነው፡፡ ቀሪው 52 በመቶ ደግሞ ውሃ፣ ፐሮፕሌን እና ኢታሊንን የያዘ ነው፡፡
ተመራማሪዎቹ የተጠቀሙት መንገድ የአውሮፕላን ነዳጅን ለማምረት ከሚያስችሉ ሌሎች መንገዶች በተሸለ አነስተኛ ወጭ የሚያስወጣ እንደሆነና በአሁኑ ወቅት ከፍኛውን የካርቦንዳይ ኦክሳይድ መጠን የሚለቁ ግዙፍ ፋብሪካዎችም መንገዱን ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡
ምንጭ PHYS.ORG
የመጀመሪያው አርተፊሻል ልብ በአውሮፓ ለገበያ እንዲውል ፈቃድ አገኘ
****************************
በአውሮፓ የዘርፉ ተቆጣጣሪዎች የመጀመሪያ የሆነውን ሰው ሰራሽ ልብ ለገበያ እንዲውል ፈቃድ መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡ ለሀያ ሰባት አመታት ያክል ሲለፋበት የነበረውና ስኬት አግኝቶ ከሰባት አመታት በፊት ፈቃድ የተሰጠው ሰው ሰራሽ ልብ ለአምራቹ ኬርሜት ትልቅ ተስፋን ሰጥቷል፡፡ ኬርሜት በዘርፉ ስቶክ ገበያ ውስጥ 66 በመቶ ድርሻ ያለው ሲሆን ይህም የገበያ ዋጋውን 407 ሚሊዮን ይሮ አድርሶለታል፡፡
ድጅቱ በያዝነው ሳምንት ምርቱን በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ውስጥ መሸጥ የሚያስችለውን ፈቃድ ማግኘቱን የዘገበው ብሉምበርግ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ይህም በልብ በሽታ እየተሰቃዩ ላሉ ህሙማን የልብ ንቅለ ተከላ ማድረግ የሚያስችላቸውን እድል ይፈጥርላቸዋል ተብሏል፡፡
ሰርጅንና የልብ ቱቦ (heart-valve) ፈጠራ ባለቤት ያደረጉት ስምምነት በፈረንሳይ ሰው ሰራሽ ልብ የሚመረትበትን መንገድ በ1993 ከፍቷል፡፡ የድርጅቱንም ድርሻ ኬርሜትና ኬርፔንቴር የተባሉ ባለቤቶች ይዘውታል፡፡ በመሆኑም የሽያጭ ፈቃዱን በማግኘቱ ኬርሜት የፊታችን ጥር የምርት ሂደቱን እንደሚጀምር አሳውቋል፡፡
ይህ አርቲፍሻል ልብ ተመርቶ ለገበያ ከቀረበ በኋላ ለኬርሜት ከ700 ሚሊዮን ዩሮ በላይ አመታዊ ገቢ እስከ 2030 እንደሚያስገኝለት ተገምቷል፡፡ ምርቱንም በፈረንጆቹ 2021 ሁለተኛ ሩብ አመት ለገበያ እንደሚያቀርብ ድጅቱ አሳውቋል፡፡
ምንጭ Bloomberg Technology
ፋብላብ አዲስ እና ላይታውስ ስልጠና እና አማካሪ ከኢንስቲትዩቱ ጋር ስምምነት ፈፀሙ
=======================
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማሳቹሴት ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ፋብላብ ማዕከልና ላይታውስ ስልጠና እና አማካሪ ድርጅት ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ጋር ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ዛሬ ፈርመዋል፡፡ ተቋማቶቹ በተለያዩ የፈጠራ ስራ ውጤቶች፣ አቅም ግንባታ፣ ሚዲያን ለማህበረሰባዊ ለውጥ መጠቀም እና ሌሎችም አበይት ጉዳዮች ላይ ነው ከኢንስቲትዩቱ ጋራ ለመስራት የተስማሙት፡፡
ላይታውስ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ቤተሰቦችን በአመራር እና አቅም ግንባታ ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን ለመስጠትና ከኢንስቲትዩቱ ጋርም የገበያ ድጋፍ፣ የሰው ኃይል አቅርቦት እና የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ በአንድላይ ለመስራት የተስማማ ሲሆን ኢንስቲትዩቱም የመረጃ፣ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
ፋብላብ አዲስም እንዲሁ ከኢንስቲትዩቱ ጋር የፈጠራ ስራዎችንና መሰረተ ልማትን በጋራ ለመጠቀም፣ አገራዊ ጥቅምና የስራ ዕድል ፈጠራ ሊያመጡ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን በማልማት ወደ ኢንተርፕራይዝ ለማሳደግ፣ ኤግዚቢሽኖች ላይ በጋራ ለማስተዋወቅ፣ ጥልቅ ምርምርን ለሚፈልጉ ፕሮጀክቶች የማማከር ስራ ለመስራት እና ሀገራዊ ጥሪን ተቀብሎ ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት አካሂዷል፡፡
በፊርማ ስነ ስርዓቶቹ ላይ ለሁለቱም ድርጅቶች ተቋማዊ መዋቅር፣ ተግባራት እና ሌሎች ኢንስቲትዩቱን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙርያ በአቶ ዳውድ መሐመድ አማካኝነት ገለፃ ቀርቧል፡፡
ስምምነቶቹ ተቋማቱ ከኢንስቲትዩቱ ጋራ ባላቸው የዓላማ መመሳሰል ሳብያ የመጡ ናቸው ያሉት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ ኢንስቲትዩቱ የሚጎሉትን ነገሮች ለመሙላት እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡
ተቋማቸውን ወክለው ስምምነቱን የተፈራረሙት የላይታውስ እና ፋብላብ ዋና ኃላፊዎች አቶ እስክንድር በላይ እና አቶ ሀብታሙ አገኘው ከኢንስቲትዩቱ ጋራ ትብብር መፍጠሩ ትልቅ እርምጃ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን በጋራ መስራቱም እንደ ሀገር ስኬታማ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
ስለ ጊዜ ያለንን አመለካከት ይለውጣል የተባለለት የ3 ደቂቃ ቪዲዮ
********************************
እንደ ሳይንስ እሳቤ ምድር እጅግ እድሜ ጠገብ እደሆነች ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ከመላምት ያለፈ በትክክል እድሜዋ ይህን ያክል ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ በተለምዶ የምሰማውን የ4.5 ቢሊዮን አመት አእምሯችን ባለው የዘመን ቆጠራ ልምድ መረዳት የምንችለው አይደለም፡፡ ነገሩን በቀላሉ መረዳት እንድንችል በሚል ቢዝነስ ኢንሳይደር የተባለ ተቋም የጊዜ ርቀቱ ከሎሳንጀለስ እስከ ኒዮርክ ቢሆን የአለማችን ዋናዋና ክስተቶች ሊገለጹ የሚችሉበትን አስገራሚ አኒሜሽን ሰርቶ አቅርቧል፡፡
በቪዲዮውም የምድር እድሜ መነሻ በሎሳንጀለስ የተወከለ ሲሆን ኒዮርክ ደግሞ 21ኛውን መቶ ክፍለ ዘመን ወክላለች፡፡ ከሎሳንጀለስ ወደ አሪዞና ከፍታ የሚደረግ ግማሽ መንገድ የአለማችን ግዙፉ አለት የተፈጠረበትን የዛሬ 3.95 ቢሊዮን አመት ወክሏል፡፡ ከዚያም ጥቂት ማይሎችን መጓዝ ህይወት በምድር ላይ መኖር ጀምሯል የሚባልበትን ከ3.8 ቢሊዮን አመታት የነበረ ጊዜን እንዲያስታውስ ተደርጓል፡፡
በቪዲዮው ውስጥ በምድራችን የተከሰቱ ግዙፋን ክስቶች እንደጥላ ሲያልፉ እንመለከታለን፡፡ በአሁን ዘመን እጅግ የሚያስጨንቁን ነገሮች ማስታወስ በማያስችል ፍጥነት የቅጽበተ አይንን ያክል ጊዜ እንኳን ሳይኖራቸው በቪዲዮው ውስጥ አልፈዋል፡፡
ምንም እንኳን ምስሉ ስለ ጊዜያችን ማጠር እጅግ ብዙ የሚያስብል ቢሆንም ውድ ተከታታዮቻችን እናንተው ተመልክታችሁ ሀሳብ እንድትሰጡበት ትተነዋል፡፡
ምንጭ፡ Science Alert
ማብሰል እና የሰው ልጅ የአዕምሮ ዕድገት
የሰው ልጅን ከሌሎች እንስሳት በተለየ ብልሀ ወይም ስማርት ያደረገው ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የሚሞክሩት አንድ የነርቭ ሳይንስ ባለሙያ የሰው ልጆች ከሌሎች እንስሳት በተለየ ብልሀ ወይም ስማርት ያደረጋቸው ሁነኛ ምክንያት የአዕምሮ መጠናቸው ከፍ ማለቱ ሳይሆን በአዕምሯቸው ወስጥ የያዙት አጠቃላይ የነርቭ ህዋስ ብዛት ወይም (total number of neurons) እጅግ የበዛ በመሆኑ ነው ይላሉ፡፡
በአሜሪካ በሚገኘው የቫንደርቤልት ዩኒቨርስቲ የነርቭ ሳይንስ ተመራማሪ የሆኑት ሱዛና ሁዩዞል ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር ባደረጉት የነርቭ ጥናት ስለአዕምሯችን አስገራሚ እውነታዎች እና ተያየዥ ጉዳዮች የሚከተለውን ይላሉ፡፡ ረዳት ፕሮፌሰር ሱዛና ሁዩዞል እንደሚያስረዱት የሰው ልጅ አዕምሮ አንድ የሚለይበት መሰረታዊ ጉዳይ በአዕምሮው ውስጥ ያሉት የነርቭ ህዋሶች ወይም (cortical neurons) እጅግ የበዛ በመሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ የሰዎች የነርቭ ህዋስ ብዛት ከጉሬላ የነርቭ ህዋስ አንጻር ሲሰላ የሰዎች 16 ቢሊዮን ብዛት ሲኖረው የጉሬላ ደግሞ 9 ቢሊዮን ብቻ ነው፡፡
ይህ አውነታ ሰዎች ከሌሎች እንስሳት በተለየ የአዕምሮ እድገቱን የጨመረለት አንዳች የህይወት ልምምድ እንዳለ የሚያመለክት ነው የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር ሱዛና ይህ የህይወት ልምምድ ደግሞ የሚመገበውን ምግብ በጥሬው ከመብላት ይልቅ በትንንሹ ቆራርጦ ማብሰል በመቻሉ ነው ይላሉ፡፡ ፕሮፌሰሯ ይህን ለማበራራት እንደሚሉት “ለምሳሌ ካሮትን በጥሬው የተመገበ አንድ ሰው ለማኘክ እና ለስርዓተ ልመት 10 እና 15 ደቆቃ ከመፍጀቱም ባለፈ ከካሮቱ የሚያገኘው የካሎሪን መጥን አንድ ሶስተኛ ላይደርስ ይችላል፡፡ ነግር ግን ካሮቱን በትንንሹ ቆራረርጦ ለጥቂት ደቂቃ ማብሰል ከቻለ በፈጣን የስርዓተ ልመት የካሮቱን 100% ካሎሪን በቀላሉ ሊያገኝ ይችላል"፡፡
ረዳት ፕሮፌሰር ሱዛና አንደሚሉት የሰዎች አዕምሮ ከፍተኛ ሃይል የሚወስድ የሰውነት አካል ሲሆን በቀን ውስጥ ቢያንስ 25 በመቶው የሰውነት ሃይል በአዕምሮ ጥቅም ላይ የሚውል ነው፡፡ ታዲያ ይህ የሰዎች የማብሰል ክህሎት ከሚመገቡት ምግብ ላይ አስፈላጊውን የካሎሪን ይዘት በሚገባ እንዲየገኙ በማስቻል የሰዎችን የአእምሮ እድገት በፍጥነት እንዲጨምር እና የማሰብ አቅም ይበልጥ አንዲጎለብት ማገዙን ረዳት ፕሮፌሰር ሱዛና ይናገራሉ፡፡
ምንጭ፡ Bigthink
በወረርሽኝ ጊዜ ጤናንና ኢኮኖሚን እንዴት ማመጣጠን ይቻላል
**********************************
አንድ ወረርሽኝ ሲከሰት እንደሚወሰደው የጥንቃቄ እርምጃ ቢወሰንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎችን ህይወት መቅጠፉ የማይቀር ነው፡፡ በአንድ አካባቢ የሚኖርን የወረርሽኝ መስፋፋት ለመከላከል በተለይ የሚጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች በትክክል መተግበራቸውን መከታተል በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ ባሳለፍነው የሀምሌ ወር በአሜሪካ በጣም ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኝ መስፋፋት ተመልክተናል፡፡ ለዚህም እንደምክንያት የሚጠቀሰው ከተወሰኑ ወራት የእንቅስቃሴ ገደብ በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች ምግብ ቤቶችና መገበያያ ሱቆች በመከፈታቸውና ሰዎችም በሰፊው መንቀሳቀስ በመጀመራቸው ነው፡፡
በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የተሰራ አንድ ሒሳባዊ ሞዴሊንግ እንዲህ አይነት በማህበረሰብ ጤናና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ወረርሽኝ በሚከሰትበት ወቅት የጉዳቱን መጠን ለማስተካከል እንደሚያግዝ ተነግሯል፡፡ ከተለያዩ የሳይንስ የሙያ ዘርፎች የተውጣጣው የምርምር ቡድን ያቀረበው ሴናሪዮ በወረርሽኝ ወቅት ሊወሰዱ የሚገባቸውን በጣም አስፈላጊ እርምጃዎች የሚመለክት ነው፡፡ ይህ ሴናሪዮ በመነሻነት የማህበረሰቡን ኢኮኖሚ በማሳደግ በተለይ እድሜያቸው ከፍ ያለ ጎልማሳ ሰዎች በቤታቸው በመቀመቀመጥ ወጣቶች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረጉ ስራቸውን እንዲሰሩ የሚያስችል ነው፡፡
ይህም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደሚባለው በአንድ በኩል በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኙ የሰዎችን ቁጥር በመቀነስ የወረርሽኙን የመስፋፋት እድል የሚቀንስና በሌላ በኩል ደግሞ ኢኮኖሚያዊው እንቅስቃሴ ፈጽሞ እንዳይቋረጥ በማድረግ ሀገርን ከከፋ ጉዳት መከላከል እንዲቻል የቀረበ ሞዴሊንግ ነው፡፡ በመሰረታዊነት የበሽታውን መስፋፋት የሚገታና ኢኮኖሚው እንደተነቃቃ እንዲቆይ የሚያደርግ የውሸባ ወይም ኳራንታይን ስርአትን የያዘ ነው፡፡
ምንጭ Sciencedaily