የድምጽና የብርሀን ብክለት አዕዋፋት ላይ ያለው ከባድ ተፅዕኖ
*********************
በካሊፎርኒያ ፖሊቴክኒክ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የተደረገ አንድ ጥናት ሰዎች የሚፈጥሩት የድምጽና የብርሀን ብክለት በአእዋፋት የመራባት ስርዓት ላይ ክፍተኛ ተጽእኖ እንዳለው አመለከተ፡፡ የናሳን የሳተላይት መረጃ በመጠቀም የምርምር ቡድኑ በሰሜን አሜሪካ እንዴት የድምጽና የብርሀን ብክለት የአእዋፋትን የመራባት ሂደት እንደሚጎዳው አጥንተዋል፡፡
ባለፉት ጥቂት አስርት አመታት የአለማችን የአእዋፋት ዝርያዎች በ30 በመቶ እየቀነሰ መምጣቱ ይነገራል፡፡ ይህ የቁትር መቀነስ በምን ምክንያት እንደሆነ ተመራማሪዎች ሲያጠኑ የቆዩ ሲሆን ከብዙ ምክንያቶች አንዱ የብርሀንና የድምጽብክለት እንደሆነ በተደረገው ምርምር ታውቋል፡፡
በምርምሩ ላይ የተሳተፉ ተመራማሪዎች በሰዎች ምክንያት ከሚደርሱ ሌሎች ጉዳቶች በላቀ መልኩ የድምጽና የብርሀን ብክለት በአእዋፋት የመራባት ሂደት ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድር ገልጸዋል፡፡
የምርምር ቡድኑ በሰሜን አሜሪካ ካሉ 142 የወፍ ዝርያዎች ውስጥ 58,506 እንዴት በድምጽና በብርሀን ምክንያት መራባት እንዳልቻሉ ከፍተኛ መጠን ያለው መረጃን ተጠቅሞ ጥናቱን አካሂዷል፡፡ የወፎች እንቅስቃሴ ከንጋትና ከብርሀን ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ማለት በመጀመሪያው የንጋት ብርሀን ወፎች ለራሳቸውና ለልጆቻቸው ምግብ ፍለጋ ከጎጇቸው ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በጥናት እንደተረጋገጠው በሳር ምድር ወይም በርጥበታማ አካባቢ የሚኖሩ አዕዋፋትን የብርሀን ብክነት አንድ ወር ያክል ቀድመው ለምግብ ፍለጋ ከጎጇቸው እንዲወጡ ያደርጋቸዋል፡፡ እደሚታወቀው ወፎች ራሳቸውን የሚተኩት በጎጇቸው በሚቀመጡበት ወቅት ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የፕላኔታችን ሙቀት በጨመረ ቁጥር የአዕዋፋት ምግብ ከመደበኛ ጊዜው ፈጥኖ ይደርሳል፡፡ ይሁን እንጂ አዕዋፋቱ የሚጠብቁት የምግብ ስብሰባ ጊዜ ስላለ ሳይታሰብ የወቅት አለመገጣጠም መጣና ምግብ ሳያገኙ ይቀራሉ፡፡ ይህም ለቁጥራቸው መቀነስ ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ አንድ ወፍ ብርሀንን ቀድሞ ባየ ቁጥር ቀድሞ ለምግብ ስብሰባ ከጎጆው ይንቀሳቀሳል፡፡
ምንጭ፡ NASA SCIENCE

አፍሪካውያን ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ያለመው የባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂ ዝርጋታ
የአውሮፓ ሕብረት የልማት ፈንድ በሴኔጋል እና አይቮሪ ኮስት ያሉ የባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂ መለያ ስርዓቶችን እየደገፈ ሲሆን ይህም በአውሮፓ የሚኖሩ ህገ ወጥ የሀገራቱ ስደተኞችን በመለየት ወደ ሀገራቸው የመመለስ ስራን ለማገዝም እንደሚውል ተዘግቧል፡፡ ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል ለተለያዩ የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽነሮች በላከው ደብዳቤ ሕብረቱ ለአምባገነን መንግስታት የሚያደርገውን የልማት ድጋፍ እንዲያሻሽል አልያም እንዲተው ጠይቋል፡፡
የባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂ ስርዓት ስም፣ ትውልድ ዕለት እና ሌሎች እንደ እጅ አሻራ፣ የፊት እና አይን አሻራ ያሉ የአካላዊ ገፅታ መረጃዎችን የሚይዝ ሲሆን በህግ ማስከበር ስራዎች ውስጥም ያለው ሚና እያደገ ነው፡፡ ኢንተርፖልም ከአሸባሪዎች ጋራ በሚደረገው ግብግብ የባዮሜትሪክ መረጃን ከአይቮሪ ኮስት እና ቡርኪና ፋሶ ጋራ በመሆን ሲሰበስብ ቆይቷል፡፡
ታድያ ቴክኖሎጂው የአንድን ሰው ሕጋዊ ሰውነት ለመመስረት የሚረዱ ቢሆኑም የባዮሜትሪክ መለያ ስርዓቶች (በተለይም የፊት ገፅታ) ማግለልን ይረዳሉ ወይም በትክክል ሳይሰሩ ቀርተው ጎጂ ወደሆኑ ውሳኔዎች ይወስዳሉ ሲሉ የተለያዩ መብት ተሟጋቾች ስጋታቸውን ይገልፃሉ፡፡
የአውሮፓ ሕብረት ለአፍሪካ የሚያቀርበው ትረስት ፈንድ በሁለት ሀገራት ውስጥ ስርዓቶቹን ለመትከል የ60 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉ አንድ እንግሊዝ ውስጥ ያለ ተቋም ይፋ አድርጓል፡፡ ድጋፉ የፈረንሳይን የሀገር ውስጥ ሚኒስቴርን ለሚያማክረውና የሴኔጋል እና አይቮሪ ኮስት ብሄራዊ የምዝገባ ስርዓትን በማዘመን የሚያግዘው ሲቪልፖል የተባለ ድርጅት ነው ኮንትራቱን የተሰጠው፡፡ በሴኔጋሉ ስራ ላይ ኢነብል የተሰኘው የልማት ድርጅትም ተሳታፊ ሆኖበታል፡፡
ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ይፋ ያደረጓቸው መረጃዎችም እንዴት የህብረቱ ሕግ ማስከበት ስልጠና ኤጀንሲ አልጄሪያ፣ ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪኒያን ጨምሮ ለልዩ ልዩ ታዳጊ ሀገራት የደህንነት ኃላፊዎች የተለያዩ ስልቶችን እንደሚያስተምር ሲያሳዩ ነበር፡፡ ከነዚህ ስልቶች ውስጥ ኃላፊዎቹ ከተጠቃሚዎች ጋር ሲገነናኙ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንት እንዲጠቀሙ የሚመክሩና አነስተኛ ሀክ የማድረጊያ ስልቶች ይገኙበታል፡፡ አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች የተሻለ ህይወት ፍለጋ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ከመርዳት ይልቅ ዕርዳታው በተቃራኒው እየሰራ ነው ሲሉም የፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል አድቮቼሲ ዳይሬክተር ኤዲን ኦማኖቪች ወቅሰዋል፡፡
እ.አ.አ 2016 ላይ የአውሮፓ ሕብረት ስደተኞች ወደተሻገሩበት አልያም እናት ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚያደርግ ስምምነትን ከአፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋራ ለመድረስ አቅዶ ነበር፡፡ ዕቅዱ የኃይል ማፈናቀሎችን ዋና ምንጭ የማድረቅ እና በየጊዜው በአሳዛኝ ሁኔታ በሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ ሰጥመው የሚሞቱ ስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ ያለመ ነው፡፡
ድጋፎቹ በየትኛዎቹ የባዮሜትሪክ መለያ ስልቶች ላይ እንደዋሉ መረጃው በዝርዝር አይገልፅም፡፡ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው በመመለሱ እንቅስቃሴ ውስጥ አንድ ተግዳሮት የነበረው የመታወቂያ አለመኖር እና ማጭበርበር ነበር፡፡ ስርዓቶቹን ማዘመኑ በሀገራቱ ውስጥ ያሉ ዜጎች የምዝገባ ስርዓቶችንንም እንደሚያዘምን ተገልጿል፡፡
ምንጭ፡ Bloomberg

ሳቅ የጤና ምንጭ
**************
ተመራማሪዎች ሳቅ ለአካልና ለአእምሮ ጤና በጣም ጠቃሚ እንደሆነ አሳወቁ፡፡ አስቂኝ የሆኑ ነገሮችን በመመልከትና በመስማት ምክንያት መሳቅ ስሜትን አስታውሎትንና ማህበራዊነትን የሚቀጣጠሩ የአእምሯችን ክፍሎችን እንዲነቃቁ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ተመራማሪዎች መሳቅ የሰዎችን አካላዊና ስነ-አእምሯዊ ደህንነትን ማሳደግ ይችላል ሲሉ የተናገሩት፡፡
ከአካላዊ ደህንነት አኳያ መጀመሪያ የሚነሳው ሳቅ የላይኛውን የሰውነት ክፍላችንን ጡንቻዎች ለማጠንከር ያለው ከፍተኛ ሚና ነው፡፡ እንደሚታወቅው ሳቅ መተንፈስ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም የፊት ጡንቻዎቻችን ውስብስብ በሆነ ቅንጅት የአይን፣ የጭንቅላትና የትክሻ እንቅስቃሴ እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ሳቅ አይን፣ ጆሮ፣ ጭንቅላት፣ እንዲሁም ሌሎች ውስብስብ የሆኑ የላይኛው የሰውነት ክፍሎችና ስሜቶች በመቀናጀት የሚፈጥሩት ልዩ የሆነ የስሜት መግለጫ ነው፡፡
ሁሉም የላይኛው አካል ክፍላችን ህዋሳት በመቀናጀት የሚፈጥሩት ይህ ስሜት የደስታንና የሳቅን በሮች በመክፈት በጥሩ የአእምሮ ሁኔታ ውስጥ እንድንሆንና ጭንቀት እንዲቀንስ ወይም እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ ሳቅ አንዳንድ የጭንቀት መድሀኒቶች የሚታዘዙለትን የህብለ ሰረሰር አካባቢ ችግሮችን ለመከላከል ያስችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሳቅ አእምሮ ለአስፈሪ ነገሮች የሚሰጠውን ምላሽ በመቀነስ አጠቃላ የስርአተ ሰውነት የመፈጸም አቅምን ሊያሳንሱ የሚችሉ ሆርሞኖች እንዳይመነጩ ያደርጋል፡፡ ለዚህ ነው ሀኪሞች ሳቅ የጭንት አንቲቦዲ ነው የሚሉት፡፡
ከስነ-አእምሮ እድገትም አንጻር ሳቅ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ተመራማሪዎች ያነሳሉ፡፡ ለዚህም ሳቅ እንደ ደስታ ሁሉ ያልተጠበቁ አስቂኝና አስገራሚ ነገሮችን ከመመልከትና ከመስማት ጋር የተያያዘ መሆኑን እንደ ማሳያ ማንሳት ይቻላል፡፡ አንድን የሚያስቅን ሁኔሳ በአእምሯችን ገምግመን ካልተረዳነው ልንስቅ አንችልም፡፡ ሁኔታውን ሌሎች እንዴት እንደተረዱት ማስተዋል በሁኔታው ከፍ ያለ ሳቅ እንድንስቅና ተዝናኖታችንን ከፍ እንዲል ያደርገዋል፡፡
የማስተዋልና ማህበራዊ ክህሎቶች አንድላይ በመሆን ከሰዎች ጋር ባሉን ግንኙነቶችና በንግግሮች መቼና እንዴት ሳቅ እንደሚፈጠር እንድንረዳ ያደርጉናል፡፡ በዚህም ምክንያት ለመሳቅ የሚስቁ ሰዎችን ማየት ላይኖርብን ይችላል፡፡ ሳቅ ከሌሎች ጋር ጥብቅ ቁርኝትና ህብረት እንዲኖረን የማድረግ ሀይል አለው፡፡
በየቀኑ ሳቅን መለማመድ በተፈጥሮ የማናገኘውን ማህበራዊነት እንድናዳብር ያደርገናል፡፡ ለምሳሌ የአንድ ጨቅላ ህጻን ሳቅ ከአሳዳጊው ወይም ከተንከባካቢው ጋር ያለውን ግንኑነት ከሚያለቅስ ህጻን የበለጠ የተሸለ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በትልልቅ ሰዎችም ዘንድ ሳቅ ሀሳብን የመጋራት፣ የመደገፍና አብሮ የመሆን ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
የአውንታዊ ስነልቦና (Positive psychology) ተመራማሪዎች ሳቅ በጎ የሆኑ ስሜቶችን በማዳበር ሰዎች ትርጉም ያለው ህይወት እንዲኖሩ ያስችላቸዋል ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ እንደ ተዝናኖት፣ ደስታና ሳቅ ያሉ በጎ ስሜቶች በጥልቀት የማሰብ ችሎታን በማዳበር የመፍጠር አቅምን ያዳብራሉ፡፡ የህም የደህንነት ስሜትን በማዳበር ሰዎች በህይወታቸው እንዲረኩና ደስተኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡
በአንድ ወቅት በተሰራ ጥናት ተመራማሪዎች የ41 ሰዎችን የሳቅ ርዝማኔና ድግግሞሽ ለሁለት ሳምንታት ከአካለዊና ከአእምሯዊ ሂኔታቸው ጋር በማታመር ተከታተሉ፡፡ በዚህም በብዛት የሚስቁ ሰዎች ያለቸው የጭንቀት ሁኔታ ያነሰ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
ምንጭ Science Alert

የማግሌቭ ባቡር ግንባታ እሽቅድምድም
=================
ቻይና እና ጃፓን በአይነቱ ልዩ የሆነ እጅግ በጣም ፈጣን ተንሳፋፊ ባቡር ለመገንባት በመሽቀዳደም ላይ ናቸው፡፡ ተንሳፋፊ ማግኔታዊ ወይም የማግሌቭ ባቡሮች ከፍተኛ ጉልበት ያላቸው ማግኔቶችን በመጠቀም ያለ እፍጋት (Friction) በከፍተኛ ፍጥነት መጓዝ ሚችሉ ናቸው፡፡ ለሙከራ አገልግሎት የተሰሩና የአጭር ርቀት ማግሌቭ ባቡር መንገዶች ያሉ ቢሆንም አሁን ግን ሁለቱ የእሲያ ግዙፍከቶኪዮ ምጣኔ ሐብት ባለቤቶች ለዓለማችን የመጀመሪያ የሆነውን የረጅም ርቀት የማግሌቭ ባቡር መስመሮችን ለመገንባት እሽቅድምድም ላይ ይገኛሉ፡፡
በአንድ በኩል የጃፓን ማዕከላዊ ባቡር መንገድ ኮርፖሬሽን የሚዘረጋው የ86 ቢሊዮን ዶላር (ዘጠኝ ትሪሊዮን የን) ማግሌቭ 2037 ኦሳካን እንደሚያገናኝ ይጠበቃል፡፡ በሌላ በኩል አንዴ እየቆመ መልሶ ደግሞ የሚጀመረው 15 ቢሊዮን ዶላር (100 ቢሊዮን ዩዋን) የሚፈጀው የማግሌቭ መስመር ዝርጋታ ሻንጋይን ከምስራቋ ወደብ ከተማ ኒንቮ ጋራ የሚያስተሳስር ይሆናል፤ ይህም በአውሮፓውያኑ 2035 እንደሚጠናቀቅ ተጠብቋል፡፡ በሀገሪቱ ገጠራማ ክፍል ባሉ ተራሮች ውስጥ ዋሻዎችን ለመስራት ከሚያስፈልገው ከፍተኛ የቁፋሮ ስራ አንፃር ነው የጃፓኑ ፕሮጀክት ዋጋው ወደድ ማለቱ፡፡
ታድያ ጃፓንም ሆነ ቻይና እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶቻቸውን በተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ በስኬት ማጠናቀቅ ከቻሉ ቀጣዩ እርምጃ ይህን አዲስ ቴክኖሎጂ ወደ ሌላው ዓለም ሀገራት መሸጡ እንደሚሆን የዘርፉ ባለሙያዎች ጥቁምታ ይነግረናል፡፡ ይህ ደግሞ ከ2 ትሪሊዮን ዶላር በላይ በሚገመተው የባቡር መንገድ መሰረተ ልማት ገበያ ላይ የሚኖራቸውን ድርሻ ጠቀም እንዲል ያደርገዋል፡፡
ሺንኮንዘን ተብሎ የሚጠራውና የዓለማችን የመጀመሪያውን እጅግ ፈጣን ባቡር መስመርን የፈጠረችው ጃፓን ለዘመናት በዓለም የፈጣን ባቡር መስመር ዝርጋታዎች ቀዳሚ የግብዓት አቅራቢ ሆና ቆይታለች፡፡ እቃና ዕውቀቱን በርካሽ የምታቀርበው ቻይና ግን ከጃፓን ጋር ያላትን የገበያ ክፍተት እያጠበበች መጥታለች፡፡ ጃፓን በማግሌቭ ባቡር ቴክኖሎጂ ላይ ያላት ጥንካሬ ቻይና ወደፊትም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ገበያ ላይ ጥሩ ድርሻ ይኖራት ዘንድ በዚህ ቴክኖሎጂ ላይ በፍጥነት አዳዲስ ከፍታዎችን እንድታስመዘግብ አድርጓታል፡፡ ቻይና የሰራችው የከፍተኛ ባቡር ሰርቶ ማሳያ በተለያዩ የባቡር ሀዲድ አይነቶች መሄድ የሚችልም ነው፤ ይህም ጃፓን ለዓመታት ለማሳካት ስትጥር የቆየችው ተግባር ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ሆኖም በቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ዙርያ ያለው ጃፓን ከቻይና አንፃር ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደኋላ እየቀረች ነው የሚለው እይታ አዲሱን ቴክኖሎጂ በፍጥነት ዕውን ታደርግ ዘንድ እንደሚገፋፋት የአንድ ዕውቅ ባለሙያ ግምት ነው፡፡ የጃፓን ማዕከላዊ ባቡር መንገድ ኮርፖሬሽን በሰዓት 500 ኪ.ሜ እየበረረ ያለውን ባቡሩን የሚሞክርበት የ43 ኪ.ሜ መሞከርያም አለው፡፡
የጃፓን ማዕከላዊ ባቡር መንገድ ኮርፖሬሽን ይህ የማግሌቭ ቴክኖሎጂውን ለማቅብ ካሰበባቸው የውጭ ገበያዎች ውስጥ አንዱ አሜሪካን ናት፡፡ በአሁኑ ሰዓት ድርጅቱ ከተለያዩ አጋሮች ጋራ በመሆን ዋሽንግተን ዲሲን ከኒው ዮርክ የሚያገናኝ መስመር ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ የጃፓን መንግስት የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ እና ለቴክኖሎጂውም የፍቃድ ክፍያ ላለማስከፈል ቃል ገብቷል፡፡
ይህ ሁሉ እንዳለ ግን በቴክኖሎጂው አዋጭነት ላይ ባለሙያዎች ጥያቄ ሲያነሱ ይታያል፡፡ የማግሌቭ ባቡሮችን መገንባት ከሚያስፈልገው ኃይል እና ጣብያ አንፃር ከሌሎች ባለ ከፍተኛ ፍጥነት ባቡሮች አንፃር ወጪው ሁለት እና ሦስት እጥፍ ሊደርስ ይችላል፡፡ ከአውሮፓውያኑ 2002 አንስቶ ሲንቀሳቀስ የቆየውና በቻይና መንግስት ባለቤትነት የሚተዳደረው ሻንጋይን ከፑዶንግ አየር ማረፊያ የሚያገናኝ የአጭር ርቀት ማግሌቭ ባቡር መስመር ትርፍ ለማስመዝገብ ሲቸገር የታየ ሲሆን በመጀመሪያዎቹ ዓመታትም የአንድ ቢሊዮን ዩዋን ኪሳራ አጋጥሞት ነበር፡፡ የጃፓኑ ፕሮጀክትም ከሚያወስጣው ከፍተኛ ወጪ አንፃር ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡
ምንጭ፡ Tech Xplore

እንደገና ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ጓንቶችን የሚያመርተው አዲሱ ስርዓት
*************************
በእያንዳንዱ ወር በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠሩ የተጣሉ የፕላስቲክ ጓንቶች ወደተለያዩ የውሃ አካላት ይከማቻሉ፡፡ በተለይም ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ይህ የሰርጂካል ጓንት አጠቃቀም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚገኝ የአለም አቀፍ ተቋማት ዘገባዎች ያሳያሉ፡፡ አብዛኞቹ እነዚህ ጥቅም ላይ የዋሉ የፕላስቲክ ጓንቶች የመጨረሻ መዳረሻቸው ውቅያኖሶችን እና የወንዝ ተፋሰሶች በመሆናቸው በአካባቢ ብክለት የሚያድረሱት ጉዳት እጅግ የከፋ ነው፡፡
ከዚህ ጋር በተገናኘ ይህን ችግር ለማቅለል በተለያዩ ቦታዎች እና ጊዚያት የተለያዩ የምርምር መፍትሄዎች የሚቀርቡ ሲሆን በቅርቡ የተሰማውም የምርምር ውጤት ይህን የአለም አቀፍ ችግር ለመቀርፍ ትልቅ ተስፋ ያሳየ ይመስላል፡፡ በስዊዲን መቀመጫውን ባደረገ ብላከንጅ የቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት የተከናወነው ይህ ምርምር የፕላስቲክ ጓንቶችን ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል የሚስችል የፈጠራ ስርዓት ሲሆን እንደማንኛውም የሰርጅክል ጓንት አይነቶች ለረዥም ጊዜ የሚቆይ እና በቀላሉ ሊተጣጠፍ የሚችል ጓንቶችን የሚያመርት ነው፡፡
በዚህ ምርምር ላይ የተሳተፉት የኢኒስቲትዩቱ ተመራማሪዎች ጀምስ ዳይሰን አዋርድ በተባለ የፈጠራ ወድድር ላይ ግንኝታቸውን ይዘው ሲቀርቡ እንዳስታወቁት በዚህ የማኑፋክቸሪንግ ሲስተም የሚመረተው የፕላስቲክ ጓንት ከፖሊቫይነል አልኮል (PVA) ማለትም በውሃ ውስጥ ሊሟሟ ከሚችል ሰው ሰራሽ ፐሊመር የሚመርት በመሆኑ እንደሌሎች የፕላስቲክ ጓንቶች የማይበሰብሱ ከመሆን ይልቅ በቀላሉ ወደፈሳሽነት የሚቀየር፣ የሚፀዳ (sterilized)፣ የሚታደስ (remolded) እና ሊበሰብስ ወይም (biodegradable) ሊሆን ወደሚችል ፕለስቲክ የሚቀይር ነው፡፡
ReGlove የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የምርምር ፕሮጀክት በጀምስ ዳይሰን አዋርድ የፈጠራ ውድድር ከመጨረሻዎቹ 20 ተወዳዳሪዎች መካከል መግባት ቢችልም አሁን ላይ በሰፊ ስኬል የማምርት ሁኔታ ላይ አለመሆኑን የሚናገሩት የኢኒስቲትዩቱ ተመራማሪዎች በቀጣይ ጊዚያት የማሽኑን የመስሪያ ስርዓት ይበልጥ በማስፋፋት ጓንቱን የማምረት ስራ እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡ Inceptive Mind

የካንሰር ህመምን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ማከም
*********************
የካንሰር ህመምን ለመፈወስ የሚያስችል የመድሀኒት ጥንቅር (Drug Combination) የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ማግኘት እንደተቻለ መረጃዎች አመለከቱ፡፡ የህክምና ሙያተኞች በከባድ የካንሰር ህመም የሚሰቃዩ ህሙማንን ለመርዳት የተለያዩ መድሀኒቶችን በማዋሀድ ይጠቀማሉ፡፡ ለካንሰር ህሙማን ከቀዶ ህክምና በተጨማሪ የጨረር ህክምና ወይም የተለያዩ መድሀኒቶችን መስጠት ወይም ደግሞ ሁለቱንም ባንዴ መጠቀም የተለመደ ነው፡፡
Drug Combination የሚባለው አሰራር የሚሰራው ውህድ መድሀኒቱ ያለውን የማዳን አቅም ከፍ የሚያደርገው ሲሆን የእያንዳንዱ መድሀኒት ምጣኔ የተስተካከለ ከሆነ ደግሞ በመድሀኒቱ የሚኖረውን የጎንዮሽ ጉዳት መቀነስ ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ የመድሀኒት ጥመራ ስራው በቤተ ሙከራ ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚወሰወድና ዋጋውም እጅግ ውድ በመሆኑ ፍቱን የሚባል ውህድ ለማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡
ምስጋና ለተመራማሪዎች ይሁንና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የካንሰር ህዋሳትን ብቻ ለይቶ ማጥቃት የሚችል Drug Combination መሰራት ተችሏል፡፡ ይህም የተሰራው Aalto University፣ University of Helsinki እና the University of Turku በተባሉ ሶስት ዩኒቨርሲቲዎች በተደረገ የጋራ ምርምር ነው፡፡
በprestigious journal Nature Communications የወጣው የምርምሩ ውጤት እንዳመለከተው በምርምሩ የተሰራው ሞዴል እጅግ አመርቂ ውጤት የታየበት ነው፡፡ ይህ ለካንሰር ህመም ተብሎ የተሰራው ሞዴል ሌሎች በሽታዎችንም ለመፈወስ ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ተመራማሪዎች ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡ SciTechDaily

የድምጽና የብርሀን ውህደት ጥልቁን የውሀ ክፍል ለመመልከት
**************************
የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሮች ብርሀንና ድምጽን በማቀናጀት በውሀ አካት የውስጠኛ ክፍል የሚገኙ ነገሮችን ለመመልከት የሚያስችል ስልትን መቀየሳቸው ተሰማ፡፡ የተመራማሪዎቹ ህልም ወደ ውሀ አካላት ውስጥ ሳንገባ ድምጽንና ብርሀንን በማዋሀድ ብቻ በአየር ላይ ሆኖ በጥልቁ ውስጥ የሰመጡ ነገሮችን ለመመልከት ነው፡፡ በዚህም በውሀ ውስጥ የሰመጡ መርከቦችንና አውሮፕላኖችን ለመፈለግና አጠቃላይ የውሀ አካላትን ጥልቀት ለመለካት እንደታሰበም የመረጃ ምንጫችን አክሎ ገልጧል፡፡
የአየር ላይና የህዋ ላይ ራዳር ምልከታ ለብዙ አስርት አመታት የመሬት ገጽ ካርታን ለመስራት ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ የውቅያኖስ ውሀን ገጽታ በዚህ መልክ መመልከት እጅግ አስቸጋሪ እንደነበር የምርምሩ መሪ ተባባሪ ፕሮፍሰር Amin Arbabian የተናገሩ ሲሆን በዚህ ረገድ የሚጠበቀው ግብም በውሀ አካላት ውስጥ የሚገኙ ነገሮችን የጠራ ምስል መመልከት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ምንም እንኳን የውሀ አካላት የምድርን 70 በመቶ ያክል የሚሸፍኑ ቢሆንም በጣም ጥቂት የሚባል ክፍላቸው ብቻ ነው በጠራ ምስል መታየት የሚችለው፡፡ እዚህ ላይ ያለው ችግር ከፊዚክስ ጋር የተገናኘ ሲሆን ለምሳሌ የድምጽ ሞገድ ከአንድ ክፍል ወደሌላ ክፍል ሲተላለፍ ያለውን የእንቅስቃሴ ሀይል ያጣል፡፡
ሌሎችም የሞገድ አይነቶች ከአንድ ቁስ አካል ወደ ሌላ ቁስ አካል በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ያላቸውን ሀይል አሟጠው ጨርሳሉ፡፡ እዚህ ላይ ያለው ዋናው ነጥብ የውሀ ክፍሎችን ምስል እንደ መሬት ገጽ በአየር ላይ ወይም በህዋ ማንሳት ቀላል አለመሆኑ ነው፡፡
ይህንንም ችግር ለመቅረፍ Photoacoustic Airborne Sonar System (PASS) የተሰኘ የብርሀንና የድምጽ ጥምረት የሆነ ስልትን ተመራማሪዎች ተጠቅመዋል፡፡ በዚህ መንገድም የብርሀንን በአየር ያለእንከን የመጓዝ ብቃትና የድምጽን በውሀ ውስጥ ያለውን የመጓዝ ብቃት ለማቀናጀት እንደተቻለ ታውቋል፡፡
አሁን ባለው ሂደት ሙከራው ትልልቅ አሳዎችን በሚያስቀምጡ ሰው ሰራሽ ኮንቴነሮች እየተሰራ ነው ያሉት ተመራማሪዎቹ ለወደፊት በድሮን ወይም በሄሊኮፍተር ለመስራት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ መረጃውን ከTeach Xplore አግኝተነዋል፡፡

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ጋራ በጋራ ለመስራት ተስማማ
====================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ጋራ በተቀናጀ መልኩ የቴክኖሎጂ ማላመድና ሽግግር ሥርዓት እንዲተገበር የሚያስችለውን ስምምነት ዛሬ ተፈራርሟል፡፡ የተለያዩ የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት፣ የኤጀንሲው እንዲሁም ኢንስቲትዩቱ አመራርና ሰራተኞች በታደሙበት የተፈረመው ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት ለሀገራዊ ምጣኔ ሐብት ልማት ግንባታ፣ ዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ሊጠቅሙ የሚችሉ ምርምሮችን ብሎም ፕሮጀክቶች በጋራ ማከናወንን ጨምሮ አስር አባይት የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ስልጠና እና የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮሩ ስራዎችን እንዲከውኑ የሚያስችል ነው፡፡
በስምምነቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ ተቋማቸው ፈጠራዎች ወደ ቢዝነስ ተቀይረው ስራ ላይ እንዲውሉ ለማድረግ እንደሚሰራ አስታውሰው ስምምነቱ በቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የሚከወነውን የቴክኖሎጂ መቅዳትን ወደተግባር የማዋል እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን ለመድፈን እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ውስጥ ከፍተኛ ልምድ እና እውቀት ያለው የሰው ኃይል በቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ተቋማት ውስጥ ይገኛል ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በኤጀንሲያቸው በኩል ክፍተቶች ቢፈጠሩ እንኳን የስልጠና ተቋማቱ ያሏቸውን በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ የሚንቀሳቀሱ መምህራንን ይዘው ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ይሰሩ ዘንድ አሳስበዋል፡፡
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂን አስመልክቶ አቶ ኢድሪስ መሐመድ ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ተቋማዊ አደረጃጀት፣ እንቅስቃሴ እና ሌሎች ኢንስቲትዩቱን በሚዳስሱ ጉዳዮች ዙርያም በአቶ ሰልማን መሐመድ አማካኝነት ለታዳሚያኑ ማብራርያ ተሰጥቶበታል፡፡

ብሪታንያ አዳዲስ የሁዋዌይ ምርቶች በ5ጂ ስርዓቷ ውስጥ እንዳይገቡ አገደች
========================
ብሪታንያ ከቻይናው የሁዋዌይ ቴክኖሎጂስ የሚመጡ የ5ጂ ስርዓት ግብዓቶችን ከቀጣዩ መስከረም መጠናቀቂያ አንስቶ እንደምታግድ አስታወቀች፡፡ እገዳው የሀገሪቱን የገመድ አልባ በይነ መረብ ግንኙነት ተሳታፊ ተቋማትን ለማብዛት ያለመው የ333 ሚሊዮን ዶላር እንቅስቃሴ አካል ነው፡፡
በሐምሌ ወር በቻይናዋ ሸንዘን መቀመጫውን ያደረገው ግዙፉ የቴክኖሎጂ ተቋም ሁዋዌ በአውፓውያኑ 2027 ከእንግሊዝ የቀጣዩ ትውልደ ተንቀሳቃሽ ግንኙነት እንደሚታገድና ግዢዎችም ከ2021 አንስቶ ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቆ ነበር፡፡ አሁን ላይ ከነዚህ እገዳዎች ጋራ ተጣጥሞ ለመስራት በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ተቋማት ከሁዋዌይ የሚመጡ ግብዓቶችን መጠቀም ለማቆም የሚገደዱ ቢሆንም እገዳው አሁን ተዘርግቶ ያለውን ስርዓት እንዲያድሱ ስለሚፈቅድላቸው ለዚህ እንዲሯሯጡ ያደርጋቸዋል ተብሏል፡፡
እገዳው በደህንነት ስጋቶችን ምክንያት በማድረግ አጋር ሀገራት ሁዋዌይን ከስርዓታቸው ያግዱ ዘንድ ከአሜሪካ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ ቀድሞ የብሪታንያ ኃላፊዎች ድርጅቱ መቆጣጠር የሚችሏቸው አነስተኛ ስጋቶች ምንጭ ሊሆን እንደሚችል የገለፁ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ከዚህ አቋማቸው በማፈግፈግ የአሜሪካንን እርምጃ ሊደግፉ ችለዋል፡፡ በዚህም ሳብያ የብሪታንያ ቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ተቋማት የሁዋዌ እገዳን ተከትሎ ትላልቅ ኮንትራቶችን ባሸነፉት በሁለቱ የስካንዲኔቪያ ቴክኖሎጂ ተቋማት ኖኪያ እና ኤሪክሰን ላይ ጥገኛ የሚሆኑ ይሆናል፡፡
ሆኖም ይህን የሁለት ተቋማት የገበያ ቁጥጥር ይቀንስ ዘንድ የሀገሪቱ መንግስት በተወዳዳሪዎች መካከል ፉክክርን ለማጎልበት እና ደህንነት ላይ ጥናት ለማድረግ ያለመውን ብሄራዊ የቴሌኮም ቤተ-ሙከራ በአውሮፓውያኑ 2022 የሚያቋቁም ሲሆን ተፎካካሪ የመሆን እምቅ አቅም ያላቸው እንደ ጃፓኑ ኤን.ኢ.ሲ ያሉ ድርጅቶችንም ይደግፋል፡፡ ቀድሞ አገልግሎት ላይ የነበሩ የ2ጂ እና 3ጂ ቴክኖሎጂዎችን ከአገልግሎት የማስወጣቱ እርምጃም የተፎካካሪ ተቋማት ብዝሀነትን እንደሚያፋጥን መንግስት ተናግሯል፡፡
እንደ ጥናቶች ከሆነ ዓለም አቀፍ የራዲዮን አክሰስ ኔትዎርክ (RAN) ገበያ 80 በመቶው በኖኪያ፣ ኤሪክሰን እና ሁዋዌይ ቁጥጥር ሰር የዋለ ሲሆን ሌላው በብሪታንያ ከፍተኛ የደህንነት ስጋትነት እየተፈረጀ ያለው ዜድ.ቲ.ኢ ደግሞ 11 በመቶ ደግሞ ድርሻን ወስዷል፤ ሳምሰንግም በዚህ ውስጥ የ5 በመቶ ድርሻ አለው፡፡ ታድያ እነዚህን ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት ሊፎካከሩ ይችላሉ ከተባሉት ውስጥ ኤን.ኢ.ሲ፣ ፉጂትሱ፣ ፓራለል ዋየርለስ እና ሜቪኒር ሲስተምስ ተጠቅሰዋል፡፡