TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መራሽ ማህበረሰብ

የዓለማችን ለውጥ የሰው ልጆችን ለአደጋ እየጋረጠ ይመስላል፡፡ እስከ 2050 ድረስ የዓለም ህዝብ ቁጥር እስከ 9 .6 ቢሊዮን ይደርሳል ተብሎ ተገምቷል፡፡ ስልጣኔ እያመጣው ያለውን ለውጥ እና ቀውስ በስልጣኔ እና በስልጣኔ ብቻ ነው መቋመቋም የሚቻለው፡፡

በዚህ ሰዓት ከባባድ ኢንደስትሪዎች ያስፈልጋሉ ፤ ይህንን ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝብ መመገብም ሆነ ማከም ቀላል የሚባል ስራ አይሆንም፤ በእነዚህ ግዙፍ ኢንደስትሪዎች የሚፈጠሩ ብክለቶችንም ለመከላከል ያላሰለሰ ጥረት ያስፈልጋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከ 1ቢሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ በቂ ምግብ በቂ ትምህርት እና በቂ ህክምና እያገኘ አይደለም፡፡

ንግድም ቢሆን መልኩን ቀይሯል፤ ግብይት አንድ ለአንድ ከመሆን አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁሉን አካታች እና ውስብስብ ወደ ሆነ መንገድ መጥቷል፡፡ ስለዚህ ስለሁሉም የሚገባው ሁሉም ነው፡፡

አገራት ዓለም መንደር እየሆነች መምጣቷን ተገንዝበው በዛ መንገድ መንቀሳቀስ ከጀመሩ ሰነባብተዋል ፡፡ ባተረፉት ነገር ያጎደሉት ካለ እሱን ለመሙላት ዓለም እያስገደደቻቸው ነው፡፡ በመሆንም በግዙፍ እንደስትሪዎቻቸው ያተረፉትን እንደመቀማመሳቸውም ሁሉ በኢንደስትሪዎቻቸው ላደረሱት ብክለትም ከተጠያቂነት ለመዳን የተሻለን መንገድ ማፈላለግ የግድ ይላቸዋል፡፡

ከትርፉም ሳይቋደሱ የገፈቱ ግን ግንባር ቀደም ተጠቂ የሆኑም አሉ፡፡ ታዳጊ አገራት እንዲህ ካለው ቀውስ ለመላቀቅ እና እየሮጡ ካሉት ተቀዳሚ አገራት ረድፍ ውስጥ ለመሰደር ያላቸው የማያዳግም አማራጭ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የበለፀገች አገር ወደ መገንባት ፊትን ማዞር ብቻ ነው፡፡

ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መራሽ እድገት የስኬት አቋራጭ መንግድ ነው፡፡ ይህንንም ማሳካት የሚቻለው ለሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ንቁ የሆነ ማህበረሰብን መፍጠር እና ማነፅ ሲቻል ብቻ ነው፡፡

….የቴክኖሎጂ እና የኢኖቬሽን ኢኒስቲቲዩት
ቀጭኔዎች ልክ እንደ ሰዉ ልጆች ከጓደኞቻቸዉ ጋር መመገብን ይመርጣሉ ተባለ፡፡

ግዙፍ አካል፣ ከፍተኛ ፍጥነት፣ ቅልጥፍናና የማየት ችሎታ ብሎም ከእንስሳት ሁሉ በቁመት የሚወዳደር የሌላት ቀጭኔ በማህበራዊ ህይወቷ ዙሪያ ከሰሞኑ አዲስ ጥናት ብቅ ብሏል ።ቀጭኔዎች ከ2 እስከ 50 የሚደርሱ አባላት ባሉት መንጋዎች ተደራጅተው አንድ ላይ የሚኖሩ ማኅበራዊ ፍጥረታት ናቸው።

በብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ በተደረገ ጥናት በእንስሳት አለም ዉስጥ ካሉት ሌሎች እንስሳት ዉስጥ በተለየ ሁኔታ ቀጭኔዎች ምግብ በሚመገቡበት ሰአት ልክ እንደ ሰዉ ልጅ በጋራ መመገብን እና በጋራ መሆንን እንደሚመርጡ ጥናቱ አስታዉቋል፡፡

በዩኒቨርሲቲዉ ምርምሩን የመሩት ዶ/ር ዙ ሙለር እንደገለጹት "ጥናቱን ያካሄድነዉ ለሁለት አመታት በኬንያ በታችኛዉ ስምጥ ሸለቆ በሚገኙ ቀጭኔዎች ላይ ሲሆን በረጃዉን በምናሰባስብበት ሰአትም ሁሉም ጥንድ የሆኑ ቀጭኔዎች ከምግብ ፍለጋ አንስቶ እስከሚበሉበት ሰአት ድርስ አብረዉ እንደሚያሳልፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡የሚያስገርመዉ ነገር ደግሞ ቀጭኔዎቹ ምግብ መብላትም የሚፈልጉት ከሚተዋወቁት ቀጭኔዎች ጋር ነዉ፡፡"ብለዋል

ምንጭ፡technology.org
*የቡና ሰአት ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ቤተሰቦች ጋር*
"የስራ ባልደረቦች ብቻ ሳንሆን ቤተሰቦችም ጭምር ነን!"

በየአስራ አምስት ቀኑ የሚዘጋጀው የቡና ስነስረአት የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ቤተሰቦችን ዛሬም እነሆ አሰባስቦ ደስታና ፈገግታን ከጨዋታና ቁምነገር ጋር እያስኮመኮመ ቤተሰባዊ የሆነች ግዜን ሰጥቶ አልፏል።

ይህ የቡና ስነስረኣት በሰራተኞች መሃል ያለ መስተጋብርን ከማጎልበትና ማህበራዊ እሴቶቻችንን ከማጠናከር አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ከመሆኑም በላይ ከተጨናነቀና ከተወጠረ የስራ ስነልቦና ለኣፍታም ቢሆን በመውጣት አዳዲስ ሃሳቦችን እና መፍትሄዎችን የምናፈልቅበት እድል ያመቻቻል።

ይህን በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት በወር ሁለት ግዜ የሚካሄድ የቡና ስነስርኣት የኢኒስቲትዩቱ የስራ ክፍሎች በየተራ ሙሉ ሽርጉዱን በመሸፈን የሚያስተናግዱት መሆኑ ሌላው ይህን መሰናዶ ቤተሰባዊ በሆነ መንፈስ ሁሉም የሚሳተፍበት አድርጎታል።

ይህን መሰሉ ተሞክሮ በሌሎችም ተቋማት ቢለመድ የሰራተኞችን ማህበራዊ መስተጋብር ከማጠናከሩ ባሻገር ጥሩ የሆነ የስራ ከባቢንና የአብሮነት መንፈስን በስራተኞች ዘንድ ለመዝራት ምቹ መደላድል መፍጠር ይቻላል።
እጅግ ፈጣን የጎግል ጎ መተግበሪያ ቀረበ
ጎግል ያለ በይነ መረብ መረጃን ለመላላክ የሚያስችለው ጎ መተግበሪያው ላይ ማሻሻያ ማድረጉ ተነግሯል። ጎግል ጎ የተባለውን መተግበሪያውን ባሳለፍነው ዓመት ያስተዋወቀ ሲሆን፥ መተግበሪያውም የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በሚጠቀሙ ስልኮች ላይ ነው የሚሰራው።
መተግበሪያው በስልካችን ላይ ያሉንን መረጃዎች አስተካክለን ለመያዝ የሚረዳ ሲሆን፥ ያለ በይነ-መረብ ግንኙነትም በተወሰነ ክልል ውስጥ ላሉ ስልኮች የተለያዩ መረጃዎችን በፍጥነት ለመላላክ ያገለግላል።በተጨማሪም በስልካች ላይ ያሉ ፋይሎችን ከፋፍለን ለማስቀመጥ፣ ስልካችን በሚሞላት ጊዜ አላስፈላጊ ፋይሎችን ለማጥፋት፣ በስልካችን ውስጥ ካለው የመረጃ መያዣ ምን ያህሉን እንደተቀምንና እንደቀረን ለማወቅ፣ ተመሳሳይ ፋይሎችን ለማጥፋት፣ ፋይሎቻችን እንዳይጠፉብት ጎግል ድራይቭ ላይ ለማስቀመጥ እና የማንጠቀምባቸውን መተግበሪያዎች አን-ኢንስቶል ለማድረግ የሚረዳ ነው።
ይህ ማሻሻያ የተደረገለት አዲሱ የጎግል ጎ መተግበሪያ ላይ “ሼር (Share)” የሚል አማራጭ የምናገኝ ሲሆን፥ ይህንን በመንካትም እንደ ፎቶግራፍ፣ ተንቀሳቃሽ ምስል እና ሌሎችም በስልካችን ላይ ያሉ ፋይሎችን በፍጥነት መላላክ አንችላለን። መረጃን የሚያስተላልፍበት ፍጥነትም ከዚህ ቀደም ከነበረው በአራት እጥፍ ጨምሯል የተባለ ሲሆን፥ በተሻሻለው መሰረትም በሰከንድ 490 ሜጋ ባይት መረጃን ለመላላክ ያስችላል። ይህ ማለት ከፍተኛ ጥራት ያላቸው 100 ፎቶ ግራፎ ምስሎችን ከ5 ሴኮንድ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከአንድ ስልክ ወደ ሌላ ስልክ ያስተላልፋል። በሁለት ስልኮች መካከል መረጃ ለመለዋወጥም ስልኮቹን በ5 ሰከንዶች ውስጥ ማገናኘት እንደሚችል ተነግሮለታል።
መተግበሪያው በቅርቡ በጎግል ፒክስል ስልክ ላይ ተጭኖ ከተለቀቀው የአንድሮይድ መተግበሪያ ስሪት ጀምሮ እስክ አንድሮይድ 5.0 የሚጠቀሙ ማንኛውም ስልኮች ላይ በመጫን መጠቀም እንችላለን። አዲሱን የጎግል ጎ ከፈለጋችሁም ወደ ጎግል ፕላይ ስቶር ጎራ በማለት ማግኘት ይችላሉ።
ምንጭ፦ Techworm
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ለቀጨኔ ሴት ህጻናት ማሳደጊያና ማቆያ ማእከል የኮምፒውተር ልገሳ አደረገ።

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት አመራሮች የቀጨኔ ሴት ህጻናት ማሳደጊያና ማቆያ ማእከልን ጎበኙ። በማእከሉ ውስጥ የሚገኘውን ቤተመጽሃፍት በኮምፒውተር ለማደራጀት የሚረዱ ከአንድ ሚልየን በላይ መጽሃፍት የተጫኑባቸው 15 ኮምፒውተሮችን ኢኒስቲትዩቱን በመወከል የኢኒስቱትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ ለህጻናት ሴቶችና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አስረክበዋል።

ክብርት ወይዘሮ አለሚቱ ኡመድ የህጻናት ሴቶችና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ የሴቶችና ህጻናትን ጥቃት ለመቅረፍና ብቁ ዜጋን ለማፍራት የሁሉም ዜጋ ያልተቋረጠ ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል። ህጻናት ክየትኛውም እገዛ በላይ የሚያስፈልጋቸው ፍቅር ነው ያሉት ሚኒስትር ድኤታዋ ከየትኛውም ቁሳዊ ልገሳ በላይ ኣንዲህ ጎብኝቷቸው ከጎናችሁ ነን የሚላቸው ቤተሰብ፣ አይዞን የሚል ዘመድ እና እኔን የሚል ወገን ህጻናት ይፈልጋሉ ብለው የኢኒስቲትዩቱን ጉብኝትና ድጋፍ አመስግነዋል።

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ በበኩላቸው ኢኒስቲትዩቱ የሚያደርጋቸውን ማህበራዊ ተሳትፎዎቹ ሰፊ ሆነው ሳለ ይህን ብዙዎች ሊያውቁትና ሊደግፉት የሚገባ ሆኖ ሳለ በብዙሃን የተዘነጋውን የሴት ህጻናት ማሳደጊያና ማቆያ ማእከል ለመመልከት እስካሁን በመዘግየታችን ተቆጭተናል ብለዋል። አስር ብር ለኣንድ ሰው መስጠት አስር ብርን ለአስር ሰው አከፋፍሎ ከመስጠት ይሻላል ያሉት ዋናው ዳይሬክተሩ፡ የምናደጋቸውን እገዛዎች በተበታተነና ባልተደራጀ መልኩ ከማድረግ ወጥተን ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጡ እገዛዎች ላይ ማተኮር ይገባል ብለዋል። በቀጣይም ለማእከሉ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የቀጨኔ ሴት ህጻናት ማሳደጊያና ማቆያ ማእከል በ1944 በእቴጌ መነን ወላጅ ላጡ ሴት ህጻናት ማሳገደጊያነት የተቋቋመ ነው። በአሁኑ ወቅት ማእከሉ እድሜያቸው ከ6 አመት በላይ የሆኑ 187 ሴት ታዳጊዎችን እያሳደገ ያለ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 12 ልዩ እገዛ የሚሹና 8 የኣእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ሴት ታዳጊዎች ናቸው።
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት በሳይንስ ጋዜጠኝነት እና ኮምዩኒኬሽን ላይ ያዘጋጀው ስልጠና ተጠናቀቀ።

ከታህሳስ 18 እስከ 19 2011 በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚኒኬሽን ስልጠና በተለያዩ ዝግጅቶች ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ በዋናነት ስልጠናው የሚዲያ ባለሙያዎችን፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋማትን እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት መምህራንና ተማሪዎችን አሳትፏል፡፡ በአጠቃላይ ዝግጅቱ በአራት ዋና ዋና መርሃ ግብሮች ተከፋፍሎ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ብሎም ሳይንስ ጋዜጠኝነትን አብይ ጉዳይ በማድረግ በፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ፣ ዶክተር ጌታቸው ድንቁ፣ ዶክተር ጤናው ተረፈ እና ዶክተር ዮሃንስ ሽፈራው ስልጠና ሰጪነት እንዲሁም በታዳሚዎች ሀሳብ ሰንዛሪነት ተከናውኗል፡፡
ከስልጠናው ባሻገር ተሳታፊዎች ኢኒስቲትዩቱ ሰራተኞች ጋር በጋራ አዝናኝ የነበረ የቡና ጠጡ ዝግጅትን ታድመዋል።
በስተመጨረሻም የዝግጅቱን መዝጊያ ንግግር የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ሳህለ ማርያም ሲያደርጉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃን ለማህበረሰቡ የማድረስ ስራዎች በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት አቅም ብቻ ሊከወኑ ስለማይችሉ ሚዲያው የራሱን ድርሻ ወስዶ ሊሰራ እንደሚገባና ወርክሾፑም ይህን ማሳካት ያስችል ዘንድ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው አፅዕኖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ ለሰልጣኞችና አሰልጣኞች በምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ላምባዲና ሶሻል ኮሚቴ የገናን በዓል አስመልክቶ የቡና ጠጡ ዝግጅት አካሄደ
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት በዛሬው እለት የገናን በዓል እንዲሁም ተቋሙ የተመሰረተበትን አምስተኛ ዓመት በድምቀት አክብሯል፡፡ በዝግጅቱም ላይ የፋና ቴሌቪዥን ፋና ቀለማት የቤተሰብ ጥየቃ አዘጋጆች የታደሙበት ነበር፡፡ ከእነርሱም በተጨማሪ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንስትርን ጨምሮ ልዩ ልዩ የመንግስት ከፍተኛ ሃላፊዎችና የተቋሙ የቀድሞ ባልደረባዎች ተገኝተው አክብረዋል፡፡ በዝግጅቱም አዝናኝ የሆኑ ልዩ ልዩ ውድድሮች የተካሄዱ ተካሂደዋል፡፡
የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ከቱሪዝም ኢትዮጵያ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት በቱሪዝም ዘርፉ ላይ የራሱን ሚና ለመወጣት ብሎም ዘርፉን ለማመንደግ የሚደረግ ሀገራዊ ጥረትን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችለውን ስምምነት ከቱሪዝም ኢትዮጵያ ጋር ተፈራርሟል።

የስምምነት ሰነዱን በቱሪዝም ኢትዮጵያ በኩል ወይዘሪት ሌንሳ መኮንን የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ የፈረሙ ሲሆን በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት በኩል ደግሞ የኢኒስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ ፈርመዋል።

ይህ በቱሪዝም ኢትዮጵያና በቴክኖሊጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት መካከል የተደረሰው መግባቢያ ብዙ የጋራ የሆኑ አንኳር ስራዎች የተካተቱበት ሲሆን በመጀመሪያ ምእራፍ ላይም የቱሪዝም ሳተላይት አካውንትን ለማስተዋወቅና በኢትዮጵያ ደረጃም በራስ አቅም አዳብሮና ኣልምቶ ስራላይ ለማዋል የሚደረግ ጥረትን ለመደገፍ የተደረሰ ስምምነት ነው።

የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት በአለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የቱሪዝም እንቅስቃሴዎችና መዳረሻዎችን ጨምሮ ሌሎችም ቱሪዝም ነክ መረጃዎች የተካተቱበት ስርአት ሲሆን ኢትዮጵያም ይህን ስርአት መተግበሯ በቱሪዝም ዘርፉ ላይ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ፋይዳ እንደሚኖረው በፊርማ ስነስረአቱ ላይ ተገልጿል።