የሮኬት ማስወንጨፊያ ድሮኖች ሳተላይቶችን ወደ ህዋ ለመውሰድ
********************************
RAVN-X የተባለው የሮኬት ማስወንጨፊያ ድሮን ያለአብራሪና ያለማስወንጨፊያ ትንንሽ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ ይዞ እንዲበር ዲዛይን ተደረገ፡፡ የመጀመሪያው በረራም ሞዴል ታህሳስ 3, 2020 ይፋ የተደረገ ሲሆን በ2021 የመጀመሪያውን ተልእኮ እንደሚፈጽምና ከሙከራ በረራም በኋላ የአሜሪካ ህዋ ሀይል (U.S. Space Force) ሳተላይትን እንደሚያጓጉዝ ታውቋል፡፡
የድሮኑ አምራቹ ተቋም አንድ ቢሊዮን ዶላር ከወታደራዊ ተቋሙ ጋር ውል ያሰረ ሲሆን የድርጅቱ መስራችና መሪ ግን ድሮኑ ከሳተላይት ማጓጓዣነት ይልቅ ለ remote-sensing ተመራማሪዎች የበለጠ ጥቅም እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ ድሮኑ የሁለት የተማሪ አውቶቢሶችን የሚያክል መጠን ሲኖረው የወፍና የሳተላይት ውህድ ቅርጽ እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡
ድሮኑ ከማንኘውም መንደርደሪያ መነሳት የሚችል ሲሆን ወደ ላይኛው የከባቢ አየር ክፍል ከፍ ብሎ ከወጣ በኋላ የተገጠመለትን ትንሽ ሮኬት ይለቃል፡፡ ሮኬቱ ህዋ እንደደረሰ ከ100 እስከ 150 ኪሊግራም የሚመዝኑ ባለክንፍ ሳተላይቶችን ይለቃል፡፡ ይህ ሁሉ አሰራር ራስ ገዝ (autonomous) ሲሆን ለሳተላይት ማስወንጨፊያ መሰረተ ልማት የሚወጣውን ወጭ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንሰው ተነግሯል፡፡
እነዚህ ከላይ የተገለጹት መሰረታዊ ነገሮች የአሜሪካውን Space Force ትኩረት መሳብ የቻሉ ሲሆን ASLON-45 የተሰኘን የተቋሙን ሳተላይት ለማጓጓዝም ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ይህ ሳተላይትን በድሮን የማጓጓዝ ስራ ለህዋ ሳይንስ ምርምር የሚወጣውን ወጭ በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ ብዙዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ታምኖበታል፡፡
ምንጭ www.sciencemag.org

ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች የሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ግንባታን ከአርማታ ወደ ጣውላ ለመቀየር እየሱሩ ናቸው
=======================
ረጃጅም ህንፃዎችን ለከባቢ በተስማማ መልኩ ለመገንባት ያለው ፍላጎት በፍጥነት እያደገ ባለበት በዚህ ጊዜ ካናዳ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎችን ለመስራት ጣውላዎች ተመራጭ እንዲሆኑ እየሰሩ ይገኛል፡፡ ብዙ ሰዎች እንጨትን እንደ ባለ 40 ወለል ላሉ ረጃጅም ህንፃዎች መስሪያነት ለማሰብ ይቸገራሉ የሚለው ካናዳ በሚገኘው የብሪቲሽ ኮሎቢ ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ትምህርት ክፍል ውስጥ የዶክትሬት ዲግሪውን በመማር ላይ የሚገኘው ማቲያስ በዛብህ ዘመናዊ ስልቶችን መጠቀም ከተቻለ እጅግ ጠንካራ የሆኑ ረጃጅም የጣውላ ህንፃዎችን መገንባት እደሚቻል በማሳየት ላይ መሆናቸውን ይናራል፡፡
ሰለሞን ከብሪቲሽ ኮሎምቢያ እና ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ከተውጣጡት አማካሪዎቹ ፕሮፌሰር ሰለሞን ተስፋማርያም እና ፕሮፌሰር ግርማ ብፁህአምላክ ጋር በመሆን ከ10 እስከ 40 ወለል ያላቸው ረጃጅም የእንጨት ህንፃዎች ግንባታን በዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሚገኝ የንፋስ ቤተ-ሙከራ (Wind Tunnel) ውስጥ እየመረመሩ ይገኛሉ፡፡ እንደ ማቲያስ አገላለፅ ህንጻዎችን አሁን ባለው የህንጻ ግንባታ መመሪያን በመጠቀም የሚሰሩት ሽቅብ እስከ 20 ወለል ከፍታ ያላቸው የጣውላ ህንፃዎች ከፍተኛ ነፋስን መቋቋም የሚችሉ ሲሆን የህንፃው ርዝመት ወደ 30 እና 40 ወለል ሲያድግ ግን የተለያዩ መዋቅራዊ እና የነፋስን እንቅስቃሴ መቋቋሚያ (aerodynamic) ማሻሻያዎችን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ግኝታቸው ያሳያል፡፡ ማሻሻያዎቹ በነፋስ አማካኝነት ከሚመጣው የህንፃው መወዛወዝ እና በዚህም ምክንያት የሚከሰተውን በህንፃው ውስጥ ያሉ ሰዎችን ምቾት ማጣት የሚፈቱ መሆን አለባቸው፡፡
ፕ/ር ሰለሞን በበኩላቸው መሻሻል የሚገባቸው ነገሮች ያን ያህል ከባድ ጉዳዮች አለመሆናቸውንና በቀላሉ ሊከወኑ እንደሚችሉ ግኝታቸው ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡ ይህም በኪነ-ህንፃ ረገድ አዳዲስ በሮችን የሚከፍትና አሁን ላይ በስፋት እየታዩ ያሉ ለአካባቢ የተስማማ ግንባታ የማድረግ እንቅስቃሴዎችንም እንደሚያግዝ የፕ/ር ሰለሞን ተስፋ ነው፡፡
ካናዳ በማጠናቀቅ ላይ ባለነው የፈረንጆች ዓመት 2020 ከጣውላ የሚሰሩ ህንፃዎች ላይ አስቀምጣው የነበረውን የ6 ፎቅ ከፍታ ገደብ በማላላት ወደ 12 ፎቅ ከፍ ያደረገችው ሲሆን በቅርብ የሚወጣው የ2021ዱ ዓለም አቀፉ የግንባታ ደንብም (IBC) እስከ 18 ፎቅ ድረስ ርዝማኔ ያላቸው ህንፃዎች
በስፋት እንዲገነቡ የሚፈቅድ ይሆናል፡፡
እንደ ክሮስ ላሚናትድ ቲምበር ያሉት የዘመናችን ቴክኖሎጂ ልዕቀት ውጤት የሆኑ ጣውላዎች ባላቸው ከፍተኛ ጥንካሬ፣ ውጤታማነት እና ውበት ሳብያ በዓለም ላይ እየተስፋፉ መሆኑን ማቲያስ ይናገራል፡፡ የምህንድስና ትምህርት ቤቱም በፕ/ር ሰለሞን የሚመራውን በጣውላ ግንባታ ከላይ ያተኩር ትምህርት እየሰጠ ይገኛል፡፡
ምንጭ፡ Tech Xplore

ቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም፤ በነገው ዝግጅታችን
**************************
በአብይ ፕሮግራም፤ ዲጂታል ላይብረሪን፣
በብላቴናት፤ የእንቁላል መፈልፈያ የሰራውን ታዳጊ፣
የተመራማሪዎች ታሪክ፤ ዶ/ር ሀብቴ ጀቤሳ፣
በተቋማት፤ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣
እንዲሁም በቴክኖሎጂ ታሪክ፤ ባሕር ሰርጓጅ መርከብን ይዘንላችሁ እንቀርባለን፡፡
እነዚህ አስተማሪ ዝግጅቶች እንዳያመልጥዎ ነገ ቅዳሜ 10 ሰዓት ላይ የቻናል ምርጫዎን MOE ቴሌቪዥን ላይ በማድረግ ይከታተሉን፡፡
በየሳምንቱ ዕሁድ እና በድጋሚ ማክሰኞ 10 ሰዓት በ MOE ከሚቀርበው በተጨማሪ ወደ ዩትዩብ ቻናላችንም (https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg) ጎራ በማለት አዳዲሶቹን ጨምሮ እስከዛሬ የተሰሩትን ፕሮግራሞች በሙሉ መመልከት ይችላሉ፡፡

YouTube
EthioTunes
Share your videos with friends, family, and the world
TECHIN seminar
==========
ቴክኢን ሴሚናር የፊታችን ሐሙስ ታህሳስ ፩ ላይ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ በዚህ ሳምንት ዝግጅታችን አቶ ብርሀን ታፈሰ “COLOR THEORY BASICS” በሚል ርዕስ ገለፃ የሚያቀርቡ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ታዳሚዎችን ተሳታፊ የሚያደርግ ውይይት ይኖራል፡፡
ዝግጅቱ የሚጀመርበት ሰዓት ከጠዋቱ 3፡30
TECHIN seminar will be held in Thursday (December 10) at TECHIN hall. In this week’s session Mr. Birhan Tafesse will be presenting about COLOR THEORY BASICS, followed by a brief discussion, which will include participants.
Starting time: 9:30 AM

የአለማችን የመጀመሪያው በሞባይል ስልክ የሚሰራ የ DNA መለያ መተግበሪያ
******************
የኮልድ ስፕሪን ሀርቦርድ ቤተ ሙከራ (CSHL) ተመራማሪዎች በአለማችን የመጀመሪያ የሆነውን ለዘረመል ልየታ የሚያገለግልን አዲስ የአይፎን መተግበሪያ ማበልጸጋቸው ተሰማ፡፡ iGenomics የተሰኘው መተግበሪያ የአይፎን ስልካችንን ለዚሁ ተግባር ከተዘጋጀ ተንቀሳቃሽ የዘረመል መለያ መሳሪያ ጋር በማገናኘት የዘረመል ሙከራ ማድረግ የሚያስችለን መተግበሪያ ነው፡፡
በተለይ መተግበሪያው እንደ ላፕቶፕ ኮምፒውተር ያሉ ለመስክ ስራ አመችነት የሌላቸውን መሳሪያዎች በማስቀረት በእጅ ስልካችን ስራዎችን ማከናወን የሚስችለን ሲሆን በይበልጥ ደግሞ በወረርሽኝ ወቅትና በስነ ምህዳር ስራ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል፡፡ ይህንንም መተግበሪያ Aspyn Palatnick ከ14 አመቱ ጀምሮ ለስምንት ተከታታይ አመታት ሲሰራው መቆየቱን የመረጃ ምንችን SciTechDaily አስነብቧል፡፡
የአይፎን መተግበሪያው ትልልቅ ሰርቨር ላቸውን ኮምፒውተሮች ብቻ በመጠቀም ይሰራ የነበረውን የዘረመል ጥናት በቀላሉ በእጅ ስልክ መፈጸም እንደሚያስችል ተነግሮለታል፡፡ የ iGenomics አሊጎሪዝም የተለያዩ ቫይረሶችን ዘረመል በቀላሉ በመለየት በሽታዎችን ማከም የሚያስችሉ አማራጮችን እንደሚያመላክት ተገልጧል፡፡
በተጨማሪም በህዋ ሳይንስ ያለውን የዘረመል ምርምር ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት ግኝቱን ወደ ህዋ መውሰድ የሚቻልበትን መንገድ በመፈለግ ላይ መሆኑን የመተግበሪያው አበልጻጊ ይናገራል፡፡
መተግበሪያው እንደ ጉንፋን፣ ዚካና ሳርስ የመሰሉ ቫይረሶችን ጅን መለየት እንደሚያስችል ተነግሯል፡፡
ምንጭ SciTechDaily

ከእይታ መሰወር የሚያስችለው ፈጠራ
**********************
ተመራማሪዎች በተለይ ወታደሮች ከሰዎች እይታ መሰወር የሚያስችላቸውን ፈጠራ መስራታቸው ተሰማ፡፡ ይህ ፈጠራ ወታደሮች በግዳጅ ወቅት በተለይ በጠላት ቀጠና አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የሚለብሱትና ከአካባቢው እይታ ጋር የመመሳሰል ብቃት ያለው ሰው ሰራሽ ቆዳ ነው፡፡
በደቡብ ኮሪያ የሚገኝ የተመራማሪዎች ቡድን ወታደሮችን በአካባቢያቸው ካለ ከማንኛውም ነገር መሰወር የሚያስችላቸውን ልዩ ፈጠራ በማበልጸግ ላይ መሆናቸውን የዘገበው futurism.com ነው፡፡ ይህ ፈጠራም ወታደሮችን ከመደበኛ ካሜራም ብቻ ሳይሆን ከምሽት እይታም (infrared-based night vision) ጭምር መሰወር እንደሚችል ዘገባው አመልክቷል፡፡
ፈጠራው ከእይታ ውጭ ከመሆን በተጨማሪ እንደ አካባቢው ሁኔታ የመሞቅና የመቀዝቀዝ ብቃት ያለው እንደሆነ ተገልጧል፡፡ በወታደራዊ ሳይንስ ዘርፍ ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል የተባለው ይህ ፈጠራ በየትኛውም አይነት ካሜራ ሙሉ በሙሉ ያለመታየት አቅምን እንደሚፈጥርም ተገልጿል፡፡
ምንጭ futurism

የመጀመሪያውን ውጤታማ የወባ መከላከያ ክትባትን ልናገኝ ይሆን?
=====================
በቅርቡ ኮቪድ-19 ላይ ከተሰሩት ግንባር ቀደም ክትባቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን ክትባት ከአስትራዜኒካ ጋር በመሆን የሰራው የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ቡድን አሁን ደግሞ አዲስ የሰራው የወባ በሽታ ክትባቱ በመጨረሻዎቹ የሰው ላይ ሙከራ ደረጃዎች ላይ መድረሱን አስታውቋል፡፡ እንደ ጀነር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተሩ ፕሮፌሰር አድሪያን ሂል ከሆነ የመጀመሪያ ሙከራዎቹ ተስፋ ሰጪ ውጤት ማሳየታቸውን ተከትሎ መጪው የፈረንጆች ዓመት ላይ የወባ ክትባቱ አፍሪካ ውስጥ በሚገኙ 4,800 ህፃናት ላይ ሙከራ የሚደረግበት ይሆናል፡፡
ፕሮፌሰሩ ከታይምስ ጋራ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ወባ ለማህበረሰብ ጤና አደጋ መሆኑን በመጥቀስ አፍሪካ ውስጥ በዓመት ምናልባትም ኮቪድ-19 ከሚያስከትለው እስከ 10 እጥፍ የበለጠ ሞት እንደሚያስመዘግብም ይናገራሉ፡፡ አክለውም ክትባቱ በብዛት ተመርቶ በአነስተኛ ዋጋ እንደሚቀርብ እና አሁን በሰዎች ላይ ሊደረግ የታሰበው ሙከራ ውጤታማ ከሆነም እስከ አወሮፓውያኑ 2024 ድረስ ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ ሊገባ እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡
ይህ ታድያ እስከዛሬ ድረስ ሙሉ እውቅና ያለው የወባ መከላከያ ክትባት አለመኖሩን ስናስብ ይህን ትልቅ እርምጃ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ከዚህ ቀደም ጂ.ኤስ.ኬ የተባለ የእንግሊዝ የህክምና ግብዓት አምራች የሰራው ክትባት ብቻ ነው ከዚህ ጋራ በሚቀራረብ ደረጃ ላይ መድረስ የቻለው፤ ምንም እንኳን ምርቱ 30 በመቶ ብቻ ውጤታማነት ያለው ቢሆንም፡፡
በወባ ትንኞች አማካኝነት የሚከሰተው የወባ በሽታ ገዳይ ከሆኑ በሽታዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃን ያየን እንደሆን በአውሮፓውያኑ 2019 ብቻ በዓለም አቀፍ ደረጃ 229 ሚሊዮን ሰዎች በበሽታው የተጠቁ ሲሆን 409ሺህ ያህሉ ደግሞ ህይወታቸውን እንዲያጡ ሆኗል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ዋጋ የምትከፍለው አፍሪካ ናት፤ 94 በመቶ የሚሆነው የተጠቂዎች እና ሟቾች ቁጥርን በመያዝ፡፡ በተጨማሪም ከአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ዕድሜያቸው ገና ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት 274,000 ወይም 67 በመቶውን እንደሚይዙ ይህ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳየናል፡፡
ምንጭ፡ The Guardian እና WHO

በክረምት አንጎሉን የሚቀንሰው ልዩ እንስሳ
-----------------------------------
የምድራችን ትናንሾቹ አጥቢ የየብስ ላይ እንስሳት የሆኑት የኤትሩስካን ፍልፈሎች (Suncus etruscus) አውራ ጣትን የሚያክሉ ሚጢጢዬ እንስሳት ናቸው፡፡ ስለዚህም እንስሳቱ አድርቀው የሚያስቀሩት የሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ የክረምት ወራትን ያለችግር ለመሻገር የሚያስችላቸውን ጉልበት ለመሰብሰብ ከሰውነት ክብደታቸው ስምንት እጥፍ እና ከዚያ በላይ የሆነ ምግብ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን ከማድረቅ ይልቅ ግን እንስሳቶቹ በክረምት ወቅቶች ሶማቶሴንሰሪ ኮርቴክስ የተባለው የአንጎላቸውን ክፍል ይዘት በ28 በመቶ በመቀነስ ኃይል እንደሚቆጥቡ አዲስ ጥናት አሳይቷል፡፡
ይህ ፍልፈሎችን ለየት የሚያደርግ ፀጋ ነው፤ ከዚህ ቀደምም ሌላ የፍልፈል ዝርያ በሆኑት ሬድ ሩትድ ፍልፈሎች ላይ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት እንስሳቱ በተወለዱ በመጀመሪያው በጋ ላይ የሰውነት እድገታቸውን ይጨርሳሉ፡፡ ሆኖም የአውሮፓውያኑ መኸር መግባት ሲጀምር በተቃራኒው መጠናቸው ማሽቆልቆል ይጀምራል፤ የአከርካሪያቸው ርዝመት፣ የራስ ቅል፣ አንጎል፣ አጥንቶች፣ ጉበትና ሌሎች የሰውነት አካላት፣ ጠቅላላው ክብደታቸው ሁሉም መጠናቸው መቀነስ ይጀምራል፡፡ የካቲት አካባቢ ላይ ደግሞ ዳግም እንደቀድሞው አድገው የሰውነት ዕድገት ጣርያቸውን የሚነኩና በፀደይ ወራቱ ለፆታዊ ግንኙነት ዝግጁ የሚሆኑ ይሆናል፡፡ አስከትለው አንዴ ብቻ ዘራቸውን ከተኩ በኋላ ወዲያው ይህችን ዓለም በሞት ይሰናበታሉ፤ ይህች የእነርሱ ምጥን የህይወት ዑደት ናት፡፡
ጥናቱን ለማጥት የተመራማሪዎች ቡድኑ ለአንድ ዓመት በአራቱም ወቅቶች 10 የኤትሩስካን ፍልፈሎቹን ኤም.አር.አይን በመጠቀም ሲከታተላቸው ቆይተዋል፡፡ በውጤቱም ምንም እንኳን እንስሳቱ በየዕለቱ ያለማቋረጥ እንደልብ እንዲመገቡ፣ የስፍራው ሙቀት መጠን ሳይለዋወጥ፣ ብርሃንም ለ12 ሰዓታት እያገኙ የቆዩ ቢሆንም በክረምቱ ወቅት የአንጎላቸው ይዘት መቀነሱን ማስተዋል ችለዋል፡፡ ታድያ ይህ ያልተቋረጠ ለውጥ ከውስጥ ከሚነሱት እንደ ዕድሜ እና የጊዜ ሂደት፤ እንዲሁም የምግብ መኖር አለመኖርን ከመሳሰሉ ውጪያዊ የተፅዕንዖ ምንጭ ሁነቶች የሚነሳ እንደሆነ ተቀምጧል፡፡
የጥናት ቡድኑ ሌሎች ላይ ባደረገው ምልከታም ከእንስሳቱ ዊስከር መልዕክት የሚቀበለውና በአደን ወቅት ጥቅም ላይ የሚውለው ይህ ሶማቶሴንሰሪ ኮርቴክስ የተሰኘ የአንጎል ክፍል መቀነስን አሳይቷል፡፡ አንዱ የሶማቶሴንሰሪ ኮርቴክስ ወለል በክረምቱ ወቅት ስፋቱን በ28 በመቶ መቀነስ ሲችል ከበጋው መግባት ጋራ ተያይዞ ደግሞ ዳግም በ29 በመቶ አድጓል፡፡ የኒሮን መጠኑም ከክረምት ወደ በጋ ሲሸጋገሩ የ42 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
እነዚህ የይዘት ለውጦች በአንጎል እንቅስቃሴው ላይም ለውጦችን አምጥቷል፡፡ የጥናት ቡድኑ ኒሮኖቹን የነቁ፣ የተጨቆኑ እና ምንም ተፅዕንዖ ያልደረሰባቸው ብሎ በሶስት ከፍሎ አስቀምጧቸዋል፡፡ የተጨቆኑት ኒሮኖች በበጋው እና የፀደይ ወቅቶች ከክረምትና መኸር አንጻር ከፍ ያለ እንቅስቃሴን አሳይተዋል፡፡ ይህ ተግባር እንስሳቱ ኃይልን እንዲቆጥቡ የሚያስችላቸው እንደሚሆን የተመራማሪዎቹ እምነት ነው፡፡ በሌላው የአንጎል ክፍል ላይ ግን የመጠን ለውጦች ሳይታዩ ቀርቷል፡፡
ምንጭ፡ The Scientist

አደጋን የመከላከል ከፍተኛ ብቃት ያላቸው የመንገድ ላይ ምልክቶች
**************************
ከራዳር ጋር ተቀናጅተው የመንገድ ላይ መጨናነቅንና የአየር ጠባይን በመተንተን ለአሽከርካሪዎች ተመራጭ የሆነን መንገድና ሰዓት ማመልከት የሚችሉ የትራፊክ ምልክቶች መሰራታቸው ተሰማ፡፡ በአለማችን በተለያዩ በሽታዎች፣ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ህይወታቸውን የሚያጡና ለከፍተኛ አካል ጉዳት የሚዳረጉ ሰዎች እየበዙ መጥተዋል፡፡ ከእነዚህ ምክንያቶች ባልተናነሰ የትራፊክ አደጋ ለብዙዎች ህይወት ህልፈትና ምስቅልቅል ከፍተኛ ድርሻ አላቸው፡፡
እነዚህ የመንገድ ዳር ምልክቶች አሽከርካሪውን ለአደጋ ሊያጋልጥ የሚችል ማንኛውንም ችግር ቀድመው በተገጠመላቸው መሳሪያ አማካኝነት ማሳወቅ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡ በፖላንድ የሚገኙ ተመራማሪዎች በተለይ የጉዳት መጠናቸው ከፍተኛ ይሆናል ተብለው በሚገመቱ የፍጥነት መንገዶች ላይ ሊኖር የሚችልን አደጋ መቀነስ የሚያስችሉ በራዳር፣ ምስልና ድምጽ መለያ እንዲሁም የትራፊክ ፍሰት መጠንና እለታዊ የአየር ጠባይን በመረዳትና በመተንተን ለአሽከርካሪዎች በጣም አስፈላጊ መረጃዎችን መስጠት የሚችሉ የመንገድ ላይ ምልክቶችን ሰርተዋል፡፡
አሁን (7-10/12/2020) እየተከናወነ ባለው 179ኛ የAcoustical Society of America አመታዊ ስብሰባ ላይ ለታዳሚዎች የጥናቱ ውጤት ይቀርባል ተብሎ እቅድ ተይዞለታል፡፡ ምርምሩም የፍጥነት መንገዶችን የፍሰት መጠን ለመለካትና በመንገድ ላይ የሚሽከረከሩ መኪኖች የሚፈጥሩትን ድምጽ በመጠቀም ሊኖር የሚችልን የመኪኖች ብዛት ማወቅ እንደሚያስችል ተነግሯል፡፡
በሂደቱም Acoustic vector sensor የተባለ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ሲሆን ለምንም አይነት ኤሌክትሮ መግነጢሳዊ ጣልቃ ገብነት እንደማይጋለጥ ተሰምቷል፡፡ መደበኛ ምልክቶች ላይም ነባራዊ ሁኔታውን መሰረት ያደረገ መላመድ እንዲችሉ ተደርገዋል፡፡ ለምሳሌ ያክል የፍጥነት ወሰን አመልካች ምልክት ካለው የመንገድ መጥበብና መስፋት ጋር የተናበበ የፍጥነት ልክ እንዲያሳይ ያስችላል፡፡
ምንጭ፡ SciTechDaily

አረንጓዴ ሽንት የሸናው ግለሰብ
ሰሞኑን ታሞ ሆስፒታል አልጋ ላይ የተኙ አንድ ግለሰብ ሽንት አረንጓዴ ቀለምን መያዙ አግራሞትን ፈጥሯል፡፡ ሆኖም ድንጋጤን የሚያጭረው ይህ ክስተት ጉዳት አልባና ግለሰቡ የሚደግላቸው ህክምና ውጤት ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በ62 ዓመት ዕድሜ ላይ የሚገኙት ግለሰቡ ክሮኒክ ኦብስትራክቲቭ ፓልሞናሪ ዲዚዝ (COPD) የተባለ የሳንባ በሽታ አጋጥሞት መተንፈስ ስለተቸገሩ ነው ወደ ሆስፒታሉ ድንገተኛ ክፍል ውስጥ እንዲገቡ የተደረገው፡፡ ሰውየው ለህይወታቸው ሊያሰጋ በሚችል አኳሀንም በደማቸው ውስጥ ከፍተኛ የካርበን ዳይ ኦክሳይድ ይዘት ተገኝቶባቸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ሆስፒታሉ ውስጥ ወዳለው የከፍተኛ ክትትል ክፍል ውስጥ እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን የአተነፋፈስ መርጃ መሳርያ እና ፕሮፎፖል የተባለ የማደንዘዣ መድሀኒት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከአምስት ቀናት ቆይታ በኋላ በከረጢት ውስጥ ሲሰበሰብ የነበረው የታማሚው ሽንት ወደ አረንጓዴነት ለመቀየር በቅቷል፡፡
አረንጓዴ ሽንት በህክምና የጎንዮሽ ተፅዕንዖ፣ አንዳንድ ኢንፌክሽኖች እና የጉበት ችግርን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ በዚህ ግለሰብ ላይ የሆነው ግን በፕሮፎፖል ሳብያ የመጣ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ይህን አይነት ህክምና ለጀነራል አንስቴዢያ ተብሎ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን አልፎ አልፎም የሰዎችን ሽንት ወደ አረንጓዴነት ሲቀይር ይታያል፡፡ እንዴት ሆነ የሚለው ግን በዘርዝር የሚታወቅ አልሆነም፡፡ ሆኖም አንዳንድ የፕሮፎፖሉ ቁሶች ተሰባብረው ሲወጡና ይህም ከጉበት ይልቅ በኩላሊት አማካኝነት ሲሆን (ለወትሮ የፕሮፎፖል ኬሚካል አፀግብሮት ወይም ሜታቦሊዝም የሚደረገው ጉበት ውስጥ ነው) ሊከሰት እንደሚችል ከ5 ዓታት በፊት ጆርናል ኦፍ ክሊኒካል ኤንድ ዲያግኖስቲክ ሪሰርች ላይ የወጣ ምርምር አመላክቶ ነበር፡፡ ሆኖም ይህ የሽንት ቀለም ለውጥ ጉዳት የሌለው እና የህክምናውን መቋረጥ ተከትሎ የሚያቆም ነው፡፡ እኚህ ታማሚም ፕሮፎፖሉ ሲነሳለት ነገሮች ወደ ቀድሞ ጤናማ ይዞታቸው ተመልሰውለታል፡፡ ኋላም ለሁለት ሳምንታት በሆስፒታሉ ቆይቶ ወደ ማገገሚያ ማዕከል አቅንቷል፡፡
የሰው ልጆች ሽንት ወደ አረንጓዴነት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቀለሞችንም ይዞ ሊወጣ ይችላል፡፡ ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት 2019 ላይ የሽንት መሰብሰቢያ ከረጢት ውስጥ የገባ የአንዲት ሴት ሽንት ከረጢቱ ውስጥ በተፈጠረው የኬሚካል አፀግብሮት ሳብያ ወደ ሐምራዊነት ተለውጦ ነበር፡፡
ምንጭ፡ Live Science

የጭንቅላት ትክክለኛ ቦታንና ጊዜን የማስታወስ ብቃት
*************************
በስነ ልቦና የትምህርት ዘርፍ በሰው ልጅ ጭንቅላት ውስጥ የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የትውስታ ሂደት እንዳለ ይነገራል፡፡ UT Southwestern በሚባል የምርምር ተቋም የሚሰሩ ተመራማሪዎች የሰው ልጅ ጭንቅላት ትውስታዎችን እንዴት ለረጅም ጊዜያት መያዝ እንደሚችል አዲስ ፍንጭ ማግኘታቸው ተሰምቷል፡፡ የምርምሩ ውጤት ከመሰረታዊው የማስታወስ ችሎታ በተጨማሪ በአልዛይመር በሽታና በጭንቅላት ላይ በሚደርስ አደጋ ምክንያት የሚመጣን የትውስታ ማጣት ችግርን ማከም የሚያስችል መፍትሔንም ያካተተ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ከአስርት አመታት በፊት 'time cells' የተባሉ ህዋሳት በአይጦች ጭንቅላት ውስጥ ተገኝተው ነበር፡፡ እነዚህ ህዋሳትም በየአጋጣሚው የሚከሰቱ ሁኔታዎችን መዝግቦ የማስቀመጥ ልዩ ሚና እንዳላቸው ታውቆ ነበር፡፡ ይህም ጭንቅላት የሚከሰቱ ሁነቶችን በቅደም ተከተላቸው ሰድሮ እንዲያስቀምጥ በማድረግ ነው፡፡ hippocampus በመባል በሚታወቀው የጭንቅላት ክፍል የሚገኙት እነዚህ ህዋሳት ነገሮችን የማደራጀት ተግባር ሲከውኑ ተስተውለዋል ያለው በምርምሩ የተሳተፈው Bradley Lega, M.D ነው፡፡
ከዚህም በመነሳት ተመራማሪዎቹ ተመሳሳይ የጭንቅላት ህዋሳት በሰዎች ውስጥ መኖርና አለመኖራቸውን ማጥናት ጀምረዋል፡፡ በሂደቱም ፈቃደኛ ሆኑ የ epilepsy ህመም ታካሚዎችን የተያዩ ምርምሮች ተሰርተዋል፡፡ ይህ በ27 ፈቃደኞች ላይ የተሰራው ምርምር 'time cells' የተሰኙ የጭንቅላት ህዋሳት በሰዎች የትውስታ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ታውቋል፡፡ ይህም ሁነቶች የተከሰቱበትን ትክክለኛ ሰዓት ሰዎች በቀላሉ እንዲያስታውሱ የሚያደርጋቸው እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
በሌላ ተያያዥነት ባለው ጥናት በሰዎች እና በእንስሳት ጭንቅላት ውስጥ የሚገኙ ነገሮች የተከወኑበትን ትክክለኛ ቦታ ማስታወስ የሚያስችሉ የጭንቅላት ህዋሳት ላይ ምርምር ተደርጓል፡፡ በዚህም ጥናት እንደመጀመሪያው ሁሉ አይጦች ተመሳሳይ ሁኔታ የታየባቸው ሲሆን አይጦች ባላቸው ቦታዎችን የማስታወስ ሂደት ውስጥ እነዚህ የቦታ ህዋሳት ቦታዎች በጭንቅላት ውስጥ በቅደም ተከተል ተደራጅተው እንዲቀመጡ ያደርጋሉ፡፡
በጥናቱም በአይጦች ጭንቅላት ውስጥ የሚስተዋልን የበፊቱንና የቅርብ ጊዜውን የቦታዎች ትውስታ የማፈራረቅ ሂደት ለመመርመር አጥኝዎቹ በአይጦቹ ጭንቅላት ውስጥ ኤሌክትሮዶችን በማስገባት ጥናቶችን አድርገዋል፡፡ በዚህም place cells የሚባሉት ህዋሳት በጭንቅላት ውስጥ የተቀረጹ የቅርብ ጊዜም ሆነ የቆዩ ምስሎችን በቅደም ተከተል እያመላለሱ ሲስተላልፉ ተስተውለዋል፡፡
ከዚህ ግኝት በመነሳት ተመራማሪዎቹ ህዋሳቱ እንዲህ አይነት ተግባራትን እንዲያከናውኑ የሚያግዟቸው ሌሎች የጭንቅላት ክፍሎችን እያጠኑ ሲሆን በዚህ የሚገኘው ውጤትም በአልዛይመርና በአደጋ ምክንያት የሚመጣን የሰዎች ትውስታ ማጣትን ለማከም የሚያስችሉ መሰረታዊ እውቀቶች እንደሚገኙ ተመራማሪዎቹ ተስፋ አድርገዋል፡፡
ምንጭ medicalxpress